Telegram Web Link
# ትዝታህ *
ለቃልህ ባትኖር ባይገዛህ ህሊና
እምነትን ሸኘሁት ደህና ሁን አልኩና
ዞረህ እንደማታይ ያወቀለት ሆዴ
ስሜቴን በእንባዬ አጠበዉ ልማዴ
ጠብቄ ባላገኝ እዉነቴን ታቅፌ
ፍቅርህንም ሸጥኩት ለሌላ አሳልፌ እንደማትመለስ በማለዳ አዉቄ
የቀረኝን ተስፋ ገደልኩት አንቄ
አለቅ ያለኝ ደዌ እስከ አጥንቴ ዘልቆ
ትዝታህ ብቻ ነዉ ነፍሴ ላይ ተጣብቆ"
@Gitemenlenante
አንቺ.....
በጣቶችሽ ጥበብ
ደስታዬን ለክቶ፥
ዝም ያለ ህይወቴን
በፍቅርሽ ነካክቶ፥
ታምር አይጎድልበት
ሁሌም ታምር ሰሪ፥
አንቺን ቀማሪ አርጎሽ
እኔን ተቀማሪ፥
ነብሴን ጥበብ ሞላት
በስልት የረቀቀ፥
የነካሽው ልቤ
ውብቅኝት ታጠቀ፥
ውብ ዜማ አፈለቀ፥
"የህይወቴ ህይወት
አንች በመሆንሽ ፥
እባክሽ ፍቅሬ ሆይ
አልጥፍ ከፊትሽ፥ "
እያለ ያዜማል
ቅኝትን ደርድሮ፥
በማይለቅ ምትሀት
ባንች ፍቅር ታስሮ:
@Gitemenlenante
።።።።።።።በውሸት አለም።።።።።።።
የአብሮነት ድልድይ መሰረት ካሳጣ
የመቻቻል ኑሮ መናናቅ ካመጣ
ከዝምድና ይልቅ ባንዳነት ካዋጣ
ዝምድና ይታጠብ ደሙን ውሻ ይላሰው
ምን ያደርጋል ታዲያ ልብ ለልብ መክሮ ካልተገናኘ ሰው
።።።።።።።።።ተስፋ።።።።።።
ጀንበር አዘቅዝቃ ሰማዩ ቢጨልም
አዲስ ቀን ይመጣል መንጋቱ አይቀርም
እናልህ ወዳጄ ፍፁም ተስፋ አትቁረጥ
ጨለማን ገፍትሮ በሚመጣው ቀን ውስጥ
ይመጣ ይሆናል ካጣኸው ደሚበልጥ
@Gitemenlenante
Channel photo updated
ሰላም👋 ውድ የ ግጥምን ለናንተ ቻናል ቤተሰቦች👥 ሰሞኑን የ ቻናላችንን ተከታዮች ቁጥር ለማብዛት በምናደርገው የማስታወቂያ ልውውጥ በማስታወቂያ እያጨናነቅናችሁ እንደሆነ እናውቃለን ቢሆንም ይሄን ችግር ለመቅረፍ የናንተ እገዛ ያስፈልገናል የቻናላችንን ሊንክ ቢያንስ ለ 5 ሰው ሼር በማድረግ እንዲሁም ባላችሁባቸው ግሩፖች ላይ ከታች ያለውን የቻናላችንን ሊንክ Forward በማድረግ እንዲቀላቀሉን በማድረግ አግዙን እኛም እናንተን ለማስደሰት የምንችለውን በሙሉ እናደርጋለን።
@Gitemenlenante
Forwarded from ʙᴇɴɪᴛᴏ 🐰
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የግጥም ችሎታና ፍቅር ላላችው በሙሉ ተብሎ የተዘጋጀ አሪፍ እና ምርጥ ቻናል ከእናንተ ሚጠበቀው Join ብሎ መቀላቀል ብቻ
#ከልጅነት_ፍቅር_አንዲት_ጠብታ

በሰላላው መንገድ
የትየለሌ አግር፥ እንደሊጥ ባቦካው
ጸአዳ ጣትሽን፥ ጉድፍ እንዳይነካው
ማጡን እየዘለልሽ፥ ዳጥ ዳጡን እያለፍሽ
ጤዛ የወረረው፥ ዛፍ እየተደገፍሽ
ትንሽ ስትመጭ፥ ብዙ ሰታዘግሚ
ሁለቴ ተራምደሽ፥ አስሬ ሰትቆሚ
ለተደናገረው፥ መንገድ ሰትጠቁሚ
የተላከ ሕፃን፥ አሰቁመሽ ስትስሚ

እኔ ሰናፍቅሽ
እኔ ስጠብቅሽ
እንደጉድ ተውቤ
ላማልልሽ ጥሬ
በጆንትራ ዘይቤ
ጠጉሬን አበጥሬ
ጅማት እያጠበቅሁ፥ ጅማት እያላላሁ
የገዛ ከንፈሬን፥ ቀርጥፌ እየበላሁ
ሰጠብቅሽ በጣም
ምሰልሽ ነው እንጂ፥ አካልሽ አልመጣም፤

ባይኖቼ ስፈልግ
መስኮት እከፍትና
ሌላ ነው የሚያልፈው፥ በሰፊው ጎዳና
ያው ገጣባ አህያ፥ ያቻት ድኩም በቅሎ
በግ እየጎተተ፥ አለፈ ቆለኛ
ቅርጫት ያጎበጣት፥ ሚስቱን አሰከትሎ
ያውና ድሀ እደግ፥ መንገድ ዳር የተኛ

የተጎነጎነ፥ የሣር አምባር መስሎ፤
ባይኖቼ ሳማትር፥ መስኮት እከፍትና
ሌላ ነው የሚያልፈው፥ በሰፊው ጎዳና፤

ሁሉም ተለውጦ
ያ ገጣባ አህያ፥ ጸጉር አቆጥቁጦ
ያች ድኩም በቅሎ፥ ስጋር ፈረስ ቀድማ
ቆለኛው ሰውየ፥ ሙከት በጉን ሽጦ
ለሚሰቱ ነጭ ሻሽ፥ ለሱ ሸራ ጫማ
በትርፉ ሸምቶ
ሁሉም ከሄደበት፥ ቀንቶት ተመልሶ
ሁሉም ከድቀቱ፥ በወግ ተፈውሶ፤

እኔ ብቻ ቀረሁ
መንገድሽ ረዝሞ፥ ባሳብ እያሳጠርሁ
አንቺን እየናፈቅሁ
አንቺን እየጠቅሁ
ጅማት እያላላሁ፥ ጅማት እያጠበቅሁ።

በውቀቱ ስዩም

@Gitemenlenante
ተይ ያልከኝን ተውኩት እታዘዝሀለው
ሌላም ካለ በለኝ እተውልሀለው
አንተ ካልወደድከው እረ ሲቀር ይቅር
የማልተወው የለም ከ አንድ አንተ በስተቀር.....................💘
@Gitemenlenante
.......አንቺ'ና ቁንጅናሽ.....

እኔም ለኔ ስልሽ
ሌላም ሠው ሢመኝሽ
ተወዳድርኩ እኔም
የግሌ ላደርግሽ
ግና ምን ያደርጋል
መስፈርትሽ ይከብዳል
እንኩዋን እኔ ቀርቶ
እብዱም ደግሞ ያብዳል።
@Gitemenlenante
#​​​ናፍቀሽኛል_ሆዴ

መንገድሽ መንገዴ
ሆኖ የዘለቀው
ፍቅርሽ ስለገዛኝ
ባሪያሽ ስለሆንኩ ነው

ሆዴ ናፍቀሽኛል
ምፈልገው ቢሟላ
የጠየኩትንም ባገኝ
አልጠግብም እኔ
አይንሽ ነው የራበኝ

ፍቅር ናፍቀሽኛል
ሆዴ ናፍቀሽኛል
አንቺን ለማግኘት
ልቤ አጥብቆ ይመኛል፡፡
@Gitemenlenante
#አስተውል!!!
መላ! ቁመናዋ ሸንቃጣነቷ አርኪ፣
የፊት ደም ግባቷ ቀለሟ ማራኪ።

ደማቅ ሀር ፀጉሯ የአይን ቅንድቦቿ፣
የባቄላ አበባ የሚመስሉ አይኖቿ።

ለስላሳ ረ'ጃጅም ጣቶቿ አለንጋ፣
አ'ጥንት አልባ መሰል የሚል እጥፍ ዘርጋ።

ቀረብ ብሎ ላየ ውጫዊ ውበቷን፣
መላ ሰውነቷ ይመግባል ፍቅርን።

ታድያ ምን ያደርጋል ቢያማልል ውበቷ፣
ውስጣዊ ነው እንጂ ገላጭማንነቷ።
@Gitemenlenante
#ካንቺ_ጋራ

ካንቺ ጋራ ሆኜ፤ የኖርኳቸው ጊዜያት
ያሳለፍኩት እድሜ
ጣፋጭ እንደኃጥያት
አጭር እንደ ጳጉሜ፤

አንቺ በላባ እግር፥ ደመና ላይ ቆመሽ
ሺ ሌሊት ከፊቴ፥ ሺ ሌት ከኋላዬ
ኮከቡን በሞላ በወረንጦ ለቅመሽ
ነዛሽው በላየ፤

ምንም እንኳ ሕዋው፥ ብርሃን ባያንሰው
ግርዶሽ ሆኖት ቆሟል፥ ይሄ ሰው ለዚያ ሰው
ግርዶሽ ቢነባበር፥ ኀይል የለው ባንች ፊት
መጋረጃው ሆነ፥ የብርሃን ወንፊት።
@Gitemenlenante
አይን'ክን ምን ሰበረው?

ከጥዋት ፀሀይ ይልቅ
ሲያበራ ማደንቀው
ከሁሉ አካላትህ
አብልጬ ምወደው
ታይቼ አይቼው በፍፁም ማልጠግበው
ተፈቃሪ ዓይንህን ዛሬስ ምን ሰበረው?

ምነው ምን ነካብኝ
ብርሃኑ ጨለመ
የፍቅር ፍንጣቂው
ጨረሩ ለጎመ
የመውደድ ስለቱ
ጫፉ ዶለዶመ

ውዴ ምነው ዓይንህ
አንገቱ ተደፋ
በድንገት ታውሮ
ልሳኑ ተሰፋ
ምነው እንደሌባ
ዓይንህ ከዓይኔ ራቀ
ነጠላ አዘቅዝቆ
እቃ እንደጠፋበት
መሬቱን ፏቀቀ

እንደሁሌ ዓይንህን አተኩሬ ሳየው
ከዓይኖቼ ይልቅ መሬቱ እንዴት ሳበው?
የምር ጎትቶህ ነው የመሬቱ ስበት
ወይስ ከኔው ዓይን ከህሊና ሽሽት?

{መአዛ ጥበቡ}
@Gitemenlenante
ገጣሚ
# Tsion
ከታች ያለውን የግጥም ስራዋን ለኛ እና ለናንተ ማለትም
ለ ግጥምን ለናንተ Channel ቤተሰቦች
እጅግ ማራኪና ድንቅ የሆነ የግጥም ስራዋን አድርሳለች
እኛም ላቅ ያለ ምስጋናችንን እንገልጻለን

ለገጣሚ #Tsion ከልብ የሆነ ምስጋናችን ይድረስልን 🙏
2024/10/02 04:17:00
Back to Top
HTML Embed Code: