Telegram Web Link
#ዜና

ህንድ ቴስላን ለመሸንገል ስትል ወደ ሃገሪቷ የሚገቡ የኤሌክትሪክ መኪኖች ላይ የሚጣለው ግብር/ታክስ ላይ ቅነሳ አደረገች።


ህንድ የኤሌክትሪክ መኪና አምራች ካምፓኒዎች በተለይ ቴስላን ሃገሪቷ ላይ ኢንቨስት አንዲያደርግ ለመሸንገል ኢምፖርት የሚደረጉ የኤሌክትሪክ መኪኖች ላይ የሚጣለው ታክስ ላይ ቅነሳ ያረገች ሲሆን ካምፓኒዎቹ የዚህ ታክስ ቅነሳ ተጠቃሚ እንዲሆኑ በትንሹ 500 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ኢንቨስት ማድረግ የሚጠበቅባቸው ሲሆን ሃገሪቷ ላይም በሶስት አመት ጊዜ ውስጥ ወደ ምርት የሚገቡ ከሆነ ብቻ ነው።

አሁን ላይ ህንድ ወደ ሃገሪቷ የሚገቡ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ላይ እንደ ዋጋቸው ከ70%-100% ቀረጥ የምታስከፍል ሲሆን በአዲሱ ህጓ ግን የመኪና አምራች ካምፓኒዎቹ በአመት ብዛታቸው እስከ 8,000 የሆነ እና የእያንዳንዳቸው ዋጋ 35,000 ዶላር እና ከዛ በላይ ለሆኑ የኤሌክትሪክ መኪኖች 15% የታክስ ክፍያን በመክፈል ብቻ ወደ ሃገሪቷ ማስገባት ይችላሉ።

ቴስላ የህንድ ገበያ ላይ የመግባት ፍላጎት ቢኖረውም የሃገሪቷ መንግስት ግን ቅድሚያ የሚሰጠው ሃገሪቷ ላይ ለሚያመርቱ አምራቾች ነው። ይሄንንም አስመልክቶ ቴስላ አዲስ ወደ ገበያ ያልወጡ መኪናዎችን ህንድ ላይ ለማምረት ጥያቄውን አቅርቦ የነበር ሲሆን የሃገሪቷን መንግስትንም እንደ ቅድመ ሁኔታ የታክስ ቅነሳ ይደረግልኝ ብሎ ጠይቆ ነበር።

#India #Tesla #electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

ፎርድ አዲስ የኤሌክትሪክ compact truck እና SUV እያበለፀገ ነው።


በዋጋቸው ተመጣጣኝ የሆኑ መኪኖች ላይ ያለው ፍላጎት ፎርድን ቁልፍ የሆኑ ለውጦችን እንዲያደርግ አስገድደውታል። ባለፈው ወር የፎርድ ceo የሆነው Jim Farley  እንደገለፀው የመኪና አምራች ካምፓኒው ዋጋቸው በጣም ቅናሽ የሆኑ መኪኖችን ማምረት የሚያስችለውን ሚስጥራዊ የሆነ ፕሮጀክት ላይ እየሰራ ሲሆን
የቴስላ ሞዴል Y ኢንጂነሪንግን ሲመራ የነበረው Alan clark  ነው ይህን ፕሮጀክት መሪ ሆኖ እየሰራ ያለው።

እንደ bloomburg ዘገባ ከሆነ የቡድኑ አባላት ከ100 ያነሱ ሲሆን የመጀመሪያውን ሞዴል ስራ አጠናቀው ለገበያ እስኪቀርብ እስከ 2026 ድረስ የሚቆይ ሲሆን የመሸጫ ዋጋውም 25,000 የአሜሪካ ዶላር ይሆናል።

ከሞዴሎቹ ውስጥም የኤሌክትሪክ compact truck እና Suv ሲኖሩ አንድ ተጨማሪ ሞዴል ደግሞ ለታክሲ አገልግሎት የሚውል ይኖራል።

#Ford #electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

የቻይና የመኪና አምራቾች አዲሱን የNVIDIAን ኮምፒውተር ለመጠቀም ስምምነት አደረጉ።


በአለም ላይ አሉ የተባሉ (powerful) የኮምፒውተር ቺፖችን አምራች እና የ2.2 ትሪሊየን ዶላር የገበያ ካፒታል ባለቤት የሆነው NVIDIA አዲስ Drive Thor የተባለ ማእከላዊ የመኪና ኮምፒውተር ሲስተም ይዞ የመጣ ሲሆን ይሄን አገልግሎት መጠቀም የሚፈልጉ የመኪና አምራቾች እና ሹፌር አልባ (autonomous) መጓጓዣዎችን አቅራቢ የሆኑ ድርጅቶች ከካምፓኒው ጋር ስምምነት ፈፀሙ።

ሁሉም የመኪና አምራቾች የቻይና ሲሆኑ BYD፣ XPENG፣ LE AUTO፣ ZEEKR፣ HAYPER የተባሉት የመኪና አምራቾች ይሄን የGenerative AI ሲስተም ቀጣይ አመት ሲወጣ የሚጠቀሙ ይሆናል።

NVIDIA እንደተናገረው Drive Thor ብዙ ፊቸሮች ላላቸው cockpit እና በጣም ለተራቀቁ ሹፌር አልባ(autonomous) መኪኖች ተመራጭ ሲሆን
በሰከንድ 1000 tera flops processing
ስፒድ አለው።
እዚህ ጋር ልብ ማለት ያለባቹ በጣም ፈጣን አቅም አለው የተባለው የgaming console እራሱ በሰከንድ የ13 tera flops processing ስፒድ ብቻ ነው ያለው።

#NVIDIA #autonomous_Cars
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Bentley የኤሌክትሪክ መኪኖቹን ዘግየት በማድረግ የነዳጅ እና የኤሌክትሪክ ሃይብሪድ (PHEV) መኪኖች ላይ እየሰራ ነው።


የቮልክስ ዋገን ግሩፕ አካል የሆነው የቅንጡ መኪናች አምራች ካምፓኒ Bentley ወደ ኤሌክትሪክ የሚያደርገውን Transition ያዘገየው ሲሆን የመጀመሪያ የኤሌክትሪክ መኪናውን ለገበያ ከሚያቀርብበት ጊዜ 2 አመት ገፋ በማድረግ 2027 ላይ አርጎታል። ለዚህም ምክንያት ሶፍትዌሩን በማበልፀግ ላይ በገጠሙኝ ቴክኒካዊ እክሎች ምክንያት ነው ብሎዋል።

2030 ላይ ሙሉ በሙሉ ወደ ኤሌክትሪክ መኪኖች ማምረት Transition ለማድረግ የነበረውን እቅዱ ወደ ጎን በማድረግ ትኩረቱን ወደ ሃይብሪድ መኪኖች ላይ አድርጎዋል።
ነገር ግን ዋና ተቀናቃኙ Rolls-Royce፤ Spectre coupe የተባለውን የኤሌክትሪክ መኪናውን ለገበያ ያቀረበ ሲሆን ላለው በ2030 ሙሉ በሙሉ ወደ ኤሌክትሪክ Transition የማድረግ  እቅድ እንደታመነ ነው።

የbentley መዘግየት ላይ አንዱ ምክንያት የሆነው የሽያጭ ገቢው እና ትርፉ ባለፈው አመት ላይ ስለቀነሰበት ሲሆን ሽያጩ በ11% ፣ገቢው በ13%፣እና ትርፉ በ17% ዝቅ ብሎበታል።

#Bentley #electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

ጀርመን ውስጥ ያሉ የመኪና አምራች ካምፓኒዎች በ 100,000 የሚቆጠሩ ሰራተኞች ስራቸውን ሊያጡ ነው


በተደጋጋሚ እንደሚነሳው በደንብ የሚታወቁት የመኪና አምራች ካምፓኒዎች በጣም አጣብቂኝ አንዳንዶቹ እንደውም ኪሳራ ውስጥ እየገቡ ይገኛሉ :: ለዚህም ማሳያ አንዱ ጀርመን ውስጥ የሚገኙ የመኪና አምራች ድርጅቶች ሲሆኑ ለእነሱ እቃ ከሚያቀርቡት ድርጅቶች አንዱ የሆነው Webasto ሲሆን እሱም የመኪኖችን ጣራ ላይ ያሉ ልክ እንደ የጣራ ሞጁሎችን, ሰንሩፍ እና ለኮንቨርተብል መኪኖች ደግሞ መሸፈኛዎችን ይሰራል :: ይህ ድርጅት አሁን ላይ 10% ማለትም 1,600 ስራዎችን ሊቀንስ ነው :: ለዚህም ምክንያቱ ባለፈው አመት ሽያጩ €4.6 ቢሊየን ዩሮ ብቻ ነበር ያስመዘገበው :: ኤክስፐርቶች ለጀርመን ካምፓኒዎች ወደ 100,000 ስራዎችን ሊያጡ እንደሚችሉ ገልፀዋል :: ለዛም ነው Webasto አሁን ላይ የባትሪ ፓኮችን መጨመር እንደ አድ ስራ አድርጎ ያስገባው :: ሌሎች ልክ እንደ Bosch, Continental እና ZF በሺዎች የሚቆጠሩ ሰራተኞቻቸውን ሊያባርሩ ይችላሉ :: ኤሌክትሪክ መኪኖች ብቻ አይደሉም ለዚህ ምክንያት መንስኤዎቹም ከዛም በፊት አውሮፓ ውስጥ የመኪኖች ሽያጭ እየቀነሰ ነበር ::

#Germany #Jobs
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

General Motors በዚህ አመት የUltium ባትሪው ላይ ትልቅ እድገትን ለማድረግ አቅዶዋል።

GM ለገበያ የሚያቀርባቸው መኪኖቹ ላይ እራሱ የሚያመርታቸውን የUltium ባትሪዎች በከፍተኛ መጠን ለመጠቀም ያቀደ ሲሆን ባለፈው አመት የultium ባትሪ የሚጠቀሙ 13,000 መኪናዎችን ሰርቶ ለገበያ አቅርቦዋል።

በዚህ አመት ያንን ቁጥር በ20 እጥፍ በማሳደግ ከ200,000 እስከ 300,000 መኪኖችን ለማምረት አቅዶዋል። GM ይሄን ይበል እንጂ ባለፈው አመት ላይ ሁኔታዎች ከእቅዱ በታች ነበር የሆነበት።

#GM #Electric
#Ultium
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Peugeot የሚያመርተውን ትልቁ SUV 5008 በሀይብሪድ እና በኤሌክትሪክ ይዞ እየመጣ ነው

Peugeot የሚያመርተው ትልቁ SUV ከ  Stellantis አዲሱ STLA ኘላትፎርም ጋር ተሰራ :: አዲሱ 7 ሰው የሚጭነው 5008 SUV በ mild-hybrid, በ plug-in hybrid እና በ electric አማራጮች ቀርቧል :: የ mild-hybrid ሞዴል በ 136 የፈረስ ጉልበት እና በ 6 ማርሽ DCT(Dual Clutch Transmission) የሚመጣ ሲሆን PHEV (Plug-in Hybrid) ላይ ደግሞ በ 92 KW (Kilowatt) ሞተር እና በ 150 የፈረስ ጉልበት ይመጣል :: ፔጆ ስለ ባትሪው የገለፀው ነገር የለም ግን በኤሌክትሪኩ ብቻ 80 ኪሎሜትር እንደሚጟዝ ተናግሯል ::

ሙሉ በሙሉ ኤሌክትሪክ የሆነው ሞዴል ደግሞ በ FWD(front wheel drive) ወይም በ AWD(all wheel drive) ሲመጣ የ FWD ሞዴሉ በ 157 kw(Kilowatt) ወይም በ 210 የፈረስ ጉልበት እና  በ 170 kw(Kilowatt) ወይም በ 227 የፈረስ ጉልበት አማራጭ ይመጣል ::የ AWD ሞዴሉ በ 237 kw(Kilowatt) ወይም በ 317 የፈረስ ጉልበት አማራጭ ይገኛል :: የሚጠቀመው ባትሪ ሊትየም አየን ሲሆን 98 Kwh ባትሪ ፓክ እና በአንድ ቻርጅ እስከ 660 ኪሎሜትር ሊጟዝ እንደሚችል ገልፀዋል :: ሌላም አነስ ያለ ሞዴል እንደሚኖር እና በአንድ ቻርጅ 500 ኪሎሜትር እንደሚሄድ አስታውቀዋል ::

ውስጡ ላይ ብዙም ማሻሻያ እንዳላካተቱ ከበፊቶቹ ሞዴሎች አንፃር ግን ደግሞ ከ Chatgpt ጋር አብሮ እንዲሰራ እንዳደረጉትም ተናግረዋል :: አዲሱ E-5008 ሞዴል ለሽያጭ ከወራት በሗላ ይቀርባል ብሏል ::

#Peugeot #e5008 #electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Volkswagen ግሩፕ ከ እስራኤል AV ቴክኖዎሎጂ (Mobileye) ጋር ያለውን ግንኙነት እያጠነከረ ነው

እነዚህ ሁለት ካምፓኒዎች አንድ ላይ በመሆን ሌቭል 2 እና 3 የድራይቭንግ አሲስት ሲስተሞችን እየሰሩ ነው :: VW  ፕሪምየም ብራንዶች ልክ እንደ Audi Bentley Lamborghini እና Porsche (Mobieye) የሚሰራቸውን ሲስተሞች መጠቀም እንዲችሉ እየሰሩ ነው :: Mobileye ከሱም በተጨማሪ ለ VW የኮሜርሻል መኪኖች በሌቭል 4 አውቶኖመስ ድራይቪንግ በ VW ID. BUZZ ኤሌክትሪክ ቫን ላይ እንደሚያካትቱ ተናግረዋል :: አሁን ላይ ከ Mobileye ጋር እየሰራ ቢሆንም ወደፊት ግን በራሳቸው በ Bosch በመታገዝ እንደሚሰሩ ገልፀዋል ::

#VW #Mobileye #Autonomous
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ጠቃሚ_መረጃ

ኢትዮጵያ ውስጥ 60 ቻርጀር ለ 100 ሺህ ኤሌክትሪክ መኪና?


በዛሬው እለት የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስተር ይፋ ባደረገው መረጃ መሰረት ሃገራችን ውስጥ የተገጣጠሙ እና ከውጭ ሃገር የገቡ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ቁጥር ከ100 ሺ በላይ መድረሱን አስታውቋል።

በመዲናችን አዲስ አበባም ወደ 60 የሚሆኑ የኤሌክትሪክ መኪና DC ፋስት ቻርጀሮች የተገጠሙ ሲሆን ካለው የመኪና ቁጥር አንፃር የለም በሚባል ደረጃ ነው ማለት ይቻላል :: ሰዉ ግን ምንም እንኳን እነዚህ ችግሮች እንዳሉ ቢያውቅም ከነዳጅ ወጪ እና ሰልፍ አይበልጥም በማለት ይመስላል ኤሌክትሪክ መኪኖችን እየገዛ ይገኛል :: በተለይ ኤሌክትሪክ መኪናን እየተጠቀማችሁ ያላችሁ ሰዎች እናንተስ ምን ታስባላችሁ? ሀሳባችሁን ኮሜንት ላይ አጋሩን ::

#Ethiopia #electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

ኪሳራ ውስጥ ገብተው የነበሩ የቻይና የኤሌክትሪክ መኪና ብራንዶች ዳግም እያንሰራሩ ነው።


በቻይና ውስጥ የኤሌክትሪክ መኪናዎች ሽያጭ እያሻቀበ ያለ ቢሆንም በጣም ብዙ የኤሌክትሪክ መኪና ብራንዶች ነው ያሉት።ይህም የብዙ የመኪና አምራቾችን ትርፍ እንዲጎዳ ላደረገው የዋጋ ጦርነት መንስኤ ሆኖዋል።

በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ አሁን ላይ በኪሳራ ምክንያት ጠፍተው የነበሩ ሶስት ብራንዶች ዳግም እያንሰራሩ ነው። እነዚህ ብራንዶች Zhidou Electric vehicles፣ Haima Automobile እና Aiways  ሲባሉ አብዛኛውን ከሃገሪቷ መንግስት ባገኙት የገንዘብ ድጋፍ ምክንያት ነው ነፍስ መዝራት የቻሉት።

የመንግስቱ ትኩረትም ከአምራቾቹ ትርፋማነት ይልቅ ለማህበረሰቡ የሚፈጥሩት የስራ እድል ቢሆንም ቀድሞውኑም በጣም ለተጨናነቅው የሃገሪቷ የኤሌክትሪክ መኪና ገበያ ጉዳት እንጂ ጥቅም የለውም። ባለፈው አመትም ቶፕ 12 ከተባሉት የሃገሪቷ የመኪና አምራቾች ውስጥ 4 ብቻ ናቸው አመታዊ የሽያጭ እቅዳቸውን ማሳካት የቻሉት።

#China #Electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
#Ad

መኪናችሁን በፍጥነት መሸጥ ላሰባችሁ...

የተለያዩ መኪኖቻችሁን በሁሌመኪና በማስተዋወቅ መሸጥ እና ማከራየትም ትችላላችሁ
በ 0911663121 ላይ በመደወል ወይም ቴሌግራም ላይ @Hulemekinaadmin ላይ የመኪኖቻችሁን ፎቶ (እስከ 10 ፎቶዎችን) በመላክ 300 ብር ብቻ በመክፈል መሸጥ ትችላላችሁ ::

@hulemekina
#ዜና

Bloomburg news energy finance የኤሌክትሪክ መኪኖች ከነዳጅ መኪኖች በጣም የፀዱ ናቸው።


አንዳንድ ሰዎች የኤሌክትሪክ መኪኖች ከነዳጅ መኪኖች የበለጠ ከባቢ አየርን በካይ ናቸው ሲሉ ይሰማል። ነገር ግን ከእውነታ የራቀ ነው። Bloomburg news energy finance እንደተናገረው ከሆነ የኤሌክትሪክ መኪኖች ከምርት እገልግሎት እና ሪሳይክል እስከመደረግ ድረስ ባላቸው የህይወት ኡደት ውስጥ ወደ ከባቢ አየር ያላቸው የካርበን ልቀት ከነዳጅ መኪኖች አንፃር በ70% ያነሰ ነው።

መካከለኛ ሳይዝ ባላቸው እና እስከ 250,000 ኪሎሜትር በተነዱ ተሽከርካሪዎች ላይ ባደረገው ጥናት በሚመረቱበት፣ ሪሳይክል በሚደረጉበት ወቅት፣ ኤሌክትሪክ ሃይልን ለማመንጨት በምንጠቀመው መንገድ፣ እና ሌላ ብዙ ምክንያት ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮችን አካቶ፤ ለኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫነት የድንጋይ ከሰልን በሚጠቀሙ ሃገራት ሳይቀር የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ከነዳጅ መኪኖች አንፃር የፀዱ ናቸው።

በሚገርም ሁኔታ ጥናቱ ላይ በነዳጅ ማውጣት፣ ማጣራ፣ እና እንደ ቤንዚል እና ናፍጣ ያሉ ነዳጆችን ለማጓጓዝ በሚደረገው ጥረት ላይ ያለውን የአየር ብክለት አላካተተም። ይህ ማለትም ጥናቱ ከሚለው በላይ የኤሌክትሪክ መኪኖች የፀዱ ናቸው።

የኤሌክትሪክ መኪናዎች በምርት ወቅት የካርበን ልቀት ቢኖራቸውም ከነዳጅ መኪኖች ጋር ፈፅሞ የሚነፃፀር አይደለም።

#Electric
#petroleum
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

BMW የ3D printing የብየዳ ሮቦት እየሞከረ ነው።


BMW ያልተለመደ የመኪና መስሪያ መንገድን እየሞከረ ነው።  መንገዱም( Wire arc additive manufacturing) ሲባል  ፕሮሰሱ በመበየጃ 3D printing እንደመስራት ነው። ሮቦቱ የአሉሚኒየም ገመድን layer በlayer በቀጭኑ እየደራረበ በመበየድ የተለያዩ ቁሶችን ወይም የቁስ ክፍሎችን ያመርታል።

BMW እንዳለው ከሆነው መሳሪያው በዋነኘት እንደ የመኪና ቦዲ፣ ቻንሲ ያሉ ትላልቅ ክፍሎችን ለመስራ ተመራችጭ ነው። በማሽኑ ስራው ተጠናቆ መጨረሻ ላይ የሚወጣው ምርት ትንሽ ለየት ያለ ገፅታ ቢኖረው በቅይጥ ብረት ከሚሰሩ የመኪና ክፍሎች የበለጠ ጠንካራ የሆነ እና ቀለል ያለ ክብደት ያለው ነው።

ደንበኞች የሚመለከቱት የማሽኑ ውጤት የሆነው የመኪና ክፍል የፊኒሺግ ስራ ይርሚያስፈልገው ሲሆን የማይታዩት ድብቅ ክፍሎቹ ግን ባሉበት ሁኔታ መተው ይቻላል። በቀጣይ አመት በተሽከርካሪዎች ላይ የሚሞከር ይሆናል።

#BMW
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

የKia አዲስ kia k4 የተሰኘ ሴዳን የቦዲ ስታይል ያለው መኪናውን ይፋ አደረገ።


Kia እንደ Forte፣ Ceed፣ እና Cerato ያሉ ሴዳን መኪናዎቹም የሚተካ kia k4 የተባለ አዲስ መኪና ሰራ። አዲሱ k4 ውጫዊ ገፅታው ማእዘናት የበዙበት ሲሆን መብራቶቹን ከዋና ከአገልግሎታቸው እና መኪናውን ከማስዋባቸው ባለፈ እንደ መለያ ዲዛይን ተጠቅመዋቸዋል።

ውስጥ ላይ ትልቅ እና ቀጭን የሆነ ዳሽቦርዱ ላይ የተለጠፈ ስክሪን ስናገኝ ቀለል ያለ እና የሚስብ ዲዛይን አለው።

Kia k4 ቀጣይ ሳምንት ኒውዮርክ አውቶ ሾው ላይ የሚቀርብ ሲሆን ስለመኪናው ብዙ መረጃዎችን ይፋ ያደርጋሉ ብለን እንጠብቃለን።

#kia_k4
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Aston Martin አዲስ CEO ቀጠረ።


Aston Martin አዲስ CEO የቀጠረ ሲሆን የቀጠረውም ሰው የ Bentley ሊቀመንበር እና CEO የነበረውን Adrian Hallmark ነው። Adrian,  Amadeo Felisa የሚተካ ሲሆን መንበሩን አዲሱ CEO እስኪረከበው ማለትም እስከ October 1 ድረስ Amado በስልጣን ይቆያል።

Adrian ከ2018 ጀምሮ ቤንትሊን ሲመራ የነበር ሲሆን እንዲሁም በvolkswagen እና በporsche ካምፓኒ ውስጥም አገልግሏል።

ነገር ግን በአዲሱ ስልጣኑ ብዙ መመቻቸት የለበትም ምክንያቱም የAston Martin Formula 1 team ባለቤት እና የAston Martin የዳይሬክተሮች ቦርድ ሃላፊ የሆነው ካናዳዊው ቢሊየነር Lawrence Stroll 2020 ላይ ስልጣኑን ከያዘ ጀምሮ አዲስ CEO ሲቀጥር Adrian 4ኛው ሰው ነው።

#AstonMartin #CEO
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Zeekr አዲስ የኤሌክትሪክ ሚኒቫኑን ይፋ አረገ።


የGeely አካል የሆነው የቻይናው የመኪና አምራች Zeekr አዲስ መኪና ይዞ የመጣ ሲሆን Mix ሲል ሰይሞታል። Mix ለድሮዎቹ Dustbustuer ሚኒቫኖች ዘመናዊው ትርጓሜ /ገፅታቸውን  የሚያሳይ ሲመስል ደስ የሚል ቅርፅ ያለው የኤሌክትሪክ ሚኒቫን ነው።

ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ የተገጠመለት የኤሌክትሪክ ሞተር 310kw ሲሆን እስከ 415 የፈረስ ጉልበት ድረስ ያመነጫል። የባትሪ ፓክ ሳይዙ የተገለፀ ባይሆንም የCATL ባትሪን ነው የሚጠቀመው።

Mix ላይ Advanced ለሆነ የdriver assistance ሲስተም ሲባል Lidar ሴንሰርን ጨምሮ ብዙ ሴንሰሮች ነው የተገጠሙለት።

የሹፌር አልባ ታክሲ ሰርቪስ ሰጪው ካምፓኒ Weymo ከ Zeekr ጋር partnership የመሰረቱ ሲሆን  እነዚህን መኪኖች ለautonomous (ሹፌር አልባ) የታክሲ አገልግሎቱ የሚጠቀማቸው ይሆናል። Zeekr እንዳለውም ከሆነ የያዝነው አመት ከመገባደዱ በፊት weymo በነዚህ መኪኖች ሚሰጠውን አገልግሎች  አሜሪካ ላይ ሊጀምር ይችላል።

#Zeekr #Electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Nikola የመጀመሪያውን የሃይድሮጅን እስቴሽን ከፈተ።


የአሜሪካው በሃይድሮጅን ፊዉል ሴል የሚሰሩ ከባድ የጭነት መኪናዎችን አምራች የሆነው Nikola የመጀመሪያውን የሃድሮጅን ነዳጅ ማደያውን መክፈቱን አስመልክቶ እያከበረ ይገኛል። የተከፈተው በደቡባዊው የካሊፎርኒያ ግዛት በምትገኘው ኦንታሪዮ ከተማ ውስጥ ሲሆን ለ class 8 ትራኮች ወይም የከባድ ጭነት ተሽከርካሪዎች ብቻ ነው አገልግሎቱን የሚሰጠው።

ማደያውን በበላይነት የሚመራው የራሱ የ Nikola ድርጅት የሆነው Hyla ሲሆን ድርጅቱ የሃድሮጅን ነዳጅን የማምረት፣ የማከፋፈል እና የመቸርቸር ስራንም ይሰራል።

ማደያው በቀን እስከ 40 የጭነት ተሽከርካሪዎችን ማስተናገድ የሚችል ሲሆን ካምፓኒው በዚህ አመት መጨረሻ ተመሳሳይ 14 ማደያዎችን የመክፈት እቅድም አለው።

#Nikola #Hydrogen #FuelCell
@OnlyAboutCarsEthiopia
#Ad

የጀርባ መስታወት መስመሮች ጥቅም ምንድነው?


ዝናብ በሚዘንብበት ወቅት በጉም በሚሸፈንበት ጊዜ በቀላሉ መስመሩ ውስጥ በሚገኙ ሽቦዎች ጉሙን ማጥፋት ነው :: ታዲያ ለተለያዩ ሞዴል መኪኖች የሚሆኑ መስታወቶች የምታገኙት ደግሞ ከ Omega Auto Glass ነው ::

Omega Auto Glass የፋብሪካ ቲንትድ የፕራይቬሲ መስታወቶችን ለአዳዲስ መኪኖችንም ለቆዩትም ታገኛላችሁ ::
አድራሻ
ቁጥር 1 - ሀብተጊዮርጊስ ድልድል ወደ አሊያንስ በሚወስደው መንገድ ላይ ፓልሪየስ ጎን
ቁጥር 3 - ጎፋ መብራት ሀይል ታገኙናላችሁ ::
ስልክ 0911241153 ወይም
0911609080 ወይም
0925494095 ይደውሉ ::

#OmegaAutoGlass
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

ቴስላ የመኪኖቹ ሲስተም ላይ ደካማ ጎን ያገኙለትን ሀከሮችን ሸለመ።


ቴስላ በመኪኖቹ ሲስተም ላይ ደካማ ጎንን ላገኙ ሃከሮች የሚከፍልበት (bug bounty) ፕሮግራም የጀመረ ሲሆን በመኪኖቹ ሲስተም ላይ 1 እክልን ወይም ደካማ ጎንን ላገኘለት የሀከር ቡድን 200,000 የአሜሪካን ዶላር እና 1 ቴስላ ሞዴል 3 መኪና በሽልማትነት አበረከተ።

ሀከሮቹ የቴስላን Electronic Control Unit(ECU) ሰብረው መግባት የቻሉ ሲሆን ይህም ማለት የትኛውንም የመኪና ክፍል ካሉበት ሆነው ማዘዝ እንዲችሉ ያደርጋቸዋል።

ይሄው የሀከር ቡድን january ላይ ሌላ ከዚህ ፍፁም የተለየ የሲስተም ድክመትን አግኝቶ በቴስላ 100,000 የአሜሪካ ዶላር ተሸልሞ ነበር።

#Tesla #Hackers
@OnlyAboutCarsEthiopia
2024/09/23 04:23:04
Back to Top
HTML Embed Code: