Telegram Web Link
#Ad

የመኪናዎን እድሜ ለማራዘም ጠቃሚ ምክሮች

የተለያዩ መኪኖቻችሁን በሁሌመኪና በማስተዋወቅ መሸጥ እና ማከራየትም ትችላላችሁ
በ 0911663121 ላይ በመደወል ወይም ቴሌግራም ላይ @Hulemekinaadmin ላይ መኪኖቻችሁን በመላክ 300 ብር ብቻ በመክፈል መሸጥ ትችላላችሁ ::

@hulemekina
#ዜና

ጣሊያን የቻይናውን የመኪና አምራች ካምፓኒ ቼሪን ሃገሯ ላይ መኪኖችን እንዲያመርት እያነጋገረች ነው።


ጣሊያ ሃገሯ ላይ የመኪና ማምረት ሂደቱ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ያልት ፍላጎቷን በደንብ ግልፅ ያደረገች ሲሆን ጣሊያን ላይ በጣም ትልቁ እና ዋነኛ የመኪና አምራች የሆነው Fiat በአመት 750,000 መኪናዎችን ሲያመርት የጣሊያን ባለስልጣናት ግን ይሄንን ቁጥር በአመት ወደ 1.3 ሚሊየን እንዲያድግ ይፈልጋሉ። ለዛም ፊያትን ምርቱን አንዲያሳድግ ከመገፋፋት አልፈው የFiat parent ካምፓኒ የሆነው Stellantis ላይ ድርሻን ለመግዛት ሃሳብ አቅርበዋል።

Stellantis ጫናውን ተከትሎ በአመት ተጨማሪ 250,000 መኪኖችን ለማምረት የተስማማ ሲሆን በድምሩ አመታዊ 1 ሚሊየን መኪኖችን እንዲመረቱ የተስማሙ ሲሆን ጣሊያን አሁንም እቅዷን ለማሳካት ተጨማሪ  300,000 መኪኖችን የሚያመርትላት ካምፓኒ ትፈልጋለች።

የውጪ የመኪና አምራቾችን ወደ ሃገሯ ለመሳብ ስትል በሃገሯ ለሚገኙ የመኪና አምራቾች የ6.5 ቢሊየን ዩሮ ድጋፍ ልታደርግ እንደሆነ የገለፀች ሲሆን ዘገባዎች እንደሚሉት  ከሆነ ጣሊያን ውስጥ ማምረቱን ይጀምራል ተብሎ ትልቅ ተስፋ የተጣለበት የቻይናው የመኪና አምራች Chery ነው።

#Italy #Chery
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Toyota እና nissan ጃፓን የሚገኙ የሰራተኞቻቸው ደሞዝ ላይ ጭማሪ ሊያደርጉ ነው

ጃፓን ላይ ትላልቅ የመኪና አምራቾች ናቸው የሚባሉት toyota አና nissan ብዙ ጊዜ ይጠየቁ የነበረውን የደሞዝ ጭማሪ ለማድረግ ሙሉ በሙሉ የተስማሙ ሲሆን በዚህ 25 አመት ውስጥ የታየው ትልቁ የደሞዝ ማሻሻያም ነው ተብሎዋል።

የቶዮታ ሰራተኞች በወር ደሞዛቸው ላይ 200 ዶላር ጭማሪ የተደረገላቸው ሲሆን ተጨማሪ የቦነስ ክፍያም ይኖራቸዋል። ባለፈው አመት ላይ እነዚህ የቦነስ ክፍያዎች የድርጅቱን የ6 ወር ክፍያን ሲስተካከሉ(እኩል ሲሆኑ) የነበረ ሲሆን በአሁን ማሻሻያ ወደ 7 ወር ተኩል ከፍ ብለዋል።

ይህም የጃፓን ባንክን በ ኔጋቲቭ የወለድ መጠን አመቱን እንዲጨርስ ሲያደርገው የጃፓን መገበያያ ገንዘብ የሆነው የንም ደካማ ሆኖ እንዲቆይ ያደርገዋል። በአንፃሩ የብዙ ጃፓን ካምፓኒዎች ገቢም በጣም ከፍ ይላል።

በመጨረሻም ሰራተኞቹ ከሰፊው ገበታ ላይ ተቋዳሽ ሊሆኑ ነው።

#Toyota #Nissan #Japan
@OnlyAboutCarsEthioopia
#ዜና

የኤሌክትሪኩ tesla model 3 Ludicrous ከነዳጁ የmercedes c63 AMG በ300 ኪሎ ያነሰ ክብደት ነው ያለው


አንዳንድ ሰዎች "የኤሌክትሪክ መኪኖች ትልቁ ችግራቸው ክብደታቸው ነው። በጣም ከባድ በመሆናቸው የተነሳ performace መኪኖቻቸው እንደ ነዳጅ performance  መኪኖች አሪፍ አይደሉም" ይላሉ።

ነገር ግን እንደ ምሳሌነት የኤሌክትሪኩን tesla model 3 Ludicrous እና የነዳጁን Mercedes c63 AMG ብናነፃፅር model 3 Ludicrous ባለ ሁለት የኤሌክትሪክ ሞተር፣በ618 የፈረስ ጉልበት እና በሰአት 261 ኪሎሜትር በሰአት ከፍተኛ ፍጥነት ኖሮት፣ ከc63 AMG አንፃር በጣምሰፋ ያለ እቃ ማስቀመጫን ቦታ ጨምሮ አካቶ በ270kg ያነሰ ክብደት ነው ያለው። (1,835kg)

Mercedes c63 AMG ባለአራት ሲሊንደር ከሃይብሪድ ጋር ሲሆን ፣በ503 የፈረስ ጉልበት እና በሰአት 249 ኪሎሜትር በሰአት ከፍተኛ ፍጥነት ሲኖረው እንደ(auto tread) መረጃ መሰረት ክብደቱ 2,111 ኪሎግራም ነው።

Mercedes c63 AMG ፈጣን የሚባል  መኪና ቢሆንም በጉልበቱም ሆነ በፍጥነቱ ከtesla model 3 Ludicrous ያነሰ ነው።


#Tesla #electric #Mercedes
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

BYD በአውሮፓ ላይ ሽያጩን ለማስፋፋት ትልቅ ህልም እና እቅድ አለው።


በአውሮፓ ገበያ ላይ የBYD መኪኖች ሽያጭ ከሌሎች አምራቾች አንፃር ዝቅተኛ የሚባል ሲሆን በቀጣይ ጥቂት አመታት ውስጥ እድገቱን ለማስፋፋት እና ገበያው ላይ ተፎካካሪ የመሆን  እቅዶች አሉት።

በ2021 አውሮፓ ገበያ ላይ ስራ ሽያጩን የጀመረው የቻይናው የመኪና አምራ BYD ባሳለፍነው አመት ሙሉ በሙሉ ኤሌክትሪክ የሆኑ 16,000 መኪኖችን የሸጠ ሲሆን ይህም ቁጥር የአውሮፓ የኤሌክትሪክ መኪና ገበያ 1.1% ብቻ ነው።

የBYD የአውሮፓ ቅርንጫፍ ሃላፊ ለአውቶሞቲቭ ዜና ጣቢያዎች እንደተናገሩት በ2026 በሃንጋሪ የሚገኘው አዲሱ ማምረቻቸው ስራ ከመጀምሩ በፊት ይህንን ቁጥር ወደ 70,000 ወይም ወደ 5% የማሳደግ እቅድ ያላቸው ሲሆን አዲሱ ማምረቻቸው ስራ ሲጀምር በአመት 150,000 መኪኖችን ሲያመርት ያም በእጥፍ ወደ በአመት 300,000 መኪኖችን ወደ ማምረት ማደግ ይችላል።

በተጨማሪ BYD በአውሮፓ ሃንጋሪ የሚገኘው የመኪና ማምረቻው አውሮፓ ገበያ ላይ ተቀባይነት እንዲያገኝ እንደሚያግዘው እምነት አለው።

#BYD #electric #Europe
@OnluAboutCarsEthiopia
#ዜና

Mercedes በግጭት ወቅት መኪናው ምን ያህል እንደሚቋቋም ለሚያዩበት ፈተና(crush test) በደምብ ዝርዝር እና ግልፅ መረጃን ለማግኘት X-Ray አየተጠቀመ ነው።


የጀርመኑ የመኪና አምራች mercedes መኪኖቹ ግጭትን ምን ያህል እንደሚቋዷሙ፣ደካማ ጎናቸው ምንድን ነው?፣ ለተሳፋሪዎች ደህንነታቸው የተጠበቀ እንዲሆን ምን ይሻሻል የሚለውን ለመመርመር የሚያደርገውን(crush test) X-Rays በመጠቀም ማድረግ ጀመረ።

ይህም (Crash Test) እየተከናወነ እያለ የመኪናው ውስጣዊ ምስሎቹን በX-Rays በቪዲዮ መልክ ማስቀረት የቻለው የመጀመሪያው የመኪና አምራች ሲያደርገው ይህን ለማሳካትም በሰከንድ ውስጥ እስከ 1,000 የ X-Ray ምስሎችን መውሰድ የሚችል፣ከተመለደው X-Rays መሳሪያ በ 1,000 እጥፍ ፈጣን የሆነ እና ለየት ያለ የX-Rays መሳሪያን ተጠቅሟል።

Mercedes እንደተናገረው ከሆነው ይሄን ቴክኖሎጂ ለማበልፀግ ለአመታት ሲሰራ የነበር ሲሆን ለዚህም ዋና ምክንያቱ በአደጋ ጊዜ ውስጣዊ ክፍሎቹ መመልከት መቻሉ እና ክፍሎቹ እንዴትና በምን ያህል ሃይል እንደሚጎዱ ማየት መቻሉ የተሳፋሪውን ደህንነት መጠበቅ የሚችሉ መኪኖችን ማምረት ያስችለዋል።

#mercedes #crashtest
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

ቮልስ ዋገን የስፖርት መኪና ብለን የምንሰይማቸውን (high performance) የኤሌክትሪክ መኪኖችን እያመረተ ነው።


ቮልስ ዋገን GTX trim line ብሎ በሰየመው መደብ ውስጥ የተለያዩ ትልቅ ጉልበት እና ፍጥነት ያላቸው ቅንጡ ልንላቸው የምንችላቸውን መኪኖች እያመረተ ሲሆን በዚህ መደብ የመጀመሪያ መኪና የሆነውን iD 4 GTX 2021 ላይ ለገበያ አቅርቧል።

አሁን ላይ ደግሞ id 3 GTX እና id 7 GTX Tour የሚባሉ ሞዴሎችን ሰርቶ ለገበያ ሊያቀርብ ሲሆን

Id 3 GTX የሚባለው ሞዴል በRWD ብቻ የቀረበ ሲሆን በ 2 የሞተር አማራጭ አለው። ቤዝ ሞዴሉ 280 የፈረስ ጉልበት ሲኖረው የፐርፎርማንስ ሞዴሉ ደግሞ 322 የፈረስ ጉልበት ሲያመነጭ ፍጥነቱ በሰአት ከ 0-100 ኪሎሜትር ለመድረስ 5.6 ሰከንድ ይወስድበታል። የተገጠመለት 79kwh ባትሪውም እስከ 600 ኪሎሜትር የሚደርስ የድራይቪንግ ሬንጅ ይሰጠዋል።

Id 7 GTX Tour በአንፃሩ AWD ሲሆን እስከ 335 የሚደርስ የፈረስ ጉልበትን ያመነጫል። በተገጠመለት 88kwh ባትሪ ፓክም በአንድ ቻርጅ 622 ኪሎሜትር ይጓዛል።

እንደ ሁሉም የGTX መኪና ሞዴሎች ለየት ያለ lighting ሲኖራቸው ውስጥ ላይ ያላቸው ዲዛይንም የስፖርት መኪና ገፅታ የሚሰጣቸውን ቅመም ጣል ተደርጎበታል።

ቮልስ ዋገን ለገበያ የሚቀርቡበትን ቀን በግልፅ ያልተናገረ ሲሆን "በቅርቡ የምናሳውቅ ይሆናል" ብሎዋል።

#Volkswagen #electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Recycle የሚደረግ በቂ የኤሌክትሪክ መኪኖች ባትሪ የለም።


ከትንሽ ጊዜ በፊት ብዙ ሰዎች የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪዎችን recycle ለማድረግ በቂ አቅም ላይ አይደለንም ሲሉ የነበር ሲሆን ABI Research ግን ችግሩ የዚህ ፍፁም ተቃራኒ ነው ሲል ተደምጧል።

በ2030 አሜሪካ ብቻዋን በአመት 1.3 ሚሊየን የኤሌክትሪክ መኪኖችን recycle የማድረግ አቅም ሲኖራት ችግሩ ግን በዛን ጊዜ recycle ለመደረግ ዝግጁ የሚሆኑት የኤሌክትሪክ መኪኖች 341,000 ብቻ ናቸው።

ABI እንደሚያምነው ከሆነ recycle የማድረግ ቢዝነሱ ትርፋማ እንዲሆን በቂ recycle የሚደረጉ ባትሪዎች እስኪኖሩ ድረስ የrecycle ፕሮጀክቱ የሚጀመርበት ጊዜን ገፋ ማድረግ አልያም መጠኑን መቀነስ የግድ ይላል።

#battery_recycle
#ev
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Telo የተሰኘ አዲስ ገና በጅማሮ ላይ ያለ ካምፓኒ በsize mini ልንለው የምንችለውን compact ፒክ አፕ አመረተ።


Telo የ mini cooper መኪናን ዱካ ተከትሎ ባለ 4 በር፣ አምስት ሰው መያዝ የሚችል ፣ከሁላ የእቃው ቦታ ላይ ደሞ 4×8 የሆነ ችፑድን አጋድሞ መያዝ የሚችል የኤሌክትሪክ ፒክ አፕ መኪናን የሰራ ሲሆን ካምፓኒው እንደተናገረው ከሆነው መኪናው  500 የፈረስ ጉልበት ማመንጨት፣ በአንድ ቻርጅ 563 ኪሎሜትር መጓዝ ይዝላል። የመሸጫ ዋጋውም 50,000 የአሜሪካ ዶላር ነው።

ካምፓኒው እስካሁን 7 ሚሊየን ዶላር በላይ ገንዘብን ያሰባሰበ ሲሆን ለጅማሮ አሪፍ የሚባል ካፒታል ቢሆንም በአውቶሞቲቩ ኢንዲስትሪ ላይ እንደሚታወቀው በቢሊየን ዶላሮች መነሻ ካፒታልን ይዘው ወደ ኤሌክትሪክ መኪኖችን ማምረት የገቡ አዲስ ካምፓኒዎች ሳይቀር የገንዘብ እጥረት ያጋጥማቸዋል።

#Telo #electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

ቮልስ ዋገን ID.1 እና  ID.2 ከ25,000 ዩሮ ባነሰ ዋጋ ለገበያ ለማቅረብ እየሰራ ነው።


ቮልስ ዋገን  በዋጋቸው ተመጣጣኝ እና ቀነስ ያሉ የኤሌክትሪክ መኪናዎችን ሰርቶ የአውሮፓ ገበያ ላይ ለማቅረብ እየሰራ ሲሆን በመጀመሪያ 2026 ላይ id 2 የተሰኘውን የኤሌክትሪክ መኪናው ከ 25,000 ዶላር ባነሰ ዋጋ ለገበያ የሚያቀርብ ሲሆን መኪናው የMEB(Modular electric drive matrix) የተሻሻለ ቨርዥን በFWD ነው። እስከ 450 ኪሎሜትር የሚደርስ ድራይቪንግ ሬንጅም ይኖረዋል።

የካምፓኒው ceo የሆነው Thomas schaffer እደተናገረው ከሆነው "ከዚህም በዋጋ ቀነስ ያለ id 1 የተሰኘን መኪና በአመት ልዩነት 2027 ለገበያ  ሚቀርብ ሲሆን የመነሻ ዋጋውም 20,000 ዩሮ ይሆናል።"

በዚህ ላይ አክሎ እንደተናገረው "እንደዚህ አይነት ቅናሽ የሆኑ መኪናዎችን የት ማምረት እንዳለብን ማወቅ economically በጣም ፈታኝ የሆነ ሲሆን በባትሪ ዋጋ ውድነት ምክንያት በተባለው ዋጋ ለገበያ ለማቅረብ ብቸኛው አማራጭ መኪኖቹን በብዛት ማምረት ነው።" ብሎዋል።

#VW#electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Zoox Robotaxi አገልግሎቱን ላስ ቬጋስ ላይ እያስፋፋ ነው


ባለፈው አመት በFoster city ካሊፎርኒያ እና በላስ ቬጋስ መንገዶች አገልግሎቱን መስጠት የጀመረው zoox Robotaxi የተባለው ሹፌር አልባ የAutonomous ታክሲ ሰርቪስ ሰጪ ካምፓኒ አሁን ላይ ላስ ቬጋስ ከተማ ውስጥ የሚሰራበትን ክልል እያስፋፋ ነው

በዚህም ማስፋፊያ ባለ 3 መደዳ መንገዶች ጨምሮ የሚጓዝ ሲሆን ለሹፌር አልባ Autonomous መኪኖች እንደ መደዳ መቀየር እንደ (double right & lefthand) እጥፋቶችን ማድረግ ያለ ውስብስብ ስራዎች ይኖሩበታል።

አሁን ላይ በሁለቱም ከተሞች እነዚህ ሹፌር አልባ ታክሲዎች በመለስተኛ ዝናብ ሰአት እና በምሽት እስከ 70 ኪሎሜትር በሰአት ፍጥረት እንዲጓዙ የተፈቀደላቸው ሲሆን ታክሲዎቹ ግን እስከ 120 ኪሎሜትር በሰአት የሚደርስ ፍጥነትን መጓዝ ይችላሉ።

#Zoox_Robotaxi
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Honda አና Nissan በጋራ የኤሌክትሪክ መኪናዎችን ሊያበለፅጉ ነው።


የኤሌክትሪክ መኪኖችን ማምረት ከባድ እና ብዙ ገንዘብን የሚጠይቅ ስራ ነው። ለዚህም ነው የጃፓፓን ግዙፍ የመኪና አምራች የሆኑት Nissan እና Honda በጋራ አንድ ላይ በመሆን የአውቶሞቲቭ ሶፍትዌር ፕላት ፎርምችን፣ መሰረታዊ የኤሌክትሪክ መኪና ፓርቶችን፣እና ከኤሌክትሪክ መኪና ጋር ተመጋጋቢ የሆኑ ምርቶችን ለማበልፀግ አብረው መስራት የሚችሉባቸውን መንገዶች እየፈለጉ ያሉት።

ባለፈው አመት Honda ከGM ጋር በመሆን በዋጋቸው አነስ ያሉ እና ተመጣጣኝ የሆኑ መኪናዎች ለመስራት አቅደው የነበር ቢሆንም ሁለቱም በየፊናቸው ለጉዳዩ መፍትሄ እናበጃለን ብለው የወሰኑት። ግን አሁን ላይ Honda ለብቻው መስራት መወሰኑ ጥሩ ሃሳብ የነበረ አለመሆኑን አውቆ የወሰነ ይመስላል።

#Nissan #Honda #electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
#Ad

ከ 1 ሚሊየን ብር በታች አሪፍ መኪና አገኛለሁ?

የተለያዩ መኪኖቻችሁን በሁሌመኪና በማስተዋወቅ መሸጥ እና ማከራየትም ትችላላችሁ

እንዲሁም ከ 1 ሚሊየን ብር በታች የተለያዩ መኪኖችን ከሁሌመኪና ላይ ታገኛላችሁ

በ 0911663121 ላይ በመደወል ወይም ቴሌግራም ላይ @Hulemekinaadmin ላይ መኪኖቻችሁን በመላክ 300 ብር ብቻ በመክፈል ማስተዋወቅ እና መሸጥ ትችላላችሁ ::

@hulemekina
#ዜና

Nio የባትሪ ቅያሪ(swapping) ሰርቪሱ ላይ ቅናሽ አረገ።


የቻይናው የኤሌክትሪክ መኪኖች አምራች የሆነው Nio የሚያመርታቸው መኪኖች ከሌሎች የኤሌክትሪክ መኪናዎች በተለየ ቻርጅ ሲያልቅባቸው ከ30 ደቂቃ እስከ 1 ሰአት ቆመው ቻርጅ አይደረጉም ይልቁንስ አቅራቢያቸው ወዳለ የባትሪ መቀየሪያ (swapping) ስቴሽን በመሄድ ከ3 ደቂቃ ባነሰ ጊዜ ውስጥ ቻርጅ ያለቀውን ባትሪያቸው ቻርጅ በተደረገ ባትሪ ቀይረው ጉዞአቸውን መቀጠል ይችላሉ።     

ይሄንንም አገልግሎት ለመጠቀም የባትሪ subscription ክፍያ ሲኖረው አሁን ላይ ገበያ ውስጥ ተፎካካሪ ለመሆን ቅናሽ አድርጎበታል።

ስታንዳርድ ሬንጅ ለሆነ ባትሪ በፊት በወር ከሚያስከፍልበት 35 ዶላር ቀንሶ 101 ዶላር በወር ያደረገው ሲሆን ሎንግ ሬንጅ ለሆነው ባትሪ ደግሞ 77 ዶላር ቅናሽ አድርጎ አሁን ላይ 156 ዶላር በወር በመክፈል ብቻ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን እንዲቻል አርጎዋል። በተጨማሪ ለአዲስ እና ለነባር ደንበኞቹ ነፃ 60 የswapping ሰርቪስን ሰጥቶዋል።

Nio ይሄን የባትሪ subscription አገልግሎቱን በ2020 ላይ የጀመረው ሲሆን አሁን ላይ 100,000 በላይ ተጠቃሚዎች አሉት።


#Nio #Battery
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

ቴስላ ገበያው ላይ ያለውን ፉክክር የተለያዩ የማስታወቂያ መንገዶችን በመጠቀም በልጦ እየተገኘ ነው።


የኤሌክትሪክ መኪና አምራቹ ቴስላ መኪኖቹን ለመሸጥ የሽያጭ መጠኑኑ ለስፋት የተለያዩ የማርኬቲግ ስትራቴጂዎችን እየተጠቀመ ሲሆን ከእነዛ መካከል በዋነኝነት የተለያዩ የማስታወቂያ መንገዶችን መጠቀም ነው።

ቴስላ በቅርብ ለገበያ አቅርቦት በቅርፁም ሆነ በገፅታው ለየት ያለው ሳይበር ትራክ መኪናው በተነዳባቸው ጎዳናዎች ሁሉ የእይታ መርከዝ በመሆን የተመልካችን አይን መስረቁን እንደቀጠለ ነው ታዲያ ቴስላ ይሄኑ ጉዳይ ሲያጤንበት ቆይቶ ለጥቅም ለማዋል አንድ መላ ዘይዷል። ሌሎች የመኪና ሞዴሎቹን በዚህ መኪና ማስተዋወቅ።

ይሄ ማለትም ሳይበር ትራክ መኪናን እንደተንቀሳቃሽ ቢልቦርድነት መጠቀም፤ ሞዴል Y መኪናውን በመስታወት በተሸፈነ ተጎታች ክፍል ላይ መስቀመጥ በሳይበር ትራክ መኪና እየተጎተተ በከተማ ውስጥ እንዲዞር ማድረግ። በተጨማሪ እንደ አለም አቀፍ አየር ማረፉ ያሉ እንቅስቃሴ የሚበዛባቸው ቦታ ላይ የቢልቦርድ ቦታዎችህን እየተከራየ ፣የተለያዩ ቪዲዮዎችን እየሰራ Youtube ad ላይ እያስተዋወቀ  ነው።

ቴስላ በሞዴል Y እና ሞዴል 3 ያሉት የመኪና ሞዴሎቹ ላይ የ2,000 ዶላር ያደረገ ሲሆን እንዲህም ሆኖ በአውሮፓ እና በአሜሪካ የኤሌክትሪክ መኪና ገበያ ላይ ያለውን ሽያጭ እየመራ ነው።

#Tesla #cybertruck
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Hyundai እና Kia በአለም ዙሪያ 770,000 የኤሌክትሪክ መኪናዎቻቸውን ወደ ካምፓኒው recall አደረጉ


ታዋቂዎቹ የመኪና አምራቾች Hyundai እና Kia በደቡብ ኮሪያ 170,000፣ በተቀረው የአለም ክፍል ላይ ደግሞ 600,000 የኤሌክትሪክ መኪና ሞዴሎቻቸው ላይ ነፃ ማስተካከያን ለማድረግ ጥሪ ያደረጉ(recall) ሲሆን ለዚህም ምክንያት እንደ Ioniq 5, Ioniq 6, Genesis GV60, and Kia EV6 ያሉ የኤሌክትሪክ መኪኖቻቸው ላይ በተደጋሚ የ ICCU ክፍላቸው ላይ ብልሽት እያጋጠማቸው ስለሆነ ነው።

መኪኖቹ ከዚህ የባትሪ ሲስተም ችግር ጋር ተያይዞ ጉዞ እያረጉ በድንገት ሙሉ ሃይላቸው የሚቋረጥ ሲሆን በICCU መበላሸት ምክንያትም over current እየተፈጠረ Transistorዎቹን በማቃጠል የ12v ባትሪው ቻርጅ እንዳያረግም ያረገዋል።

በዚህ የጥራት መጓደል ችግር ምክንያ የአሜሪካው የመንገድ ደህንነት ባለስልጣን (NHTSA) በሁለቱ የመኪና አምራቾች በተመረቱ መኪኖች ላይ ይፋዊ ምርመራንም ከፍቶዋል።

#Hyundai #kia #electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

በነገው እለት (March 19) BYD አዲስ የኤሌክትሪክ ሞዴል መኪና በ 11,000 የአሜሪካን ዶላር መነሻ ዋጋ ይለቃል


BYD የኤሌክትሪክ መኪና ምድብ ውስጥ አዲስ ያካተቱን Yuan UP ሞዴል ለገበያ ያወጣሉ :: መነሻ ዋጋውም ከ 11,000 ዶላር ወይም ከ 79,800 ዩአን ሲሆን ከ BYD Destroyer 05 Honour Edition ጋር ተመሳሳይ ዋጋ ነው ያለው ::

Yuan UP ከ Song L ዲዛይን ጋር ተቀራራቢ አድርገው የሰሩት መኪና ነው :: ይህንን መኪና የሰሩት ለከተማ ውስጥ ጉዞ አስበው ነው ::

Yuan UP በ 2 የሞትር አማራጭ ሲገኙ በ 70 kW(Kilowatt) and 130 kW (Kilowatt) ነው :: በባትሪ አማራጭም ሲለያዩ ከ 32 kWh እስከ 45.1 kWh ባትሪ ፓክ ሲኖራቸው በአንድ ቻርጅ ከ 301 እስከ 401 ኪሎሜትር መጟዝ ይችላሉ :: እስኪ ነገ ሲወጣ ደግሞ በደንብ እንዳስሰዋለን ::

#BYD #electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

የኤሌክትሪክ መኪኖች ባትሪ አምራቹ የCATL ገቢ የአደጋ የማስጠንቀቂያ ምልክቶችን እያሳየ ነው።


በቻይና ሚገኘው የአለም ትልቁ የኤሌክትሪክ መኪኖች ባትሪ አምራች የሆነ CATL ያለፈው አመት ገቢውን ሪፖርት ያቀረበ ሲሆን ያስገባው ገቢ የሚደነቅ ቢሆንም የማስጠንቀቂያ ምልክቶች ይታዩበታል።

የለቀቀው የገቢ ሪፖርት ላይ
55.6 ቢሊየን ዶላር የገቢው በ22% እድገት ሲያሳይ
የ6.1 ቢሊየን ዶላር የተጣራ ትርፉ በ43% እድገት አሳይቶዋል

ይሄ እድገት የመጣው ቻይና ላይ ባለው ጠንካራ የኤሌክትሪክ መኪኖች ሽያጭ ቢሆንም አንድ ሶስተኛው የCATL ገበያ ከባህር ማዶ ነው።
እንደ Tesla,Ford, BMW, Daimler, Sellantis, Volkswagen, Hyundai እና Honda ላሉ የመኪና አምራቾች ባትሪን ያቀርባል።

4ኛው እሩብ አመት ላይ ግን ነገሮች ያን ያህል ጥሩ አልነበሩም። ከሚያስገባው ገቢ ላይ በ1% የቀነሰ ሲሆን የምርት ሂደቱ ከ83% ወደ 70% ወርዶዋል።

#CATL #Battery #electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

NTSB በ BlueCruise በተባለው የፎርድ driving assistance ላይ ይፋዊ ምርመራ ከፈተ።


National Transportation Safety board (NTSB) የford mustang mach E መኪናን ባሳተፈው አደጋ ምክንያት bluecruise በተባለው መሪውን ለቀን መኪናው እራሱን በራሱ እያሽከረከረ መጓዝ የሚያስችለን የford driving assistance ሶፍትዌር አደጋው በደረሰበት ወቅት አገልግሎት እየሰጠ ነበር ወይስ አይደለም(የአደጋው መንሴ እሱ ነው?) የሚለውን ለማጣራት ይፋዊ ምርመራ ተጀመረ።

አደጋው የተከሰተው San antonio በምትባለው በቴክሳስ ግዛት ውስጥ በምትገኝ ከተማ ሲሆን Ford mustang mach E መኪና ቆሞ ከነበረን Honda CRV መኪናን ከኋላ መቶ በመግጨት በCRV ውስጥ የሚገኘው አሽከርካሪ ህይወት እንዲያልፍ ምክንያት ሆኗል።

የፎርድ ቃል አቃባይ እንደተናገረው ከሆነ ስለ አደጋው እንዳወቁ ለNTSB መረጃ የሰጡ እንደሆነ እና በምርመራው ላይ እንደሚተባበሩ ገልፆዋል።NTBSም የቅድመ ምርመራውን ሪፖርት በ30 ቀናት ውስጥ ይፋ የሚያደርግ ይሆናል።

በእንደዚህ አይነት የdriving assistance ሶፍትዌሮች ምክንያት አደጋ ሲደርስ ትልቅ የሚዲያ ሽፋን የሚሰጣቸው ሲሆን NTSB ስለአደጋ መንስኤ ምርመራ ከማድረጉ በተጨማሪ ምን ያህል አደጋዎችን ከመከሰት እንደተከላከሉ ጭምር ጥናትን ቢያደርግ መልካም ነው።

#Ford #Mache #electric
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Vinfast የአውቶሞቲቭ ኢምፓየር እያስፋፋ ነው።

የ vinfast መኪና መስራች የሆነው ቬትናማዊው ቢልየኔር Pham Nhat Vuong  የራሱን የአውቶሞቲቭ ኢምፓየር እየገነባ ነው። ከvinfast መኪና በተጨማሪ በሃገረ ቬትናም green sm ብሎ የሰየመው የራሱ የታክሲ ድርጅትን የከፈተ ሲሆን አሁን ላይ ደግሞ V green የተባለ አለም አቀፍ የኤሌክትሪክ መኪኖች ቻርጅ ማድረጊያ ኔትዎርክ እየዘረጋ ነው።

በመጪው 2 አመታት ውስጥ የቻርጂንግ ስቴሽኖቹን ቁጥር  ለመጨመር እና ተደራሽነታቸውን ለማስፋት ወደ 400 ሚሊየን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ ኢንቨስት ሊያደርግ ነው።

ግን እስካሁን ባለው Vinfast በሌሎቹ ስራዎቹ በጣም ጥገኛ የሆነ ሲሆን vgreen የተባለው ቻርጅ ስቴሽንን የሚከፍተው vinfast መኪኖቹን በብዛት በሚሸጥባቸው ቦታዎች ብቻ ነው። ለሌሎች የመኪና ብራንዶች አገልግሎቱን መስጠት የሚጀምረው ከ5 አመታት በኋላ ነው። በተጨማሪ vinfast ባለፈው አመት ላይ ወደ 35,000 መኪኖችን የሸጠ ሲሆን ከዚህ የሽያጭ ቁጥር ውስጥም 70%ቱን የሚይዘው Green sm ለተባለው ለራሱ የታክሲ ድርጅት ነው የሸጠው።

ገበያው ላይ ለረዥም ጊዜ ለመቆየት የግድ አዳዲስ ደንበኞችን ማፍራት ይጠበቅበታል።

#vinfast #Vietnam
@OnlyAboutCarsEthiopia
2024/09/23 06:35:07
Back to Top
HTML Embed Code: