Telegram Web Link
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችን መቀበል ከመጀመራቸው በፊት የተቋማቱ ዝግጁነት እንደሚረጋገጥ ተገለጸ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን መልሶ ለመክፈት የሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ በጅማ ዩኒቨርስቲ መሰብሰቢያ አዳራሽ ውይይት ተካሂዷል፡፡

በውይይቱ መጀመሪያ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሙሉ ነጋ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በመከላከል የትምህርትና ስልጠና ተቋማት መልሶ የመክፈት ሂደትና ዝግጅት በሚል ርዕስ ምክረኃሳብ አቅርበዋል፡፡

በ2012 ዓ.ም የተቋረጠዉን ትምህርት በልዩ ዕቅድ ለማጠናቀቅ በሚሰሩ ስራዎችና ትምህርት ሲጀመር ሊደረጉ ስለሚገባቸው ጥንቃቄዎች እንዲሁም ቀደም ተብለው በከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ የሚደረጉ ጥንቃቄዎች ምን መምሰል እንዳለባቸው በምክረሃሳባቸው ቀርቦ ውይይት ተካሂዶባቸዋል፡፡

በጉባኤው የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ በበኩላቸው መች እንክፈት  ለሚለው ትክክለኛ መልስ እያንዳንዱ ዩኒቨርስቲ በዓለም የጤና ድርጅት መለኪያ መስፈርት መሰረት ደረጃውን ጠብቆ በተዘጋጀ ዝርዝር በጥልቀት የዝግጅት መጠኑ ተፈትሾ ዝግጁ ሲሆን ብቻ ነው ብለዋል፡፡  በዚያ መሰረት የተቋማት ዝግጅት ይፈተሻል። በዳሰሳውም መሰረት መቀበል እንደሚችሉ ፍቃድ ይሰጣል ሲሉ አብራርተዋል፡፡

ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ እንደገለፁት ቅድሚያ ለተመራቂዎች በመስጠት ተማሪዎችን በመከፋፈል በትንሽ ቁጥር ይጀመራል፡፡ ይህም ከሚታዩ ነገሮች እየተማርን የተማሪ ቁጥር ለመጨመር እድል ይሰጠናል ብለዋል፡፡ ዝርዝር አፈጻጸሙ በምን እንደሚመራ ከጤና ሚኒስቴር  ጋር በመሆን ፕሮቶኮል ይዘጋጃልም ብለዋል፡፡

ዩኒቨርስቲዎች የለይቶ ማቆያ ማዕከላት እንደመሆናቸው የክልል መንግስታት ስራ ይጠበቅባቸዋል። አማራጭ የኳረንቲን ቦታዎችን ማዘጋጀትም ግድ ስለሚላቸው እዚያ ላይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት ይሰራል ብለዋል፡፡  

ተማሪዎችን በማጓጓዝ ሂደት ችግር እንዳያጋጥም ከትራንስፖርት ሚኒስቴርና ጤና ሚኒስቴር  ጋር በትብብር እንሰራበታለን ብለዋል፡፡

ዩኒቨርስቲዎች ተማሪዎችን መልሶ ለመቀበል የሚያስችል እቅድ ካሁኑ አዘጋጅተው ከአስተዳደር ሰራተኞችና መምህራን ጋር በመወያየት የጋራ ሊያደርጉ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡ የበፊቱን አሰራር ይዘን መቀጠል አንችልም፡፡ ዝግጅታችንን ተጋላጭነታችንን አውቀን ተማሪ እንቀበላለን።  አንድ ብሎክ ወይም አንድ ካምፓስ ኮቪድ 19 ቢያጋጥም ምን እናደርጋለን ከሚለው ጀምሮ በዝርዝር መስራት እና እያንዳንዱ እቅድ ያለተማሪዎች እገዛ ተፈፃሚ ስለማይሆን ወደነሱ ለማስረፅ መስራት የግድ ይለናል ብለዋል፡፡

ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ እንዳሉት ጊዜው የተማሪዎች ህብረት ኃላፊነት የሚፈተንበት  ነው። የተማሪዎች ህብረት አባላት የመፍትሄ ኃሳብ ሆናችሁ ለተፈፃሚነቱ ከዩኒቨርስቲያችሁ ጋር በትብብር እንድትሰሩ ከእናንተ ይጠበቃል፡፡ ሰላማችሁን ማስጠበቅና ለደህንነታችሁ ዘብ መቆም ለትምህርታችሁ ቀጣይነት ዋስትና ነው ሲሉ አብራርተዋል፡፡ ዩኒቨርስቲዎች መከፈታቸው ላይ ብቻ ሳይሆን ተመልሰው እንዳይዘጉም ጭምር የተማሪዎች ድርሻ ከፍተኛ እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡

የጥንቃቄ ቁሳቁሶችን አስመልክቶም የትኞቹ በዩኒቨርስቲዎች ይቅረቡ የትኞቹ በተማሪዎች ይሟሉ የሚለውን ከተጨባጭ ሁኔታ አንፃር ለይቶ መወሰን አስፈላጊ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

በውይይቱ ማጠቃለያ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶ ውይይቱ ተቋማት የት ላይ እንደሆኑ ለይተን ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችል ግንዛቤ ለመያዝ ታስቦ የተካሄደ ነው ብለዋል፡፡ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መሪዎች በአሁኑ ጊዜ ቁርጠኝነት የሚፈልግ የለውጥ ስራ እየሰራን እንደሆነ መገንዘብ እና በዛው መጠን መፍጠን ያስፈልጋቸዋል ብለዋል፡፡ ተማሪዎችን ወደትምህርት የመመለስ ሂደት ባለድርሻ አካላትን በተገቢው መንገድ የማቀናጀት ኃላፊነት ተወስዶ መሰራት ያለበት ጉዳይ ነውም ብለዋል፡፡

ተማሪዎችን ከመመለስና የኮቪድ 19 ለይቶ ማቆያ ቦታዎችን ከማዘጋጀት አንፃር የፌደራልም ሆነ የክልል መንግስታት እያንዳንዱ የራሱን ኃላፊነት ወስዶ እንዲሰራ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ መስራት ያስፈልጋል ሲሉ ገልፀዋል፡፡ እንደከፍተኛ ትምህርት ዓለም አቀፋዊና አገራዊ አጀንዳዎች ላይ ትኩረት እናደርጋለን፡፡ ምርምር ላይ የተገኘውን እውቀት ተጠቅመን ለአገር የሚውል አድርገን መጠቀምም ይገባናል ብለዋል፡፡
ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶ ስራውን በማስፈፀም ሂደት ኃላፊዎች የኮሙኒኬሽን ክፍተት እንዳይኖር በመነጋገር ሊሰሩ እንደሚገባ ጠቁመው አመራር የሁሉ ነገር ቁልፍ እንደመሆኑ በጋራ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

ነገ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጉዳዩ ላይ እንደሚወያይና ውሳኔ እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል የተባለ ሲሆን ከዚያም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ተቋማቱን ለመክፈት ያበቃሉ ተብለው የተቀመጡ ዝርዝሮችን በመያዝ በዩቨርስቲዎች በመገኘት ብቁ መሆን አለመሆናቸው ታይቶ አስፈላጊውን መስፈርት ካሟሉ ብቻ እንዲከፍቱ ይደረጋል ብለዋል፡፡

ተማሪዎችን መልሶ ለመቀበል በሚደረግ ቅድመ ዝግጅት ወደኃላ የቀራችሁ ዩኒቨርስቲዎች ካላችሁ ፈጥናችሁ ዝግጅታችሁን አጠናቅቁ ብለው መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን ጉዳዩንም እንደፕሮጀክት ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንዳለባቸው አስበዋል፡፡

ከተሳታፊዎች የተለያዩ ስጋት ናቸው ተብለው የተነሱ ጉዳዮች ተነስተው ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን በሂደት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ሆኖ ለመፍታት እንደሚሰራ ተገልጿል፡፡
#Moshe

Join @MUSUofficalchannell
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጉዳይ ይወያያል!

በዛሬው ዕለት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጉዳዩ ላይ እደደሚወያይና ውሳኔ እንደሚያሳልፍ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶ ትላንት ጅማ ዩኒቨርሲቲ በነበረው መድረክ ተናግረዋል።

ምክር ቤቱ ተወያይቶ ውሳኔ ካሳለፈ በኃላ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ተቋማቱን ለመክፈት ያበቃሉ ተብለው የተቀመጡ ዝርዝሮችን በመያዝ በዩቨርስቲዎች በመገኘት ብቁ መሆን አለመሆናቸው አይቶ አስፈላጊውን መስፈርት ካሟሉ ብቻ እንዲከፍቱ ያደረጋል።

ተማሪዎችን መልሶ ለመቀበል እንተደረገ በሚገኘው የቅድመ ዝግጅት ስራ ወደኃላ የቀሩ ዩኒቨርስቲዎች ካሉ ፈጥነው ዝግጅታቸውን እንዲያጠናቀቁ ሚኒስትሩ አሳስበዋል።
"ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ እንዳሉት ጊዜው የተማሪዎች ህብረት ኃላፊነት የሚፈተንበት  ነው። የተማሪዎች ህብረት አባላት የመፍትሄ ኃሳብ ሆናችሁ ለተፈፃሚነቱ ከዩኒቨርስቲያችሁ ጋር በትብብር እንድትሰሩ ከእናንተ ይጠበቃል፡፡ ሰላማችሁን ማስጠበቅና ለደህንነታችሁ ዘብ መቆም ለትምህርታችሁ ቀጣይነት ዋስትና ነው ሲሉ አብራርተዋል፡፡ ዩኒቨርስቲዎች መከፈታቸው ላይ ብቻ ሳይሆን ተመልሰው እንዳይዘጉም ጭምር የተማሪዎች ድርሻ ከፍተኛ እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡"

ዶር ሳሙኤል ክፍሌ
Read the above papers abt the final discution with MOSHE to start Educations !!
This is #Moshe (Dr Samuel Hurqato -Minister and his team members) #Uni presidants and Ethiopian Students Union pic. Thank You #MoSHE for listening our students Isues.
Thank you #JIMMA UNI and Community
#Galatoma

Join @MUSUofficalchannell
#MOH
ከጥቅምት 09-13/2013 ዓ.ም የሚሰጠውን የብቃት ምዘና ፈተና በዳግም ምዘና (Re Exam) የምትወስዱ ጤና ባለሙያዎች በሙሉ ከመስከረም 13-27/2013 ዓ.ም ድረስ በኦንላይን hple.moh.gov.et ላይ በመግባት መመዝገብ የምትችሉ ሲሆን ከተጠቀሰው ቀን በኋላ ምንም ዓይነት የምዝገባ ጥያቄ የማናስተናግድ መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን፡፡

ማሳሰቢያ፡- ፈተናውን ለመጀመሪያ ጊዜ የሚወስዱ ተመዛኞች የስም ዝርዝራቸውን ከተማሩበት ተቋም በቀጥታ ስለምንቀበል በዚህ የኦንላይን ምዝገባ (online registration) መመዝገብ የማይጠበቅባቸው መሆኑን እየገለጽን ይህንን በመተላለፍ በኦንላይን ሲስተሙ ከተመዘገቡ ሲስተሙ ከፈተና ዝርዝር የሚሰርዛቸው መሆኑንና ለዚህም ሀላፊነቱን የማንወስድ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን፡፡
#MOH
car Accident.
ቀድመው ዝግጅት ያጠናቀቁ ዩኒቨርሲቲዎች ከመስከረም 25 ጀምሮ 'ለተመራቂ ተማሪዎች' ጥሪ ማድረግ እንደሚችሉ ተወስኗል!

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ወጥነትን ሳይጠብቁ ቀድመው ዝግጅታቸውን ያጠናቀቁ ዩኒቨርሲቲዎች ከመስከረም 25 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ ለተመራቂ ተማሪዎች ጥሪ በማድረግ ወደ መማር ማስተማር ሥራው እንዲገቡ በጅማ ዩኒቨርሲቲ በተካሄደው የውይይት መድረክ ውሳኔ ተላልፏል።

ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ጥሪ ከተደረገ በኋላ ከመጓጓዣ ሂደት ጀምሮ በየዩንቨርሲቲዎቹ በሚኖራቸው ቆይታ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እንዳይዛመት ከፍተኛ ዝግጅት መደረግ እንዳለበትም ተገልጿል።

በቀጣይነትም ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሁኔታ ጋር በሚስማማ መልኩ ተለዋዋጭ እቅዶችን በመያዝ ቀሪዎቹ ተማሪዎች ወደ ትምህርታቸው እንዲመለሱ እንደሚሠራ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ደቻሳ ጉሩሙ ለጀርመን ድምፅ ሬድዮ ተናግረዋል

tikvahethiopia
የቅድመ ምረቃ ትምህርት ዳግም እንዲጀመር ተወሰነ!

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተወካዮችን በማሳተፍ በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በጅማ ዩንቨርሲቲ ሲካሄድ የቆየው የሦስት ቀናት ጉባኤ የተለያዩ ውሳኔዎችን በማስተላለፍ ተጠናቋል።

በዚህም የቅድመ ምረቃ ትምህርት ዳግም እንዲጀመር መወሰኑን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ደቻሳ ጉርሙ ለዶይቼ ቨሌ ተናግረዋል።

በውይይቱ ዩኒቨርሲቲዎች የኮቪድ-19 ለይቶ ማቆያና ምርመራ ማዕከላት ሆነው ሲያገለግሉ መቆየታቸው እንደስጋት የተነሳ ሲሆን ጉዳዩን ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመምከር ለጊዜው ተመራቂ ተማሪዎችን ቅድሚያ በመስጠት ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ ተወስኗል፡፡

በመሆኑም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ ወጥነትን ሳይጠብቁ ቀድመው ዝግጅታቸውን ያጠናቀቁ ዩኒቨርሲቲዎች ከመስከረም 25 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ ለተመራቂ ተማሪዎች ጥሪ በማድረግ ወደ መማር ማስተማር ሥራው እንዲገቡ አቅጣጫ ተቀምጧል።

አምና በከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ የመማር ማስተማር ሂደቱ ላይ ፈተና ሆኖ የከረመው የፀጥታ መደፍረስ እንዳያጋጥም ከአምና ልምድ መወሰዱን ጉባኤው የመከረበት ሲሆን ዩንቨርሲቲዎች ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር እንዲሠሩበት እቅድ መያዙ ተገልጿል።
Via #DW
Phases to return??
1.GC - First phase

2.3rd and 4th - second phase

3.1 and 2d year- 3rd phase to be returned
dears , pls dont repeat questions just follow the updates.

Join @MUSUofficalchannell
Freqantly asked questions!!
4.how to return 5th year Medical Students ??
5.how to return students with Add and drop case ? this question is raised by the students Union at Jimma Uni Moshe s Meeting? - we will update you with a clear information.
2024/09/24 17:19:36
Back to Top
HTML Embed Code: