Telegram Web Link
አንድ ብቻውን የሚኖር አቅመ ደካማ ሽማግሌ ነበር፡፡ ሁሌም አላህን ሲለምን ...አላህ ሆይ!!! ለቡጋስ እንደምትለግሰው ሁሉ ለኛም ለግሰን፡፡› ይላል፡፡

ቡጋስ የወፍ ዝሪያ ሲሆን ሲወለድ ምንም ዓይነት ፀጉር የሌለው ሆኖ ነጭ ሰውነት ይዞ ነው፡፡ ጥቁር ባለመሆኑ ምክንያት እናትና አባቱ የኛ ነው ብለው ስለማያስቡ ይመስላል አይቀልቡትም፡፡ እሱም ቢሆን የመብረር አቅም ስለሌለው ሄዶ ሪዝቁን ማምጣት አይችልም፡፡

ነገርግን ሪዝቅ ቢርቅም አርረዛቅ አለ፡፡ ቡጋስ ሽታው አንዳንድ ጉንዳኖችን የመሳብ ሀይል አለው፡፡ ፀጉሩ እስኪበቅልለት ድረስ እነኚህኑ ይመግባል፡፡ በዚህ ጊዜ እናቱ ታውቀውና እሱን መመገብ ትጀምራለች፡፡


#እውነትም_ለቡጋስ_እንደምትለግሰው_ሁሉ_ለኛም_ለግሰን፡፡

@አሚር ሰይድ

join👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
#የኪፍል_ተዉበትና_የአሏህ_አቀባበል
    አሚር ሰይድ


  ማንኛወም ሰዉ ከተዉበት ተዘናግተናል..በተለይ ብዙዎቻችን አሁን ላይ ቦይፍሬድ ገርልፍሬንድ ስም በተጨማለቅንበት  በዝሙት ላይ ሁነን ለመቶበት አንዴ ገብተንበታል በሚል አስተሳሰብ የብስ በወንጀል ላይ ወንጀል እየደራረብን ነዉ፡፡ነገ ይሄን ዛሬ ሞቻችንን ሳናቀዉ በጊዜያዊ ደስታ ዱንያችንን  አኼራንም እያጣን ነዉ...እስኪ ዝሙት የሚሰራዉ በአራጣ በቁማር ወንጀል ላይ የነበረዉ ኪፊል  ለሊት ሙቶ አደረ አላህም ተዉበቱን ተቀበለዉ በምን ይሆን ተዉበተን የተቀበለዉ??እስኪ የሀቢቡና ሙሀመድ የተናገሩትን ሀዲስን ልጋብዛችሁ



ዐብደሏህ ቢን ዑመር(ረ.ዐ)እንዳወሩት እኔ የአላህ መልዕክተኛ ﷺ  ከሰባት ጊዜ በላይ እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ:-

    በበኒ አስራኤል ውስጥ ኪፍል የሚባል ሰው ነበረ:: ይሄ ሰው ማንኛዉም ወንጀል በመሥራት ይታወቃል። አላህን የማይፈራ የለየለት ሙጅሪም ሰው ነበረ፡፡ ያገኘውን ሀጥያት የሚሠራ ሰው ነበረ፡፡

አንድ ቀን አንዲት ሴት ተቸገረችና (መቼስ አላህ ድህነትን ያላለጠበት ሰው ፈተናው ከባድ ነውና) እርሱ ጋ መጥታ ገንዘብ ጠየቀችው፡፡ እርሱ ሃብታም ሰው ነበር፡፡ ወንጀል የሚባል ግን አንድም የቀረው ነገር የለም፡፡ ከዚያም ስድሳ ዲናር ሊሰጣትና እርሷ ደግሞ ለዚና እራሷን ልታመቻችላት ዘገድ እነጋገራት፡፡ እንግዲህ አስቡት! በዚያን ጊዜ 60 ዲናር ማለት  በጣም ከፍተኛ ብር ነው፤ በኃይለኛው ያማልላል፡፡

ይህች ሴትም ፈቃደኛ ሆነች  ተቸግራለችና ድህነቱ አስገደዳት)፡፡ ከዚያም ስድሳወጣም ዲናር ሰጣት፡፡ ከዚያም እርሷ እራሷን አመቻቸች፡

እርሱም ዚና ለመስራት  እላይዋ ላይ ተቀምጦ ሳለ  ይህች ሴት ከመቅፅበት ተንቀጠቀጠች አለቀሰች😢 ተርገበገበች፤ ተንዘፈዘፈችና በኃይለኛውም አነባች፡፡
.... ኪፍልም ምን ነካሽ? ብዙ ገንዘብ አይደል እንዴ የሰጠሁሽ? አስገድጄሻለሁ እንዴ? በፍላጎትሽ አይደለም እንዴ? እናም ምን ሆነሽ ነው የምታለቅሺዉ?? አላት፡፡
....ከዚያም ይህች ሴት ወሏሂ! እኔ ይህንን የዚና ኃጢአት በዕድሜዬ እኮ ሠርቼው አላውቅም፤ ችግሩ አስገድዶኝ ነው እንጂ። ፈፅሞ ሠርቼው የማላውቀው ወንጀል ስለሆነ አሁን አላህን ፈርቼ ነው የማለቅሰው አለቸው፡፡ ......አርሱም አላህን ፈርተሽ ነው የምታለቅሺውን??
...... አላት፡፡ አዎ› አለችው፡፡

አስቡት አንግዲህ! ይሄ ዕድሜ ልኩን ወንጀል ሲሠራ የኖረ ሰው ነው፡፡ መች ይህ ብቻ እንድም መልካም ሥራ ሠርቶ አያውቅም፡፡  የዚህች ሴት ተቅዋና የርሷ መንቀጥቀጥ ልቡን ነካውና ወዲያው ይህንን ሁሉ ስድሳውን ዲናር ውሰጂው፡፡ እኔ አሁን ተወብት ገብቻለው እናም አልነካሽም ዚና አልሰራሽም፡፡ እኔ ካሁን ጀምሮ አበደን አላህን አልወነጅልም፡፡ ኃጢአት፣ ዝሙት፣ ፀያፍ ድርጊት የሚባል ነገር ካሁን ወዲያ ምንም አልሠራም፡፡ አንቺ ችግሩ እያለብሽ፣ ገንዘቡንም ለመውሰድ እየፈለግሽ ግን የአላህ ፍራቻው ገታሽ፡፡ አኔም ከዚህ በኋላ አላህን ፈፅሞ አላምፅም አለ፡፡


ከዚያም ነብዩ ﷺ እንደተናገሩት ይህ ሰው በዛቸው ለሊት ሞቶ አደረ፡፡ መሞቱም በበሩ ላይ ተፅፎ በተገኘዉ ፁሁፍ  ተረዳ፤ በአላህ መላእክት አማካኝነት፡፡


አላህ ለኪፍል ምሮታል የሚል ዐ.ነገር በበሩ ላይ ለየት ባለ ጽሑፍ ተፅፎ ተገኘ፡፡» (ቲርሚዚ ዘግበዉታል)


⚠️⚠️  ከዝሙት እንቶብት አሁን ዝሙትን መሥራት ውሃን የመጠጣት ያህል እና እጮኛን መያዝ ሻንጣን የመያዝ ያህል ቀላል በሆነበት ዘመናዊት ዓለም ውስጥ በመዘናጋት ያለተዉበት ሞትን እየጠበቅን ነዉ...ይቺ ነገ እንቶብታታለን ያልናት ቀን ነገ ሳትደርስ ሞት ቀድማን ከነገ ወዳ ያለዉን የአኼራ ህይወት  የቀብር ህይወት የነኪርና ነኪር ጥያቄ ...አላህ ፊት ያለ አስተርጓሚ ለጥያቄ ለመቅረብ  ምን ያህላችን ዝግጁዎች ነን??
ምን ያህሎቻችን ለመቶበት ዝግጁዎች ነን??


ሼር በማድረግ ኢስላማዊ ግዴታዉን ይወጡ..በዚህ ፁሁፍ የተነሳ አንድ ሰዉ ቢቶብት ትልቅ ነገር ነዉና...


join👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
ድል ያለ ሰርግ ተደግሶ ባል እና ሚስት ቃለ መሀላ ለመፈጸም እየተዘጋጁ ሳለ ነው ባል ቃል ከመግባታችን በፊት መናገር የምፈልገው ነገር አለ በማለት ማይኩን የተቀበለው።

ቀጠለናም የታሸገ ፖስታ ለሁሉም የሰርጉ ታዳሚዎች እንዲሰራጭ እና ታዳሚዎቹም ፖስታውን ከፍተው እንዲመለከቱት ያደርጋል፡፡ 

የታሸገው ፖስታ ውስጥ ያለው ሚስቱ ለመሆን ቃለመሃላ ለመፈፀም እየተቁነጠነጠች ካጠገቡ የቆመችው ሴት እና አንደኛ ሚዜው የኔ ፍቅር የኔ ውድ እየተባባሉ ሲማግጡ የሚያሳይ ፎቶ ነበር፡፡ 

ሙሽራው አሁንም ማይኩን እንደያዘ  “በፎቶው ላይ የምትመለከቱት ምስል ውዷ እጮኛየ እና የልብ ጓደኛዬ ማንም አያየንም ብለው ተደብቀው ሲማግጡ የሚያሳይ ነው። ታዲያስ  ከእንደዚች አይነት ሴት ጋር ትዳር ባልመሰርት የሚፈርድብኝ አለ?!"ብሎ ታዳሚውን ጠየቀ።መልስ አላገኘም።

ኋላም ሙሽሪት በድንጋጤ በቆመችበት ደህና ሁኚ ብሏት ከቤተሰቦቹ ጋር የሰርጉን አዳራሽ ጥሎ ወጥቷል፡፡
☞ የዴይሊ ሜይል ዘገባ ነው

#ከዝሙት እንጠንቀቅ እንቶብት...ዝሙት ዛሬም ነገም ከነገ ወዳም መዘዙ ሰፊ ነዉ፡፡ለ15 ሰከንድ የሀራም እርካታ የ40 የ50 አምት ፕላናችንን አናበላሽ፡፡
አላህን አምፀን አላህ በዱንያ ዋጋችንን ያስከፍለናል ብድር በምድር‼️

ነገ እኛም በዝሙት ላይ ያለን እኛን በምን እንደሚያዋርደን አይታወቅም፡፡

ወላሂ ዝሙተኛ ሰዉ ሰላም የለዉም...በዱንያ ድህነት ጭንቀት ነዉ፡፡ሴቷም እራሷን ዝቅ ታደርጋለች.ዝሙተኛ ሴት ቤተሰብ የማያቃት ሴተኛ አዳሪ ማለት ነች..ለምን ዚና ስትሰራ ቤተሰቧ ሳያያት ነዉ፡፡ልጄ ጎበዝ ናት ዲነኛ ናት ይላል ቤተሰብ..እሷ ግን ቤተሰብ የማያቃት ሴተኛ አዳሪ ነች


ለሌሎች ያካፍሉ
join👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
#አይነስዉሩ_ልጅ
አሚር ሰይድ

አንድ ሰውዬ ነበር ሁለት ልጆች አሉት በዲኑ ላይ ብዙም አይደለም፡፡ብዙን ጊዜ በሰዎች በማሾፍና በማላገጥ የተጠመደ ነው።አንድ ቀን መንገድ ላይ የሚሄድ ዐይነ ሥውር አጋጠመው ሰዎችን ሊያስቅበት ብሎ ከጎኑ  እየሄደ በዚህ ሰው ማላገጥ ጀመረ፡፡በዚህን ጊዜ ዐይነ ስዉሩ ሰው ልቡ ተሰበረበ እጅጉ😔ተሰማው፡በውስጡ ያለውን ደግሞ አላህ ይወቅ፡፡ከወራት በኋላ ይህ ሰው ዐይነ ስውር የሆነ ልጅ ተወለደለት፡፡ በዚም የተነሳ ተደናግጦና ሃሳብ ገብቶት ከዚህ ልጅ ጋር ግንኙነቱን አቋረጠ፡፡ እሱን ትቶ ለሌሎቹ ሁለት ልጆች ትኩረት ሰጠ፡፡ አዲሱን ልጁን ለእናቱ በመተው የሚያስፈልገውንም ወጭ ለሷ መስጠት ያዘ።ሆኖም ግን ውስጡ በእጅጉ ተጎድቶ ነበር፡፡ ይህ ልጅ ለመጥፎ ድርጊቶቹ መቀጫ ይሆን ዘንድ የተላከበት መሰለው፡፡የአባትነትን ፍቅር ለልጁ ነፈገዉ


ህፃኑ ልጅ ስድስት ዓመት ሞላው።አንድ ቀን እናት ከሁለት ልጆቹ ጋር ወጣ ብላ ስለነበር አባት ከዐይነ ስውር ልጁ ጋር ብቻውን ቤት ውስጥ ቀረ፡፡ቀኑ ጁሙዓ ነውና ልጁ አባቱ ወደ መስጊድ እንዲወስደው ጠየቀ፡አባት የስድስት ዓመት ልጁ የሚሰግድ መሆኑን ባወቀ ጊዜ ደነገጠ፡ከዚህ በፊት መስጅድ ይወስደው የነበረ ማን እንደሆነ ጠየቀው። ልጁም እናቱ እንደሆነች ነገረው፡፡ አባት ልጁን ወደ መስጅድ ይዞት መሄድ ጀመረ።

አንድ የሚያውቀው ትልቅ ሽማግሌ ይዞ የሚሄድ ዓይነት ተሰማው። ልጁ ከቁርአን የአል ከህፍን ምዕራፍ እያነበበ ነበር፡፡ አባት ይህን ሲሰማ ማልቀስ ጀመረ፡፡ በልጁ ሰበብ አላህን አወቀ፡፡ ልጁ በቃሉ ቁርኣንን መሸምደዱ ገረመው፡፡

ስብራቱ የነበረው ልጅ በዚህ መልኩ ወደ ፀጋ የተለወጠ ሆኖ አገኘው:: ሱብሀነሏህ፡
ትበድልና  ይሰብርሃል፡፡ ትግጎዳለህም፡፡ወደሱ ተጠግተህ በለመንከው ጊዜ ግን ስብራቱን ወደ ፀጋ ይለውጥልሀል፡፡
💚እናትነት ይህ ነዉ
🔴🔉🔉ታላቅ የምስራች ተጅዊድን መማር ለምትፈልጉ ተማሪዎች🟡📢📢

🔊
#ዚክራ_ኦንላይን_የቁርአን_ማእከል
የተጅዊድ ትምሀርት  ይዞላችሁ መጥቷል

🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘🔘

   
#የሚሰጠው_ኪታብ📚
البرهان في تجويد القرآن📚

    
#የሚሚሰጡ_ትምህርቶች📜📜

🔶
#የቁርአን አነባበብ ህጎች
🔶
#የቁርአን መጀመሪያና ማቆምያ ህጎች
🔶
#የፊደላት መውጫ (መኻሪጁል ሁሩፍ
🔶
#የፊደላት ባህሪያት (ሲፋቱል ሁሩፍ)
🔶
#የኑነ ሳኪና ወተንዊን ህጎች
🔶
#የመድ (የመሳብ) ህጎች
🔶
#የ ''ሯ'' ህጎች
🔶
#የሚመሳኪና ህጎች
🔶
#የሀምዘተል ወስል እና ቀጥእ ህግ
🔶
#የኢድጋም ህጎች
🔶
#የቀልቀላ ህጎች

📚📚📚📚📚
#የትምህርቱ_አሰጣጥ📘📕

1,በዙም አፕልኪሼን
2,በቴሌግራም አፕልኬሽን
    
       
#የቆይታ_ጊዜ 🕙

በሳምንት 4 ቀን


#ትምህርቱን_ለመከታተል_የሚያስፈልጉ

🔹ዋይፋይ(ፈጣን ኔትወርክ)
🔸ስማርት ስልክ

ይህን ሁሉ ደርስ በ #500 ብር ብቻ ይማሩ

ለመመዝገብ
👇👇👇👇
@zikra0835


👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.tg-me.com/zikraquran



   በተጨማሪም
👉 ቁርአንን በተጅዊድ ማንበብ
👉  ለጀማሪዎች ቃኢዳ
👉  ሀዲስ እና የአቂዳ ኪታቦችን በግል(VIP)  እና በግሩፕ እናስቀራለን።
በግል ለመመዝገብ
https://www.tg-me.com/+251931800835

#ዚክራ_የቁርአን_መድረሳ
#ምድራዊውና_ዘልዓለማዊው_ዓለም

ኢብኑ መስዑድ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ “በርግጥ አላህ ሲሳያችሁን በመካከላችሁ እንዳከፋፈለ ሁሉ ሥነ-ምግባራችሁንም በመካከላችሁ ከፋፍሏል፡፡ አላህ ለሚወደው ሰውም ሆነ ለማይወደው ሁሉ ሁበት ይሰጣል፡፡ ሃይማኖትን ኢስላምን ለሚወደው ሰው ካልሆነ በስተቀር አይሰጥም፡፡
አላህ ሃይማኖት የሰጠው ሰው በርግጥ አላህ ወድዶታል፡፡


ነፍሴ በእጁ በሆነችው ጌታ እምላለሁ! የአንድ የአላህ ባሪያ ልብና ምላስ ኢስላምን በወጉ እስካልተቀበሉ ድረስ ኢስላምን አይቀበልም፡፡ ጐረቤቱንም ከችግሮቹ ካልጠበቀ አያምንም፡፡" ሰዎችም "የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ችግሮቹ ምንድን ናቸው?" ሲሉ ጠየቋቸው፡፡ እሳቸውም “ተንኮሉና በደሉ ናቸው፡፡ አንድ ሰው ገንዘብ አያግኝ፡ በእሱም ይባረክለት ዘንድ ያገኝ ዘንድ ከእሱ አይመፅውት፡፡ ከበስተጀርባውም አይተወውም፡፡ ይህ በራሱ ወደ እሳት የሚከተው ካልሆነ በስተቀር፡፡ አላህ መጥፎ ነገርን በመጥፎ አያጠፋም፡፡ ነገር ግን መጥፎ ነገርን በመልካም ነገር ያጠፋል።"

አሚር ሰይድ



join👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
#በታሪክ_ትልቁ_ሶላት_አልጀናዛ


 
ሱልጧን ሱለይማን አልቃኑኒ ከእለታት በአንዱ ለሊት
አንድ ህልም አዩና ተደናግጠው ከእንቅልፋቸው ተነሱ
የቅርብ ዘባቸውን ተጣርተው
ፈረስ እንዲያዘጋጅላቸውና ሲነጋ ጎዳና ላይ ወጥተው
የህዝቡን የቀን እንቅስቃሴ ማየት እንደሚፈልጉ አስረዱት
ከነጋ በኋላ በተዘጋጀላቸው ፈረስ ብቻቸውን ጎዳና ላይ
በመውጣት የህዝቡን እንቅስቃሴ መቃኘት ጀመሩ በዚህ
መካክል አንድም ሰው ያልተከተለው አንድ አስከሬን
በጎዳናው ላይ ሁለት ሰዎች ብቻ ወደ መቃብር ሲወስዱት
ተመለከቱ
ሱልጧን ሱለይማንም ቀርብ ብለው ይሄ ብቻውን ወደ
መቃብር የሚሸኘው አስከሬን የማነው? ብለው ሲጠይቁ
ይሄማ ዝሙተኛና ኸምር ጠጪ ከሚስቱ ውጭ ልጅም ሆነ
ቤተሰብ የሌለው ግለሰብ አስከሬን ነው ስለዚህ የዚህን
ዝሙተኛ እና መጠጥ ጠጪ አስክሬን ማንም ሰው
ሊሸኘውና ሊሰግድበት ፍቃደኛ የሆነ ሰው የለም ይሏቸዋል
ሱልጣን ሱለይማንም በጣም ይቁጡና ይሄማ እንዴት
ይሆናል የሙሀመድ ኡመት አይደለምን? ይሉና አስከሬኑን
ተሸክመው ወደ ባለቤቱ ይመልሱታል
እዛም እንደደረሱ ባለቤቱ እጅግ አዝና ታነባለች ሱልጣኑም
በመገረም እንዴት እንደዚህ ታለቅሻለሽ ባለቤትሽ
ዝሙተኛና ጠጪ አልነበረም አንዴ? ይሏታል
የሟች ሚስትም የሚጠይቃት ሰው ሱልጣን ሱለይማን
መሆናቸውን አታውቅም
ባለቤቴ አላህ ይዘንለትና አላህን የሚፈራ ነበር ልክ
እንደሱ አላህን ፈሪ ልጅ ይመኝ ነበር ነገር ግን ሞት
ቀደመው ትላቸዋለች
ሱልጣኑም ባለቤትሽ ከዝሙተኝነቱና ከጠጪነቱ ውጭ
ምን የተለየ ነገር ይሰራ ነበር ? ይሏታል
ሚስትም ባለቤቴ ሁልጊዜም በእየመንደሩ እየዞረ መጠጥ
ወደሚገኝበት ቦታ በመሄድ መጠጦችን በብዛት በመግዛት
ወደ ቤት ያመጣና ግቢ ውስጥ ባዘጋጀው ጉድጓድ ውስጥ
ይደፋውና አልሀምዱሊላህ ዛሬ ለብዙ ሙስሊም ወጣት
ወንድሞቼ ብዙ ወንጀልን ቀነስኩላቸው እያለ ጌታውን
ያመሰግን ነበር
በማስከተልም ሁልጊዜ ምሽት በሆነ ቁጥር ወደ ሴተኛ
አዳሪዎች መንደር በመጓዝ ለብዙ ሴተኛ አዳሪዎች ዝሙት
ሰርተው የሚጋኙትን ሙሉ የቀን ገቢያቸውን ክፍያ
ከሰጣቸው በኋላ ወደቤታቸው እንዲመለሱ ያደርግና እቤቱ
መጥቶ አልሀምዱሊላህ ዛሬ ለብዙ ሙስሊም ወጣት
ወንድሞቼ የዚናን ወንጀል ቀነስኩላቸው እያለ ጌታውን
ያመሰግን ነበር
እኔም ሰዎች ከላይ የምትሰራውን ብቻ ነው የሚመለከቱት
አንድ ቀን መሞትህ አይቀርም ያኔ ጀናዛህን አጥቦ ሶላተል
ጀናዛ የሚሰግድብህና የሚቀብርህ አንድም ሰው አታገኝም
እለው ነበር
እሱም እያሰቀ ጀናዛየን ሱልጣን ሱለይማን አጥቦ በጀናዛየ
ላይም ሱልጣን ሱለይማን ከእነ ሰራዊቱ ከእነ
ምኒስትሮቹና ከታላቅ የሀገሪቱ ሼኮች ጋር ሆኖ የሀገሪቱ
ሁሉም ሙስሊሞች ሲሰግዱብኝ ታያለሽ እያለ ይነግረኝ
ነበር በማለት የባሏን የህይወት ታሪክ አጠገቧ ለቁመው
ሰው ትነግረዋለች
ሱልጣን ሱለይማንም ከልቡ በማልቀስ አዎ ልክ ነው እኔ
ሱልጣን ሱለይማን ነኝ እኔው እራሴ ጀናዛውን አጥበዋለሁ
ይለና የዚህን ምርጥ የአላህ ባሪያ ጀናዛ እራሱ ካጠበ
በኋላ
ለሀገሪቱ ሙሉ ሰራዊት ለሀገሪቱ ሙሉ ባለስልጣናት
ለሀገሪቱ ሙሉ መሻኢኾች ለሀገሪቱ ሙስሊሞች በሙሉ
ትዕዛዝ በማስተላለፍ በዚህ የአላህ ባሪያ ጀናዛ ላይ
እንዲገኙ በማድረግ ሱልጧን ሱለይማን አልቃኑኒ በታሪክ
ትልቁን ሶላተል ጀናዛ በዚህ ድንቅ የአላህ ባርያ ላይ
አሰገዱ።
ውጭ ላይ ለእኛ በተገለጠልን ነገር ላይ ብቻ ተመርኩዘን
የአላህን ባሮች መለካት መመዘን ደረጃን መስጠት ከባድ
ነገር ነው ከእኛ እውቀትም ውጭ ነው...


በዚህ አስተማሪ ታሪክ ብዙዎች ሊማሩበት ይችላሉና ለወዳጅ ዘመዶችዎ  ሼር ሳያደርጉ አይለፉ!!


ለሌሎች ያካፍሉ
join👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
🔰#የሙስሊሞችን_ሥጋ_የተመገበው_የእንግሊዙ_መሪ_ሪቻርድ


   አውሮፓውያን "የአንበሳ ልብ" ሲሉ ያሞካሹታል። ታሪኩን በሚገባ ያወቁት ደግሞ “የአሳማ ልብ ባለቤት” ብለው ይጠሩታል። እርሱ አያቶቹ መስቀላዊያን በይተል መቅዲስን በተቆጣጠሩ ጊዜ ያደረሱትን በደል በአካ ከተማ የደገመው ሪቻርድ ነው። 
   ከግብፅ እስከ ዱባይ ከቦሊዩድ እስከ ፎረስት ጋምብ ጸሐፊዎች ገፃቸውን፣ ዳይሬክተሮች ስክሪብታቸውን ፕሮዲዩሰሮች ፊልሞቻቸውን በስሙ አስውበውበታል። በጀግንነት እያወደሱ ስብእናውን እያገነኑ አውስተውታል። ግና እርሱ ሙስሊሙን ጀግና ፈረሰኛ ኢሳ አል አዋምን ወደ ክርስቲያን ጦረኛ የቀየረ፣ የሙስሊሞችን ስጋ የበላ ሙስሊም ጠሉ ሪቸርድ ነው።
"ከቀናቶች በአንደኛው ቀን ምግብ ሰሪ አገልጋዩን ለምሳ ትኩስ የአሳማ ሥጋ እንዲያቀርብለት አዘዘ። ጣፋጭ አድርጎ እንዲሰራለትም ተናገረ። ምግብ ሰሪው አሳማ የት ሀገር እንደሚገኝ አያውቅም። ቢፈልግም ማግኘት አልቻለም። ከየት ያምጣ ግራ ገባው።  በምግብ ጠረጴዛው ላይ የአሳማ ስጋ ከሌለ መገደሉ አይቀሬ ነውና ተጨነቀ። አንድ መላ ዘየድ። ሁለት ሙስሊም እስረኞችን አረደና ስጋቸውን አብስሎ ጠረጴዛው ላይ አስቀመጠ😔። የምሳ ሰአት ደረሰ። ንጉስ ሪቻርድ ምግቡን መብላት ጀመረ። ተመግቦ እንዳበቃ በጥፍጥናው ተገረመ። የሰራለትን ሰው አመሰገነ ግና ስጋው የአሳማ አለመሆኑን ተገነዘበ። ምግብ ሰሪውን አስጠራና  "የአሳማውን ጭንቅላት አምጡ" ሲል አዘዘ።
   ምግብ ሰሪው ምን ያርግ? ምንስ ይበል?! ምላሱ ተኮላተፈ። በእጅጉ ተሸበረ። በፍርሃት ራደ። በድንጋጤ ተንቀጠቀጠ። በመጨረሻም እውነቱን ለማሳየት ወሰነ። የታረዱትን የሁለቱን ሙስሊም ምርኮኞች ጭንቅላት ወደ ሪቻርድ ማምጣት ነበረበትና ፊት ለፊቱ አቀረበ።
ሪቻርድ ቅንቅላቶቹን ሲመለከት በሳቅ እና በደስታ ቦረቀ። እንዲህም አለ:- "ስልሳ ሺህ ሙስሊም እስረኞች እስካሉን ድረስ የአሳማ ሥጋ ከእንግዲህ አንፈልግም እነሱን እያረዳችሁ አቅርቡልኝ ስጋቸው ጣፋጭና ጥዑም ነው" አለ።
ሰላሐዲን አልአዩቢ ሙስሊም ምርኮኞቹን እንዳይገድል ሠላሳ መልዕክተኞችን ላከ። ግና ሪቻርድ ሠላሳዎቹንም መልዕክተኞች ገድሎ ስጋቸው ተጠብሶና ተቀቅሎ እንዲመጣ በማድረግ ለጓደኞቹ የክብር መስተንግዶን አዘጋጀላቸው። ጭንቅላታቸው ተቀቅሎ እንደመረቅ ቀረበ።
በአካ ከተማ ሀያ ሺህ በሌላ ዘገባ ስልሳ ሺህ ሙስሊሞችን ጨፈጨፈ። ወንዶች ከከሴቶች ሳይለይ ህፃን ከአረጋውያን ሳይመርጥ አረደ። በርካቶችን ማርኮ አረደ። ብዙዎችን በቁማቸው ቀበረ"
   ይህ ነው የሙስሊሞችን ሥጋ ተመጋቢው ሪቻርድ።


ምንጭ-
                  البداية والنهاية
                  النوادر السلطانية والمحاسن اليوسفية
Mahi mahisho


ለሌሎች ያካፍሉ
join👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
🔥#በዝሙት_በሽታ_የተበከለ_ትዉልድ🔥🔥
        
           🔰 #ምዕራፍ አንድ ➊
                አሚር ሰይድ

ነሀሴ 23/12/2016 ተጀመረ
╔══════════════════════╗
              #ዝሙትና_የሚያመጣዉ_መዘዝ
╚══════════════════════╝



   #በመጀመሪያ ደረጃ ይሄን ተከታታይ  ፁሁፍ ሼር አድርጋችሁ ለብዙ ሙስሊም ወንድም እህቶች እንዲደርስ በአላህ ስም እጠይቃችሆለሁ አይታወቅም በዚህ ተከታታይ ፁሁፍ የአንድ ሰዉ መቶበት ከአላህ ዘንድ ሼር ያደረገዉም የወንጀላችንን መማሪያ ሊሆን ይችላልና፡፡በተጨማሪ ቻናል ያላችሁ ይህን ፁሁፍ በታስተላልፉት ብዙ ሰዉ ይማርበታል፡፡ፀሀፊ አሚር ሰይድ የሚለዉን አጥፍቶ መፓሰት ይቻላል፡፡አላማየ ለማስተማር እና ተደራሽነቱን ለማስፋት ነዉ፡፡

ይህን ተከታታይ የሆነ ፁሁፍ ሳዘጋጅ ከእናንተ የተሻልኩ ሁኜ ሳይሆን ከአበብኩት ከሰማሆቸዉ ተንተርሼ ነዉ...ይህ ፁሁፍ 65%የተዘጋጀዉ በዝሙት መዘመን ስልጣኔ ወይስ የአለም ፍፃሜ ምልክት ከሚለዉ መፅሀፍ ሲሆን 35%ደግሞ ከሌሎች መፅሀፎችና በራሴ የጨመርኳቸዉ የተሻሉ አመለካከቶች ተሰናድተዋል፡፡በዝሙት መዘመን የሚለዉን መፅሀፍ ገዝታችሁ ብታነቡት በጣም ትምህርት ትወስዱበታላችሁ፡፡ይህ መፅሀፍ 408 ገፅ ያለዉ ሲሆን በ2009 ዓም የተፃፈ ነዉ ጥቅሙ ግን ብዙ ነዉ

🔰ይህ ፁሁፍ ሲዘጋጅ በጣም ፈታኝ ነበር ከ408ገፅ ተለቅሞ የተፃፈ እና ኦርደር ለማደረግ ፈታኝ ነበር በምናነበዉ ተጠቃሚ ያድርገን

አሁን ያለነዉ ማህበረሰብ ብዙ ሰዉ ዝሙትን ዉሀ የመጠጣት ያህል ቀላል አድርጎ ይዞታል፡፡በዚህ ፁሁፍ ማንበቡና ለሌሎች ሼር ማድረጉ ብዙ ጠቀሜታ አለዉ፡፡ፁሁፉን ለማዘጋጀት በጣም ብዙ ቀናት ፈጅቻለሁ ለምን የዝሙት ጉዳይ በጣጣጣም አሳሳቢ ላይ ደርሷል...የሀይማኖት አባቶችም ስለዝሙት በአደባባይ ማስተማር እስከሚፈሩ ድረስ ዝሙት በየቤቱ በር አንኳክቷል በተለየይ አዲስ አበባ ላይ ዝሙት ከቁጥር ዉጭ  ሁኗል በዝሙት ከአፍሪካ አንደኛ ከአለም አራተኛነትን ደረጃ ላይ ነች፡፡
ኢትዮጲያ ሙስሊሙም ክርስቲያኑም ሀይማኖተኛ ነኝ በሚልባት ሀገር ዝሙትግን በጣም ተንሰራፍቷል ከቁጥጥር ዉጭ ሁኗል፡ቤተሰብና ሴት ልጅ ሳይተዋወቁ እየኖሩ ይገኛሉ፡፡አላህ ለሁላችንም ይድረስልን፡፡

                  እነሆ ወደ ፁሁፉ

ዝሙት ማለት በቀላል ቋንቋ አንድ አላህን የማይፈራ ኢማን የሌለዉ ወንድ አላህን የማትፈራ አጂ ነብይ የሆነች ሴት ማህፀን ዉስጥ በሀራም ግንኙነት ጊዜያዊ ደስታ ፈጥሮ..የዱንያም ለአኼራም ፈተና ላይ መዉደቅና ነገ ጀሀነም ከሚገቡት ሰዎች መሰለፍ ማለት ነዉ

ዝሙት የአላህን ቁጣ እንደሚያመጣ ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡- በአንድ መንደር ዉስጥ ዝሙትና ወለድ ይፋ ከወጡ እነርሱ የአላህን ቁጣ በራሳቸዉ ላይ አድርገዋል(አልሀኪም ዘግበዉታል)

☞በሌላ ሀዲስ ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል ከሺርክ ቀጥሎ ያለዉ ሀጥያት ባልተፈቀደለት ማህፀን ዉስጥ በሰዉየዉ የተረጨ የወንዱ የዘር ፈሳሽ ነዉ፡፡



☞በሌላ ሀዲስ ሰይዲና ሙሀመድ ﷺ እንዲህ ብለዋል
ብእርግጥ እኔ ለናንተ እምፈራላችሁ ርካሽ ስሜቶችን ነው:: በሆዳችሁና በብልቶቻችሁ ምከንያት የሚፈጠሩ አጥፊ ስሜቶቻችሁን ነው፡፡ (አሕመድ) ብለዋል፡፡


     በዘመናችን በርካታ የተዛቡና በካይ የሆኑ አስተሳሰቦች ብዘዎች ዘንድ በተለይ ወጣት ማህበረሰቡ ላይ ተይዘዋል፡፡Sex is Life»! «Sex is Free» «Sex is Gift from God! ወዘተ የሚሉት በዋናነት ይጠቀሳሉ፡፡በርግጥ ኢስላምም የከለከለው ወሲብን ሳይሆን ዝሙትን ነው፡፡ ማንኛውም ሕጋዊ ወሲብ ከሀላል ሚስቱ ጋር በኢስላም አልተከለከለም፡፡ነገር ግን ወሲብ በሚል ሽፋን አብዛኛው ወጣት ዝሙትን እንደ መዝናኛ ይዞታል።ከዚህም የተነሳ ለዝሙትም የወሲብን ስያሜ በመስጠት ከአስተሳሰብ ጀምሮ ብዙ ሰዎችን በዝሙት ባሕር ውስጥ ለማስመጥ ተችሏል፡፡

ሀቢቡና ሙሀመድﷺ እንዲህ ብለዋል፦

#ሙስሊሞች_ሆይ! ዝሙትን ተጠንቀቁ ራቁት፡፡ እርሱም ስድስት ጉዳቶችን ያስከትላል፤ ሶስቶቹ በዚህ ዓለምና ሌሎቹ በቀጣዩ ዓለም ሲሆኑ፡፡

#ዱንያዊ ጉዳቶቹን በተመለከተ
➊ የፊት መገርጣት/መደብዘዝ፣
➋አጭር ዕድሜና
➌ረጅም ድህነት ናቸው

#የቍጣዩ ዓለም ጉዳቶቹ ደግሞ
➊የአላህን ቁጣ መውረስ፣
➋ጥብቅ (ኮስተር ያለ) ምርመራና
➌በእሳት ውስጥ መቀጣት ናቸው፡፡»(ኢብን ዐዲይ)

     ዝሙት በርካታ ዓለማዊና አኼራዊ ጉዳቶችን ያስከትላል፡፡ መዘዙና አስከፊነቱ ከፍተኛ ነው፡፡ ዝሙት ለተለያዩ በሽታዎች ይዳርጋል፡፡ከነዚህም መካከል
☞ኤችአይቪ/ኤድስ የዝሙት አብይ ጉዳት መሆኑ አይካድም
☞ዝሙት ለውርጃ ይዳርጋል፡፡
☞ ዝሙት ለአስከፊው የሴተኛ አዳሪነት ሕይወትና ለሴሰኝነት ይዳርጋል፡፡
☞ዝሙት ከትዳር ያርቃል
☞ ዝሙት ለትዳር አለመረጋጋትና ለቤተሰብ መበታተን አብይ መንስኤ ነው::
☞ ዝሙት ለተለያዩ ደባል ሱሶች ይዳርጋል፡፡
☞ዝሙት አባቶቻቸው የማይታወቁ ልጆች በማህበረሰቡ ውስጥ እንዲበዙ ያደርጋል
☞ዝሙት ድህነትን ያስወርሳል፡፡
☞ዝሙት በረካን ይነሳል፡፡
☞ ዝሙት ሰብአዊ ክብርን በመግፈፍ እንስሳዊ ባህሪን ያላብሳል፡፡


   ዝሙተኛ ወንድ ዝሙተኛ ሴትን ዳግም ሊያገኛት ይችላል፤አንድም ድርጊቱ ስርቆት ስለሆነ የተገኘውን አጋጣሚ በመጠቀም በአነቃቂ መድሀኒቶች በርካታ ዙሮችን ይሄዳል።በተለይ አሁን አሁን ወንዱ ዝሙተኛ የተለያዩ የወሲብ ማነቃቂያ ዕፆችን በመጠቀም የወሲብ ጀብደኛ ለመሆን ይፈልጋል፡፡ በብልግናው ዘርፍ የወሲብ ጀብደኛ ማለት ደግሞ በሕገወጥ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ላይ ረጅም ሰዓትን የሚያሳልፍ ሰው ማለት ነው፡፡ነገር ግን ከኢስላማዊ አስተምህሮት አንፃር ዝሙተኛው ዝሙትን በሚፈፅምበት ጊዜ ኢማኑ ከልቡ ውስጥ ወጥቶ ከላዩ ላይ ያንጣልላል፡፡የዚህም ምሳሌ ልክ አንድ ሰው ሸሚዙን አውልቆ እንደሚሰቅለው ማለት ነው፡፡ይህም ማለት ግለሰቡ በዝሙት ድርጊት ላይ ረጅም ጊዜን የሚያሳልፍ ከሆነ ኢማኑ በልቡ ውስጥ የሚቆየው ለአጭር ጊዜ ብቻ ይሆናል፡፡ ልክ እንደዚሁ ይህንኑ ፀያፍ ድርጊቱን አብዝቶ የሚደጋግም ከሆነ ኢማኑም በዚያው ልክ በተደጋጋሚ ከልቡ ውስጥ ወልቆ ከላዩ ላይ ያንጣልላል፡፡ይህ እንግዲህ ዝሙትን መሥራት፣ በዝሙት ጀብደኛ መሆን፤ ዝሙትን እንደ መዝናኛ የመውሰድ አባዜ፣በዝሙት መዘመንና ዝሙትን የሕይወት ልማድ አድርጎ መያዝ ምን ያህል በኢማን መጫወት እንደሆነ ያሳየናል፡፡
ምክንያቱም
ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺዝሙተኛ ዝሙትን በሚሰራበት ጊዜ እርሱ ሙዕሚን ሆኖ አይደለም ብለዋልና፡፡


    እንደሚታወቀው ዝሙት በራሱ ትልቅ ደዌና አደገኛ ሱስ ነው::ለሴሰኝነት ይዳርጋል፤እዚያም እዚሀም ያልከሰከሳል፡፡ምክንያቱም መንገድነቱ የከፋ ነውና፡፡ወደ ዝሙት ለመግባት ከባድ ነው፡፡ አንዴ ከገቡበት በኋላ ግን ለመደጋገም ቀላል ነው፡፡ በዚያው ልክ ለመተው ከባድ ነው፤ምክንያቱም ዝሙት አደገኛ ሱስ ነውና፡፡በዚህን ጊዜ የዝሙት ሱሰኛው ከሱስ መላቀቁ ይቀርና ወደባሰው እርከን ይሸጋገራል፡፡ቀማሽና አተራማሽ ይሆናል፡፡ከዚያም በኖርማል ወሲብ መርካት ይሳነዋል፡፡ቀጥሎም የወሲብ ፈልም ቅጥቅጥ ለመሆን ይሞከራል፡፡ ይህንኑ እውን ለማድረግ ደግሞ ልዩ ልዩ ሱስ አስያዥ ዕፆችን መጠቀም ይጀምራል፡፡ይህም በተራው ለተለያዩ ወሲባዊ እብደቶች አሳልፎ ይሰጠዋል፡፡ግለሰቡ የጥፋት ጎዳናን ተከትሎ ይሄዳል፡፡ከዚህም በላይ ከላይ ለመግለፅ እንደተሞከረው አንድ ሰው በማንኛውዏ ጊዜ ዝሙት ላይ ሲወድቅ ኢማኑም እንደዚያው ከልቡ ወልቆ በላዩ ላይ ማንጣለሉን👇👇👇
ይቀጥልበታል፡፡ ይህም እውነታ የዝሙትን ድርጊት እጅግ አደገኛና የማይወጡት የወንጀል አዙሪት ያደርገዋል፡፡ ለዚህም ነው «ዝሙትን አትቅረቡት» የሚባለው፡፡


 🌙🌙 ታላቁ ሊቅ ኢማም ኢብኑል ቀይም እንዲህ ብለዋል፡- ስሜትን ከዚና መቆጣጠር ምንዳው ጀነት ነዉ
ዩሱፍ (ዐ.ሰ) መጀመሪያ ባሪያ ነበር፡፡ የዓለም ግማሽ ቁንጅና እንደፈሰሰበት ይነገርለታል፡፡ እርሱን በባለቤትነት የያዘችው የባለሥልጣኑ ሚስትም በፍቅሩ ናወዘች፡፡ ለዝሙትም ገፋፋችው፡፡ እርሷ ውበትና ሥልጣን ያላት ሴት ናት፡፡ እርሱ ግን እምቢ አለ፡፡ ስሜቱንም ተቆጣጠረ፡፡ ከዚያም ተዶልቶበት ወደ ዘብጥያ ተላከ። ነገር ግን የኋላ ኋላ የግብጽ ገዥ (ዐዚዝ) ሆነ፡፡ ስሜቱን የሚቆጣጠር ሰው ምንዳ ይሉሀል ይሄ ነው::

አላህ ሱወ  በተከበረ ቁርአኑ ላይ በሱረቱል ናዚዓት ላይ እንዲህ  ብሏል
በጌታው ፊት መቆምን የፈራ ሰውማ ነፍሱንም ከዝንባሌዋ የከለከለ፤ ገነት እርሷ በእርግጥ መኖሪያው ናት፡፡ (አን-ናዝዓት፡40-41)
   ╔══════════════════════╗
     95%በላይ ሴቶች ይህን የሀቢቡና               ሙሀመድﷺሀዲስ በተደጋጋሚ ሰምተዉታል    ╚═══════════════════════

ማንኛዉም ሽቶን ተቀብታ በሰዎች ፊት የምታልፍና ከማዕዛዋ የምታደርግ ሴት እርሷ ዛኒያ(ዝሙተኛ)ናት፡፡
ግን ሽቶ ሳይቀቡ አይንቀሳቀሱም..ሴቶች ሆይ ማወቅ ያለባችሁ ግዴታ ሽቶ ብቻ ሳይሆን የምትቀቡት ፌር ጥፍር ቀለም  ሊፒስቲክ ቻፕስቲክ ሽታ ስላለዉ ሽቶ ጋር እንደሚካተት ልታቁ ይገባል፡፡


ዝሙት ስንሰራ አላህ እንደሚያየን ልናቅ ልንገነዘብ ይገባል፡፡አሏህ ሱወ አንዲት ቅጠል የምወድቅበትን ቦታ የሚያቅ ጌታችን ዝሙት ስንሰራ ጀሊሉ ፊት ወንጀል እየሰራን እንደሆነ ልናስተነትን ይገባል፡፡


አላህ (ሱ.ወ) ወንጀልን ለሚሰሩ ባርያዎቹ እንዲህይላል፦

እነርሱ ያንን ቀን ሩቅ አድርገዉ ያያሉ፡እኛም ቅርብ ሆኖ እናየዋዉለን(አል መዐሪጅ 6-7)
ሰአቲቱ እነርሱ የማያዉቁ ሆነዉ በድንገት ልትመጣባቸዉ እንጅ ይጠባበቃሉን(አል ዙህሩፍ 66)


⚠️ አንዲት ሴት ከብረ ንፅህናዋን መጠበቅ እንዳለባት ካላወቀች ለነገ ህልም ከሌላት ድንግልና ለጥብቅ ሴቶች የትዳር ዋስትና መሆኑን ካላወቀች ሀያዕ ከሌላት ህይወቷ በዝሙት ምክንያት ምስቅልቅሉ ይወጣል፡፡ ክብረ ንፅህናዋን ለመጠበቅ ደግሞ ሐያእ (የእፍረት ስሜት) ወሳኝ ባህሪ ነው፡፡ ሴት ልጅ ከሐያእ ከተራቆተች ለክብረ ንፅህናዋ ተገቢውን ከለላ አላደረገችም ማለት ነው፡፡
☞ከኢኽቲላጥ ከተቃራኒ ፆታዎች ልቅ ቅልቅል ካራቀች ለዝሙት መንገድ ከፍታለች ማለት ነው፡፡
☞ዕይታዋን ዝቅ ካላደረገች ለዝሙት መንገድ ከፍታለች ማለት ነው፡፡
☞ምላሷን መቆጣጠር ካልቻለች አሁንም ለዝሙት መዳረሻ መንገድ ከፍታለች ማለት ነው፡፡
☞ከምንም በላይ ሴት ልጅ ጆሮዋን ከዘፈን ካልጠበቀች ለዝሙት የመጋለጥ ዕድሏ ሰፊ ነው፡፡ እንደሚታወቀው ፆታዊ ፍቅር ወደሴቶች የሚገባው በዋናነት በጆሮ ሲሆን ወደ ወንዶች ደግሞ በዓይን ነው፡፡

ለወንዱም ቢሆን ዕይታውን መቆጣጠርና ዓይኖቹን ዝቅ ካላደረገ የዝሙት መዳረሻ መንገድን ተዳፈረ ማለት ነው፡፡
ጥብቅነቱን መጠበቅ እንዳለበት፣ አልያም አቅሙ ከቻለ ካልፆመ  ከተቃራኒ ጾታዎች ጋር ከተቀላቀለ የዝሙትን መዳረሻ መንገዶች ተዳፈረ ማለት ነው፡፡
ከሴት ጋር የርሷ መሕረም አጠገቧ በሌለበት ሁኔታ እሷ ጋር ከሆነ የዝሙት መንገድን ተዳፈረ ማለት ነው፡፡

በጥቅሉ ደግሞ ዝሙት ሐራምና መንገድነቱም የከፋ መሆኑን እያወቀ የሚያጠፋ፣ ትዳር የተቀደሰና የተባረከ ሕይወት መሆኑን፣ ከትዳር በፊት የወንድም ሆነ የሴት ጓደኛን መያዝ ሐራም መሆኑን የሚያዉቅ አዉቆ ጠፍ በዝሙት ላይ የመውደቅ ዕድሉ ሰፊ ነው፡፡ ስለዚህ የዚህ አዉቆ ጠፍ  ከዝሙት የመራቁ ጉዳይ ከባድ ነው፡፡

  ሰይዲና ሙሀመድ  ﷺ ዝሙትን ቀጥታ ከኢማን ጋር አያይዞታል፡፡ እንዲህም ሲሉ ተናግረዋል፡-

«ዝሙተኛው ዝሙትን በሚሠራበት ጊዜ እርሱ ሙእሚን ሆኖ አይደለም (የርሱ ኢማን ከርሱ ጋር የለም)፡፡» ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበዉታል፡፡

ዝሙት በምንም መልኩ አሁን በርካታ ወጣቶች እንደሚያስቡት የመዝናኛ ዓይነት ሳይሆን ቀጥታ ከኢማን ጋር የተያያዘ ነገር መሆኑን ነው፡፡ ስለዚህ ይህንን አለማወቅ በወንጀሉ ውስጥ ለመውደቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው፡፡

 ⚠️በኢትዮጵያ ሀገራችን የዝሙት ጉዳይ በጣጣም አሳሳቢ ጉዳይ ላይ ደርሷል ፡ከዚህ ቀደም የተደረጉ ጥናቶች እንዳመለከቱት ከአዳጊዎች መካከል ከ21.5%-24.8% የሚሆኑት በወሲብ ንቁ ናቸው፡፡ እንዲሁም የመጀመሪያ የግብረ ሥጋ ግንኙነት አማካይ ዕድሜ ከ15-16 ዓመት ነበር፡፡ ይህም ችግር ሥር የሰደደ ሲሆን የቅድመ ጋብቻ ወሲብ የማህበራዊ ጤና ችግር እየሆነ መጥቷል፡፡ አዳጊዎች በለጋነት ዕድሜያቸው ወሲባዊ መነሳሳቶች ውስጥ በሚገቡበት ጊዜ ያልታሰቡ በርካታ ማህበራዊ ችግሮች ይከሰታሉ፡፡ ለምሳሌ
☞ በአዳጊነት ውስጥ የእናትነት ሕይወትን መምራት፣
☞ለነጠላ ወላጅነት መዳረግ፣
☞ ለአባላዘር በሽታዎች መጋለጥ ናቸው፡፡


ግን እንደዚህ ሁነን ወደየት ወደየት እያመራን ነዉ???

🙄እኛ ኢትዮጲያን የነጃሺ ሀገር በአለም ሁለተኛ ሙስሊም የተቀበልን የኢትዮ ግማሽ ፐርንሰንት በላይ ሙስሊም ነን ..ዲነኛ ነን ኪታብ ቀርተናል ..መስጊድ ተነካ..ኢስላም ተደፈረ ..ወዘተ በምላስ እንላለን በጎን ዚና እንሰራለን ዚናን መከላከል አልቻልንም

ክርስቲያኖች ኢትዮ የሙሴ ፅላት አለ ..አርባ አራት ታቦት አለ ..ኢትዮ ገማደ መስቀሉ አለ ይሄን ያህል ገዳም አለን.. ኢትዮ የኛ ናት የክርስቲያን ደሴት ናት ይባላል በጎን ዚና እንሰራለን🤔ዚናን መከላከል አልቻልንም፡፡
   ወዴት እያመራን ነው? ያልተፈታ የዘመናችን እንቆቅልሽ ...


 #ሴት_ዝሙተኛ☞ አመንዝራይቱ፣ ሸርሙጣ፣ ሴተኛ አዳሪ፣ የቡና ቤት ሴት፣ ሸሌ፣ ባር ሌዲ፣ ወዘተ የሚሉትን አስቀያሚ ስሟ ነዉ፡፡
#ወንዱ ዛኒያም☞ ዝሙተኛ፣ ሂያጅ፣ አመንዝራ፣ ዘልዛላ፣ የወሲብ መንገደኛ፣ ወንድኛ አዳሪ፣ ወንድ ሸሌ፣ ሸርሙጣ፣ ወዘተ በመባል በሀገራችን ባህል ይጠራል
ዝሙተኛ ከመሆን ይጠብቀን..ዝሙት ላይ ያለነዉን እንደ ምንጭ ዉሀ ኩልል ያለ ተዉበት አላህ ይወፍቀን

⚡️#በቀጣይ_ክፍል በዝሙት እንዴት ሴቶች ጉዳት እንደሚደርስባቸዉ እንዳስሳለን

#ምዕራፍ
ይቀጥላል......

አስተያየት ካለ በዚህ ማቀበል ይቻላል👇
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot

ለሌሎች ማከፈልዎን አይዘንጉ
join👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የነብዩ ﷺ የዘር ሀረጋቸዉ

ጁምአ ሶሉ አላሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ💚

join👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
🔥#በዝሙት_በሽታ_የተበከለ_ትዉልድ🔥🔥
        
           🔰 #ምዕራፍ_ሁለት
                አሚር ሰይድ


╔══════════════════════╗
   በዝሙት ወንጀል ምክንያት የማይለቁ ችግሮች     
╚══════════════════════╝
 
#ሴቶችና_ዝሆኖች_ጠባሳቸውን_ፈፅሞ_አይረሱም
    

   ⚡️⚡️ ዝሙት ድህነትን ያስወርሳል፡፡ዝሙተኞች በድህነትና በበረከት እጦት ይሰቃያሉ፡፡ በሀዲሰል ቀዱስ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ማለቱን ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ
ነግረውናል፦ «እኔ አምባገነኖችን አጠፋቸዋለሁ፤ ዝሙተኞችንም በድህነት እቀጣቸዋለሁ፡፡»ብሏል ጌታችን አሏህ፡፡

     የዝሙት የመጀመሪያው ሥነ-ልቦናዊ ጉዳት ጭንቀት ነው፡፡ በልቡ ውስጥ የአተምን ከብደት ያህል ኢማን ያለው ሰው ዝሙትን ከሰራ በውጤቱም ምቾትን ከሚነሱት ስሜቶች ጋር ተቆራኝቶ ይቀራል፡፡ ይህም እርሱ የፈለገውን ያህል ከአላህ(ሱ.ወ) ምሕረትን ቢማፀንም ያው ነው፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት፣ ምንም እንኳን አላህ(ሱ.ወ)ለነዚያ ምሕረቱን ለሚለምኑት ቢቸራቸውም፣ ግና ያ አካላዊ ንኪኪው አይፋቅም፡፡ ትዕይንቱ ከአዕምሮው ጓዳና ከመረጃ ቋቱ አይሰረዝም፡፡ በተለይ ይህንኑ ፀያፍ ድርጊት በተደጋጋሚ የሠራ ሰው ከሆነ ከጌታው የሚያገኘው ምሕረት ወንጀሉን ቢያብስለትም ግለሰቡ ግን ኃጢአቱን አይረሳውም፡፡ ምክንያቱም ይህ ድርጊት የሌላን ሰው ክብር ጭምር ያካተተ ነበርና፡፡

ግለሰቡ የሚሠራው ዝሙት የአንድን ሰው ሴት ልጅ ያካተተ ነበር፡፡ በውጤቱም አርግዛለች አስወርዳለች፡፡ወይ እያለቀሰች ነዉና...ዝሙት የአንድን ሰው እህት፣ ሚስት ወይም እናትን ያካተተ ነበር፡፡ በተለይ ሴቷ ትዕይንቱን ፈፅሞ አትረሳውም፤ ምክንያቱም ሴቶችና ዝሆኖች ጠባሳቸውን ፈፅሞ አይረሱምና፡፡

ግለሰቡ ከወንጀሉ ቶበቶ ይበልጥ ወደ አላህ (ሱ.ወ) በተቃረበ ቁጥር ደግሞ ይኸው ቀጣይነት ያለው የጭንቀት ስሜት የበለጠ እያደገ ይመጣል፡፡ ምክንያቱም እርሱ ጌታውን የበለጠ ባወቀው ቁጥር ለጌታው የበለጠ ሐያእን ያዳብራልና፡፡ በዚህን ጊዜ ይበልጥ ከአላህ (ሱ.ወ) ፊት ምቾት የማይሰማው ሆኖ ይቀራል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ አንዳንዴ ዝሙትም ልክ እንደ ስርቆት ሁሉ በፍጥነት የመከሰት ዕድል አለው፡፡ ልክ ሌባ ማንኛውንም ለመስረቅ የሚያስችለውን አጋጣሚ ሲያገኝ በፍጥነት እንደሚጠቀምበት ሁሉ ዝሙተኛውም አንዳንድ ጊዜ በፍጥነት ፀያፍ ድርጊቱን ሠርቶ መሰወር ይፈልጋል፡፡ በመሠረቱ ዝሙትም ቢሆን ስርቆት እንደመሆኑ መጠን አንዳንድ ጊዜ በአሳፋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ይከሰታል፡፡ የመኪና የኋላ መቀመጫዎች ላይ፣ በጓሮ ውስጥ፣ በቤት ግድግዳ ሥር፣ በመፀዳጃ ቤቶች ውስጥ፣ በኢሊቬተሮች ውስጥ፣ በመንገድ ዳር፣ በህንፃዎች መካከል፣ በዛፎች ሥር፣ ወዘተ ይከሰታል፡፡ እንደዚህ ያሉ ቦታዎችና ሁኔታዎች ለአንድም የዝሙት ጥንዶች የበለጠ የፍቅር ወዳጅነትን ለመፍጠር በቂ አይደሉም፡፡ ዝሙተኞቹ መልካም ጊዜ ሊኖራቸውና ቁርኝታቸው ሊጠናከር አይችልም፡፡ በርግጥ ቀድሞ ነገር ግንኙነቱ ህገወጥ እንደመሆኑ መጠን ምንም ህጋዊ የሆነ ፆታዊ ትስስርና ወዳጅነት ማደግ የለበትም፡፡ የዚህ ዓይነቱ የዝሙት ድርጊት ደግሞ ከእንስሳዊ ወሲብም የባሰ አስቀያሚና አሳፋሪ ነው፡፡

#ለምሳሌ_ውሾች_በጎዳናዎች_ላይ_ወሲብ_ያደርጋሉ፡፡ እነርሱ የሚፈልጉት ወሲብን ብቻ ነውና፡፡ ወዳጅነት፣ ትስስር፣ ቁርኝት፣ ፍቅር የሚል ነገር እነርሱ ዘንድ የለም፡፡ ዝሙትም ቢሆን ይኸው ነገር ይንፀባረቅበታል፡፡

    የአንድ አዳጊ ወንድ ወይም ሴት የመጀመሪያው ወሲባዊ ሕይወቱ በዝሙት የተጀመረ ከሆነ፣ ዝሙቱ እርሷ ላይ ከላይ ባለው ሁኔታ ውስጥ ይበልጥ የመከሰት ዕድል አለው፡፡ ከዚያም ያ ዝሙቱ የተካሄደበት ትዕይንት በርሱም ሆነ በርሷ አዕምሮ ውስጥ ታትሞ ይቀራል፡፡ በውጤቱም መላው የወሲብ ሕይወቱ በዚህ ይጠቃል፡፡ ይህ ደግሞ በተራው የግለሰቡን የጋብቻ ሕይወት አብዝቶ ይጎዳዋል፡፡ ታዲያ የግለሰቡ የጋብቻ ሕይወት ይበልጥ በተጎዳ ጊዜ እርሱም የበለጠ ጭንቀታም እየሆነ ይመጣል። በጭንቀት ውስጥም ይኖራል፡፡ ይህ ቀጣይነት ያለው የጭንቀት ስሜትም በሂደት ወደ ጥፋተኛነት ስሜት ያድጋል፡፡ ያም በተራው ግለሰበውን ሰርክ ያሳድደዋል፡፡

ነብዩሏህ የሱፍ አለይሂ ሰለም ዙለይካ ስታስቸግረዉ ይህን ነበር ያለዉ...የሱፍ አይለይሂ ሰላም ከዝሙት ራሱን ተከላከለ ከፍ ያለደረጃ በዱንያም በአኼራም ተጎናፀፈ.
  «ጌታዬ ሆይ! ወደርሱ ከሚጠሩኝ ነገር ከዝሙት ይልቅ መታሰር ለኔ የተወደደ ነው(የሱፍ 33)

╔══════════════════════╗
   #በስንት_አመት_ላይ_የወሲብ_ፍላጎት ይመጣል??    
╚══════════════════════╝

 
      ሁላችንም እንደምናውቀው በዛሬዋ ዓለም ውስጥ ወደትዳር መቻኮል እምብዛም የለም፡፡ ይልቁንም ትዳርን ማዘግየት የተለመደ ሆኗል፡፡ የትዳር አጀንዳን የሰረዙም አሉ፡፡ የዚህ አብይ መንስኤም የዝሙት መስፋፋት ነው፡፡ ምክንያቱም ጥናቶች እንደሚያመለከቱት በአዳጊ ሀገራት እንኳን ወጣቶች ወደ ትዳር ፊታቸውን የሚያዙሩት በአማካይ ከ25-30 ባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ ነውና፡፡


ነገር ግን አንድ አዳጊ ወንድ በአማካይ በ16 ዓመቱ ወሲባዊ ጉልምስናው ጥግ ይደርሳል፡፡ በ16 አመቱ የቴስቶስትሮን ሆርሞን የምንጨታው መጠን ከፍተኛ ይሆናል፡፡ ወሲባዊ ኃይሉ ጣሪያ ይነካል፡፡

በሌላ በኩል አንዲት ሴት ደግሞ ከ8 ዓመት ጀምሮ ለወሲባዊ ጉልምስና ትደርሳለች፡፡ ሴት ልጅ ከ8አመቷ ጀምሮ ለወሲብ ደርሳለች ማለት ነዉ ..ልብ ይበሉ እነዚህ ሁሉ ሳይንሳዊ እውነታዎች ናቸው::

እንግዲህ አስቡት! አንድ ወንድ አዳጊ በአማካይ በ16 ዓመቱ ወሲባዊ ኃይሉ ጣሪያ ከነካና ያለ ጋብቻ ደግሞ እንደገና ተጨማሪ ሌሎች 10 እና 15 ዓመታትን መጠበቅ ካለበት፣ለመሆኑ ይህን ሰውነቱ የሚያመነጨውን ወሲባዊ ኃይሉን ምን ላይ የሚያውለው ይመስላችኋል? ምናልባትም አንዳንዶቻችሁ እራሱን ይቆጣጠራል ልትሉ ትችላለችሁ፡፡ነገር ግን ይህንን ከፍተኛ የሆነ ወሲባዊ ኃይሉን ለ10 እና ለ15 ዓመታት እንዴት ተቆጣጥሮት ይዘልቃል?ከሎጂክ አንፃርም አንድ በአፍላነት ዕድሜ ላይ ያለ አዳጊ ወንድ ለ10 እና ለ15 ዓመታት እራሱን ተቆጣጥሮና ታቅቦ ለጤናማ ትዳር ይበቃል ብሎ ማሰብ ይከብዳል፡፡ስለዚህ ቢበዛ አንድ ሁለት ዓመት እራሱን ከተቆጣጠረ በኋላ ዝሙት ላይ የመውደቅ ዕድሉ ከፍ ያለ ነው፡፡ሌላው ቢቀር ለግለ ወሲብ ይዳረጋል፡፡ ይህ አፍላ ወጣት ከትዳር በፊት ለዝሙት የመጋለጥ ዕድሉ ከፍተኛ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡

 🟢 በተለይ አሁን አሁን ዝሙትን መሥራት ውሃን የመጠጣት ያህል እና እጮኛን መያዝ ሻንጣን የመያዝ ያህል ቀላል በሆነበት ዘመናዊት ዓለም ውስጥ ወጣቱ በአፍላነቱ ወደ ትዳር እንዳይገባ ዝሙት ትልቁ የጋብቻ ተቀናቃኝ ሆኖበታል፡፡ ምንም እንኳን ጋብቻም ቅርብ ቢሆንም መንገዱ ግን አስቸጋሪ ነው፡፡ ልክ ገንዘብ መናገር ሲጀምር እውነት ዝም እንደምትል ሁሉ ዝሙት ሲንሰራፋም ጋብቻ ዝም ተባለ፡፡ዝሙት እየለመለመ፣ ሰፊ የመስፋፊያ ማሳን እያገኘና የተለያዩ ማዳበሪያዎች በላዩ ላይ እየተነሰነሱበት ሲመጣ በተቃራኒው ደግሞ ትዳር ይበልጥ እየቀጨጨና እየኮሰመነ መጣ፡ከዚህም የተነሳ ዝሙት ይበልጡኑ ጋብቻን መቀናቀን ቻለ፡፡👇👇👇
«መጥፎዎቹ ወንዶች ልጃገረዶችን ያበላሻሉ፡፡ ከዚያም ማግባትን ሲያስቡ ሷሊሕ  ሚስት ፍለጋ ይሄዳሉ፡፡ ግን የምታገኛት ሚስት ያንተው ዓይነት ሥነ-ምግባር ያላት ትሆናለች፡፡ አብዛኛው ወጣት ገርልፍሬንድ ብሎ የያዛትን ሕገወጥ የወሲብ አጋሩን በፍፁም አላገባትም ይላል፡፡ ታዲያ እኔ የምልህ ነገር ቢኖር የዝሙት ጓደኛህን ባታገባትም እንተ የምታግባት ሚስት የሌላ ሰው የዝሙት አጋር እንደነበረች ቅንጣት ታክል አትጠራጠር፡፡ ከፈለክ ይህንን የአላህ ተባረከ ወተዓላ ቃልን አንብብ፡- መጥፎዎቹ ሴቶች ለመጥፎዎች ወንዶች መጥፎዎቹ ወንዶችም ለመጥፎዎቹ ሴቶች የተገቡ ናቸው፡፡ (አን-ኑር 26)

╔══════════════════════╗
    #ሴቶች_በዝሙት_የሚያስተናግዱት_ጉዳት 
╚══════════════════════╝

      በዚና ሳቢያ የሴቶች ወሲባዊ ህይወት ውጥንቅጡ ወጥቷል፡፡ትዳርና ቤተሰብን አጥተዋል፡፡ለሰቅጣጭ ወሲባዊ እብደቶች ተዳርገዋል፡፡ ከሰው ያልተፈጠሩ በሚመስል መልኩ የወሲብ መንገደኞች የጭካኔ አያያዝ አርፎባቸዋል፡፡ሴቶች የሕዝቡ መሠረት መሆናቸው ቀርቶ የሕዝብ ቢራቢሮ ሆነዋል፡፡እራሳቸውን ለማሻቀጥ እዚያም እዚህም ሲርመሰመሱ ይውላሉ፡፡
☞ ውርጃ እንደጉድ ይካሄድ።
☞የእንስቶች ማሕፀን እንደጉድ ይሳሳል፡፡
☞ የማሕፀን ግድግዳቸው ይደማል፡፡
☞ ሴትነታቸው ረክሶ የስሜት ማራገፊያ ዕቃ ተደርጎ ይታያሉ፡፡ ታዲያ የነዚህ ሁሉ ጉዳቶች ሰለባ የሆኑ ሴቶች ብዙኃኑ ወሲብ ቀስቃሽ አለባበስን የሙጥኝ ያሉ ናቸው፡፡

  
🟡 ሴቶቹ በተደጋጋሚ በሚደርስባቸው ወሲባዊ ጥቃቶችና በሚፈፀምባቸው ወሲባዊ እብደቶች የተነሳ እነሆ ዛሬ ዛሬ የወሲብ ሕይወታቸው ምስቅልቅሉ ወጥቶ በወንዱ ፍላጎት ውስጥ ታጥረው ይገኛሉ፡፡ ይህች ዓለም ከሴቶች ማግኘት የሚገባትን ፈርጀ ብዙ አስተዋፅኦ ተጨናግፎ፣ሴቶች የማህበረሰቡ የሕይወት አካል ሳይሆኑ ለወንዶች የስሜታቸው ማራገፊያ እንደሆኑ ተደርገው ታይተዋል፡፡


ዛሬ ዛሬ ሴቶች ስብዕናቸው ወርዶ፣ ገመናቸው ገሀድ ወጥቶ፣ ገላቸው በአሻንጉሊት ቅርፅ ሳይቀር ተሠርቶ፣ የሴትነት ወጋቸው ጠፍቶ፣ክብራቸው ተዋርዶ፣ዓለም በሴት ልጅ ላይ ፊቷን አዙራ የሚደርስባትን ችግር ብቻዋን ትጋፈጠዋለች፡፡የዓለማችን እኩያንና የኢስላም ጠላቶች ሴቶችን አራቁተው በገላቸው ይዝናናሉ፡፡ ሴት ልጅ የሕይወት አጋር መሆኗ ቀርቶ የወሲብ አጋር ብቻ ተደርጋ ትታያለች፡፡ይህም ችግር በዓለም ደረጃ ሥር የሰደደና የዝሙት መስፋፋትን በጉልህ የሚያሳይ ነው::



 ⚠️ከዚና ወንጀል ተውብትን ሳያደርጉ የሚሞቱ ግለሰቦች ቅጣት በመቃብራቸው ውስጥ ይጀምራል፡፡በረጅም ሐዲስ ውስጥ እንደተዘገበው አንድ ጊዜ የአላህ መልዕክተኛ ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ ህልም ማየታቸውን ተናገሩ፡፡ከርሳቸውም ጋር ሁለት ሰዎች (ጂብሪልና ማሊክ በሰው ሱረት ሆነው) ነበሩ፡፡ሁለቱ ሰዎች በርካታ ቁጥር ያላቸው ኃጢአተኞች አንዴት በበርዘኸ(በሞትና በፍርዱ ዕለት መካከል ባለው ሕይወት ውስጥ) ሲቀጡ እንደነበረ ያሳዩዋቸው ጀመር፡፡ ይህንኑ ሲገልፁ ነብዩ ﷺ እንዲህ ይላሉ፡-

« በመሬት ውስጥ ያለ ጉድጓድ ዘንድ እስከምንደርስ ድረስም እንዲሁ እያሳየኝ ወደፊት መዛዛችንን ቀጠልንበት፡፡ የመጋገሪያ ጉድጓድ ይመስላል፡፡ ከላይ በኩል ጠባብና ከታች በኩል ደግሞ ሰፊ የሆነ ነው፡፡ ጉርምርምታና ድምፆችም ከርሱ ውስጥ ይወጡ ነበር፡፡ ወደ ውስጡ ተመለከትን፡፡እርቃነ ስጋቸውን የሆኑ ወንዶችና ሴቶችንም እየናቸው፡፡ከጉድጓዱ ስር ከታች በጣም የነደደ እሳት ነበር፡፡ እርሱ ድንገት በነደደ ቁጥርም ወንዶቹና ሴቶቹ ይጮኻሉ፡፡ወደላይም ከፍ ይላሉ፤ከሞላ ጎደል ከጉድጓዱ ውስጥ ለመውደቅ አስከሚቀርቡ ድረስ፡፡ እሳቱ እያነሰ በሄደ ቁጥርም ወደ ስሩ ይመለሳሉ፡፡እኔም እነዚህ እነማን ናቸው? ስል ጠየኳቸው፡፡እነርሱም,እነዚያን ራቁታቸውን በጉድጓዱ ውስጥ ያሉትን ወንዶችና ሴቶችን በተለመከተ፤ እነርሱ በዚና ላይ የወደቁ ወንዶችና ሴቶች ናቸው በማለት መለሱልኝ::(ሰሒህ ቡኻሪ)


╔════════════════════════╗
#ስሜትን_ለመቆጣጠር_የሚያስችሉ ጥበባዊ ምክሮች     
╚════════════════════════╝

ታላቁ ሊቅ ኢማሙ ኢብኑል ቀይም (ረሂመሁሏህ) ስሜትን ለመቆጣጠር የሚያስችሉ ጥበባዊ ምክሮች አል-ፈዋኢድ ከተሰኘ መፅሀፋቸዉ የተወሰዱ ምክሮችን ያስተንትኗቸዉ

➊ የሰው ልጅ የመላዕክት አእምሮ የእንሰሳት ፍላጎትና የሰይጣን ትልም አለው፡፡ከነዚህም አንዳቸው ያይላል፡፡ አንተ ትልምህንና ፍላጎትህን ማሸነፍ ከቻልከ ከመላኢካ የበለጠ ከፍ ያለ ደረጃ ላይ ትሆናለህ፡፡ ትልምህና ፍላጎትህ ካሸነፉ ግን አንተ ከውሻ የበለጠ ዝቅ ያለ ደረጃ ላይ ትሆናለህ

➋ ነፍስያህን ተጠንቀቃት፤ምክንያቱም በርሷ ቢሆን እንጂ ምንም መጥፎ ዕድል አያገኝህምና፡፡ስለዚህ ከርሷ ጋር በጭራሽ አትታረቅ፡፡በአላህ እምላለሁ! ክብሯ የሚገኘው ለአላህ እጅ በመስጠቷ ነው፡፡ ልዕልናዋ የሚገኘው ከመተናነሷ ነው፡፡ሕዳሴዋ የሚገኘው ከስብራቷ ነው::ምቾቷ የሚገኘው ከፈተናዎቿ ነው፡፡ ደህንነቷ የሚገኘው ከአላህ ፍራቻዋ ነው፡፡እንዲሁም ደስታዋ የሚገኘው ከሐዘኗ ነው፡፡

➌ ለአላህ ጥራት ይገባው! ውጫዊ ገፅታዎቻችሁን በተቅዋ ልብሶች አስጊጦላችኋል፤ውስጣዊ ማንነቶቻችሁ ለከንቱ ስሜቶች እጅ በሰጠቡት ጊዜ፡፡ እናም ልብሶቻችሁ የትም ባወዱ ጊዜ፣የከንቱ ፍላጎቶቻችሁ ተፅዕኖ ብቅ ይላል፡፡ታማኝ ሙእሚኖች ግን ከዚያ ችላ ይላሉ፡፡ክፉ ሠሪዎች ግን ወደዚያ ያዘነብላሉ፡፡

➍ አንድ ሰው የእዝነት የለሽ ሚስት ባለቤት፣ምህረት የማያደርግ ልጅ አባት፣ የማይታመን ጎረቤት፣ ምንም ምክር የማይለግሰው ጓደኛ፣በተሳሳተ መንገድ የሚፋረደው የስራ አጋር፣ጠላትነቱ ፈፅሞ የማይቋረጥ ባላንጣ፣ ወደ ከፋት የተዘነበለች ነፍስያ፣ የተጋጌጠች ዓለም፣ ከንቱ ፍላጎቶች፣ ተፅዕኖ ፈጣሪ ስሜቶች፣ ከባድ ንዴት፣ የሰይጣን ሽንገላ እና የቁጥጥር ድከመት ባለቤት ሆኖ ሳለ እንዴት ነው ደህንነት ሊሰማው የሚችለው? በርግጥ አላህ እርሱን ከታደገውና ከመራው እነዚህ ሁሉ ችግሮች በቁጥጥሩ ሥር ይሆናሉ፡፡ ግን አላህ እርሱን ችላ ካለውና ከተወው፣ እርሱን ለራሱ ትቶት፣ እነዚህ ሁሉ ጭንቀቶች እርሱን ያጠፉታል፡፡

➎ ባሪያው ከፊት ለፊቱ የሚቆምለት ጌታ አለው፤ ብሎም የሚኖርበት ቤት አለው፡፡ ይህም በመሆኑ እርሱ ከአላህ ጋር ከመገናኘቱ በፊት የአላህን ውዴታ ማግኘት አለበት፤ ልክ ወደቤቱ ከመግባቱ በፊት የቤት ዕቃውን ማስገባት በዕቃ መሙላት እንዳለበት ሁሉ፡፡

➏ / መሬት ሰፊ ናት፡፡በርሷ ላይ የሚተከልባትን ማንኛውንም ነገርም ትቀበላለች፡፡አንተ የእምነትና የተቅዋ ዛፍን ከተከልክባት የአኼራን ጣፋጭነት ትሰጥሀለች፡፡ የድንቁርናና የስሜትን ዛፍ ከተከልከባት እርሷም መራራ ፍሬ ትሰጥሀለች፡፡

➐/ አላህ የመጪውን ዓለም ደስታዎች ቃል ገብቶላችኋል፡፡ስለዚህ ችኩል አትሁኑ፡፡እነርሱንም በዚህች ዱንያዊ ሕይወት ውስጥ አትፈልጉ፤ ልክ እናንተ ሰብሎችን ከመሰብሰቢያ ጊዜያቸው በፊት እንደማትቆርጧቸው ሁሉ፡፡ከቆያችሁ እነርሱ ለናንተ በላጭ ይሆናሉ፡፡ልክ እንደዚሁ የመጪው ዓለም ደስታዎች እጅጉን በላጮች ናቸው፡፡»

📌በቀጣይ ክፍል ኢትዮጲያ እንዴት ዝሙት እንደተስፋፋ እና አዲስ አበባ ላይ ያሉ የተደበቁ የዝሙት እዉነታዎች ላይ እንዳስሳለን...

📚#ምንጭ☞65%በዝሙት አንዘምን መፅሀፍ

#ምዕራፍ ➌ይቀጥላል.....

join👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
🔥 #በዝሙት_በሽታ_የተበከለ_ትዉልድ🔥🔥
        
           🔰 #ምዕራፍ_ሶስት
                አሚር ሰይድ

╔══════════════════════╗
   🇪🇹🇪🇹 #ኢትዮ_ዝሙት_እንዴት_ተስፋፋ??🇪🇹🇪🇹     
╚══════════════════════╝

     ዝሙት በዓለም ላይ ትልቁ ሰው ሰራሽ ችግር መሆኑን ጠቅሰናል፡፡የሀገራችንን ተጨባጭና እውነታን በምናይበት ጊዜም ዝሙት በሀገራችን ደረጃም ትልቁ እኩይ ሀይማኖትና በርካታ ተከታዮች ያሎት ስለመሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው፡ምክንያቱም አገራችንም ከወቅታዊው የዓለማችን ሁኔታ ውጭ መሆን አትችልምና፡፡ምንም እንኳን በኢትዮጵያ ገዢው መንፈስ ጫት ቢሆንም፣አብዛኛው ወንድ በጫት ምርቃና የተያዘ ቢሆንም፣ይህ ግን በሴቶች ላይ የሚጎላ አይደለም፡፡ እናም ወንዱንም ሴቱንም በጋራ ቀፍድዶ የሚገዛው መንፈስ የዝሙት ዛር ሆኖ ይታያል፡፡


 🇪🇹 ይህች ሀገር ሀይማኖተኛ እንደነበረች ይታወቃል፡፡ በቅኝ ግዛት ያልተነካች እንደመሆኗ በርካታ እሴቶቿ ከጥንት ጀምሮ ለልጅ ልጆቿ ሲተላለፉ ቆይተዋል፡፡ የኢሰላምም ሆነ የክርስትና ሃይማኖቶች የተስፋፉበት በመሆኑ ህዝቦቿ ጥብቆችና ከነውር የራቁ ነበሩ፡፡ በባህል ደረጃም ቢሆን ሀገሪቷ የበርካታ እፁብ ድንቅ ወሲባዊ እሴቶች ባለቤት እንደነበረች ይታወቃል:: በሚያስደንቅ ሁኔታ በዚህች ሀገር ባህሎችም ሆነ ሀይማኖቶች በወሲብ ረገድ ጠበቅ ያለ ህግጋት ነበራቸው::ለዚህም ነበር በፊት በፊት በርካታ የወሲብ መንገደኞች «ለምንድነው እዚህ ሀገር ወሲብ ኃጢአት ሊሆን የቻለው?? እያሉ ወሲባዊ እሴቶቻችንን ሲያወግዙ የነበረው::

ሀገሪቷ በነበራት እፁብ ድንቅ ወሲባዊ እሴቶች የተነሳ በበርካታ የወሲብ መንገደኞችና የወሲብ ተንሸራሻሪዎች ስትነቀፍ ቆይታለች፡፡ቀደም ሲል የህዝቡን ወሲባዊ እሴቶች ጥይት እንኳን ይበሳቸዋል ተብሎ አልተገመተም ነበር፡፡በተለይም የማህበረሰቡ አባላት የወሲብ ንግድን በይፋ ቢዝነሳቸው አድርገው ይይዙታል ተበሎ አይገመትም ነበር፡፡ግን አሁን ይሄ ሁሉ ታሪከ ሆኖ አልፏል፡፡በሀገራችን የሴተኛ አዳሪነት ስራ ለመጀመሪያ ጊዜ በጣልያኖች አማካኝነት እንደተጀመረ ፊታውራሪ አመዴ ለማ የሕይወት ታሪኬ በተሰኘው መፅሐፋቸው ገፅ 41 ላይ ጠቅሰዋል፡፡

  🇪🇹 ሀገሪቷ በቅኝ ግዛት ስር ባትገባም ከአስተሳሰብ ወረራ ግን አላመለጠችም፡፡ እናም በግሎባላይዜሽን (ዓለምአቀፋዊነት) እና በኡርባናይዜሽን (ከተሜነት) ወጀብ ከፉኛ ተመታች::የምዕራቡ ዓለም እኩይ ባህሎች በሳይንስና ቴከኖሎጂ ስም እየወረራት ፀያፍ ነገሮች ገሀድ ወጡባት፡፡

የማህበረሰቡ አባላትም በተለያዩ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ብልግናን ማየትና መስማት ጀመረ፡፡ይባስ ብሎ ሕዝቡ የኤሌከትሮኒክ ሚዲያዎች ሱሰኛ ሆኖ ሌሎች ባህላዊና ስፖርታዊ የመዝናኛ ዘዴዎቹን ሁሉ መተው ጀመረ፡፡ ኤሌክትሮኒክ መዝናኛም በተለይ በወጣቱ ዘንድ ተቀባይነትን እያገኘ መጣና የዛኑ ያህል ብልግናና ፀያፍ ነገሮችን አስወረሰን፡፡
የምዕራቡ ዓለም
☞ የፊልም ተዋንያን ከትዳር ውጭ እንደፈለጉ ሲሳሳሙ፣
☞ወሲባዊ ልፊያን ሲያደርጉና
☞ አንሶላ ሲጋፈፉ ማየት ተጀመረ፡፡

በፊት የአማረኛ ፊልሞች ቀልድ አዘል ሁነዉ የሚያስተምሩ ነበሩ በሂደት ግን የምዕራባዉያንን ፊልም ስታይል መከተል ጀመርን..በሂደት ከኬንያ የሚተላለፈዉን ቃና tv በሙስሊሙም ክርስቲያኑም ቤት ሰተት ብሎ ገባ፡፡ቀስ በቀስም አይደፈሬው የወሲብ ፊልም ማየት ተለመደ፡፡ ከወሲብ ፊልም መስፋፋት ጋር ተያይዞም ወጣቱ እንኳን ዝሙትን ሊፀየፍ ቀርቶ ጤናማ ወሲብ ሁሉ ማድረግ ኋላቀርነት አድርጎ ማየት ጀመረ፡፡ በዚሁ አካሄድም ዛሬ ዛሬ እነሆ ታላላቅ ሰቅጣጭ ወሲባዊ እብደቶች ሁሉ መላውን ሀገር ሳይቀር አዳረሰ፡፡

╔══════════════════════╗  
⚠️#ዝሙትና_የአዲስ_አበባ_ድብቅ_እውነታዎች        
╚══════════════════════╝

በርካታ ጥናቶች እንዳመለከቱት አዲስ አበባ የወሲብ ንግድ በከፍተኛ ሁኔታ የተስፋፋባት ከተማ ሆናለች፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ በወሲብ ንግድ የቀዳሚነት ስፍራን የምትይዘው ሀገር ታይላንድ ስትሆን በአህጉራችን ደረጃ ደግሞ ኢትዮጵያ አፍሪካዊቷ ታይላንድ የሚል ስያሜን አግኝታለች፡፡
አዲስ አበባ በአለም አራተኛ በአፍሪካ አንደኛ የወሲብ ንገድ ከተሜ ነች፡፡የታይላንድ ዋና ከተማ የሆነችው ባንኮክ የዓለም የወሲብ ከተማና የወሲብ ተንሸራሻሪዎች መዳረሻ እንደሆነች ሁሉ በአፍሪካ ደረጃም አዲስ አበባ በወሲብ ንግድ አፍሪካዊቷ ባንኮክ ተብላለች፡፡

በተዘዋዋሪ ደግሞ የኢትዮጲያ መረጃዎች እንዳመለከቱት በዓለም አቀፍ ደረጃ በኢንተርኔት አማካኝነት የሚለቀቁትን #የወሲብ_ፊልሞች_በመጠቀም (የብልግና ፊልምን በማየት ኢትዮጵያ ከታይላንድ ቀጥላ የሁለተኛነት ደረጃን ይዛለች፡፡ይህንኑ እውነታም የኢትዮጵያ መንግስትም ተቀበሎታል፡፡በርግጥ ከመቀበል ውጭ የትም መሸሽ አይቻለውም፡፡የኢትዮጵያ ቴሌኮም በግልፅ ያውቀዋል፡፡በየአመቱ  በቢሊዮን ብር የሚያተረፈው ኢትዮ ቴሌኮም ለዚህ ሁሉ ትርፋማነት እንዲበቃ ያደረገው አንዱ ምክንያት የዜጎቿ የወሲብ ፊልም ፍጆታ ከጊዜ ወደ ጊዜ መጨመሩ እንደሆነ ይነገራል፡፡


ይህ ጥናት አዲስ አበባ ላይየተደረገዉ ከ2009 በፊት ነዉ፡፡አሁን 2016 ላይ እንዴት እንደሚጨምር አስተንትኑት
☞ዶ/ር ኬቨን ላሮ የተባሉ ምሁርን ጥናትን ጠቅሶም የዕለት እንጀራቸውን የተለያየ ቅርፅ ባለው የወሲብ ንግድ ላይ የመሰረቱ ወደ
ሩብ ሚሊዮን የሚጠጉ ሴተኛ አዳሪዎች በአዲስ አበባ እንደሚገኙ እና
14 በመቶ የሚሆኑት ከ18 ዓመት
6 በመቶዎቹ ደግሞ ከ14 ዓመት በታች የሚገኙ እንደሆኑ በመጠቆምም መጣጥፉን ያጠቃልላል፡፡»


╔══════════════════════╗
✏️  #ልዩ_ልዩ_መልክ_ያላቸው_ሴተኛ_አዳሪዎች   
╚══════════════════════╝
ሴተኛ አዳሪነት በፊት በፊት ከሚታወቅበት መደበኛ ይዘቱ በተጨማሪነት አሁን አሁን የተለያዩ ቅርፆችን ይዞ በርካታ ሴቶችን እያሳተፈ ይገኛል፡፡እነዚህም በሴተኛ አዳሪነት ሥራ ውስጥ ቢዝነስ የሚል መጠሪያ የተሰጣቸው ሲሆን እነርሱም የየራሳቸው ፈርጅና መገለጫ አላቸው::

«በአሜሪካን ተራድኦ ድርጅት ድጋፍ የተደረገ አንድ ጥናትም በመዲናችን በተለመደው መንገድ ከሚደረገው የወሲብ ንግድ በተጨማሪ በስልክ እየተጠሩ የወሲብ
አገልግሎት የሚሰጡ ተባራሪ የወሲብ ሰራተኞች
(Transactional and Semi Transactional Sex Workers) መኖራቸውን ይጠቁማል፡፡
በመዲናችን የሚገኙ 21,913 አስተናጋጆች፣
62,545 የቀን ሰራተኞች እና ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ የሁለተኛ እና የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እንዲሁም የተለያዩ የቢሮ ሠራተኞች ጭምር በተባራሪ የወሲብ ሥራ ላይ እንደሚሳተፉም የጥናቱ ውጤት ያሳያል፡፡የጥናቱን ውጤት አስደንጋጭ የሚያደርገዉ ደግሞ በዚህ ዓይነቱ የወሲብ ንግድ ሆስተሶች እና የኤንጂኦ ሠራተኛ የሆኑ ሴቶች ጭምር እንደሚሳተፉ ስለሚጠቁም ነው፡፡(ከ2009 በፊት ጥናት ነዉ አሁን 2016ላይ ደግሞ እንዴት እንደሚጨምር እሰቡት)

🟢የሥነ-ልቦና ባለሙያውና ካውንስለሩ ዐብዱል ገፍ-ፋር ሸሪፍ)እንዲህ ብሏል

እኔ ባገኘሁት መረጃ መሠረት በአዲስ አበባ ውስጥ ከ150-200 ሺ መደበኛ ሴተኛ አዳሪዎች አሉ፡፡ ይኸው አኃዝ በተለያዩ ዓለም አቀፍ ጉባኤዎችና አሕጉራዊ ስብሰባዎች ሰሞን በእጥፍ በመጨመር 400 ሺ ይደርሳል፡፡»👇👇👇
2024/10/01 15:39:59
Back to Top
HTML Embed Code: