Telegram Web Link
Forwarded from DW Info®
💉🖍በትምህርት ቤቶች አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ትምህርት ለመጀመር ዝግጅቶች እየተጠናቀቁ እንደሆነ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ!

💉🖍በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ለ 7 ወራት የተቋረጠውን መደበኛ ትምህርት ለማስቀጠል ትምህርት ሚኒስቴር አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጉን አስታወቀ፡፡መንግስት በትምህርት ቤቶች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል፣ የውሃ እና የእጅ ማፅጃ አቅርቦቶችን በማሟላት እንዲሁም ትምህርት ቤቶችን የማፅዳት ስራዎችን በማከናወን መደበኛ ትምህርት እንደሚጀመር ተገልጿል፡፡

💉🖍የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ (ዶ/ር ኢንጂ.) ትምህርት ቤቶች ሲከፈቱ ተማሪዎች እንደየ ደረጃው ወደ ክፍል ገብተው ትምህርታቸውን እንደሚከታተሉ የገለፁ ሲሆን ትምህርት ሲጀመርም በአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች የሚጀመር መሆኑን እና በቀጣይም ሌሎች የትምህርት ክፍሎች ወደ መደበኛ ትምህርቱ እንደሚገቡ ተናግረዋል፡፡

💉🖍በትምህርት ቤቶች የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል የተቀመጡ ጥንቃቄዎች ሙሉ በሙሉ የሚተገበሩ መሆኑን እና የትምህርት አሰጣጡ ሂደትም በፈረቃ የሚሰጥ መሆኑንም ሚኒስትሩ አብራርተዋል፡

💉🖍የፈረቃ ስርዕቱም እንደየአካባቢው ሁኔታ ከ 2 እስከ 3 ሊሆን እንደሚችልም ተገልጿል፡፡

💉🖍የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል በትምህርት ቤት ውስጥ መምህራኖች ትልቁን ሃላፊነት ሊወጡ እንደሚገባ የተገለፀ ሲሆን ወላጆችም ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት ሲልኩ አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።መደበኛ ትምህረቱም መንግስት ውሳኔ እንዳሳለፈ እንደሚጀምር ተገልጿል፡፡የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስፈላጊውን የጥንቃቄ እርምጃዎችን በመተግበር ትምህርት ቤቶችን መክፈት እንደሚቻል ለህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ምክረ ሃሳብ ማቅረቡ ይታወሳል፡፡

MoE

@Dweyane1967
@Dweyane1967bot
Forwarded from DW Info®
💉📌ትምህርት በፈረቃ እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ!

💉🖍ትምህርት ሲጀመር የትምህርት አሳጣጥ ሂደቱ በፈረቃ እንደሚሆን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

💉🖍በፈረቃ የሚሰጠው ትምህርት እንደየአካባቢው ሁኔታ ከ2 እስከ 3 ፈረቃ ተከፍሎ ሊሰጥ እንደሚችልም ተገልጿል።

💉🖍የመማር ማስተማር ሥራው በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች እንደሚጀመር ትምህርት ሚኒስቴር አመልክቷል።

💉🖍ሚኒስቴሩ እንዳለው በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ለሰባት ወራት ተቋርጦ የቆየው መደበኛ ትምህርት አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ዳግም ለማስጀመር አስፈላጊው ዝግጅት ተጠናቋል።

💉🖍መንግስት በትምህርት ቤቶች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ፣ ውሃ እና የእጅ ማጽጃዎችን በማሟላት እንዲሁም ትምህርት ቤቶችን በማጽዳት መደበኛው ትምህርት እንደሚጀመር አስታውቋል።

@Dweyane1967
@Dweyane1967bot
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን መልሶ ለመክፈት የሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡
የጤና ሚኒስትር የዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት ያስቀመጣቸውን መስፈርቶች በመተግበር ትምህርት ቤቶችን መክፈት ይቻላል የሚል ምክረኃሳብ ማቅረቡን ተከትሎ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ኃላፊዎች እና ባለድርሻ አካላት ጋር በጅማ ዩኒቨርስቲ የመሰብሰቢያ አዳራሽ እየመከሩ ይገኛሉ፡፡
በውይይታቸው በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ወሳኝ በሆኑ ጉዳዮች እንደሚመክሩና የዩኒቨርስቲዎች ትምህርትን መልሶ ለማስጀመር የተደረገ የዝግጅት ምዕራፍ ስራ ያለበት ደረጃ ገምግመው በአፋጣኝ መሰራት ያለባቸው ሁኔታዎች ላይ አቅጣጫ የሚቀመጥ ይሆናል፡፡
በቆይታቸው ከዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንቶች ጋር በጋራና በጥልቀት በመወያየት ዩኒቨርስቲዎችን መልሶ መክፈት ላይ ስምምነት እንደሚደርሱ ተገልጿል፡፡
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ያዘጋጀውና ትኩረቱን ወረርሽኙን በመከላከል ትምህርት ማስቀጠል ላይ ያደረገ ጉባዔ በጅማ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው።

የሚኒስቴሩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና የዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዚዳንቶች በጉባዔው ታድመዋል።

በዩኒቨርሲቲዎች በኩል ተቋርጦ የቆየውን ትምህርት ለማስቀጠል የተደረገውን ቅድመ ዝግጅት ሚኒስትር ዴኤታው ዶክተር ሙሉ ነጋ አብራርተዋል።

በዚህም ትምህርት በተቋረጠበት ጊዜ ተማሪዎች ከትምህርት እንዳይርቁና የስነ-ልቦና ጉዳት እንዳይደርስባቸው ስለተሰራው ስራ ጠቅሰዋል።

የድህረ ምረቃ ተማሪዎች በቴክኖሎጂ በመታገዝ ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ ማድረግ አንዱ መሆኑን አውስተዋል።

የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች በያሉበት የኢንተርኔት አገልግሎት በቅናሽ ዋጋ እንዲያገኙና ከትምህርት እንዳይርቁ ለማድረግ ተሞክሯልም ብለዋል።

ሚኒስትር ደኤታው የተቋረጠውን ትምህርት ለማስቀጠል ስልቶችና ታሳቢ የተደረጉ ጉዳዮችንም አብራርተዋል።

የተቋረጠውን ትምህርት በልዩ ሁኔታ ለማጠናቀቅ ኮርስ የጨረሱ የሕግ፣ የሕክምና ቨተርነሪ ተማሪዎችን በአንድ ሳምንት ማካካሻ ለማስጨረስ ታስቧል ነው ያሉት።

ሁለተኛ ሴሚስተር ያልጀመሩ ተማሪዎችን በሁለት ወር፣ የሴሚስተሩን 25 በመቶ የተማሩትን ደግሞ በ45 ቀናት ማካካሻ ለማስጨረስም ታሳቢ ተደርጓል።

እንደ ሚኒስትር ዴኤታው ገለጻ ነባር ተማሪዎችን በሶስት መርሃ ግብር፤ ተመራቂ ተማሪዎችን ደግሞ እስከ ሁለት ወር ለማሰጨረስ ነው የታሰበው።

ተመራቂ ያልሆኑ ነባር ተማሪዎች ጉዳይ እየታየ የሚቀጥል ሲሆን ትምህርት ማስቀጠያው ከጥቅምት እንዲጀምርም ታስቧል።

በአንድ ክፍል ውስጥ ከ25 እስከ 30 ተማሪዎችን ለማስተማር ታቅዷል፤ ሌሎች መማሪያ ክፍሎች ደግሞ የመያዝ አቅማቸውን ግማሽ ብቻ እንዲይዙ ይደረጋል።
@capital_news1
@capital_news1
Mekelle University has presented its COVID 19 Research , technology development and dissemination and community service activities at Jimma university.
2024/09/24 19:24:04
Back to Top
HTML Embed Code: