Telegram Web Link
ፍቅር💖 በወረቀት 📝

#ገጣሚ desitana fiker

ሊፅፉት ላይቻል ፍቅርን በውረቀት
ቢያነቡት ላይገባ ለምን ይከትቡት
ፅንሰ-ሃሳብ ለሌለው ፊደል አይቀልሙ
ፍቅር ያለተግባር ፈፅሞ አያልሙ
ቃላትን ሰብስቦ በገፅ ቢያሰፍሩት
ፍቅር ዋጋ የለው በልብ ካላተሙት
ሆነው ካልተገኙ ድርጊት ካላሣዩት
ተፅፎ ከማንበብ ቢቀርስ ይበጃል
ፊት ሆነው ካልመሩት መቼ ይፀነሳል
ሂወትን ይወርሳል..........
መኖርን ያድሳል............
ሆነው ካልቀረቡት እኮ ፍቅር መቼ
የደስታ ጅረቱን ወንዞቹን ያፈሳል
ድሎት ያስቀልሳል
ፍቅር በወረቀት እንዴት ይዳሰሳል
ዘልቆ በእውነቱ ልብ ያረሰርሣል
ባዶ ነው........ባዶ ነው
ባዶ ነው........ባዶ ነው
ፍቅር በወረቀት ደርሶ ገለባ ነው
ፍሬ እንኳን ያሌለው.....
ትርጉምን አይሠጥም.....
ሰምና ወርቅ የለው...,
ከዋኒ አፍቃሪ ካልሆኑ ለፍቅር
ወዴት ንቅንቅ ሊል የዋዛ አይደለም
ፍቅር በወረቀት ከቶ አይፃፍም
ድርጊት ፈላጊ ነው እወቁት ግዴለም
@Gitemenlenante
ግጥም.......ማነው ተደናቂ

ሚስተር አርምስትሮንግ ከሰው በልጦ
ከመመልከት ይልቅ ወደ ላይ አንጋጦ
ከመሬት ተነሰቶ ህዋን አቆራርጦ
በሰው ልጆች ታሪክ ጨረቃን ረግጦ
የጨረቃን አፈር ቆፍሮ እየዛቀ
ይዞ ወደ መሬት ሲወርድ እየሳቀ
ዓለም ተገረመ እጅግ ተደነቀ
ከመሬት ተነስቶ ጨረቃ መድረሱ
አፈሯን ማምጣቱ ህዋንስ ማሰሱ
ምኑ ያስደንቃል ደርሶ መመለሱ
ይልቅ የረቀቀው የተውሰበሰበ
የመውጣቱን ጥበብ አፍልቆ ያሰበ
እጅግ ከሱ በላይ ልቆ የከበረ
መድረስ እንደሚችል እሱን ያስተማረ
መደነቅ ያለበት መምህሩ ነበረ
..............................................
sonaf or li sona formulate
poet ይርጋወሰን የማርያምወርቅ
@Gitemenlenante
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሰው

ሲመክሩት አዳምጦ
ለዛውም በተመስጦ
ባጠፋው ጥፋት እጅግ ተጸጽቶ
ዳግም ላያጠፋ ምሎ ተገዝቶ
በቀኝ ጆሮ ሰምቶ በግራ እያስወጣ
ብሎ የምን ጣጣ
ከቦታው ፈቅ ሳይል መሀላውን ረስቶ
ታጥቦ ጭቃ ይሆናል ከ ጥፋት ተጋብቶ
@Gitemenlenante
ሰው

ሲመክሩት አዳምጦ
ለዛውም በተመስጦ
ባጠፋው ጥፋት እጅግ ተጸጽቶ
ዳግም ላያጠፋ ምሎ ተገዝቶ
በቀኝ ጆሮ ሰምቶ በግራ እያስወጣ
ብሎ የምን ጣጣ
ከቦታው ፈቅ ሳይል መሀላውን ረስቶ
ታጥቦ ጭቃ ይሆናል ከጥፋት ተጋብቶ
@Gitemenlenante
😭አብጄ ቀረሁኝ😭
ከልቤ ስወድሽ አፀፋሽ መጥላት ነዉ:
ላንቺ ስኖርልሽ ሀሳብሽ ለሱ ነዉ፡

እልህ ዉስጥ ከተሽኝ አልላቀቅ ብልሽ፡
አሁንም ልብሽን ከኔ አርቀሽ ሰደሽ፡

የኔ ሳቶኝ የኔ አድርጌ ብሾምሽ፡
መቼም ላላገኝሽ ሳላገኝ አጣሁሽ፡

የማይሆነዉ ይሆን ብዬ እያሠብኩኝ፡
እንደማይሆን ሆኖ አብጄ ቀራሁኝ።
😖😖😖😖😖😖😖
@Gitemenlenante
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡ተመስገን፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
በረሀ መሀል ላይ አንድ ሰው ነበረ
ረሀብ ጠንቶበት ብዙ ያማረረ
ፊቱን ካረጠበው የእንባ ጎርፍ ጋራ እየተናነቀ
ምግብ እንዲሰጠው ፈጣሪን ጠየቀ
ፈጣሪም ሳይዘገይ ምላሽ አሳወቀ
በሰማይ የሚበር አንድ ቆቅ ወደቀ
ተመስገንም ሳይል እየተጀነነ
ቆቅ ትንሽ ነው ብሎ ሰውየው አዘነ
በግ ባለመውደቁ ፈጣሪን ኮነነ
@Gitemenlenante
ድሮ ድሮ ድሮ… ድንጋይ ዳቦ እያለ
ሰማይ እንደ ጣራ ሳይርቅ ዝቅ እንዳለ
ዶሮም እንደ አሞራ መብረር እየቻለ
ታስታውሺ ነበር እወድሽ ነበረ…
.
ታድያ ምን ያደርጋል ሁሉም ተቀየረ
ድንጋይ ዳቦ ትቶ ድንጋይ ሆኖ ቀረ
ሰማይ አፈንግጦ እንደዚህ ከፍ አለ
ዶሮም መብረር ትቶ መራመድ ጀመረ
ልቤ ግን ልብ ነው ያኔ እንደነበረ
በዘመኑ ሙሉ ሲያፈቅርሽ የኖረ።
@Gitemenlenante
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡ይታይሀል፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
አንተ ወንድሜ
እኔ ፊትህ ቆሜ
እንዴት ልየው ጀርባዬን
መንጻት መቆሸሼን
ላንተ ግን ይታይሀል ይሄ አለብሽ በለኝ
ለኔም የኔ ሳይሆን ያንተ ነው ሚታየኝ
@Gitemenlenante
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ ደብረ ታቦር (ቡሄ) 🔥በዓል በሰላም አደረሣችሁ፡፡

🥖 #መልካም_በአል 🥖

@Gitemenlenante
::::ሜሮን ጌትነት:::
( በአረንጓዴ ቢጫ ~ በቀይ
የተዋበች
እምዬ ኢትዮጵያ ~ ጥበብ
ትመስላለች )
.
ከሰሜን ተወልዳ ~ ጥጥ ፈታይ
እናቴ፣
ከደቡብ ጫፍ መጥቶ ~ ሸማኔው
አባቴ፣
ከምስራቅ ሲያስውበው ~
ስፌቱን አጎቴ፣
ከምዕራብ ተገኝቶ ~ ጥለት ሰሪ
አያቴ፣
መሃል አገር ሆና ~ ቋጨችው
አክስቴ፤
.
እንዲህ በአንድ አብረው ~
የሰሩትን ጥበብ
ቀላል ይሆናል ወይ?
እህት ወንድሞቼ ልነጥልህ ቢሉት
~ በሰበባ ሰበብ።
.
አይገርማችሁም ወይ?
ላጨልምህ ሲሉት
የአገራችን አርማ~ በሰማይ
ደመቀ
በአራቱም ማዕዘን
በሦስቱ ቀለማት ~ ምድር
ተጨነቀ ።
።።።።።።።።።።።
(ሜሮን ጌትነት)
@Gitemenlenante
2024/10/02 06:28:37
Back to Top
HTML Embed Code: