Telegram Web Link
Forwarded from Hawassa University
was a truly inspirational experience and this victory represents a significant step forward for Hawassa University School of Law in the esteemed global arena. We are confident that our team will continue to shine on the national and international stages", he added. The coach has also thanked Mr. Behailu Eshetu (the school head), Dr. Debrework Debebe (Dean of the College of Law and Governance) and Mr. Fikre Tinsae (for co-coaching the students) for their support to the team, underscoring the need for better attention and support from the management for the future.

Hawassa University
Ever to Excel!

Our Social Media Platforms:
***
Website: https://www.hu.edu.et
You tube: www.youtube.com/@hawassauniversity7400
Facebook: https://www.facebook.com/Hawassa.University?mibextid=ZbWKwL
Telegram: https://www.tg-me.com/HUCommunicationsoffice
Email: [email protected] or [email protected]
Telephone: +251462205168
P. O. Box: 05, Hawassa
👍5👏1
Hawassa University Students' Information Center pinned «ለኢንክሉሲቭነስ ክበብ ንቁ አባላት የቀረበ የአቻ ውይይት ስልጠና!! ኢንክሉሲቭነስ ክበብ ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ዳይሬክቶሬት እና ከኒው ጀነሬሽን ፀረ-ኤድስና ሚኒሚድያ ክበብ ጋር በመተባበር የአቻ ውይይት ስልጠና አዘጋጅቷል።የክበቡ ንቁ አባላትም ስልጠናው ላይ እንድትሳተፍ ተጋብዛችዋል። ውይይቱን ለሚያጠናቅቁ ተማሪዎች የማረጋገጫ ወረቀት (certificate) ይወስዳሉ።…»
Forwarded from HU GC
#Update

የ2016 ዓ.ም አጋማሽ ዓመት የመውጫ ፈተና የሚሰጥበት ጊዜ ተራዝሟል።

የመውጫ ፈተናው ከጥር 27 እስከ የካቲት 01/2016 ዓ.ም ይሰጣል ተብሎ እንደነበር አይዘነጋም።

ትምህርት ሚኒስቴር አዲስ ይፋ ባደረገው መርሐግብር ፈተናው ከየካቲት 06 እስከ 09/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ታውቋል።

ለአዲስ ተፈታኞች ሞዴል ፈተና ከጥር 27 እስከ 30/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ቲክቫህ ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘው መረጃ ያሳያል።

የተፈታኞች ዝርዝር ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ በቀጣይ ቀናት እንደሚላክም ተገልጿል።

HU_GC

https://www.tg-me.com/+vajm7ZnKWQk3OGFk
👍1
Forwarded from UNA-ET HU CHAPTER (Raguel Shitu)
📢Announcement

we are very pleased to announce that a new communication head has been assigned to UNA_ET_HU_CHAPTER for the current year 2024 academic calendar.

@UNA_ET
👏5👍2
Forwarded from UNA-ET HU CHAPTER (Raguel Shitu)
📢Announcement

We are very pleased to announce that new team heads and Co-graphics designer have been appointed to manage UNA_ET_HU_CHAPTER teams for the year 2024 academic calendar.

@UNA_ET
👍7👏2
📣ደስ የሚል ዜና📣
የቤተ-መጻህፍት ክበብ ልዩ የእንኳን ደህና መጣችሁ ዝግጅት አዘጋጅቷል።
በዝግጅቱም
➭ ስለ ክበቡ አላማ እና እቅድ ገለፃ
➭ የንባብ ልምድ ማካፈል በተጋባዥ እንግዶች
➭ የተለያዩ የመዝናኛ ፕሮግራሞች
➭ ቤተ-ማጻህፍትን በተመለከተ ንግግር

ለዚህ ፕሮግራም ሁላችሁም ተጋብዛችኋል።
#ቀን፡ ቅዳሜ 25/05/2016ዓ.ም
#ቦታ ፡አፍሪካ ሕብረት አዳራሽ
#ከጠዋት 2፡30 ጀምሮ

⚠️ አባላት በፕሮግራሙ መገኘት ግዴታ ነው!!
ክበቡን መቀላቀል ለምትፈልጉ ልጆች የአድስ አባላት ምዝገባ ይኖረናል።

እናንብብ  ራሳችንን በእውቀት እንገንባ

#የሀዋሳ_ዩኒቨርሲቲ_የቤተ_መጻህፍት_ክበብ
@HUlibraryclub
Forwarded from Inclusiveness club HU main campus (Ermias Worku)
የሎሬት የትነበርሽ ንጉሴ አጭር የህይወት ታሪክ.

በያኔት_ገብረጻድቅ

ሎሬት_የትነበርሽ_ንጉሴ እ.ኤ.አ በጥር 24/1982 የተወለደች ሲሆን የዓይን ብርሃኗን ያጣችው በ 5 ዓመቷ ነበር።ፈጣሪዋን ከማማረር እና ከመውቀስ ግን ይህን አጋጣሚ በአካባቢዋ በብዛት ይፈጸም ከነበረው የልጅነት ጋብቻ የማምለጫ ዘዴ አድርጋ ቆጠረችው።12 ዓመት እስኪሞላት ድረስ የነበረባት የጤና እክል በሌሎች ዘንድ ተቀባይነቷን ሊቀንሰው እንደሚችል አስባው አታውቅም ነበር።

በእድሜዋ የነበሩ ልጆች ግን ጓደኛዋ ከመሆን ሲቆጠቡ ስታይ በክፍለ ሃገር ውስጥ ዓይነ ስውር ሴት መሆኗ ብዙ እንቅፋቶችን ሊጥልባት እንደሚችል ተገነዘበች።"ለ 6 ወራት ጓደኛ አልነበረኝም።ሁሉም በጨዋታ ሜዳ ላይ እየዋለ እኔን ልብ የሚለኝ አልነበረም።በትምህርቴ ከፍተኛ ውጤት ማምጣት ስጀምር ግን እንድረዳቸው ሁሉም ጓደኛዬ መሆን ፈለጉ።ለራሴ በልጬ ከተገኘሁ፣ራሴ ላይ ለውጥ ማምጣት ከቻልኩ ሌሎችን መርዳት እችላለሁ ብዬ አሰብኩ"ትላለች።

የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቷን በምኒሊክ_ሁለተኛ_ደረጃ_ትምህርት_ቤት አጠናቃ የከፍተኛ ደረጃ ትምህርቷንም በአዲስ_አበባ_ዩኒቨርሲቲ ያጠናች ሲሆን የመጀመሪያ ዲግሪዋን በህግ ማስተርሷን ደግሞ በሶሻል_ወርክ ይዛለች።በተለያዩ የዪኒቨርሲቲ ክበቦች ላይ ስትሳተፍ የነበረ ሲሆን የፀረ-ኤድስ እንቅስቃሴ ክበብ ላይም #ሊቀመንበር ሆና ከመስራት ባሻገር በ #2006 የሴት ተማሪዎች ማህበር በመመስረት #በኘሬዚደንትነት ሰርታ ነበር።የፀረ-ኤድስ እንቅስቃሴ በምትሰራበት ወቅት በጣም ብዙ ሃገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ሽልማቶች ተበርክተውላታል።

ለአብነትም በ#2003 #ከደቡብ_አፍሪካ
AMANITARE የተባለዉ ሽልማት ሲሆን ለሴቶች ትምህርት በነበራት ጠንካራ ትግል የተሸለመችዉ ነበር።ከ 10 ለሚበልጡ ነጻ አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች የሰራች ሲሆን ከእነርሱ ውስጥ አንዱ በሆነዉ የሴት ዓይነ ስውራን ማህበር ለአራት ዓመት #በሊቀመንበርነት አገልግላለች።ከዛም በኋላ ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር በመተባበር የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች እና እድገት ማዕከል የመሰረተች ሲሆን አላማው በእድገት እና በኢኮኖሚ ላይ የአካል ጉዳተኞችን ተሳትፎ መጨመር ነው።

እ.ኤ.አ በ2017 The_alternative_Nobel_price የተሰኘዉን አርአያነት ያላቸዉን ግለሰቦች ለማክበርና ድጋፍ ለመስጠት የሚዘጋጀዉን ሽልማት አሸናፊ ሆነች።ይህንን ሽልማት ከአንድ ጠበቃ እና ጋዜጠኛ ጋር የተጋራች ሲሆን ሽልማቱ ወደ 250,000 ዩሮ ይደርሳል።"ከዚህ ሽልማት ጋር ዓለም አቀፍ እውቅና ይመጣል፤ከእውቅና ጋር ተያይዞ ደግሞ ኃላፊነት ይመጣል በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ አካል ጉዳተኞች ብዙ አይነት መገለል ይገጥማቸዋል።የኔ ሥራ በሁለቱ ማህበረሰብ ውስጥ ግንኙነት መፍጠር ነዉ" ስትል ተናግራለች።

ከ 2016 ጀምሮ በፊት አምባሳደር ለነበረችበት LIGHT_FOR_THE_WORLD ለተባለ ለትርፍ ያልቆመ ድርጅት በአማካሪነት በመስራት ላይ ትገኛለች።#ባለ_ትዳር እና የሁለት ሴት ልጆች እናት ሆናለች።

ኢንክሉሲቭነስ ክበብ
በጎነት ለራስ ነው!!

join our Channel 👇👇
@inclusivness_club
👍2
Hawassa University Students' Information Center pinned «የሎሬት የትነበርሽ ንጉሴ አጭር የህይወት ታሪክ. በያኔት_ገብረጻድቅ ሎሬት_የትነበርሽ_ንጉሴ እ.ኤ.አ በጥር 24/1982 የተወለደች ሲሆን የዓይን ብርሃኗን ያጣችው በ 5 ዓመቷ ነበር።ፈጣሪዋን ከማማረር እና ከመውቀስ ግን ይህን አጋጣሚ በአካባቢዋ በብዛት ይፈጸም ከነበረው የልጅነት ጋብቻ የማምለጫ ዘዴ አድርጋ ቆጠረችው።12 ዓመት እስኪሞላት ድረስ የነበረባት የጤና እክል በሌሎች ዘንድ ተቀባይነቷን ሊቀንሰው…»
ማስታወቂያ

ለሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ሴት ተማሪዎች ብቻ

ለሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ሴት ተማሪዎች ብቻ የአቻ ለአቻ ጊዜ ፕሮግራም ለመስጠት ስለታሰበ ሁላችንም ሴት ተማሪዎች መሳተፍ እንደምትችሉ ለማሳወቅ እንወዳለን።  ይህንን ፕሮግራም ለሚጨርስ የምስክር ወረቀት የሚሰጥ ይሆናል።

ለበለጠ መረጃ:
+251985228419 Sumeya Mustefa
+251988748880 Mstire Ashenafi
0982682151 Kalkidan Sitotaw
0975362177 Mekdes Desalegn
0914338798 Aziza Yimam

ከተማሪዎች መማክርት
👍1
በ መራሒት ስር የሚንቀሳቀሰው የበጎ አድራጎት ቡድን ባለፈው አመት መጨረሻ ላይ "አንድ ሞዴስ ለእህቴ" በሚል መሪ ቃል በተሳካ ሁኔታ ለንፅህና መጠበቂያ ሞዴስ ማሰባሰብያ አድርጓል። መራሒት ሞዴስ ገዝታ ለሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሴቶች፤ ህፃናት፤ ወጣቶች፤ ኤች አይ ቪ ኤድስ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ማስረከቡን በደስታ እንገልፃለን። ለዚህ የበጎ አድራጎት ዘመቻ አስተዋፅዖ ላደረጉት ሁሉ እንዲሁም በግዥው ሂደት ለረዱን ሁሉ ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባለን። በማህበረሰባችን ውስጥ አዎንታዊ ተጽእኖ በማሳደር አካል ስለሆናችሁ እናመሰግናለን።

#መራሒት
#እኔ_የእህቴ_ጠባቂ_ነኝ
#merahit
@merahitclub
#I_am_my_sisters_keeper
👏2
ሰላም ዉድ የመራሒት ቤተሰቦች 🤗🤗

እነሆ መራሒት ከመርሳ ሚዲያ ጋር በመተባበር ተወዳጁን የአርብ ምሽት ፕሮግራሟን ወደ እናንተ ለማቅረብ ዝግጅቷን አጠናቃ ምሽታችሁን ከእኛ ጋር ሁኑ ትላለች ።
🗣🗣ዝምታውን እንስበር ፣ ስለ ወጣቶች የአእምሮ ጤና እናውራ! በሚል ርዕስ በተሰናዳዉ ፕሮግራማችን ኑ በጋራ ደማቅ አርብ ምሽትን እናሳልፍ!!

አርብ ምሽት በዜሮ ኘላን:-
👉 ስለ መራሒት ትውውቅ
👉ውይይት
👉 አዝናኝ ኘሮግራም
👉 'open mic'
ፕሮግራሞች የእናንተን መምጣት ይጠብቃሉ።
🚶‍♀🚶‍♀ዛሬም አልቀርም....እግሮች ሁሉ ወደ መራሒት zero plan ያቀናሉ🏃‍♀🏃‍♀

📍አድራሻ : 309 በሚገኘዉ zero plan

ምሽት 1:30 ማንም አይቀርም።
🔉ኑ ምሽታችንን በጋራ እናሳልፍ...

#መራሒት
#mersamedia
#እኔ_የእህቴ_ጠባቂ_ነኝ
@merahitclub
👍2
የምክንያታዊ ባለራዕዮች ስብስብ (RVC)

ውድ የRVC ቤተሰቦች እንዴት ቆያችሁን፤ ሳምንቱ በመልካም እንዳለፈ እምነታችን ነው።

  እንሆ ቀዳሚት ደርሳለችና ኑ በቤታችን ሀሳብ እንጋራ፣ በምከክንያታዊነት እንድመቅ፣ የቆምንበትን መሰረት እንፈትሽ፣ ከአነበብነው እናጋራ ብለን
ሁላቹንም ጋብዘናል።

  በምሽታችን ስለ "ሰው ሰራሽ አስተውሎት (Artificial Intelligence "AI")" ለመምከር መድረኩን ክፍት አድርገን ቤታችንን አሰናድተን ልክ ምሽት 1:00 ሰአት እንጠብቃችኋለን።

  ታዲያ እስከዛው እናንተም የሚከተሉትን ሀሳቦች እያሰላሰላቹ ቆዩልን።

1. ሰው ሰራሽ አስተውህሎት (Artificial intelligence) ምንድነው?

2. የኛ ትውልድ የAI አጠቃቀም ጠቃሚ ነው ወይንስ ጥገኛ እያደረገን ነው?

3. የAI የመጨረሻ ግቡ ምንድንነው? ሰው ሰራሽ አስተውህሎት ከተስፋፋ የሰው ልጅ ድርሻስ ምን ይሆናል?

4. AI ሌሎች የኢንተርኔት platforms ከመጠቀም በምን ይለያያል? ለምሳሌ Google.

5. AIን እደስርቆት ማየት እንችል ይሆን?

6. የAI ተአማኒነት እስከምን ድረስ ነው? በAI (development) እስከየት ነው መሄድ ያለብን?


  📍 አድራሻችን Main Campus Radio ጣቢያው ፊት ለፊት የሚገኘው አዳራሽ።


📌 መቅረት አይደለም ማርፈድ አይታሰብምና ሰዓት ይከበር !!!


#ኑ_የቆምንበትን_መሠረት_እንፈትሽ
#የምክንያታዊ_ባለራዕዮች_ስብስብ
#የተሻለ_ትውልድ_ለተሻለች_ኢትዮጵያ🇪🇹🇪🇹🇪🇹
@RvcClub
@RvcClub
👍4
2025/07/13 06:19:19
Back to Top
HTML Embed Code: