Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (ባሕራን)
†
🕊 💖 ሰ ላ ም ታ 💖 🕊
❝ ክርስቶስ ተንስአ እሙታን
▸ በዐቢይ ኃይል ወስልጣን ፤
አሠሮ ለሰጣን
▸ አግዐዞ ለአዳም ፤
ሰላም
▸ እምይእዜሰ ፤
ኮነ
▸ ፍስሐ ወሰላም ❞
🕊
❝ ክርስቶስ በታላቅ ኃይልና ስልጣን ከሙታን ተነሳ ፤ ሰይጣንን አሰረው ፤ አዳምንም ነጻ አወጣው ፤ ስለዚህም ከእንግዲህ ወዲህ ፍፁም ሰላም እና ደስታ ሆነ።
▬▬▬▬▬▬ † ▬▬▬▬▬▬
[ 🕊 እነሆ ሁሉም አዲስ ሆነ ! 🕊 ]
† † †
💖 🕊 💖
❝ አርአየ ሥልጣኖ ላዕለ ሞት ንጉሠ ነገሥት ወእግዚኣ ኣጋእዝት አርአየ ሥልጣኖ ላዕለ ሞት ኦ ትዕግሥት ወአርምሞ በፍቅረ ዚአነ በጽሐ እስከ ለሞት አርአየ ሥልጣኖ ላዕለ ሞት ወንሕነኒ ንግበር በዓለነ ቅድስተ ፋሲካ በሐሴት አርአየ ሥልጣኖ ላዕለ ሞት ገባሬ ሕይወት ክርስቶስ ❞
[ በሞት ላይ ሥልጣኑን አሳየ ፣ የነገሥታት ንጉሥ የጌቶች ጌታ በሞት ላይ ሥልጣኑን አሳየ ፣ ... ወዮ ትዕግሥትና ዝምታ ፣ እኛን ከመውደዱ የተነሣ እስከ መሞት ደረሰ ፣ በሞት ላይ ሥልጣኑን አሳየ፣ እኛም የተቀደሰች በዐላችንን ፋሲካን [ ትንሣኤን ] በደስታ እናክብር ፣ ሕይወትን የሠራ [ የፈጠረ ] ክርስቶስ በሞት ላይ ሥልጣኑን አሳየ። ]
-------------------------------------------------
[ ድጓ ዘፋሲካ ]

[ † እንኳን ለኃያሉ ሰማዕት ቅዱስ ብሶይ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! †
🕊 † ቅዱስ አባ ብሶይ ሰማዕት † 🕊
† ቅዱሱ አባታችን ከዘመነ ሰማዕታት ጣፋጭ ፍሬዎች አንዱና ግንባር ቀደሙ ነው::
† ጥንተ ነገሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ :-
በ፫ [3] ኛው መቶ ክ/ዘመን ማጠናቀቂያ አካባቢ ታግሕስጦስና ክሪስ የሚባሉ ክርስቲያኖች ነበሩ:: በቀናው የጽድቅ ጐዳና ቢኖሩም ከጋብቻ በኋላ ለአሥራ ሰባት ዓመታት መውለድ አልቻሉም::
የአሥራ ሰባት ዓመት ልመናቸውን የተመለከተ እግዚአብሔር ቅዱስ ገብርኤልን ልኮ አበሰራቸው:: "ሕፃኑ ለሰማዕትነት ተመርጧልና ብሶይ በሉት" አላቸው:: ብሶይ በተወለደ በሰባት ዓመቱ ወላጆቹ ይማር ብለው ወደ ገዳም ወሰዱት:: በገዳም ውስጥ መጻሕፍትን አጥንቶ ዲቁናን ተሾመ:: ወደ ዓለም ተመለስ ቢሉትም እንቢ አለ::
ከባልንጀራው ቅዱስ ጴጥሮስ ጋር ለሃያ አንድ ዓመታት በድንግልና : በተጋድሎ : ጾምና ጸሎትን እያዘወተሩ ኖሩ:: ቅዱስ ብሶይ ሃያ ስምንት ዓመት በሞላው ጊዜ መልአኩ የተናገረው የትንቢት ዘመን ደረሰ:: በርካታ ምዕመናን ክርስቲያን በመሆናቸው ብቻ ታረዱ:: ወደ እሳትም ተጣሉ:: ሞትን የፈሩ ደግሞ በየዱር ገደሉ ተሰደዱ::
ቅዱስ ብሶይም በሚያውቁት ሰዎች ተከሶ ለፍርድ ቀረበ:: ድንገት ከሰማይ ፍጡነ ረድኤት ወሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ደረሰለት:: "አይዞሕ! እኔ እስከ መጨረሻው ከአንተ ጋር ነኝ" አለው::
የጦር መኮንኑ ክርስቶስን እንዲክድ አባበለው:: ቅዱሱ ግን ጣዖታቱ የአጋንንት ማደሪያ መሆናቸውን በገሃድ ነገረው:: መኮንኑ ቢበሳጭ ወታደሮቹ እንዲጨምቁት አዘዘ:: ደሙ እየወረደ ገረፉት:: በፊትና በኋላ ብረት አድርገው ሥጋውን ጨፍልቀው እሥር ቤት ውስጥ ጣሉት:: ሊቀ መላእክት መጥቶ ዳስሶ አዳነው::
መኮንኑ እርሱን ማሰቃየት ደከመው:: የቅዱሳን ሕይወት ግርም ይላል:: ተገራፊው እያለ ገራፊው : ስቃዩን የሚቀበለው እያለ አሰቃዩ ይደክመዋል::
† ይሕንን መሰለኝ አባ ጽጌ ድንግል :-
"እመዐዛ ጽጌኪ ድንግል ውስተ ዐውደ ስምዕ ዘሰክረ::
ውግረተ አዕባንኒ ይመስሎ ሐሰረ::
እሳትኒ ማየ ባሕር ቆሪረ" ያለው::
ቅዱስ ብሶይን ከአንዱ መኮንን ወደ ሌላው እያመላለሱ አሰቃዩት:: አካሉን ቆራረጡት:: ዓይኑን በጋለ ብረት አወጡት:: በምጣድ ቆሉት:: በጋን ውስጥ ቀቀሉት:: እርሱ ግን በፈጣሪው ፍቅር የጸና ነውና ሁሉን ታገሰ:: በነዚሕ ሁሉ የስቃይ ዓመታት ቁራሽ ዳቦ እንኳ አላቀመሱትም:: በረሃብ ቀጡት እንጂ:: ለእርሱ ግን ምግቡ የክርስቶስ ስም ነበር::
በመጨረሻ ንጉሡ ዲዮቅልጢያኖስ አንገቱን በሰይፍ አስመታው:: ሥጋውንና የተቆረጠ አንገቱን ገንቦ [ጋን] ውስጥ ከቶ ጣለው:: የቅዱሱን አካል የያዘችው ጋን ግን በእግዚአብሔር ቸርነት : ማንም ሳይሸከማት ከመሬት ከፍ አለች:: ለሃያ ቀናት ተጉዛ ከሶርያ ግብጽ [ቦሃ] ደረሰች:: ክርስቲያኖች ተቀብለው ሲከፍቷት የቅዱስ ብሶይ ራሱና አንገቱ ተጣብቆ ተገኝቷል:: በክብርም አሳርፈውታል::
🕊 † ቅዱስ ያዕቆብ † 🕊
† ዳግመኛ በዚሕ ቀን ጻድቅና ተአማኒ [ታማኝ] የተባለ የምሥራቅ ሰው ቅዱስ ያዕቆብ መታሠቢያ ይደረግለታል::
ቅዱስ ያዕቆብ ቁስጥንጥንያ አካባቢ በርሃ ውስጥ ይኖር የነበረ አባት ነው:: ከቅድሰና ሕይወቱ ባሻገር በደፋርነቱ [ጥብዐቱ] ይታወቃል:: በ ፫፻፵ [340] ዎቹ ዓ/ም ታናሹ ቆስጠንጢኖስ አርዮሳዊ በሆነ ጊዜ ይሔ አባት በይፋ ገስጾታል::
በዚህም ምክንያት መከራን ተቀብሏል:: ታስሯል:: ተገርፏል:: እግዚአብሔርም መናፍቁን ንጉሥ ለጦርነት በወጣበት ቀስፎታል:: ቅዱሱ በዚህች ቀን ዐርፎ ወደ ወደደው ክርስቶስ ሔዷል::
† ቸር አምላክ ከሰማዕቱ ቅዱስ ብሶይ እና ከቅዱስ ያዕቆብ በረከት ያሳትፈን:: በምልጃቸውም ይቅር ይበለን::
[ † ሰኔ ፭ [ 5 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. ቅዱስ አባ ብሶይ [ኃያል ሰማዕት]
፪. ቅድስት ማርታ ለባሲተ ክርስቶስ (በቅድስናዋ የተወደሰች : በስደት ያረፈች እናት ናት::]
፫. ቅዱስ ያዕቆብ ምሥራቃዊ
፬. ቅዱስ ቢፋሞን ሰማዕት
፭. ቅዱስ መቃርስ ሰማዕት
፮. ቅዱስ መርቆሬዎስና ማኅበሩ [ሰማዕታት]
[ † ወርኀዊ በዓላት ]
፩. ቅዱስ ጴጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት
፪. ቅዱስ ጳውሎስ ሐዋርያ
፫. አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
፬. ቅዱስ ዮሐኒ ኢትዮጵያዊ
፭. ቅዱስ አሞኒ ዘናሒሶ
፮. ቅድስት አውጋንያ [ሰማዕትና ጻድቅ]
† "ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ : ወይስ ጭንቀት : ወይስ ስደት : ወይስ ራብ : ወይስ ራቁትነት : ወይስ ፍርሃት : ወይስ ሰይፍ ነውን?
" ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን:: እንደሚታረዱ በጐች ተቈጠርን" ተብሎ እንደ ተጻፈ ነው:: በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን:: " † [ሮሜ.፰፥፴፭-፴፰]
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬

✞ እንኩዋን ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ዕርገት በሰላም አደረሳችሁ ✞
🕊 ዕርገተ እግዚእ 🕊
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በዓለ ዕርገትን ፪ [2] ጊዜ ታከብራለች:: አንዱ "ጥንተ በዓል": ሁለተኛው ደግሞ "የቀመር በዓል" ይሠኛል:: ጥንተ በዓል ማለት ጌታችን በትክክል ያረገበትን ቀን ያመለክታል::
የክብር ባለቤት መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ በኪነ ጥበቡ [በሕማሙ: በሞቱ] ዓለምን አድኖ: ፵ [40] ቀን ለሐዋርያቱ መጽሐፈ ኪዳንን: ትምሕርተ ኅቡዓትን አስተምሯቸዋል::
በ፵ [40] ኛው ቀን ፻፳ [120] ውን ቤተሰብ ይዟቸው ወደ ቢታንያ ወጣ:: በዚያም እስከ ሊቀ ዽዽስና ድረስ ሾሟቸው: ከኢየሩሳሌም እንዳይወጡም አዟቸው የመንፈስ ቅዱስን ተስፋ ጠብቁ ብሏቸዋል:: እየባረካቸው በተዋሐደው ሥጋ ወደ ሰማያዊ ዙፋኑ አርጉዋል::
ሰማያት: ምድር: ደመናት: ነፋሳት: መባርቅትና መላእክት: ፍጥረት በሙሉ አመስግኗል:: አይሁድ መናፍቃን እርገቱን ምትሐት ነው እንዳይሉ: ጌታችን ትንሳኤውን አማናዊ እንደሆነ ለማስረዳት በ፵ [40] ኛው ቀን ዐረገ::
አንድም ራስ ባለበት ሌሎች የሰውነት ክፍሎች ሊኖሩ ይገባልና ጌታችን ዕርገቱን በገሃድ አደረገው:: "ዐርገ እግዚእ ከመ ያለቡ ዕርገተ ጻድቃን ንጹሐን" እንዲል::
" ዐርገ እግዚአብሔር በይባቤ:: ወእግዚእነ በቃለ ቀርን:: ዘምሩ ለአምላክነ ዘምሩ::" [መዝ.፵፮፥፮] (46:6)
ከበረከተ ዕርገቱ ይክፈለን::
"እስከ ቢታንያም አወጣቸው:: እጆቹንም አንስቶ ባረካቸው:: ሲባርካቸውም ከእነርሱ ተለየ:: ወደ ሰማይም ዐረገ:: እነርሱም ሰገዱለትና በብዙ ደስታ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ:: ዘወትርም እግዚአብሔርን እያመሰገኑና እየባረኩ በመቅደስ ኖሩ::" [ሉቃ.፳፬፥፶] (24:50-53)

" እግዚአብሔር በመለከት ድምፅ ዐረገ ! "
---------------------------------------------
💖 እንኳን ለበዓለ ዕርገት በሰላም አደረሰን ! 💖
" አምላክ በእልልታ ፥ እግዚአብሔር በመለከት ድምፅ ዐረገ። ዘምሩ ፥ ለአምላካችን ዘምሩ ፤ ዘምሩ ፥ ለንጉሣችን ዘምሩ።
እግዚአብሔር ለምድር ሁሉ ንጉሥ ነውና ፤ በማስተዋል ዘምሩ። እግዚአብሔር በአሕዛብ ላይ ነገሠ ፤ እግዚአብሔር በቅድስናው ዙፋን ይቀመጣል። [መዝ.፵፯፥፭፥፰]
▬▬▬▬▬▬ † ▬▬▬▬▬▬
† [ ዕርገት ] = ሰኔ ፮ [ 6 ] ይሆናል።
† [ ጰራቅሊጦስ ] = ሰኔ ፲፮ [ 16 ] በዓለ ጰራቅሊጦስ ይውላል ።
† [ ፆመ ሐዋርያት ] = ሰኔ ፲፯ [ 17 ] ይገባል ።
† [ የጾመ ድህነት ] = ሰኔ ፲፱ [ 19 ] ይገባል።
† † †
💖 🕊 💖
" እግዚአብሔር በመለከት ድምፅ ዐረገ ! "
---------------------------------------------
💖 እንኳን ለበዓለ ዕርገት በሰላም አደረሰን ! 💖
" አምላክ በእልልታ ፥ እግዚአብሔር በመለከት ድምፅ ዐረገ። ዘምሩ ፥ ለአምላካችን ዘምሩ ፤ ዘምሩ ፥ ለንጉሣችን ዘምሩ።
እግዚአብሔር ለምድር ሁሉ ንጉሥ ነውና ፤ በማስተዋል ዘምሩ። እግዚአብሔር በአሕዛብ ላይ ነገሠ ፤ እግዚአብሔር በቅድስናው ዙፋን ይቀመጣል። [መዝ.፵፯፥፭፥፰]
▬▬▬▬▬▬ † ▬▬▬▬▬▬
† [ ዕርገት ] = ሰኔ ፮ [ 6 ] ይሆናል።
† [ ጰራቅሊጦስ ] = ሰኔ ፲፮ [ 16 ] በዓለ ጰራቅሊጦስ ይውላል ።
† [ ፆመ ሐዋርያት ] = ሰኔ ፲፯ [ 17 ] ይገባል ።
† [ የጾመ ድህነት ] = ሰኔ ፲፱ [ 19 ] ይገባል።
† † †
💖 🕊 💖
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (ባሕራን)
†
🕊 💖 ሰ ላ ም ታ 💖 🕊
❝ ክርስቶስ ተንስአ እሙታን
▸ በዐቢይ ኃይል ወስልጣን ፤
አሠሮ ለሰጣን
▸ አግዐዞ ለአዳም ፤
ሰላም
▸ እምይእዜሰ ፤
ኮነ
▸ ፍስሐ ወሰላም ❞
🕊
❝ ክርስቶስ በታላቅ ኃይልና ስልጣን ከሙታን ተነሳ ፤ ሰይጣንን አሰረው ፤ አዳምንም ነጻ አወጣው ፤ ስለዚህም ከእንግዲህ ወዲህ ፍፁም ሰላም እና ደስታ ሆነ። ❞
▬▬▬▬▬▬ † ▬▬▬▬▬▬
[ 🕊 እነሆ ሁሉም አዲስ ሆነ ! 🕊 ]
† † †
💖 🕊 💖
🕊 እንኳን ለበዓለ ዕርገት በሰላም አደረሰን 🕊
"ወሶበ ተንሥአ ዐርገ ውስተ ሰማያት ወዘኒ ወረደ ዘእንበለ ሥጋ ውእቱ ዘዐርገ ሥግወ ወአሐዱ ውእቱ ዘእምቅድስት ሥላሴ ወኢወሰከ ኍልቆ ራብዐየ ወኢካልዐ ገጸ ወነበረ በየማነ አብ ፤
[ ከተነሣም በኋላ ወደ ሰማይ ዐረገ። ሥጋ ሳይይዝ የመጣ እርሱ ሰው ሆኖ ዐረገ። ከሦስቱ አካላት አንዱ አካል እርሱ ነው። ለሥላሴ አራተኛ ለቃል ሁለተኛ አልሆነም። በአብ ዕሪና ኖረ፤ ]
[ ቅዱስ ባስልዮስ ]
ከበዓሉ ረድኤት በረከት ይክፈለን አሜን።

Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (ተአምኆ ቅዱሳን)
❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #ሰኔ ፯ (7) ቀን።
❤ እንኳን #አምላክን_ለወለደች_ለእመቤታችን #ለድንግል_ማርያም_ቤተ ክርስቲያን_ለተከፈተበትና ለከበረችበት፣ ቀሊን ከምትባል አገር ቅዱስና ቡሩክ ድል አድራጊም ለሆነ #ለአባ_አበስኪሮን_ሰማዕትነት ለተቀበሉበት #ለዕረፍታቸው_በዐል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚህ ቀን ከሚታሰቡ፦ መኰንን አርማንዮስ ካሠቃያቸው #ከአስራ_ስድስት_ሺህ_ሰማዕታት ከዕረፍታቸው መታሰቢያና ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝️ ✝️ ✝️
#በዚች_ዕለት_አምላክን_የወለደች_የእመቤታችን_የድንግል_ማርያም_ቤተ_ክርስቲያን_የተከፈተበትና_የከበረችበት ነው። እርሷም ዌላ በሚባል አደባባይ ያለች ሦስት ዓመት ከስድስት ወር ተዘግታ የኖረች ነበረች። ይኸውም በአንድ ሽህ ሃያ ዓመተ ሰማዕታት ነው። ከእመቤታችን ድንግል ማርያም ሰው ለሆነ ሕይወትና መድኃኒት አድርጎ እርሷን ለሰጠን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን ለዘላለሙ አሜን።
✝️ ✝️ ✝️
❤ #አባ_አበስኪሮስ፦ ይህም ቅዱስ ከእንዴናው ገዥ ከአርያኖስ ጭፍራ ውስጥ ነበር የከሀዲው ንጉሥ የዲዮቅልጥያኖስ ስለ አምልኮ ጣዖት የሆነች ትእዛዝ በደረሰችው ጊዜ። ወዲያውኑ ይህ በሕዝብ መካከል ተነሥቶ ንጉሡን ረገመው ጣዖታቱንም ሰደበ ወታደር ስለ ሆነም ያሠቃየው ዘንድ ማንም አልደፈረም ነገር ግን በንጉሥ አዳራሽ ውስጥ አሠሩት።
❤ መኰነንኑም ወደ አገረ አስዩጥ በሔደ ጊዜ ወደ ንጉሥ ላከው ከእርሱም ጋራ ሌሎች ወልደፍዮስ፣ አርማንዮስ፣ አርኪያስ፣ ጴጥሮስና ቀራንዮስ የተባሉ ነበሩ እሊህም ክብር ይግባውና ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደማቸውን ሊአፈሱ ከአባ አበስኪሮስ ጋር ተስማሙ። በንጉሡም ፊት በቆሙ ጊዜ በጌታችን ታመኑ ንጉሡም ትጥቃቸውን ይቆርጡ ዘንድ በየአይነቱ በሆነ ሥቃይም እንዲአሠቃዩአቸው አዘዘ ንጉሡ እንዳዘዘም አደረጉባቸው። ከእኒህ ከአምስቱ ግን ራሶቻቸውን የቆረጡአቸው አሉ የሰቀሉአቸውም አሉ እንዲህም ገድላቸውን ፈጽመው የሕይወት አክሊል ተቀበሉ።
❤ የከበረ አበስኪሮስን ግን ታላቅ ግርፋትን እንዲገርፉት አዘዘ ከዚያም በኋላ ከራሱ እስከ አንገቱ ቆዳውን እንዲገፉ በፈረስ ጅራትም አሥረው በከተማው ውስጥ እንዲጐትቱት አዘዘ። ይህንም ሁሉ አደረጉበት። ከዚህም በኋላ በብረት ምጣድ ውስጥ አድርገው በላዩ አፉን ዘግተው ተሸክመው ወስደው በውሽባ ቤት ማንደጃ ውስጥ ጨመሩት በሥቃዩም ውስጥ ሁሉ የእግዚአብሔር መልአክ ወደርሱ ይመጣና ያጽናናው ነበር ያስታግሠውም ነበር ያለ ምንም ጉዳት አድኖ በደኅና ያስነሣው ነበር።
❤ ከማሠቃየቱም በደከመ ጊዜ ከሥራየኞች ሁሉ የሚበልጥ በሥራዩም ወደ አየር ወጥቶ ከአጋንንት ጋራ የሚነጋገር ሥራየኛ አመጣለት። እርሱም የውሽባ ቤቱን ዘግተው ሽንት እንዲረጩበት አዘዘ እንዲሁም አደረጉ። እባብንም ይዞ በላዩ አሾከሾከና ለሁለት ክፍልም ሁኖ ተሠነጠቀ መርዙንና ሆድ ዕቃውን ወስዶ በብረት ወጭት አድርጎ አበሰላቸው በውሽባ ቤቱ ውስጥ ወደ አባ አበስኪሮን አቅርቦ ያንን መርዝ ይበላ ዘንድ ሰጠው ቅዱሱም በላ ግን ምንም ምን ጉዳት አልደረሰበትም። ያም መሠርይ "የመኳንንተ ጽልመት አለቃቸው ሆይ በዚህ ክርስቲያናዊ ላይ ኃይልህን አድርግ" ብሎ ጮኸ ምንም ምን ጥፋት ባልደረሰበት ጊዜ መሠርዩ አደነቀ። ቅዱስ አበስኪሮንም መሠርዩን "የሚራዳህ ሰይጣንህስ በክብር ባለበት በጌታዬ በኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል አንተን ይቀጣሃል" አለው። ወዲያውኑ ጥሎ የሚያንከባልለው ክፉ ሰይጣን ተጫነበት ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እስከ ታመነ ድረስ አሠቃየው። መኰንኑም የመሠርዩን ራስ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘና በሰማዕትነት ሞተ። በቅዱስ አበስኪሮን ላይ ግን ቁጣና ብስጭትን በመጨመር ጽኑዕ ሥቃይን አሠቃየው አባለ ዘሩንም እንዲቆርጡ አዘዘ እርሱ ግን በመከራው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመሰግን ነበር። ከዚህም በኋላ ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘና ሰኔ 7 ቀን ቆረጡት የድል አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ።
❤ ከቅዱስ አበስኪሮን ተአምራትም አንዱን እንነግራችኋለን በግብጽ ደቡብ በስሙ የታነፀች ቤተ ክርስቲያን ነበረች ካህናቷም ክፉ ሥራ የሚሠሩ ክፉዎች ነበሩ ቅዱስ አበስኪሮንም ከክፋታቸው ተመልሰው ንስሓ ቢገቡ ብሎ ጠበቃቸው። ባልተመለሱ ጊዜ ግን የንዳድ በሽታ አምጥቶ ሁሉም በአንዲት ጊዜ ሞተ።
❤ ከዚህም በኋላ ቅዱስ አበስኪሮን በፈረስ ተቀምጦ የላዕላይ ግብጽ የሆነች ብያሁ ወደምትባል አገር ደረሰ የአገር ሰዎችም በደጃቸው ተቀምጠው ሳይተኙ በጨረቃ ብርሃን እርስ በርሳቸው ያወሩ ነበር። የከበረ አበስኪሮንም ከፊታቸው ደርሶ "ሰላም ለእናንተ ይሁን" አላቸው በአዩትም ጊዜ የሰላምታውን አጸፋ እየመለሱ ተነሥተው ተቀበሉት ሁለተኛም "ያቺን የሚሻትን ምድር እያመለከታቸው ከምድራችሁ ጥቂት እንድትሰጡኝ እሻለሁ" አላቸው። እነርሱም "ጌታችን እንደወደድክ ይሁንልህ" አሉት መቶ የወርቅ ዲናርም ሰጥቷቸው ተሠወራቸው። እነርሱም ከዚህ ራእይ የተነሣ አደነቁ።
❤ ከተኙ በኋላም ቤተ ክርስቲያኒቱን አፍልሶ ከግብጽ ደቡብ ወደ ላይ ግብጽ ብያሁ ወደምትባል አገር በመቶ የወርቅ ዲናር ወደ ገዛት ምድር ከንዋየ ቅዱሳቷ ሁሉና ከዐፀዷ ጋር አምጥቶ በዚያ አቆማት። የአገር ሰዎችም በጥዋት ነቅተው ወደ ውጭ በወጡ ጊዜ ቤተ ክርስቲያቱን በደጃቸው አገኙዋት እጅግ ፈጽሞም አደነቁ ምስጉን እግዚአብሔርንም አመሰገኑት። ከዚያች ጊዜ ጀምሮ ድንቅ ተአምር የሚደረግባት ሆነ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በሰማዕቱ በአባ በአበስኪሮን ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሰኔ 7 ስንክሳር።
✝️ ✝️ ✝️
❤ "#ሰላም_ዕብል_ለርኅወተ_ቤትኪ_ዮም። ከመ ኤልያስ አርኀወ ኆኅተ ዝናም። በስሱ አውራኅ ወበሠላስ ዓም። ማርያም ሥመሪ አርኅዎቶ ለሕሊናየ ሕቱም። ከመ ላዕሌሁ ይትከዐው ምስለ ጽድቅ ሰላም"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የሰኔ 7።
✝️ ✝️ ✝️
❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "ያበድሮን እግዚአብሔር ለአናቅጸ ጽዮን። እምኵሉ ተዓይኒሁ ለያዕቆብ። ነኪር ነገሩ በእንቲአኪ ሀገረ እግዚአብሔር"። መዝ 86፥2-3። የሚነበቡት መልዕክታት 2ኛ ቆሮ 6፥11-ፍ.ም፣ 1ኛ ጴጥ 1፥6-10 እና የሐዋ ሥራ 12፥10-21። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 17፥14-22። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታችን ማርያም ቅዳሴ ነው፡፡ መልካም በዓል የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም በዐልና የበዓለ ሃምሳ ጊዜ። ለሁላችንም ይሁንልን።
@sigewe
https://www.tg-me.com/joinchat-AAAAAFGQ22bI0Ij80hYpFA
https://www.facebook.com/profile.php?id=100063896616886

Telegram
ተአምኆ ቅዱሳን ወግጻዌ (የቅዱሳን ሰላምታ) Teamho Kidusan Wegtsawe (Yekidusa Selamta)
❤ በየቀኑ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በስንክሳር የሚታሰቡ የቅዱሳን ታሪክ፣ የኢትዮጵያኑ ቅዱሳን በየበዐላቸው ቀን አስደናቂ፣ አስገራሚ ገድላቸው፣ ቃል ኪዳናቸው፣ የቅዱሳን ሰላምታ፣ የየቀኑ የቅዳሴ መልዕክታ፣ የሐዋርያት ሥራ፣ የወንጌል ጥቅስ እና ምስባክ ይቀርብበታል።
❤ የፌስቡክ አድራሻዬ ሊንክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100063896616886
❤ የፌስቡክ አድራሻዬ ሊንክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100063896616886
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (ተአምኆ ቅዱሳን)
❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ ሰኔ ፯ (7) ቀን።
❤ እንኳን #ለኢትዮጵያዊው_ጻድቅ ለታላቁ አባት #አቡነ_ተክለ_ሃይማኖት_ከሾሟቸውና_በሀገራችን ለስብከተ ወንጌል ካሰማሯቸው #ከ47ቱ ቅዱሳን አንዱ ለሆኑት #ለአቡነ_ማቴዎስ_ዘእንደርታ_ለዕረፍታቸው መታሰቢያ በዐልና ለታላቁ አባት #ለጻድቁ_ለሐዋርያም ለደራሲም ለመላእክት በዐል የሚቀደሰው ከ14_ቅዳሴ አንዱ የሆነ በስሙ የተሰየመው ቅዳሴ ለደረሰ ለተከራካሪ መምህርም #ለያዕቆብ_ዘሥሩግ_ለዕረፍት_በዐል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።
✝️ ✝️ ✝️
❤ #አቡነ_ማቴዎስ፦ እኚህ ጻድቅ ትውልድ አገራቸው እንደርታ ሲሆን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ከሾሟቸውና በሀገራችን ለስብከተ ወንጌል ካሰማሯቸው ከ 47ቱ ቅዱሳን ውስጥ አንዱ ናቸው። ጻድቁ መላ ሰውነታቸው እንደ እሳት ያቃጥል ነበር። ወንጌልን በመስበክና በተአምራታቸው ድውያንን እየፈወሱ ብዙ ያገለገሉ ታላቅ አባት ናቸው። መዝገበ ቅዱሳንና ቅዱሳን በዓላት ላይ።
✝️ ✝️ ✝️
❤ #አቡነ_ያዕቆብ_ዘሥሩግ፦ አገሩ ሶርያ ሲሆን አባቱ ሊቀ ካህናት ነበር። በኤጲስ ቆጶስነት የተሾመባት አገር በጤግሮስና በኤፍራጥስ መካከል በምትገኝ ሥሩግ በምትባል አገር ስለሆነ ያዕቆብ ዘሥሩግ ተባለ። በ 3 ዓመቱ እናቱ ቤተ መቅደስ ስትወስደው መልአክ እጁን ይዞ በሊቀ ጳጳሱ እጅ እንዲቆርብ አድርጎታል። በዚህም ጊዜ ምሥጢራት ሁሉ ተገልጠውለታል። ገና በ 7 ዓመቱ ስለ ሦስት ነገሮች በእጅጉ ያለቅስ ነበር። "ነፍሴ ከሥጋዬ ተለይታ ስትወጣ ከጌታችን ጋር ስትገናኝና መጨረሻውን ፍርድ ስሰማ እነዚህን ሦስት ነገሮች በእጅጉ እፈራለሁ" እያለ ያለቅስ ነበር።
❤ በ 12 ዓመቱ ብሉይንና ሐዲስን አጠናቆ ተመምሮ ጨርሷል። ጸጋውን ዐውቀው 5 ቱ ታዋቂ ሊቃነ ጳጳሳት መጥተው እጅ ነስተውት አዲስ ድርሰት ድረስልን ቢሉት እርሱም በፍጹም ትሕትና "በእናንተ ፊት እንኳን አዲስ ድርሰት ልደርስ ቀርቶ የተደረሰውንም መናገር አልችልም"። አላቸው። እርሱ በነበረበት ዘመን በሮማው መናፍቅ ልዮን አማካኝነት ቤተ ክርስቲያን ለመጀመርያ ጊዜ ለሁለት የተከፈለችበት ጊዜ ነበርና እነ ዲዮስቆሮስ "የውሾች ጉባኤ" ከተባለው ከኬልቄዶን ጉባኤ ተለይተው ሃይማኖትን ሲያጸኑ ልዮንንም ማውገዛቸውን ያዕቆብ ሲሰማ በዲዮስቆሮስ ጽናት በእጅጉ ተደስቶ ደብዳቤ ጽፎ አመስግኖታል። እነ ልዮንን ግን አውግዞ እረግሟቸዋል። ልዮንም ተከታይ ባገኘ ብሎ "እኔን ምሰል" በማለት ለያዕቆብ ደብዳቤ ጻፈለት። ያዕቆብም "ሳጥናኤል ከመላእክት ጋር ምን አንድ አደረገው? አንተ ርኩስ ነህ፤ የዲዮስቆሮስን ጥርስ አስወልቀህ፣ ጢሞን አስነጭተህ፣ ሃይማኖትህን የቀየርህ ከሁለት ዓለም ስደተኛ ጋር አልተባበርም፣ ይልቅስ ንስሓ ግባ፣ ንስሓ ባትገባ ግን አንተ ዲያብሎስ ነህ ተከታዮችህም አጋንንት ናቸው። በማለት መልሱን ጽፎለታል። እምቢ ብሎ በክህደቱ ቢጸናበትም አውግዞ እረግሞ ንጽሕናውን ቅድስናው እንደ መላእክት ነው የተባለለት ያዕቆብ ዘሥሩግ ጻድቅም ሐዋርያም ደራሲም ተከራካሪ መምህርም ነው። ሦስት ድርሰቶች ያሉት ሲሆን በስሙ የተጠራው ቅዳሴም አለው። ዕረፍቱ ሰኔ 7 ቀን ነው። ከአባታችን ከአቡነ ያዕቆብ ዘሥሩግ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን በጸሎቱም ይማረን። ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱሳን።

💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
🕊 ም ክ ረ ቅ ዱ ሳ ን 🕊
▷ " የመንፈሳዊ ሰው ልብ "
[ " አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ ... ! " ]
[ 🕊 ]
-----------------------------------------------
" ከኃጢአቴ ፊትህን መልስ ፥ በደሌንም ሁሉ ደምስስልኝ።
አቤቱ ፥ ንጹሕ ልብን ፍጠርልኝ ፥ የቀናውንም መንፈስ በውስጤ አድስ። ከፊትህ አትጣለኝ ፥ ቅዱስ መንፈስህንም ከእኔ ላይ አትውሰድብኝ።" [ መዝ.፶፩፥፱ ]
🕊 💖 🕊
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
🕊 ም ክ ረ ቅ ዱ ሳ ን 🕊
▷ " የመንፈሳዊ ሰው ልብ "
[ " አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ ... ! " ]
[ 🕊 ]
-----------------------------------------------
" ከኃጢአቴ ፊትህን መልስ ፥ በደሌንም ሁሉ ደምስስልኝ።
አቤቱ ፥ ንጹሕ ልብን ፍጠርልኝ ፥ የቀናውንም መንፈስ በውስጤ አድስ። ከፊትህ አትጣለኝ ፥ ቅዱስ መንፈስህንም ከእኔ ላይ አትውሰድብኝ።" [ መዝ.፶፩፥፱ ]
🕊 💖 🕊
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (ባሕራን)
†
🕊 💖 ሰ ላ ም ታ 💖 🕊
❝ ክርስቶስ ተንስአ እሙታን
▸ በዐቢይ ኃይል ወስልጣን ፤
አሠሮ ለሰጣን
▸ አግዐዞ ለአዳም ፤
ሰላም
▸ እምይእዜሰ ፤
ኮነ
▸ ፍስሐ ወሰላም ❞
🕊
❝ ክርስቶስ በታላቅ ኃይልና ስልጣን ከሙታን ተነሳ ፤ ሰይጣንን አሰረው ፤ አዳምንም ነጻ አወጣው ፤ ስለዚህም ከእንግዲህ ወዲህ ፍፁም ሰላም እና ደስታ ሆነ። ❞
▬▬▬▬▬▬ † ▬▬▬▬▬▬
[ 🕊 እነሆ ሁሉም አዲስ ሆነ ! 🕊 ]
† † †
💖 🕊 💖
🕊 እንኳን ለበዓለ ዕርገት በሰላም አደረሰን 🕊
"ወሶበ ተንሥአ ዐርገ ውስተ ሰማያት ወዘኒ ወረደ ዘእንበለ ሥጋ ውእቱ ዘዐርገ ሥግወ ወአሐዱ ውእቱ ዘእምቅድስት ሥላሴ ወኢወሰከ ኍልቆ ራብዐየ ወኢካልዐ ገጸ ወነበረ በየማነ አብ ፤
[ ከተነሣም በኋላ ወደ ሰማይ ዐረገ። ሥጋ ሳይይዝ የመጣ እርሱ ሰው ሆኖ ዐረገ። ከሦስቱ አካላት አንዱ አካል እርሱ ነው። ለሥላሴ አራተኛ ለቃል ሁለተኛ አልሆነም። በአብ ዕሪና ኖረ፤ ]
[ ቅዱስ ባስልዮስ ]
ከበዓሉ ረድኤት በረከት ይክፈለን አሜን።
† † †
💖 🕊 💖
🕊 💖 ሰ ላ ም ታ 💖 🕊
❝ ክርስቶስ ተንስአ እሙታን
▸ በዐቢይ ኃይል ወስልጣን ፤
አሠሮ ለሰጣን
▸ አግዐዞ ለአዳም ፤
ሰላም
▸ እምይእዜሰ ፤
ኮነ
▸ ፍስሐ ወሰላም ❞
🕊
❝ ክርስቶስ በታላቅ ኃይልና ስልጣን ከሙታን ተነሳ ፤ ሰይጣንን አሰረው ፤ አዳምንም ነጻ አወጣው ፤ ስለዚህም ከእንግዲህ ወዲህ ፍፁም ሰላም እና ደስታ ሆነ። ❞
▬▬▬▬▬▬ † ▬▬▬▬▬▬
[ 🕊 እነሆ ሁሉም አዲስ ሆነ ! 🕊 ]
† † †
💖 🕊 💖
🕊 እንኳን ለበዓለ ዕርገት በሰላም አደረሰን 🕊
"ወሶበ ተንሥአ ዐርገ ውስተ ሰማያት ወዘኒ ወረደ ዘእንበለ ሥጋ ውእቱ ዘዐርገ ሥግወ ወአሐዱ ውእቱ ዘእምቅድስት ሥላሴ ወኢወሰከ ኍልቆ ራብዐየ ወኢካልዐ ገጸ ወነበረ በየማነ አብ ፤
[ ከተነሣም በኋላ ወደ ሰማይ ዐረገ። ሥጋ ሳይይዝ የመጣ እርሱ ሰው ሆኖ ዐረገ። ከሦስቱ አካላት አንዱ አካል እርሱ ነው። ለሥላሴ አራተኛ ለቃል ሁለተኛ አልሆነም። በአብ ዕሪና ኖረ፤ ]
[ ቅዱስ ባስልዮስ ]
ከበዓሉ ረድኤት በረከት ይክፈለን አሜን።
† † †
💖 🕊 💖
Forwarded from ✝️ የደብረ ናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ እና ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ኆኅተ ጥበብ ሰንበት ትምህርት ቤት ✝️ (ኆኅተ ጥበብ ሰ/ት/ቤት)
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM