Forwarded from ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
የዓለም ሁሉ መድኃኒት የምትሆን ብላቴና እግሯ የተመላለሰበቱን ምድር እስም ዘንድ ማን በከፈለኝ፡፡ ይቅርታን የምታሰጥ ብላቴና ጥላዋ ይነካኝ ዘንድ ማን በከፈለኝ፡፡ የብርሃን ልጅ ወደ ሄደችበት እከተላት ዘንድ ማን በከፈለኝ የእግሯንም ጫማ እሸከም ዘንድ ማን በከፈለኝ፡፡
አሁንም ያን ጊዜ በዕብራይስጥ ማሪሃም ከተባለች ከተመረጠች ድንግል ማርያም ጋራ ያን ጊዜ ካሉት አላንስም ሀሳቤን ከዚያ እንዳለሁ አድርጌ አለሁና፡፡ በስጋ አልነበርሁም በመንፈስ ግን አለሁ፡፡ ባነዋወር አልነበርሁም በሃይማኖት ግን አለሁ በገጽ አልነበርሁም በማመን ግን አለሁ፡፡ ሳልኖር እራሴን እንዳለሁ ያረደረግሁ እኔ የተመሰገንሁ ነኝ ጌታችን በወንጌል እንደተናገረ እንዲህ ሲል ሳያዩኝ የሚያምኑብኝ ግን የተመሰገኑ ናቸው፡፡
እኔ ባሪያህ ስለሃይማኖቴ የተመሰገንሁ ነኝ፡፡ ስለ ዕውነቴ አይደለም ስለ መረዳቴም የተመሰገንሁ ነኝ፡፡ ስለ ንጽህናዬም አይደለም በእግዚአብሔር ስም ስለ አመንኩ የተመሰገንሁ ነኝ፡፡ በናቱም ጸሎት ስለ አመንሁ ንዑድ ክቡር ነኝ፡፡
(አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በአርጋኖን)

Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (♱ ባሕራን ♱)
🕊
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †
[ † መስከረም ፳፰ [ 28 ] † ]
🕊 † ቅዱሳን አባዲርና እህቱ ኢራኢ † 🕊
† በ፫ ኛው መቶ ክ/ዘመን የሮም መንግስት ዓለምን የሚያስተዳድረው በሁለት ከተሞች: ማለትም በራሷ በሮምና በአንጾኪያ ነበር:: የወቅቱ ንጉሥ ኑማርያኖስ ሲሆን የቤተ መንግስቱ ልዑላንና የጦር አለቆች ቅዱሳኑ :- ፋሲለደስ: ገላውዴዎስ: ፊቅጦር: መቃርስ: አባዲር: ቴዎድሮስ [ሦስቱም] አውሳብዮስ: ዮስጦስ: አቦሊ: ሌሎቹም ነበሩ::
ሴቶቹ ደግሞ ቅዱሳቱ:- ማርታ: ሶፍያ: ኢራኢ: ታኡክልያ: ሌሎቹም ነበሩ:: ለእነዚህ ሁሉ የበላይ ደግሞ ቅዱስ ፋሲለደስ ነበር:: ወቅቱ ከፋርስ: ከቁዝና ከበርበር ጦርነት የሚበዛበት ነበርና ባጋጣሚ ንጉሡ ኑማርያኖስ በሰልፍ መካከል ተመትቶ ወደቀ/ሞተ::
የሮም መንግስትም ባዶ ሆነች:: ዙፋኑን መያዝ ለቅዱስ ፋሲለደስም ሆነ ለሌሎቹ ቅዱሳን ቀላል ነበር:: ግን እነሱ ዝም ብለው ጠላትን ለመዋጋት ወጡ::
በዘመኑ ደግሞ በግብጽ የፍየል እረኛ የነበረና ከልጅነቱ ሰይጣን የሚያናግረው አንድ አግሪዻዳ የሚሉት ጉልበተኛ ሰው ነበር:: ንጉሡ ከወለዳቸው ልጆች ሁለቱ ሴቶች ክፉዎች ነበሩና ትንሿ አግሪዻዳን ማንም በሌለበት አንግሣ ጠበቀቻቸው:: ስሙንም ዲዮቅልጢያኖስ አለችው::
በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ከሰይጣን ቀጥሎ እንደዚህ የከፋ ስም የለም:: የዓለም ክርስቲያኖችን የጨፈጨፈ ሰው ነው:: ትልቋ ደግሞ የትንሿን አይታ መክስምያኖስ የሚባል አውሬ አግብታ አነገሠችው:: ዓለምም በእነዚህ ጨካኝ ሰዎች እጅ ወደቀች::
ሠራዊቱ ሁሉ በሚሊየን ይቆጠራሉ:: የተደረገውን ሲያዩ ተበሳጩ:: ይህንን የተመለከተው ቅዱሱ ፋሲለደስ ግን ልዑላኑንና አለቆችን ሰብስቦ:- "ይህ ዓለም ከነ ክብሩ ጠፊ ነው:: ስለዚህ የተሻለውን የክርስቶስን መንግስት እንምረጥ" አላቸው:: ሁሉም እንደ አንድ ልብ መካሪ ደስ ተሰኝተው ምድራዊ ክብራቸውን ሊተው ወሰኑ::
ቀጥለውም በአንድ ቤት ተሰብስበው ይጾሙ: ይጸልዩ ገቡ:: ወደ ውጪ የሚወጡት ለምጽዋት ብቻ ነበር:: ቅዱሳኑ አባዲርና ኢራኢም ከእነዚህ መካከል በመሆናቸው ተጋድሏቸውን ቀጠሉ:: በተለይ ቅዱስ አባዲር በሌሊት በመካነ ጸሎቱ ሲጸልይ ያድርና በቀን ነዳያንን ይጐበኛል::
አመሻሽ ላይ ደግሞ ልብሱን ለውጦ ወደ እሥር ቤት ይሔዳል:: እሱ የአንጾኪያ ሠራዊት አለቃ: ኃያል የጦር መሪ ነውና ሁሉ ይወደውና ያከብረው ነበር:: በዚህም ምክንያት የእሥር ቤት ዘበኞች ምንም ከዲዮቅልጢያኖስ ከባድ ትዕዛዝ ቢኖርባቸውም ለቅዱሱ ግን ይከፍቱለት ነበር::
እርሱም ወደ እሥር ቤት ገብቶ ቁስላቸውን ጠርጐ: እግራቸውን አጥቦ: ለረሃባቸው መደገፊያ የሚሆን ማዕድም አጉርሷቸው ይወጣ ነበር:: በእንዲህ ያለ ግብር ሳለ ስለ ክርስቶስ የሚሰዋበት ጊዜ ደረሰ::
አንድ ቀን በመካነ ጸሎቱ ለምስጋና ሲተጋ ክብር ይግባውና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገለጠለት:: "ስምህን ለዘለዓለም አከብረዋለሁ:: በሰማያዊት ርስቴም አነግሥሃለሁና ከእህትህ ኢራኢ ጋር ወደ ምድረ ግብጽ ወርዳችሁ መስክሩ" ብሎት: ለእሷም በተመሳሳይ "ወንድምሽ የሚያዝሽን ሥሪ" ብሏት መድኃኒታችን ዐረገ::
ከዚያች ቀን ጀምሮ ቅዱስ አባዲርና እህቱ ኢራኢ ወደ ግብጽ የሚወርዱበትን መንገድ ይፈልጉ ነበር:: እናታቸው ግን (የቅዱስ ፋሲለደስ እህት ናት) ነገሩን ስትሰማ አለቀሰችባቸው:: "ልጆቼ አትሙቱብኝ: ዲዮቅልጢያኖስንም አትናገሩት" ስትል አማለቻቸው::
ከጥቂት ቀናት በኋላም ቅዱሱ ከእህቱ ጋር ከሶርያ ጠፍቶ ግብጽ ገቡ:: በዚያ ግን ፈተና ገጠመው:: በየመንገዱ የሚያየው ሕዝቡና ሠራዊት ሁሉ "ጌታችን አባዲር" እያለ ይሰግድለት ገባ:: ቀደም ሲል እንዳልነው እርሱ ኃያል የጦር መሪ: የሠራዊቱም አለቃ ነውና::
ቅዱሱ ግን ወደ ክርስቶስ ሊሔድ ናፍቋልና ሠራዊቱን እና ሕዝቡን:- "የሚገርማችሁ ሁሉም ሰው እንዲህ ይለኛል:: ግን'ኮ እኔ አንድ ተራ ምስኪን ክርስቲያን እንጂ የምትሉት ሰው አይደለሁም" ብሎ አታለላቸው::
ቀጥሎ በክርስትናው ተከሶ ከእህቱ ጋር ለፍርድ ቀረበና ስቃይ ታዘዘባቸው:: ለሰው ዐይን የሚከብዱ ብዙ ስቃዮችን ካሳለፉ በኋላም ሞት ተፈረደባቸው:: ነገር ግን አንገታቸው ከመሰየፉ በፊት መኮንኑ አርያኖስ ትክ ብሎ ሲያየው ተጠራጥሮ "ማንነትህን እንድትነግረኝ በአምላክህ አምየሃለሁ" አለው::
ቅዱስ አባዲርም መልሶ "አንተም ማንነቴን ካወቅክ በኋላ እኔን መግደል እንዳትተው ማልልኝ" አለው:: ማለለትም "እኔ አባዲር ነኝ" አለው:: በዚያች ቅጽበት አርያኖስ ከመደንገጡ የተነሳ መሬት ጠበበችው:: በፊቱ ተደፍቶ "ወዮልኝ! ጌታየን አባዲርን ያሰቃየሁ" እያለ አለቀሰ:: ነገር ግን ምሏልና በ300 ዓ/ም አካባቢ እያዘነ በዚህች ቀን ቅዱስ አባዲርንና እህቱን ኢራኢን አሰይፏቸዋል::
🕊 † ቅድስት ሶስና † 🕊
† ይህች እናት የነበረችው ቅ.ል.ክርስቶስ በ፭፻ [500] ዓመት አካባቢ ነው:: እሥራኤላውያን በናቡከደነጾር ተማርከው ፋርስ ባቢሎን ወርደው ሳሉ: የኬልቅዩስ ልጅ: የደጉ ኢዮአቄም ሚስት የሆነች እናት ናት::
ቅድስት ሶስና በስደት ሃገር እግዚአብሔርን የምታመልክ: ለባሏ የምትታመን: ለቤተሰቦቿም ኩራት የሆነች ወጣት: በዚያውም ላይ እጅግ የምታምር ነበረች:: በዘመኑ ሕግን እናውቃለን የሚሉ ፪ ረበናት ግን ከቅድስናዋ ሊያጐድሏት ይሹ ነበርና: አልሳካላችሁ ቢላቸው በሃሰት ከሰው በወገኖቿ ፊት ሞትን አስፈረዱባት::
በፍርድ ፊት ቁማ ሳለ እርሷ በፍጹም እንባ ወደ ፈጣሪዋ ትጸልይ ነበርና እግዚአብሔር ፍርዱን ላከ:: ሊገድሏት ሲወስዷት የኋላው ነቢዩ ቅዱስ ዳንኤል ያን ጊዜ ብላቴና ነበርና "እኔ ከዚህች የተባረከች ሴት ደም ንጹሕ ነኝ" ሲል ጮኸ::
ይህንን የሰሙ ዳኞችም የፍርድ ዙፋኑን ለቀቁለት:: ሁለቱን ረበናት ለየብቻቸው አድርጐ ዝሙትን ስትሠራ በየት ቦታ ላይ እንዳዩዋት ጠየቃቸው:: ጌታ ሲፈርድባቸው አንዱ በኮክ: ሌላኛው በሮማን ዛፍ ሥር አለ:: በዚህ ጊዜ ሕዝቡ እነዚህን ሃሰተኛ ረበናት [መምሕራን] ስለ እርሷ ፈንታ ወግረው ገደሏቸው:: ቅድስት ሶስና ግን ባለ ዘመኗ ሁሉ ፈጣሪዋን አገልግላ በዚህች ቀን ዐርፋለች::
† አምላከ ቅዱሳን ከክፉ ሰዎች ምክር: ከአጋንንትም ሴራ በቸርነቱ ይጠብቀን:: የወዳጆቹንም ጸጋ ክብራቸውን ያድለን::
🕊
[ † መስከረም ፳፰ [ 28 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅዱስ አባዲር ሰማዕት
፪. ቅድስት ኢራኢ እህቱ
፫. ቅድስት ሶስና እናታችን
፬. ቅዱስ ሉቃስ መነኮስ
፭. ቅዱስ ዻውፍርና
[ † ወርሐዊ በዓላት ]
፩. አምላካችን አማኑኤል
፪. አበው ቅዱሳን አብረሃም, ይስሐቅ, ያዕቆብ
፫. ቅዱስ እንድራኒቆስ ሚስቱ ቅድስት አትናስያ
፬. ቅድስት ዓመተ ክርስቶስ
፭. ቅዱስ ቴዎድሮስ ዘሮሜ ሰማዕት
† " ሶስናም ቃሏን አሰምታ ጮኸች:- 'ዘላለም ጸንተህ የምትኖር: የተሠወረውን የምታውቅ: የሚደረገውን ሁሉ ሳይደረግ የምታውቅ ፈጣሪ ሆይ! በሐሰት እንደ ጣሉኝ አንተታውቃለህ:: እነዚህ መመሕራንም ክፉ ነገርን ባደረጉብኝ ገንዘብ: የሠራሁት ኃጢአት ሳይኖር እነሆ እሞታለሁ' አለች:: እግዚአብሔርም ቃሏን ሰማት::" † [ሶስና.፩፥፵፩]
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖

[ † እንኳን ለድንግልና ሰማዕት አርሴማ ቅድስት ወዮሐንስ ወንጌላዊ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ። † ]
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †
🕊 † ቅድስት አርሴማ ድንግል † 🕊
† እናታችን ቅድስት አርሴማን በምን እንመስላታለን? እርሷ በአድማስ ላይ ተቀምጦ እንደሚያበራ እንቁ ናትና ክብሯ ብዙ ነው:: መድኃኒታችን ክርስቶስ በወንጌል እንዳለው "በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሠወር አይቻላትምና" የሰማዕቷ ሕይወት በፊታችን እንደ ብርሃን ተገልጦ ይታያል::
¤ ቅድስት አርሴማ እንደ ልጅ ወላጆቿን በመታዘዝ ደስ ያሰኘች ቡርክት ናት::
¤ ቅድስት አርሴማ ይሕ ቀረሽ የማይሏት ውብ ናት::
¤ ቅድስት አርሴማ ድንግል ናት::
¤ ቅድስት አርሴማ ባሕታዊት ጻድቅ ናት::
¤ ቅድስት አርሴማ ኃያል ሰማዕት ናት::
ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ :-
አበው በትውፊት እንደ ነገሩን ከሆነ ቅዱሱ ጐርጐርዮስ የታላቋ ሰማዕት ቅድስት አርሴማ ትልቅ ወንድም ነው:: በዜና ሰማዕታት ተጽፎ እንደሚገኘው በዚያ የመከራ ዘመን ቅዱስ ጐርጐርዮስ ሦስት ኃላፊነቶች ነበሩበት :-
፩. ቅድስት አርሴማን ጨምሮ ደናግሉን ማጽናት::
፪. ትምሕርተ ቤተ ክርስቲያንን በሚገባ ማጥናት::
፫. የሚመጣውን መከራ ለመቀበል ራሱን ማዘጋጀት::
ቅዱሱ ሦስቱንም ኃላፊነቶች በሚገባ በመወጣቱ ከራሱ አልፎ ለሌሎቹ አርአያ መሆን ቻለ:: ያቺን ንጽሕት አርበኛ ቅድስት አርሴማንም አጽንቶ የደናግሉ መሪ አደረጋት:: መከራው በጣም ገፍቶ እስከ መጣበት ጊዜ ድረስ በአንድ የደናግል ገዳም ውስጥ ሆነው ይጸልዩ: ይጾሙ: ገዳማዊ ሥራንም ይሠሩ ነበር::
ለዚህም ነው ቅድስት አርሴማና ቅዱስ ጐርጐርዮስ ጻድቃን የምንላቸው:: በኋላ ግን ማሕደረ ሰይጣን ዲዮቅልጢያኖስ በመልኳ ተማርኮ ቅድስት አርሴማን ካላገባሁ በማለቱ ቅዱስ ጐርጐርዮስ ድንግሏን አርሴማን ጨምሮ ፲፳፯ ክርስቲያኖችን ይዞ ወደ አርማንያ ተሰደደ::
በአርማንያም በአንድ ገዳም ውስጥ ተደብቀው በጾምና በጸሎት ለጥቂት ጊዜ ቆዩ: ነገር ግን ረሃብ ፈጃቸው:: የሚላስ የሚቀመስ ነገር በአካባቢው ባለ መኖሩ ቅዱስ ጐርጐርዮስ ወደ ከተማ ለመውጣት ተገደደ::
በዚያም በድርጣድስ ቤተ መንግስት ውስጥ ባርነት ተቀጠረ:: በሚያገኛት ገንዘብም ወገኖቹን ይረዳ ነበር:: መከራው ግን አለቀቃቸውም:: ርጉም ዲዮቅልጢያኖስ ቅዱሳኑ ወደ አርማንያ መሔዳቸውን ስለ ሰማ ይዞ እንዲልክለት ድርጣድስን ላከው::
ድርጣድስ ግን ቅድስት አርሴማን ባያት ጊዜ ከውበቷ የተነሳ መታገስ ባለመቻሉ "ካላገባሁሽ" አላት:: ድንግሊቱ ግን "እኔ የክርስቶስ ሙሽራ ነኝ: አይሆንም" አለችው:: ሊያስፈራራት ሞከረ:: ዐይኗ እያየ ደናግሉን ጨፈጨፋቸው::
አልሳካልህ ቢለው በአደባባይ በግድ ሊያገባት ቢሞክር እጁን ጠምዝዛ በሰው ሁሉ ፊት መሬት ላይ ጣለችው:: እጅግ ስላፈረ አስገረፋት: አሰቃያት: ዐይኗንም አወጣ:: በመጨረሻም አንገቷን አስቆርጦ ከሰማዕታቱ ጋር ተራራ ላይ ጣላት::
ከነገር ሁሉ በኋላ ድርጣድስና ባለሟሎቹ ለአደን በሔዱበት ርኩስ መንፈስ ወደ አውሬነት [እሪያነት] ቀየራቸው::
የንጉሡ እንስሳ [አውሬ] መሆን በአርማንያ ታላቅ ድንጋጤን ፈጠረ:: የንጉሡ እህት ስታለቅስ በራዕይ "ለእመ ኢያዕረግምዎ ለጐርጐርዮስ አልብክሙ ድኂን - ጐርጐርዮስን ከተቀበረበት ካላወጣችሁት አትድኑም" አላቸው:: ወዲያውም ቆፍረው አወጡት::
ቅዱሱ እንደ ወጣ ዕረፍትን አልፈለገም:: ለ፲፭ ዓመታት ቀባሪ አጥቶ የተበተነውን የቅድስት አርሴማንና የሰማዕታቱን አጽም ሰብስቦ በክብር አኖረው:: ድርጣድስና ባለሟሎቹንም ወደ በርሃ ሒዶ ፈወሳቸው::
የሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ አጽም በ፲፬ኛው መቶ ክ/ዘመን ከሌሎች ሰማዕታት አጽም ጋር ወደ ሃገራችን እንደ መጣ አባቶቻችን በትውፊት ነግረውናል:: ለዚህም ይመስላል ቡርክቷ እናታችን ከሌሎች ሃገራት ለይታ ለኢትዮዽያውያን ልዩ ፍቅር ያላት:: በዋናው ገዳሟ [ወሎ / ኩላማሶ / ስባ / ውስጥ የሚገኝ ነው] ጨምሮ ስሟ በተጠራበት ሁሉ ኃይልን ታደርጋለችና::
ነገር ግን ወንድሞቼና እሕቶቼ በቅድስቷ እናታችን ስም የሚነግዱ ሥጋውያን ሰዎች በዝተዋልና እንጠንቀቅ:: የሰማዕቷ ክብር ብዙ ነውና በሕልም ላይ ብቻ አንታመን:: አባ እንጦንስ እንዳሉት "በሕልሙ የሚታመን ሰው ከንቱ ነውና::"
በዚህ ዕለት ከሰማዕቷ ጋር የመንፈስ እናቷን ቅድስት አጋታን ልናስባት ይገባናል:: ይህች እናት እመ-ምኔት ስትሆን ቅድስት አርሴማን ታስተምራት: ታጸናት: ከጐኗም ትቆምላት ነበር:: ረሃቧን: ጥሟን: ስደቷን: መከራዋንም ሁሉ አብራት ተሳትፋለች:: በፍጻሜውም አብራት ተሰይፋለች::
🕊 † ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ † 🕊
- የቤተ ክርስቲያን ምሰሶ
- ምድራዊው መልአክ
- የጌታ ወዳጅ
- የድንግል ማርያም የአደራ ልጅ
- የንጽሕና አባት
- ቁጹረ ገጽ
- የፍቅር ሐዋርያ
- የምሥጢር አዳራሽ
- የሐዋርያት ሞገሳቸው
- ነባቤ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ ዛሬ ይከብራል::
ምክንያቱም "ቀዳሚሁ ቃል" [ዮሐ.፩፥፩] ብሎ እንደ ንስር መጥቆ ወንጌሉን በዚህች ቀን ጽፏልና::
✞ አምላከ ቅዱሳን ለኛ ለባሮቹ የቅድስቷን ጽናት: የወንጌላዊውንም ፍቅር ያድለን:: በረከታቸውን ከማይጐድል እጁ አብዝቶ ይስጠን::
🕊
[ ✞ መስከረም ፳፱ [ 29 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅድስት አርሴማ ድንግል [ሰማዕት]
፪. ቅድስት አጋታ [እመ ምኔት]
፫. "፻፲፱" ሰማዕታት [የቅድስት አርሴማ ማሕበር]
፬. ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ [ነባቤ መለኮት]
፭. ቅድስት ክርስቶስ ክብራ ኢትዮዽያዊት [በዚህ ቀን ነፍሳትን ከሲዖል ታወጣለች]
[ ✞ ወርኀዊ በዓላት ]
፩. የፈጣሪያችንና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት
፪. ቅዱስ ዼጥሮስ ተፍጻሜተ ሰማዕት
፫. ቅዱስ ማርቆስ ዘቶርማቅ
፬. ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ኢትዮዽያዊት
፭. ቅዱስ ዘርዐ ክርስቶስ [ጻድቅና ሰማዕት]
✞ " በመጀመሪያ ቃል ነበረ:: ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ:: ቃልም እግዚአብሔር ነበረ :: ይህ በመጀመሪያው በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ:: ሁሉ በእርሱ ሆነ:: ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም:: በእርሱ ሕይወት ነበረች:: ሕይወትም የሰው ብርሃን ነበረች:: ብርሃንም በጨለማ ይበራል:: ጨለማም አላሸነፈውም::" ✞ [ዮሐ. ፩፥፩]

[ † እንኳን ለታላቁ ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ ሊቀ ዻዻሳት እና ለአባ ሣሉሲ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †
† ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ †
† በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ከሐዋርያት ቀጥሎ የቅዱስ አትናቴዎስን ያሕል ስለ ሃይማኖት የተዋጋ ቅዱስ ፈልጐ ማግኘት አይቻልም::
† ቅዱስ አትናቴዎስ ማን ነው ?
† ቅዱስ አትናቴዎስ በቤተ ክርስቲያን ትውፊት መሠረት በዘመነ ሰማዕታት መጠናቀቂያ [በ፫ መቶ [300] አካባቢ] እስክንድርያ ግብፅ ውስጥ ነው የተወለደው:: ወላጆቹ አረማውያን በመሆናቸው ክርስትናን አልተማረም ነበር::
ሕጻን እያለ ለጭዋታ ከቤቱ ሲወጣ የክርስቲያን ልጆች ሃይማኖታዊ ጨዋታ ሲጫወቱ ተመለከተ:: ሊቀላቀላቸው ቢፈልግም ክርስቲያን ባለመሆኑ ከለከሉት:: አትናቴዎስም ክርስቲያን ልሁንና አጫውቱኝ ብሏቸው እሺ ስላሉት ሕጻናቱ ዕጣ ተጣጣሉ::
ላንዱ ቄስ: ላንዱም ዲያቆን መሆን ሲደርሳቸው ለአትናቴዎስ ፓትርያርክ መሆን ስለ ደረሰው ሌሎቹ ሕጻናት ይሰግዱለት ጀመር:: በአጋጣሚ ሕጻናቱ ይሕንን ሁሉ ሲያደርጉ የወቅቱ ፓትርያርክ ቅዱስ እለእስክንድሮስ በመገረም ያያቸው ነበርና ለሕጻኑ አትናቴዎስ ትንቢት ተናገረለት::
ከዚያም የአትናቴዎስ አባቱ ሲሞት ሊቀ ዻዻሳቱ ከእናቱ ወስዶ አጥምቆ: የሚገባውን መንፈሳዊ ትምሕርት ሁሉ በልቡናው ላይ ቀረጸበት:: ከዚሕ በኋላ ዲቁናን ሹሞ አስተምር አለው:: ምንም ሕጻን ቢሆንም ከሊቅነቱ: ከአመላለሱና ከአንደበቱ ጣፋጭነት የተነሳ የሰማው ሁሉ ይደነቅ ነበር:: ጸጋ እግዚአብሔር በእርሱ ላይ አድራለችና::
ቅዱስ አትናቴዎስ ሊቀ ዲቁና በተሾመ ወራት አርዮስ ቤተ ክርስቲያንን በመረበሹ ኒቅያ ላይ 318ቱ ሊቃውንት ሲሰበሰቡ ጸሐፊ አድርገው ሾሙት:: በጊዜውም በዕድሜ የስንት ጊዜ ትልቁ የሚሆነውን አርዮስን ተከራክሮ ምላሽ አሳጣው:: ቅዱስ አትናቴዎስ ከሊቃውንቱ ጋር ሆኖ ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ወልደ አምላክ: እግዚአብሔር መሆኑን በአደባባይ መሠከረ:: ጸሎተ ሃይማኖትንም ያረቀቀው እርሱ ነው::
ከዚሕ በኋላ የእስክንድርያ [የግብፅ] ፳ [20]ኛ ፓትርያርክ ሆኖ ተሾመ:: ቤተ ክርስቲያንን በመልካም እረኝነት ለ፵፰ [48] ዓመታት ሲመግብ ብዙ መከራዎችን ተቀበለ:: ለ፭ [5] ጊዜ ከመንበሩ አፈናቅለው ወደ በርሃ ሲያግዙት በስደት ከ፲፭ [15] ዓመታት በላይ አሳልፏል::
በተሰደደባቸው ቦታዎች መከራን እየተቀበለ ያላመኑትን አሳምኗል:: በጎቹ እንዳይባዝኑበት ደግሞ በጦማር [በደብዳቤ] ይጠብቃቸው ነበር:: ዛሬ በሃይማኖተ አበው የምናገኘው ቃለ ሃይማኖት በዚሕ ዘመን የተጻፈ ነው:: ሐዋርያዊው ቅዱስ ስለ ኦርቶዶክስ ተዋግቶ: ብዙ ስቃይንም ተቀብሎ በ፫፻፸ [370] ዎቹ ዓ/ም አካባቢ አርፏል::
† ቤተ ክርስቲያን
¤ ሊቀ ሊቃውንት:
¤ ርዕሰ ሊቃውንት:
¤ የቤተ ክርስቲያን /የምዕመናን/ ሐኪም [Doctor of the Church] :
¤ ሐዋርያዊ ብላ ታከብረዋለች::
† ይህች ዕለት ለታላቁ ሊቅ የስደቱ መታሠቢያ: ከስደቱም የተመለሰባት ቀን ናት::
ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ :-
በወቅቱ የነበረው ንጉሥ [ትንሹ ቆስጠንጢኖስ] የአባቱን [ታላቁ ቆስጠንጢኖስን] ዕረፍት ተከትሎ ነገሠ::
ወዲያውም አርዮሳዊ መናፍቅ ሆነ:: ሃይማኖታቸው የቀና አባቶችንም ያሳድድ ገባ:: ከአበው ቅዱሳን መካከል ግን የዚህ መከራ ቀዳሚው ገፈት ቀማሽ ታላቁ ሊቅ ቅዱስ አትናቴዎስ ነበር::
በተለይ አንድ ጊዜ ንጉሡ ቅዱሱን ወደ በርሃ አግዞ: መናፍቅ ዻዻስ በግብጽ ሹሞ: ብዙ ክርስቲያኖችን በግፍ ሲያስገድል: ቅዱሱን ለ6 ዓመታት አሰቃየው:: የወገኖቹ [የልጆቹን] ስቃይ የሰማው ቅዱስ አትናቴዎስ ግን በድፍረት ወደ ቤተ መንግስት ገብቶ ተናገረው::
ሁለት አማራጭን አቅርቦ "ወይ ግደለኝና እንደ አባቶቼ ሰማዕት ልሁን: ካልሆነ ግን ወደ መንጐቼ [ምዕመናን] መልሰኝ" አለው:: መናፍቁ ንጉሥም ቢገድለው ብጥብጥ እንደሚነሳ ስለሚያውቅ በስልት ሊያጠፋው ወሰነ::
ቀዛፊ: መቅዘፊያ: ምግብና ውሃ በሌላት ጀልባ ውስጥ ከቶም ሜዲትራኒያን ባሕር ውስጥ ጣለው:: ድንገት ግን ከሰማይ ጌታችን መላእክቱን አስከትሎ ወረደ::
ሚካኤልና ገብርኤል ባሕሩን እየቀዘፍ: ሌሎች መላእክት እየመገቡት በዚህች ቀን እስክንድርያ [ግብጽ] አድርሰውት ተሠውረዋል:: ሕዝቡም በታላቅ ሐሴት እየዘመሩ አባታቸውን ተቀብለውታል::
† 🕊 አባ ሣሉሲ ክቡር 🕊 †
† የእኒህ አባት ዜና ሕይወትን ሳስበው እጅግ ይገርመኛል:: የአባቶቻችን የሕይወት ፈሊጥ ምን እንደ ሆነ እንድረዳ ስላደረጉኝ በእውነቱ አመሰግናቸዋለሁ:: ጻድቁ የዘመነ ከዋክብት አንድ ፍሬ ናቸው::
በነበሩበት ገዳም የሚታወቁት ግን 'የማይጾመው: የማይጸልየው: ሥራ ፈቱ መነኩሴ' በሚል ነበር:: ገዳሙ ውስጥ ከሚኖሩ መነኮሳት መካከል አንድም ቀን ቢሆን ሲጸልዩና ሲሰግዱ ያያቸው የለም:: ሁሌ ብቻ እንደ ሞኝ ቁጭ ብለው ያኝካሉ::
በዚህ ምክንያትም ሥጋ ወደሙን ወስደው አያውቁም:: አንድ ቀን ግን በገዳሙ በዓል ላይ አበምኔቱና መነኮሳቱ መከሩ:: 'አባ ሣሉሲን አሥረን አውለን ለቁርባን ቢያንስ እናብቃቸው' ሲሉ ወሰኑ:: በውሳኔው መሠረትም በጧት ሒደው ጻድቁን አሠሯቸው::
አባ ሣሉሲም "ፍቱኝ ቁርሴን ልብላበት" ሲሉ ተቆጡ:: መነኮሳቱ ግን "ሳትቆርብ አንለቅህም" አሏቸው:: በዚህ ጊዜ ጻድቁ ቆባቸውን አውልቀው " እመቤቴ የሰው ልጅስ ጨካኝ ነው:: አንቺ ግን ርሕርሕት ነሽ" ብለው በቆባቸው ግድግዳውን ቢመቱት ለ፪ [2] ተሰነጠቀ::
እርሳቸውም ፪ [2] ክንፍ አውጥተው በረው ተሰወሩ:: ባዩት ነገር የደነገጡ መነኮሳት እያለቀሱ ፫መቶ [300] ጊዜ "እግዚኦ . . ." አሉ:: በዚህ ጊዜ የጻድቁን ቆብ አገኙ:: በዚህች ቆብም አጋንንትን አሳደዱ ተአምራትንም ሠሩ::
† ምሥጢሩስ ምንድን ነው ቢሉ: አባ ሣሉሲ :-
፩. 24 ሰዓት ሙሉ በተመስጦ [በልባቸው] ስለሚጸልዩ::
፪. በጧት ተነስተው የሚያኝኩት ደረቅ ሣር እንጂ ምግብ አልነበረምና ነው:: ከውዳሴ ከንቱ መራቅ ማለት ይሔው ነው:: ጻድቁ በዚህች ቀን ዐርፈው ተቀብረዋል::
† አምላከ አበው ምሥጢራቸውን አይሰውርብን:: ከበረከታቸውም ያድለን::
[ † መስከረም ፴ [ 30 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ
፪. አባ ሣሉሲ ክቡር ጻድቅ
፫. ቅዱሳን ያዕቆብና ዮሐንስ ሐዋርያት [ለወንጌል የተጠሩበት /ማር.፩፥፲፱/ (1:19/)
፬. ቅዱስ ጐርጐርዮስ ዘአርማንያ
፭. አባ አብሳዲ ዘደብረ ማርያም
፮. አባ አሮን ዘገሊላ
[ † ወርኀዊ በዓላት ]
፩. ቅዱስ ማርቆስ ዘአንበሳ (ሐዋርያ)
፪. ቅዱስ ጐርጐርዮስ ነባቤ መለኮት
፫. ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት
፬. ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት
† " ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ ብጹዓን ናቸው:: መንግስተ ሰማያት የእነርሱ ናትና:: ሲነቅፏችሁና ሲያሳድዷችሁ: በእኔም ምክንያት ክፉውን ሁሉ በውሸት ሲናገሩባችሁ ብጹዓን ናችሁ:: ዋጋችሁ በሰማያት ታላቅ ነውና ደስ ይበላችሁ:: ሐሴትንም አድርጉ:: ከእናንተ በፊት የነበሩትን ነቢያትን እንዲሁ አሳደዋቸዋልና::" † [ማቴ. ፭፥፲]