Telegram Web Link
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ ✞✞✞ ክርስቶስ ተንሥአ እም ሙታን
በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን
አሰሮ ለሰይጣን
አግዓዞ ለአዳም
ሰላም
እምይእዜሰ
ኮነ
ፍስሐ ወሰላም


እንኳን አደረሳችሁ

❖ ሰኔ 1 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

+"+ ቅዱስ_ዮሴፍ_ጻድቅ +"+

=>ቤተ_ክርስቲያን
በዚህ ስም ብዙ ቅዱሳን አሏት:: በተለይ ደግሞ እስራኤል
የተባለ የቅዱስ_ያዕቆብ
ልጅ ቅዱስ ዮሴፍ ከሁሉም ቅድሚያውን ይይዛል::
ታላቁ ቅዱስ_መጽሐፍ
ላይ በስፋት ታሪካቸው ከተጻፈላቸው ቅዱሳን አንዱ ነው::

+ስለዚህ ቅዱስ ዝርዝር መረጃን
ለማግኘት ኦሪት_ዘፍጥረትን
ከምዕራፍ 39 እስከ 50 ድረስ ማንበብ ይኖርብናል::
ከዚህ በተረፈም በዜና ቤተ ክርስቲያን ስለ ቅዱሱ ብዙ
ተብሏል::

+መጽሐፍ ቅዱስ ሲጀምር ስለ ቅዱስ ሰው አዳም
ይነግረናል:: ቀጥሎም ስለ ቅዱሳኑ
ሴት
ሔኖክ
ኖኅ
ሴም
አብርሃም
ይስሐቅና
ያዕቆብ
ነግሮን ቅዱስ_ዮሴፍ
ላይ ይደርሳል::

+ቅዱስ ዮሴፍ ያዕቆብ (እስራኤል) ከሚወዳት
ሚስቱ ራሔል
ከወለዳቸው 2 የስስት ልጆቹ አንዱ ነው:: ቅዱሱ ምንም
እናቱ ብትሞተበትም በአባቱና በፈጣሪው ፊት ሞገስ
ነበረው::
ምክንያቱም ቅን: ታዛዥና የፍቅር ሰው ነበርና::

+እንዲያ አምርረው ለሚጠሉት ወንድሞቹ እንኳን ክፋትን
አያስብም ነበር:: ይልቁኑ ለእነሱ ምሳ (ስንቅ) ይዞ
ሊፈልጋቸው
በበርሃ ይንከራተት ነበር እንጂ::
+መንገድ ላይ ቢርበው አለቀሰ እንጂ ስንቃቸውን
አልበላባቸውም:: የአባቶቹ አምላክ ግን ድንጋዩን ዳቦ
አድርጐ
መግቦታል:: 10ሩ ወንድሞቹ ግን ስለ በጐነቱ ፈንታ
ሊገድሉት ተማከሩ:: ከፈጣሪው አግኝቶ በነገራቸው ሕልም
"ሊነግሥብን
ነው" ብለው ቀንተውበታልና::
+በፍጻሜው ግን በይሁዳ መካሪነት ለዐረብ ነጋድያን
ሸጠውታል:: በዚህም ለምሥጢረ ሥጋዌ (ለጌታ መሸጥና
ሕማማት) ምሳሌ
ለመሆን በቅቷል:: ወንድሞቹ ለክፋት ቢሸጡትም ቅሉ
ውስጡ ፈቃደ እግዚአብሔር ነበረበትና በባርነት
በተሸጠበት በዺጥፋራ
ቤት ፈጣሪው ሞገስ ሆነው::
+ወጣትነቱን በፍቅረ እግዚአብሔር ሸብ አድርጐ አስሮ
ነበርና የዺጥፋራ ሚስት የዝሙት ጥያቄ
አላንበረከከውም:: "ማንም
አያየንም" ስትለውም "እፎ እገብር ኃጢአተ በቅድመ
እግዚአብሔር" (ማንም ባያይስ እንዴት በፈጣሪየ ፊት
ኃጢአትን
አሠራለሁ?) በማለት ከበደል አምልጧል:: ስለዚህ
ፈንታም የእሥር ቅጣት አግኝቶታል::
+ጌታ ከእርሱ ጋር ቢሆን በእሥር ቤትም ሞገስን አገኘና
አለቅነትን ተሾመ:: "ኢኀደረ ዮሴፍ ዘእንበለ ሲመት"
እንዲል
መጽሐፍ:: ከዚያም የንጉሡን (የፈርዖንን) ባለሟሎች
ሕልም ተረጐመ:: ቀጥሎም ንጉሡን በሕልም ትርጓሜ
አስደመመ::
ፈርዖንም ቅዱሱን በግዛቱ (ግብጽ) ላይ ሾመው::
+ቅዱስ ዮሴፍ በምድረ ግብጽ ነግሦ ሕዝቡን ከረሃብ
ታደገ:: ለቅዱስ አባቱ ለእሥራኤልና ክፉ ለዋሉበት
ወንድሞቹም መጋቢ
ሆናቸው:: አስኔት (አሰኔት) የምትባል ሴት አግብቶም
ኤፍሬምና ምናሴ የተባሉ ልጆችን አፍርቷል::
+በመንገዱ ሁሉ እግዚአብሔርን አስደስቶ: ከአባቱ
ዘንድም ምርቃትና በረከትን ተቀብሎ በ110 ዓመቱ
በዚህች ቀን በመልካም
ሽምግልና ዐርፏል:: ወገኖቹም በክብርና በእንባ
ቀብረውታል:: "አጽሜን አፍልሱ" ብሎ በተናገረው ትንቢት
መሠረትም ልጆቹ
(እነ ቅዱስ ሙሴ) ከግብጽ ባርነት ሲወጡ አጽሙን ወደ
ከነዓን አፍልሠዋል::

+" ቅዱስ ለውንትዮስ ሰማዕት "+

=>ቅዱሱ የተወለደው በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን አካባቢ
ሲሆን ሃገሩ ጠራብሎስ ትባላለች:: በወቅቱ በወታደርነት
ነገሥታቱን
ያገለግል ነበር:: ድንግል: ደም ግባት የሞላለት ወጣት ስለ
ነበር በሰዎች ፊት ሞገስ ነበረው::

+እርሱ ግን ምን ወታደር ቢሆን ጾምና ጸሎትን ያዘወትር
ነበር:: በተለይ ደግሞ የዳዊትን መዝሙር እየመላለሰ
ይጸልየው:
ይወደው ነበር:: ንግግሩ ሁሉ በመንፈስ ቅዱስ ጨውነት
የታሸ ነውና ብዙ ጉዋደኞቹን ከክህደት ወደ ሃይማኖት:
ከክፋት ወደ
ደግነት መልሷል::

+የመከራ ዘመን በደረሰ ጊዜም በገሃድ ስመ ክርስቶስን
ይሰብክ ነበር:: ክፉ ሰዎች ከሰውት በመኮንኑ ፊት በቀረበ
ጊዜም
አልፈራም:: ወታደሮቹ መሬት ላይ ጥለው እየደበደቡት:
ደሙ እንደ ጐርፍ እየተቀዳ እርሱ ግን ይዘምር ነበር::

+በመጨረሻም ስለ ክርስቶስ ፍቅር አንገቱን ተሰይፏል::
ቅዱስ ለውንትዮስ እጅግ ተአምረኛ ሰማዕት ነውና
በእምነት
እንጥራው:: ቤተ ክርስቲያንም ዛሬ የቅዱሱን ተአምራት
ታስባለች:: ቅዳሴ ቤቱም የተከበረው በዚሁ ዕለት ነው::

=>አምላከ ቅዱሳን ወርኀ ሰኔን የፍሬ: የበረከት: የንስሃና
የጽድቅ አድርጐ ይስጠን:: ከሰማዕቱ ጽናትን: ጸጋ በረከትን
ይክፈለን::

=>ሰኔ 1 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ዮሴፍ ጻድቅ (የያዕቆብ ልጅ)
2.እናታችን አስኔት (የቅ/ ዮሴፍ ሚስት)
3.ቅዱስ ለውንትዮስ ክቡር ሰማዕት
4.ቅዱስ ቢፋሞን ሰማዕት
5.ቅዱስ ቆዝሞስ ሰማዕት

❖ወርኃዊ በዓላት
1፡ ልደታ ለማርያም
2፡ ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ
3፡ ቅዱስ ሚልኪ ቁልዝማዊ
4፡ ቅዱስ ራጉኤል ሊቀ መላእክት
5፡ ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና

=>+"+ እንዲህም አላቸው:- "ወደ ግብጽ የሸጣችሁኝ እኔ
ወንድማችሁ ዮሴፍ ነኝ:: አሁንም ወደዚህ ስለ ሸጣችሁኝ
አትዘኑ:: አትቆርቆሩም:: እግዚአብሔር ሕይወትን ለማዳን
ከእናንተ በፊት ሰዶኛልና . . . እግዚአብሔርም በምድር
ላይ
ቅሬታን አስቀርላችሁ ዘንድ: በታላቅ መድኃኒትም
አድናችሁ ዘንድ ከእናንተ በፊት ላከኝ::" +"+ (ዘፍ.
45:4-8)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
Forwarded from M.A
Forwarded from M.A
Forwarded from M.A
ስለ ምሥጢራተ ቅድሳት

ከኢትዮዽያ #ኦርቶዶክስ_ተዋሕዶ ምዕመናን አብዛኛው #ከቅዱስ_ሥጋውና_ክቡር_ደሙ የራቀ መሆኑን ሳስብ በጣም አዝናለሁ!

ግን ለምን ???

ለምን ብዙዎቻችን #ሕይወት_መድኃኒት ከሆነው ማዕድ ተለየን ???

ከቅዱስ ሥጋው ሳይበሉ: ከክቡር ደሙ ሳይጠጡ መዳን ይኖር ይሆን ???

በሰማያዊው ዙፋን #በዘለዓለም_አምላክ_በክርስቶስ ፊትስ በቂ መልስ ይኖረን ይሆን ???

ሁልጊዜ ባልረባ ምክንያት ሕይወት ከሆነው #ማዕደ_ክርስቶስ እስከ መቼ እንርቃለን ???

+እርሱ ግን አሰምቶ ይጠራናል:: "ኑ! ሥጋየን ብሉ: ደሜንም ጠጡ" ይለናል:: "ሥጋየን የሚበላ: ደሜንም የሚጠጣ የዘለዓለም ሕይወት አለው:: እኔም በእርሱ አድሬበት እኖራለሁ" ይለናል:: (ዮሐ. 6:56)

+ሌላ መንገድ አለ እንዳይመስለን ደግሞ "የሰውን ልጅ (የክርስቶስን) ሥጋውን ካልበላችሁ: ደሙንም ካልጠጣችሁ በራሳችሁ ሕይወት የላችሁም" (ዮሐ. 6:53) የሚል ተግሣጽን ልኮልናል::

+ቤተ ክርስቲያን እኛን ወደ #ምስጢረ_ቁርባን ለማድረስ ከእነዚህ የተረፈ ነገር አልጫነችብንምኮ!

¤በሃይማኖት መኖር (መመላለስ)
¤ከክርስቶስ (ከጌታችን) ጋር ለመኖር ቁርጥ ውሳኔ
¤በመምሕረ ንስሃ ሥር መጠለል
¤በንስሃ ሕይወት መመላለስና
¤ቀዋሚ የሕይወት መሥመር (ጋብቻ ወይ ምናኔ) መያዝን ትሻለች እንጂ መቼ ሌላ ቀንበር ጫነችብን!

+እናም የመንፈስ ወንድሞቼና እህቶቼ . . .
¤የራቅን እንቅረብ!
¤የቀረብንም እንበርታ!
¤የበረታንም እንጽና!
¤የጸናንም ደካሞቹን እንርዳ! (ይህ በጌታ ዘንድ ዋጋው ትልቅ ነውና!)

#የምሕረት_ጌታ #ለምሥጢራተ_ቅድሳት የምንበቃበትን የምሕረት ዘመን ያምጣልን::

☞ግን እናስብበት!!!

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

Re. Dn Yordanos Abebe
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (ባሕራን)
🕊

[ † እንኳን ለቅዱሳን ነቢያት ዮሐንስና ኤልሳዕ ዓመታዊ የፍልሠት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †

🕊† መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ † 🕊

† የቅዱሳኑ ዘካርያስና ኤልሳቤጥ ልጅ ቅዱስ ዮሐንስ :-

- በብሥራተ መልዐክ የተጸነሰ
- በማሕጸን ሳለ መንፈስ ቅዱስ የሞላበት
- በበርሃ ያደገና በገዳማዊ ቅድስና ያጌጠ
- እሥራኤልን ለንስሃ ያጠመቀ
- የጌታችንን መንገድ የጠረገ
- ጌታውን ያጠመቀና
- ስለ እውነት አንገቱን የተቆረጠ ታላቅ ሰው ነው::
ስለዚሕም ቤተ ክርስቲያን :-

ነቢይ :
ሐዋርያ :
ሰማዕት :
ጻድቅ :
ገዳማዊ :
መጥምቀ መለኮት :
ጸያሔ ፍኖት :
ቃለ ዐዋዲ . . . ብላ ታከብረዋለች::

🕊  †  ቅዱስ ኤልሳዕ ነቢይ  †  🕊

† ከነቢያተ እሥራኤል አንዱ ኤልሳዕ :-

- ከእርሻ ሥራ ቅዱስ ኤልያስን የተከተለ
- መናኔ ጥሪት የተባለ
- በድንግልና ሕይወት የኖረ
- የታላቁ ነቢይ ኤልያስ መንፈስ እጥፍ የሆነለት
- እጅግ ብዙ ተአምራትን ያደረገ
- አንዴ በሕይወቱ : አንዴ በአጽሙ ሙታንን ያስነሳ ታላቅ ነቢይና አባት ነው:: ቅዱሳት መጻሕፍት ሁለቱን ቅዱሳን በመልካቸውም ይገልጿቸዋል::

ቅዱስ ዮሐንስ ፦

- ቁመቱ ልከኛ
- አካሉ በጸጉር የተሸፈነ
- የራሱ ጸጉር በወገቡ
- ጽሕሙ እስከ መታጠቃያው የወረደ
- ግርማው የሚያስፈራ የ31 ዓመት ጎልማሳ ነበር::

ቅዱስ ኤልሳዕ ፦

- በጣም ረዥም
- ራሱ ገባ ያለ [ ራሰ በራ ]
- ቀጠን ያለ
- ፊቱ ቅጭም ያለ [የማይስቅ] ሽማግሌ ነበር::

በዚሕች ቀን በ፫፻፶ [350] ዓ/ም አካባቢ የሁለቱም ቅዱሳን አጽም ከኢየሩሳሌም ወደ ግብፅ ፈልሷል:: በወቅቱ ክፋተኛ የነበረው ንጉሥ ዑልያኖስ ክርስቲያኖችን ለማጥፋት ሞክሮ ነበር:: ለዚሕ እንዲረዳው በ፸ [70] ዓ/ም የፈረሰውን የአይሁድ ቤተ መቅደስ አንጻለሁ ቢልም ፫ [3] ጊዜ ፈረሰበት::

ምክንያቱን ቢጠይቅ "የክርስትያኖች አጽም በሥሩ ስላለ እሱን አውጥተህ አቃጥል" አሉት:: ሲቆፈር በመጀመሪያ የሁለቱ ቅዱሳን አጽም በምልክት በመታወቁ በኢየሩሳሌም የነበሩ ክርስቲያኖች በብዙ ብር ገዝተው : ወደ ግብፅ አውርደው ለቅዱስ አትናቴዎስ ሰጥተውታል:: እርሱም በስደት ላይ ነበርና በክብር ደብቋቸዋል::

በኋላም በቅዱስ ቴዎፍሎስ ዘመን ቤተ ክርስቲያናቸው ታንጾ በዚህ ቀን ተቀድሷል:: በቅዳሴው ሰዓትም ቅዱስ ቴዎፍሎስ ዮሐንስ መጥምቁና ቅዱስ ኤልሳዕ ወርደው ሕዝቡን ሲባርኩ በይፋ ተመልክቷል::

† አምላከ ቅዱሳን የወዳጆቹን ፍቅር ያድለን::

🕊

[ † ሰኔ ፪ [ 2 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት [ፍልሠቱ]
፪. ቅዱስ ኤልሳዕ ነቢይ [ፍልሠቱ]
፫. አባ ቀውስጦስ ኢትዮዽያዊ

[ †  ወርኀዊ በዓላት ]

፩. ቅዱስ ታዴዎስ ሐዋርያ
፪. ቅዱስ ኢዮብ ጻድቅ ተአጋሲ
፫. ቅዱስ አቤል ጻድቅ
፬. ቅዱስ አባ ዻውሊ ገዳማዊ [ታላቁ]
፭. ቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ
፮. አባ ሕርያቆስ ዘሃገረ ብሕንሳ

" ጌታ ኢየሱስ ለሕዝቡ ስለ ዮሐንስ ሊናገር ጀመረ . . . ምን ልታዩ ወጣችሁ? ነቢይን? አዎን እላችሁአለሁ ከነቢይም የሚበልጠውን . . . እውነት እላቹሃለሁ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሳም . . . ነቢያት ሁሉና ሕጉ እስከ ዮሐንስ ድረስ ትንቢት ተናገሩ:: ልትቀበሉትስ ብትወዱ ይመጣ ዘንድ ያለው ኤልያስ ይሕ ነው:: የሚሰማ ጀሮ ያለው ይስማ :: " † [ማቴ.፲፩፥፯-፲፭] (11:7-15)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (ባሕራን)
                           †                           

🕊  💖        ሰ ላ ም ታ        💖  🕊

❝ ክርስቶስ ተንስአ እሙታን
▸ በዐቢይ ኃይል ወስልጣን ፤
አሠሮ ለሰጣን
▸ አግዐዞ ለአዳም ፤
ሰላም
▸ እምይእዜሰ ፤
ኮነ
▸ ፍስሐ ወሰላም ❞

🕊

❝ ክርስቶስ በታላቅ ኃይልና ስልጣን ከሙታን ተነሳ ፤ ሰይጣንን አሰረው ፤ አዳምንም ነጻ አወጣው ፤ ስለዚህም ከእንግዲህ ወዲህ ፍፁም ሰላም እና ደስታ ሆነ።

▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

🕊  እነሆ ሁሉም አዲስ ሆነ !  🕊   ]

†                       †                        †
💖                    🕊                     💖

❝ በከመይቤ መጽሐፍ ማእከለፈጣሪ ወፍጡራን
ለዕረፍት ዘኮንኪ ጽላተ [ ትእምርተ ] ኪዳን
ሰንበተ ሰንበታት ማርያም ዕለተ ብርሃን
ብኪ ይትፌሥሑ ዘገነተጽጌ ጻድቃን
ወብኪ ይወጽኡ ኃጥአን እምደይን፡፡ ❞

[ መጽሐፍ እንደተናገረ በፈጣሪ እና በፍጡራን መካከል ለዕረፍት የቃል ኪዳን ማደሪያ [ ምልክት ] የሆንሽ የብርሃን ቀን ሰንበተ ሰንበታት ማርያም ሆይ በገነት ያሉ ጻድቃን በአንቺ ደስ ይላቸዋል፡፡ ኃጥአንም ከደይን በአንቺ ይወጣሉ፡፡ ]

[   አባ ጽጌ ድንግል   ]


     🕊       ክብርት ሰንበት       🕊

†                       †                        †
💖                    🕊                     💖
Forwarded from ገድለ ቅዱሳን (ባሕራን)
🕊  💖  ▬▬   †    ▬▬  💖  🕊

[ የተዘጋች ገነት የታተመች ጉድጓድ ]

▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

❝ ሕዝቅኤል ፦ "ድንቅ በሆነ ታላቅ ቁልፍ የተዘጋች ደጅ በምሥራቅ አየሁ፡፡ ከኃያላን ጌታ በቀር ወደ እርሷ ገብቶ የወጣ የለም፡፡" አለ፡፡ [ሕዝ.፵፬፥፩] ይህ የተዘጋ በር የድንግልናዋ ዜና ነው፡፡ " እግዚአብሔርም ፦ ይህ በር ተዘግቶ ይኖራል እንጂ አይከፈትም፥ ሰውም አይገባበትም፤ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ገብቶበታልና ተዘግቶ ይኖራል። " [ሕዝ.፵፬፥፩]

ሰሎሞንም ፦ "የተዘጋች ገነት የታተመች ጉድጓድ [ ያንቺ መንገዶች ናቸው ] አለ፡፡ " እኅቴ ሙሽራ የተቈለፈ ገነት ፥ የተዘጋ ምንጭ የታተመም ፈሳሽ ናት።" [ መኃ.፬፥፲፪ ]

በገነት አካባቢ ምን ይገኛል ? የሚጣፍጥ ፍሬ አይደለምን ? የሚጣፍጠው ፍሬ ምንድን ነው ? የእናቱ የድንግል ማርያም ፍሬ ኢየሱስ ክርስቶስ አይደለምን ? የተዘጋች ገነት ማለትስ በድንግልና ቁልፍ በተዘጋች በአንቀጸ ሥጋዋ ይተረጎማል፡፡ ዳግመኛ ከጉድጓድ ከሚጣፍጥ ውሃ በስተቀር ምን ይገኛል ? የሚጣፍጥ ውሃ ምንድን ነው ? በወንጌል ፦ " ማንም የተጠማ ቢኖር ወደ እኔ ይምጣና ይጠጣ። " [ዮሐ.፯፥፴፯] ያለው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ የታተመች ጉድጓድ የተባለው የንጽሕይት እናቱ የድንግልናዋ ኃይል ነው፡፡ ሁሉም ነቢያት ስለ ሥጋዋ በር ፦ " የተዘጋች ፥ በድንግልና የታተመች" ብለዋታልና፡፡

ለቀደሳትና ላነጻት [ በንጽሕና ለጠበቃት ] ለእግዚአብሔር ለዘላለም ምስጋና ይሁን፡፡ ❞

[ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ]

†                       †                         †
💖                    🕊                     💖
#የወጣቱን_ሕይወት_እንታደግ

የ23 አመት ወጣት ነው ሙሴ አሻግሬ ይባላል ተወልዶ ያደገው ወልድያ ከተማ ሲሆን ዛሬ ላይ ሁለት ኩላሊቶቹ መስራት አቁመው የኩላሊት የንቅለ ተከላ ህክምና አስፈልጎት አድኑኝ እያለ ይማጸናል።

እህቱ ፍሩታ አሻግሬ አረብ ሀገር ተንከራትታ ያጠራቀመችውን ገንዘብና ያላትን ጌጣ ጌጥ ሳይቀር ሽጣ ስታሳክም ነበር። አሁን ላይ ሳትሰስት ኩላሊቷን ለወንድሟ ለመስጠት ኢትዮጵያ ገብታለች።

እናም እናንት ደጋግ ኢትዮጵያውያን ይህንን ወጣት ህይወቱን ለማትረፍ አነሰ በዛ ሳትሉ የእርዳታ እጃችሁን ትዘረጉ ዘንድ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።
ፍሩታ አሻግሬ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000629004045

ለበለጠ መረጃ
➛ ፍሩታ አሻግሬ - 0969886929
➛ ደህንነት አሻግሬ - 0925009689
Forwarded from Bketa @¥
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from Bketa @¥
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
2024/11/20 03:37:57
Back to Top
HTML Embed Code: