Telegram Web Link
#ዜና

የDongfeng የኤሌክትሪክ Off - Road  ለገበያ ሊቀርብ ይችላል።

ወደገበያ የመምጣት ሰፊ እድል ያለው ሚገርም ገፅታ የተላበሰውን የኤሌክትሪክ off - Road መኪና ላስተዋውቃቹ። M- HUNTER ይባላል። M-HERO በሚባለው የቅንጡ መኪኖች አምራች ብራንድ የሚመረት ሲሆን ብራንዱ በDongfeng ስር ያለ አምራች ካምፓኒ ነው።

ስለመኪናው ብዙ ዝርዝር መረጃዎች የወጡ ባይሆንም  እንደ የmilitary  ደረጃ ቴክኖሎጂን የሚጠቀም እና በAerospace ደረጃ ባለ carbon fiber የተሰራ ነው የሚል ሸንጋይ ቃላቶችን በመጠቀም እያስተዋወቁት ነው ያለው።

Gasgoo አንደዘገበው ከሆነ M-HERO መኪናውን ወደ ምርት ለማስገባት አቅዶዋል። አሁን ላይ ሌላ 917 የተባለ ረዥም የኪሎሜትር ሬንጅ ያለው በኤሌክትሪክ ሃይል የሚሰራ ትልቅ SUV መኪና ይዞ ለገበያ ቀርቦዋል።
መኪናው ባለ4 የኤሌክትሪክ ሞተር ሴታፕ ያለው ሲሆን እስከ 1088 የሚደርስ የፈረስ ጉልበትን ያመነጫል። ፍጥነቱ በሰአት ከዜሮ እስከ 100 km ለመድረስም 4.2 ሰከንድ ይወስድበታል።
Extended Range Electric Vehicle(EREV) ቨርዥኑ ደግሞ 816 የፈረስ ጉልበት የሚያመነጭ ሲሆን በአንድ ቻርጅ እስከ 1,000kዎች ይጓዛል። የመነሻ ዋጋውም 90,000 የአሜሪካን ዶላር ነው።

#DONGFENG #M-HUNTER
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Honda ለቻይና ገበያ የሚውል አዲስ የኤሌክትሪክ መኪና seriesን ይፋ አረገ።


Honda ለመጀመሪያ ጊዜ በ2021 አሳይቶት የነበረው የመኪና concept በዚህ አመት የቻይና ገበያ ላይ ለሚቀርበው የኤሌክትሪክ መኪና lineup ጅማሪ መነሳሻ ሆኖታል።

አዲሱ ( Ye ) series በግልፅ የዲዛይን ፅንሰ ሃሳቡን የወሰደው ከዛሬ 3 አመት በፊት ይፋ ሆኖ በረበረው ከ( e:N ) የመኪና concept ነው። የመኪኖቹ የመጨረሻ ገፅታቸውም አሁን ላይ ካሉት የHonda መኪኖች በጣም የተለየ ነው።

ሞዴሎቹ ቻይና ውስጥ በተሰራ አዲስ የኤሌክትሪክ መኪኖች ፕላትፎርም የሚሰሩ ሲሆን P7 እና S7 SUV መኪኖች የያዝነው አመት ከመገባደዱ በፊት ለገበያ ይቀርባሉ።
መኪኖቹም በባለ አንድ ሞተር በRear wheel drive(RWD) እና በባለ 2 ሞተር All wheel drive(AWD) ሆነው ይቀርባሉ።

ቀጣዩ የ( Ye ) series መኪና 2025 ከማለቁ በፊት ለገበያ የሚቀርብ ሲሆን የGT concept የምርት ቨርዥኑ ነው የሚሆነው።
Honda አስከ 2027 ባለው ጊዜ ውስጥ ቻይና ላይ 6 የ( Ye ) series መኪኖችን ሰርቶ ለገበያ እንደሚያቀርብም ተናግሮዋል።

#Honda #Ye #P7andS7
@OnlyAboutCarsEthiopia
#Ad

የሳምንቱን ያገለገሉ እና አዳዲስ መኪኖች ዋጋ ማወቅ ይፈልጋሉ?

እንግዲያውስ ሁሌመኪና ላይ በመግባት የተለያዩ መኪኖችን ሙሉ መረጃቸውን ከነዋጋቸው ያገኛሉ :: እንዲሁም በሁሌመኪና በቀን በሺዎች ተመልካች ባለው ቻናላችን ላይ በማስተዋወቅ መሸጥ እና ማከራየትም ትችላላችሁ :: ተጨማሪ መረጃ በ 0911663121 ላይ በመደወል ወይም ቴሌግራም ላይ @Hulemekinaadmin ላይ የመኪኖቻችሁን ፎቶ (እስከ 10 ፎቶዎችን) በመላክ 300 ብር ብቻ ቴሌብር ላይ ከላይ ባስቀመጥነው ስልክ ላይ በመክፈል መሸጥ እና ማከራየት ትችላላችሁ ::

@hulemekina
#ዜና

Maserati አዲስ የኤሌክትሪክ መኪና ለገበያ ሊያቀርብ ነው።


Maserati እንደ አብዛኞቹ የመኪና አምራቾች ከጥቂት አመታት በፊት የኤሌክትሪክ መኪኖችን ወደ ማምረት የሚያደርገው የለውጥ ሂደት ፈጣን ይሆናል ብሎ አንዳሰበው አልሆነለትም።
ነገር ግን የGranCabrio የኤሌክትሪክ ቨርዥን የሆነውን መኪናውን እያስተዋወቀ ነው።

መኪናው እንደ ሃርድ ቶፑ GranTurismo Folgore በ800- ቮልት አርክቴክቸር ፅንሰ ሃሳብ ነው የተሰራው። 83 kilowatt-hour ባትሪ ፓክ ሲኖረው የተገጠሙለት 3 የኤሌክትሪክ ሞተሮች 610 kilowatt ወይም 818 የፈረስ ጉልበትን ያመነጫሉ።

ፍጥነቱ በሰአት ከ0-100 km ለመድረስም 2.8 ሰከንዶች ብቻ ነው ሚፈጅበት። ለGranCabrio Folgore መኪና ከደንበኞች ትዛዝ መቀበል የሚጀምረው August ላይ ሲሆን ሽያጩ ደሞ በአራተኛው የሩብ አመት አጋማሽ ላይ ይከተላል። የመነሻ ዋጋውም 200,000 የአሜሪካ ዶላር ነው ተብሎ ይገመታል።

#Maserati  #GranCabrio_Folgore 
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Alfa Romeo የአዲሱን CUV መኪናውን ስም ለመቀየር ተገደደ።


የጣሊያን መንግስት በ Alfa Romeo ፓረንት ካምፓኒ stellantis በጣም የተበሳጨ ሲሆን ለዚህም ምክንያት ሰሞኑን ባቀረብንላቹ ዜና መሰረት ካምፓኒው የAlfa Romeo Milano የተባለው መኪናውን ፖላንድ ሃገር ላይ እንዲመረት በመወሰኑ ነው።

ከዚህም በላይ የStellantis Ceo የሆነው Carlos Tavares መኪናው ከፖላንድ ይልቅ በጣሊያን ውስጥ የሚመረት ከሆነ ተጨማሪ 10,000 ዩሮ ያሶጣል ማለቱ ከፍተኛ ቁጣን የጫረባቸው ባለስልጣናቱ በ2000ዎቹ መጀመሪያ ላይ ሃገሪቷ ላይ ከጣሊያን ውጪ ለተመረቱ ምርቶችን ጣሊያናዊ ስምን መስጠት እንዲከለከል የወጣውን ህግ አንስተው "Milano" የሚለውን ስም እንዲቀይር ካምፓኒውን ከሰውታል።

ካምፓኒውም የመኪናውን ስም ወደ Junior እንዲቀይር የተገደደ ሲሆን በሰጣ ገባው ምክንያት ለአዲሱ መኪና ነፃ ማስታወቂያ በማግኘቴ የጣሊያን መንግስትን ላመሰግን እወዳለው ብሎዋል።

#Alfa_Romeo #Junior
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

ቻይና ጀርመን ከምታመርተው የመኪኖች በላይ ኤክስፖርት ታረጋለች።


የቻይና የመኪና ኤክስፖርት ቢዝነስ በሚያስገርም ሁኔታ እያደገ ነው። እንደ China Association of Automobile Manufacturers መረጃ መሰረት በወርሃ March ቻይና 502,000 መኪኖችን ወደሌሎች ሃገራት ኤክስፖርት አርጋለች። ይህም ካለፈው አመት ሲነፃፀር በ38% እድገት አሳይቶዋል።

ኤክስፖርት የተደረጉትም ቀላል እና እና የንግድ ተሽከርካሪዎች ሲሆኑ 424,000 ቀላል ተሽከርካሪዎች የተቀሩት 78,000ዎቹ ደግሞ የንግድ ተሽከርካሪዎች ናቸው።

ቻይና በዚህ መጠን ኤክስፖርት ማረጓን ከቀጠለች በአንድ አመት ውስጥ ቁጥሩ ወደ 6 ሚሊየን ይደርሳል። ለንፅፅር ጀርመንን ብንመለከት ባለፈው አመት 4.1 ሚሊየን ተሽከርካሪዎችን አምርታለች።
ይህ ማለትም ጀርመን በአመት ውስጥ ከምታመርተው የተሽከርካሪዎች ቁጥር በ2 ሚሊየን ብልጫ ያላቸውን ተሽከርካሪዎችን ቻይና ኤክስፖርት ታረጋለች።

#Chinese_Car_Export
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

BMW በኤሌክትሪክ መኪኖች ምርት እና ሽያጭን በጥሩ ሁኔታ ይዞታል።


BMW በቀላሉ እንደ Mercedes ፣ Audi ፣ Cadillac እና ሌሎች ልጠቅሷቸው የምችሏቸውን Legacy የቅንጦት ብራንዶችን በሽያጭ ረቷቸዋል።

Bloomberg እንደዘገበው እንደዚህ በጥሩ ሁኔታ ገበያውን ሊቆጣጠረው ከቻለባቸው ምክንያቶች መካከል ከዚህ በፊት ሽያጩ አሽቆልቁሎበት በነበረው i3 ክተሰኘው የኤሌክትሪክ መኪናው በከባዱ ስለተማረ ነው።

የኤሌክትሪክ መኪኖችን ለማምርት ሌላ አዲስ ማምረቻ በመገንባት ፋንታ የነዳጅ መኪኖችን በሚያመርትበት ተመሳሳይ ፕላትፎርም ላይ ተራ በተራ እያረገ እያመረተ ነው። አንዲሁም የራሱን የባትሪ ማምረቻ ገንብቶ ከማምረት ይልቅ እንደ የቻይናው CATL ካሉ የመኪና ባትሪ አምራቾች በመግዛት እራሱን ከቢሊየን ዶላሮች ከሚፈጅ የኢንቨስትመንት ወጪ አድኖዋል።

በቀጣይ አመት ሁለተኛ አጋማሽ ላይ "Neue Klasse"  ተብሎ የተሰየመውን የጣዩን የኤሌክትሪክ መኪና ጀነሬሽን ማምረት የሚጀምር ይሆናል። በጥሩ ሁኔታ የሚሸጡለት ከሆነ ትልቅ የሚባል ትርፍን ያስገኙለታል።

#BMW #Neue_Klasse
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ማሳሰቢያ

ይህ ዛሬ 22 መክሊት ህንፃ አከባቢ የደረሰ አደጋ ነው፡፡

እባክዎ! አሽከርካሪዎች በዝግታ፣ በማስተዋል እና በእርጋታ ያሽከርክሩ ራስዎንና ወገኖዎትን ከአስከፊው የትራፊክ አደጋ ይከላከሉ‼️
ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ አዲስ አበባ ላይ ባለፉት 9 ወራት 286 ሰዎች በመኪና አደጋ ህይወታቸው አልፏል :: እና በተቻለ አቅም አሽከርካሪዎች ፍጥነታችሁን ቀነስ አድርጋችሁ አሽከርክሩ :: እግረኞችም መሻገር ባሉባችሁ ቦታዎች እንዲሁም ዜብራ የሌለበት መንገድ ከሆነ አይተው በጥንቃቄ ይሻገሩ ::

ምንጭ - TMA

@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Boston Dynamics አዱሱን(Humanoid Robot) ሰው መሳይ ሮቦት ይፋ አደረገ።


አሁን ላይ ባለቤትነት በHyundai ስር የሆነው ሮቦቶች ላይ የሚሰራው የምርምር ተቋም Boston Dynamics ለ11 አመታት ያህል ሮቦትን እንዴት በተሻለ መንገድ መስራት እንደሚችል የተማረበትን Atlas የተባለውን ሮቦቱን ጡረታ አሶጣው።

ከተመረተበት 2013 ጀምሮ ከባድ የሚባል ኑሮን ያሳለፈው Atlas ከባድ እቃዎችን መወርወር ፣ መዝለል ፣ መገለባበጥ እና ሌሎች ብዙ ነገሮችን ማድረግ ይችላል። አበልፃጊው ቡድኑ ብዙ ብዙ አይነት መሰናክሎችን እያበጁ ስለ ሮቦት መስራት የተማሩበት ሲሆን በእነዚህ ፈተናዎች ምክንያት የሮቦቱ ሰውነት ላይ የተለያዩ የግጭት እና የመጫጫር  ምልክቶች ይታዩበታል።

በመጨረሻም ጡረታ አሶጥተውት በምትኩ አዲስ 001 የተባለ ሰው መሳይ የሮቦት ቨርዥን ይፋ አድርገዋል።
አዲሱ ሮቦት እንደ Atlas የሃይድሮሊክ ሲስተም ከመጠቀም ይልቅ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሪክ ሲስተም ነው የሚሰራው።

#Hyundai #BostonDynamics
@OnlyAboutCarsEthiopia
#Ad

መኪናዎትን ቶሎ ለመሸጥ አስበዋል?

እንግዲያውስ የተለያዩ መኪኖቻችሁን በሁሌመኪና በማስተዋወቅ መሸጥ እና ማከራየትም ትችላላችሁ
በ 0911663121 ላይ በመደወል ወይም ቴሌግራም ላይ @Hulemekinaadmin ላይ የመኪኖቻችሁን ፎቶ (እስከ 10 ፎቶዎችን) በመላክ 300 ብር ብቻ ቴሌብር ላይ ከላይ ባስቀመጥነው ስልክ ላይ በመክፈል መሸጥ እና ማከራየት ትችላላችሁ ::

@hulemekina
#ዜና

የንግድ ኤሌክትሪክ መኪናዎች አገልግሎት ለመስጠት ከነዳጅ መኪኖች ያነሰ ወጪ ያስወጣሉ?


ብሉምበርግ የአንድ Elite Home Care የተባለ Ford E-Transits መኪኖችን የሚጠቀም የጭነት አገልግሎት ሰጪ ኩባንያ ባለቤት አናግሮ የሚከተለውን ምላሽ አግኝቷል።
"የኤሌክትሪክ መኪኖችን ለስራዬ መጠቀም ከጀመርኩ በሗላ ለጥገና እና ለቻርጅ የማወጣው ዋጋ በፊት የነዳጅ መኪኖችን ለመጠቀም ከነበረው ጊዜ ሲነፃፀር በአመት 6,500 ዶላር ወጪን አስቀርቶልኛል።"

ይሄ ጉዳይም የቤት የኤሌክትሪክ መኪኖች ሽያጭ ላይ መቀዛቀዝ ቢኖርም የንግዶቹ የኤሌክትሪክ መኪኖች ላይ ያለው ሽያጭ መጨመሩ አንዱ ምክንያት ነው።

የ Ford CEO Jim Farley አንዳለው E-Transit መኪናን በሚፈለገው ፍጥነት ማምረት አልቻልንም።
በመጀመሪያው እሩብ አመት 3,000 ገደማ የሚሆኑ መኪኖችን ሽጧል። ይሄ ማለትም በ147% እድገት አሳይቷል ነገር ግን እስካሁን በነዚህ መኪኖች ትርፍን እያገኘ አይደለም።

Ford Pro የተባለው የካምፓኒው የንግድ መኪኖች አምራች ክፍል በዚህ አመት ላይ ለFord ትልቁ የትርፍ ማዕከል ሆኖለታል።  በአመት ከ 8- 9 ቢሊየን ዶላሮች ትርፍን ሲያስገባለት ለዚህ ዋናው ቁልፍ ምክንያት የሆነውም ለጭነት አገልግሎት ሰጪ ደንበኞቹ የሚሰጠው የSubscription ሰርቪስ ነው።
ይሄ የSubscription ሰርቪስ በ2026 የFord Proን 20% ትርፍ ይይዛል ተብሎ ይጠበቃል።

#Ford #electric # E-Transit
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Google Map ላይ የኤሌክትሪክ መኪኖች ቻርጅ ስቴሽን ቦታ ተካተተ።


Google የኤሌክትሪክ መኪና ቻርጀሮች ቦታን በቀላሉ ማግኘት የሚያስችለንን ፊቸር Goolge Map ላይ አካተተ። በመጪው ወር በAI( Artificial Intelligence) በመታገዝ ቻርጀሮቹ የሚገኙበትን ቦታ ዝርዝር መረጃ ማሳየት ይጀምራል።

መረጃው የተሰበሰበው እለት ተእለት ማፑ ላይ በሰዎች በሚሰጠው በሚሊየኖች የሚቆጠር አስተያየት ሲሆን ይሄም ትክክለኛ መረጃን እንዲይዝ እና በየጊዜው ከሚደረጉ ለውጦች ጋር አብሮ ማሻሻያ እንዲያደርግ ያደርገዋል።

Google ሌላ ተጨማሪ ፊቸርም ይዞ የመጣ ሲሆን ይሄም ቅርባችን ያለውን ቻርጀር ማሳየት፣ ምን ያህል አገልግሎት መስጠት የሚችሉ ቻርጀሮች እንዳሉ እና የቻርጂንግ ፍጥነታቸውን ያሳያል። Google ይሄን ፊቸር የ Google ሲስተም ከተጫነባቸው መኪኖች ጀምሮ በአለም ዙሪያ ላሉ ተጠቃሚዎቹ በመጪው ወር ይፋ ያደርገዋል።

#GoogleMaps #ChargingStation
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

አዲሱ Toyota Camry በሃይብሪድ አማራጭ ብቻ ነው የቀረበው


አዲሱ Toyota Camry በሃይብሪድ አማራጭ ብቻ የቀረበ ሲሆን የካምፓኒው 5ኛ ጀነሬሽን ሃይብሪድ  ሲስተም ነው የተገጠመለት። ይሄም 4 ባለ 2.5 L ሲሊደር Engine ከኤሌክትሪክ ሞተር ጋር የያዘ ሲሆን የሁለቱ ጥምረት Front wheel drive ሞዱ ላይ 225 የፈረስ ጉልበት ማመንጨት እንዲችል ያረገዋል።

አዲሱ የCamry All wheel drive ቨርዥኑ ላይ engineኑን ከኋላ ጎማዎቹ ጋር የሚያገኛኘውን የድሮው ሜካኒካል ሴታፕ በመተው የኤሌክትሪክ ሞተሩን ከኋላ Axleሉ ጋር አያይዞታል። ይሄም እስከ 232 የፈርስ ጉልበት እንዲያመነጭ ሲያስችለው አሁን ገበያ ላይ ካለው የCamry ሞዴል ሲነፃፀር በ30የፈረስ ጉልበት ብልጫ አለው።


Toyota Camry በሃይብሪድ አማራጭ ብቻ በመቅረቡ ምክንያት የሞተሩን ክብደት በመቀነስ ከlithium ion ባትሪው የሚመጣውን ሃይል ጨምረውለታል።  አዲሱ camry የነዳጅ እና የኤሌክትሪክ ሞተሮቹ ተደምረው በሊትር 21kmዎች ይጓዛል ተብሎ ይጠበቃል።

ከToyota Prius ጋር ምን ያህል ልዩነት አላቸው ካላቹ Prius በFront wheel drive ቨርዥኑ በሊትር 24kmዎችን ይጓዛል። ነገር ግን  በall wheel drive ቨርዥን ላይ Camry ከPrius በሊትር 1.7km ብቻ ያነሰ ጉዞ ነው ሚያረገው።

ይሄም አዲሱ Camry የማድረሻ ዋጋውን ጨምሮ በ29,000 ዶላር ፀደይ ላይ ለገበያ ሲቀርብ የPriusን ገበያ ይቀማ ይሁን? የሚለውን መመልከት አጓጊ ያረገዋል።

#Toyota_Camry #Toyota_Prius #Hybrid
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

ቴስላ  ሁሉንም Cybertruck መኪኖቹን ወደ ካምፓኒው recall አደረገ።


ቴስላ ሁሉንም ያመረታቸውን cybertruck መኪኖች recall ያደረገ ሲሆን አንዴ ልሌላ ጊዜው በቀላል የሶፍትዌር update የሚስተካከል ችግር አይደለም።

The National Highway Traffic Safety Administration እንደተናገረው 3,878 Cybertrucks መኪኖቹ ወደ ካምፓኒው ለጥገና ተጠርተዋል።  እንዲጠሩበት ምክንያት የሆነውም ችግር የሃይል መስጫ(የነዳጅ ) ፔዳሉ በመላላት ቦታውን ለቆ ውስጥ ላይ ካለው የመኪና ክፍል ላይ ነክሶ ይቀራል።

NHTSA እንዳለው ነክሶ የቀረው ፔዳል የነዳጅ መስጫውንም ሆነ የፍሬን መያዣ መስመሩን በማቋረጥ ፍጥነት እንዳንጭምር ወይም መኪናውን ማቆም እንዳንችል በማረግ ለትራፊክ ለአደጋ ያጋልጣል።

ቴስላም የተለያዩ የመኪና ባለቤቶች ይሄች ችግር በምስል ቀርፀው የማህበራው የትስስር ገፆች ላይ ካጋሩ ቡሃላ የCybertruck መኪኖቹ ላይ ያለው ሽያጭ አቁሞዋል።

#Tesla #Cybertruck
@OnlyAboutCarsEthiopia
#Ad

ከ 600 ሺህ ብር ጀምሮ የሚሸጡ መኪኖች እንዲሁም የሳምንቱን ያገለገሉ እና አዳዲስ መኪኖች ዋጋ ማወቅ ይፈልጋሉ?

እንግዲያውስ ሁሌመኪና ላይ በመግባት የተለያዩ መኪኖችን ሙሉ መረጃቸውን ከነዋጋቸው ያገኛሉ :: እንዲሁም በሁሌመኪና በቀን በሺዎች ተመልካች ባለው ቻናላችን ላይ በማስተዋወቅ መሸጥ እና ማከራየትም ትችላላችሁ :: ተጨማሪ መረጃ በ 0911663121 ላይ በመደወል ወይም ቴሌግራም ላይ @Hulemekinaadmin ላይ የመኪኖቻችሁን ፎቶ (እስከ 10 ፎቶዎችን) በመላክ 300 ብር ብቻ ቴሌብር ላይ ከላይ ባስቀመጥነው ስልክ ላይ በመክፈል መሸጥ እና ማከራየት ትችላላችሁ ::

@hulemekina
#ዜና

Toyota Highlander ሙሉ በሙሉ የኤሌክትሪክ መኪና ሞዴል ሆነ።


Toyota የኤሌክትሪክ መኪኖችን መስራት ላይ ለዘብ ያለ ነው ተብሎ ሲተች የነበረ ቢሆንም ከዚህ ሃሳብ በተለየ አንዱን የመኪና ሞዴሉ ሙሉ በሙሉ የኤሌክትሪክ አርጎታል። CarBuzz ዘገባ Toyota Highlander ወደ በኤሌክትሪክ ብቻ ወደ የሚገኝ የመኪና ሞዴል መለወጡን አረጋግጧል።

መኪናው በአሜሪካ Kentucky ግዛት ውስጥ በሚገኘው የቶዮታ ማምረቻ የሚመረት ሲሆን በሌክሰስ ዘርም ይኖረዋል።
ይሁን እንጂ አስከ 7 ሰው መያዝ የሚችለው Grand Highlander የነዳጅ ሆኖ የሚቀጥል ሲሆን የፕለግ-ኢን ሃይብሪድ አማራጭ ይጨመርለታል።

የኤሌክትሪኩ Highlander መቼ ለገበያ ይፋ እንደሚሆን የጊዜ ሰሌዳ የቀመጠለት ባይሆንም ቶዮታ አዳዲስ የኤሌክትሪክ መኪኖችን 2026 ላይ በአሜሪካ  ገበያዎች ላይ ያወጣል።
በተጨማሪ CarBuzz ካሞፓኒው "BZ" የሚለውን የስየማ መንገዱን ይበልጥ አሳማኝ እና በሰው ዘንድ የተለመደ በሆነ የአሰያየም መንገድ ሊለውጠው እያሰበ እንዳለ ዘግቦዋል።

#Toyota #Highlander #Electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Nissan የሽያጭ እና የትርፍ ቅድመ ትንበያው ዝቅ አደረገ።


Nissan በወርሃ March ለሚጠናቀቀው የሽያጭና የትርፍ የበጀት አመት ቅድመ ትንበያን ዝቅ አደረገ ።
የNissan CEO ንግግር ከመጠን በላይ አዎንታዊ የነበር ቢሆንም አሁን ላይ  3.44 ሚሊየን ተሽከርካሪዎች እንሸጣለን ብለው ይጠብቃሉ። ይህም ቀደም ሲል ከነበረው ዒላማ በትንሹ ማለትም ከ100,000 ፍሬ ዝቅ የተደረገ ሲሆን ይህም ራሱ ከ3.7 ሚሊዮን ፍሬ  ተብሎ ከነበረ የቅድመ ትንበያ ዝቅ የተደረገ ነው። 

በእውነቱ Nissan ሽያጭ 2019 ላይ 5.5 ሚሊየን ተሽከርካሪዎች ከሸጠበት ጊዜ ጀምሮ ወጥ በሆነ መልኩ እየወረደ ነው የመጣው።
በተጨማሪም የሚጠበቀው የሽያጭ መቀነስ ገቢውን፣ የሥራ ትርፉንና የበጀት አመቱን አጠቃላይ ገቢውን ይቀንሳል። ከዚህም በላይ ኩባንያው ቀደም ሲል በኒሳን የሽያጭ ትንበያዎች ላይ ተመስርተው ኢንቨስት ላደረጉ አቅራቢዎች የገንዘብ እርዳታ ይከፍላል። ስለዚህ እነዚህ ወጪዎች በመጪው ገቢው ቁጥር ላይ ይንጸባረቃሉ ።

#Nissan
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ኢንዱስትሪ ለCopper(ለመዳብ) ያለው ፍላጎት ጨምሮዋል።


የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ለመስራት የሚያስፈልጉ እንደ lithium ያሉ ጥሬ እቃዎች ዋጋ ሲቀንስ የሌሎቹ ዋጋ ደሞ ጨምሮዋል። እንደ የሸቀጣ ሸቀጥ ንግድ ላይ የሚሰራው Trafigura የተባለው ኩባኒያ ጥናት መሰረት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ምርት መስፋፋት ጋር ተያይዞ Copper (መዳብ) ላይ ያለው ፍላጎት በመጪው 10 አመታት ውስጥ በጣም እንደሚጨምር ይገመታል።

ኩባኒያው እንደተናገረው ከ10 ሚሊየን ቶን 1/3ኛው የመዳብ ፍላጎት ከኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች አምራች ካምፓኒዎች ነው። አሁን ላይ የመዳብ ዋጋ በLondon Metal Exchange በቶን 10,000 ዶላር ገብቶዋል።

ለዚህም ምክንያት የሆነው አቅርቦት ላይ ባለው እጥረት እና ያለው ከፍተኛ ፍላጎት ከአቅርቦቱ ጋር ሊጣጣም ባለመቻሉ ነው። የዘርፉ ተንታኖች የመዳብ ገበያው በዚህ አመት 26 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን እጥረት እንደሚያጋጥመው ገምተዋል።

#EV_Industries #Copper
@OnlyAboutCarsEthiopia
2024/09/22 22:32:08
Back to Top
HTML Embed Code: