Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (♱ ባሕራን ♱)
🕊
✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞
† ጥቅምት ፩ [ 1 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት †
† 🕊 ቅድስት አንስጣስያ ሰማዕት 🕊 †
በቀደመው ዘመን: በተለይም በሮም አካባቢ ይህ ስም በጣም የተለመደ ነበር:: በዚህ ስም የሚጠሩ ቅዱሳትም ቁጥራቸው ቀላል የሚባል አልነበረም:: የቤተ ክርስቲያን ታሪክ እንደሚነግረን ሃገረ ሮሜ እስከ ፭ኛው መቶ ክ/ዘመን ቅረስ የሁሉ መኖሪያ ነበረች::
ደጉም ሆነ ክፉው: ኃጥኡና ጻድቁ: አረማዊና ምዕመኑ: ጨካኙና ርሕሩሁ: ወዘተ. . . በአንድ ላይ ይኖሩባት ነበር:: በዚህ ዘመንም ቦታዋ ብዙ ሐዋርያትን: ሰማዕታትን: ሊቃውንትንና ጻድቃንን አፍርታለች:: [ዛሬን አያድርገውና]
ከእነዚህ ቅዱሳን እንዷ ደግሞ ሰማዕትነትን ከጽድቅና ድንግልና ጋር የደረበችው እናታችን አንስጣስያ ናት:: ቅድስቲቱ በ፬ኛው መቶ ክ/ዘመን አካባቢ ተወልዳ ያደገችው እዛው ሮም ውስጥ ነው:: ወላጆቿ ክርስቲያኖች በመሆናቸው ገና በልጅነቷ የክርስትናን ምንነት ጠንቅቃ አውቃለች::
ወጣት በሆነች ጊዜም ይህቺ ዓለም ጠልፋ እንዳትጥላት ትጠነቀቅ ነበር:: ይህቺ ዓለም ወጥመዶቿ ብዙ ናቸውና:: በተለይ ደግሞ መልክ ስለ ነበራትና ወላጆቿም ባለጠጐች ስለ ነበሩ እርሷ ትኅርምትን ታበዛ ነበር::
ድንግልናዋን በንጽሕና ትጠብቀው ዘንድ ጾምንና ጸሎትን ከስግደት ጋር አዘወተረች:: በሒደትም በውስጧ ፍቅረ ክርስቶስ እየተቀጣጠለ በመሔዱ ይህንን ዓለም ልትተወው አሰበች:: ነገር ግን ወላጆቿ "ልጃችን ለአካለ መጠን ደርሰሻልና እንዳርሽ" አሏት::
እርሷም "እኔ ለሰማያዊው ሙሽርነት: ለመንፈሳዊውም ሠርግ ተጠርቻለሁና ተውኝ" ብላቸው ወደ ገዳም ሔደች:: በዘመኑ በሮም ከተማ ዙሪያ ብዙ የደናግል ገዳማት ነበሩና ከእነዚያው ከአንዱ ገባች::እንደ ገባች ለሰውነቷ ምክንያትን ልትሠጠው አልፈለገችም::
ራሷን በጾም ትቀጣው ዘንድ በ ፵፰ ሰዓት [በ፪ ቀን] አንዴ ብቻ ትበላ ነበር:: ምግቧም ቁራሽ ቂጣ በጨው ብቻ ነበር:: ዓቢይ ጾም በደረሰ ጊዜ ግን ከእሑድ በቀር እህልን አትቀምስም ነበር:: የጌታዋ ፍቅር አገብሯታልና ለሳምንት ራሷን ከምግብና ከምቾት ትከለክል ነበር::
ይህም ሲሆን ቁጭ ብላ አይደለም:: በጸሎትና በስግደት እየተጋች: ለደናግሉ በሙሉ እየታዘዘች ነው እንጂ:: ለጥቂት ዓመታት በእንዲህ ያለ ገድል ቆይታ ከእመ ምኔቷ ጋር በዓል ለማክበር አንድ ቀን ከገዳማቸው ወጡ:: በመንገድ ላይ ሳሉ አረማዊ ንጉሥ ክርስቲያኖችን ሰብስቦ ሲያሰቃይ ደረሱ::
በእርግጥ ዐይተው እያዘኑ ማለፍ ቢችሉም ቅድስት አንስጣስያ ግን አልቻለችም:: የወገኖቿ ስቃይ ቢያንገበግባት በድፍረት ወደ መኮንኑ ቀርባ ዘለፈችው:: "አንተ አዕምሮ የጐደለህ! እንዴት በአምላካቸው ደም የተገዙ ክርስቲያኖችን እንዲህ ያለ በደላቸው ታሰቃያቸዋለህ?" አለችው::
በድፍረቷ የተገረመው መኮንኑም ወደ እርሱ አስቀርቦ "ማንን ታምኚያለሽ?" አላት:: እርሷም ሰማዩንና ምድሩን: ባሕሩንና የብስን የፈጠረውን: ስለ ሰው ፍቅርም የሞተውንና የተነሳውን: ዘለዓለማዊ ንጉሥ ኢየሱስ ክርስቶስን አመልካለሁ" አለች:: እጅግ ስለ ተበሳጨም ስቃይን አዘዘባት:: በገድል የተቀጠቀጠ ለምለም አካሏን በብዙ መክፈልተ ኩነኔ ወታደሮቹ አሰቃዩዋት:: በመጨረሻም ሞት ተፈርዶባት በዚህች ቀን ገደሏት::
ቅድስት እናታችን አንስጣስያ የጽድቅን: የድንግልናን: የምስክርነትን አክሊል በእግዚአብሔር መንግስት አገኘች:: ይህን ሁሉ ስትጋደል ግን እድሜዋ ገና ወጣት ነበር::
† 🕊 ቅድስት ማርያም እንተ ዕፍረት 🕊 †
በዘመነ ሐዋርያት በተመሳሳይ 'እንተ ዕፍረት-ባለ ሽቱ' ተብለው የሚጠሩ ፪ እናቶች ነበሩ:: ፪ቱም ስማቸው ማርያም ስለ ነበር ለመለየት እንዲያመች አንደኛዋን 'ማርያም ኃጥዕት-ከኃጢአት የተመለሰች': ፪ኛዋን ደግሞ 'ማርያም እኅተ አልዓዛር-በቢታንያ የነበረችው ብለው አበው ይጠሯቸዋል::
በሉቃስ ወንጌል ላይ የምትገኘው ከኃጢአት ሕይወት የተመለሰችው ስትሆን በዮሐንስ ወንጌል ፲፪፥፩ ላይ ያለችው የአልዓዛር እህት [ድንግሊቱ] ናት:: ዛሬም የምናስባት ይህቺውን እናታችን ነው::
ቅድስት ማርያም መድኃኒታችን ክርስቶስ ወደዚህ ዓለም መጥቶ በሚያስተመርበት ዘመን በቢታንያ አካባቢ ትኖር የነበረች ድንግል ወጣት ናት:: ወላጆች ባልነበረበት ቤት ውስጥ ታላቆቿ አልዓዛርና ማርታ አሳድገዋታል::
በቤተሰብ ደረጃ እንግዳን ይቀበሉ ነበርና ጌታችን ወደዳቸው:: አልዓዛርን ከ፸፪ቱ አርድእት: ማርያምና ማርታን ደግሞ ከ፴፮ቱ ቅዱሳት አንስት ቆጥሯቸዋል:: ወንድማቸው አልዓዛር በታመመ ጊዜ ወደ ጌታ ልከው ነበር::
ያለ ጊዜው የማይሠራ ጌታ ባይመጣ አልዓዛር ሞተ:: በ፬ኛው ቀን አምላክ ሲመጣ ቅድስት ማርያም በጌታ ፊት ሰግዳ "እግዚእየ ሶበሰ ኀሎከ ዝየ እምኢሞተ እኁየ-አንተ በዚህ በኖርክስ ወንድሜ ባልሞተ ነበር" ብላ አለቀሰች:: [ዮሐ.፲፩]
ጌታም ስታለቅስ ባያት ጊዜ አምላክነቱ አራርቶት አለቀሰ:: ወዲያውም በስልጣነ ቃሉ አዞ አልዓዛርን አስነሳው:: ከፋሲካ [ጌታ ከመሰቀሉ ፮ ቀናት] በፊትም ቅዱሳኑ ለጌታ ግብር አገቡ:: እርሱም ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ታደመላቸው:: [ዮሐ.፲፪፥፩]
በዚያም አልዓዛር ከጌታ ጐን ሲቀመጥ: ቅድስት ማርያም ከጌታ ሥር ተንበርክካ: ናርዶስ የሚሉትን የ፫፻ ዲናር ሽቱ በጌታ ላይ አፈሰሰች:: መዓዛ መለኮቱና ሽቱው ሲገናኝ "መልዐ መዓዛሁ" እንዲል ምስጥ የሚያደርግ ሽታ ቤቱን ሞላው::
በወቅቱ ይሁዳ ቢቃወምም ጌታ ምላሹን ሰጥቶታል:: ቅድስት ማርያምንም "ማርያምሰ ኃርየት መክፈልተ ሠናየ ዘኢየኃይድዋ" ብሎ አመስግኗታል:: ያስመሰገናት ቁጭ ብላ በተመስጦ መማሯ ብቻ እንዳልሆነ አባ ሕርያቆስ መስከሯል::
ሲመክረንም "አርምሞንና ትዕግስትን እንደ ማርያም ገንዘብ እናድርግ" ብሎናል:: [ቅዳሴ ማርያም] ቅድስት ማርያም በጌታችን ክርስቶስ በኅማሙ ጊዜ: ሲቀብሩት ነበረች:: ትንሳኤውንም ዐይታለች::
ከጌታ እርገት በኋላም መንፈስ ቅዱስን ተከትላ ለወንጌል አገልግሎት ተግታለች:: ቅድስት እናታችን ማርያም እንተ ዕፍረት ዛሬ እንዳረፈች እናዘክራለን:: የእናቶቻችን ቅዱሳት አምላክ ፍቅራቸውን ያድለን:: በረከታቸውንም ያብዛልን::
🕊
[ † ጥቅምት ፩ [ 1 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅድስት አንስጣስያ [ድንግል: ጻድቅት: ሰማዕት]
፪. ቅድስት ማርያም እንተ ዕፍረት
፫. ቅድስት ሶስና ድንግል
፬. ቅድስት ኅርጣን ድንግል
" ሲሔዱም ወደ አንዲት መንደር ገባ:: ማርታ የተባለች አንዲት ሴትም በቤቷ ተቀበለችው:: ለእርሷም ማርያም የምትባል እኅት ነበረቻት:: እርሷም ደግሞ ቃሉን ልትሰማ በኢየሱስ እግር አጠገብ ተቀምጣ ነበረች . . . ኢየሱስም መልሶ . . . 'ማርያምም መልካም እድልን መርጣለች:: ከእርሷም አይወሰድባትም' አላት::" [ሉቃ.፲፥፴፰]
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖

[ † እንኳን ለቅዱሳን ሊቃውንት አባ ሕርያቆስ እና አባ ሳዊሮስ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †
🕊 † ሊቁ አባ ሕርያቆስ † 🕊
† ክርስቲያን ሆኖ እመቤታችንን የሚወድ ሰው ሁሉ ይህንን አባት ያውቀዋል:: አባ ሕርያቆስ ተወልዶ ያደገው በምድረ ግብጽ ሲሆን አካባቢው ብህንሳ [ንሒሳ] ይባላል:: ይህቺ ቦታ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስን ጨምሮ በርካታ ቅዱሳንን ያፈራች ናት::
አባ ሕርያቆስን በዚህ ዘመን ነበረ ብየ ትክክለኛውን ዓ/ም ለመናገር ይከብደኛል:: ከቤተ ክርስቲያን ትውፊት መረዳት እንደሚቻለው ግን የነበረበት ዘመን ፬ኛው: ወይ ፭ኛው መቶ ክ/ዘመን እንደ ሆነ መገመት ይቻላል::
ቅዱሱ በዘመኑ የተለየ ማንነት የነበረው ሰው ነው:: ገና ከልጅነቱ እመ ብርሃንን የሚወዳት በመሆኑ ቅን: የዋህና ገራገር ነበረ:: መቼም እመቤታችንን ይወዳል ሲባል እንደ ዘመኑ በአፍ ብቻ እንዳይመስለን:: ቀንና ሌሊት ለፍቅሯ የሚተጋ: ማዕበለ ፍቅሯ የሚያማታው ሰው ነበር እንጂ::
የእመቤታችን ድንግል ማርያምን ስም ሲጠራ ምስጥ ብሎ ልቡናው ይሰወርበት ነበር:: ዘወትር የእርሷን ፍቅር ከማሰብ በቀር ሌላ ሥራ አልነበረውም:: የልጅነት ጊዜው ሲያልፍም ድንግልንና ቸር ልጇን ያገለግል ዘንድ መነነ::
ዘመኑ ዘመነ ሊቃውንት እንደ መሆኑ ሁሉም ለትምሕርት ሲተጉ እርሱ ግን ለጸሎትና ለደግነት ብቻ ነበር የሚተጋው:: ከትምሕርት ወገንም የሰሞን ጉዋዞችን: አንዳንድ ቅዳሴያትንና የዳዊትን መዝሙር ተምሮ ነበር::
በተለይ ግን የዳዊትን መዝሙር እየጣፈጠው መላልሶ: መላልሶ ያመሰግንበት ነበር:: ከዳዊት መካከል ደግሞ መዝ. ፵፬ን ፈጽሞ ይወዳት ነበር:: ይህቺ ጥቅስ የምትጀምረው "ጐስዐ ልብየ ቃለ ሠናየ" ብላ ነው:: የውስጧ ምሥጢርም ስለ ድንግል ማርያምና ስለ ክርስቶስ ነው::
አባ ሕርያቆስ ይህቺን መዝሙር በቃሉ አጥንቶ: ቁሞም ተቀምጦም: ተኝቶም ተነስቶም ያለ ማቋረጥ ይላት ነበር:: እየጣፈጠችው "ልቡናየ በጐ ነገርን አወጣ" እያለ ይዘምር ነበር:: በወቅቱ ታዲያ የብህንሳ ኤዺስ ቆዾስ በማረፉ ምትክ ሲያፈላልጉ መንፈስ ቅዱስ አባ ሕርያቆስን መረጠ::
ምንም አለመማሩ ቢያሰጋቸውም "በጸሎቱ: በደግነቱ ሃገር ይጠብቃል" ብለው ሾሙት:: ነገር ግን ምንም በሥልጣን የበላያቸው ቢሆን ተማርን የሚሉ ሰዎች ይጠሉት: ይንቁትም ነበር:: እርሱ ግን እንደ ጠሉኝ ልጥላቸው: እንደ ናቁኝ ልናቃቸው ሳይል በፍቅር ያገለግል ነበር::
አንድ ቀን ታዲያ መንገድ ይወጣል:: በበርሃ ብቻውን እየተራመደ: "ጐሥዐ ልብየ ቃለ ሠናየ" እያለ እየዘመረ: ተመሥጦ ቢመጣበት መንገድ ሳተ:: እርሱ በምስጋናው ሲደሰት እግሩ ግን ከገደል ጫፍ ደርሶ ነበር:: ገደሉን ልብ አላለውም ነበርና ሳይታወቀው ወደ ገደሉ ውስጥ ተወረወረ::
በዚህ ጊዜ ደንግጦ ቢመለከት እጅግ ጥልቅ በሆነ ገደል ውስጥ ራሱን አገኘው:: ነገር ግን አንድም አካሉ አልተነካም:: ልብሱም አልቆሸሸም:: ለራሱ ተገርሞ ዙሪያ ገባውን ሲመለከት እርሱ ቁጭ ያለበት ብርሃንን የተሞላ የልብስ ዘርፍ ነበር::
"እመ ብርሃን!" ብሎ ሲጮህ የሰማይና የምድር ንግሥት የሆነች እመቤታችን ከፊቱ ቁማ ታየችው:: እመ አምላክን በገሃድ ቢያያት እንደ እንቦሳ ዘለለ::
የሚገርመው ደግሞ የተቀመጠበት የድንግል ማርያም የቀሚሷ ዘርፍ ነበር:: እመቤታችን አነጋገረችው: ባረከችው:: ፍቅሯ ቢመስጠው ከሰው ሳይገናኝ: ምግብም ሳይበላ: እዚያው ገደሉ ውስጥ ለ፩ ዓመት ያህል በተመስጦ ቆይቷል::
በኋላ እመ ብርሃን መጥታ ከገደሉ አውጥታ ወደ ሐገሩ መለሰችው:: ከጥቂት ጊዜ በኋላም አንድ ፈተና ገጠመው:: አንድ ቀን እመቤታችን በተወለደችበት ግንቦት ፩ ቀን ቅዳሴ "ማን ይቀድስ" ሲባል ሰዎቹ "አባ ሕርያቆስ ይሁን" አሉ::
እርሱ ግን "እኔ አይቻለኝም: እናንተ ሊቃውንት ቀድሱ" አላቸው:: "አይሆንም" ብለው እርሱኑ አስገቡት:: ይህንን ያደረጉት ለተንኮል ነበር:: ልክ ወንጌል ተነቦ ፍሬ ቅዳሴ ሲመረጥ እርሱ "እግዚእን [የጌታ ቅዳሴን] ልቀድስ" ቢል እነርሱ "የሚቀደሰው የሊቅ ቅዳሴ ነው" አሉት::
ይህንን ያሉት እርሱ የሊቃውንቱን ቅዳሴ አያውቅምና በሰው ፊት እንዲዋረድ ነው:: እንዲህም ብለው ባለመማሩ ተሳለቁበት:: አባ ሕርያቆስ ግን እያዘነ ወደ መንበሩ ዞረ:: ድንግልንም "እመቤቴ መናቄን: መገፋቴን ተመልከች" አላት::
ወዲያው ግን ድንግል ማርያም ወርዳ ቀጸበችው [ጠራችው]:: በዘርፋፋው ቀሚሷ ላይም ረቂቅ የሆነ ቅዳሴን አሳየችው:: ደጉ ሰው ደስ ብሎት "ጐሥዐ ልብየ" ሲል ሁለቱ እግሮቹ ከመሬት ከፍ አሉ:: እርሱም "ወአነ አየድእ ቅዳሴሃ ለማርያም" ብሎ እስከ ኃዳፌ ነፍሱ ድረስ አደረሰው::
ሕዝቡና ካህናቱ በሆነው ነገር ሲደነቁ: አንዳንዶቹ "ዝም ብሎ ነው የቀባጠረ" አሉ:: ቅዱሱ ግን ቅዳሴ ማርያምን በብራና ጠርዞ በሕዝቡ መካከል ድውይ ፈወሰበት:: እሳት ሳያቃጥለው: ውሃ ሳይደመስሰው ቀረ::
መጽሐፈ ቅዳሴው ሙትንም አስነስቷል:: ከዚህች ሰዓት ጀምሮ በዘመኑ ቁጥር ፩ ሊቅ ሆነ:: ብዙ መጻሕፍትን ሲተረጉም አጠቃላይ ድርሰቶቹም እልፍ [፲ ሺህ] ናቸው:: ሊቁ እንዲህ በንጹሕ ተመላልሶ ዐርፏል:: ይህቺ ቀን ለቅዱሱ የልደቱና ዕረፍቱ መታሰቢያ ናት::
🕊 † ታላቁ ቅዱስ ሳዊሮስ † 🕊
† ቅዱስ ሳዊሮስ በ፮ኛው መቶ ክ/ዘመን መጀመሪያ አካባቢ በሶርያ አንጾኪያ የተነሳ አባት ነው:: ወቅቱ መለካውያን [፪ ባሕርይ ባዮች] የሰለጠኑበት እንደ መሆኑ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምእመናን ያነሱበትና የሚሰደዱበት ጊዜ ነበር:: በዚህ ጊዜ ነበር ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ሳዊሮስ በሥላሴ ፈቃድ ለቤተ ክርስቲያን የተነሳው:: ሊቃውንት "አንበሳ" ሲሉ ይጠሩታል::
ቅዱሱ ለተዋሕዶ ሃይማኖት ብዙ ሆኖላታል:: የመናፍቃን ጸር በመሆኑ ብዙ ድርሰቶችን ደርሷል:: ንጉሡን ዮስጢያኖስን [Justinian] ሳይቀር በይፋ ይገስጸው ነበርና ንጉሡ ሊገድለው ቆረጠ::
ሃይማኖቷ የቀና ንግሥቲቱ ታኦድራ ግን ይህንን ስትሰማ በሌሊት ወደ ሊቁ ሒዳ "እባክህን ሽሽ" አለችው:: እርሱ ግን "ሞት ለእኔ ክብር ነውና አልሔድም" ሲል መለሰላት:: አባቶችን ሰብስባ "ስለ ቤተ ክርስቲያን ስትል" ብለው ለምነው ወደ ግብጽ ሸኙት::
እርሱ እየሔደ ገዳዮቹ ያሳድዱት ገቡ:: መንገድ ላይ ቢደርሱበትም ተሰወረባቸው:: ለብዙ ቀናትም አብሯቸው ተጓዘ:: እነርሱ ተስፋ ቆርጠው ሲመለሱ እርሱ ግን ምድረ ግብጽ ደረሰ::
በምድረ ግብጽም የዽዽስና ልብሱን ትቶ የመነኮሳትን አሮጌ ልብስ ለብሶ ሕዝቡንና መነኮሳቱን አስተማረ: አጸና:: በየቦታውም ብዙ ተአምራትን ሠራ::
አባቶች መነኮሳትም ማንነቱን ባወቁ ጊዜ ሰገዱለት:: ዶርታኦስ [ዱራታኦስ] በሚባል አንድ ደግ ሰው ቤትም በ፮ኛው መቶ ክ/ዘመን አጋማሽ አካባቢ የካቲት ፲፬ ቀን ዐርፏል:: ይህቺ ቀን ዕለተ ስደቱ ናት::

† አምላከ ቅዱሳን ሊቃውንት የድንግል እመቤታችንን ጣዕሟን ፍቅሯን ያሳድርብን:: የአበውን ሃብትና በረከትም አይንሳን::
🕊
[ † ጥቅምት ፪ [ 2 ]ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ሊቁ አባ ሕርያቆስ
፪. ቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ
፫. ቅድስት ቴክላ ሰማዕት
፬. አቡነ ማቲያስ ዘፈጠጋር [የአቡነ ተክለሐይማኖት የመንፈስልጅ]
🕊
[ † ወርኀዊ በዓላት ]
፩. ቅዱስ ታዴዎስ ሐዋርያ [ከ፲፪ቱ ሐዋርያት]
፪. ቅዱስ ኢዮብ ጻድቅ ተአጋሲ
፫. ቅዱስ አቤል ጻድቅ
፬. ቅዱስ አባ ዻውሊ ገዳማዊ [ታላቁ]
፭. ቅዱስ ዮሐንስ ነቢይ [መጥምቀ መለኮት]
† " . . . ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኩአችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ::" † [ይሁዳ. ፩፥፫]
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖
🕊
[ † ጥቅምት ፪ [ 2 ]ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ሊቁ አባ ሕርያቆስ
፪. ቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ
፫. ቅድስት ቴክላ ሰማዕት
፬. አቡነ ማቲያስ ዘፈጠጋር [የአቡነ ተክለሐይማኖት የመንፈስልጅ]
🕊
[ † ወርኀዊ በዓላት ]
፩. ቅዱስ ታዴዎስ ሐዋርያ [ከ፲፪ቱ ሐዋርያት]
፪. ቅዱስ ኢዮብ ጻድቅ ተአጋሲ
፫. ቅዱስ አቤል ጻድቅ
፬. ቅዱስ አባ ዻውሊ ገዳማዊ [ታላቁ]
፭. ቅዱስ ዮሐንስ ነቢይ [መጥምቀ መለኮት]
† " . . . ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኩአችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ::" † [ይሁዳ. ፩፥፫]
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (♱ ባሕራን ♱)
🕊
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። †
† ጥቅምት ፫ [ 3 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት †
† 🕊 " ቅዱስ ጊዮርጊስ ሐዲስ " 🕊 †
† ሰማዕቱ የተወለደው በምድረ ግብጽ አሕዛብ [ተንባላት] በሰለጠኑበት የመጀመሪያው ዘመን ነበር:: በተለይ ተንባላቱ ግብፅና ሶርያን ከያዙ በኋላ ባልተጠበቀ ፍጥነት በኃይልም በሰውም ተደራጅተው ነበር:: ቅዱስ ጊዮርጊስ [ልብ በሉልኝ ሊቀ ሰማዕታት አይደለም] የተወለደው በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ ነበር::
እናቱ የተመሠከረላት ክርስቲያን ብትሆንም እንዳለመታደል አባቱ ተንባላታዊ [አሕዛብ] ነበር:: ስሙንም መዛሕዝም ይሉታል:: ሕጻኑ እንደተወለደ ያወጡለት ስም አሕዛባዊ ከመሆኑ ባለፈ በሰዓቱ መጠመቅ አልቻለም:: የወቅቱ ሕግ ከወላጆቹ አንዱ አሕዛባዊ ከሆነና አጠምቃለሁ ቢባል የሚከተለው ሰይፍ ነበር:: በዚሕ ምክንያት ሳይጠመቅ ፯ ዓመት ሞላው::
እናቱ ግን ሕጻን ቢሆንም ፍቅረ ክርስትናን ታስተምረው ነበር:: ባይጠመቅም ጸበሉን: እመነቱን ትቀባው ነበር:: ደብቃ ቅዳሴ ታሰማውም ነበር:: አንድ ቀን ግን ሕጻናት ሲቆርቡ አይቶ ካልቆረብኩ ብሎ አለቀሰ:: ምን ታድርገው? ወደ ውጪ አውጥታ ከአውሎግያ [የሰንበት በረከት] አበላችው:: "ጌታየ! ልጄን እርዳው" አለች::
ልክ በአፉ ሲቀምሳት መዓዛ መንፈስ ቅዱስ አደረበትና ፍጹም ተደሰተ:: ትንሽ ከፍ ሲል ለምን እንደማይጠመቅና እንደማይቆርብ እናቱን ጠየቃት:: "ልጄ ሆይ! ይገድሉሃል" አለችው:: ከዚህች ቀን ጀምሮ የሚጠመቅበትን ዘዴ ይፈልግ ጀመር::
አስቀድሞ ትምሕርተ ክርስትናን ተማረ:: ለአካለ መጠን ሲደርስ አፈላልጐ ጠንካራ ክርስቲያን የሆነች ሴት አገባ:: ጥቂት ጊዜ ከቆየ በኋላ ሚስቱን ስለ መጠመቅ አማከራት:: "ሌላ ሃገር ሒደህ ተጠመቅ" አለችው:: ከግብፅ ተነስቶ ሶርያ ገባ::
አባቶችን አፈላልጎ ተጠመቀ:: ቀጥሎም መንገዱን ወደ ልዳ አደረገ::
ወደ ደብሩ ተጠግቶ አባቶችን "ስም አውጡልኝ" ቢላቸው መንፈስ ቅዱስ አናግሯቸው "ጊዮርጊስ" አሉት:: እሱም ደስ እያለው: ባጭር ታጥቆ የልዳውን ቅዱስ ጊዮርጊስ ያገለግለው ገባ:: ትንሽ ቆይቶ ሁከት መንፈሳዊ ተሰማው:: ማለትም ስለ ሃይማኖቱ ደሙን ማፍሰስ ፈለገና ወደ ግብፅ ተመለሰ::
በዚያ ያሉ አሕዛብ በክርስትና ስም: ልብስና ሞገስ ሲመለከቱት ተበሳጩ:: ዕለቱኑ አሠሩት:: ሌሊት እናቱና ሚስቱ መጥተው አሉት:- "አደራ! ፍቅረ ዓለም እንዳያታልልህ:: ሰማዕት ብትሆን ላንተም ክብር: ለእኛም ሞገስ ነው" ብለውም አጽናኑት:: እንዲህ ያሉ እናትና ሚስት ማግኘትም ታላቅ እድል ነው::
ሐዲስ ጊዮርጊስም ጸና:: ከዚያች ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ቀናት ደበደቡት: አካሉን ቆራረጡት: ደሙንም መሬት ላይ አንጠፈጠፉት:: በየመንገዱ እየጎተቱ ተሳለቁበት:: እርሱ ግን ክርስቶስን ወዷልና ሁሉን ታገሰ:: ሌሊት በሆነ ጊዜም ጌታችን ተገልጦ "ከሰማዕታት ተቆጠርህ" አለው::
በማግስቱ በአደባባይ አንገቱን በሰይፍ ቆረጡት:: ክፋታቸው የጸና ነውና ሥጋውን በእሳት አቃጠሉት:: ወደ ባሕርም ጣሉት:: እናቱ ከባሕር ስታወጣው ግን ምንም አላገኘውም ነበር:: በዚሕች ቀን እናቱና ሚስቱ በክብር ቀብረውታል::
† 🕊 " አባ ስምዖን ሊቀ ዻዻሳት " 🕊 †
በምድረ ግብጽ ተነስተው: በማርቆስ ወንጌላዊ መንበር ላይ ይቀመጡ ዘንድ ከተገባቸው ሊቃነ ዻዻሳት አንዱ እኒህ አባት ናቸው:: ከልጅነታቸው መንነው ብዙ ዘመናትን በተጋድሎ በማሳለፋቸው ሥጋዊ አካላቸው ደካማ ሆኖ ነበር::
ከገዳማዊ አገልግሎታቸው ቀጥሎም ከእርሳቸው በፊት ለነበሩ ሁለት ፓትሪያርኮች ረዳት ሆነው አገልግለዋል:: በዚህ ጊዜም ለመንጋው የሚሆኑ ተግባራትን ከመፈጸማቸው ባሻገር በጾምና በጸሎት መጋደልን አልተዉም ነበር::
ጊዜው ደርሶ በእግዚአብሔር ፈቃድ: በሕዝቡና ዻዻሳቱ ምርጫ: የእስክንድርያ ፶፩ኛ ፓትርያርክ ሲሆኑ እርሳቸው እንደ ሌሎቹ አበው 'አልፈልግም' ብለው ነበር::
ቀደም ሲል እንዳልነው አካላቸው በተጋድሎ የተቀጠቀጠ ነበርና በመንበራቸው ላይ ለብዙ ጊዜ መቆየት አልቻሉም::እግራቸውን በጠና በመታመማቸው ፈጣሪ ነፍሳቸውን እንዲቀበል ለመኑት: እርሱም ሰማቸው:: ሊቀ ዻዻሳት ሆነው በተሾሙ በ፻፷፭ ኛው ቀን [ማለትም በ፭ ወር ከ፲፭ ቀናቸው] በክብር ዐርፈው ተቀብረዋል::
† ቸሩ አምላክ ከሰማዕቱ ጽናትን: ትእግስትን: ጸጋ በረከትን ይክፈለን::
🕊
[ † ጥቅምት ፫ [ 3 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅዱስ ጊዮርጊስ ሐዲስ [ሰማዕት]
፪. አባ ስምዖን ሊቀ ዻዻሳት
፫. ቅዱስ ጐርጐርዮስ ዘአርማንያ
፬. ቅድስት ታኦድራ ልዕልት
፭. ቅድስት ታኦፊላ
፮. አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
[ † ወርኀዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. በዓታ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ
፪. ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና
፫. ቅዱሳን ሊቃነ ካህናት አበው [ዘካርያስና ስምዖን]
፬. አባ ሊባኖስ ዘመጣዕ
፭. አቡነ ዜና ማርቆስ
፮. አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ዘደብረ በንኮል
፯. ቅዱስ ቄርሎስ ሊቅ [ዓምደ ሃይማኖት]
† " ስለዚሕ ወንድሞቼ ሆይ ጣዖትን ከማምለክ ሽሹ:: ልባሞች እንደመሆናችሁ እላለሁ:: በምለው ነገር እናንተ ፍረዱ:: የምንባርከው የበረከት ጽዋ ከክርስቶስ ደም ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን? የምንቆርሰውስ እንጀራ ከክርስቶስ ሥጋ ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን?... እኛ ብዙዎች ስንሆን አንድ ሥጋ ነን:: ሁላችን ያን አንዱን እንጀራ እንካፈላለንና:: "† [፩ቆሮ.፲፥፲፬-፲፰]

†
† 🕊 ክብርት ሰንበት 🕊 †
❝ የሰው ልጆች ያርፉባት ዘንድ ሰንበትን አዘጋጀ፡፡ ለጻድቃንም ለኃጥአንም ፣ ለሞቱትም በሕይወት ላሉትም ፡ የሰው ልጆች ያርፉባት ዘንድ ሰንበትን አዘጋጀ፡፡
የክርስቶስ ሰንበቱማ እርሷ ናት ፣ ለልዑልም የስሙ ማደሪያ ናት፡፡ ዛሬስ በሰማያት ያለች ተስፋችንና ሕይወታችን በዚህች በተቀደሰች ቀን ነው ፣ በርሷ በሚያርፉባት በሰንበት ቀን፡፡ ❞
[ ቅዱስ ያሬድ ]
🕊
[ መጽሐፍ እንደተናገረ በፈጣሪ እና በፍጡራን መካከል ለዕረፍት የቃል ኪዳን ማደሪያ [ ምልክት ] የሆንሽ የብርሃን ቀን ሰንበተ ሰንበታት ማርያም ሆይ በገነት ያሉ ጻድቃን በአንቺ ደስ ይላቸዋል፡፡ ኃጥአንም ከደይን በአንቺ ይወጣሉ፡፡ ]
[ አባ ጽጌ ድንግል ]

[ † እንኩዋን ለቅዱሳን ነገሥታት "አብርሃ ወአጽብሃ" እና ለቅዱስ "ሐናንያ ሐዋርያ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ † ]
† 🕊 ቅዱሳን አብርሃ ወአጽብሃ 🕊 †
እነዚህ ነገሥታት ሞገሶቻችን: ብርሃኖቻችን ናቸውና ደስ እያለን እንወዳቸዋለን: እናከብራቸዋለን:: ሥላሴ ቢመርጧቸው ዛሬ ላለንበት ሕይወት መሠረቱን ጥለው አልፈዋልና::
፪ቱ ቅዱሳን ነግሥታት መንትያዎች ሲሆኑ ወላጆቻቸው ንጉሥ ታዜር / አይዛና / ሠይፈ አርዕድ እና ንግሥት አሕየዋ / ሶፍያ ይባላል:: ንጉሡና ባለቤቱ ልጅ ቢያጡ ወደ እግዚአብሔር ለመኑ:: ፈጣሪም በቅዱስ ሚካኤል አብሳሪነት ፪ ዕንቁዎችን አስረከባቸው::
ንግስት አሕየዋ [ሶፍያም] መጋቢት ፳፱ ቀን በ፫፻፲፩ ዓ/ም ጸንሳ: ታሕሳስ ፳፱ ቀን በ፫፻፲፪ ዓ/ም ፪ቱን ቅዱሳን ወልዳቸዋለች:: "አምላክ ሽሙጥን አራቀልኝ" ስትልም "አዝጉዋጉ" ብላቸዋለች:: እነዚህ ፪ ፍሬዎች በልጅነታቸው ከወቅቱ ሊቀ ካህናት እንበረም ኦሪቱን ጠንቅቀው ተምረዋል::
ከእግዚአብሔር የተሰጡ ናቸውና በ፲፪ ዓመታቸው ወደ ቤተ መቅደስ ገብተዋል:: ትንሽ ቆይቶ ግን አባታቸው ታዜር በማረፉ ሕዝቡ ፪ቱን ቅዱሳን "ንገሡልን" አሏቸው:: እነርሱም "እኛ የፈጣሪ አገልጋዮች ነንና አንችልም" በማለታቸው ለተወሰነ ጊዜ እናታቸው አስተዳደረች::
ቆይቶ ግን ቅዱስ ሚካኤል ለሊቀ ካህናቱ እንበረም "የፈጣሪ ፈቃዱ ስለ ሆነ አትዘኑ:: ፪ታችሁም በአንድ ዙፋን ላይ ንገሡ: ታላቅ ጸጋ ለሃገሪቱ ይሆናል በላቸው" አለው::
ሊቀ ካህናቱም የታዘዘውን ተናግሮ: በ፲፱ ዓመታቸው: ፪ቱንም በአንድ ዙፋን ላይ "ነገሥተ ኢትዮዽያ" ሲል አስቀምጦ ቀባቸው:: ስማቸውን "ኢዛና" እና "ሳይዛና" አላቸው:: ቅዱሳኑ እንደ ነገሡ ቀዳሚ ሥራቸው የቀናችውን ሃይማኖት መፈለግ ሆነ::
በወቅቱ ፍሬምናጦስ [የሁዋላው አቡነ ሰላማ] በቤተ መንግስቱ ውስጥ የቅርብ አማካሪ ነበርና ጠርተው ተጨዋወቱት:: "አንተ ወንድማችን! ክርስቶስ ይወርዳል: ይወለዳል ተብሎ የተቆጠረው ሱባኤ እኮ አልፏል:: ምነው ቀረሳ? በርግጥ ምሥጢሩ ንገረን" አሉት::
እርሱም አትቶ: አመሥጥሮ: ከ፫፻ ዓመታት በፊት አምላክ ሰው መሆኑንና ዓለምን ማዳኑን አስተማራቸው:: "አጥምቀን?" ቢሉት "አልችልም" አላቸው:: እነርሱም ከብዙ ስጦታ ጋር ወደ ግብጽ ላኩት::
ቅዱስ አትናቴዎስም ፍሬምናጦስን "አቡነ ሰላማ" ብሎ ከብዙ መጻሕፍት ጋር ላከው:: በመጀመሪያ ኢዛናና ሳይዛና ተጠመቁ:: ስማቸውም "አብርሃ ወአጽብሃ" ተባለ:: ቀጥሎም ሠራዊቱና ሕዝቡ ተጠመቀ::
ሃገራችንም በእነዚህ ቅዱሳን አማካኝነት ከጨለማ ወደ ብርሃን መጣች:: የክርስትና ደሴት ሆነች:: ሃገረ እግዚአብሔርነቷንም አጸናች:: ቅዱሳኑ ከዚህ በሁዋላ በሞገስ ክርስትናን ያስፋፉ ዘንድ ደከሙ:: ከ፻፶፬ በላይ አብያተ ክርስቲያናትን ሲያንጹ አብዛኞቹ ፍልፍል ነበሩ::
በተለይ ግን በአክሱም ከተማ ላይ ያነጿትና ፲፪ ቤተ መቅደሶች የነበሯት የጽዮን ቤተ ክርስቲያን ልናያት ትናፍቀናለች:: ጌጧ: ብርሃኗ ውል ውል ይልብናል:: ይህቺው ቤተ ክርስቲያን በ፲ ኛው ክ/ዘመን ዮዲት ጉዲት በእሳት አውድማታለችና:: መሠረቱ ግን ዛሬም አለ::
ቅዱሳን አብርሃ ወአጽብሃ ግን ክርስትናን ለማስፋፋትና መንግስትን ለማጽናት ሲሉ ከአክሱም በተጨማሪ በሽዋም ዙፋንን ዘረጉ:: ለብዙ ዓመታትም አምላክ በፈቀደው መንገድ እስከ የመን ድረስ ገዙ:: ክርስትናንም አስፋፉ::
ቅዱስ አብርሃ በተወለደ በ፶፪ ዓመቱ: በ፫፻፷፬ ዓ/ም ጥቅምት ፬ ቀን ሲያርፍ ወንድሙ ለ፲፭ ዓመታት ብቻውን አስተዳድሯል:: በ፫፻፸፱ ዓ/ም ደግሞ በዚሁ በጥቅምት ፬ ቀን ቅዱስ አጽብሃም በተወለደ በ፷፯ ዓመቱ በክብር ዐርፏል::
ከሁለቱም መቃብር ላይ ለ፴ ቀናት የብርሃን ምሰሶ ተተክሎ ታይቷል:: ጌታችንም በማይታበል ቃሉ "ስማችሁን የጠራውን: መታሰቢያችሁን ያደረገውንም እምርላቹሃለሁ" ሲል ቃል ኪዳን ገብቶላቸዋል::
† 🕊 ቅዱስ ሐናንያ ሐዋርያ 🕊 †
ሐናንያ ቁጥሩ ከ፸፪ቱ አርድእት ሲሆን መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ስማቸው ተመዝግቦ ከተቀመጠልን ከጥቂቶቹ ዋነኛው ነው:: ከነገደ እሥራኤል ተወልዶ: በሕገ ኦሪት አድጐ: ከወጣትነት ዕድሜው ትንሽ እልፍ ሲል ጌታችን ወንጌልን ማስተማር ጀምሯልና ጠራው:: እርሱም በበጐ ፈቃድ ተከትሎታልና ከ፸፪ቱ አርድእት ደመረው::
ለ፫ ዓመታት ከጌታ እግር ተምሮ: ከዕለተ ስቅለት በፊት ሀብተ ፈውስም ተሰጥቶት ነበር:: ምክንያቱም ቅዱስ ሉቃስ እንደ ጻፈልን ሰብዐው አርድእት "ጌታ ሆይ! አጋንንት በስምህ ተገዙልን" ማለታቸውን አስቀምጦልናል:: [ሉቃ.፲፥፲፯] ቅዱስ ሐናንያ በበዓለ ዕርገት ተባርኮ በ፶ኛው ቀንም መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ ለስብከተ ወንጌል ወጥቷል::
በሚያስተምር ጊዜ የሶርያዋን ደማስቆን ማዕከል አድርጐ ነበር:: በሁዋላም አበው ሐዋርያት የዚህች ከተማ የመጀመሪያው ዻዻስ አድርገው ሹመውታል:: ጌታ ባረገ በ፰ኛው ዓመት ክርስቲያኖችን ያሰቃይ የነበረው ሳውል [የሁዋላው ቅዱስ ዻውሎስ] ወደ ደማስቆ የተጉዋዘው ክርስቲያኖችን በተለይም ቅዱስ ሐናንያን ለማሠር ነበር::
ለእግዚአብሔር ምርጥ ዕቃ ይሆን ዘንድ መብረቅ ዐይኑን አጠፋው:: ወዲያውም ጌታችን ሳውልን ወደ ሐናንያ እንዲሔድ ነው የነገረው:: ከ፫ ቀናት በሁዋላ ጌታችን ለሐናንያ ተገልጦ አነጋግሮታል:: ሳውል [ዻውሎስ] ወደ ሐናንያ የደረሰው በመሪ ነበር::
፪ቱ እንደተገናኙ ቅዱስ ሐናንያ ሳውልን አስተማረው: ፈወሰው: አጠመቀው: በጐ መንገድንም መራው:: በዚህ ምክንያት ቅዱሱ ሐዋርያ የቅዱስ ዻውሎስ የንስሃ አባቱ ይሰኛል:: [ሐዋ.፱፥፩-፲፱]
ከዚህ በሁዋላ ቅዱስ ሐናንያ ለብዙ ዓመታት በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ወንጌልን አስተማረ መከራንም ተቀበለ:: በመጨረሻም በዚህ ቀን ክፉዎች ከብዙ ስቃይ በሁዋላ በድንጋይ ወግረው ገድለውታል::
አምላከ አብርሃ ወአጽብሃ "ድሃ ተበደለ: ፍርድ ተጉዋደለ" የሚል ዳኛ: ሃይማኖቱ የቀና መሪንም ያምጣልን:: የቅዱሳኑን ክብር በእኛ ላይ ያድርግልን::
🕊
[ † ጥቅምት ፬ [ 4 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅዱሳን ነገሥት አብርሃ ወአጽብሃ
፪. ቅዱስ ሐናንያ ሐዋርያ [ከ፸፪ቱ አርድእት]
፫. ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ
፬. ቅዱስ ባኮስ ሰማዕት
፭. ቅዱሳን ባባ እና ማማ
፮. ቅዱስ ዮሐንስ ሕጽው
[ † ወርኀዊ በዓላት ]
፩. ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ
፪. ቅዱስ እንድርያስ ሐዋርያ
፫. ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት
፬. ቅዱስ ዮሐንስ ዘሐራቅሊ [ሰማዕት]
" እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ: ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር: ልመናና ጸሎት: ምልጃም: ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ: ስለ ነገሥታትና መኩዋንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ:: ሰዎች ሁሉ ሊድኑና እውነቱን ወደ ማወቅ ሊደርሱ በሚወድ በእግዚአብሔር በመድኃኒታችን ፊት መልካምና ደስ የሚያሰኝ ይህ ነው:: " [ጢሞ.፪፥፩-፬]

❖ ጥቅምት ፭ [ 5 ] ❖
[ ✞ እንኩዋን ለጻድቁ "አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ" እና "ቅዱስ ኪራኮስ አረጋዊ" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞ ]
† 🕊 አቡነ ገብረ ሕይወት 🕊 †
ጻድቁ የተወለዱት ግብፅ [ንሒሳ አካባቢ] ሲሆን አባታቸው ስምዖን እናታቸው አቅሌስያ ይባላሉ:: አባታችን ገብረ ሕይወት የጻድቃን አለቃ: የቅዱሳን የበላይ: ተጋድሎአቸውና ድንቅ ተአምራቸው እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዛ ቅዱስ ሰው ናቸው::
የጻድቁን ክብር መናገር የሚችል ምን አነደበት ይኖራል? እንደ ምንስ ባለ ብራና ይጻፋል? ዜናቸውንስ ለመስማት የታደለ እንደ ምን ዓይነት ሰው ይሆን?
አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስ ለ፭፻፷፪ [562] ዓመታት በዚህች ዓለም ሲኖሩ እህል ያልቀመሱ [ምግባቸው ምስጋና ነውና]: ልብስ ያልለበሱ [ጠጉር አካላቸውን ይሸፍን ነበርና]: ሐዋርያዊ ሆነው ከግብፅ እስከ ኢትዮዽያ ብዙ ነፍሳትን ያዳኑ አባት: ሃገራችንን አስምረው: አስራት እንድትሆናቸውም ተቀብለው ምድረ ከብድ አካባቢ አርፈዋል::
ጻድቁ ገብረ መንፈስ ቅዱስም: ገብረ ሕይወትም ይባላሉ:: በ፭፻፷፪ [562] ዓመታት ሕይወታቸው እንደ ሐዋርያት ከምድረ ግብጽ እስከ ኢትዮዽያ ወንጌልን ሰብከዋል:: በዚህም በሚሊየን [አእላፍ] ለሚቆጠሩ ነፍሳት የድኅነት ምክንያት ሆነዋል::
ጻድቁ እንደ ሰማዕታትም ከከሃዲ ሰዎች ብዙ መከራን ተቀብለዋል:: እንደ ባሕታውያን ለብዙ መቶ ዓመታት ሰው ሳያዩ ቆይተዋል:: ለየት የሚለው ግን የጽድቅ ሕይወታቸው ነው:: ከእልፍ አዕላፍ አጋንንት ጋር ተዋግተው ድል ማድረግ ችለዋልና::
የንሒሳው ኮከብ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ለኢትዮዽያ ልዩ ፍቅር አላቸው:: ስለ ሃገሪቱና ሕዝቧ ፍቅር ሲሉ ለ፻ [100] ዓመታት በደብረ ዝቁዋላ መከራን ተቀብለዋል:: ምሕረትን ሲለምኑ ሥጋቸው አልቆ በአጥንታቸው ቁመው ነበርና ሃገራችን አሥራት ሆና ተሰጠቻቸው::
ስለዚህም ነው በሃገሪቱ ውስጥ ከ፳፻ [2,000] በላይ የጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳማትና አድባራት ዛሬም ድረስ ያሉት:: በ፰ [8] ኛው ክ/ዘመን አካባቢ የተወለዱት አባታችን ያረፉት በ፲፬ [14] ኛው መቶ ክ/ዘመን አካባቢ ነው:: ፍጥረታትን ሁሉ አዘው መጋቢት ፭ [5] ቀን ሲያርፉ ግሩማን መላእክት ገንዘው አካላቸውን ሠውረዋል::
ሥላሴን የተሸከመ አካላቸው በጐልጐታ ተቀብሯል የሚሉም አሉ::
"ሰላም ለመቃብሪከ ዘኢተከሥተ ለባዕድ:
ከመ መቃብሩ ለሙሴ ወልደ ዮካብድ:
ዜና መቃብሪከሰ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ጸማድ:
ቦ ዘይቤ በኢየሩሳሌም አጸድ:
ወቦ ዘይቤ ኀለወ በከብድ::" እንዲል::
የጻድቁ በዓል ጥቅምት ፭ [ 5 ] ቀን የሚከበረው ብዙ ጊዜ መጋቢት ፭ [ 5 ] ዐቢይ ጾም ውስጥ ስለሚውል ተውላጥ [ቅያሪ] ሆኖ ነው::
† 🕊 ቅዱስ ኪራኮስ አረጋዊ 🕊 †
ይህ ቅዱስ አባት ስም አጠራሩ የከበረ: ሽምግልናውም ያማረ ነው:: ብዙዎቻችን የምናውቀው በበዓለ መስቀል ስሙ ተደጋግሞ ሲጠራ ነው:: ግን ይህ ታላቅ ሰው ለቅድስት እሌኒ መካነ መስቀሉን አሳያት ከሚል አረፍተ ነገር የዘለለ ታሪኩ ሲነገርለት ብዙ ጊዜ አንሰማምና እስኪ በዕለተ ዕረፍቱ ስለ ቅዱሱ ጥቂት እንበል::
ቅዱስ ኪራኮስ የተወለደው በ፫ [3] ኛው መቶ ክ/ዘመን ሲሆን እናቱ ቅድስት ሐና ትባላለች:: በእጅጉ የተባረከች ሴት ናት:: ምንም በነገዳቸው አይሁድ ቢሆኑም የዘመኑ የአይሁድ ክፋት አልገዛቸውም:: የተባረከች እናቱ ታሪክ እያስጠናች ከማሳደጉዋ ባለፈ አስቀድማ ኦሪቱን: ነቢያቱን እንዲያውቅ አደረገች::
አስከትላም ሕገ ክርስትናን እንዲረዳ አደረገችው:: የታሪክና የመጻሕፍት ምሑሩ ቅዱስ ኪራኮስ ከእናቱ ጋር ሆኖ እግዚአብሔርን እያገለገለ: ክርስቶስን እያመለከ ቆየ:: በዚህ ጊዜ ግን እድሜው እየገፋ ነበር::
ሠለስቱ ምዕት [፫፻፲፰ [318] ቱ ሊቃውንት] ጉባኤያቸውን ከፈጸሙ በሁዋላ ቅድስት እሌኒም መስቀሉን ፍለጋ ስትወጣ ትልቁ ፈተናዋ የተቀበረበትን ቦታ ማወቅ አለመቻሏ ነበር:: እንዲያውም አማራጭ ስታጣ በአካባቢው የነበሩ አይሁድን ምሥጢር እንዲያወጡ ቀጥታቸው ነበር:: በሁዋላ ግን ኪራኮስ ስለሚባል ደግ ታሪክ አዋቂ ሰው ሰምታ ተገናኙ::
ቅዱስ ኪራኮስም አባቶቹ አይሁድ ናቸውና አካባቢውን ያውቀው ነበር:: ችግሩ ቆሻሻው ተራራ በመሆኑ ከ፫ [3] ቱ የትኛው እንደ ሆነ አለመታወቁ ነበር:: ቅዱሱ ግን ለዚህም መፍትሔ ነበረውና "ደመራ ደምረሽ: በእሳት አቃጥለሽ: እጣን ጨምሪበትና ይገለጥልሻል" አላት::
ቅድስት እሌኒም የተባለችውን በትክክል ፈጽማ የመድኅን ክርስቶስን ቅዱስ ዕጸ መስቀል አገኘች:: ቅድስት እሌኒ ወደ ሃገሯ ከተመለሰች በሁዋላም ቅዱስ ኪራኮስ በኢየሩሳሌም አካባቢ ዻዻስ ሆኖ ተሾመ::
አረጋዊው ቅዱስ የሚገርም እረኛ ነውና የባዘኑትን ሲፈልግ: በቤቱ ያሉትንም ሲያጸና ብዙ ደከመ:: በቅርቡ ያሉትን በአፉ: የራቁትን ደግሞ በጦማር [በመልእክት] አስተማረ:: በወቅቱ በአካባቢው ኤልያኖስ የሚሉት ከሃዲ ንጉሥ ነበርና በቅዱስ ኪራኮስ ላይ ተቆጣ::
ወደ እርሱ አስጠርቶ በአደባባይ: ቅዱስ ቃሉን ይጽፍበት የነበረው ቀኝ እጁን አስቆረጠው:: ቅዱስ ኪራኮስ ግን እጁ መሬት ላይ ወድቃ: ደሙ እየተንጠፈጠፈ ተናገረ :- "አንተ ልብ የሌለህ ንጉሥ! እጄን ቆርጠህ ከክርስቶስ ፍቅር ልትለየኝ አትችልም" አለው::
በዚህ የተበሳጨ ንጉሡ እሳት አስነድዶ: አልጋውን አግሎ ቅዱሱን ጠበሰው:: ኪራኮስ ግን በእሳቱ ላይ ሳለ ወደ እሥራኤል ፈጣሪ በእብራይስጥኛ ጸለየ:: በማግስቱ እናቱን ቅድስት ሐናን አምጥተው የነደደ እሳት ውስጥ ጣሏት::
ለ፫ [3] ሰዓት ያህል በእሳት ውስጥ ስትጸልይ ቆይታ በጦር ወግተው ገደሏት:: ቅዱስ ኪራኮስንም ለአራዊት ሰጡት:: አራዊቱ ሰገዱለት:: በሌሎች ዓይነት ስቃዮችም ፈተኑት: ግን እንቢ አላቸው:: በመጨረሻው በዚህ ቀን ገድለውት የክብርን አክሊል ተቀዳጅቷል::
አምላከ ቅዱሳን በእነርሱ ላይ የበዛች ፍቅሩን ለእኛም ያድለን:: ፍሬ ትሩፋት: ፍሬ ክብር እንድናፈራም ይርዳን:: ክብራቸውንም አያጉድልብን::
🕊
[ † ጥቅምት ፭ [ 5 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ጻድቅ
፪. ቅዱስ ኪራኮስ አረጋዊ [ዻዻስ ወሰማዕት]
፫. ቅድስት ሐና ሰማዕት [እናቱ]
፬. ቅዱስ ያዕቆብ ወልደ እልፍዮስ [ከ፲፪ቱ ሐዋርያት]
፭. አባ ዻውሎስ ሰማዕት [አርዮሳውያን አንቀው የገደሉት አባት]
[ † ወርሐዊ በዓላት ]
፩. ቅዱስ ዼጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት
፪. ቅዱስ ዻውሎስ ብርሃነ ዓለም
፫. ቅዱስ ዮሐኒ ኢትዮዽያዊ
፬. ቅዱስ አሞኒ ዘናሒሶ
፭. ቅድስት አውጋንያ [ሰማዕትና ጻድቅ]
" ነገር ግን ዓለም ለእኔ የተሰቀለበት: እኔም ለዓለም የተሰቀልሁበት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ:: በክርስቶስ ኢየሱስ አዲስ ፍጥረት መሆን ይጠቅማል እንጂ መገረዝ ቢሆን ወይም አለመገረዝ አይጠቅምምና:: " [ገላ.፮፥፲፬] (6:14)