Telegram Web Link
#መልካምነት

አንድ የ 24 አመት ወጣት ከሚጓዝበት ባቡር አሻግሮ በሚያያቸዉ ነገሮች ተገርሟል፡፡

ከዛም ጮክ ብሎ "አባቴ ፥ ዛፎቹን እያቸዉማ ወደኀላ እየሆዱኮ ነዉ! "

ሲለዉ አባትየዉ #ፈገግ አለ ፤ በቅርብ ያሉ ተሳፋሪዋች ግን የ 24 አመት ወጣቱን በሀዘን ስሜት እንደ ልጅና #ህመምተኛ ተመለከቱት፡፡


ወጣቱ በድንገት በመደነቅ ደግሞ "አባቴ ፥ ተመልከት ደመናዉ እኮ አብሮን እየሄደ ነዉ!" አለዉ፡፡

አባትየዉ አሁንም ልጁን #በፈገግታ ተመለከተዉ ፤ በቅርብ

ያለ አንድ ሰዉዬ ግን ወጣቱ በሚያሳየዉ የልጅ ፀባይ አላስችል ብሎት በንዴት ...

"ለምን ልጅህን ወደ ጥሩ የአዕምሮ ሆስፒታል አትወስደዉም?" አለዉ ለወጣቱ አባት፡፡

አባትየዉ በአንዴ ፊቱ በሀዘን ተሞላ ፣ አይኖቹ እንባ እየተናነቀዉ

በእርጋታ እንዲህ ብሎ መለሰለት..."ሆስፒታል

ወስጄዋለሁ... ፥ አሁን ራሱ ከዛ እየተመለስን ነዉ ፥ ልጄ ከልጅነቱ

ጀምሮ ማየት አይችልም ነበር ለወራት ከታከመ በኀላ ዛሬ ነዉ

ታክሞ አይቶ ከሆስፒታል የወጣዉ" አለዉ ፡፡

#ትምህርት

በዚህ ምድር እያንዳንዱ ሰዉ የራሱ የሆነ ታሪክ አለዉ፡፡ የሰዉን ታረክ ሳናዉቅ ሰዉ ላይ ለመፍረድ አንቸኩል፡፡ ምክንያቱም እዉነታዉን ስንሰማና ስናዉቅ ሁሌ የተናገርነው ይቆጨናልና፡፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

#ለሰዋች_የደስታ_ምንጭ_መሆን_ባንችል_የሀዘን_ምክንያት_አንሁን

#አላህ_ሀገራችንን_ይጠብቅልን_ሰላም_ያርግልን

መልዕክቱ የተመቸዉ ደግሞ #share በማድርግ ሌሎችን ያስተምራል !
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

Join 👇 here
@ONLYFORTRUTHERSJ
@ONLYFORTRUTHERSJ
@ONLYFORTRUTHERSJ
Aselamuwaleykim 🙌
Hey brothers and sisters in Islam😎
Inshallah let's all get ready to fast tommorow 😋and be strong in making Dua 🤗
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🔗::::;;ያልተፈታ ህልም::::::::🔗

ክፍል ::::::::::1⃣


እኔም እንደ አብዛኛው ሰው ተፈጥሮን አደንቃለሁ ዛሬ በጠዋት ነው የነቃሁት ቀኑ ደስ ይላል ፀሀይ በትንሹ እንደመውጣት እያለች ነው እኔም በትንሹ የወጣችውን ፀሀይ ለመሞቅ ፀሀይዋ ወደ አለችበት አቅጣጫ በእንጨት ከተሰራው ትንሹ ወንበር ላይ ተቀምጬ ፀሀይ እየሞኩ ነው፡፡ የተወሰነ እንደሞኩኝ ሰውነቴ መነቃቃት ሲጀምር ከ እቤት በኩል በተደጋጋሚ ሰሚር .... ሰሚር እያለች በምትጠራኝ በ እማዬ ድምፅ ነበር ከተቀመጥኩበት የተነሳሁት፡፡ ወደ እቤት ስገባ እማዪ ቁርስ ሰርታ ጨርሳ አቀራርባ ነበር አንድበላ የጠራችኝ በዛች በደሳሳ ጎጆ ውስጥ ከ እኔ እና ከ እማዪ ወጪ የሚኖር ሰው የለም የቤታችን ግቢ አነስ ያለና ጠባብ የሚባል አይነት ነው የዛሬን አያርገውና ሙና ይህቺ ጠባብ ግቢያችን ፅድት አድርጋ ትይዘው ስለነበር ሰፊ ግቢ ካላቸው ሰዎች በተሻለ ያምር ነበር ሙኒ አበባ መትከል እነሱን መንከባከብ በጣም ያስደስታታ ነበር በዚች በጠባብ ግቢ ላይ በግራና ቀኝ በጣሳ በጣሳ ተደርገው የተቀመጡ አበባዎች አሉ በእርግጥ አበባዎቹ ለግቢው ውበት ቢሰጡትም በዛ ከተባለ አምስት ሰው ብቻ የማሚያቆም ቦታ ነው ያለው ስለግቢያችን እያወራሁ አደከምኳቹ አይደል እና ካቆምኩበት ልቀጥልና እማዬ የሰራችውን ቁርስ ድብን አድርጌ ከበላሁ በኃላ የበለሁበትን እማዬ እንድታነሳው ትቼላት ተነሳሁ በነገራችን ላይ እማዬ ምንም አይነት ምግብ ብትሰራ ሁሌም ቢሆን እየጣፈጠኝ ጥርግ እድርጌ ነው የምበለው እንዲህ ሲሆን እማዬን ደስ ይላታል ለ ነገሩ ባይላትም እማዬ የሰራችውን ምግብ መተው አያስችለኝም ፡፡
.
ከጓደኞቼ ጋር በጠዋት ለመገናኘት ተነጋግረን ስለነበር ቁርስ ከበላሁ በኀላ ፀጉሬን ወደ ሳሎን ቤት ከመግቢያው በር ጎን በተንጠለጠለው መስታወት ሳየው ቆሽሿል የብርድ ልብስ የተነጫጨ ስላለው ጓደኞቼ ጋር ከመሄዴ በፊት ታጥቤ ልፈርዘው ብዪ ወደ መኝታ ቤታችን ገባሁ ....
ሁል ግዜ እኔ የምጠቀምባቸውን እቃዎች በስርአቱ አላስቀምጥም እማዬ ሁል ግዜ ነው የምትቆጣኝ አቃህን በስርአቱ አስቀምጥ እያለች ትናገረኛለች ግን ልምድ ሆኖብኝ ነው መሰል አንድም ቀን በስርአቱ አስቀምጬ አላውቅም ፡፡ ዛሬም ጄሌን የት እንዳስቀመጥኩት አላውቅም መኝታ ቤቱን እየዞርኩ ፈለኩኝ ግን አላገኘሁትም ወደ ሳሎን ቤት ሄጄ እማዬን ስጠይቃት እንዳላየችው ነገረችኝ ምን ላድርግ እንዳልተወው ፀጉሬ ቆሽሿል ከታጠብኩ ደግሞ የግድ ጄል መቀባት አለብኝ የኔ ፀጉር ጄል ካልተቀባሁት በጣም ነው የሚያስጠላው ከመፈለግ ውጪ ሌላ ምርጫ ስላልነበረኝ በድጋሚ ለመፈለግ ወደ መኝታ ቤት ገብቼ መፈለጌን ተያያዝኩት አሁንም ላገኘው አልቻልኩም ሁሉም ቦታ ፈልጌ ሳጣው በቃ ልተወው ብዬ ልወጣ የመኝታ ቤቱ በራፍ ላይ ስደርስ ለካ አልጋው ስር አልፈለኩም ብዪ ተመልሼ ወደ ወስጥ ገባሁ በጉልበቴ ተንበርክኬ ከወገቤ ዝቅ ብዬ እጄን ወደ አልጋው ስር ልኬ ጄሌን ስፈልግ እጄ የሆነ በፌስታል የታሰረ እቃ ላይ አረፈ በእጄ ስነካው ትንሽ ጠጠር ያለ ነገር እን መፅሀፍ ነገር ይመስላል ምን እንደሆነ ለማወቅ ስለፈለኩ ፌስታሉን በእጄ እየጎተትኩ ከ አልጋው ሰር አወጣሁት ፌስታሉ አቧራ ብቻ ነው አቧራውን በእጄ እንደ ማራገፍ አድረጌ የተቋጠረውን ፌስታል ለመፍታት መታገል ጀመርኩ በጣም ጠብቆ ስለታሰረ በቀላሉ መፍታት አልቻልኩም ታግዬም ቢሆን በመጨረሻ ፈታሁት ፌስታሉ ውስጥ ሁለት መካከለኛ የሆኑ የህይወት ታሪክ መፃፊያ (ዲያሪ) ደብተሮች አሉ የማን ነው ብዪ ለመክፈት ስሞክር በቁልፍ ተቆልፎዋል ፡፡ መክፈት አልችልም ማለት ነው ግን የሰው ሚስጥር ማየት ምን ያደርግልኛል ብዬ እንደመጀመሪያው ፌስታል ውስጥ ከተትኩት እውነት ለመናገር የማን እንደሆነ ለማወቅ እና ለማየት በጣም ጓጉቻለሁ ግን ተቆልፋል ሲያናድ ቁልፉ ባይኖር ኖሮ አነበው ነበር ቁልፋን ለመስበር ስታገል እማዪ ከመጣች ስለምትቆጣኝ ነው የተውኩት እማዪ ከቤት ስትወጣ እሰብረዋለሁ ብዪ እዛው አልጋው ስር መለስኩት ፡፡ አገኘኃው እንዴ አለችኝ እማ ሳሎን ቤት ውስጥ ሆና እኔ ምን እየፈለኩ እንደነበር እራሱ እረስቼዋለሁ ሀሳቤ እንዳለ ፌስታሉ ላይ ስለነበር ምኑን ብላትስ ለእማዬ.....
... አንተ ቀልበ ቢስ ምኑን ትለኛለህ እንዴ ልትፈልገው የገባኧውን ነዋ... ስሙ ምን ነበር ይሄ ለ ፀጉርህ የምትቀባውን ስትለኝ ጄል ልፈልግ እንደ ገባሁ አስታወስኩ እውነትም ቀልበ ቢስ ነኝ..
.
... አንዳላገኘሁት ለእማዪ ነግሪያት መኝታ ቤቱን ለቅቄ ወጣሁ፡፡ አማራጭ ስላጣሁ ፀጉሬን በጠር በጠር አድርጌ በትንሽዬ ቅባት ነካክቼ ወጣሁ ጓደኞቼን አግንቼ ትንሽ ካወራን በኃላ እኔ ስለደበረኝ ወደ ቤት ተመለስኩ እንደ አጋጣሚ ሆኖእቤተት ስደርስ እማዬ እቤት አልነበረችም ፡፡ ቤቱ አልተስተካከለም እነንዳደርንበት ነበር የእማዬን ያህል ባይሆንም ያቅሜን ያህል እያስተካከልኩ ሳለሁ ያ የቅድሙ ፌስታል አስታወስኩ የማስተካክለውን ቤት ትቼ ወደ መኝታ ቤት አመራሁ ፌስታሉን ካስቀመጥኩበት አንስቼ ወስጡ ያለውን ዲያሪ አወጣሁ ፡፡ ቁልፋን ለመክፈት ያሰብኩትን ያህል አላስቸገረኝም በቀላሉ ተከፈተልኝ የዲያሪው የመጀመሪያ ገፅ ላይ በትልቁ በ አልበም ሳያዝ የተለጠፈ የወንድ ፎቶ አየሁ ልጁ ለ አይኔ አዲስ አልነበረም ግን የሱ ፎቶ ያለበት ዲያሪ እኛ ቤት ውስጥ ምን ይሰራል ?እያልኩ ቀጣዮን ገፅ ገለፅኩ በቀጣዪ ገፅ በስተ ግራ በኩል ዋሌት ፎቶ ተለጥፎዋል ፎቶው የሙና እና የመጀመሪያ ገፅ ላይ የለው ልጅ አብረው የተነሱት ፎቶ ነው፡፡ ሙና ማለት የ አክስቴ ልጅ ናት እኛ ቤት ትኖር ስለነበር አብዛኛው እቃዎቿን እኛ ቤት ነበር የምታስቀምጠው፡፡
ሙና ሁሉም ነገር ሳይበዛ ሳያንስ የተሰጣት ይመስላል ቆንጆ የምትባል አይደለችም ግን አታስጠላም የ ሆነ የሚስብ ነገር አላት ቁመቷ እረጅም አይደለችም አጭርም አትባልም መካከለኛ ቁመት ያላት ናት የፊቷ ከለር ቀይ የሚባል አይደለም ጥቁርም አይደለችም ጠየም ያለች ቸኮሌት ከለር ነገር ነች ፡፡
.
ሙና እኛ ቤት ውስጥ ከ አስር አመት በላይ ኖራለች ፡፡ግን እንዴት ዲያሪ ስትፅፍ አይቻት አላውቅም ? ሙና የአክስቴ ልጅ ትሁን እንጂ ለ እኔ ልክ እንደ እህት ነበረች መወለድ ቋንቋ ነው አይደል የሚባለው ......
ዲያሪውን ማንበብ ፈልጊያለው ግን ትንሽ ከበደኝ የግሏ ሚስጥር ነው ብዬ ዲያሪውን ወደ ነበረበት መልሼ ወደ ፅዳቴ ተመለስኩ እንደ ነገሩ ቤቱን አፀዳድቼ ጨረስኩ ፡፡ያው እንደምታውቁት ግቢያችን መስተካከል የሚያስፈልገው አይነት አይደለም የወዳደቁትን አቃዎችን አነሳስቼ ወደ ሳሎን እንደገባሁ በስተ ግራ በኩል ባለው ከፍ ተደርጎ በተሰራው የ እንጨት ወንበር ላይ ተቀምጬ ትንሿ ስልኬን ከኪሴ አውጥቼ ካንዲ ክረሼን መጫወት ጀመርኩ ግን ቀልቤ እንዳለ ዲያሪው ጋር ነው ቆይ ግን ባነበው ምን ችግር አለው ኧረ ግን የሰውን ሚስጥር ማንበብ ይደብራል እያልኩ ከራሴ ጋር ማውራት ጀመርኩ በመጨረሻም አንድ ውሳኔ ወሰንኩ የ እህቴ አይደል ባነበው ችግር የለውም ብዪ ዲያሪውን ከመኝታ ቤት ወደ ሳሎን ቤት ይዤው መጣሁ በኤል ሼፕ ቅርፅ በተነጠፈው ፍራሽ መሀል ተቀምጬ ማንበብ ጀመርኩ.....

፡ ይ.....ቀ......ጥ....ላ.....ል

@ONLYFORTRUTHERSJ
@ONLYFORTRUTHERSJ
Audio
ስኬት በርግጥም ልፋትን ይጠይቃል፡፡
፨፨፨፨፨፨
፨ ጉንዳን ካሰበችው ለመድረስ ሺ ጊዜ ከምሰሶው ላይ ትወድቃለች፤ትነሣለች፡፡

፨ ንብ ጣፋጩን ማር ለመጋገር ሚሊዮን ጊዜ አበቦች አካባቢ ትመላለሣለች፡፡

፨ ወፍ መኖርያ ጎጆዋን ለመሥራት ማልዳ ወጥታ አምሽታ ትገባለች፡፡

አዎን - ስኬት ትኩረትንና ትእግስትን ይጠይቃል… ያለ ጥረትም ከስኬት ጫፍ አይደርሰም፡፡ ልብ በሉ፡-

፨ ተኩላ ያለመውን ለማደን ቦታና አቅጣጫ ቀያይሮ ያደባል፣

፨ ድመት የተመኘችውን ለማግኘት በትእግስት ትጠባበቃለች፤

፨ አንበሣ ያቀደውን ለመያዝ በአንክሮ ይከታተላል፡፡


ስኬትና ውጤት ያለ እንቅስቃሴ አይገኝም፡፡ አስተዉሉ …

፨ ነብር ካልተወረወረ አይዝም፣
፨ ቀስት ካልተስፈነጠረ አያድድንም፣
፨ ሰይፍ ካልተሠነዘረ አይገድልም፡፡


ተንቀሣቀስ አትተኙ…
፨ ለረጅም ጊዜ የተኛ ውሃ ይሸታል፡፡
፨ በአንድ ቦታ ላይ ለዘመናት የቆየ ድንጋይ አንድ ቀን ይፈለጣል፡፡

፨ እንቅስቃሴ በረከት አለው፡፡
፨ በሥራ ዉስጥ ለውጥ አለ፡፡
፨ ሥራ ፈት ዋጋ የለዉም ዜሮ ቁጥር ነው፡፡


፨ ሽቶ ጫን ጫን ሲሉት ጥሩ ሸተተ፡፡
፨ ሰንደል ሲያቃጥሉት አከባቢውን አወደ፡፡
፨ የሰው ልጅም በችግሮች ሲደበደብ ካልሆነ ጥሩ ጠረን አይወጣውም፡፡

ወዳጆቼ !
መከራ፣ ፈተና ችግርን አትጥሉ፡፡
###
ከመተኛቴ በፊት ይህቺን ምክር ያዙ-

# ዱኒያን የታገላት ነው የሚጥላት፡፡
# ዓለምን እልህ የተጋባ ነው የሚያሸንፋት፡፡
# ጀነትን በመንገዷን የፀና ነው የሚያሳካት፡፡
****

@ ህይወት በየቀኑ ሩጫ ናት፡፡
@ የስኬት ገበያ ሁሉ ከባድ ውድድር አለው፡፡
@ መጀመሪያ የጨሠ ነው ኋላ ብርሃን የሚወጣው፡፡
@ ዛሬ የደከመ ነው ነገ የሚያርፈው፡፡
፨፨፨፨፨፨፨

“በረካ” ከተሠኘው መጽፌ ነው የጋበዝኳችሁ፡፡
መልዕክቷን ለሌሎች አካፍሉ፡፡
ደህና እደሩ፡
አላህ ያሰብሽውን ይሠጥሻል! ደስም ይልሻል!
💛💛💛💛💛💛💛💛💛💛💛
ዲኔ ላይ ደህና ነኝ፡፡ መልክ አለኝ ባይባልም አልከፋም፡፡ በባህሪዬ ጥሩ ነኝ ብዬ አስባለሁ፡፡ ከቤተሰብ ሳልርቅ ነው ያደግኩት፡፡ የልጅነት ጊዜዬ አልፎ ወጣትነት መጣ፡፡ እንደማንኛዋም ሴት ትዳር አሰብኩ፡፡ ግና በማላውቀው ምክንያት ድርሻዬ ዘገየብኝ፡፡ ለጋብቻ የሚጠይቀኝ ጠፋ፡፡ ከኔ በኋላ የተወለዱ የቤተሰብም፣ የዘመድም፣ የሰፈርም ልጆች አንድ በአንድ አገቡ፡፡ ወለዱ፡፡ ልጆቻቸዉም አደጉ፡፡ ሳላስበው 34 ዓመት ሆነኝ፡፡ ዕድሜዬን ሳስታውሰው ደነገጥኩ፡፡ ብቻዬን ቆሜ የቀረሁ እስኪመስለኝ ድረስ ተሠማኝ፡፡
፨፨፨
የሆነ ጊዜ ከቅርብ ዘመድ የሆነ አንድ ወጣት ለጋብቻ ጠየቀኝ፡፡ ፈቃደኝነቴን ገለጽኩ፡፡ ሁለት ዓመት ይበልጠኛል፡፡ ዲኑም ፀባዩም ቆንጆ ነው፡፡ ደስ አለኝ፡፡ ከሀሳቤ የተገላገልኩ መሰለኝ፡፡ ቤተሰብም ደስ አለው፡፡
.
ኒካሕ ለማሰር ተዘጋጀን፡፡ አንዳንድ ጉዳዮችን ለመጨረስ ብሎ መታወቂያዬን ይዞ ሄደ፡፡
.
.ከሁለት ቀን በኋላ ስልክ ተደወለልኝ፡፡ እናቱ ነበረች፡፡ እንደምትፈልገኝ ነገረችኝ፡፡ ምን ይሆን ብዬ እየበረርኩ ሄደኩኝ፡፡ ቤታቸው ገባሁ፡፡ ጥቂት ካወራን በኋላ መታወቂያዬን እያሳየችኝ እዚህ ላይ የተጠቀሰው የትውልድ ቀኔ ትክክል ስለመሆኑ ጠየቀችኝ፡፡ አዎን ትክክል ነው አልኳት፡፡
እንግዲያዉስ አንች አርባ ተጠግተሸል መውለድ አትችይም፡፡ አለችኝ፡፡ 34 ዓመቴ እኮ ነው እንዴት አልችልም አልኳት፡፡
አይ … አንች ሰላሳ አልፎሻል እኔ ደግሞ ልጅ አይደለም ገና የልጅ ልጅ ማየት እፈልጋለሁ አለች፡፡ ጋብቻው እንዲሰረዝ ሞገተች፡፡ ልጇንም አሳመነች፡፡ ለቤተሰቤ ምን እንደምላቸው እያሰላሰልኩ ተስፋ ቆርጬ ወደቤቴ ተመለስኩ፡፡
፨፨
ቀናት አለፉ፡፡ ድፍን ስድስት ወራትን በሐዘን አሳለፍኩ፡፡ ረጃጅም ቀንና ሌሊቶችን ስብሰለሰል ከረምኩ፡፡ በር በሩን ባይ እኔን ብሎ የሚመጣ ለኔ የተፃፈ ባል ጠፋ፡፡ ብቸኝነት፣ ባይተዋርነት፣ አጥንት ድረስ ዘልቆ ተሰማኝ፡፡
አባቴ ሁኔታዬን ይከታተላል፡፡ ስለኔ አብዝቶ ተጨነቀ፡፡ በመጨረሻም ከወንድሜ ጋር ለዑምራ እንድሄድ መከረኝ፡፡ ሂጂና በተከበረው የአላህ ቤት አጠገብ ብሶትሽን ተናገሪ፤ የዉስጥሽን የዉስጥ አዋቂ ለሆነ ጌታ ተንፍሺ አለኝ፡፡
ዑምራ ሄድኩኝ፡፡ የአላህ ቤት ከዕባ ፊት ቁጭ ብዬ ረጅም ዱዓ አደረግኩ፡፡ ለርሱ የዉስጥ ስሜቴን ሁሉ አንሾካሸኩ፡፡ አለቀስኩ፤ ፈረጄን ያቀርብልኝ ዘንድ ተማፀንኩት፡፡
፨፨
የሆነ ቀን ሱንና ከሰገድኩ በኋላ ጥቂት ቁጭ አልኩ፡፡ ከኋላዬ አንዲት ሴት ባማረ ድምጽ ቁርኣንን ታነባለች፡፡
“የአላህ ችሮታ ብዙ ነው፡፡” የሚል ትርጉም ያለዉን የቁርኣን አንቀጽ ስታነብ ቀልቤ በተለየ መልኩ ወደዚያ ተሳበ፡፡ በቁርኣን ዉስጥ የዚህ ዓይነት አንቀጽ ስለመኖሩ ገረመኝ፡፡ አላህ በችሮታው ያስበኝ ዘንድ ተማፀንኩት፡፡
ሴትዮዋ አየችኝ፡፡ ምን እንደሆንኩ ጠየቀችኝ፡፡ ሁኔታዬን ነገርኳት፡፡
አብሽሪ አለችኝ “ አብሽሪ አላህም ያሰብሽዉን ይሠጥሻል፤ ኢንሻአላህ ደስም ይልሻል፡፡” አለችኝ፡፡
፨፨
ዑምራውን አጠናቅቄ ተመለስኩ፡፡ ድንገት የረጅም ጊዜ ጓደኛዬንና ባሏን በዐይሮፕላን ማረፊያው አገኘኋቸው፡፡ የባሏን ጓደኛ ለመቀበል እየጠበቁ ነበር፡፡ ሰላምታ አቅርቤላቸው ትንሽ እንዳወጋን ጓደኛቸው ደረሰና ተሰነባበትን፡፡ ወዲያው አባቴ ደርሶ ተቀበለኝ፡፡
፨፨
ጥቂት ቀናት አለፉ፡፡ አሁን ከበፊቱ በተሻለ ልቤ በመጠኑ ሰክኗል፡፡ ዱዓዬን አላቋረጥኩም፡፡
የሆነ ቀን ያች ጓደኛዬ ደወለችልኝ፡፡ ያን ቀን ያየኝ የባሏ ጓደኛ ለትዳር እንዳሰበኝ ነገረችኝ፡፡ በአንድ ቀን እይታ እንዴት ሊሆን ይችላል ብዬ ተገረምኩ፡፡ ግና ለአላህ ምን ይሳነዋል!!፡፡
በእውነቱ የማይታሰብ ነገር ሆነብኝ፤ ማመን አቃተኝ፡፡ እሱ ግን የምሩን ነበር፡፡ ስለኔ ሁሉን ነገር ከጓደኛዬ ከሰማ በኋላ አላንገራገረም፡፡ ወደ ቤተሰቦቼ ሽማግሌ ላከ፡፡ ደስ አለኝ፡፡ ተስፋዬ ለመለመ፡፡ ወዜ ተመለሰ፡፡ ስሜቴ ታደሰ፡፡
፨፨
በመጨረሻም አገባሁ፡፡ ጥሩ አፍቃሪ፣ መልካምና ደጋፊ፣ አዛኝና አሳቢ ባል … አላህ ሠጠኝ፡፡ ለኔም ለወላጆቹም ጥሩ ሰው ነበር፡፡
.
ካገባሁ ቀናት ሄዱ፣ ሁለትና ሦስት ወራት ተተኩ፡፡ ሌላ ሀሳብ አስጨነቀኝ፡፡ የእርግዝና ምልክት ናፈቀኝ፡፡ ግና እስካሁን ምንም አላስተዋልኩም፡፡ ሲበዛ አሳሰበኝ፡፡ እንቅልፍ አጣሁ፡፡
.
መመርመር እንደምፈልግ ለባሌ ነገርኩት፡፡ ወደ ሀኪም ቤት ሄድን፡፡ ጥቂት ቆይተን ለዉጤቱ ተጠራን፡፡ ልቤ መምታቱን ጨመረ፡፡ ገና እንደገባሁ “መዳም መብሩክ!” አለችኝ ሀኪሟ፡፡
አርግዤ ነበር፡፡ ሱብሐነላህ!፡፡ ለዚህ ብስራት ነበር እንዴ አላህ እዚህ ድረስ ያመጣኝ አልኩ፡፡
.
የእርግዝና ጊዜዬ ሰላማዊ ነበር፡፡ ግና የዕድሜዬ መግፋት መጠነኛ ተጽእኖ ነበረው፡፡ ሆዴ እያደገ ሲመጣ ሰዉነቴ ከበደኝ፡፡ እንደምንም የድካሙ ወራት አለፈ፡፡ የምጡ ቀን ደረሰ፡፡ በቀዶ ጥገና ነበር የወለድኩት፡፡ ከተሠጠኝ ሰመመን ስነቃ ቤተሰቦቼና ባለቤቴ ዙርያዬ ተሰብስበዋል፡፡ ይስቃሉ፣ ይጫወታሉ፡፡
“ምን ወለድኩ?” አልኳቸው ያለሁበትን ሁኔታ እያስታወስኩ፡፡
.
የተመካከሩ ነበር የሚመስለው፡፡ አንድ ላይ ሆነው ነበር ሰርፕራይዝ ያደረጉኝ “ወንድ እና ሴት!” አሉኝ፡፡ መንታ!!፡፡ የኔን መንቃት ሲጠብቅ የነበረው ባሌ በደስታ ተፍነከነከ፡፡ እኔንም ሀሴት የምሆነውን አሳጣኝ፡፡ ብችል ተነስቼ በዘለልኩ፡፡ ቁስሌ ገና እርጥብ ነው፡፡ ሱጁድም ራቀኝ፡፡ በተኛሁበት እንባዬ በሁለቱም ጉንጮቼ በኩል ዝምብሎ ሲፈስ ይታወቀኛል፡፡ በትኩስ እንባ ፊቴ ታጠበ፡፡ ምስጋናዬን ያወጣሁበት ቃል እሱ ነበር፡፡
ያቺ “አላህ ያሰብሽዉን ይሠጥሻል፤ ኢንሻአላህ ደስ ይልሻል፡፡” ያለችኝ ሴት ትዝ አለችኝ፡፡
፨፨፨
“ወለሰውፈ ዩዕጢከ ረቡከ ፈተርዷ” የሚለዉን የቁርኣን አንቀጽ አስታወስኩ፡፡ ስለ አላህ አስብኩና በሀሳብ ርቄ ሄድኩ፡፡ የሱ ሥራ አብዝቶ ገረመኝ፡፡ እኛ ተስፋ እንቆርጣለን እንጂ እሱ ያዘጋጀልን ነገር አለ፡፡ እኛው ሁለት ልብ ሆነን ተቸገርን እንጂ በርግጠኝነት በአንድ ሆነን ልብ ይሠጠናል ብለን ብንለምነው ይሠጠናል፡፡
እኛው እንቸኩላለን እንጂ እሱ ለሁሉም ነገር መላና መፍትሄ አለው፤ ለሁሉም ነገር ምክንያትና ጊዜ አለው፡፡ ለአላህ ዉሳኔ መታገስና ፈረጃዉን መጠበቅ ትልቅ ዒባዳ ነው፡፡

እንኳን እኛ ነቢዩ ዘከርያም በልጅ እጦት ተፈትነዋል፡፡ “ጌታዬ ሆይ ብቻዬን አትተወኝ፡፡ …” ሲሉ ነበር ዱዓ ያደረጉት፡፡
ኢንሻአላህ ፈጣሪሽ ያሰብሽዉን ይሠጥሻል፤ አንቺም አንድ ቀን ደስ ይልሻል፡፡
፨፨፨፨፨፨፨
“ቂሰሱን ሚነል ዋቂዕ” ከተሠኘ መጽሐፍ የተወሰደ፡፡

https://www.tg-me.com/ONLYFORTRUTHERSJ
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
.....
ቀኑ በፆምተኞች ኑር ሲያበራ መስጂዶች በምዕመኖቻቸው ተሞልተው ውብ ሲሆኑ የአዛንታው ድምፅ በራሱ ለሀሴት ምግብ ነው ሱብሀነላህ እውነትም ሸይጣን ሚታሰርበት ወር.....

ግና...እነዝያ እናቶች ከሌላው ቀን በተለየ ቀኑ የሚጨልምባቸው፣ ሀዘን የሚወርሳቸው ፣አንገት የሚደፉት ምስኪኖች……………
እኔ ልሳቀቅ እማ.... ስቅቅ ሲሉ ስሁር ሳይበሉ ፁመው የመግሪብ አዛንታን ባልደረሰ ብለው የሚፀልዩ የየቲም እናቶች .......
"እማ አናፈጥርም አዛን እኮ ብሎዋል" የሚሉትን ህፃናት ላለመስማት ጆሮ ዳባ ብላ የምታልፈው ባይሞላላት እኮ ነው እኔ ኩርምት ልበል እማ .......
አንዳንዴማ አንጀታቸውን በመቀነት አስረው ከደቀቀ ፍራሻቸው ኩርምት ማለታቸውን ስታይ መኖር ያስጠላሀል…
ያ....አላህ..... እንዴት ያማል
እናም ውዶቼ ወደ እናንተ ስመለስ ይሄ ሁሉ የሚጠብቀው እኔን አንተን አንቺን ነው።

እናም ውዶች ይህን የተቀደሰ እና ድንቅ የሆነ ሀሳብ ከእናንተ ጋር ለመስራት #ኡሚዎች ኑ እያሉ ነው ግን ማን አለ በዚህ ሰዓት ጀነትን እንግዛ የሚል የአሄራ ስንቅ ሰንቀው ውሰዱና ምንዳችሁን አፋፉ እያሉ ነው መቼም ወደኃላ የለም
እናም ኡሚዎች
#እኔ_እያለው_ሳያፈጥሩ_አያድሩም!"
በሚል መሪ ቃል #5ተኛ_ዙርን ከወዲሁ ሽር ጉዱን ተያይዘውታል እንደ ከዚህ በፊቱ ለመነሻ 150 ቤተሰቦችን ታሳቢ በማድረግ እንቅስቃሴ ተጀምሮዋል።
አልሃምዱሊላህ ሁሌም አንድ ስራ ስናስብ በደስታ የምንጀምረው
#ያንተ
#ያንቺ
#የእርሶ
#የሁላችሁም እገዛ እና ዱአ አብሮን እንደሆነ ስለምናውቅ ነው ሁላቹንም ጀዛከላሁም ኸይረን ከአላህ ጋር የናንተ እገዛ ተጨምሮ ካሰብነው በላይ እንደምናሳካ እርግጠኞች ነን ረመዳኑንም ያማረ የተዋበ እናደርገዋለን ኢንሻላህ……
#ለአንድ_ቤተሰብ
ሙሉ አስቤዛ #1300 ብር
ግማሽ አስቤዛ #650 ብር
ሩብ አስቤዛ #325 ብር
#በአስቤዛ መሸፈን እችላለው ካሉ
*ዱቄት *ሩዝ
*ቂንጬ *ቴምር እና ዘይት

ንግድ ባንክ
#1000278180388
ኡሚ የየቲሞች መረዳጃ
አድራሻ
ቤተል አልመሻን ህንፃ 3ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 316&317
ስልክ ቁጥር
0912927557/0926688698
አዳማ ፖስታ ቤት በደዊ ህንፃ 3ተኛ ፎቅ
0980482001/091 072 9106
@ummicharityinstitut
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
==>ዱንያ ማለት ምን ማለት ናት 😊
ብሎ ለጠየቃቸው አንድ ሰው....

ዱንያ ማለት አሉ ኢማም ሀሰነል በስሪ ፦ መጀመርያዋ ለቅሶ መካከሏ ድካም መጨረሻዋ ጥፋት ነው። ሀላል ብትሰራ ሂሳብ ሀራም ብትሰራ ደግሞ ቅጣት ነው። ዱንያ ማለት ይህች ናት አሉት ይባላል፡፡
@ONLYFORTRUTHERSJ
Aselamuwaleykim🙌
"Ahlen ikweti "
Inshallah let's all have " niyah " to fast tomorrow and make Dua for the Ummah to be guided in straight path 🙏 and let's be charitable slaves to have more (in this world and here after)😁
👇👇👇👇👇👇👇
@ONLYFORTRUTHERSJ
👆👆👆👆👆👆👆👆
ልብ ትረጋለች የጌታዋ ስም ሲወሳ ትረካለች።

الَّذِينَ آمَنُوا وَتَطْمَئِنُّ قُلُوبُهُم بِذِكْرِ اللَّهِ ۗ أَلَا بِذِكْرِ اللَّهِ تَطْمَئِنُّ الْقُلُوبُ

(እነሱም) እነዚያ ያመኑ ልቦቻቸውም አላህን በማውሳት የሚረኩ ናቸው፡፡ ንቁ! አላህን በማውሳት ልቦች ይረካሉ፡፡

ልቡን ለአላህ የሰጠና ወደ እርሱም የተጠጋ ፍርሃት ፍፁም የለበትም።


وَتَوَكَّلْ عَلَى اللَّهِ ۚ وَكَفَىٰ بِاللَّهِ وَكِيلًا

በአላህም ላይ ተጠጋ፡፡ መጠጊያም በአላህ በቃ፡፡

فَتَوَكَّلْ عَلَى اللَّهِ ۖ إِنَّكَ عَلَى الْحَقِّ الْمُبِينِ

በአላህም ላይ ተጠጋ፡፡ አንተ ግልጽ በኾነው እውነት ላይ ነህና፡፡

አንተ ሰው ሆይ! መጠጊያህን ምረጥና ጥግህን ያዝ፣ ልብህ በሠላት ትርጋ ወደ ጌታዋ ትቃረብ።

وَاسْجُدْ وَاقْتَرِب ۩

ስገድም፤ (ወደ አላህ) ተቃረብም፡፡
ያቤት አስፈራኝ

ቤቴን እረስቼ ብዙ ከርሜያለሁ
ማሳመርን ትቼ ሳበላሽ ኖሬያለሁ
መሰነቅ ሲገባኝ ላዛ ለሩቅ ቤቴ
ዱንያ አሞኘችኝ አወየው ጥፋቴ

ምን አስቀደሜ ይሆን ብዬ ብጠይቀው
ለጨለማው ጉድጓድ ነገ ለማገኘው
መልሱ አስደንጋጭ ነው አይ የኔ ኪሳራ
ህይወቴን ጨረስኩት በተራ ዳንኪራ

ስንቅን ሳልሰነቅ ሳልዘጋጅ ደግሞ
እንዴት ልችለው ነው ያቤቴ ጨልሞ
ያንን ቤት ፈራሁት ነገ ምገባበት
ድቅድቁን ጨለማ የትሎች ባለቤት

እንዴት ልችለው ነው ያንን የጭንቅ ኑሮ
ከመሬት ስር ካለው በአፈር ተነባብሮ
አወይ የኔ ጥፋት አወይ ከንቱነት
ቀብሬን ዘነጋሁ ዱንያን ሳሳዳት
ሳሳድድ ሳሳዳት ላሊዛት ሳባራት
ሁሉን አሳጥታ ጣለችኝ ከጥፋት

ታዲያ እንዴት ልችል ነው የቀብርን ኑሮ
መልካም ስራ ሳይኖር የሚያባሽር አብሮ
እንዴትስ ልሆን ነው በዛ ቀውጢ ሰአት
የሆድ አጥንቶቼ በሚጣበቁበት
ምንስ ልመልስ ነው ባዶ ሆኖ ስንቁ
ነኪርና ሙንከር እኔን ሲጠይቁ

በቃ አለቀልኝ ጠፋሁኝ ጠፋሁኝ
በተስፋ መቁረጥ ሆኜ እጮሀለሁኝ
ግና ምን ዋጋ አለው ፀፀት አይጠቅም ያኔ
ከንቱ መመኘት ነው ማለት ወይኔ ወይኔ

ከዚህ ሁሉ ችግር ማምለጥ የሚቻለው
ለነገ ቤታችን ዛሬ ስንሰራ ነው
ዛሬ ስናስቀድም መልካም ሁሉን ስራ
ዱንያን ችላ ብለን ስንሰራ ለአሂራ

በዛ በጭንቅ ቀን ተስፋ እናገኛለን
ሌሎች ሲቸገሩ እኛ እንድናለን

ለመዳን ከፈለክ በጭንቅ ቀን ያኔ
ለትእዛዛት እደር ለጌታህ ውሳኔ ።
©
https://www.tg-me.com/ONLYFORTRUTHERSJ
Forwarded from UMMI/ኡሚ (: ًٍٜ۪۪۪۪۪ٜٜٜٜ͜͡Ha ًٍٜ۪۪۪۪۪ٜٜٜٜٖٜ͜͡Yu✵ٌٍٍٍٍٍٍۘۘۘۘ͜͡Na ًٍٜ۪۪۪۪͜͡)
Forwarded from UMMI/ኡሚ (: ًٍٜ۪۪۪۪۪ٜٜٜٜ͜͡Ha ًٍٜ۪۪۪۪۪ٜٜٜٜٖٜ͜͡Yu✵ٌٍٍٍٍٍٍۘۘۘۘ͜͡Na ًٍٜ۪۪۪۪͜͡)
.....
ቀኑ በፆምተኞች ኑር ሲያበራ መስጂዶች በምዕመኖቻቸው ተሞልተው ውብ ሲሆኑ የአዛንታው ድምፅ በራሱ ለሀሴት ምግብ ነው ሱብሀነላህ እውነትም ሸይጣን ሚታሰርበት ወር.....

ግና...እነዝያ እናቶች ከሌላው ቀን በተለየ ቀኑ የሚጨልምባቸው፣ ሀዘን የሚወርሳቸው ፣አንገት የሚደፉት ምስኪኖች……………
እኔ ልሳቀቅ እማ.... ስቅቅ ሲሉ ስሁር ሳይበሉ ፁመው የመግሪብ አዛንታን ባልደረሰ ብለው የሚፀልዩ የየቲም እናቶች .......
"እማ አናፈጥርም አዛን እኮ ብሎዋል" የሚሉትን ህፃናት ላለመስማት ጆሮ ዳባ ብላ የምታልፈው ባይሞላላት እኮ ነው እኔ ኩርምት ልበል እማ .......
አንዳንዴማ አንጀታቸውን በመቀነት አስረው ከደቀቀ ፍራሻቸው ኩርምት ማለታቸውን ስታይ መኖር ያስጠላሀል…
ያ....አላህ..... እንዴት ያማል
እናም ውዶቼ ወደ እናንተ ስመለስ ይሄ ሁሉ የሚጠብቀው እኔን አንተን አንቺን ነው።

እናም ውዶች ይህን የተቀደሰ እና ድንቅ የሆነ ሀሳብ ከእናንተ ጋር ለመስራት #ኡሚዎች ኑ እያሉ ነው ግን ማን አለ በዚህ ሰዓት ጀነትን እንግዛ የሚል የአሄራ ስንቅ ሰንቀው ውሰዱና ምንዳችሁን አፋፉ እያሉ ነው መቼም ወደኃላ የለም
እናም ኡሚዎች
#እኔ_እያለው_ሳያፈጥሩ_አያድሩም!"
በሚል መሪ ቃል #5ተኛ_ዙርን ከወዲሁ ሽር ጉዱን ተያይዘውታል እንደ ከዚህ በፊቱ ለመነሻ 150 ቤተሰቦችን ታሳቢ በማድረግ እንቅስቃሴ ተጀምሮዋል።
አልሃምዱሊላህ ሁሌም አንድ ስራ ስናስብ በደስታ የምንጀምረው
#ያንተ
#ያንቺ
#የእርሶ
#የሁላችሁም እገዛ እና ዱአ አብሮን እንደሆነ ስለምናውቅ ነው ሁላቹንም ጀዛከላሁም ኸይረን ከአላህ ጋር የናንተ እገዛ ተጨምሮ ካሰብነው በላይ እንደምናሳካ እርግጠኞች ነን ረመዳኑንም ያማረ የተዋበ እናደርገዋለን ኢንሻላህ……
#ለአንድ_ቤተሰብ
ሙሉ አስቤዛ #1300 ብር
ግማሽ አስቤዛ #650 ብር
ሩብ አስቤዛ #325 ብር
#በአስቤዛ መሸፈን እችላለው ካሉ
*ዱቄት *ሩዝ
*ቂንጬ *ቴምር እና ዘይት

ንግድ ባንክ
#1000278180388
ኡሚ የየቲሞች መረዳጃ
አድራሻ
ቤተል አልመሻን ህንፃ 3ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 316&317
ስልክ ቁጥር
0912927557/0926688698
አዳማ ፖስታ ቤት በደዊ ህንፃ 3ተኛ ፎቅ
0980482001/091 072 9106
@ummicharityinstitut
ብዙ እህቶች (አላህ ሂዳያ ይስጣቸውና!) ጥፍራቸውን ያስረዝማሉ ቀለም ይቀባሉ፣ የተወሰኑ ወንዶችም ያስረዝማሉ፣ ሸሪዓዊ ብይኑ ምን ይሆን…?

ታላቁ ዓሊም ኢማሙል አልባኒይ (ረሂመሁላህ) እንዲህ ብለዋል:–
«ይህ ጥፍርን መቀለም ሙስሊም ሴቶች ተከትለውት የሚተገብሩት ቆሻሻ የሆነ ልምድ የተወሰደው ከአውሮፓ ጠማማዎች ነው፣ እንዲሁም ማስረዘሙን፣ ከፊል ወጣት ወንዶችም ይፈፅሙታል። ይህ የተገበረው ሰው ላይ የአላህን እርግማን የሚያስይዝ የሆነውን ተፈጥሮን መለወጥ ያለበት የሆነ ተግባር ነው፣ የተከለከሉ በሆኑ ተግባሮች ከሀዲዎችን መከተል እርግማን እንዳለበት በበርካታ ሀዲሶች መጥቷል። ከነዚያም ነቢዩ ‘ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም’ እንዲ ማለታቸው ነው:– “በከሃዲዎች የተመሳሰለ ሰው እሱ ከነሱ ነው”
ይህ ተግባር በድጋሚም ተፈጥሮን የሚቃረን ነው {فِطْرَتَ اللَّهِ الَّتِي فَطَرَ النَّاسَ عَلَيْهَا}
“የአላህን ፊጥረት ያችን አላህ ሰዎችን በርሷ ላይ የፈጠረባትን” ሩም 30
የአላህ መልእከተኛ ‘ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰልም’ እንዲህ ብለዋል:– “ተፈጥሮ አምስት ናቸው:– ግርዛት፣ የብልት አካባቢ ፀጉርን ማስወገድ፣ ቀድሞ ቀመስን ማሳጠር፣ ጥፍርን መቁረጥ፣ የብብትን ፀጉር መንጨት።” ናቸው።
አነስ ‘ረዲየላሁ ዐንሁ’ እንዲህ ብሏል:– “የአላህ መልእክተኛ ﷺ የብልት አካባቢ ፀጉርን በማስወገድ፣ ቀድሞ ቀመስን በማሳጠር፣ ጥፍርን በመቁረጥ፣ የብብትን ፀጉር በመንጨት፣ ከ40 ለሊት በላይ እንዳይቆይ የጊዜ ገደብን አድርገውልናል።” » [ምንጭ:– ኣዳቡ ዘፋፍ 132/135]
በዚህን ጊዜ የብዙ ሙስሊም ሴቶች ተግባር እጅግ በጣም አሳፋሪ ነው! የከሃዲ ሴቶችን ኮቴ በኮቴ እየተከተሉ ጭራሽ ሙስሊም መሆናቸውንና በእያንዳንዱ እንቅስቃሴያቸው እስልምና እንደሚመለከተው ዘንግተዋል። አዎ! እህቴ ቆም ብለሽ ስለ እስልምናሽ አስተውይ! ሙስሊሞች ሀይማኖታቸው በኢያንዳንዱ እንቅስቃሴያቸው ይመለከታቸዋ፣ የተወገዙ እንቅስቃሴዎችን ይከለክላቸዋል ጥሩ የሆነውን ይፈቅድላቸዋል።
✍🏻ኢብን ሽፋ: ረቢዕል አወል 13/1440 ዓ. ሂ
@Halal_life
2024/10/01 09:30:27
Back to Top
HTML Embed Code: