Telegram Web Link
በቤተክርስቲያን የጽጌ ማኅሌት እንጂ የጽጌ ጾም የሚባል ነገር የለም¡
━━━━━━━✦༒🌻 ༒✦━━━━━━━ 

📌 ሙሉ ይነበብ

የደብረ ሊባኖስ አገልጋይ የሆኑ አንድ አባት ከወንድሞች ጋር ሆነን ቅድመ ቅዳሴ ተምረን፣ ተመክረንና አድምጠን እንወጣበት በነበረበት ጉባኤ ቤት በተለየ መልክ በመጪው "የጽጌ ጾም" ስለሚገኘው በረከት እየነገሩን  አባቶች በልዩ ፍቅር ተጠብቀው እንዴት እንደተጠቀሙባት እየነገሩን እንድንዘጋጅ  ይመክሩን ጀመር ። በቸኮለ ማቅኛ (ድፍረት በነዳው አንደበት) ድንገት ማረም አማረኝና  «በቤተክርስቲያን ወርኃ ጽጌ ፣ ዘመነ ጽጌ ፣ ማኅሌተ ጽጌ  እንጂ የጽጌ ጾም የሚባል ነገርኮ የለም አባታችን!» አልኳቸው። 

አልተናደዱም ግን አዘኑ። በትካዜ እጅጉን ዝግ ባለ ድምጽ "እንዲያ እያላችሁ ነው ምታስተምሩት? " አሉኝ። "ለምን መሰልዎት አባታችን… " ብዬ ለማስረዳት እኔ የጽጌን ጾም ንቄና አጥቅቼ ሳይሆን የፈቃድ ጾም ስለሆነ እያልኩ ላብራራ ስንደረደር በከንቱ መውተርተሬን ገትተው እንዲህ አሉ "ተወው የኔ ልጅ አባቴ ቅዱስ ያሬድ እንዲህ ብሎሃል «ጾም ታጸምም ኵሎ ፍትወታት ዘሥጋ ትሜህሮሙ ለወራዙት ጽሙና» #ጾም_የሚባል_የሌለው_በዓለ_ሃምሳ_ብቻ_ነው። ቀንበር አለዘብን ብላችሁ ሸክም አታክብዱ፤ መብል ሥጋን ያገዝፋል ጾም ግን ሰውነትን ያቀላል …  ዛሬማ ፍቅር በራቀበት፣ ተስፋ በመነመነበት፤ ትውልድ እያለቀ ፣ እምነት እየደረቀ  ያለጊዜዋ ምድርን ልታሳልፉ  ጾም የለም እያላችሁ መስበክ ጀምራችኋላ? " ተግሳጹ ከጅራፍ በላይ የሚያም ነበር!  ያኔ  ኅሊናውን ዋሻ፣ አንደበቱን ጋሻ አድርጎ ራሱን የሚከላከል «ሰው» በተፈለገው ልክና በተገቢው መንገድ መጥፋቱ እያስጨነቃቸው  «ምላሱ የሰላ አእምሮው የላላ» ከልክ በላይ የሚፈነጭ የኔቢጤው በየቦታው "ጾመ ጽጌን" ማውገዙ  እጅጉን ሕመም እንደሆነባቸው አስረድተው በአላዋቂነት ስለሰጠሁት ማቅኛ ይቅርታዬን ተቀብለው አለፉኝ። 

ከቅዱስ ያሬድ የነገሩኝን እያሰላሰልኩ 
ጾመ … ጻመወ …  ጸመወ … (ጾመ፣ መከራ ተቀበለ፣ ዝም አለ) የሚለውን ዘር እየቆጠርኩና እያዛመድኩ   ጿሚ፣ ጸማዊ፣ ጽምው ለመሆን በመጣር ከጽሙና መንደር ደርሶ መቆጠብ ያለውን ዋጋ እየመዘንኩ ተመለስኩ።

ባለ ብዙ መልእክት ሆኖ "«ጾም ታጸምም ኵሎ ፍትወታት ዘሥጋ ትሜህሮሙ ለወራዙት ጽሙና» አለ አባቴ ቅዱስ ያሬድ" ያሉት በውስጤ ተመላለሰ። 

ጾም የሥጋን ፍላጎቶች ሁሉ ጸጥ ታደርጋለች። ለወጣቶችም ዝምታን ታስተምራቸዋለች።  (እውነት ነው እርጋታ፣ ዝምታ፣ ጽሙና…  የጾም ውጤት ነው) 

በቤተክርስቲያናችን የበዙ የጾም ቀናት አሉን፤ በዓመት ውስጥ በአጠቃላይ ወደ ፪፻፷ ገደማ ይደርሳሉ ከእነዚህ ውስጥ ወደ ፩፻፹ የሚጠጉ ቀናት ለሁሉም አማንያን እንደ ግዴታ በአዋጅ አጽዋማት ውስጥ ተካትተዋል። ቀሪዎቹ ደግሞ በካህናቱ እና ሌሎች  ምዕመናን በቀኖና፣ በፈቃድ…  የሚጾሟቸው ናቸው። መናንያኑ ግን ከዓመት እስከ ዓመት የዱር ዕፀው ቅጠላ ቅጠል ከውኃ ጋር ሰንበትና በዓለ ፶ እየቀመሱ ከዓመት እስከ ዓመት ይጾማሉ። 

【 Ethiopian Christians observe an extraordinary number of fast days, generally reckoned to be about 250. Of these approximately 180 are obligatory for all believers, while the rest are observed by the clergy and other particularly devout individuals. In addition to the organized calendric fasts, throughout the history of the Ethiopian Church there were ascetics renowned for their extreme fasting, often subsisting on little more than wild plants and water.】  ⇝ Sergew Hable Selassie “Worship in the Ethiopian Orthodox Church” & "The Church of Ethiopia: a Panorama of History and Spiritual Life" 

ቅዱስ ያሬድ ሌላ ምክርም አለው ፦ 

"በፍኖተ ጽድቅ ፍትሑ ለእጓለ ማውታ ወአነሂ እትመየጥ ኀቤክሙ ለሣህል ከመ ፈለገ ሰላም ዛቲ ጾም በቍዔት  ባቲ ትፈሪ ጽድቅ ትሜህሮሙ ለወራዙት ጽሙና ወታበጽሕ ውስተ አዕምሮ ዚአሁ" 

በእውነት መንገድ ለድሃ-አደግ ፍረዱ (የተቸገረውን እርዱ)  እኔም ወደእናንተ ለይቅርታ እንደ ሰላም ወንዝ እመለሳለሁ፤  ጥቅም የሚገኝባት  ይህች ጾም ጽድቅን የምናፈራባት ለወጣቶች እርጋታን የምታስተምር እርሱን ወደማወቅ የምታደርስ ናት ። 

የተዋህዶ ዓይን የኢትዮጵያ ብርሃን ቅዱስ ያሬድ ሌላም ምዕዳን ይጨምራል 

ጾም ቅድስት ትሜህሮሙ ለወራዙት ጽሙና ዛቲ ጾም ቅድስት ወበይእቲ ጾም ተመጠወ ሙሴ ሕገ እግዚአብሔር ጾም ቅድስት ወበይእቲ ጾም ኤልያስ ዓርገ ውስተ ሰማያት ጾም ቅድስት ወበይእቲ ጾም ዳንኤል ድኅነ እምአፈ አናብስት ጾም ቅድስት ሶስና ድኅነት እምዕደ ረበናት ጾም ቅድስት ዓቀመ ኢያሱ ፀሐየ በገባዖን ጾም ቅድስት ጳውሎስኒ ይቤ ትግሁ እንከ አኃውየ በጾም ወበጸሎት ዛቲ ጾም ቅድስት ወበይእቲ ጾም ጾም ቅድስት ትሚህሮሙ ለወራዙት ጽሙና። 

ቅድስት ጾም ለወጣቶች እርጋታ ዝምታን ታስተምራቸዋለች።  ጾም የተለየችና  የተቀደሰች ናት። በዚህች በተቀደሰችዋ ጾም  ሙሴ የአምላኩን ሕግ ተቀበለባት፤  ጾም የተለየችና  የተቀደሰች ናት። በዚህች ቅድስት ጾም ኤልያስ ወደ ሰማይ ዐረገባት ፤  ጾም የተለየችና  የተቀደሰች ናት። በዚህች ቅድስት ጾም ዳንኤል ከአንበሶች አፍ ዳነባት በዚህች ቅድስት ጾም ሶስና ከመምህራኑ ክስ ተርፋለች በዚህች ቅድስት ጾም ኢያሱ በገባዖን ፀሐይን አቆመ ። ጾም የተለየችና  የተቀደሰች ናት! ጳውሎስ እንዲህ አለ ‘ እንግዲህ ወንደረሞቼ በጾምና በጸሎት ትጉ’ ጾም የተለየችና  የተቀደሰች ናት። በዚህች በተቀደሰችዋ ጾም … ቅድስት ጾም ለወጣቶች እርጋታ ዝምታን ታስተምራቸዋለች። 

ደራሲውም እንዲህ ሲል መክሮናል 

… ማርያም ታቦት ጽላተ ኪዳን ሐዲስ፣ 
ቅብዕኒ ርጢነ ጾም እስከ ሰኮና እግር ወርእስ፣ 
እስመ ጾም ትፌውስ ሕማማ ለነፍስ። 

ለሐዲስ ኪዳን ጽላት ታቦቱ ፡ ማርያም አንቺ ነሽና
የጾም መድኃኒቱን ቀቢኝ ፡ ከራስጠጉር እስከ እግር ሰኮና
የነፍስ ሕመም የሚፈወስ ፡ በጾም «በጸሎት» ነውና። 

እንግዲህ ከአባቴ ይኼን ያዝኩላቸው በቤተክርስቲያናችን ጾም የሌለው ለበዓለ ሃምሳ ብቻ ነው። ይልቅ ሰውን በማንጠቅምበት አልፎም ለማያድንም ምክንያት ጾመ ጽጌን አንንቀፋት።

"ወዝኬ ዘሰ ዘይሜህር ዘእንበለ ይኅሥሡ እምኔሁ ወዘእንበለ ምክንያተ ድልወት ለበቁዔተ ሰማእያን ውእቱኬ አብድ ወአኮ ጠቢብ ➺ ይኸውም አስተምረን ሳይሉት እና ሰሚዎቹን የሚጠቅምበት ምክንያት ሳይኖረው ላስተምራችሁ የሚል ሰው አላዋቂ ነው እንጂ አዋቂ አይባልም፡፡ ሰነፍ እንጂ ጠቢብ አይባልም" (ፊልክስዩስ) 

እንኳን ለጽጌ ጾም አደረሰን አደረሳችሁ። በማኅሌት የታጀበውን ተወዳጁን ዘመነ ጽጌ ወርኃ ጾም ተደርቦበት የበረከት ዋጋና በጎ ምላሽ የሚያሰጠን ያድርግልን። 
ከቴዎድሮስ በለጠ
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (♱ ባሕራን ♱)
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (♱ ባሕራን ♱)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
                          †                          

🌼  [   🕊    ወርኃ ጽጌ    🕊   ]  🌼

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

[ ከመስከረም ፳፮ [ 26 ] እስከ ኅዳር ፮ [ 6 ]

“እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ ጽጌ ጸዐዳ ወቀይሕ
አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ
ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ እምላሕ
ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ
ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ”

[ ነጭም ቀይም አበባ የተባለ ልጅሽን እያቀፍሽው በተአምርና በንጽሕና ቀን ወደ ቤተ መቅደስ በገባሽ ጊዜ ርግቤ ድንግል ማርያም ሆይ ከልቅሶ ከሐዘን ታረጋጊኝ ዘንድ ነዪ ፤ መልካማዬ ከደስተኛው ገብርኤልና እንዳንቺ ርኅሩኅ ከኾነው ከሚካኤል ጋር ነዪ ]

 🕊

[ አባ ጽጌ ድንግል ]

🌼🌼      🌷🌷🌷      🌼🌼                     
                    
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (♱ ባሕራን ♱)
🕊

[  † እንኳን ከዘመነ ክረምት ወደ ዘመነ መጸው አሸጋግሮ ለቅዱስ ዮናስ ነቢይ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። †  ]


† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †

† ስንዱ እመቤት ቤተ ክርስቲያን [ሃገራችን] ሁሉ ነገሯ በሥርዓት ነውና ዓመቱን በዘመናት ከፍላ ትጠቀማለች:: እሊሕም ዘመናት መጸው [ጽጌ] : ሐጋይ [በጋ] : ጸደይ [በልግ] ና ክረምት ናቸው:: ዘመናቱ ወቅቶችን ከመለየትና ማሳወቅ ባሻገር የእኛ ሕይወትም ምሳሌዎች ናቸውና ልብ ልንላቸው ይገባል::

ዘመነ መጸው /ወርኀ ጽጌ/ ጥቢ እየተባለም ይጠራል:: በዚህ ወቅት ምድር በአበባ የምታጌጥበት: ክረምት የተለፋበት አዝመራ የሚደርስበት በመሆኑ ደስ ያሰኛል:: በጊዜውም :-

፩. የእመቤታችን የቅድስት ድንግል_ማርያም ስደቷ ይታሠባል:: እርሷ ስለ እኛ :-

-  የሕይወት እንጀራን ተሸክማ መራቧን::
-  የሕይወት መጠጥን ይዛ መጠማቷን::
-  የሕይወት ልብስን አዝላ መራቆቷን::
-  ሙቀተ መንፈስ ቅዱስን የሚያድለውን ተሸክማ ብርድ መመታቷን እናስባለን::
-  ዘመኑ የበረከት ነው::

፪. በሌላ በኩል ጊዜው ወርኀ ትፍሥሕት [የደስታ ወቅት] ነው:: በክረምት የደከመ ዋጋውን አግኝቶ: በልቶ: ጠጥቶ ደስ ይለዋልና:: ያልሠራው ግን ከማዘን በቀር ሌላ እድል የለውም:: ይኼውም ምሳሌ ነው::

ዘመነ ክረምት የዚህ ዓለም ምሳሌ: ዘመነ መጸው ደግሞ የመንግስተ ሰማያት:: በዚህ ዓለም ምግባር ትሩፋትን የሠራ በወዲያኛው ዓለም ተድላን ሲያደርግ ሰነፎች ኃጥአን ግን እድል ፈንታቸው: ጽዋ ተርታቸው ከግብዞች ጋር የመሆኑ ምሳሌ ነው::

በወርኀ ትፍስሕት እንደ ሊቃውንቱ እንዲህ ብለን ልንጸልይ ይገባል::

"ድኅረ ኀለፈ ክረምት ወገብአ ዝናም: ዘአስተርአይከ እግዚኦ ጽጌያተ ገዳም :
አፈወ ሃይማኖት ነአልድ ወፍሬ ምግባር ጥዑም :
አትግሃነ ለስብሐቲከ ከመ ትጋሆሙ አዳም :
ለጽብስት ንሕብ ወነአስ ቃሕም::"

† የዘመናት ባለቤት ዘመነ መጸውን ወርኀ ትፍስሕት ያድርግልን::

🕊

🕊  †  ቅዱስ ዮናስ ነቢይ  †  🕊

† ዮናስ ማለት 'ርግብ: የዋህ' ማለት ሲሆን ከ፲፪ቱ ደቂቀ ነቢያት አንዱ ነው:: በሰራፕታ ተወልዶ ያደገው ነቢዩ በልጅነቱ ታሞ ሙቶ ነበር:: ታላቁ ነቢይ ኤልያስ ግን ፯ ጊዜ ጸሎት አድርጐ ከሞት አስነስቶታል:: [፩ነገ.፲፯፥፲፯] እናቱ የሰራፕታዋ መበለትም ደግ ሴት ነበረች::

ቅዱስ ዮናስ በእድሜው ከፍ ሲል የቅዱስ ኤልያስ ደቀ መዝሙር ሆነ:: የነ ኤልሳዕና አብድዩም ባልንጀራ ነበረ:: ነቢየ እግዚአብሔር ኤልያስ ካረገ በሁዋላ: ቅ.ል.ክርስቶስ በ፰፻ ዓመት አካባቢ የነነዌ ሰዎች ኃጢአት ከመሥፈርቱ በማለፉ የእግዚአብሔር ቃል ወደ አማቴ ልጅ ወደ ዮናስ መጣ::

"ሒድና ለነነዌ ሰዎች ንስሃን ስበክላቸው" አለው:: ከነቢያት ወገን ከሙሴና ከዳዊት ቀጥሎ የዮናስን ያህል የዋህ [ገራገር] የለምና እንቢ አለ [ሰምቶ ዝም አለ]:: እግዚአብሔር እየደጋገመ ሲናገረው ግን "እንዲህ የሚዘበዝበኝ ከፊቱ ብቀመጥ አይደል!" ብሎ ወደ ተርሴስ ኮበለለ::

ወገኖቼ አንድ ነገርን ልብ እንበል:: እንኩዋን ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዮናስ እኛ ክፉዎችም ከጌታ ፊት መሸሸት እንደማይቻል ጠንቅቀን እናውቃለን:: ታዲያ ለምን ሸሸ ቢሉ :- ጥበበ እግዚአብሔር በውስጡ ስለ ነበረበት ነው::

ምክንያቱም ዮናስ በአሣ አንበሪ ሆድ ፫ ቀን እና ሌሊት ኖሮ: ሙስና [ጥፋት] ሳያገኘው መውጣቱ ለጌታ ትንሳኤ ጥላ [ምሳሌ] ነው:: ለዚህም ምስክሩ ራሱ ጌታችን ነው::
"ወበከመ ነበረ ዮናስ ውስተ ከርሠ አንበሪ ሠሉሰ ዕለተ ወሠሉሰ ለያልየ: ከማሁ ይነብር ወልደ እጉዋለ እመ ሕያው ውስተ ልበ ምድር ሠሉሰ ዕለተ: ወሠሉሰ ለያልየ" እንዲል:: [ማቴ.፲፪፥፴፱]

ቅዱስ ዮናስ በገንዘቡ ዋጅቶ ወደ መርከብ በገባ ጊዜ ታላቅ ማዕበል ሆነ:: የእምነት ሰው ነውና እንዲያ እየተናወጡ እርሱ በእርጋታ ተኝቷል:: እነርሱ ግን ቀስቅሰው ቢጠይቁት [እጣ ወድቆበታልና] "የእኔ ጥፋት ስለ ሆነ ወደ ማዕበሉ ጣሉኝ" አላቸው::

እያዘኑ ቢጥሉት ታላቅ ጸጥታ ሆነ:: እነዚያ አሕዛብም እግዚአብሔርን በመስዋዕትና በስዕለት አከበሩ:: ዮናስ ግን በማዕበልና በአሣ አንበሪ ሆድ ውስጥ ለ፫ ቀናት ጸለየ:: አሣ አንበሪው በ፫ኛው ቀን ወደ ነነዌ ተፋው::

ቅዱሱም "እስከ ሠሉስ ዕለት ትትገፈታእ ነነዌ ዐባይ ሃገር" እያለ ንስሃን ሰበከ:: የነነዌ ሰዎች ኃጢአታቸውን አምነው ቢጸጸቱ ከሰማይ ወርዶ ከደመና ደርሶ የነበረው የእሳት ማዕበል ተመልሶላቸዋል::

የነቢዩ ትንቢት ግን አልቀረምና ታላቋ ነነዌ ከ፫፻ ዓመታት በሁዋላ ጠፍታለች:: ቅዱስ ዮናስ ግን በቀሪ ዘመኑ ፈጣሪውን እያገለገለ ኑሯል:: ጠቅላላ እድሜውም ፻፸ ዓመት ነው::

† አምላከ ቅዱስ ዮናስ እድሜ ለንስሃ: ዘመን ለፍስሃ አይንሳን:: ከበረከቱም ይክፈለን::

🕊

[  †  መስከረም ፳፭ [ 25 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት  ]

፩. ጸአተ ክረምት [የክረምት መውጫ]
፪. ቅዱስ ዮናስ ነቢይ
፫. ቅዱስ እንጦንዮስ
፬. ቅድስት በርባራ
፭. ሐዋርያት ዼጥሮስ ወዻውሎስ
፮. ቅዱስ ዕፀ መስቀል

[  †   ወርሐዊ በዓላት   ]

፩. ቅዱስ መርቆሬዎስ ሰማዕት
፪. ቅድስት ቴክላ ሐዋርያዊት
፫. ቅዱስ አበከረዙን ሰማዕት
፬. ቅዱስ ዱማድዮስ ሶርያዊ
፭. አቡነ አቢብ [አባ ቡላ]
፮. ቅዱስ አባ አቡፋና ጻድቅ
፯. ታላቁ አባ ቢጻርዮን ገዳማዊ

" ክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክት ይሻል:: ከነቢዩም ከዮናስ ምልክት በቀር ምልክት አይሰጠውም:: ዮናስ በአሣ አንበሪ ሆድ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እንደ ነበረ: እንዲሁ የሰው ልጅ በምድር ልብ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ይኖራል:: የነነዌ ሰዎች በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ተነስተው ይፈርዱበታል:: በዮናስ ስብከት ንስሃ ገብተዋልና:: እነሆም ከዮናስ የሚበልጥ ከዚህ አለ:: " † [ማቴ.፲፪፥፴፱]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
Audio
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (♱ ባሕራን ♱)
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (♱ ባሕራን ♱)
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (♱ ባሕራን ♱)
🕊                        💖                       🕊   

  [       🕊  እንኳን አደረሳችሁ   🕊       ]

    ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

🌼

እንኳን ለእናታችን ለእመቤታች ለቅድስት ድንግል ማርያም ለልጇ ለወዳጇ ለክብር ባለቤት ለጌታችን ለመድኃኒታች ለኢየሱስ ክርስቶስ ለስደታቸው መታሰቢያ ለፈቃድ ጾም [ለጽጌ ጾም] በሰላም አደረሰን።


[ 🕊    ወርኃ ጽጌ   🕊 ]

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ስርአት መሰረት ከመስከረም ፳፮ [ 26 ] ቀን እስከ ሕዳር ፮ [ 6 ] ቀን ያለው ፵ [ 40 ] ቀን የእመቤታችን ና የልጇን ስደት በማሰብ ወርኃ ጽጌን [ ዘመነ ጽጌን ] ታከብራለች፡፡ ይህ ፵ [ 40 ] ቀን የእመቤታችንና የጌታችንና የአምላካችን ስደት የሚታሰብበት ዘመን ነው፡፡ ወቅቱ የአበባና የፍሬ ወቅት በመሆኑ እመቤታችን በአበባ ጌታን በፍሬ እየተመሰሉ ጌታችን በአምልኮት እመቤታችን በፈጣሪ እናትነቷ በተለየ ምስጋና ይመሰገናሉ ፡፡

በዚህ በወርኃ ጽጌ [ በዘመነ ጽጌ ] የሚጾሙ ክርስቲያኖች ሲኖሩ ጾሙን መንፈሳውያን ሰዎች ሳይታዘዙ በራሳቸው ፈቃድ የሚጾሙት ጾም በመሆኑ [የፈቃድ] የትሩፋት ጾም ይባላል፡፡ በቀኖና ቤተክርስቲያን ከታዘዙት ከ ፯ [ 7 ] ቱ አጽዋማት ውጪ የሆነ ትርፍ ጾም ማለት ነው፡፡ ከታዘዘው አትርፎ የጾመ ሰው የመጾሙን ዋጋ ያገኛል፡፡ ብዙ መንፈሳዊ ሥራ የሰራ ሰው ብዙ ክብር እንደሚያገኝ መጽሐፍ ይናገራልና፡፡ ‘’እጅግ ወዳለችና ብዙ ያለው ሐጢአትዋ ተሰርዮላታል፡፡ ጥቂት ግን የሚሰረይለት ጥቂት ይወዳል’’ [ሉቃ.፯፥፵፯] እንዲል፡፡

የጽጌን ጾም የሚጾሙ ሰዎች እመቤታችን ከልጇ ጋር በስደት የተቀበለችውን መከራና የደረሰባትን ሀዘን እየሰቡ በክብርም ከእመቤታችን ጋር ይተባበራሉ፡፡ ከእመቤታችን ጸጋንና በረከትን ያገኛሉ፡፡

ነገር ግን የጽጌን ጾም የሚጾሙ ሰዎች ለመመጻደቅ መጾም የለባቸውም፡፡ የማይጾሙ ሰዎችንም መንቀፍና መክሰስ የለባቸውም፡፡ የጽጌ ጾም እንዲጾም በቀኖና ቤተክርስቲያን ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ ተደርጎ ስላልተወሰነ የማይጾሙ ሰዎች ሕገ ጾምን እንዳፈረሱ አድርጎ መውሰድ ስሕተት ነው፡፡ ይልቁንም የሚጾሙ ሰዎች ቢችሉ መጾማቸው እንዳይታወቅባቸው ቢያደርጉ የተሻለ ነው፡፡ "ስትጾሙ እንደግብዞች አትጠውልጉ" [ማቴ.፮፥፲፮] የተባለው ለዚህ ዓይነቱ ጾም ነው፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፡ ወለወላዲቱ ድንግል ፡ ወለመስቀሉ ክቡር !

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]


🕊                        💖                       🕊
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (♱ ባሕራን ♱)
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (♱ ባሕራን ♱)
🕊                        💖                       🕊   

  [       🕊  አዘክሪ ድንግል   🕊       ]

    ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

🌼                        


❝ አዘክሪ ድንግል ንግደቶ ዘምስሌኪ እንዘ ትጐይዪ ምስሌሁ እምሀገር ለሀገር በመዋዕለ ሄሮድስ ንጉሥ ፤ አዘክሪ ድንግል ረኀበ ወጽምዐ ምንዳቤ ወሐዘነ ወኲሎ ዐጸባ ዘበጽሐኪ ምስሌሁ… ❞


[ ድንግል ሆይ ፦ ርጉም በኾነ በሄሮድስ ዘመን ከርሱ [ ከልጅሽ ] ጋራ ካገር ወደ አገር ስትሸሺ ካንቺ ጋር መሰደዱን አሳስቢ ፤ ድንግል ሆይ ረኀቡና ጥሙን ፣ ችግሩንና ጒዳቱን ከርሱ ጋራ የደረሰብሽን ጸዋትወ መከራ ኹሉ አሳስቢ ፤ ድንግል ሆይ ከዐይኖችሽ የፈሰሰውንና በተወደደ ልጅሽ ፊት የወረደውን መሪር እንባ አሳስቢ ፤ ጥፋትን ያይደለ ይቅርታን አሳስቢ መዐትን ያይደለ ምሕረትን አሳስቢ ፤ ለጻድቃን ያይደለ ለኃጥኣን አሳስቢ ፤ ለንጹሓን ያይደለ ለተዳደፉት አሳስቢ ]
                          
[  🕊 አባ ሕርያቆስ 🕊   ]


🕊                        💖                       🕊
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (ተአምኆ ቅዱሳን)
🌹 "በስመ አብ ወወልደ  ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። 🌹

           🌹 #መስከረም ፳፮ (26) ቀን።

🌹 እንኳን #ለመላእክት_አለቃ_ለቅዱስ_ገብርኤል ወደ በራክዩ ልጅ ወደ #ቅዱስ_ዘካርያስ_ለተላከበት #መጥምቀ_መለኮትን ከእርሱ ስለ መወለዱ ለአበሰረበት፤ ( #ለመጥምቀ_መለኮት #ለቅዱስ_ዮሐንስ_ለጽንሰት_በዓል)ና ለሰማዕቱ #ለቅዱስ_ዮስጦስ_ልጅ_ለቅዱስ_አቦሊ ለሥጋው ፍልሰት በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከዐሥር_ሽህ_ሰማዕታት#ከቅድስት_አጋታ_ከበርባራ_ከዮልያና#ከአባት_ጊዮርጊስም_ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

                               
🌹 #የየመላእት_አለቃ_ቅዱስ_ገብርኤል #ለቅዱስ_ዘካርያስ_የመጥምቀ_መለኮትን_የቅዱስ_ዮሐንስ_መጸነስ_እዳበሰረው፦ ስሙ የተመሰገነ እግዚአብሔር ልጅን ይሰጠው ዘንድ አስቀድሞ ሁል ጊዜ በመጸለይ ወደ እግዚአብሔር ይማልድ ነበር። ልጅ ያልወለደውን እግዚአብሔር ብዙ ተባዙ ምድርን ምሉዋት ያለውን በረከት ያጣ ነው በማለት እስራኤል ይገዳደሩት ነበርና።

🌹 ልመናውንም ሰማ በቤተ መቅደስም ቁሞ ዕጣንን ሲያሳርግ መልአኩን ላከለት በከበረ ወንጌልም እንደተባለ መንገዱን ይጠርግ ዘንድ በንጉሥ ክርስቶስ ፊት እንደሚሔድ የተነገረለት ታላቅ ነቢይ ዮሐንስ ከእርሱ መወለዱን አበሠረው።

🌹 ዘካርያስም የሰውነቱን መድከም የመውለጃውም ዘመን እንዳለፈና ፈጽሞ እንዳረጅ የሚስቱም እንዲሁ ዘመኗ እንዳለፈና ፈጽማ እንዳረጀች መካንም እንደሆነች ያውቃልና ስለዚህ ይህ ነገር እንዴት ይሆንልኛል "እኔ ያረጀሁ ሽማግሌ ነኝ ሚስቴም እንዲሁ ዘመኗ አልፎ መካን ሁናለች" ብሎ የእግዚአብሔርን መልአክ ተከራከረው።

🌹 መልአኩም "እኔ ይህን ልነግርህ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወዳንተ ተልኬ ነበር ልትጠራጠር ባልተገባህም ነበር አሁንም ይህ በጊዜው እስቲፈጸም ዲዳ ሁነህ መናገር ይሳንሃል" ብሎ ገሠጸው። ዘካርያስም የወልደ እግዚአብሔርን መንገድ የሚጠርግ ዮሐንስ እስከሚወለድበት ጊዜ ድረስ ዲዳ ሆነ።

🌹 በሚገረዝበትም ቀን የሕፃኑን አባት ዘካርያስን የሕፃኑን ስም ምን ብለው እንደሚሰይሙት ጠየቁት እርሱም ብራና ለምኖ "ስሙ ዮሐንስ ነው" ብሎ ጻፈ በዚያም ጊዜ አንደበቱ ተፈትቶ እግዚአብሔርን አመሰገነው። ስለ ልጁ ዮሐንስም እርሱ የልዑል ነቢይ እንዲባል መንገዱንም ይጠርግ ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት እንደሚሔድ ትንቢት ተናገረ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ዘካርያስና በቅድስት ኤልሳቤጥ በልጃቸው በቅዱስ ዮሐንስ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

                            
🌹 "#ሰላም_ለፅንሰትከ_በሠሌዳ_ከርሣ_ዘተገልፈ። ለኤልሳቤጥ እምከ እምድኅረ ወርኃ ኀለፈ። ዮሐንስ መልአክ እንተ ትኴንን አእላፈ። ከመ እፈጽም ዘወጠንኩ ስብሐቲከ ትሩፈ። በውስተ ዕዝንየ አልኆስስ መጽሐፈ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የመስከረም_26

                             


@sigewe

https://www.tg-me.com/joinchat-AAAAAFGQ22bI0Ij80hYpFA

https://www.facebook.com/profile.php?id=100063896616886

https://www.facebook.com/profile.php?id=61552828743736&mibextid=ZbWKwL
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (ተአምኆ ቅዱሳን)
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (ተአምኆ ቅዱሳን)
🌹 "በስመ አብ ወወልደ  ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። 🌹

           🌹 #መስከረም ፳፮ (26) ቀን።

🌹 እንኳን #ለእናታችን_ለእመቤታች_ለቅድስት_ድንግል_ማርያም ለልጇ ለወዳጇ ለክብር ባለቤት ለጌታችን ለመድኃኒታችን ##ለኢየሱስ_ክርስቶስ ለስደታቸው መታሰቢያ #ለፈቃድ_ጾም_ለጽጌ ጾም (ለዘመነ ጽጌ) እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።

                           
🌹 "#አዘክሪ_ድንግል_ንግደቶ_ዘምስሌኪ እንዘ ትጐይዪ ምስለ እምሀገር ለሀገር በመዋዕለ ሄሮድስ ርጉም። #አዘክሪ_ድንግል_አንብዐ_መሪረ ዘውኅዘ እምአዕንትኪ ወወረደ ዲበ ገጸ ፍቁር ወልድኪ። #አዘክሪ_ድንግል_ረኃበ_ወጽምዐ_ምንዳቤ_ወኀዘን ወኵሎ ዐፀባ ዘበጽሐኪ ምስሌሁ"። ትርጉም፦ #ድንግል_ሆይ_ርጉም_በሆነ_በሄሮድስ ዘመን ከእርሱ (ልጅሽ) ጋር ከሀገር ወደ ሀገር ስትሸሺ ከአንቺ ጋር መሰደዱን አሳስቢ። #ድንግል_ሆይ_ከዓይኖችሽ የፈሰሰውንና በተወደደ ልጅሽ ፊት የወረደውን መሪር ዕንባ አሳስቢ፡፡ #ድንግል_ሆይ_ርኃቡንና_ጥሙን ችግሩንና ኀዘኑን ከእርሱ ጋር በመሆን የደረሰብሽን ጭንቅ (መከራ) ሁሉ አሳስቢ"። #ሊቁ_አባ_ሕርያቆስ_በቅዳሴ_ማርያም_በቁጥር_167_169_ላይ

                            
🌹 #የዘመነ_ስደት_መታሰቢያ ለምን በዚህ ጊዜ ሆነ?
#ከመስከረም_26_እስከ_ህዳር_5

🌹  እመቤታችን ከልጅዋ ጋር ስደትን የጀመረችው ጥር 3 ነው፥ አገረ ግብጽ የገባችው ግንቦት 24 ነው፥ በግብፅ እና በኢትዮጵያ ሦስት ዓመት ከስድስት ወር ከቆዩ በኋላ ስደቱ አብቅቶ ተመለሱ ብሎ መልአኩ ሲነግራቸው ካሉበት ተነስተው ቁስቋም ከተባለች ቦታ ኅዳር 6 ደርሰዋል ።

🌹#የስደት_መታሰቢያ_ለምን_በመነሻው_ጥር_3 አልሆነም?

ይህ ወቅት ዘመነ አስተርእዮ የደስታ ጊዜ ነው ታኅሣሥ 29 ልደቱን ጥር 11 ጥምቀቱን የምናከብርበትና በልደቱ እና በጥምቀቱ የተደረገልንን እያሰብን ደስ የምንሰኝበት ጊዜ በመሆኑ ለስደት መታሰቢያ ለማድረግ አይመችም።

🌹 #ግንቦት_24_አገረ_ግብፅ_የገባችበትን ይዘን ለምን ስደትን አናስብም?

🌹 ግንቦት 24 በዓለ ሃምሳን የምናከብርበት እንደመሆኑ በዚህ ወቅት ጌታችን በትንሳኤው የሰጠንን ነጻነት የምናስብብት ደስ የምንሰኝበት ጊዜ ስለሆነ መስገድ መጾም ስለማይፈቀድ የስደት መታሰቢያ ለማድረግ አይመችም።

🌹 ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 5 ዕፅዋት አበባን ፍሬን የሚያሳዩበት ወቅት ነው።

🌹 ወቅቱ ለምሳሌ የተመቸ ነውና።

"ትወጽእ በትረ እምሥርወ እሤይ ወየዓርግ ጽጌ እምኔሃ"  ኢሳ 11፥1 እንዲል የዕሤይ የዘር ግንድ ከተባለች ከእመቤታች ጽጌ ጸኣዳ ወቀይህ የተባለ የፍጥረት ሁሉ ጌጥ ጌታችን የተገኘ ነውና በዚህ መስሎ ለማስተማር የሚያመች ወቅት ነውና። በተጨማሪም ጽጌ በእመቤታች ፍሬ በጌታችን ይመሰላል።

🌹 #አንድም፦ ተመለሰ ከማለት በፊት ተሰደደ ማለት ይቀድማል።

🌹 በዓመት ውስጥ ያሉት የወራት ቅድመ ተከተል ኅዳር 6 ከጥር 3 እና ከግንቦት 24 ይቀድማል። ኅዳር ላይ ከስደት ተመለሰ ብለን ካከበርን በኋላ ጥር ተሰደደ ግንቦት ግብፅ ገባ ብንል አመቺ አይደለም።

ስለዚህ ከጥር 3 ወይም ከግንቦት 24 ይልቅ ኅዳር 6 መታሰቢያ ለማድረግ አመቺ በመሆኑ ቤተክርስቲያን በዚህ ወቅት የስደቱን መታሰቢያ ታደርጋለች።

🌹 በቅዱስ ያሬድ አባባል ስደት #ከመስከረም_26_እስከ_ጥቅምት_20 ሲነገር፤ #ከጥቅምት_21_እስከ_ኅዳር_6 ድረስ ሚጠት (መመለሳቸው) ይነገራል። ይኼውም ተመየጢ ተመየጢ ሰላመ ሰጣዊት የሚለው ሰላም እንዲቀርብ በማኅሌት ስለተወሰነ ነው። ምንጭ፦ አምኃ ሥላሴ መኩሪያ ተስፋዬ።

🌹 ጾሙ ከአገራችን ኢትዮጵያ ጦርነትን የሚያጠፋ እና ሰላም፣ ፍቅርን አንድነትንና መተሳሰብ የሚያመጣ ያድርግልን። መልካም ጾም ለሁላችንም ይሁንልን።

@sigewe

https://www.tg-me.com/joinchat-AAAAAFGQ22bI0Ij80hYpFA

https://www.facebook.com/profile.php?id=100063896616886

https://www.facebook.com/profile.php?id=61552828743736&mibextid=ZbWKwL
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (ተአምኆ ቅዱሳን)
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (♱ ባሕራን ♱)
🕊

[  † እንኳን ለቅዱሳኑ ኤዎስጣቴዎስ: አንጢላርዮስ: ጤቅላ እና አባ ዮሐንስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን። †  ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †


🕊 † ቅዱስ ኤዎስጣቴዎስና ቤተሰቡ †  🕊

† ቅዱስ ኤዎስጣቴዎስ በቀድሞዋ ሮሜ ግዛት ውስጥ የጦር አለቃ የከተማዋ መኮንን እና እጅግ ባለጸጋ የነበረ ሰው ነው:: ግን በእምነቱ አረማዊ: በስሙም 'ቂዶስ' ተብሎ የሚጠራ ነበር:: ምክንያቱ ባይገባውም እጅግ ቅን ደግና ለምጽዋት የሚፋጠን ነበር::

እግዚአብሔር ታዲያ ይህን ሰው ወደ ቀናው ጐዳና ሊመራው ወደደና ተገለጠለት:: ቂዶስ ለአደን ወጥቶ ዋሊያ ሲያድን መድኃኒታችን በዋሊያው ራስ ላይ የብርሃን መስቀልን ገልጦ ተነጋገረው::

ክርስቲያን እንዲሆንና መከራንም እንዲታገሥ አዘዘው:: ቂዶስም ወደ ቤቱ ተመልሶ ለሚስቱና ለ፪ ልጆቹ የሆነውን ነገራቸው:: ክርስትናን ተምረው ሲጠመቁ አበው ቂዶስን 'ኤዎስጣቴዎስ' አሉት::

ከዚህ በሁዋላ ክርስቶስን እያመለኩ ቆይተው ረሃብ በሃገሪቱ መጣ:: ቅዱሱ ምንም መኮንንና ሃብታም ቢሆንም ገንዘቡ በምጽዋት በማለቁ ባሮቹ ተበትነው ደሃ ሆነ:: የሚበላውንም አጣ:: ከሥጋዊ ሥልጣኑም ተሻረ:: እርሱ ግን ይህንን ስለ ክርስቶስ ፍቅር ታገሠ::

ቅዱስ ኤዎስጣቴዎስ ረሃቡ ከአቅሙ በላይ ሲሆንበት ሚስቱንና ፪ ልጆቹን ይዞ ስደት ተነሳ:: ለጉዞ በተሳፈረበት መርከብ የሚከፍለው ገንዘብ ስላልነበረው ሚስቱን ቀሙት:: ልጆቹን ይዞ እያለቀሰ ከሌላ ወንዝ ደረሰ::

እንዳይሳፈር መርከበኞቹ ልጆቹን ሊቀሙት ስለሆነ ለመዋኘት ወሰነ:: አንዱን ልጁን ተሸክሞ አሻግሮት ሲመለስ ትቶት የሔደውን ልጁን አንበሳ ወስዶት አገኘው:: እያለቀሰና እየቸኮለ ወደ ፪ኛው ቢመለስ ደግሞ ይህኛውንም ተኩላ ወስዶት ነበር::

ቅዱስ ኤዎስጣቴዎስ አንጀቱ በሃዘን ተቃጠለ:: በግንባሩ መሬት ላይ ተደፍቶ መራራ ለቅሶን አለቀሰ:: ነገር ግን ኢዮባዊ ሰው ነውና "እግዚአብሔር ሰጠ: እርሱም ነሣ" ብሎ በእንባ ተጉዋዘ:: በአንዲት ሃገርም ባርነት ተቀጥሮ ፈጣሪውን ሲያመሰግን ኖረ::

ከብዙ ዓመታት በሁዋላ የረሃቡ ዘመን አልፎ የቅዱሱ ወዳጅ የነበረ ሰው በሮም ላይ በመንገሱ ወታደሮችን "ወዳጄን ኤዎስጣቴዎስን ፈልጋችሁ አምጡ" ብሎ ላካቸው:: ከአድካሚ ፍለጋ በሁዋላ ያ ደግ ጌታቸው በባርነት ተቀጥሮ: ተጐሳቁሎ አገኙት::

ፈጥነው ወደ ሮም ከተማ ወስደው በቀደመ ክብሩ ላይ አኖሩት:: እርሱ ግን ሃዘንተኛ ነበር:: ከቀናት በሁዋላም አዳዲስ ወታደሮችን ከተለያየ ቦታ መለመለ:: ከእነዚያም መካከል መልካም የሆኑትን ፪ቱን አለቆች አደረጋቸው:: ሁለቱ ደግ ወጣቶችም በጣም ይዋደዱ ነበር::

አንድ ቀን እኒህ ፪ ወጣቶች ወይን ሊገዙ ሔደው ጠባቂዋን 'ስጭን' አሏት:: ሰጥታቸው እዚያው ያወራሉ:: አንደኛው "ታሪኬን ልንገርህ" ይለዋል:: "እሺ" ሲለው "እኔ ወላጆች የሉኝም:: ሕጻን እያለሁ በሃገራችን ረሃብ መጥቶ: ሃብታችን አልቆ ስንሰደድ እናታችንን መርከበኛ ወሰዳት:: አባቴ ወንድሜን ሲያሻግረው እኔን አንበሳ ወስዶ ከአንድ መንደር ጣለኝ" አለው::

ባልንጀራው ገርሞት "ታሪካችን ተመሳሳይ ነው:: እኔም እንዳንተ ሆኜ: አባቴ ሲያሻግረኝ ተኩላ ወስዶ አንድ መንደር ውስጥ ጣለኝ" አለው:: ይህንን ትሰማ የነበረችው ወይን ጠባቂ "ልጆቼ!" ብላ ጮሃ አለቀሰችና ደነገጡ:: እርሷም ቀርባ አቅፋቸው እያለቀሰች ነገሩን ሁሉ አስታወሰቻቸው::

ይህን ጊዜ ቅዱስ ኤዎስጣቴዎስ ሰምቶ ደረሰ:: ከረጅም ዓመታት በሁዋላ ሚስቱ አትክልት ጠባቂ ሁና ማንም ሳይነካት: ፪ ልጆቹንም አገኘ:: እያለቀሱ ተቃቀፉ:: እግዚአብሔርንም ፈጽመው አመሰገኑት:: የሰማ ሁሉ "ዕጹብ! ዕጹብ!" አለ::
[እኛ የምናመልከው ጌታ እንዲህ ነው:: ክብር ለእርሱ: ለድንግል እናቱና ለወዳጆቹ]

ቅዱስ ኤዎስጣቴዎስና ቤተሰቡ በቀሪ ዘመናቸው ቤተ ክርስቲያን አንጸው በምጽዋት ኑረዋል:: በመጨረሻም ዘመነ ሰማዕታት መጥቶ "ክርስቶስን አንክድም" በማለታቸው ብዙ ተሰቃይተው ፬ቱም በዚህች ቀን ሰማዕት ሆነዋል::


🕊  †  ቅዱስ አንጢላርዮስ  †   🕊

ይህ ቅዱስ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ እጅግ የታወቀ ነው:: በቀደመ ሕይወቱ "ሊቀ መጸብሐን-የቀራጮች አለቃ" ይሉታል:: እጅግ ኃጢአተኛና ጨካኝ ሰው ነበር::

አንድ ቀን ግን አንድ የኔ ቢጤ ነዳይ ከመሰሎቹ ጋር ተወራርዶ " በእንተ ማርያም" ብሎ ቢለምነው በደረቅ ዳቦ ራሱን ገመሰው:: በሌሊትም ራዕይ አጋንንት ነፍሱን ሲናጠቁዋት መላእክት ደግሞ በዛች ደረቅ ዳቦ አመካኝተው ሊያድኑት ሲሞክሩ አየ::

በዚያች ቅጽበትም ፍጹም ተለወጠ:: መጀመሪያ ሃብት ንብረቱን በምጽዋት ጨረሰ:: ቀጥሎ የሚመጸውተው ቢያጣ ነዳያንን "ሽጣችሁ ተካፈሉኝ" አላቸውና ሸጡት:: በባርነት በተሸጠበት ሃገርም በጾምና በጸሎት ተጋደለ:: እረኛ ሲያደርጉትም በደረቅ በርሃ ላይ ውሃ እያፈለቀ: ለምለም ሳር እያበቀለ ይመግባቸው ነበር:: ዘወትርም መልአክ ያጽናናው ነበር::

በሁዋላ ግን ማን መሆኑ ሲታወቅበት ሸሸ:: በመንገድም የከተማዋ ዘበኛ መስማትና መናገር አይችልምና እፍ ቢልበት ከቅዱሱ አፍ እንደ እሳት ያለ ነገር ወጥቶ ቢነካው ዳነ:: ቅዱስ አንጢላርዮስም ቀሪ ዘመኑን በበርሃ ሲጋደል ኑሮ በዚህች ቀን ዐርፏል::


🕊 † ቅድስት ጤቅላ ሐዋርያዊት † 🕊

ይህቺ ቅድስት እናት በመጀመሪያው መቶ ክ/ዘመን ከነበሩ ቅዱሳት አንስት አንዷ ናት:: ቅዱስ ዻውሎስ በእስያ የወንጌል ጉዞ ሲያደርግ ይህችን ቅድስት መቄዶንያ ላይ አግኝቷል:: ቅድስት ጤቅላ ምንም ወላጆቿ አረማውያን ቢሆኑ: እርሷ እስከ ፫ ቀናት ድረስ ያለ ምንም ምግብ ቃለ እግዚአብሔርን ትሰማ ነበር::

የብርሃነ ዓለም ቅዱስ ዻውሎስ ተከታይ ሁና በእስያ ወንጌልን ሰብካለች:: በብዙ ስቃይ ውስጥ ስታልፍም በኃይለ እግዚአብሔር እሳትን አጥፍታለች:: አንበሶችም ሰግደውላታል:: ቅድስት ጤቅላ ፈጣሪዋን አስደስታ በዚህ ቀን ዐርፋለች::


🕊 † አባ ዮሐንስ ዘደብረ ጽጌ † 🕊

እኒህ ኢትዮዽያዊ ጻድቅ በገዳም ውስጥ ሲጋደሉ ሰውነታቸው አለቀ:: ቅዱሱ ከማረፉቸው በፊት የገዳሙ አባቶች ውሃ በጋን ሞልተው በላያቸው ላይ ቢያፈሱ አንድም ጠብታ ወደ መሬት ሳይወርድ ቀረ:: አካላቸው ከመድረቁ የተነሳ ጠጥቶት ነበርና:: ዛሬ ዕለተ ዕረፍታቸው ናት::

አምላከ ኤዎስጣቴዎስ ትእግስቱን:
አምላከ አንጢላርዮስ ምጽዋቱን:
አምላከ ቅድስት ጤቅላ አገልግሎቷን:
አምላከ አባ ዮሐንስ ጽናታቸውን ያሳድርብን:: የሁሉም በረከታቸው ይብዛልን::

[  † መስከረም ፳፯ [ 27 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት   ]

፩. ቅዱስ ኤዎስጣቴዎስና ቤተሰቡ [ሰማዕታት]
፪. ቅዱስ አንጢላርዮስ ጻድቅ
፫. ቅድስት ጤቅላ ሐዋርያዊት
፬. አባ ዮሐንስ ዘደብረ ጽጌ

[    † ወርኀዊ በዓላት     ]

፩. የጌታችንና አምላካችን መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በዓለ ስቅለት
፪. አቡነ መብዐ ፅዮን ጻድቅ
፫. ቅዱስ መቃርስ [የመነኮሳት ሁሉ አለቃ]
፬. ቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ
፭. ቅዱስ ገላውዴዎስ ሰማዕት [ንጉሠ ኢትዮዽያ]
፮. ቅዱስ ቢፋሞን ጻድቅና ሰማዕት
፯. ማር ቅዱስ ፊቅጦር ሰማዕት
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (♱ ባሕራን ♱)
" ለቅዱሳን ስለሚሆነው አገልግሎት ልጽፍላችሁ አያስፈልግምና:: በጐ ፈቃዳችሁን አውቄአለሁና:: ስለዚህም ' አካይያ ከአምና ጀምሮ ተዘጋጅቷል' ብየ ለመቄዶንያ ሰዎች በእናንተ እመካለሁ:: ቅንዓታችሁም የሚበዙቱን አነሣሥቷል:: " [፪ቆሮ.፱፥፩]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
Audio
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (♱ ባሕራን ♱)
Forwarded from M.A
"ፀሐይን የምትለብሽ የብርሃን ልጅ ቅድስት ድንግል ማርያም ከክፉ ከሄሮድስ ዘንድ ልጅሽን ባሸሸሽ ጊዜ የደረሰብሽን ችግሮች ጨረቃን የሚጫሙ እግሮችሽ በመንገድ ብዛትና በአሸዋ ግለት እንደ ጎበጎቡ ሲሰማ ሰው ይቅርና ድንጋዩም ባለቀሰ ነበር፡፡"

ሰቆቃወ ድንግል
2024/11/15 18:30:57
Back to Top
HTML Embed Code: