Telegram Web Link
የዝሙት መዳረሻዎች ከሞላ ጎደል እየለፈለፉ የተንሰራፉ ሲሆኑ ኢኽቲላጥ ግን ድምፁን አጥፍቶ ውስጥ ለውስጥ የገዘገዘን የዝሙት መጋዝ ነው፡፡ እንደነርሱ እምነት ከሆነ እነዚህ መስፈርቶችም ኢኸቲላጥን በተገቢው ገደቦች ውስጥ የሚጠብቁ ናቸው::

     ሆኖም ግን ለመሆኑ እናንተ ይፈቀዳል የምትሉት ኢኸቲላጥ  ዛሬ ዛሬ በየት/ቤቱ፣ በየኮሌጁ፣ በየዩኒቨርሲቲው፤ በየመሥሪያ ቤቱ፣ በየገበያ ማዕከሉ፣ በየንግድ ታዎሩ፣ በየመጓጓዣው፣ በየአደባባዩ፣ በየማህበራዊና ሕዝባዊ ስብስቦቹ ላይ የምናየው ዓይነት ነውን? እሺ! እነዚህ ሁሉ የኢኸቲላጥ ዓይነቶች እናንተ ይፈቀዳሉ በምትሏቸው ገደቦች ውስጥ ናቸውን? ለመሆኑ እናንተ ይፈቀዳሉ የምትሏቸው የኢኸቲላጥ ዓይነቶች በገሀድ አሉን? ሲባሉ አጥጋቢ ምላሽ የላቸውም፡፡ በእውነቱ ዛሬ ዛሬ በየቦታው የምናያቸው የኢኸቲላጥ ዓይነቶች በአለባበስ፣ በአነጋገር፣ በወንዶችና ሴቶች መካከል ባለው ኢንተራከሽንና በምግባር ረገድ በሸሪዓዊ ገደቦች ውስጥ የሉም፡

ዛሬ ዛሬ ባሉ ኢኸቲላጦች ውስጥ የሴቶች መገላለጥ (ተበርሩጅ)፣ የሒጃብ መስፈርቶች ጥሰት፣ የሴቶች ልቅነትና በአጠቃላይም ሥርዓት አልበኝነት የሰፈነበት ሆኖ እናገኘዋለን፡፡

እነሆ በኢኸቲላጥ ሳቢያም ቁጥር ስፍር የሌላቸው ፊትናዎችን እያየን ነው፡፡ በተቃራኒ ፆታዎች መካከል ለሚፈፀሙ ወንጀሎች ሁሉ ምንጩና መፈልፈያው ኢኸቲላጥ ነው፡፡ ሌላው ቢቀር ኢኽቲላጥ ሲኖር በወንዶችና በሴቶች መካከል በቀላሉ የሚያስጠርጥሩ ግንኙነቶች ይፈጠራሉ፡፡ስለዚህ ዛሬ ዛሬ እየተከሰተ ያለው የኢኸቲላጥ ዓይነት ምንም ተቀባይነት የለውም፡፡

✏️✏️ ከሴቶች ልቅነት የተነሳ በሸሪዓዊ ገደቦች ውስጥ የሚደረጉ ኢኽቲላጦችም ተውጠዋል፤ ከስመዋል ማለት ይቻላል፡፡ ወጣም ወረደም ሸሪዓው እንዲህ በታመቀበት አግባብ ውስጥ በሸሪዓዊ ገደቦች ውስጥ የሚደረጉትን ኢኽቲላጦች እንኳን ማበረታታቱ አግባብነት የለውም፡፡

    ከላይ ለመጥቀስ እንደተሞከረው ለዝሙት ለም የሆነ የማብቀያ መሬትን በማዘጋጀት ይህንን ደዌ ለዚህ ደረጃ ያበቃው ትልቁ ነገር ኢኸቲላጥ (የፆታዎች ቅልቅል) ነው፡፡ዝሙትን መሥራት ውሀን የመጠጣት ያህል ቀላል ያደረገውና ከዚያም አልፎ ሰዎች በዝሙት እንዲፎካከሩ ያደረገው ይኸው ኢኽቲላጥ የተባለው ደዌ ነው፡፡

ዛሬ ዛሬ የዓለምን ማህበረሰብ ቀፍድዶ የያዘው የዝሙት ዛር በዋናነት የተፈለፈለው ከኢኸቲላጥ ነው፡፡እናም ከኢኸቲላጥ ጋር የተያያዘውን እውነታ መገንዘብና ማህበረሰቡን ከገባበት ሕመም መፈወስ እንገብጋቢ ጉዳይ ሆኖ ይታያል፡፡ እንደ ኢኸቲላጥ በዝምታ የዝሙትን መርዝ የረጨው ሌላ የመዳረሻ መንገድ የለምና፡፡ሌሎች የዝሙት መዳረሻዎች ከሞላ ጎደል እየለፈለፉ የተንሰራፉ ሲሆኑ ኢኽቲላጥ ግን ድምፁን አጥፍቶ ውስጥ ለውስጥ የገዘገዘን የዝሙት መጋዝ ነው፡፡

ዛሬ ላይ ኢኽቲላጡ ያለማካበድ ከሌሎች ሀይማኖት በላይ ሙስሊሙ ላይ ይስተዋላል፡፡የኢኽቲላጥ መንገድ በኸይር ስራ ስም፡በሙስሊም የመድረክ ዝግጅቶች፡በሙነሺድ ተብየዎች በሚያዘጋጁት የነሺዳ ማስመረቂያ ሰም ኢህቲላጥ ተበራክቷል፡፡በፊት ታስታዉሱ ከሆነ የዛሬ 3አመት በፊት ሙነሺዶች መጣን መጣን ባሉ ጊዜ እነዚህ ሰዎች ይዘዉ የመጡት ነገር ከባድ ነዉ ለወደፊት ከባድ መዘዝ ይዘዉ መጥተዋል እያልኩ ብቻየን ፁሁፍ ሳዘጋጅ በጣጣም ተቃዋሚ ይበዛ ነበር ትችቱ ከአቅሜ በላይ ሲሆን ተዉኩኝ..ይሄዉ ዛሬ ነሺዳና ሙዚቃ መለየት እስከሚያቅተን በዜማ ሲጣሉ ሊደባደቡ ሲደርሱ
ነሺዳና ሙዚቃ ሲሰራረቁ እያየን ነዉ፡፡

የአሁን ሴት ሮል ሜድልሽ ማን ነዉ ብትባል አንዱን ሙነሺድ ነዉ😬 የምጠራዉ...ሚዲያ ላይ በፊት ብዙ ሴቶች በማስረጃ እንደነገሩኝ በጣጣም ብዙ የሙነሺዶች ገመና አቃለሁ የሚሰቀጥጡ ነገሮች በማስረጃ የማቀዉ አለ

አሁን ላይ የሚሻለዉ እነሱን አለመከታተል ነዉ ለምን የሚሰሩት ለአሏህ ብለዉ የአላህን ወዴታና የነብዩን ዉዴታ ለማግኘት ሳይሆን ታወቂ ለመሆን ለሴቱ የተሻለ ስራ እኔን ሴቱ እንዲወደኝ የትኛዉ ስራ ልስራ ስለሆነ እነሱን መከታተሉን ትቶ...አላህ ሆይ ቀጥተኛ መንገድ ምራቸዉ ወይ በዚሁ በዱንያ በሙነሺድ ስም የሚሰሩትን ግፍ ያሳየን ብሎ ዱአ ማድረጉ ይሻላል፡፡

«አደገኛው የኢስላም ጠላት አላዋቂ ሙስሊሞች ናቸው።በአላዋቂነታቸው ላይ ስሜታዊ ይሆኑና በድርጊታቸው የኢስላምን እውነተኛ ውበት ያጠለሻሉ።የሌላው ዓለም ሰዎች የነርሱን ድርጊት በመመልከት ኢስላም ያ እንደሆነ ያስባሉ። (ሽህ ኢሕመድ ዲዳት) የተናገሩት ንግግር የአሁን ዘመን ሙነሽዶችን ያካትታል👌👌


🫵 በተጨማሪ ዛሬ ላይ ኢኽቲላጡ በሙስሊሙ በዲን ስም ተጋኗል፡፡

🔶 #ሙነሺዶች፡ሚንበር ቲቪ የተለያዩ ሙሀለጣ ባላቸዉ ፕሮግራሞች አኽቲላጥ አለ በዚህ ኢኽቲላጥ ወደ ዝሙት መስመር የሚገቡ አሉ

🔶 #የሙስሊም_በጎ_አድራጎት_ማህበር እየተባሉ ሴትና ወንድ የሚደባለቁበት አለ፡፡አረጋዉያንን መንከባከብ..የተቸገሩ ለመርዳት ስበብ ለጀመአችን ማጠነከሪያ እየተባለ የሙስሊም ሴቶች ተበጃጅተዉ አንፀባራቂ ሎሚ ከለር ልብስ ለብሰዉ ከአጂ ነብይ ወንድ ለጀመአ ማጠናከሪያ በሚል ብር ማሰባሰብ..ለጀመአችን እየተባለ ሲዋክ መሸጥ...ቡና እያፈሉ በየመንገዱ መሸጥ...ጫማ የሚጠርጉ አለ...
የደካሞች ቤት ተብሎ የጀመአየ ልጅ አብረዉ ወንድ ጋር ሂደዉ ሴቶች ልብስ ሲያጥቡ ወንዱ ቤት ያስተካክላል..ሰዉ ያላስተዋለዉ ሙዱን የቀየረዉ የዝሙት መንገድ ነዉ☺️

#አሁንም እየሆነ ነዉ ለወደፊትም ታዩታላችሁ የዝሙት መንገድ ነዉ አሁንም አንዳንዶችም በድብቅ ገብተዉበታል::

የአላህን ዉዴታ አጅር ለማግኘትና ሴት ልጅ ቡና የምታፈላዉ ቤተሰቦቿን ለመሀደም እንጂ መንገድ ላይ ወንድ እንዲያት አይሆንም ነበር...ለጀመአየ ብላ ጫማ የምጠርገዉ የእናቷን የአባቷን ጫማ ረግጣ ወጥታ ነዉ...የአረጋዉያን ልብስ ልጠብ ብላ ስትወጣ የእናት የአባቷ ልብስ ግን ቆሾሾ ተቀምጧል...መቅደም ያለባቸዉ የአክስት የአጎቶቿ ልብስ የሚያጥብላቸዉ ተቸግረዋል ወይም ጎረቤቷ እማማ እንትና ልጅ የላቸዉ የሚንከባከብ የላቸዉ ልብሳቸዉን የሚያጥብላቸዉ የለ በርሀብ እየተሰቃዩ ይሆናል..ይህን ሁሉ አልፎ ሂዶ ጀመአየ አዘዘኝ አሚሬ አዘዘኝ ብሎ መንጦልጦል  ከምር አስመሳይነት ነዉ🙄፡፡በፊት ወንድ ሴትን ልጅ ለማዉራት ካፌ ወይ ወጣ ያለቦታ ነበር ዛሬ ግን  የጀመአ ፕሮግራም አለ በሚል ስም መገናኘት ሆነ አልሸሹም ዘወር አሉ ነገር ግን ኮዱን ቀየሩ😊 ነዉ የምንለዉ ወዳጄ..ቤተሰብ ሆይ ንቁ እባካችሁ‼️‼️

ግን ሴቶች ለብቻ ወንዶች ለብቻ የሆነ በጎ አድራጎት ወይ ጀመአዎች አሉ በተጨማሪ ትላልቅ ሰዎች ባለሀብቶች አሉ ለኸይር ስራ የተቋቋሙ እነዚህን ግን እንደማያካትት ልታቁልኝ ይገባል፡፡የእኔ ሀሳብ ኢኽቲላጥ ያለባቸዉ የወጣቶች ጀመአዎችን ነዉ


#በቀጣይ_ክፍል...የእጅ ዚና የጆሮ ዚና ላይ ያተኮረ ፁሁፍ ቢኢዝኒላህ ይዤ እቀርባለሁ


 #ሴት_ዝሙተኛ☞ አመንዝራይቱ፣ሸርሙጣ፣ሴተኛ አዳሪ፣የቡና ቤት ሴት፣ሸሌ፣ባር ሌዲ፣ ወዘተ የሚሉትን አስቀያሚ ስሟ ነዉ፡፡
#ወንዱ ዛኒያም☞ ዝሙተኛ፣ሂያጅ፣አመንዝራ፣ዘልዛላ፣ የወሲብ መንገደኛ፣ ወንድኛ አዳሪ፣ ወንድ ሸሌ፣ ሸርሙጣ፣ ወዘተ በመባል በሀገራችን ባህል ይጠራል
ዝሙተኛ ከመሆን ይጠብቀን..ዝሙት ላይ ያለነዉን እንደ ምንጭ ዉሀ ኩልል ያለ ተዉበት አላህ ይወፍቀን

#ምዕራፍ
ይቀጥላል....
አስተያየት ካለ በዚህ ማቀበል ይቻላል
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot
join👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከአሏህ ስሞች አንደኛዉ ሽኩር ነዉ.

አላህ አመስጋኝ ባርያዎችን ይወዳል

join👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
🔥#በዝሙት_በሽታ_የተበከለ_ትዉልድ🔥🔥
        
           🔰 #ምዕራፍ_ሰባት
                አሚር ሰይድ




አቡ ሁረይራ ረዐ  እንዳስተላለፉት የአላህ  መልዕክተኛ የሆኑት ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ እንዲህ ብለዋል፤ «በአደም ልጅ ላይ የዝሙት ድርሻ ተጽፎበታል። ይህን ድርሻውን  ያለ ጥርጥር ያገኛል። ሁለት ዓይኖች ዝሙታቸው ማየት ነው፡፡ሁለት ጆሮዎች ዝሙታቸው  መስማት ነው፡፡ የምላስ ዝሙት መናገር ነው፡፡ የእጅ ዝሙት መጨበጥ ነው። የእግር ዝሙት መራመድ ነው።ልቦና ያስባል፤ይመኛል። ብልት ደግሞ ይህን ምኞት እውነት ወይም ሐሰት ያደርጋል።» (ቡኻሪና ሙስሊም)

ዚና አይነቱ ብዙ ነዉ የአይን ዝሙት ብዙዎቻችን የተጠመድንበት ነዉ በየመንገዱ በየሰፈሩ ሴቱም ወንድም አፍጥ አግጥን ሆነን ኢማናቻን ከተንሸራተተ ዋል አደር ብሏል በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በtiktok የምናየዉ ተቀራኒ አጂነብይ የአይን ዚና መሆኑን ሊሰመርበት ይገባል፡፡

ዛሬ ሰፋ ያለ ፁሁፍ ያዘጋጀሁት የእጅ ዚናና የጆሮ ዚና ላይ ያተኮሩ ናቸዉ፡፡ወደ ፁሁፉ እናማራ

╔══════════════════════╗
    🔰🔰 #የእጅ_ዚና_ምንነትና_አደገኛነት 🔰🔰
╚══════════════════════╝


💚 ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡-
  ከናንተ አንዳችሁ ከዚያ ያቺን ለርሱ የተከለከለችውን ሴት ከመንካት ይልቅ ጭንቅላቱ በብረት ወስፌ ቢሰፋ ይሻለዋል፡፡»ብለዉናል

    ይህ እንግዲህ የእጅ ዚና ቅጣትን የሚመለከት ነው፡፡ ታዲያ ከዚህ የባሱ ፀያፍና ሕገ-ወጥ ድርጊቶች:- ለምሳሌ መተቃቀፍ፣ መሳሳም፣ መተሻሸትና  ወሲብን መፈፀም ከዚህ የክፉ ቅጣቶችን እንደሚያስከትሉ ከዚሁ መገመት ይቻላል፡፡

⚡️⚡️ለምሳሌ ሕገወጥ መሳሳምን በተመለከተ ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡-

«እርሱ ያ ያቺን ለርሱ ያልተፈቀደችውን ሴት በምኞት በጋለ የወሲብ ስሜት የተነሳ የሚነካት ሰው፣ በፍርዱ ቀን እጁ ከአንገቱ ጋር ታስሮ ይቀሰቀሳል፡፡ እርሱ ስሟት ከሆነ ከንፈሮቹ በእሳት ውስጥ ይቃጠላሉ፡፡ በመጨረሻም እርሱ ዝሙት ላይ ወድቆ ከሆነ ጭኖቹ እኔ ያልተፈቀደ ነገር ላይ ተኝቻለሁ ሲሉ በፍርዱ ቀን በርሱ ላይ ይመሰክራሉ፡፡ ከዚያ ከአላህ ቁጣ የተነሳ ወደርሱ ይመለከታል፡፡ በዚህን ጊዜ የሰውየው የፊቱ ሥጋ ተገሽልጦ ይወድቃል፡፡ እርሱም በትዕቢት እኔ ፈፅሞ ይህንን አልሠራሁም የሚል ከሆነ ከዚያም ምላሱ እኔ ያልተፈቀደን ንግግር ተናግሬያለሁ ሲል ይመሰክርበታል፡፡ እጆቹም እኔ ያልተፈቀዱ ነገሮችን ነክቻለሁ ይላል፡፡ ዓይኖቹም እኔ ያልተፈቀደውን ነገር አይቻለሁ ትላለች፡፡ እግሮቹም እኔ የሄድኩት ወደተከለከሉ ነገሮች ነበር ይላሉ፡፡ በመጨረሻም ብልቱ እኔ በገቢር እዋልኩት ይላል፡፡ ጠባቂ መላእኮችን በተመለከተ አንዱ እኔ ሰምቻለሁ ሲል ሌላኛው ደግሞ እኔ ፅፌዋለሁ ይላሉ፡፡ በመጨረሻም አላህ እኔ ሁሉንም አውቃለሁ፣ ነገር ግን ለርሱ ደብቄለት ነው እንጂ ይላል፡፡

ከዚያም አላህ (ሱ.ወ) ለመላኢኮቹ እርሱ ይቀጣ ዘንድ ወደ ጀሀነም🔥🔥🔥🔥እሳት ውሰዱት፡፡ የኔ ቁጣ በነዚያ ከኔ ምንም ሐያእ በማያደርጉት ላይ በረታች ይላል፡፡ ይህም በአላህ (ሱ.ወ) በቁርአኑ  በእነሱ ላይ ምላሶቻቸው፣ እጆቻቸውና እግሮቻቸውሞ ይሠሩት በነበሩት እኩይ ነገር በሚመሰከሩባቸው ቀን ከባድ ቅጣት አላቸው ተብሎ ተጠቅሷል፡፡ (አን-ኑር 24:24), (ኢማም ዘሀቢ አል-ከባኢር ውስጥ እንደጠቀሱት)


🌙🌙  በዑለሞች አተያይ የእጅ ዚና ሲባል የዘመኑ ቴከኖሎጂን በመጠቀም ባዳ ሴቶችና ወንዶች የሚፃፃፉትና የሚላላኩት የተለያዩ ሕገወጥ መልዕከቶችም በዚህ ውስጥ ይጠቃለላሉ፡፡
☞ስልክ ቁጥሮችን የሚከትቡና
☞ቴክስት ሜሴጆችን የሚፅፉ ጣቶችም ከእጅ ይቆጠራሉ፡፡
☞የሞባይል ሰክሪኖችን የሚነካኩና
☞በቀን ውስጥ በተደጋጋሚ ቻት ሴክስን፥ ፎን ሴከስንና የወሲብ ፊልምን ሳይቀር ጠቅ ጠቅ የሚያደርጉ ጣቶችም በዚሁ ውስጥ ይካተታሉ፡፡

በተመሳሳይ መልኩ ይህ እውነታ ወደ ዓይን ዚና፣ ወደ ምላስ ዚና፤ . ጆሮ ዚናና ወደሌሎችም ሁሉ በየፊናቸው በሚኖራቸው ተሳትፎ ልክ ይለጠጣል፡፡


╔══════════════════════╗
    🔰🔰 #የጆሮ_ዚና_ምንነትና_አደገኛነት 🔰🔰    
╚══════════════════════╝

የጆሮ ዚና ማለት ብዙ አይነት ነዉ ከነዛ ዉስጥ በጥቂቱ

☞ወሲባዊ ውይይቶችን ማዳመጥ፣
☞ወሲብ ቀስቃሽ ዘፈኖችን መስማት
☞በስልክና በሌሎችም የርቀት መገናኛ ዘዴዎች ስለወሲብ መስማትና ማዳመጥ፣
☞የወሲብ ፊልሞችን ከላሲካል ማጀቢያዎችን ማዳመጥ፣ ወዘተ ከጆሮ ዚና የሚቆጠሩ ናቸው::

   ብዙውን ጊዜ ግን ከዚና ጋር የተያያዙ ድምፅ-ነክ ነገሮች ወደ ጆሮ የሚገቡት ዘፈንን በማዳመጥ በኩል ነው፡፡ እንደሚታወቀው ዘፈን ዛሬ ዛሬ የዚና ነዳጅ ሆኗል፡፡ እዎ ዘፈን ከዝሙት አበይት መዳረሻ መንገዶች አንዱ ከመሆኑም ባሻገር ልብን ያሸፍታል፤ በአድማጩ ልብ ላይም ኒፋቅን ያሰርፅበታል፡፡ ይህም በግለሰቦች ኢማናዊ ኃይላቸው ላይ ከፍተኛ ድከመትንና መንኮታኮትን ያስከትላል፡፡

✏️✏️ ዘፈንን አስመልከተው ታላቁ ሊቅ ኢማም ኢብኑል ቀይም (ረሂመሁሏህ) አል-ፈዋኢድ ውስጥ እንዲህ ብለዋል፦
የዘፈን ፍቅርና የቁርአን ፍቅር በአንድ ግለሰብ ልብ ውስጥ በጋራ አይመጡም! አንዱ ሌላውን የሚያስወጣው ቢሆን እንጂ፡፡”

✏️✏️ አንድ ሌላ ሰለፍ ደግሞ እንዲህ ብለዋል፡-

መሳም የወሲብ፤ ዘፈን የዝሙት፣ ማየት የፍቅር፣ በሽታ የሞት መነሻ እንደሆኑ ሁሉ ወንጀልም የከህደት መነሻ ነው፡፡,,ብለዋል




╔══════════════════════╗
🔰#ወንዶች_ሴትን_በሀራም_መቀያየር_ደስታ_የለዉም
╚══════════════════════╝

    አንዳንድ ጋጠወጦች (ፋሲቆች) ሴት ሲያዩ በሙሉ ዓይናቸው አፍጠው ያያሉ፡፡ ልባቸውም ይከተላታል፡፡ ቁመናዋንና ፈታኝ ውብቷን በማሰላሰል ይባዝናሉ፡፡ ሊያግኟትም ይመኛሉ፡፡ ብሎም ያዱንያ ጣፋጭ ነገር፣ ደስታ ሁሉ በርሷ ውስጥ የተወሰነ ብቻ መሰሎ ይታያቸዋል፡፡ የዱንያ ሰቆቃና ስቃይ ደግሞ እርሷን በማጣት የሚመጣ ይመስላቸዋል፡፡በዱንያ ውስጥ የሚፈለገው ሁሉ በርሷ ውስጥ ያለ መስሎ ይታያቸዋል፡፡ ባስታወሳት ቁጥር ያብድላታል፡፡ ይህን ሁሉ አስቦ ያግኛት እንደሆነ ደስታው የግማሽ ደቂቃ ያህል ብቻ ሆና ትቀራለች፣ ትከስማለች፡፡ ሳይጠግባት ይሰለቻታል፡፡

በሐሳቡ ሲስላት የነበረው ነገር ሁሉ ከንቱ ይሆንበታል፡፡ ከዚያም ስለሌላ ሴት ማሰብ ይጀምራል፡፡ የሚያስባትን ሊያገኝ ደግሞ እንደዚሁ ተስፋው ይከስማል፡፡ እንደገና ሌላ ይመኛል፡፡ ከዚህችኛዋ ያጣውን ደስታ ከሌላኛዋ የሚያገኝ መስሎ ይሰማውና እንደገና ሌላ ለማግኘት ማሰላሰል ይጀምራል፡፡ ይህችንም ሲያገኝ እንደዚሁ ተስፋው ይከስማል፡፡ እንዲህ እያለ ሊያገኘው የማይችለው ደስታን በመፈለግ እንደባዘነ አንዷን ካንዷ ሲያቀያይር አንድም ቀን የፈለገውን እርካታ ሳያገኝ፣ ሐሳቡ ሳይሞላለትና ሳይጠግብ ዕድሜው ያከትማል፡፡👇👇👇
እናንተ ሰዎች ሆይ! እርካታን ማግኘት ማለት ምንድን ነው? እርካታን ማግኘት ማለት ወሲባዊ ግንኙነት ብቻ ነው ትላላችሁ? አይደለም! አይደለም! ሰዎች፡፡ እርካታን ማግኘት ማለት ወሲባዊ ግንኙነት ብቻ ሳይሆን ልብ ለልብ መገናኘት፣ ሴትና ወንድ ባንድ በተቀደሰ የትዳር ትስስር ሥርዓት ውስጥ መተሳሰር ነው፡፡



 ✏️✏️ለሴቶችም እንደዚሁ የዚህ ዓለም ወንዶች ሊያረኳቸው ቢሰበሰቡም እርካታን አያገኙም፡፡ ግን ይሆን አልረካ ያለ ስሜት አንዲት የሐላል ሴት አንድ የሐላል ወንድ ያረኩታል፡፡

ሰዎች ሆይ፤ አንድ ሰው ገንዘቡ ሀብቱ እጁን ወደፈለገው ለመሰደድ ቢያስችለውም ጉልበቱ ይችል ይሆን? አካሉስ ስሜቱን መሸከም ይችል ይሆን? ቢችል እንኳ አንድ ቀን መሸነፉ! በበሽታ መጠቃቱ አይቀርም፡፡ ማድረግ እየፈለገ አይችልም፡፡ ዓይኑ እያየ እያማረው ያጣዋል፤ ያቅተዋል፡፡ እንደዚህ ከሆነ ታዲያ ለምን ከወንጀሉ አይታቀብም? አካሉንና ከብሩን ለምን አይጠብቅም? አካሉንና ከብሩን አጥቶ፣ነፍሱን በበሽታ አስጠቅቶ፣ያማረውን እርካታ ከማጣት በአዱኛ ከመሰቃየት በአኼራ ወደ ገሀነም ከመወርወር አሁን ቢቆጠብ አይሻለውም ትላላችሁ?

ወንድሞቼ ሆይ! ከአላህ (ሱ.ወ) አፈጣጠር ተአምራት ውስጥ አንዱ በቁንጅና የሚመሳሰሉ ሴቶችንም ሆነ ወንዶችን አለመፍጠሩ ነው፡፡ ሴቶች ሁሉ አይመሳሰሉም፡፡ ወንዶችም እንደዚሁ:: ከሁሉም ሴቶች ወንዶች የሚገኘው እርካታም አንድ ዓይነት አይደለም፡፡ ነገር ግን ሕጋዊ ባለትዳሮች በተፈጥሯቸው የሰመረ ወሲባዊ ጥምረትን መፍጠር የተሻለ እርካታን ማግኘት ይችላሉ፡፡

#በቀጣይ_ክፍል ☞ዝሙት ስለሚያመጣዉ አደገኛ መዘዝ ይቀርባል


 #ሴት_ዝሙተኛ☞ አመንዝራይቱ፣ሸርሙጣ፣ሴተኛ አዳሪ፣የቡና ቤት ሴት፣ሸሌ፣ባር ሌዲ፣ ወዘተ የሚሉትን አስቀያሚ ስሟ ነዉ፡፡
#ወንዱ ዛኒያም☞ ዝሙተኛ፣ሂያጅ፣አመንዝራ፣ዘልዛላ፣ የወሲብ መንገደኛ፣ ወንድኛ አዳሪ፣ ወንድ ሸሌ፣ ሸርሙጣ፣ ወዘተ በመባል በሀገራችን ባህል ይጠራል
ዝሙተኛ ከመሆን ይጠብቀን..ዝሙት ላይ ያለነዉን እንደ ምንጭ ዉሀ ኩልል ያለ ተዉበት አላህ ይወፍቀን


#ምዕራፍ
ይቀጥላል...
አስተያየት ካለ በዚህ ማቀበል ይቻላል
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot
join👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
🔥#በዝሙት_በሽታ_የተበከለ_ትዉልድ🔥🔥
        
           🔰 #ምዕራፍ_ስምንት
                አሚር ሰይድ



  ዛሬ ደግሞ እንደ ቀልድ የያዝነዉ ዝሙት ከአኼራ ቅጣት ከጀሀነም ቀጥሎ በዱንያ የተለያዩ ችግሮችን ይዞ ብቅ ብሏል ከዛ ችግሮች የተወሰነዉን እንዳስሳለን

╔══════════════════════╗
   🔰 #የኤች_አይቪ_ኤድስ_በሽታ 🔰         
╚══════════════════════╝

    በመጀመሪያ ደረጃ እዚህ ቻናል ላይ ኤች አይቪ ኤድስ ያለባቸዉ ተከታታዮች እንዳሉ አቃለሁ ..ብዙዎቻችሁ ከቤተሰብ ከልጅነት ጀምሮ በበሽታዉ እንደተያዛችሁ አቃለሁ..እናም ይህን ፁሁፍ ሲዘጋጅ እናንተን ለመንካት አስቤ አይደለም፡፡እናንተንም አይመለከትም ..ይህ ፁሁፍ አላማዉ አሁን ላይ ወጣቱ ዚናን ቀላል አድርጎ ይዞ በሀራም እየተሽከረከረ ስለሆነ ለእነሱ ማስተማሪ ቢሆን ብየ በማሰብ የተዘጋጀ ነዉ፡፡



 ✏️✏️ከዝሙት አበይት መዘዞች መካከል አንዱና በመላው ዓለም የተሠራጨዉ የዝሙት ካንሰር የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ በሽታ ነው፡፡ ይህ በሽታ በገዳይነቱ አቻ የሌለው ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜ መኖሩ የተረጋገጠው እኤአ 1981 በአሜሪካ ነበር፣ በ UNAIDS መረጃ መሠረት ኢኤ.አ በ2007 በዓለም አቀፍ ደረጃ በኤች.አይ.ቪ ኤድስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 33.2 ሚሊዮን የነበረ ሲሆን፣ እስከ 2.4 ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎች በዚያው ዓመት በኤድስ የተነሳ ሞተዋል፡፡ በዚያው ዓመት እስከ 4 ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡

መረጃው አያይዞ እንደጠቆመው በቫይረሱ ከሚያዙት አዳዲስ ሰዎች ውስጥ 40 በመቶው የሚሆኑቱ ዕድሜያቸው ከ15-24 ዓመት የሚሆኑ ወጣቶች ነበሩ፤ ☞ከሰሐራ በታች ባለው ክፍለ አህጉር ደግሞ ሴቶች ከአጠቃላይ የኤችአይቪ ተጠቂዎች ውስጥ 60 በመቶውን፣
☞ አዲስ ከሚያዙት ውስጥ ደግሞ 77 በመቶውን ድርሻ ይዘዋል፡፡ በውጤቱም ኤች.አይ.ቪ የዚህች ዓለም ትልቁ ሰጋት ሆኖ ተገኝቷል፡፡


📌📌እንደው ለአብነት ያህል የኤች.አይ.ቪ ቫይረስ በዓለም፣ በኢትዮጵያና በአዲስ አበባ ያለውን ሥርጭት በመጠኑ ብናይ ጥሩ ይመስለኛል፡፡ ለምሳሌ እኤአ በ2011 UNAIDS ባወጣው ሪፖርት መሠረት ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ የተገኘባቸው ወገኖች 34.2 ሚሊዮን ሲሆኑ፣
☞በኢትዮጵያ 789,900 ዜጎች!
☞በአዲስ አበባ ደግሞ 91,680 ሰዎች ላይ ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ ተገኝቶባቸዋል፡፡

አሁን ደግሞ በቅርብ በተደረገው ጥናት መሠረት የበሽታው ሥርጭት እምብዛም ሳይቀንስ
☞በኢትዮጵያ 741,487 የኤች.አይ.ቪ ቫይረስ በደማቸው የሚገኝባቸው ወገኖች እንዳሉ ታውቋል፡፡ በዚህም መሠረት በሀገር አቀፍ የበሽታው ሥርጭት 1.2% ሆኗል፡፡


📌📌በ2008 ደግሞ ኢትዮጵያም በኤድስ ከፍተኛ ጉዳት ከደረሰባቸው አገራት አንዷ ስትሆን
🔸አንድ ነጥብ አራት ሚሊዮን ሰዎች በኤች.አይ.ቪ ተይዘዋል፤
🔸 129 ሺህ አዳዲስ ሰዎች ደግሞ በየዓመቱ ይያዛሉ፡፡
🔸 ዕድሜያቸው ከ15-49 ባሉ አዋቂዎች ላይ ሶስተኛው የሞት መንስኤ ከመሆኑ በላይ በየዓመቱ ከ30ሺህ የሚበልጡ ሕፃናት ኤች.አይ.ቪን በደማቸው ይዘው ይወለዳሉ፡፡



📌📌 በአዲስ አበባ ደግሞ 117.320 ኤች.አይ.ቪ በደማቸው የሚገኝባቸው ወገኖች እንዳሉ የተጠቆመ ሲሆን፣ የበሽታው ሥርጭትም 3.5% ደርሷል፡፡ በፆታ ስብጥርም
🔻ሴቶች 4.9% እና
🔻 ወንዶች 2.5% እንደሆነ EPHl estimate 2015 ያሳያል፡፡ ስለዚህ ይህ በሽታ አምራችና የተማረ (ብዙ የሥራ ልምድ ያለውን) እና ዕድሜያቸው ከ15-49 ያሉ ዜጎችን፤ በተለየ ሁኔታ ሀገር ገንቢ የሆኑ የሕብረተሰብ ከፍሎችን በማጥቃት በአጠቃላይ በሀገር ዕድገት ላይ ትልቅ እንቅፋት ሆኗል፡፡

🧷በደቡብ አፍሪካ ከ5 ሰዎች አንዱ ኤች.አይ.ቪ አለበት፡፡
🧷 በድሬዳዋ ከ10 ሰዎች መካከል በ2ቱ ላይ ቫይረሱ አለባቸው፡፡
🧷አዲስ አድማስ ሕዳር 17 ቀን 2009 ባወጣዉ ዘገባ መሠረት ከ4 ሴተኛ አዳሪዎች መካከል አንዷ ኤች አይ ቪ አለባት፤

....በዓመት 17,000(አስራ ሰባት ሺህ) ሰዎች በላይ በቫይረሱ ይያዛሉ፡፡ በቀን ደግሞ ከ40 ሰዎች በላይ በበሽታው ይሞታሉ፤ እንደዚሁም በዓመት ከ24 ሺህ ሰዎች በላይ በቫይረሱ ይያዛሉ፤ በሀገር አቀፍ ደረጃ ቫይረሱ የተገኘባቸው ዜጎች ብዛት 740 ሺ ሲሆኑ ከነዚህም ውሰጥ አብዛኞቹ ባለትዳሮች ናቸው፤

የሴት ተጠቂዎች 450 ሺህ የወንዶች ደግሞ 290 ሺህ ነው ፡፡በመኪና አደጋ ህይወታቸዉን ከሚያጡት ይልቅ በኤድስ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በ500% ይበልጣል፤ በሌላ አነጋገር ከዋና ገዳይ መንስኤዎች መካከል አንዱ፣ ዛሬም ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ነው፡፡


,,, የዝሙት መዘዞች በሀገሪት ላይ ከፍተኛ ወጪን ያስከትላሉ፡፡ ለምሳሌ ለኤች.አይ.ቪ/ኤድስ መድኃኒት መግዣና ሕከምና የሚወጣው ከፍተኛ ወጪ የዝሙት መዘዝ ነው፡፡ ለኮንደምና ለእርግዝና መከላከያ መድኃኒቶች ከፍተኛ ወጪ ይወጣል፡፡ ዛሬ ዛሬ በዓለም ደረጃ ድህነትን ለመዋጋት ሳይሆን የዝሙትን መዘዞች ለማከም ከፍተኛ ገንዘብ እየፈሰሰ ነው፡፡ ለምሳሌ ጁን 9 ቀን 2016 የወጣው የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ የበጀት ጥየቃ እንደሚያመለከተው ከሆነ ለ2017 የበጀት ዓመት ለፌዴራል ኤች.አይ.ቪ መርሃ ግብር 34 ቢሊዮን ዶላር እንዲመደብ ጠይቋል፡፡ ከዚህ ፈንድ ውስጥ 27.5 ቢሊዮን ዶላር ለሀገር ውስጥ ፀረ- ኤች.አይ.ቪ መርሃ ግብር የሚውል ሲሆን 6.6 ቢሊዮን ዶላር ግን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሚደረግ ፀረ-አይ.አይ.ቪ ሥራዎች የሚውል ነው:: የ2017 የበጀት ዓመት የኤች አይ ቪ ጭማሪ ጥየቃ ከባለፈው ዓመት የ1 ቢሊዮን ዶላር ጭማሪን ያሳየ ሲሆን የዚህም ምክንያት ለሕከምናና ለመከላከል የሚውለው ውጪ ከፍ ማለት አለበት ከሚል እሳቤ የተነሳ እንደሆነ ከዋይት ሐውስ የወጣው መረጃ ያመለከታል፡፡

....እንግዲህ ይህ ሁሉ ገንዘብ በኤች.አይ.ቪ ላይ ሲፈስ በተቃራኒው ድህነትን ለማጥፋት ቢውል ኖሮ ምን ያህል ለውጥ እንደሚያመጣ ለአፍታ እናስብ፡፡ ይህ እንግዲህ የዓለማችን ከፍተኛ ገንዘብ ወዴት እየሄደ እንደሆነ ያመላክታል፡፡ ዝሙት ቁጥር 1 ዓለም አቀፍ እኩይ ሀይማኖት በመሆኑ ለዓለማችን ድህነትን ማስወረሱን ያረጋግጥልናል፡፡

╔══════════════════╗
🔰 #የእርግዝና_መከላከያ_ፓስትፒል 🔰
╚══════════════════╝
    ☞በአፍሪካ ዉስጥ በአመት 8ሚለየን ዉርጃ ይካሄዳል፡በጦርነት ግን 8 ሚሊየን ህዝብ አያልቅም::


    ወጣቱ ዘንድ ዝሙትን መፈፀም ተራ ነገር ሁኗል፡ ነገር ግን እንደፈለጉ የዝሙት ዛር እንዳይጫጫሱ እርግዝና ትልቅ እንቅፋት ሆኖባቸዋል:: በብልግናው እንደፈለጉ እንዳያተረማምሱ እርግዝናው ገድቧቸዋል፡፡ የአሁን  ወጣቶች ትልቁ ስጋትም እርግዝናው እንዳይፈጠርና ሆድ ከፍ እንዳይል ነው፡፡ ግን #ፖስትፒል ከጭንቀታችን ገላግሎናል ይላሉ፡፡ እንደነርሱ እሳቤም እርግዝናን በፖስትፒል ሸውደዋል፡፡ ይህም በተራው የፖስትፒል ጥገኞችና ሱሰኞች እንዲሆኑ አድርጓቸዋል።በተደጋጋሚ ፒስትፒል መጠቀሙ የሚያደርሰዉን ጉዳት አላወቁትም፡፡ አንድ ሴት በህይወት ዘመና ፒስትፒል ልዉሰድ ካለች ከ3ቴ በላይ መዉሰድ ከባድ የህይወት አደጋ ተጓዳኝ በሽታ ያመጣል፡፡👇👇👇
ነገር ግን ይሄን ባለማወቅ በብልግናው ረገድ ይኸው እንከብል የተለመደ ሱስ ሆኗል፡፡ ዝሙት እራሱን የቻለ አደገኛ ሱስ ነው፡፡ የእንከብሉ ሱስ ሲታከልበት ደግሞ በሱስ ላይ ሌላ ደባል ሱስ ስለሚሆን አደጋውን አያድርስ ያስብላል፡፡ ታዲያ በፖስትፒል ሱስ የተደፋፈረውና ይበልጥ ለማተረማመስ የልብ ልብ የተሰማው ወጣት ዓላማው ዝሙትን እንተው፤ ከዝሙት እንራቅ የሚለው ሳይሆን ዝሙትን ልማዳችን አድርገን እንውሰድ የሚል ይመስላል፡፡ ለዚህም ማረጋገጫ የፖስትፒል ሱሰኞች መሆናቸው ነው::

📚 ዘመናዊዎቹ የሸገር ወጣቶች በልቅ ወሲብ አየተጫጫሱ ነው፡፡ በአዲስ አበባ በተደረገ ጥናት  ወሲብ ፈፅመው ከሚያውቁ 24 ሴቶች ውስጥ ቢያንስ ለአንድ እና ከዚያ በላይ ለሆነ ጊዜ ሁሉም ልቅ ወሲብን ፈፅመዋል። ከእነዚህ ውስጥ

ተመርምረን የጋብቻ ጥርጊያ መንገድ እያሰናዳን ስለሆነ የሚል ምክንያት ሶስቱ ያቀረቡ ሲሆን፣
አራቱ በባዶ ወሲብ ከመፈፀማቸው በፊት የኤች.አይ.ቪ የደም ምርመራ ማድረጋቸውን ገልፀዋል፡፡
17ቱ ግን ቅድመ የደም ምርመራ ሳያከናውኑ አንዴ እና ከዚያ በላይ ለሚሆን ጊዜ በልቅ ወሲብ ተደስተዋል፡፡ ሁሉንም የሚያመሳስላቸው ወሲብ ከፈፀሙ በኋላ ሁሌ ፖስትፒል መጠቀማቸዉን ተናግረዋል፡፡


     ╔═════════════════╗
      🔰 #የሴቶች_ዉርጃ_መበራከት 🔰    
     ╚═════════════════╝



እኤእ የ2014 የውርጃ ዳታ እንደሚያሳየው
☞በመላው ሀገሪቷ 73,167 ውርጃዎች ተካሄደዋል፡፡
☞በአዲስ አበባ ውስጥ ደግሞ 135,999 ውርጃዎች ተፈፅመዋል፡፡ ይህም በቀን በአማካይ 373 ውርጃዎች ይካሄዳሉ ማለት ነው፡፡

አሁን የሚወጡ መረጃዎች ደግሞ በአዲስ አበባ ውስጥ የውርጃ መጠኑ በእጥፍ መጨመሩን ያሳያሉ፡፡
በአፍሪካ ደግሞ በዓመት 8 ሚሊዮን ውርጃ ይፈጸማል፡፡ ከዚህም ውስጥ የኢትዮጵያ ብቻውን አስር ከመቶውን ይዟል፡፡

⚡️⚡️በሙስሊሙ ማህበረሰብ ውስጥ በሁለት ጥንዶች መካከል ከጋብቻ በፊት ብዙውን ጊዜ ያልተፈለገ እርግዝና ሲከሰት እንስማለን፡፡ ታዲያ ይህ ችግር እጅጉን የሰፈና የበዛ በመሆኑ በተለይ በአፍሪካ ቲቪ የፋታዋ ፕሮግራም ላይ በብዛት የሚጠየቀው ይህንኑ ነጥብ አስመልከቶ ነው፡፡ በተጨማሪም በአዲስ አበባ በርካታ ኢማሞች በተደጋጋሚ እየተደወለላቸው ከጋብቻ ውጭ ላረገዙ ሴት ልጆቻቸው ኒካህ እንዲያስሩላቸው በወላጆች ይጠየቃሉ፡፡

╔══════════════════════╗
   🔰 #ዓረብ_አገር_ያሉ_ኢትዮጵያዉያን
          #ሙስሊሞች_የሚስተዋሉ_ችግር 
╚══════════════════════╝



    ዓረብ አገር ያሉ ኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች ዘንድ ከጋብቻ ዉጭ እያረገዙ ኒካህ ይታሰርንል በማለት በብዛት ሥር ሰድዶ ይገኛል፡፡ ደግሞ ከቁጥጥር ከአቅም በላይ ሥር ሰድዶ የሚገኘው ችግር ማግባትና መፍታት ሱስ ሆኖ መገኘቱ ነው፡፡ አረብ ሀገር አንድ ወንድ ምናልባትም በዓመት ውስጥ በአማካይ ሁለት ጊዜ ይፈታል፤ ሁለት ጊዜ ቀያይሮ ያገባል፡፡ ይህም እንደ ልማድ ተወራርሶ በርካቶች ይህንኑ የሙጥኝ ብለውታል፡፡ እነርሱ ዘንድ መፍታትና ማግባት ውሃ የመጠጣትን ያህል ቀላል ሆኖ ይታያል፡፡


╔══════════════════════╗
  🔰 #በአረብ_ሀገር_የኢትዮጲያ_ሴቶች
              #በዝሙት_መሰማራት    
╚══════════════════════╝

    ሌላው ዓረብ ሀገር የተለመደው ችግር የሴቶች ልቅነትና በተለያዩ የዝሙት ሥራ ላይ መሰማራት ነው፡፡ በርካታ ሰዎች እማኝነታቸውን በመናገር እንደገለፁት በተለይ ዱባይ ያሉ ኢትዮጵያዉን ሒጃቢ ሴቶች ሳይቀሩ በየሀገሩ ካሉ ዜጎች ጋር ይማግጣሉ፡፡ ብሎም በርካታ ቋንቋዎችን በአጭር ጊዜ በመማር በርካታ ወንዶችን ማጥመድ እንደቻሉ ይነገራል፡፡ እነዚህ ሴቶች ወንድን የጫማን ያህል በመቀያየር የሚታወቁ ናቸው፡፡ የተለያዩ ቋንቋዎችንም በመናገር ተከነውበታል፡፡
ስራቸው ዚና ብቻ ሁኖ ሀብት የሚያጠራቅሙ በዙ ኢትዮጲያን ዱባይና ሳዑዲአረቢያ እንደሚገኙ ብዙ ሰዎች ምስክረት ሰጥተዋል፡፡ከዚህ ስራ አላህ ተዉበት ወፍቋቸዉ የተገላገሉ ሴቶች በዱባይና በሳዑዲ አረቢያ በጣጣም ልቅነት እንዳለ ይመሰክራሉ፡፡



╔══════════════════════╗  
 🔰#አባታቸዉ_በዉል_የማይታወቅ_ልጆች_መበራከት     
╚══════════════════════╝

የዝሙት ትልቁ መዘዝ ለዝሙት ልጆች መበራከትና ከዚህም የተነሳ በማህበረሰቡ ውስጥ የተለያዩ ወንጀሎች መበራከትና መስፋፋት ነው፡፡
  ዝሙት እና አባታቸው በውል የማይታወቁ ልጆች የታጨቁባት ዘመናዊዋ ዓለማችን ምን ደረሰቸ???

   ጥናቶች እንደሚያመለከቱት
☞ 40% አሜሪካዉያንና
☞ 50% እንግሊዛዉያን አባቶቻቸውን በውሉ አያውቁም፡፡ (ዓለምን የሚመሩት እነዚሁ መሆናቸውን ልብ ይበሉ፡፡)

☞እንደዚሁም 65% ስዊዘርላንዳዉያን አባቶቻቸውን አያውቁም::
☞ በ እንግሊዝ 2/3ኛው ሕፃናት የሚያድጉት በነጠላ ወላጆች አማካኝነት ነው፡፡ በሌላ አነጋገር እነዚህ ሁሉ ከጋብቻ አልጋ ዉጭ የተወለዱ ናቸው፡፡ የዓለም አባቶቻቸውን በወጉ በማያወቁ ሕዝቦች መመራትም ዝሙት በዓለም አቀፍ ደረጃ ምን ያህል ስር እንደሰደደ ይጠቁማል። ሌላው ጥናት እንዳመለከተው አሁንም 40% እሜሪካዉያን ልጆች የሚወለዱት ከነጠላ ወላጆች (በትዳር ካልተጣመሩ) ነው::

  እንግሊዞች ከመቶ ርዕሰ መምህር አንድ አባት ይሻላል የሚል አባባል ቢኖራቸዉም ግን 2/3ህፃናት የሚያድጉት ያለ አባቶቻቸዉ እንክብካቤ ከእናቶቻቸው ጋር ብቻ ነው:


✏️✏️«እንደ ግለሰቦች ሁሉ ሀገር እና ማህበረሰብም ይታመማሉ፡፡ በቶሎ ሕክምና ካለገኙም እንደ ግለሰቦች ሁሉ ሀገርና ማህበረሰብም ይሞታሉ፡፡ (ዶ/ር ዴሚ አሚሮስት)


✏️✏️አንድ ሀገር ታሟል፤ ከባድ ማህበራዊ ውድቀትም ከፊቱ ተደቅኗል.. የሚባለው የማህበረሰቡ አስኳል የሆነው ወጣቱ በተሳሳተ አስተሳሰብ ሲሞላና በተሳሳተ የሕይወት ጎዳና ላይ ሲጓዝ ነው፡፡.. (ዶ/ር ዴሚ አሚሮስት)

#በቀጣይ_ክፍል ስለቦይ ፍሬንድ ገርል ፍርድ የዝሙት መግቢያ መንገድና ...በፊት የቦይፍሬንድ አመጣጥ ከምዕራባዉያን እንዴት ወደኛ ጓዳ እንደገባ እንዳስሳለን

#ምዕራፍ
ይቀጥላል........

አስተያየት ካለ በዚህ ማቀበል ይቻላል
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot
join👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
🔥#በዝሙት_በሽታ_የተበከለ_ትዉልድ🔥🔥
        
           🔰 #ምዕራፍ_ዘጠኝ
                አሚር ሰይድ

╔══════════════════════╗ 
🔰--------------🔰-------------🔰 #ቦይ_ገርልፍሬንድነት( #የወንድ_ሴት_ፍቅረኛነት)  
╚══════════════════════╝


አላህ (ሱ.ወ) በተከበረ የቁርአን ቃሉ እንዲህ ይላል፡-
   መጥፎ ሥራዎችንም ከእርሷ የተገለፀውንም የተደበቀውንም ሁሉ አትቅረቡ፡፡ (አል-አንአም 151)

       በዓለም አቀፍ ደረጃ ለዝሙት መንሰራፋትና ይፋ መውጣት ትልቁን ድርሻ ያበረከተውና ወጣት ሙስሊሞችን ሳይቀር ያጠመደው ዓለም አቀፉ የዝሙት መረብ ቦይፍሬንድ እና ገርልፍሬንድ የሚባለው ሕገ-ወጥ የወንድና የሴት ግንኙነት ነው። ይህ የተኩላን ለምድ ለብሶ የመጣው የምዕራቡ ዓለም እኩይ ባህል የዝሙት ሌላኛው ስሙ ነው፡፡ ለሰው ሠራሽ የዝሙት መዳረሻ መንገዶች ዋናው ምንጭም ይኸው ሚዲያ መራሹ የዝሙት ርዕዮት ነው፡፡ ይህ ርዕዮትም ታላቅ የዝሙት አብዮትን አስከትሏል፡፡ ዝሙትም በተለያዩ ማህበረሰቦች ውስጥ ስር እንዲሰድ ከፍተኛ የሆነ ሕገወጥ ወሲባዊ ንቅናቄን አቀጣጥሏል፡፡ በርካቶችም በዚህ ንቅናቄ ውስጥ አቀንቃኝ ሆነው ብዙ ተከታዮችን አፍርተዋል፡፡

   የምዕራቡ ዓለም በሥልጣኔ ስም ወደ ዓለም ካሰረፃቸው እኩይ ነገሮች ዋናዋናዎቹ
☞ዝሙት
☞ቦይፍሬንድነት
☞ግለኝነት
☞የወሲብ ፊልም
☞ አልኮሊዝም  ሲሆኑ ከነኝህ መካከል ግን በሙስሊሙ ማህበረሰብ ውስጥ ሳይቀር  ተቀባይነትን ያገኘው ቦይገርልፍሬንድነት ነው:: የተኩላ ለምድን ለብሶ ወደ ሙስሊሞች ቤት ዘው ብሎ የገባው ፀያፍ ነገር ቢኖር ይኸው ቦይ ገርልፍሬንድነት ነው:: የሚገርማችሁ ከቦይገርልፍሬንድነት በስተቀር ዝሙት እንኳን ሙስሊሞች ቤት የገባው እየተሳበና እየዳኸ ነው፡፡

   #በብዙዎች_ዘንድ ቦይ-ገርልፍሬንድነት ለወደፊቱ ትዳር መሰረትን ይጥላል ተብሎ በየዋህነት ስለሚወሰድ ይኸው ደዌ በዚሁ ደካማ ጎን በመግባት ሰዎችን በቀላሉ ለማጥመድ ችሏል፡፡ ይህም የቦይ-ገርልፍሬንድነት አደገኛነትን ያሳያል፡፡

ሌላው የቦይ–ገርልፍሬንድነት አደገኛነቱ ግንኙነቱ በራሱ ገና ከጅምሩ ሕገወጥ መሆኑ ነው፡፡ ወሲብ እንኳን ባይኖርበት ድርጊቱ ሙሉ በሙሉ ሕገወጥና ለበርካታ ዓመታት መዝለቅ የሚችል ነው፡፡ ከዚህም በላይ ለማህበረሰቡ መጥፎ አርአያ የሚሆን ነው፡፡ የማህበረሰቡን ወሲባዊ እሴቶች የሚሸረሽር ነው፡፡ ወሲብ እንኳን ባይኖርበት ሁለመናው ይፋዊ ዝሙት ነው፡፡

ለምሳሌ አንድ ወንድ አንዲትን ሴት በገርልፍሬንድነት ይዞ ሲያበቃ ከርሷ ጋር በግልፅ ቢታይና ብሎም እርሷን በገርልፍሬንድነት ስም ለሌሎች ቢያስተዋውቃት ይህ ሁሉ ድርጊቱ ይፋዊ ዝሙት ነው፡፡ ሕገወጥ ወሲብ ከታከለበት ደግሞ ወንጀሉ እየተነባበረ ይሄዳል፡፡


╔══════════════════════╗
  🔥 #የቦይፍሬንድ_እና_ገርልፍሬንድ_ምንነት🔥
╚══════════════════════╝



  በርካታ ሙስሊሞች፣ በተለይም ወላጆች ቦይፍሬንድ እና ገርልፍሬንድ የሚሉትን ቃላት ሲሰሙ ተራ የወንድና የሴት ጓደኝነት ስለሚመስላቸው እንዲሁ እንደዋዛ ያዩታል፡፡ ከዝሙት ጋር የሚያያዝም አይመስላቸውም፡፡ ምዕራባዊ ባህል መሆኑን እንጂ ሕገወጥ መሆኑን አይገነዘቡትም፡፡ ሥልጣኔ እንጂ ሰይጣኔ መሆኑንም አያስተውሉትም፡፡

ከዚህም የተነሳ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ይህንኑ እኩይ ባህልን በትዕግስት ተቀብሎ በራሱ ውስጥ ለማንሰራፋት ሁሉ በቅቷል፡፡ ይፋም ወጥቷል፡፡ አሁን አሁንማ #እናቶች_ሳይቀሩ «ከያዝሽ አይቀር ደህናውን የቦይፍሬንድ ያዢ› እያሉ ልጆቻቸውን ማበረታታት ጀምረዋል፡፡ በዚህ ይሁንታ በመደፋፈርም ሴት ልጆች ሳይቀሩ ቦይፍሬንዶቻቸውን ለወላጆቻቸው ማስተዋወቅ ጀምረዋል፡፡ የሙስሊም ት/ቤቶች ሳይቀሩ የቦይ ገርልፍሬንድ መፈልፈያዎች ሆነዋል፡፡


💫💫 ቦይ ፍሬንድ ማለት የአንድ ግለሰብ በሮማንቲክ ግንኙነት ውስጥ በፍቅር ወዳጅነት ውስጥ መደበኛው የወንድ የወሲብ አጋሩ ማለት ነዉ:: ባጭሩ ቦይ ፍሬንድ ማለት የአንድ ግለሰብ ሕገወጥ ባል ማለት ነው::

#ይህ_አንድ ግለሰብ የተባለው አካል ወንድም ሴትም ሊሆን ይችላል፡፡ ስለዚህ አንዲት ሴት መደበኛ የወሲብ አጋር ወይም ቦይ ፍሬንድ መያዝ ትችላለች ማለት ነው፡፡ በተመሳሳይ መልኩ ቃሉን መገደብ ስለማንችል #አንድ_ወንድም ቦይፍሬንድን መያዝ ይችላል ማለት ነው:: ይህ ደግሞ #ለግብረሰዶማዊነት_ግንኙነት የሚውል ነው፡፡ ይህንን ቃል ወደ አማርኛ ስናመጣው ደግሞ በአንድ ቃል መተካት አዳጋች ይሆናል፡፡ ሆኖም ግን የከንፈር ወዳጅ የሚለው ትንሽ ይቀርበዋል፡፡

የከንፈር ወዳጅ የሚለውም ድፍን ያለ ስለሆነ በመጠኑም ቢሆን የቦይ ፍሬንድነትን በርካታ መገለጫዎችን በውስጥ ይይዛል፡፡

#በሌላ_በኩል_ገርልፍሬንድ ሲባል የአንድ ግለሰብ በሮማንቲከ ግንኙነት ውስጥ ወይም በፍቅር ግንኙነት ውስጥ መደበኛው የሴት የወሲብ አጋሩ ናት፡፡ ከመደበኛው የወሲብ አጋር ፆታ በስተቀር ቦይፍሬንድና ገርልፍሬንድ ምንነታቸው ተመሳሳይ ነው፡፡



╔══════════════════════╗
 🔥#የቦይፍሬንድ_እና_ገርልፍሬንድ_አመጣጥ 🔥
╚══════════════════════╝



   እውነታውን እንነጋገር ከተባለ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከዝሙት ጋር በተያያዘ ትልቁን ድርሻ የሚይዘው ይኸው ቦይ–ገርልፍሬንድ የተባለው በሽታ ነው፡፡ ይህ በሽታ በቀደምት ሥልጣኔዎች ውስጥ ከናካቴው ያልነበረና ህብረተሰቡም ፈፅሞ የማይታግሰው ፀያፍ ነገር ነበር፡፡ ግና የሳይንስና ቴከኖሎጂ ምጥቀትን ተከትሎ ሴኩላሪዝም ሲንሰራፋ መንፈሳዊነት እየተዳከመ ሄደ፡፡ በዚህን ጊዜ በሳይንስና ቴክኖሎጂ በመታገዝ «ፀያፍ የሚባል ነገር የለም፤ ከመች ወዲህ ነው ዝሙት ኃጢአት የሆነው? ማንም የፈለገውን ማድረግ ይችላል›› በሚል ሰይጣናዊ ርዕዮት መነሻነት ቅድመ-ወሲብ ልፊያዎችና ወሲባዊ ትዕይንቶች ለዓለም ሕዝብ ይፋ መደረግ ጀመሩ፡፡

 ⚡️⚡️⚡️ይህንኑ ተከትሎ #Free_Sex  (ነፃ ወሲብ) የሚል አዲስ የዝሙት ማስፋፊያ አስተሳሰብ ተቀመረና በሰፊው ዕውቅናን እንዲያገኝ በየሚዲያዎቹ ማስተዋወቅ ተጀመረ፡፡ ይህም የበለጠ ተደራሽ እንዲሆን ተብሎም ቦይ‐ገርልፍሬንድነት በስፋት ተቀባይነትን ያገኝ ዘንድ የሙቪዎች፣የፊልሞች፣የጋዜጦች፣ የመጽሔቶች፣ የመጻሕፍት፣ የድራማዎች፣ የልበወለዶች፣ የቲቪዎች፣የሕትመት ውጤቶች የዘወትር ሥራቸው ሆነ፡፡

በዚህም መንፈሳዊ ማህበረሰቦች ሳይቀሩ ተወረሩና ቦይ–ገርልፍሬንድነትን ተቀብለው ለማስተናገድ ተገደዱ፡፡ ይህም አስተሳሰብ ወደ ብዙኃን ማህበረሰቦች ተጋባና ቦይ ፍሬንድና ገርል-ፍሬንድ የሚሉት ፋሽኖች እንደጉድ ተቀባይነትን አገኙ፡፡ በዚህም የዝሙት አክሰስና ተደራሽነት በየቦታው እንደ ድር ተዘረጋ፡፡ ሰዎችም በዚህ የዝሙት ድር በመጠለፍ ሕገወጥ ወሲቦችን መሥራት ጀመሩ፡፡ የኋላ ኋላም ሴትን በገርል ፍሬንድነት መያዝ ሀይላንድን የመያዝ ያህል ቀላልና ተደራሽ ሆነ፡፡ ዝሙት መስራትም ውሀን የመጠጣት ያህል ቀላል ሆነ፡፡ ሙስሊሙም ከዓለማችን ተፅዕኖ ውጭ መሆን ስለማይችል አነሰም በዛም በዚህ ድር ተጠለፈ፡፡

 ⚡️⚡️ በርካታ ሀይማኖተኛ የነበሩ ማህበረሰቦችም ተፍረከርከው እነሆ ዛሬ ዛሬ ለቦይ ገርልፍሬንድነት ሁኔታዎችን እያመቻቹና መፈልፈያዎችንም እያዘጋጁ ይገኛሉ፡፡ በተቋም ደረጃ እንኳን ብናይ ከት/ቤት እስከ ዩኒቨርሲቲ ቦይ-ገርልፍሬንድነት ሰፊ ተቀባይነትን አግኝቷል፡፡ በጥቅሉ የትም እየተሠራበት ያለ ነገር ነው ማለት ይቻላል፡፡👇👇👇
#ለምሳሌ ወደ ማህበረሰባዊ የአገልግሎት ዘርፎች ብንመጣ፣ ካፌዎች፣ ልዩ ልዩ የመዝናኛ ቦታዎች፣ ሆቴሎች፣ ገስት ሐውሶች፣ ወዘተ ሁሉም ፊታቸውን ከማህበረሰቡ ቀደምት እሴቶች አዙረው ቢዝነሳቸው ሁሉ የቦይ‐ገርልፍሬንድ ግንኙነት ተኮር እንዲሆን አድርገዋል፡፡ ለሕገወጥ ጥንዶች የተለያዩ አገልግሎቶችን የሚሰጡ ማዕከላት በጣም በዙ፡፡ በውጤቱም ለብዙ ዜጎችም ይኸው ፀረ-ትዳር ግንኙነት የኢኮኖሚያቸው አውታር ሁሉ ለመሆን በቅቷል፡፡



 ✏️✏️ ቦይፍሬንድ እና ገርልፍሬንድ ወደ ዝሙት መግቢያ ኬላ ሲሆን በተለይም አዳጊ ሴቶችን ጨምሮ ወደ ዝሙት ለማምጣት የተቀመረ ሴራ ነው፡፡ በዚሁ መሠረት ወንዱ ለአዳጊዋ ሴት «እኔ ወደፊት ለትዳር ስለሚፈልግሽ ገርልፍሬንዴ ሁኚኝ ይላታል፡፡ እናም ወንዱ የሴቶችን የትዳር ወዳድነትን ተፈጥሯዊ ባህሪያቸውን ስለሚያውቅ በቀላሉ በዚህ በኩል ይግባባና ብዙም ሳይቆይ ይተኛታል፡፡ ከዚህ በኋላ የልጅቷ ሕይወት ምስቅልቅሉ ይወጣል፡፡ ሴት ልጅ አንዴ ቀይ የደም ሴሏን ከኒካህ ውጭ ካጣችው ለወደፊቱ ከባድ የሆነን ዋጋ እንደሚያስከፍላት እሙን ነው፡

✏️✏️ #ቦይ_ፍሬንድ እና ገርልፍሬንድ ግንኙነት ሴቶችን ወደ ወሲባዊ ዕቃነትና እና የስሜት ማራገፊያ ሸቀጥነት ለመለወጥ ታስቦ የተወጠነ ሴራ ነው፡፡

📌📌 #በተፈጥሮ አንድ ወንድ አንዲትን ሴት በቀጥታ ለዝሙት ቢጠይቃት እርሷ በተፈጥሯዊ ስብዕናዋ ላይ ከሆነች እሺ አትለውም፡፡ ግና አሁን በተዘረጋው ሰይጣናዊ መረብ እርሷ የወደፊት ትዳሬን በዚህ አጋጣሚ እውን አደርገዋለሁ በሚል ምኞት ለገርልፍሬንድነት ስትጠየቅ እሺ ትላለች፡፡ በዚህ ዓይነት አካሄድም ቦይ ገርልፍሬንድ ግንኙነት ሴቷን ለወንዱ የስሜት ማራገፊያ ያደርጋታል፡፡

የሆነ ሆኖ ከቦይፍሬንድ እና ገርልፍሬንድ በስተጀርባ በርካታ ሰይጣናዊ የእጅ ሥራዎች አሉበት፡፡

⚠️ #በቀጣይ_ክፍል#ስለ_ፓርኖግራፊ(የወሲብ ፊልም)ላይ ያተኮረ ይቀርባል.....


#ሴት_ዝሙተኛ☞ አመንዝራይቱ፣ሸርሙጣ፣ሴተኛ አዳሪ፣የቡና ቤት ሴት፣ሸሌ፣ባር ሌዲ፣ ወዘተ የሚሉትን አስቀያሚ ስሟ ነዉ፡፡
#ወንዱ ዛኒያም☞ ዝሙተኛ፣ሂያጅ፣አመንዝራ፣ዘልዛላ፣ የወሲብ መንገደኛ፣ ወንድኛ አዳሪ፣ ወንድ ሸሌ፣ ሸርሙጣ፣ ወዘተ በመባል በሀገራችን ባህል ይጠራል
ዝሙተኛ ከመሆን ይጠብቀን..ዝሙት ላይ ያለነዉን እንደ ምንጭ ዉሀ ኩልል ያለ ተዉበት አላህ ይወፍቀን

⚠️⚠️⚠️⚠️ አደራ ለአንድ ሰዉ እንኳን ቢሆን ሼር ማድረግ እንዳይዘነጉ


#ምዕራፍ
ይቀጥላል......
አስተያየት ካለ በዚህ ማቀበል ይቻላል
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot
join👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
🔥#በዝሙት_በሽታ_የተበከለ_ትዉልድ🔥🔥
        
           🔰 #ምዕራፍ_አስር
                አሚር ሰይድ


╔══════════════════════╗
 🎖🎖 #ፓርኖግራፊ ( #የወሲብ_ፊልም)🎖🎖
╚══════════════════════╝


   ማንም ይሁን ማን  እነዚያ በሙእሚኖች መካከል ፀያፍ ነገሮች እንዲስሩ የሚወዱና የሚያስፋፉ ወገኖች በቁርአን ከባድ ዛቻ ተሰንዝሮባቸዋል፡፡


‹‹እነዚያ በእነዚያ ባመኑት ሰዎች ውስጥ መጥፎ ወሬ እንድትስፋፋ የሚወዱ ለእነሱ በቅርቢቱም በመጨረሻይቱም ዓለም አሳማሚ ቅጣት አላቸው፡፡ አላህም ያውቃል እናንተ ግን አታውቁም፡፡ (አንኑር 24፡19)

   ምንም እንኳን ቁርአን ፀያፍ ነገሮችን በሙእሚኖች መካከል የሚያስፋፉ ሰዎችን አብዝቶ ቢያስፈራራቸውም ነገር ግን በተለያዩ መንገዶች በርካታ ፀያፍ ድርጊቶች ወደ ማህበረሰባችን ተሰርፀዋል፡፡ ከነዚህም መካከል አንዱና አይደፈሬ ሲባል የቆየው #የወሲብ_ፊልም ነው፡፡ ይህም የብልግናዎች ሁሉ ጥግ እንደሆነ ይታመናል፡፡ ያም ሆኖ ግን በብዙዎች ዘንድ ተቀባይነትን አግኝቶ ሱስ እስከመሆን ደርሷል፡፡ በርካቶቹ የወሲብ ፊልም ሱሰኞችም ከርሱ እኩይ ልምዶች በማካበት ወደ ወሲባዊ እብደቶች ገብተዋል፡፡

     የወሲብ ፊልምን ማየት ያለ ምንም ጥርጥር #ሐራም ነው፡፡ ለአንድ ሙስሊም በማንኛውም ሁኔታ የሌላን ሰው ዐውራ” (የግል አካላት) ማየቱ ለማንም አይፈቀድምና፡፡ የወሲብ ፊልምን ተከትሎ የሚመጣው ሴጋም እንዲሁ ሐራም ነው::

🟢 ከዚህም በላይ በፊልሙ ውስጥ የሚሳተፉ ተዋንያን ዝሙትን እየሠሩ ነው፡፡ ታዲያ አንድ ሙስሊም እንኳን የዝሙትን ትዕይንት ሊመለከት ቀርቶ በሕጋዊ ጋብቻ ውስጥ የሚሠራውን የሌላን ሰው ሕጋዊ የወሲብ ትዕይንት ማየቱ እንኳን ፈፅሞ አይፈቀድለትም፡፡ እንኳን የፖርኖግራፊ አርቲስቶችን ወሲባዊ አካላት መመልከት ቀርቶ የነርሱን ዐውራ እንኳን መመልከቱ ፈጽሞ የተከለከለ ነው፡፡



╔══════════════════════╗
🎖#በወሲብ_ፊልም_ላይ_የተደረጉ_ጥናቶች🎖
╚══════════════════════╝


 ☞ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ከሆነ ከአለም አቀፍ ደረጃ #የኢትዮጲያ የፓርን ፍጆታ ከታይላንድ ቀጥሎ ሁለተኛ ናት፡፡
☞ጥናቶች እንደሚያመለከቱት ከ400 ሚሊዮን በላይ አንላይን ፍለጋዎች መካከል 12.5% ለወሲብ ፊልም ነው፡፡
     

🟡 እንደሚታወቀው በአስቀያሚው የወሲብ ፊልም ውስጥ ፊት ለፊት የሚሳተፉት አብዛኞቹ ተዋንያንና ገፀ-ባህሪያት ያው እንደኛው ሰዎች ናቸው፡፡ እንደዚሁም የስራው ስፖንሰሮች፣ አቀናባሪዎች፣ ከስክሪኑ በስተጀርባ ያሉ ሠራተኞችና ሌሎችም እነዚያ በፊልሙ ላይ ፊት ለፊት የማይታዩ ግለሰቦች ያው የሰው ልጆች ናቸው፡፡

☑️ #ጥናቶች እንደሚያመለከቱት ከሆነ እነዚህ ግለሰቦች ለዚህ ዓይ ዓይን አውጣነትና ድርቅና የበቁት #የአሳማ_ሥጋን ከመብላትም አልፈው አዘውትረዉ በመመገባቸው ነው፡፡ እንደሚታወቀው አሳማ ኃፍረተ ቢስ እንስሳ ነው፡፡ ወንድና ሴት አሳማ ግንኙነት ሲያደርጉ ሌሎቹ አሳማዎች ትዕይንቱን ከበው ያያሉ፡፡ ነጮች «You are what you eat» (አንተ ማለት የምትመገበው ነገር አምሳያ ነህ) እንዳሉት ሁሉ እነዚህም የአሳማን ሥጋ በማዘውተር ሀፍረተ ቢሶችና ዓይን አውጣዎች ሆኑ። የኋላ ኋላም የአሳማን ወሲባዊ ትዕይንት ለዓለም ሕዝብ አስተዋወቁ፡፡

 ☑️ አሳማን በተመለከተ ሌላው እውነታ አሳማ #ቅናተ_ቢስ (የቀናተኛነት መንፈስ የራቀው) እንስሳ ነው፡፡ ከዚህም የተነሳ ሚስቱን ሳይቀር ለሌላው ያቃጥራል ሌላ ወንድ አሳማ ጋር ሴክስ እንድታደርግ ያመቻቻል፡፡በሌላ በኩል የአሳማ ትል ያለው ሥጋ፣ የፈለጉትን ያህል ቢቀቅሉትም ትሉ አይሞትም፡፡ ታዲያ ይህ ትል ከሥጋው ጋር ከተወሰደ በቀላሉ ወደ ተመጋቢው ደም ስሮች ይሰረፃል፡፡ በተመጋቢው የደም ስርዓት ውስጥም ይዘዋወራል፡፡ በዚህ ምክንያት የግለሰቡን ባህሪም ከአሳማ ጋር ያመሳስለዋል፡፡ ታዲያ የሚገርመው የወሲብ ፊልም ተመልካቹም ይህንኑ ባህሪን መወረሱና ጨቅላ ሆኖ መገኘቱ ነው፡፡

🔵 ሄለን አሰፋ #የቦሌ_ጉዶች በሚለዉ መፅሀፏ ገፅ 31 ላይ እንዲህ ብላ አስፍራለች

  «የወሲብ ንግድ ስሙ የነሱ ቢሆንም ብልግናው ግን የጋራችን ሆኗል፡፡ እንግዲህ እኔ የቤት ልጅ ነኝ፡፡ የቤት ልጅ ሆኜ እንዲህ ዓይነት የብልግና ታሪከ ካለኝና ይህን በኔ ያልተጀመረውን ብልግና በተግባር ካደረግሁ ከየትኛው ክፍል ልትመድቡኝ ትችላላችሁ? ከቡና ቤት ሴቶች አትመድቡኝ ነገር ከነሱ በላይ ነኝ፡፡ የቤት ልጅ አትሉኝ ነገር በጨዋ ደንብ ወሲብ አልፈፀምኩም፡፡ የኔ ታሪክ ከሴተኛ አዳሪዎች ታሪክ ጋር ተካቶ አልተፃፈም፡፡ የሌሎቹ የቤት ልጆች ታሪከም አልተፃፈም፡፡ ከቡና ቤት ሴቶች በላይ መፃፍ ያለበት የብልግና ታሪክ ያለው ግን የቤት ልጆች ላይ ነው፡፡ በዚህ ዓይነቱ ከገደብ ያለፈ ብልግና ውስጥ እንድንገባ ካደረጉን ነገሮች ውስጥ አንዱና ዋናው ምከንያት የነጮቹን የወሲብ ፊልም መውደዳችን ነው፡፡ መውደድ ብቻ አይደለም፤ ፈልገን ማየታችን እንጂ፡፡ በቀድሞዋ እኔ ላይም ከፍተኛ ተፅዕኖ ያሳደረው ይሄው ነጥብ ነበር፡፡ ያ የያኔው ዓይን አውጣነት የመጣው ከየት ነው? ብዬ በወቅቱ አስብ ነበርና ምላሹ ከወሲብ ፊልም የሚል ሆኖ ነበር ያገኘሁት፡፡››



🔵 በተጨማሪ ሄለን አሰፋ #የቦሌ_ጉዶች በሚለዉ መፅሀፏ ገፅ29-30 እንዲህ ብላለች

  በተለይ በአሁኑ ወቅት ተዓምር የሆነ ነገር ነው ያለው፡፡ በወጣቱ ስልክ ላይም አለ፡፡ ብዙኃኑ ኢትዮጵያዊ ኢንተርኔት ላይ የሚተከለውም ይህንኑ የብልግና ፈልም ለማየት ነው:: ሁሉም ባይባልም ከግማሽ በላዩ ተበላሽቷል! ያንን ያየ ደግሞ ኖርማል ወሲብ ምንም ስሜት አይሰጠውም፡፡ ስለዚህ እንደኔ ያየውን በተግባር ማድረግ ይፈልጋል፡፡ የራሱን ሴት ካፈረ ወደብልግና ቤቶቻችን ይመጣል፡፡,”


🔵 ሮዛ ቁጥር ➋ በሚለዉ መፅሀፍ ገፅ121 ላይ እንዲህ የሚል ሰፍሯል
    «የዚህ ዘመን ልጆች ከምንጊዜውዏ ይብሳሉ፡፡ የ8ኛ ክፍል ተማሪ ሳሉ አስተማሪ ጥቁር ሰሌዳ ላይ ሲፅፍ በሞባይሎቻቸው ልቅ የወሲብ ቪዲዮዎችን ከወንድና ከሴት ጓደኞቻቸው ጋር ይለዋወጣሉ፡፡ የዘመን ልዩነት ገረመኝ፡፡ እኔ የወሲብ ፊልም ለመጀመሪያ ጊዜ ያየሁት ማትሪክ በወሰድኩበት አመት የክረምት የዕረፍት ወቅት ላይ አንዲት አብሮ አደግ ጓደኛዬ ቤት ነበር፡፡ እንዳሁኑ ሲዲ፣ ዲቪዲ፣ ኮምፒዉተር፣ ላፕቶፕ፣ ሞባይል፣ አይ ፎን፣ አይፓድ የሚባል የዕቃ ዕቃ መዓት አልነበረም፡፡ የጓደኛዬ ወንድሞችና ወላጆች ሲወጡ እግራቸውን ጠብቀን ነበር የወሲብ ፊልም ካሴቱን ዴክ ውስጥ ከተን ላጥ ላጥ አድርገን የኮመኮምነው፡፡ በእርግጥ የ11ኛ ከፍል ተማሪ እያለን Playboy የሚባል የወሲብ መፅሔት በቦርሳዋ ደብቃ በዕረፍት ሰዓት የምታሳየን ልጅ ነበረች፡፡ አዲሱ ትውልድ ፈጣን ነው፡፡ ነገሮችን በፍጥነት ይረዳል፤ በጥድፊያ ይሞከራል፡፡ እንደሰማሁት ከሆነ በአንዳንድ የግል ትምህርት ቤቶች በትምህርት ክ/ጊዜ ሞባይሎቻቸውን፣ አይፎንና አይፓዳቸውን እንዳይጠቀሙ ከልክለዋል፡፡ የክልከላው ዋና ምክንያት ተማሪዎቹ በስፋት የተለዋወጧቸው የወሲብ ቪዲዮዎችና የቻት መልዕክቶች ናቸዉ ብላለች፡፡ በመፅሀፏላይ


✏️✏️ የቅርብ ጊዜ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ከሆነ ከ5የሞባይል ኦላይን ፍለጋዎች መካከል አንዱ ለፓርኖግራፊ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡👇👇👇
በተጨማሪም የ «Covenant Eye ስታትስ እንዳመለከተው ከሆነ ከ10 አዳጊ ወንዶች መካከል 9ኙ 18 ዓመት ሳይሞላቸው ለወሲብ ፊልም የተጋለጡ ናቸው፡፡
✏️✏️ ስታትሱ አያይዞ እንደጠቆመው እንድ አሜሪካዊ ልጅ ለመጀመሪያ ጊዜ በአማካይ በ12 ዓመቱ ለፊልሙ ይጋለጣል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ጥናቶች እንደሚያመለከቱት የሙስሊሞች የወሲብ ፊልም ተጠቃሚነትም ሙስሊም ካልሆኑ ወገኖች እምብዛም አይተናነስም፡፡  የዒባዳ ሙስሊም መሆንና በቀን አምስቱን ዕለታዊ ሶላቶች በወቅታቸው መስገድ ብቻውን ግለሰቡን ከዚህ እኩይ ድርጊት ሊጠብቀው ዘንዳ በቂ ላይሆን ይችላል፡፡ በመሠረቱ ዒባዳ ብቻውን ሙስሊሙን ከኃጢአትና ከፀያፍ ነገሮች አይጠብቀውም፡፡ በዚህ ረገድ ትልቁን ሚና የሚጨዋተው ግብረገብነትና ሰናይ ሥነ- ምግባር ነው፡፡ አንድ ሙስሊም ዒባዳን እዳው አድርጎት ሊፈፅመው ይችላል፡፡ ከዚህ ዓይነት ፀያፍ ነገር የሚጠብቀው ግን የአላህን ተቆጣጣሪነት (ሙራቀባን) ከግምት ውስጥ ማስገባትና የራስህን ስሜት ለመቆጣጠር በአላህ (ሱ.ወ) መታገዝ ነው፡፡ እነዚህ መፍትሔዎች መልካም ሥነ-ምግባርና ግብረገብነት ጋር ተደማምረው አንድን ሙስሊም በርግጠኝነት የወሲብ ፊልምን ከመመልከት ይጠብቁታል፡፡



╔══════════════════════╗
 🎖🎖🎖-----🎖🎖🎖------🎖🎖🎖 #የወሲብ_ፊልምን_የሚያወግዙ_ነብያዊ_ንግግሮች
╚══════════════════════╝

ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺእንዲህ ብለዋል

ማንም ወንድ ወይም ሴት ካልተጋቡ በስተቀር አንዱ የሌላውን እርቃነ ስጋ መመልከት አይፈቀድለትም፡፡›› (ሶሒሕ ሙስሊም)

ታላቁ ሰሓባ ሰልማን አል-ፋሪሲ (ረ.ዐ) እንዳወሩት የአላህ መልዕከተኛ የሆኑት ሀቢቡና ሙሀመድ  ﷺእንዲህ ብለዋል፦ «በአላህ እምላለሁ! እኔ ከሰማያት ላይ መወርወርንና ወደተለያዩ ክፍሎች መበታተንን እመርጣለሁ፤ ከዚያ የአንድን ሰው የግል አካላትን ከመመልከት ወይም አንድ ሰው ወደግል አካላቴ እንዲመለከት ከመፍቀድ፡፡›› (አል-መብሱሥ ኪታቡል ኢስቲሕሳን)

ታላቁ ኸሊፋ ዐሊ ቢን አቡጧሊብ (ረ.ዐ) እንዳወሩት  ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ «ጭናችሁን ለማንም አታጋልጡ፤ ወደሌላ ሰው ጭንም ፈፅሞ አትመልከቱ፣ እርሱ የሞተ ሰው እንኳ ቢሆን፡፡» (ኢብን ማጀህ፣ አቡ ዳዉድና ደረቁጥኒ)

ሰሓባው ጀርሃድ አስለሚ (ረ.ዐ) እንዳወሩት አንድ ጊዜ የአንድ ሰው ጭን በሰዎች ፊት ተገለጠ፡፡ ነብዩም ﷺ ወዲያው «ጭን ተሸፍኖ መቆየት እንዳለበት እታውቅምን?.› አሉት፡፡ (ሙዐጥ-ጠእ ኢማም ማሊከ፣ ቲርሚዚ፣ አቡ ዳዉድ)



╔══════════════════════╗
   🎖🎖 #ፖርንን_የሚመለከቱ_እስታቶች🎖🎖
╚══════════════════════╝

  ይህ ጥናት የዛሬ 8አመት በፊት የተጠና ጥናት ነው ዛሬስ ቢሆን?ስንት እጥፍ ይጨምር ይሆን?

⚡️ የሞባይል ዳታ ዲቫይሶች መፈብረከ በዓለም ላይ እጅጉን የተለመዱ 11 የፖርን ሳይቶችን ወደ 300 አሳድጓቸዋል፡፡

⚡️ከአጠቃላይ የፖርን ሳይት ጎብኚዎች መካከል 60% ሞባይላቸዉን በመጠቀም  ነው።

⚡️ በሞባይል ፎኖች የሚተላለፉ የፖርን ፊልሞች በወር ውስጥ ከ1.3 ቢሊዮን ጎብኚዎችን ይስባሉ፡፡


⚡️ ፖርን በሚጨምር ሁኔታ ሰፊ ተቀባይነትን አግኝቷል፡፡ አዳጊዎችና ወጣቶችም ስለፖርን በሚያወሩበት ጊዜ የበለጠ ከርሱ ፈላጊዎች ሆነው ነው፡፡
⚡️ 13% አዳጊዎችና 17% ወጣቶች ስለፖርን በአዎንታዊና በግድ የለሽነት መንገድ
ያወራሉ፡፡ 40% አዳጊዎችና 43% ሁሉም ሰዎች አንዳንድ ጊዜ ፖርንን ይመለከታሉ ብለው ያስባሉ፡፡ 37% አዳጊዎችና 36% ወጣቶች ፖርንን ስለመመልከት ሞራሊቲ አያወሩም፡፡


╔══════════════════════╗🎖#በህንድና_በደቡብ_አፍሪካ_የተደረገ_ጥናት🎖
╚══════════════════════╝


📌 በህንድ በ400 ተማሪዎች ላይ በተደረገው የአሰሳ ጥናት መሠረት፡-
☞70% ወንዶች ልጆች ፖርንን ማየት የጀመሩት በ10 ዓመታቸው ነው፡፡
☞93% ወንዶች ልጆች እንዳሉት ፖርንም ልክ እንደመጠጥ ሁሉ ሱስ አስያዥ ነው
☞86% እንዳሉት ፖርን ወደ ወሲባዊ ድርጊቶች መርቷቸዋል፡፡

📌 በሕንድ ውስጥ በ8ሺ ልጃገረዶችና ሴቶች ላይ በተደረገው ጥናት 49% እንዳሉት ስለወሲብ የተማሩት የፖርን ፊልሞችን በማየት ነው፡፡

📌በደቡብ አፍሪካ ከ4ሺ ወንዶች በላይ በተደረገው የአሰሳ ጥናት መሠረት
☞ 67% ፖርንን ተመልክተዋል፡፡
☞27% ደግሞ በሳምንት ውስጥ ለበርካታ ጊዜያት ግለወሲብን ፈፅመዋል

📌 በቅርብ የተሠራው አንድ የአሰሳ ጥናት እንዳመለከተው ከ10 ባለትዳር ደቡብ ኮሪያዉን ወንዶች መካከል 4ቱ ለሚስቶቻቸው ታማኞች አይደሉም፡፡

📌 በአየርላንድ ውስጥ በ1002 የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ላይ በተደረገው ጥናት መሠረት 83% ወንዶችና 56% ሴቶች ፖርንን ተመልከተዋል፡፡

📌 በባሎቻቸው ላይ የሚማግጡ እንግሊዛዉያን ሴቶች ቁጥር ባለፉት 20 ዓመታት ውስጥ ብቻ በ40% ጨምሯል፡፡


🟡 #በቀጣይ_ክፍል☞ስለወሲብ ፊልም በኢትዮጲያና በአለም ሙስሊሞች የደቀነዉን መዘዝ እንዳስሳለን




#ምዕራፍ
ይቀጥላል......
አስተያየት ካለ በዚህ ማቀበል ይቻላል
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot



join👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
🔥#በዝሙት_በሽታ_የተበከለ_ትዉልድ🔥🔥
        
          🔰 #ምዕራፍ_አስር_አንድ ➊➊
                አሚር ሰይድ

 
.................... ከምዕራፍ 10 የቀጠለ................
╔══════════════════════╗
   #ምዕራባዉያን_ለወሲብ_ፊልም_ለማሰራጨት
        #ምንያህል_ወጭ_ያወጣሉ
╚══════════════════════╝



     አበልቃሲም ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡- መጥፎና ፀያፍ ነገር በህዝቦች ዉስጥ በምንም መልኩ ግልፅ አትሆንም ፡በዉስጣቸዉ ቀደምት አባቶቻቸዉ የማያዉቅት ወረርሽኝ እና የተለያዩ በሽታዎች ቢከሰቱ እንጂ በማለት ይገልፃሉ

   ፓርኖግራፊ(ልቅ ወሲባዊ ፊልሞች እና ምስሎች)መመልከት ያልተገደበ ወሲባዊ ጡዘትን እና የአእምሮ መረብሽን ያስከትላል፡ልቦናን መረጋጋት እንዳይኖረዉ በማድረግ ላልተፈለገ የወሲብ ሩጫ እና መልከስከስ ይጋብዛል፡፡ አንድ ቀን የሚታይ የወሲብ ፊልም ወይም ምስል ሁለት ወይ ሶስት ቀን ሙሉ አእምሮ ይረብሻል በተደጋጋሚ በአይነ-ህሊና እየመጣ የዉስጣችንን ሰላም የሚያናጋ ክስተት ነዉ፡፡


 🎖🎖🎖 ኢስላም የተራቆቱ ገላዎች መመልከት ግልፅ በሆነ ቁርአናዊ አንቀፅ የተከለከለ እና በተለያየ ነብያዊ ሀዲሶች አፅንኦት ተሰጥቶት የተወገዘ ተግባር ነዉ ፡፡ ይህን አስመልክቶ አሏህ በተከበረ ቁርአኑ እንዲህ ይላል ፡-
""ለምእመናን ንገራቸዉ ዓይኖቻቸዉን ያልተፈቀደን ከማየት ይከልከሉ ፡ብልቶቻቸዉንም ይጠብቁ፡ይህ ለነርሱ የተሻለ ነዉ ፡ አላህ እነርሱ በሚሰሩት ሁሉ ዉስጥ አዋቂ ነዉ፡፡""(ሱረቱ ኑር 30)

ይህ የፊልም ሱስ አመጣጣጡ ምዕራባዉያን ዲነል ኢስላምን ለማቀጨጭ ለማዳከም...ማንኛዉንም ወጣት የማይጠቅም የማይጎዳ ለማድረግ እና ወጣቱን ለማዳከም እና ሴቶች እናትነትን ረስታ የባለጌ ወንዶች መጫወቻ እንድትሆን ታስቦ የተዘጋጀ ነዉ ፡፡ በዚህ የወሲብ ፊልም የተነሳ
☞በርካታ ወጣቶች ለሞት ዳርጓል
☞በርካቶች ለተለያዩ ህመምና ስቃይ ዉስጥ እያቃሰቱ እንዲኖሩ አድርጓል፡
☞በርካቶች በዚሁ ተለክፈዉ የቀን ዉሏቸዉ የለሊት አዳራቸዉ እርሱ ሁኗል...በዚህ ምክንያት ዉድ የሆነ ሒወታቸዉ ጊዜያቸዉን የገንዘብ ብኩንነት ..ሰላማቸዉ ተናግቶ ደስታ የራቀዉ ሒወት እየተገደዱ ነዉ፡፡

እንደ ተርብ እስታስቲክስ መረጃ ከሆነ ለፓርኖግራፊክስ(ለልቅ የወሲብ ፊልሞችና ምስሎች)ድህረ ገፆች የሚወጣዉ ገንዘብ በአመት

☞57.8ቢሊዮን ዶላር ሲሆን
☞በአሜሪካ ብቻ 12 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ይደረጋል..
☞የፓርናግራፊ ድህረ ገፆች ብቻ 4.2ሚሊየን እና 420.ሚሊየን ገፆች ይጠጋሉ፡
በአጠቃላይ ድህረ ገፅ 12በመቶ ለዚሁ ርካሽ ተግባር ማስፋፊያነት ተመድቧል ፡፡
☞በሳምንት 70ሚሊየን የሚጠጉ ሰዎች የብልግና ምስሎችን በኢንተርኔት ይመለከታሉ ከእነዚህ ሰዎች መካከል 20ሚሊየኑ የሚገኙት በአሜሪካ እና በካናዳ ሲሆን በአዉሮፓ ደግሞ ጀርመን እንግሊዝ ስፔን ቀጣዮችን ቦታዎች ይይዛሉ..ምዕራባዊያን እራሳቸዉን ሆነ የዓለምን ህዝብ ወደ አልሆነ መጥፎ አቅጣጫ እየመሩት እንደሆነ መመልከት ይቻላል፡፡

እንደ እስታስቲካዊ መረጃዎች ከሆነ
#ሙስሊም_በሆኑ_ሀገሮች_ላይ_ያሉ_ወጣቶች_ቁጥር ሙስሊም ባልሆኑ ሀገር ላይ ካሉት ወጣቶች ቁጥር በጣም በልጦ ይገኛል ..

በአጠቃላይ የሙስሊም ዓለም ወጣት ብዛት 70 በመቶ ሲጠጋ
በምዕራቡ ዓለም ያለዉ ወጣት ቁጥር 25 በመቶ መሆኑን ያሳያል ፡፡ስለዚህ ለወደፊቱ አለምን የሚረከበዉ ጠንካራ ትዉልድ ያለዉ በሙስሊሙ ዓለም መሆኑ ምዕራቡን አለም ክፉኛ ስላሳሰባቸዉ ሙስሊሙን ወጣት በዚህ የፊልም ሱስ ተለክፎ ከአላህ ጋር ከቁርአን ከሀዲስ ከመስጊድ ያለዉን ግንኙነት ቀንሶ ከዲነል ኢስላም ርቆ ለኢስላም የማይጠቅም የማይጎዳ ትዉልድ ለማድረግ የመጣ ነዉ፡፡


ምእራባዉያን ለወደፊት ለሚመጣዉ ሙስሊም ትዉልድ እንዲበላሽ ከበፊት ጀምሮ ዛሬም ጭምር ቀን ለሊት እየሰሩ ነዉ ፡፡ እኛስ ለሚመጣዉ ትዉልድ ዲነል ኢስላምን ለማስረከብ ምን እየሰራን ነዉ???


    በጣም የሚያሳዝነዉ ይህን ፊልም መመልከት ለተለያዩ የወሲብ ችግሮች መፍትሄ ይሆናል በሚል እምነት የሚናገሩና የሚተገብሩ መኖራቸዉ ነዉ፡፡ ወጤቱ ግን በለቃራኒዉ መሆኑን ዘንግተዉታል

📚📚 አላህ ከብልግና ፀያፍ ነገር..ከማንኛዉም መጥፎ ተግባር እንዲሁም ወሰንን ከማለፍ ይከለክላል
በሱረቱል ነህል 90 ላይ ..በዚህ አንቀፅ ፋህሽ ሙንከርና አል-በግይ የሚሉ ቃላቶች ሰፍረዋል ፡፡
☞ ፋህሽ ማለት ብልግና እፍረተቢስና ቆሻሻ ማለት ሲሆን ወሲባዊ ፊልሞችና ምስሎችን ያካትታል፡፡

☞ ሙንከር የሚለዉ ደግሞ ማንኛዉም በአለም ዙሪያ ያሉ ኢሞራላዊ መጥፎ ስነ-ምግባሮች መገለጫ የሆኑ ባህሪያትን ያካትታል ፡፡ አልበግይ የሚለዉ ኢፍትሀዊ የሆኑ ተግባሮችን ድንበር ያለፈ ጋጠወጥነትን ያካትታል፡፡ከዚህ የተነሳ ልቅ የወሲብ ፊልሞችና ምስሎች በዚህ የቁርአን አንቀፅ ዉስጥ የተገለፀ ስለሆነ ህዝቡን የሚጎዱ ለክፉ ዉድቀት የሚዳርጉ ስለሆነ ህዝበ ሙስሊሞ ሊርቃቸዉና ሊያወግዛቸዉ ሀራም መሆኑን አዉቆ ሊጠነቀቅ ይገባል፡፡





╔══════════════════════╗
#የወጣቱ_የስከሪን_ቀበኛነትና_የወሲብ_ፊልም               #ተጠቃሚነቱ_ከፍ_ማለት
╚══════════════════════╝



    የኢትዮጲያ መረጃዎች እንዳመለከቱት በዓለም አቀፍ ደረጃ በኢንተርኔት አማካኝነት የሚለቀቁትን የወሲብ ፊልሞች በመጠቀም የብልግና ፊልምን በማየት ኢትዮጵያ ከታይላንድ ቀጥላ የሁለተኛነት ደረጃን ይዛለች፡፡ ይህንኑ እውነታም የኢትዮጵያ መንግስትም ተቀበሎታል፡፡ በርግጥ ከመቀበል ውጭ የትም መሸሽ አይቻለውም፤ ምክንያቱም እያነፈነፉ ወደኋላ መሄድና የሀገሪቷን ገመና ማየት ይቻላልና፡፡ እውነታውንም የኢትዮጵያ ቴሌኮም በግልፅ ያውቀዋል፡፡በየአመቱ   በቢሊዮን ብር የሚያተረፈው ኢትዮ ቴሌኮም ለዚህ ሁሉ ትርፋማነት እንዲበቃ ያደረገው አንዱ ምክንያት የዜጎቿ የወሲብ ፊልም ፍጆታ ከጊዜ ወደ ጊዜ መጨመሩ እንደሆነ ይነገራል፡፡

   በተለይ ወጣቱ ሙስሊም አማራጭ መዝናኛ ስለሌለውም ሊሆን ይችላል፤ አልያም ሱስ ሆኖበት ይሆናል፤ ከሞባይሉ ስከሪን ስር አድብቷል፡፡ ይህ ዕቃ ዕቃ ጨዋታም ሰፌድ በሚያከል ሞባይል መሆኑ የሆነን እኩይ ተልዕኮ እንደሚያሳካ ያሳብቅበታል፡፡ ወጣቱ ከሞባይሉ ስከሪን ሥር የሚያደባው ብቻውን ሆኖ ነው፡፡ አንድ ግለሰብ ብቻውን ሆኖ ይህንን ልቅና ጋጠወጥ የሆነውን ሶሻል ሚዲያን ሲቀጠቅጥ ደግሞ ኢብሊስ ወዲያው መጥቶ ሥራን ይሰጠዋል፡፡ ግለሰቡም ወዲያው ወደወሲብ ሳይት ይገባል፡፡ ይህንን ባያደርግ እንኳ በርካታ #ቀበጥ_የኦንላይን_ሒጃቢስቶች ብቅ ይሉለታል፡፡ እርሱም ከነርሱ ጋር ቻት ይጀምራል፡፡ ብሎም ፎን ሴክስ ይሰራል፡፡ በቀን ውስጥ እስከ አስር ጊዜ ፎን ሴክስ የሚሠሩ መኖራቸውም ታውቋል፡፡ በዚህ ዓይነት ሁኔታም ወጣቱ በዝሙት ድርጊት ውስጥ ይዳከራል፡፡

🔶🔶 በእውነቱ የስክሪን ቀበኛ የሆነ ወጣት ለወሲብ ፊልም፤ ለፎን ሴክስ፣ ለቻት ሴክስና ለመሳሰሉት ብልግናዎች የመጋለጥ ዕድሉ ከፍተኛ ነው፡፡ ይህንን የሚያከል ሰፌድ ሞባይል ሲዘረጋም በዚያው ልከ ዕይታውም ልቅ ስለሚሆን ዓይኖቹም ወደፈለጉ ሳይቶች ይወረወራሉ፡፡ በዕይታ የገባ ነገር ደግሞ በቀጥታ ሐሳብ ይሆናል፡፡ ሐሳብ የሆነው ነገር ደግሞ ወደ አስተሳሰብነት ይለወጣል፡፡ አስተሰሳብ ማለት ደግሞ ራሱ ግለሰቡ ነው፡፡👇👇👇
ታዲያ የስከሪን ቀበኛው ወጣት ለበርካታ የብልግና መረጃዎች ሲጋለጥ እርሱ የፈለገውን ያህል ሀይማኖተኛ እንኳን ቢሆን እነዚህ ነገሮች በአዕምሮው በኩል እየገቡበት በነፃነት የማሰብ ችሎታው ውስጥ ጣልቃ ይገቡበታል፡፡ በሂደትም የአስተሳሰቡ አካል ይሆናሉ፡፡

ከዚህም የተነሳ የስከሪን ቀበኛው ለዝሙት የመጋለጥ ዕድሉ ከፍተኛ ነው፡፡ ብዙ ጊዜ የስከሪን ቀበኛ የሆኑት እነዚያው የሴት ቀበኛ የሆኑ ግለሰቦች ናቸው፡፡ የበርካታ ወጣት የስክሪን ቀበኛ የመሆኑ እውነታም የብዙ ወጣት አስተሳሰብ በዝሙት መበከሉን እንገነዘባለን፡፡ ይህም በኡማው መካከል ትልቁ የወጣቶች ገመና ሲሆን ከአስተሳሰብ ጀምሮ ዝሙት ለመስፋፋቱ ትልቁ ማሳያ ነው፡፡

የስከሪን ቀበኛ የወሲብ ፊልም ሱሰኛ ነው፡፡ የስከሬን ቀበኛ የፎን ሴከስ ሱሰኛ ነው፡፡ ሱስ ደግሞ የትም ተከትሎህ ይሄዳል፡፡ ባርያው ያደርግሃል፡፡ ለአደጋ ይዳርግሀል፡፡


 🟢 አንድ ቀን  አንድ መኪና ከሌሎች ሁለት መኪናዎች ጋር መጋጨቱን በዜና ሰማሁ፡፡ ይኸው መኪና በአፍንጫው በኩል እንዱን መኪና ሲገጭ ከኋላው ደግሞ ሌላ መኪና ገጭቷል፡፡ ገጪው ብዙም ሳይጎዳ እነዚያ የተግጩ መኪናዎች ግን መካከለኛ ጉዳቶችን አስተናግደዋል፡፡ በዚሁ መሰረት ይህ ሁለት መኪናዎችን በአንድ ጊዜ እንዲህ የሚጋጭ ሹፌር በምን ዓይነት ሙድ ውስጥ ቢሆን ነው ??? እየተባለ ብዙዎች ማጉረምረም ጀመሩ፡፡

ትራፊከም መጣ፡፡ ለገጪው መንጃ ፈቃድህን አምጣ አለው፡፡ ገጪው ሹፌር እስካሁን አልወረደም፡፡ መኪናው ውስጥ ቁጭም ብሎ በሐሳቡ ሄዷል፡፡ ውረድ ሲባልም ዝም አለ፡፡ ለካ እርሱ በስከሪን ላይ ተተከሎ
#ብልግናን_ሲያይ_ነበር  የወንድነት ስሜቱ እየተፈታተነው ነበር፤ የስከሪን ቀበኛው ቅሳሬ ላይ ነበረ፡፡ ከዚያም ትራፊኩ ሞባይሉን ተቀበሎት ውረድ አለው፡፡ ግና መውረድ አልፈለገም፡፡ ተደናግጧል፡፡ ከዚያም ትራፊኩ ሞባይሉን ከፍቶ ሲያይ ሰውየው ለካ የወሲብ ፊልም እያየ ነበር፡፡ እንዳይዘጋው በአደጋው የተነሳ ተደናግጧል፤ድንብርብሩ ወጥቷል፡፡ግለሰቡ ሰፌድ በሚያከል ሞባይል የወሲብ ፊልም እየጨመጨመ ነበር፡፡ በዚህ እኩይ ድርጊቱ እራሱንም ዜጎችንም አደጋ ላይ ጣለ፡፡
ብዙ ያልተነገሩ ያልተወሩ በወሲብ ፊልም የተሰሩ መዘዞች የደረሱ ወንጀሎች ቤት ይቁጠረዉ....



╔══════════════════════╗
🎖#የወሲብ_ፊልም_ሱስ_የሚደረግ_ህክምና🎖
╚══════════════════════╝



    ልቅ የወሲብ ፊልሞችና ምስሎችን የመመልከት ሱስን ለማስወገድ የሚደረገዉ ህክምና በጣም ከባድ ሁኗል..ምክንያቱም ሱሱ በአንጎል ዉስጥ በቀላሉ ለመፋቅ በማይቻል መልኩ ትዉስታዉን ጥሎ ስለሚያልፍ ይላሉ የተመራመሩ ባለሙያዎች ..ይሄ ሱስ በማንኛዉም ሁኔታ ትዝ እያለ ህይወትን ሊረብሽ የሚችል #የትዝታ_ዕፅ ነዉ፡፡ ነገር ግን እንደ ኢስላም አላህ ሁሉን ቻይ ከመሆኑ አኳያ እና ኢማን ከዚህም በላይ ተአምር ይሰራል ..የሰዉ ልጅ ከዚህም በላይ በከፋ በጣም መጥፎ ልምዶች ዉስጥ ተነክሮ መዉጣት በመቻሉ ከዚህ ሱስ መላቀቅና መዉጣት ይቸላል..መጀመሪያ በአላህ ተስፋ ማድረግ ከዛም ጠንካራ ዉሳኔ ወስኖ ከችግሩ ለመራቅ ቆራጥ አቋም ለመያዝ ሞክሮ መላቀቅ ይቻላል ..የመጀመሪያ መፍትሄዉ ከእነዚህ ልቅ የወሲብ ቻናሎች መዉጣት እና ከተለያዩ እነዚህ ካሉባቸዉ ሚዲያዎችና ደህረ ገፆች ማግለል የመጀመሪያዉ መፍትሄ ነዉ፡፡ ከዛም ቁርአን መቅራት እና ሙሉ በሙሉ ቶብቶ ወደ አላህ መመለስ ነዉ ይሄ ካልሆነ ለወደፊት ትዳር ቤተሰብ መምራት እንደማይቻል ሊታሰብበት ይገባል


🔰🔰 #በቀጣይ_ክፍል
በወሲብ ፊልም እና ዚና ላይ እንዴት በጓደኛ ተፅእኖ እንደሚወድቁና... ለዝሙት መስፋፋት የአሁን ዘመን ሴቶች በሒጃብ ስም የሚለብሱት ልብስ እንደሆነ የሚያተኩር ፁሁፍ ይቀርባል፡፡

አደራ ለአንድ ሰዉ እንኳን ቢሆን ሼር ማድረግ እንዳይዘነጉ


#ምዕራፍ ➊➋
ይቀጥላል......
አስተያየት ካለ በዚህ ማቀበል ይቻላል
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot



join👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
🔥#በዝሙት_በሽታ_የተበከለ_ትዉልድ🔥🔥
        
          🔰 #ምዕራፍ_አስር_ሁለት ➊➋
                  አሚር ሰይድ


╔══════════════════════╗
  #ለዚና_ዋናዉ_ምክንያት_የጓደኛ_ተፅእኖ_ነዉ
╚══════════════════════╝


#ከጓደኞቿ_ከፍ_ያለች_ማሽላ_ወይ_ለወፍ_ወይ_ለወንጭፍ

     በዳይም ከመልክተኛው ጋር ቀጥተኛን መንገድ ይዤ በኾነ ዋ ምኞቴ  እያለ በፀፀት ሁለት እጆቹን የሚነክስበትን ቀን አስታውስ::ዋ ጥፋቴ፤ እገሌን ወዳጅ ባልያዝኩ ኖሮ እመኛለሁ፡፡ (የእምነት ቃልን) ከመጣልኝ በኋላ ከማስታወስ በእርግጥ አሳሳተኝ "ይላል፡፡ ሰይጣንም ለሰው አጋላጭ ነው>> (አል-ፉርቃን 25-29)

     ከዝሙት መዳረሻ እና ልቅ የወሲብ ፊልም ለመግባት አበይት መንገዶች መካከል አንዱ የጓደኛ ግፊት ነው፡፡ ጓደኛ ለመልካምም ሆነ ለመጥፎ ነገር የመዳረግና ሰበብ የመሆን ዕድሉ ከፍተኛ ነው፡፡ በጥቅሉ ጓደኛ ለአንድ ሰው ቅናቻም ሆነ ጥመት፣ መስተካከልም ሆነ መበላሸት፣ ጥፋትም ሆነ ልማት ሰበብ ከሆኑ ነገሮች መካከል በሦስተኛ ደረጃ ላይ ይቀመጣል፡፡ ይህንኑ ቀጥሎ ካለው አንድ ታላቅ ዓሊም ንግግር መረዳት ይቻላል፡፡ አንድ ወቅት አል-አሕነፍ ቢን ቀይስ የተባሉ ታላቅ ሊቅ ‹‹ለአንድ (የአላህ) ባሪያ ሊሰጠው የሚችል መርጡ ነገር ምንድነው?›› ተብለው ተጠየቁ፡፡ እርሳቸውም ምላሽ ሲሰጡ፡-

➊ተፈጥሯዊ የሆነ ቀጥተኛ የማሰብ ችሎታ (ህሊና ወይም ዐቅል) ነው አሉ፡፡
➋ ቀጥሎም «ይህ ሳይሆን ቢቀርስ?›› ተባሉ፡፡ እርሳቸውም «መልካም ሥነ-ምግባር ነው አሉ፡፡

➌ አሁንም ይህ ሳይሆን ቢቀርስ?›› ተባሉ፡፡ እርሳቸውም ሁነኛ ታማኝ ጓደኛ ነው አሉ፡፡

➍ አሁንም “ይህ ሳይሆን ቢቀርስ?›› ተባሉ፡፡ እርሳቸውም «ከአላህ ጋር የተያያዘች ልብ አሉ፡፡

➎ አሁንም «ይህ ሳይሆን ቢቀርስ?» ተባሉ፡፡ እርሳቸውም «ረጅም የሆነ ዝምታ» አሉ፡፡
➏ አሁንም ይህ ሳይሆን ቢቀርስ?» ተባሉ፡፡ እርሳቸውም «አስቸኳይ የሆነ ሞት› እሉ፡፡

   ከጥያቄና መልሱ እንደምንረዳው ጓደኛ በአንድ ግለሰብ ሕይወት ላይ ያለው አስተዋጽፅኦ በሦስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡ መጥፎ ጓደኛ ቀጥተኛ ዐቅል የሌለውንና ሰናይ ሥነምግባር የሌለውን ሰው ይዞ ገደል የመግባት ዕድሉ ከፍተኛ ነው፤ ምክንያቱም ይህንን ሰው ከጓደኛው እኩይ ግፊት ምንም የሚያስጥለው ነገር የለምና፡፡ በተለይ እኩይ ጓደኛ ለነውርና ፀያፍ ድርጊት ሰበብ የመሆንና ግፊት የማድረግ አስተዋፅኦው ከፍተኛ ነው፡፡


#ኡለሞች_እንዲህ_ይላሉ
እያንዳንዱ አመፀኛ እሱን ከአላህ መንገድ የሚያግደው እገሌ የሚባል ጓደኛ አለው:: በትንሳኤው ዕለትም የጓደኛውን ስም እየጠራ ዋ ጥፋቴ! ምነው እገሌን ወዳጄ አድርኔ ባልያዝኩት ኖሮ, እያለ በፀፀት ሁለት እጆቹን ይነክሳል፡፡ ይህም በያንዳንዱ ፋሲቅ ላይ የሚከሰትና የፀና አምላካዊ ቃል ነው፡፡ እናም ጓደኛችሁን በጥንቃቄ ምረጡ፡፡ በውቀቱ መጥፎ ጓደኛን የያዘ ሰው እርሱ እራሱ በዳይ ነው፡፡» (ዑለሞቻችን)

    በአንድ ግለሰብ ሕይወት ላይ የጓደኛ ተፅዕኖ እጅግ ከፍተኛ ነው። ምናልባትም ከወላጆች ቀጥሎ ትልቁን አሻራ ማሳረፍ የሚችለው ጓደኛ ነው፡፡
   በተለይ አሁን አሁን ወላጆች ለልጆቻቸው በቂ ትኩረት፣ እንከብካቤና ተርቢያ በማይሰጡበት ጊዜ ልጆቻቸው ላይ የሚያርፈው የጓደኛ አሻራ የበለጠ ይጨምራል፡፡ መልካም ጓደኛ የያዘ ሰውም ወደላይ ከፍ ይላል፡፡ ከመጥፎ ሰው የተጎዳኘም በጓደኝነቱ ሳቢያ መቀመቅ ይወርዳል፡፡




╔══════════════════════╗
   #ትክክለኛ_ሒጃብ_ያለመኖር_እና_አለባበስ
╚══════════════════════╝


ስለሂጃብ ጉዳይ ብዙዙዙ ተከታታይ ፁሁፎች በየወቅቱ ቀርቧል፡፡ስለሂጃብ ሁሉም ሴቶች ያቃሉ ..አንድ ፀጉሯን ያሳየች 70,000 መላኢካ እንደሚረግማት እና ሽቶ ተቀብታ የምትሄድ ሴት ዜና እንደሰራች ይቆጠራል የሚለዉን የነብዩ ሀዲስ አብዘሀኛዉ ሴቶች በቀኝ ጆሯቸዉ አዳምጠዉ በግራ ጆሯቸዉ ማፍሰሱን ተለማምደዉታል

  “አንተ ነቢዩ ሆይ! ለሚስቶቸህ፣ ለሴቶች ልጆችህም፣ ለምእምናን ሚስቶችም ከመከናነቢያዎቻቸው በላያቸው ላይ እንዲለቁ ንገራቸው፡፡ ይህ እንዲታወቁና (በባለጌዎች) እንዳይደፈሩ ለመሆን በጣም የቀረበ ነው፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡» (አል-አሕዛብ፡59)

  
  ፋጢማ ቢንት ሙሐመድ (ረ.ዐ) «ምርጥ ሴት ማለት ያቺ ወንዶችን የማታይና ወንዶችም እርሷን እንዲያዩዋት የማታደርግ ናት» ብላለች፡፡ ይህም ማለት ወንዱ ዓይነስውር ቢሆን እንኳን፣ ልክ እርሱ እንደማያያት ሁሉ እርሷም እርሱን ማየት የለባትም ማለት ነው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ አንድ ጊዜ ዓኢሻ እና ሀፍሳ (ረ.ዐ) ከነብዩ ﷺ
ጋር ተቀምጠው ሳሉ ዓይነስውሩ ዐብደሏህ ኡም መከቱም (ረ.O) መጣ፡፡ ከዚያም ነብዩ.ﷺ ለሚስቶቻቸው:-

«እራሳችሁን ከርሱ ሸፍኑ አሏቸው፡፡ እነርሱም የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ታዘናል አሉና (ግን) እርሱ ዓይነስውር ነው፡፡ እናም እኛን ለይቶ ሊያውቀን አይችልም እኮ በማለት ጠየቋቸው፡፡ በዚህን ጊዜ ነብዩ ﷺእናንተ ግን ዓይነስውሮች አይደላችሁም፤ እናም እርሱን ማየት ትችላላችሁ, አሏቸው፡፡» (ቲርሚዚ፣ አሕመድና አቡ ዳዉድ ዘግበዉታል)

    ሴቶች በወንዶች ላይ የተተዉ ከባዱ ፈተና ናቸው የተባለበት አብይ ምክንያት ጋጠወጥ ሴቶች ወሲብ ቀስቃሽ ልብሶችን ለብሰው ወደባዳ ወንዶች ስለሚቀላቀሉ ነው፡፡ ይህም ወንዶችን ከምንም በላይ ይፈታተናቸዋል፡፡ ታዲያ ሒጃብም ግዴታ የተደረገው ይህንኑ ፊትናን ለማስቀረት ሲባል ነው፡፡ ወሲብ ቀስቃሽ አለባበስን የሚከተሉ ሴቶች
☞ተሳስተው አሳሳቶች፣
☞አጥፍቶ ጠፊዎችና
☞ነድደው አቃጣዮች ናቸው::


አንዲት ሴት ወሲብ ቀስቃሽ አለባበስን ስትከተል በትንሹ እራሷንና አንድ ሌላ ነፍስን ታጠፋለች፡፡ እናም ለዝሙት መስፋፋት ትልቁ በር የሴቶች ወሲብ ቀስቃሽ አለባበስና የትከከለኛ ሒጃብ አለመኖር ነው፡

ከዝሙት አበይት መዳረሻ መንገዶች አንዱና ትልቁ መስፈርቶቹን ያላሟላ የሴቶች ሒጃብ መንሰራፋት ነው፡፡ ይኸውም ሴቶች ትክከለኛውን ሒጃብ ካልለበሱ ሊሸፍኑ የሚገባቸውን የሰውነት ክፍሎቻቸውንና ጌጣጌጦቻቸውን በየቦታው ለባዳ ወንዶች ይገላልጣሉ፡፡ በተለምዶም ከሴተኛ አዳሪዎች ተሞክሮ እንደምናውቀው ሴቶች አጭርና ስስ ጨርቆችን የሚለብሱ ከሆነ፣ ተገላልጠው፣ ተኳኩለውና ተጋጊጠው ወደ ባዳ ወንዶች የሚቀላቀሉ ከሆነ ይህ እራሱ የሚያስተላልፈው መልዕክት አለው፡፡ አንድም ወንዶችን ዒላማቸው እንዳደረጉ ይጠቁማል፡፡ ከዚህም ባሻገር ገላቸው ለወንዶች ግበዣ የቀረበ መሆኑን ያሳብቃል፡፡

    በተቃራኒውም ሴቷ ሒጃቧን በአግባቡ ከለበሰች ይህም የሚያስተላልፈው የራሱ መልዕክት አለው፡፡ ይኸውም እኔ ላንተ የተከለከልኩ ነኝ የሚል ይሆናል፡፡ እነ ሴቶች ሒጃባቸውን በአግባቡ ከለበሱ ጨዋ እንደሆኑ ተለይተው ይታወቃሉ፡፡ በባለጌዎችም አይደፈሩም፡፡ በመሠረቱ ሒጃብ ማለት አማኝ ሴቶች ለአስገዳጅ ነገሮች ከቤቶቻቸው ሲወጡ ሰውነታቸውን የሚሸፍኑባቸው ልብሶች ናቸው፡፡ ኢስላም ሴቶች ሰውነታቸውን እንዲሸፍኑ ያዛል፤ በዚህም እነርሱ ደካማና ስሜቶቻቸውን መቆጣጠር የማይችሉትን ወንዶች ከመፈታተን ይርቁ ዘንድ ነው፡፡ በኢስላም ወንዶችና ሴቶች ኢስላማዊውን የጨዋ አለባበስ እንዲከተሉ ታዘዋል፡፡ እንዲሁም እርቃነ ስጋቸውን እንዳይታዩም ተከልክሏል፡፡👇👇👇
  “እህቴ ሆይ! አንቺ ምናልባትም አሁን በሕይወት እያለሽ የተሟላወን ሒጃብ ለመልበስና በአግባቡ ለመሸፋፈን ላትፈልጊ ትችያለሽ፡፡ ያው በግልፅ እንደምናየው
☞ሽቶ ተቀባብተሸ፣
☞ከናፍርሽን ሊፒስቲከ አጥግበሽ፣
☞ጡቶችሽን አሹለሽ፣
☞ደረትሽ ከፍተሽ፣
☞ ዓይኖችሽን ተኳኩለሽ፣
☞እጆችሽንና እግሮችሽን ገላልጠሸ፣
☞ወሲብ ቀስቃሽ ጨርቆችን ለበስሽ የትም እየታየሽ ነው፡፡ ከሩቁ ድብን ብላሽ የሰው ዓይን ውስጥም እየገባሽ ነው፡፡ በእውነቱ #ቀበጦቹ_ሒጃቢስቶች ዓይነ ግቡ ለመባል ከፍተኛ ጥረትን እያደረጉ ነው፡፡

ነገር ግን አስታውሺ! አንድ ቀን ከራስ ፀጉርሽ እስከ እግር ጥፍርሽ ድረስ በተገቢው ሁኔታ ትለብሻለሽ፡፡ ግን የዛኔ #ወደመቃብር_ነው_የምትወርጂው፡፡ ስለዚህ ያንን ቀን ለመጀመሪያ ጊዜ የተሟላ ሒጃብን የምትለብሽበት ዕለት አታድርጊው፡፡ እባከሽን አሁኑኑ ልበሺው ዞሮ ዞሮ ከቤት፤ ኖሮ ኖሮ ከመሬት, ሲባል አልሰማሽም? ገላ ፈራሽ ነው፤ ውበትም ጠፊ ነው፡፡ አዎ! ምንም ያህል ብታምሪ፣ የቱንም ያህል ድብን ብለሽ የወንዶች ዓይን ውስጥ ብትገቢ አንድ ቀን ሟች ነሽ፡፡ እናም ከወዲሁ የአኼራ ሕይወትሽን ገንቢ፡፡ በዱንያ ሳለሽ ለቀብርሽ ስንቅ ያዥ፡፡

  #ሙስሊሟ_እህቴ_ሆይ! ልክ እንደ ሉል ሁኚ፡፡ እንደሚታወቀው ሉል ውድ እና ብርቅ ነው:: ለዚህም የበቃው የረጋበት ቦታ ነው፡፡ ሉል ለአሳሾች እሩቅ ነው፡፡ ከዚህም የተነሳ ውድ ሆኗል። አንቺም እንደዚያ መሆን አለብሽ፡፡

በሌላ በኩል እንደዘመኑ ቀበጥ ሒጃቢስቶች እዚያም እዚህ አትታይ፡፡ የትም የሚገኘው እኮ #ድንጋይ_ነው፡፡ እንደ አበባም አትሁኚ ተጠቅመውብሽ ይወረውሩሻልና፡፡ እናም አንቺ ትከከለኛ ሒጃቢ ሴት ሁኚ። በዚያን ጊዜ ሒጃብሽ መከበሪያሽ ይሆናል፡፡ ምንዳሽም ጀነት ይሆናል፡፡



╔══════════════════════╗
  #እስልምናን_ስትተገብሪዉ_ወደ ኢስላም_ትጠሪያለሽ
╚══════════════════════╝



⚡️⚡️አሜሪካዊው ታላቁ ዳዒይና በቁርኣን ተፍሲር ትልቅ ዕውቅናን ያገኘው ኑእማን አሊ ካህን በበኩሉ በምዕራቡ ዓለም እጅጉን የተንሰራፉ ነገሮች በተለይ ወለድና ዝሙትን የመሳሰሉ ኃጢአቶች እነሱ ዘንድ ከሞላ ጎደል እንደማይታወቁ ይናገራል፡፡ በተለይም ከጥቂት ዓመታት በፊት የደረሰውን የምዕራቡን ዓለም የገንዘብ ቀውስን አስመልክቶ ቀውሱ ሙስሊሞችን እምብዛም እንዳላጠቃቸው በመጥቀስ አሜሪካዊው ሙስሊም ከወለድ የራቀ መሆኑን እንደማሳያ ያነሳል፡፡

#ቀጥሎም ዝሙትን አስመልከቶ አሜሪካዉያን ሙስሊሞች ከዚህ መራቃቸውን እንደ ማሳያ የሚያነሳው ነገር ቢኖር የመስሊም ሴቶችን ታላቅ ግብረገብነትና የሒጃብ አለባበሳቸውን በመጥቀስ ነው::

በዚህች ሀገር የሴቶች ትልቁ መከበሪያቸው ሒጃብ ነው:: የራስ መተማመናቸውና ለኢስላም ያላቸው ፍቅር ያስደንቅሃል፡፡ ሴቶቹ እንዴ ከሰለሙ በኋላ ወሲብ ቀስቃሽ አለባበስን ሊከተሉ ቀርቶ ከቶውኑ አያስቡትም፡፡ ቀድሞውኑ ኢስላምን አጥንተውትና መርጠው ስለሚመጡ ሰዉ ምን ይለኛል የሚለውን ነገር ከመጤፍ አይቆጥሩትም፡፡ ወንዶቹም ቢሆኑ አብዛኞቹ ያገቡ ስለሆኑ ስለዝሙት አይነሳባቸውም፡፡

እንደውም በአንድ አጋጣሚ የተከሰተውን ነገር ለምን አልነግራችሁም? በአንድ ወቅት አንዲት ደምቃና የሰዎችን ትኩረት ለመሳብ ተሸሞንሙና የወጣች እንስት ከአንድ ወጣት ሙስሊም ጋር በባቡር ላይ ይገናኛሉ፡፡ ሰዉ ሁሉ አተኩሮ ያያታል፡፡ እርሷም እየተገማሸረች የምትወጣው ለዚህ ነው፡፡ ወንዱ ሁሉ በአድናቆትና በምኞት ይመነጥራል፡፡ ይህ ወጣት ግን አንዳችም ትኩረት ላይሰጣት ቀረ፡፡ እርሷ ግን አልፎ አልፎ ትገረምመዋለች፡፡ እርሱ ወይ ፍንክች አላለም፡፡ ታዲያ ተሳፋሪው ቀስ በቀስ እየወረደ ሲቀንስ እርሷ አውቃ የወጣቱ ዓይን ውስጥ ለመግባት ተጠጋችው፡፡ እርሱ ግን አሁንም ከምንም አልቆጠራትም፡፡ ወዲያ ወዲህ ብትቀበጥም አላተኮረባትም፡፡
..... በመጨረሻም በኃይለኛው ተቆጥታ ለመሆኑ አንተ ወደኔ አንዴም የሚታየው እኔ ይህን ያህል ቀፋፊ ነኝ እንዴ? ቆይ እንዲህ ከሆነ እኔ ለማነው ተጋጊጬ የምወጣውን ስትል አቧረቀችበት፡፡

እርሱ ግን በተረጋጋና የራስ መተማመን መንፈስ በተሞላበት ሁኔታ ይህንን ለምን እንደማያደርግ አስረዳት፡፡ አየሽ! እኛ ሙስሊሞች ዕይታችንን እንድንቆጣጠር ታዘናል፡፡ ስለዚህ ወደ ባዳ ሴት ሆነ ብሎ መመልከት የተከለከለ ነው፡፡ ለዚህ ስል ብቻ ነው እኔ ወደ አንቺ የማላየው፡፡ ከዚህ ውጭ በግል ምንም ያደረግሸኝ ነገር የለም፡፡ የእምነት ጉዳይ ሆኖብኝ ነው ወዳንቺ የማልመለከተው አላት፡፡ ልጅቷ በሰማችሁ ነገር ተገረመች፡፡ እንዲህ ዓይነት ሰውና እምነት እንደዚያ ሰይጣንን አብዝታ በምታበረታታው ሀገረ አሜሪካ መኖሩ አስደነቃት፡፡ እምነት ሰውን ከብልግና ሲታደግ አስተዋለች፡፡ እናም ለመሆኑ ያንተ እምነት ምንድነው? ስትል ወጣቱን ጠየቀችው፡፡ እርሱም እምነቱ ኢስላም መሆኑን ነገራት፡፡ ስለኢስላምም አንዳንድ ነገሮችን ነገራት፡፡ ከዚያም ስልክ ተለዋወጡና በዚሁ ተለያዩ፡፡

ልጅቷ በሰማቸውና ልጁ ላይ ባየችው እፁብ ድንቅ ምግባር እጅጉን ተደምማለች፡፡ እንዲህ ዓይነት ወጣት ገጥሟት ስለማያውቅ ስለርሱ እምነት ልታጠና ጓግታለች፡፡ ወዲያው በነጋታው ደውላ የቁርአንን ኮፒ እንዲሰጣት ጠየቀቸው:: እርሱም የቁርአን ኮፒ ሰጣት ልጅቷም ቁርአንና ሌሎችንም ኢስላማዊ መጻሕፍት ለስድስት ወራት አከታትላ አጠናችው፡፡ ስድስት ወሩ እንዳለቀም ለልጁ ደወለችና ኢስላምን መቀበል እንደምትፈልግ አበሰረችው፡፡ እሱም ወደመስጊድ ወሰዳትና ሰለመችም፡፡ የአላህን አንድነትና ብቸኛ አምላክነቱን መሰከረች፡፡ገና ልትሰልም ስትመጣ እራሱ ሒጃቧን በወጉ ለብሳ ነበር፡፡ እናም አሁን በኛ ማዕከል ውስጥመደበኛ ሴት ዳዒይ ስትሆን በርሷ ሰበብም በርካታ ሴቶች ወደ ኢስላም መጥተዋል፡፡
(ምንጭ፡- ቮይስ ኦፍ ኢስላም - አሜሪካ)

በመጨረሻም ኑእማን አሊ ካን አያይዞም እንዲህ ይላል፡-
«በአሜሪካ ፊትናው ከባድ ነው:: ግና የሰለምቴው ንቃተ ሕሊና ከፍተኛ ነው::

ሙስሊሙ ሐራምና ሐላልን በሚገባ ለይቶ ያውቃል፡፡ እዚህ በአላህ (ሱ.ወ) ሕግ ማቻቻል የሚባል ነገር የለም፡፡ አንዳች ነገር ሐራም መሆኑን ካወቁ ከቤተሰብ ጋር የሚያለያይ እንኳን ቢሆን ለኢስላም ሲሉ ያደርጉታል፡፡,, (ምንጭ፡- ቮይስ ኦፍ ኢስላም - አሜሪካ)

✏️አላዋቂነት ለሁሉም ኃጢአት አብይ ምክንያት ነው፡፡ በተለይ ዝሙት ላይ የድንቁርና አሻራ እጅጉን ይጎላል፡፡ የሰው ልጅ ዓይን ስላለው በጭለማ ውስጥ እንደማያይ ሁሉ ጭንቅላት ስላለው ብቻ ዕውቀት አለው ማለት አይቻልም፡፡ ዕውቀት ከሌለው ደግሞ ድንቁርና መጥቶ እንደ ወቃቢ ይሰፍርበታል፡፡ በርግጥም ከድንቁርና የበለጠ ክፉ ውቃቢ የለም፡፡ ታዲያ የድንቁርና ውቃቢ ያለበት ሰው ቢያንስ በአራት መንገዶች ዝሙት ላይ የወድቃል በአይኑ በምላሱ በእጁ...

#በቀጣይ_ክፍል
ፊልም ቤቶች፣ ሲኒማ ቤቶች እና ማስሚዲያዎች እንዴት ዝሙትን እንዳስፋፉ የሚያተኩር ፁሁፍ ይቀርባል


አደራ ለአንድ ሰዉ እንኳን ቢሆን ሼር ማድረግ እንዳይዘነጉ


#ምዕራፍ ➊➌
ይቀጥላል......
አስተያየት ካለ በዚህ ማቀበል ይቻላል
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot



join👇👇👇
www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
  www.tg-me.com/IslamisUniverstiy_public_group
2024/09/22 10:18:01
Back to Top
HTML Embed Code: