Telegram Web Link
#ዜና

Rivian የሽያጭ ቁጥሩ በ 71% አደገ


አሁን ላይ ለኤሌክትሪክ መኪና አምራቾች መኪኖቻቸውን መሸጥ ብዙም አስቸጋሪ ባይሆንም Rivian 13,500 መኪኖችን ሽጧል :: ምንም እንኳን ብዙም ባይሆንም ግን በ 71% ከፍ ብሏል ከባለፈው አመት ጋር ሲነፃፀር :: እሱ ብቻ ሳይሆን ከ Highway Safety Insurance Institute ከፍ ያለ የሴፍቲ ሬቲንግም አግኝቷል :: ከዛም በተጨማሪ 97% መኪኖቹ ደንበኞቹ እንደሚፈልጉት አድርገው መስራታቸው ተመራጭ አድርጟቸዋል ::

#Rivian #HSII
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

በRenault እና በ Volvo አዲስ የኤሌክትሪክ ቫን ሊሰሩ የጀመሩት ላይ አዲስ ድርጅት አስገቡ


በRenault እና በ Volvo አዲስ የኤሌክትሪክ ቫን ሊሰሩ የጀመሩት ባሳለፍነው አመት ሲሆን አሁን ላይ የሎጅስቲክስ እና የሺፒንግ ካምፓኒ የሆነውን CMA CGM 10% (Stakeholder) ሼር በመስጠት አዲስ (Joint Venture) መስርተዋል :: ቫኖቹ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሪክ ሀይል የሚሰሩ ሲሆኑ 800 ቮልት ይኖራቸዋልም ተብሏል :: የሚጠቀሙት ፕላትፎርም የ Renault ይሁን የ Volvo የታወቀ ነገር የለም :: ግን የሚሰሩት Renault ፈረንሳይ ውስጥ ባለው ቦታ ነው :: በ 2028 ለገበያ የሚቀርብ ሲሆን አሁን አውሮፓ ውስጥ በየአመቱ 40% የኤሌክትሪክ ቫን ሽያጭ በማደጉ ነው ::

#Renault #Volvo
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ማስጠንቀቂያ

ትክክለኛ የመንገድ አጠቀቃቀም ባልተከተሉ እግረኞች ላይ የእርምት እርምጃ እየተወሰደ ስለሆነ ተጠ ንቀቁ


(መጋቢት 25/2016):- የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ጉለሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከጉለሌ ክፍለ ከተማ ትራፊክ ፖሊሶች ጋር በጋራ በመሆን ላላፉት ተከታታይ ቀናት በደንብ ቁጥር 395/2009 ላይ ለእግረኞች ስለመገድ አጠተቃቀም ግንዛቤ ሲሰጥ ቆይቷል፡፡
ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በሽሮ ሜዳ አካባቢ ባደረገው የቁጥጥር ስራ ተገቢውን ጥንቃቄ ሳያደርጉ መንገድ ባቋረጡ፤ ለተሸከርካሪዎች በተፈቀደ መንገድ ላይ ያለበቂ ምክንያት በተጓዙ፤ ለእግረኞች መንገድ ተብሎ ከተከለለ መንገድ ውጭ በተጓዙና ከዜብራ ውጪ መንገድ ያቋረጡ እግረኞች ላይ በደንቡ መሰረት እርምጃ ተወስዶባቸዋል፡፡ ስለዚህ ይህንን በማሰብ እግረኞች በጥንቃቄ ህጉን ባከበረ መልኩ እንድትጟዙ እናሳስባለን ::

ምንጭ - TMA

#AddisAbaba
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና
በኒውዮርክ አውቶ ሾው ላይ ተቃዋሚዎች ዘይት ኤሌክትሪክ ፒክአፕ ላይ ደፉ


Ford F-150 Lightning ነበር ለዚህ ታርጌት ሰለባ የነበረው :: ይህ የኢንቫይሮመንት ተቃውሞ በኒውዮርክ አውቶ ሾው ላይ የተፈፀመ ሲሆን ዘይት መሬት ላይ እና የመኪናው ኮፈን ላይ ረጭተውታል :: ከዛም በተጨማሪ "የአየር ማስጠንቀቂያ" እና "ኤሌክትሪክ መኪኖች ሊታደጉን አይችሉምም" በመጮህ አሰምተዋል :: ወደተለየ ነገር እንዳይለወጥ በማሰብ ፖሊሶች እና ሴኩሪቲዎች እነዚህ ሰዎች ከፕሮግራሙ አስወጥተዋቸዋል ::

እነሱም የ Extinction Rebellion ግሩፕ አባል ሲሆኑ ኤሌክትሪክ መኪኖች በነዳጅ መኪኖች ምክንያት የሚፈጠሩ ችግሮችን አይፈቱም ምክንያቱም ባትሪዎቹን ለመስራት የሚያስፈልጉት ማቴሪያሎች ከመሬት ውስጥ ስለሚወጡ ነው :: ብቻ የዚህ ግሩፕ ሰዎች ኤሌክትሪክም የነዳጅም መኪኖች እንዲኖሩ አይፈልጉም :: በአጠቃላይ መኪኖች እንዲኖሩ አይፈልጉም ::

#Extinction_Rebellion #NewYork_Auto_Show
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Renault በ3D Printing የመኪና ወንበሮችን ለመስራት እየሞከረ ነው።


የፈረንሳዩ የመኪና አምራች Renault ላለፉት 2 አመታት ሲሰራበት ስለነበረው የ3D Printing ሂደት ይፋ አረገ። የመኪና interior ክፍሎችን ከ Thermoplastic Polyurethane ወይም TPU ተብሎ ከሚጠራው material ለመስራት እየሞከረ ያለ ሲሆን ጥልፍልፍ መሰል ወይም ጥልፍልፍ መዋቅር ያለው ውስጣዊ ክፍል አለው። ይህም ትንሽ ልዩነት ቢኖረውም ስፖንጅ በእጃችን ስንይዝ ያለውን አይነት ስሜት እንዲሰጥ ያረገዋል።

ይህ ፈጠራ ምን አልባት አንድ ቀን እንደ የመኪና ወንበር የጀርባ መደገፊያ እና መቀመጫውን፣ የእጅ መደገፊያ፣... ያሉ ክፍሎች ይሰሩበት ይሆናል። በአንድ ጥሬ እቃ ብቻ በመጠቀም መሰራት መቻሉ ለወንበር መስሪያ ምንጠቀማቸውን እንደ የቆዳ እና የጨርቃጨርቅ ውጤቶች፣ስፖንጅ፣ማጠናከሪያዎችን በማስቀረት የወንበሩን ክብደት በ30% እንዲቀንስ ያረገዋል።

Renualt በጋራ ሆኖ አብሮት እየሰራው ያለው በፈረንሳይ መንግስት ፈንድ እየተደረገ የሚሰራው CEA የተባለው የጥናት እና ምርምር ቡድን እንደተናገረው ከሆነም ምን አልባት አንድ ቀን ለእያንዳንዱ እሽከርካሪ በራሱ ሳይዝ እና ፍላጎት customize ወንበሮችን በ3D Printing ምናዘጋጅበት ቀን ይመጣል።

#Renault #3D_Printing
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

የቻይናው ሹፌር አልባ ተሽከርካሪ(Av) Moose test ተብሎ ሚጠራውን ፈተና አለፈ።


የቻይናውች የመኪና አምራች IM Motors በወርሃ may አዲሱን L6 የተባለው ሴዳን መኪናውን ለገበያ ከማቅረቡ በፊት የመኪናውን አቅም ለህዝቡ እያሳየ ነው። 
Car News China መኪናው ውስጡ ላይ ሰው ሳይኖር Moose test ተብሎ ሚጠራውን መኪኖች በፍጥነት አየተጓዙ በመሰናክሎች ውስጥ የሚሽሎኮለኩበትን ፈተና ጥሩ በሚባል ሁኔታ ሲያልፍ የሚያሳየውን ቪዲዮ አጋርቶዋል።

እዚህ ጋር እናንተ ዳኛ ሁኑ! Moose test የተባለው ፈተና ላይ በመደበኛ ጊዜ የፊት ወንበሮች ላይ 2 ሰዎች መቀመጥ ይኖርባቸዋል ፣ ከኋላ ኮፈኑ ላይም ክብደት ይጨምር እና መኪናው ወደ መሰናክሉ ከመግባቱ በፊት ቢያን በሰአት 72km ፍጥነት እየተጓዘ መሆን ይኖርበታል። ነገር የL6 በሰአት 71km ፍጥነት ወደ መሰናክሉ ገብቶ በሰአት በ49km ፍጥነት ነው የወጣው። በተጨማሪ መኪናው ይሄን ፈተና የራሱን ሴንሰሮች ተጠቅሞ ይሁን አሊያም በቅድሚያ መንገዱን በሰው ሹፌር እንዲማር ተደርጎ እንደሆነ አልገለፁም።

#IM_Motors #L6 #AV
#Moose_Test
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

የአለም የመጀመሪያው ሹፌር አልባ የመንገድ ማፅጃ መኪና።



የአለም የመጀመሪያው level 4 autonomous/ ሹፌር አልባ የመንገድ ማፅጃ መኪናን ተዋወቁት።
Robosweeper S1 ይባላል። በ WeRide በተባላ ካምፓኒ የተሰራ ሲሆን በ400L የውሃ ታንከር እና በ240 L የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ገንዳ ጋር በ3 በተለያዩ መዋቅሮችና ፊውቸሮች ይዞ ቀርቦዋል።

መኪናው በራሱ ከመንገድ ላይ ቆሻሻን መጥረግ እና ማንሳት፣ የጠረገውን ቆሻሻ ትልቅ ገንዳ ላይ ወስዶ መጣል፣ እና እራሱን ፓርክ ማረግ ይችላል።
መኪናውን እንደ መናፈሻዎች፣ ፓርኮች፣ የእግረኛ መንገዶች፣ እና የሞተር አልባ ተሽከርካሪ መንገዶችን ለማፅዳት የሚጠቅም ሲሆን
ገና ካሁን የብዙዎችን ቀልብ ሳይገዛ አልቀረም።
WeRide እንደተናገረው ከሆነ መኪናውን ለገበያ ይፋ ባረገበት ቀን 10 ሚሊየን ትዛዞችን ተቀብሎዋል።

#WeRide #Robosweeper_S1 #AV
@OnlyAboutCarsEthiopia
# ዜና

BYD የኤሌክትሪክ ፒክ አፕ ትራኮችን ወደማምረት ገባ።


እንደ Toyota ፣ Ford ፣ እና Nissan ያሉ በአለም አቀፍ ደረጃ ፒክ አፕ መኪኖችን አምራች የሆኑ ካምፓኒዎች ከወዲሁ አይናቸውን ቢከፍቱ ሳይሻላቸው አልቀረም ምክንያቱም BYD ገበያቸውን እየተቀላቀለ ነው። ለሁለቱም የቀኝ አና የግራ መሪ ለሚጠቀሙ ሃገራት እንዲሆን አርጎ የሰራውን አዲሱን ፒክ አፕ መኪናውን አስተዋውቆዋል።

እስካሁን ስም ያልወጣለት ሲሆን BYD እንዳለው መኪናው plug-in ሃይብሪድ ነው። በኤሌክትሪክ ሃይሉ ተጨማሪ 100 ኪሎሜትሮች የሚጓዝ ሲሆን በድምሩ ከነዳጁ ጋር እስከ 1,000 ኪሎሜትር የሚደርስ የድራይቪንግ ሬንጅ አለው። Active suspension ሲስተምም እንደሚኖረው አክሎ ተናግሯል።

ፒክ አፕ ትራኩ በዚህ ወር ቻይና ላይ የሽያጭ ፍቃዱን የሚያገኝ ሲሆን በቀጣይ አመት ደግሞ እንደ አውስትራሊያ እና ደቡብ አፍሪካ ያሉ ጠንካራ የፒክ አፕ ገበያ ወዳላቸው ሃገራት ኤክስፖርት ይደረጋል።

#BYD #Electric_PickUp
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Renault አዲሱ Captur መኪናውን ይፋ አደረገ።


የፈረንሳዩ የመኪና አምራች Captur በሚል የሞዴል  ስም የሚያመርተውን subcompact crossover መኪና በዚኛው አመት እሻሽሎ እና የዲዛይን ለውጦችን አርጎበት አቀረበው።

ያለፈው ሞዴል ላይ ከፊት ላይ የነበረውን ሰፊ ግሪል በመዝጋት አነስ ያለ እና አግድም በሆነ ግሪል የለወጠው ሲሆን ከፊት መብራቶቹም ጋር ፍሰት እንዲኖራቸው ተደርጎ ነው የተሰራው።  ከኋላ ላይ የ "C" ቅርፅ ያላቸው የኋላ መብራቶችን ስናገኝ የ"C"ቅርፅ ያለው መብራቱ ተለጥጦ የኮፈኑ በር ላይ ጭምር እናገኘዋለን።

ውስጥ ላይ ስንገባ ከሁሉ ቀድሞ (center screen) እይታን የሚስብ ሲሆን ዳሽ ቦርዱ ላይ (vertically) ተገጥሞ ታብሌት የሚመስል ገፅታን ሰጥቶታል። ውስጡ ላይ አንደ Android Automotive 12፣ Apple CarPlay፣ እና Google ያሉ ሲስተሞች ተካተውለታል። 10.13 ኢንች የጌጅ እስክሪን ተጥሞለታል።

አዲሱ Captur ሙሉ በሙሉ አዲስ በሆነ የelectronic architecture ያለው ሲሆን ይህም ብዙ የቴክኖሎች ፊውቸሮችን ጨምሮ እንዲይዝ እንዲሁም Level 2 Autonomous Driving አንዲኖረው አርጎዋል።

መኪናው አብዛኛውን ሃይል የሚያገኘው ከ ባለ 4 ሲሊንደር አና ከ Mild- Hybrid ሞተሩ ሲሆን የPropane ወይም የ(LPG) አማራጭም ይዞ ቀርቦዋል።

Captur በሃገረ ስፔን መመረቱን የሚቀጥል ሲሆን በቅርቡ የአውሮፓ ገበያ ላይ የሚቀርብ ይሆናል።

#Renault #Captur
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Canoo ከሚያስገባው ገቢ በላይ ለCeoው የprivate jet  በረራው ያወጣው ወጪ ይበልጣል።


ገና በደንብ እግሩ ያልቆመው የኤሌክትሪክ መኪና አምራች ካምፓኒ Canoo አሁላይ በደንብ የገንዘብ ምንጩን ማስፋት እና ገንዘብ መያዝ እንደሚጠበቅበት ግልፅ ነው። ነገር ግን ካምፓኒው ላይ ኢንቨስት ለማረግ ሃሳብ ያላቸውን ኢንቨስተሮች ሃሳብ የሚያስቀይርን ነገር ልንገራቹ።

ካምፓኒው ባለፈው አመት ካስገባው ገቢ በላይ በሁለት እጥፍ ለካምፓኒው Ceo Tony Aquila የግል ጀት( private jet) በረራዎች ላይ አውጥቶዋል።  በቅርቡ ባጋራው አመታዊ የካምፓኒው ሪፖርት መሰረት ካምፓኒው ለCeoው የprivate jet በረራ 1.7 ሚሊየን ዶላሮችን ያወጣ ሲሆን በአንፃሩ በዛው አመት ያስገባው ደሞ 886,000 ዶላሮችን ብቻ ነው።

Canoo አንደተናገረው የካምፓኒው ጥሬ ገንዘብ እና ወደ ገንዘብ ሊቀየር የሚችል ንብረቱ ካለፈው እሩብ አመት አንፃር በ20% በመውረድ 6.4 ሚሊየን ዶላር ሆኖዋል።

ማለት የምንችለው ይሄን ሁሉ ነገር አድርገን እንዳላዩ የሚያልፉን የድርጅት የዳይሬክተሮች ቦርድ ማግኘት መታደል ነው።

#Canoo #Private_Jet
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

በቻይና የኤሌክትሪክ መኪኖች የኢንሹራንስን ዋጋ በጣም ውድ ነው።


የኤሌክትሪክ መኪኖች ሽያጭ ቻይና ላይ እየቀነሰ ነው።ይሄን የሽያጭ መቀነስ የሚያባብስ ነገር ደግሞ እነሆ።
Bloomberg አንደዘገበው በቻይና የሚገኙ ብዙ የኤሌክትሪክ መኪና ባለንብረቶች ሶሻል ሚዲያን በመጠቀም ውድ ስለሆነው የኢንሹራንስ ዋጋ ቅሬታቸውን እያሰሙ ነው።

አንድ ባለ ንብረት እንደተናገረው ምንም አይነት አደጋ ሳይደርስብ የኢንሹራንስ ማደሻ የአረቦን(premium) ክፍያ ላይ ጭማሪያ ያረጉብናል። ሌላኛው ባለንብረት ደግሞ ረዥም እለታዊ ጉዞዎችን ማረግ እንደ ከፍተኛ የአደጋ ስጋት ታይቶ በኢንሹራንስ ካምፓኒዎች የኢንሹራንስ መግቢያ ጥያቄው ውድቅ ሆኖበታል።

የኤሌክትሪክ መኪኖች የአረቦን(premium) ክፍያ ውድ የሆነበት ምክንያት ጥገና ለማድረግ  ብዙ ወጪ ስለሚያስወጡ ነው። ይህም የሆነበት ምክንያት ደግሞ የመለዋወጫዎቹ ዋጋ ውድ መሆን እና ጥገናውን ለማከናውን ብቁ የሆኑ ቴክኒሻኖች ቁጥር ማነስ ነው።

እንደ S&P Global Ratings መረጃ መሰረት ቻይና ላይ የኤሌክትሪክ መኪኖች የአረቦን(premium) ክፍያ ከነዳጅ መኪኖች እንፃር  ከበ20% ጀምሮ እስከ እጥፍ ከፍ ያለ ነው።

#electric_cars #Insurance #Premium
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Nikola ይሸጣል ተብሎ ከተገመተው በላይ ሸጠ።


ቁጥሩ አሁንም ትንሽ ቢሆንም የአሜሪካው የሃይድሮጅን እና የኤሌክትሪክ መኪኖች አምራች ካምፓኒ የሆነው Nikola Analystቶች በመጀመሪያው እሩብ አመት ይሸጣል ብለው ከገመቱይ በላይ በሃይድሮጅን የሚሰሩ የጭነት ተሽከርካሪዎችን ሸጠ።

30 የጭነት መኪኖችን ይሸጣል ብለው ገምተው የነበር ሲሆን Nikola ግን በአሜሪካ አሪዞና ግዛት ውስጥ ባለው ማምረቻ  43 የጭነት ተሽከርካሪዎችን በማምረት ከነዛ ተሽከርካሪዎች ውስጥም 40ዎቹን ሸጦዋል። የተቀሩት 3ቱ የጭነት ተሽከርካሪዎቹ ደግሞ ኦርደር  የተደረጉ ሲሆን በዚህ ወር ለባሌቤቶቻቸው ይላካሉ ብሎዋል።

በተጨማሪ አሁንም የሃይድሮጅን ማደያ ስቴሽኖችን እየገነባ ያለ ሲሆን በዚህ አመት ሽያጩ በደንብ እንደሚያድግ ያምናል። ባለፈው አመት ከባትሪያቸው ጋር ተያይዞ በእሳት አደጋ ስጋት ምክንያ ወደ ካምፓኒው recall ተደርገው የነበሩት የጭነት መኪኖቹን ተገቢውን ማስተካከያ አርጎባቸው ወደ ባለቤቶቻቸው የመመለስ ሂደቱን እንደጀመረ አሳውቆዋል።

#Nikola #Haydrogen_Trucks
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Ford ቁልፍ የሆኑ ከየኤሌክትሪክ መኪኖች ጋር የተያያዙ ጅማሬዎቹን አዘገየ።


Ford በኤሌክትሪክ መኪኖች  ላይ ከመጠን በላይ መዋዕለ ንዋዩን አፍስሷል እና ቢያንስ ለአንድ ዓመት ያህል ሁለት ጉልህ ጅማሮዎችን ሊያዘገይ ነው።

Blue Oval City ብሎ የሰየመውን በአሜሪካ ቴነሲ ግዛት ውስጥ በመገንባት ላይ ያለውን ግዙፍ የመኪና መገጣጠሚያውን ግንባታ አቀዝቅዞታል። መገጣጠሚያው ዘመናዊ የሆኑ የኤሌክትሪክ full size pick up መኪኖችን የሚያመርት ሲሆን ስራ የሚጀምርበት ጊዘ በ1 አመት አዘግይቶታል።

በተጨማሪ በOalville ካናዳ ማምረቻው ሚመረቱ እስከ 7 ሰው ድረስ የሚይዙ SUV መኪኖች ለገበያ መቅረብ የሚጀምሩበትን ቀን በ2 አመት አዘግይቶታል።
Ford እንዳለውም ይሄ እርምጃ ለነዚህ መኪኖች ገበያ ላይ ያላቸው ፍላጎት እንዲጨምር ያረጋል።

Fors አሁን ላይ ትኩረቱን ሃይብሪድ መኪኖች ላይ ያረገ ሲሆን እስከ 2030 መጨረሻ ድረስ ለሁሉም መኪኖቹ የሃይብሪድ አማራችን ለማቅረብ አቅዶዋል።

#Ford #Electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

አዲሱ የChevrolet ኤሌክትሪክ ፒክ አፕ መኪና በአንድ ቻርጅ 740 ኪሎሜትር ይጓዛል።


በ ጀነራል ሞተርስ ስር የሚተዳደረው Chevrolet የመጀመሪያውን የኤሌክትሪክ ፒክ አፕ መኪናውን የሰራ ሲሆን Silverado RST ይሰኛል።

Silverado 200kwh ባትሪ ፓክ ያለው ሲሆን ይህ ማለት ባትሪው ከሶስት ቴስላ ሞዴል 3 ሎንግ ሬንጅ ቨርዥን ባትሪ ፓክ ይበልጣል። በአንድ ቻርጅ ብቻ እስከ 760 ኪሎሜትር መጓዝ ሲያስችለው የ 300 kw(Kilowatt) ቻርጂንግ ፍጥነት አለው።የተገጠመለት የኤሌክትሪክ 551 kw(kilowatt) ሞተርም 754 የፈረስ ያመነጫል።

ጀነራል ሞተርስ Chevrolet Silverado RST መጀመሪያ ለገበያ ካወጣበት ዋጋ በ10,000 ዶላር ቅናሽ አድርጎበት አሁን ላይ በ96,395 የሜሪካ ዶላር አቅርቦታል።

#Chevrolet #Silverado_RST #GM
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Didi እና GAC Aion በሚመጣው አመት RoboTaxi ለመስራት ተስማሙ


የቻይና ራይድ ሂሊንግ ካምፓኒ የሆነው Didi እና የኤሌክትሪክ መኪኖችን በማምረት የሚታወቀው GAC Aion እንዳስታወቁት ከሆነ ፈቃዱን በማግኘታቸው እነዚህን ደረጃ 4 እራሳቸውን በራሳቸው መንዳት የሚችሉ መኪኖች በብዛት ቻይና ውስጥ ሊያመርቱ ነው ::

እነዚህ ሁለት ድርጅቶች ባለፈው አመት በጆይንት ቬንቸር መስራት የጀመሩ ሲሆን (autonomous vehicles) ለመስራት እንዲሁም የመጀመሪያው RoboTaxi ኤሌክትሪክ SUV መኪናቸውን የሚቀጥለው አመት ይለቁታል ::

#GAC #Didi #electric #robotaxi
@OnlyAboutCarsEthiopia
#Ad

መኪናዎትን ባሰቡት ዋጋ መሸጥ ፈልገዋል?

እንግዲያውስ የተለያዩ መኪኖቻችሁን በሁሌመኪና በማስተዋወቅ መሸጥ እና ማከራየትም ትችላላችሁ
በ 0911663121 ላይ በመደወል ወይም ቴሌግራም ላይ @Hulemekinaadmin ላይ የመኪኖቻችሁን ፎቶ (እስከ 10 ፎቶዎችን) በመላክ 300 ብር ብቻ ቴሌብር ላይ ከላይ ባስቀመጥነው ስልክ ላይ በመክፈል መሸጥ እና ማከራየት ትችላላችሁ ::

@hulemekina
#ዜና

Elon Musk Robotaxi በወርሃ August ይፋ እንደሚሆን ተናገረ።


ብዙዎች ሞዴል 2 ነው የሚሉት የቴስላ የ25,000 ዶላር መኪና ሳይመረት ሊቀር ይችላል። January ላይ የቴስላ CEO የሆነው Elon musk በዋጋቸው ዝቅተኛ የሆኑ የኤሌክትሪክ መኪኖች በ2025 ሁለተኛ አጋማሽ ላይ አሜሪካ ቴክሳስ ግዛት ውስጥ በሚገኘው ማምረቻው እንደሚመረቱ ተናግሮ ነበር። ነገር ግን ባሳለፍ ነው አርብ በቴስላ በሰራተኞች ስብሰባ ላይ ከተገኙ ሁለት በካምፓኒው ከሚገኙ የመረጃ ምንጮች ባገኘው መረጃ መሰረት Reuters ቴስላ ፕሮጀክቱን እንደዘጋው ዘግቧል።

ይሄ ይሁን እንጂ ዜናው ይፋ እንደወጣ ብዙም ሳይቆይ Elon Musk በTwitter ገፁ ላይ “Reuters is lying (again)” ("Reuters እየዋሸ ነው(በድጋሚ)") ብሎ tweet አርጎዋል። ነገር ግን እንዲ ያለበት ጉዳይ ስለምን እንደሆነ በግልፅ ተጠቀሰው ነገር የለም።

ግን ሁለቱንም ወገን የሚያስማማ አንድ ነገር አለ። እሱም ቴስላ የRobotaxi ማበልፀጉን እየገፋበት እንደሆነ ነው። እሱም ከሞዴል 2 ጋር ተመሳሳይ በሆነ platform ነው የሚመረተው።
ሮይተርስ እንዳለው ከሆነ አሁን ላይ ቴስላ ትኩረቱ Robotaxi ላይ አርጎዋል እናም የሞዴል 2 ሳይመረት መቅረት ምክንያትም ይሄ ነው።

"Reuters እየዋሸ ነው(በድጋሚ)" የሚለው tweet ካደረገ ብዙም ሳይቆይ Elon "Robotaxi 8/8 ላይ ይፋ ይሆናል" ብሎ tweet አርጎዋል። አመተምህረቱን አለመግለፁን ተያይዞ ሰዎች የአሁኑ August ነው ብለው ወስደውታል።

#Tesla #Elon_Musk #Model_2 #Robotaxi
@OnlyAboutCarsEthiopia
2024/09/22 22:33:18
Back to Top
HTML Embed Code: