Telegram Web Link
የገጣሚ #Tsion ስራን ለማየት ለማንበብ👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
ዘቅጠናል በክፉ እርቅን ስጥመናል
እንኳን ማንሰራራት
ማሰብ ተስኖናል
ማእበሉም ከፍቷል
ለሰጠሙት ቀርቶ
ላዩትም ያስፈራል
በድምጹ ሚሽሹም
እጀጉን በዝተዋል ከፊሉም በወሬ መምጣቱን ቀጥሏል
ይህ ሁሉ ቢዋዥብ ለኛ ምኑ በጀን
ማእበሉ ሳይደርስ
ቀድመን ለሰጠመን
በትንሹ ባህር ወዲ ወድያ ስንል
መዋኝት አቀቶን ለተቅበዘበዝን
ባለማወቅ ገብተን
መውጫው ለራቀብን
ለኛማ መፍትሄ
ከወዴት ይምጣልን?
ልባችን ተሰርቆ በላይኛው ውብት
ዘለው ሲገቡ አይተን
ተከትለን ገብተን
ስንለፋ ቢያዩን በጭንቀት ተውጠን
ደስታ ነው በለው የቀሩትም መጡ
መጥፎ ይሁን ጥሩ ሳያረጋግጡ
እረ እንደው ምን እብደት
ምን አለማወቅ ነው??
በጥቂት ተማርከን
ሳናስብ መላለሰን
አይሆን ይሆን? ብለን
መጠየቅ ቢያቀተን
ማስተዋል ይክበደን??
አይናችንስ ቢሆን
አንዴት ሲቃን ከሳቅ
መለየት ያቅተው
ያለቀሰው ሁሉ ያማረ ይምሰለው
የቆሰለን አይቶ ማዘኑን ቢተወው
ለኔ በሎ ማሰብ
እረ እንዴት ተሳነው?
ምን ይሆን አይምሮን
እንዲ ያጨለምው?....

መልሱን እዚያው ትቼ
መዋተት ቀጠልኩኝ ስጋዬን ዘንግቼ
ስለ ነፍሴ ጮህኩኝ
አሰብኩት ዘመኔን
ትርጉም አልባ ህልሜን
ቀስቃሽ በመጠበቅ
ደጋፊን በመሻት
ዛሬየን ቀብሬ ለነገ ስማቅቅ
ዙሪያዪን ጨርሼ
ባህር ማዶ አልቀረኝ ሁሉን አዳርሼ
እኔነቴን ውጬ ለሌለኝ ስማስን
የጋቱኝን ሁሉ ሳጣጥም በጭፍን
ትርጉሙን ሳልጠይቅ
ሳጌጥ የኖርኩበት
የፊቴን ገፍቼ ሩቅ ያለምኩበት
ያባቴን ቅዱስ ቤት የዘነጋሁበት
ውብ የናቴን ጓዳ ያሽቀነጠርኩበት
የዘመድ አዝማዱን ፍቅር የረሳሁት
ፍቺ ቢስ ቅኔዬን ጠያቂ ስጠብቅ
ሰጥሜ መቅረቴ እያረገኝ ስቅቅ
ባስታወስኩት ቁጥር
ያሳዝነኝ ጀመር
ኋላ ምን ያረጋል
ደቁሶ ማንቋረር?........
ለካ ልምዴ ኖርዋል
ያስቀረኝ አባክኖ
አባናኝ ስናፍቅ አምሮዬ ባዝኖ
ቅዠቴ ማለቁን በረዳም እረፍዶ
በጥገኝነት ጥግ ሃሳቡ ተጠመዶ
እነደኔ ለጠፋው ማንነቱን ከድቶ
ለመጣው ከኋላ በጭፍን ተመርቶ
በእንባ ተሞልቼ ስለምን ስረየት
ብረሳው ለቅስፈት የሃጥያቴን ብዛት
ይባስብሽ ብሎ ሲቃዬን ሲያበዛት
አሳየኝ በአይኔ አመጣው ከጎኔ
ቢያስተወሉ ብዬ ከቀደመኩት ከኔ
በለቅሶዬ ስቀው ተከተሉኝ መጡ
ልመናዬን እንኳን ሳለጨርስ በቅጡ
አረፉት ብሰውት ጥለወኝ መጠቁ
እህህ ማለቴን ማንን በጠየቁ?
ማን በነገራቸው
መውጫው እንደራቀን
ከስጥመቱ ግርጌ
ገብተን እንደቀረን
እማኝ በሌለበት አልቃሽ በጠፋበት
በዛ በጨለማው
መስካሪ እንኳን ጠፍቶ
ሁሉም በእብደታችን
አንድ ላይ ተስማምቶ
አጨብጭቦ ሸኝን
ድምጽን አሰምቶ!!
ወዮ ለቀጣዪ
ለሰማው ጭምጭምታ
እንዳይነዳ እሱም
ቅኔውን ሳይፈታ!!!
# Tsion24
@Gitemenlenante
እንዲሁም ሌሎች የቻናላችን ቤተሰቦች👥 የግጥም ሰራዎቻችሁን ማድረስ ለምትፈልጉ የቻናላችን ቤተሰቦች በ Inbox
👉 @AS_CJman ላይ በማጋራት በማድረስ የግጥም ስራዎቻችው እንዲተዋወቅላችው ማድረግ ትችላላችሁ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
#Alazar {CJ}

ካንቺ ጋር ሳወራ

ከህይወቴ ቅኔ ከማፈቅርሽ ጋራ
ልክ ተገናኝተን ካንቺ ጋር ሳወራ
በንዴት ቀልቶ የነበረው አይኔ ይጠራና
የጨለመብኝ ቀን ይበራልኝና
የተኮሳተረው ፊቴ በሳቅ ይበራና
የናፈቀሽ ልቤ ደግሞ ይመታና
ልክ አንቺ ስትሄጂ ወዲያው ይቀየራል
የበራው ፊቴ ወዲያው ይጨልማል
የጠራልኝ አይኔ ደግሞ ይደፈርሳል
ልክ አንቺ ስትጠፊ አለም ባዶ ይሆንብኛል
እስከ ምንገናኝ ልቤ ይናፍቅሻል
የኔ ፍቅር ካንቺ ጋር ሳወራ
ይታየኛል የጨለመው ቀኔ በአንቺ ሲበራ
ካንቺ ጋር ሳወራ ይጠፋና ሀዘኔ
ደስተኛ እሆናለው ሀዘን ጠፍቶ ከእኔ
@Gitemenlenante
ሀሳብና አስተያየት ካላችሁ በ Inbox 👇
@AS_CJman
ከ ቻናላችን ቤተሰብ #Tsion የተላከ የግጥም ስራ ነው የግጥም ስራውን ለማየት ለማንበብ 👇👇👇👇

እኔ ማውቀው ፍቀር

እኔ ማውቀው ፍቅር ፣
ካንተ ጋራ ፍጹም ተቃራኒ ናቸው ፣
እንዳንተ አስቤም አልገነባዋቸው፣
እንዲው በማመኔ አብዘቼ ሳልጠይቅ፣
መመርመር ሳልሻ ከቶ ሳላጨነቅ፣
በ ፍርሃትም አይደል እንዲያው በመሳቀቅ፣
በደስታ ነው እንጂ በእምነት በመጥለቅ፣

ግን ውዴ አንድ እውነት ፣
ላካፈልህ አድመጠኝ፣
እኔ ማውቀው ፍቅር፣
ከ ስቃይ ያወጣኝ ፍርሃቴን ጠራርጎ፣
ከኔ ያራቀልኝ፣
ፍጹም ደስተኛ እንድሆን ያረገኝ፣
እኔ ማውቀው ፍቅር፣
በ ዋዛም አይገኝ፣

አንተ ግን በቀመር ፣
በቁጥር አስልትህ፣
አፈቅርኩሽ ብትል፣
ቃላት አሰማማረህ፣
ሞትኩልሽ ብትለኝ፣
በፍቅርሽ ተራብኩኝ፣
ጨዋታ ነው እንጂ ስሜትም አይመስለኝ፣

ምን አልባት ከልብህ ፣
ተሰምቶህ ከሆነ፣
አድምጠው ወስጥህን፣
አትፍራው ቃልህን፣
አስበህ አትበልኝ፣
ሰምተህ አትንገረኝ፣
ይልቅ ሁሉን ትተህ ከውስጥህ ቅረበኝ፣
ያኔ ቃላት ሳይሆን፣
ነፍስህ ከነፍሴ ጋር፣
አምረው ያብባሉ በ ጠለቀ ፍቅር❤️
#Tsion 24
@Gitemenlenante
ዘቅጠናል በክፉ እርቅን ስጥመናል
እንኳን ማንሰራራት
ማሰብ ተስኖናል
ማእበሉም ከፍቷል
ለሰጠሙት ቀርቶ
ላዩትም ያስፈራል
በድምጹ ሚሽሹም
እጀጉን በዝተዋል ከፊሉም በወሬ መምጣቱን ቀጥሏል
ይህ ሁሉ ቢዋዥብ ለኛ ምኑ በጀን
ማእበሉ ሳይደርስ
ቀድመን ለሰጠመን
በትንሹ ባህር ወዲ ወድያ ስንል
መዋኝት አቀቶን ለተቅበዘበዝን
ባለማወቅ ገብተን
መውጫው ለራቀብን
ለኛማ መፍትሄ
ከወዴት ይምጣልን?
ልባችን ተሰርቆ በላይኛው ውብት
ዘለው ሲገቡ አይተን
ተከትለን ገብተን
ስንለፋ ቢያዩን በጭንቀት ተውጠን
ደስታ ነው በለው የቀሩትም መጡ
መጥፎ ይሁን ጥሩ ሳያረጋግጡ
እረ እንደው ምን እብደት
ምን አለማወቅ ነው??
በጥቂት ተማርከን
ሳናስብ መላለሰን
አይሆን ይሆን? ብለን
መጠየቅ ቢያቀተን
ማስተዋል ይክበደን??
አይናችንስ ቢሆን
አንዴት ሲቃን ከሳቅ
መለየት ያቅተው
ያለቀሰው ሁሉ ያማረ ይምሰለው
የቆሰለን አይቶ ማዘኑን ቢተወው
ለኔ በሎ ማሰብ
እረ እንዴት ተሳነው?
ምን ይሆን አይምሮን
እንዲ ያጨለምው?....

መልሱን እዚያው ትቼ
መዋተት ቀጠልኩኝ ስጋዬን ዘንግቼ
ስለ ነፍሴ ጮህኩኝ
አሰብኩት ዘመኔን
ትርጉም አልባ ህልሜን
ቀስቃሽ በመጠበቅ
ደጋፊን በመሻት
ዛሬየን ቀብሬ ለነገ ስማቅቅ
ዙሪያዪን ጨርሼ
ባህር ማዶ አልቀረኝ ሁሉን አዳርሼ
እኔነቴን ውጬ ለሌለኝ ስማስን
የጋቱኝን ሁሉ ሳጣጥም በጭፍን
ትርጉሙን ሳልጠይቅ
ሳጌጥ የኖርኩበት
የፊቴን ገፍቼ ሩቅ ያለምኩበት
ያባቴን ቅዱስ ቤት የዘነጋሁበት
ውብ የናቴን ጓዳ ያሽቀነጠርኩበት
የዘመድ አዝማዱን ፍቅር የረሳሁት
ፍቺ ቢስ ቅኔዬን ጠያቂ ስጠብቅ
ሰጥሜ መቅረቴ እያረገኝ ስቅቅ
ባስታወስኩት ቁጥር
ያሳዝነኝ ጀመር
ኋላ ምን ያረጋል
ደቁሶ ማንቋረር?........
ለካ ልምዴ ኖርዋል
ያስቀረኝ አባክኖ
አባናኝ ስናፍቅ አምሮዬ ባዝኖ
ቅዠቴ ማለቁን በረዳም እረፍዶ
በጥገኝነት ጥግ ሃሳቡ ተጠመዶ
እነደኔ ለጠፋው ማንነቱን ከድቶ
ለመጣው ከኋላ በጭፍን ተመርቶ
በእንባ ተሞልቼ ስለምን ስረየት
ብረሳው ለቅስፈት የሃጥያቴን ብዛት
ይባስብሽ ብሎ ሲቃዬን ሲያበዛት
አሳየኝ በአይኔ አመጣው ከጎኔ
ቢያስተወሉ ብዬ ከቀደመኩት ከኔ
በለቅሶዬ ስቀው ተከተሉኝ መጡ
ልመናዬን እንኳን ሳለጨርስ በቅጡ
አረፉት ብሰውት ጥለወኝ መጠቁ
እህህ ማለቴን ማንን በጠየቁ?
ማን በነገራቸው
መውጫው እንደራቀን
ከስጥመቱ ግርጌ
ገብተን እንደቀረን
እማኝ በሌለበት አልቃሽ በጠፋበት
በዛ በጨለማው
መስካሪ እንኳን ጠፍቶ
ሁሉም በእብደታችን
አንድ ላይ ተስማምቶ
አጨብጭቦ ሸኝን
ድምጽን አሰምቶ!!
ወዮ ለቀጣዪ
ለሰማው ጭምጭምታ
እንዳይነዳ እሱም
ቅኔውን ሳይፈታ!!!
# Tsion24
@Gitemenlenante
#Alazar {CJ}

ካንቺ ጋር ሳወራ

ከህይወቴ ቅኔ ከማፈቅርሽ ጋራ
ልክ ተገናኝተን ካንቺ ጋር ሳወራ
በንዴት ቀልቶ የነበረው አይኔ ይጠራና
የጨለመብኝ ቀን ይበራልኝና
የተኮሳተረው ፊቴ በሳቅ ይበራና
የናፈቀሽ ልቤ ደግሞ ይመታና
ልክ አንቺ ስትሄጂ ወዲያው ይቀየራል
የበራው ፊቴ ወዲያው ይጨልማል
የጠራልኝ አይኔ ደግሞ ይደፈርሳል
ልክ አንቺ ስትጠፊ አለም ባዶ ይሆንብኛል
እስከ ምንገናኝ ልቤ ይናፍቅሻል
የኔ ፍቅር ካንቺ ጋር ሳወራ
ይታየኛል የጨለመው ቀኔ በአንቺ ሲበራ
ካንቺ ጋር ሳወራ ይጠፋና ሀዘኔ
ደስተኛ እሆናለው ሀዘን ጠፍቶ ከእኔ
@Gitemenlenante
ምንም አልል...
ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን


እኽ..ሺ እንግዲህ በዝምታ
የልቤን ደም ሥር ትርታ
የደቂቅ እድሜን ትዝታ
ትር ስትል አፍታ ለአፍታ
እያዳመጥኩ እያስታመምኩ ፥ ጊዜዬን እያሠላሠልኩ
ሳልናገር ሳልጋገር ፥ እየደገምኩ እያሠለሥኩ
ሳልሰለች እየመላለስኩ......

እኽ ሺ እንግዲህ በፀጥታ
የልቤን ደም ሥር ትርታ
የእስትንፋሴን ቃል ጉምጉምታ
ትር ስትል አፍታ ለአፍታ
ሳልሰለች እየደጋገምኩ
በእግረ ህሲና እያደቀቅኩ
እየቋጠርኩ እየቆጠርኩ......

እሺ እንግዲህ አልናገርም
በአንደበቴ አልተነፍስም
በልሳኔ አመሰክርም
አልልም። ምንም አልልም
እንዲያው ዝም እንጂ ዝም ዝም
የልቤ ደም ሥር ሲያቃጭል
ልሳኔን ሲያስነሳ ሲያሰጥል
ቃላቴን ሲቃኝ ሲያጋግል
ትንፋሼን ሲያንር ሲያዳውል
ክል ሲል ትር ድም ሲል
ማዳመጥ ማስታመም እንጂ ፥ ሌላ ምንም ምንም አልል።

ጥቅምት ፦ ፲፱፻፷፫ ፒያሳ
ሎሬት ፀጋዬ ገብረ መድሕን
" እሣት ወይ አበባ "
@Gitemenlenante
. . . #ውርሰ_ውበት. . .

ሞትሽን አልመኝም
አንቺ ከሞትሽ ግን...
.
በፈረሶች ፀጉር
ለሚዋቡ ሴቶች
ውርስ ተይላቸው
አብሮሽ አይቀበር
ውበት ይሁናቸው

ብዙ ኩል ቀላቅለው
አሳር ለሚበሉ
ስራ አቅልይላቸው
አይንሽን ይትከሉ


ለቁንጅና ድጋፍ
አፍንጫ ጆሯቸው
ለጌጥ ለሚበሱ
ያንቺን አውርሻቸው
ውብ ጌጥ ነው በራሱ

ሳቃቸው እንዲያምር
ተነቅሰው በመፋቅ
አሳር ለሚበሉት
ጥርስሽን ስጫቸው
ወስደው ያስተክሉት

ሁሉንም አካልሽን
ከአፈር መበስበስ
መቀበር አድኚ
ቆመሽ ብቻ አይደለም
ሞተሽ ውበት ሁኚ

ፀባይሽ ግን ውዴ...
እኔ ያልቻልኩትን
አፈሩ ከቻለው
አደራ አታውርሺ
ፀባይሽ ቢወረስ
ትርፉ መቃጠል ነው
.
ሞትሽን አልመኝም
አንቺ ከሞትሽ ግን...

ውበትን ለሚሹ
ሴቶች አውርሻቸው
እኔም ያንቺ አፍቃሪ

እኔም ያንቺ አፍቃሪ
ውርስሽን ልካፈል
እነሱን ላግባቸው፡፡
@Gitemenlenante
:::::::::::::::::ሰክሬ የፃፍኩት::::::::::::::::::
ሰክሬ የፃፍኩት ፁሁፍ ካልታያችሁ
ፊደላቶች ጎለው ከተምታታባችሁ
ቃላት ተሰባጥረው ስሜት ካልሰጣችሁ
ሰክራችሁ አንብቡት ሀሳቤ ይግባችሁ
@Gitemenlenante
>>>> የሚስት ያለህ <<<<

የክረምቱ ብርድ ደመናው ቢያስፈራኝ
ሚስት ፈለኩና አቅፋ ምታሞቀኝ
ሰማዩን እያየሁ ፎቶ ተነሳሁኝ
ፖስታ ቁጥሬንም በጋዜጣ አውጥቼ
የሚስት ያለህ እያልኩ ጠበኩኝ ጓጉቼ
ሀሳቤም ተሟልቶ በላይ ከገመትኩት
አስር ሺህ ደብዳቤ ደረሰኝ በሳምንት
ሁሉንም በተራ ቸኩዬ ባነበው
ወንዶች የላኩት ነው ሚስቴን ውሰድ ብለው
😁😁😁😁😁😁😁😁😁😁
@Gitemenlenante
ሩቅ የማትባል
ምዕራብ ላይ ያለች ግብፃዊት ወድጄ
አህያ ሳጣ
ደብዳቤ ልካለው አባይ ዳር ወርጄ
====================
የደብዳቤው መግቢያ
የደብዳቤው መደምደሚያ
የደብዳቤው ፍሬ ነገር
ከግድቡ ና ከግድቡ ሌላ...ሌላም አይናገር
=====================
ምላሹን ስትልኪ አትላኪ በወንዙ
የወንዙ አመሉ ወደፊት መጓዙ
ስ..ለ..ዚ..ህ ከወደድሽኝ
መጠነኛ ገንዘብ በእጆችሽ ያዢ
ደብዳቤው ይደርሰኛል ቦንዱን ስትገዢ
================
ስሟን የጠየቀ ወዮለት😁😜

ሳሙኤል አለሙ
@Gitemenlenante
ሰላም ውድ የ ግጥምን ለናንተ ቻናል ቤተሰቦች 👥 ሰላም ለናንተ ይሁን 🙏 ዛሬም የራሷን የግጥም ስራዎች በማቅረብ የምናውቃት ጺዮን {#Tsion} ዛሬም እንደተለመደው እጅግ ማራኪና ድንቅ ስራዋን አቅርባልናለች
እኛም ላቅ ያለ ምስጋናችንን እንገልጻለን
ለገጣሚ #Tsion ከልብ የሆነ ምስጋናችን ይድረስልን 🙏 እንዲሁም ሌሎች የ ቻናላችን ቤተሰቦች የራሳችሁን የግጥም ስራዎች ማድረስና ለሌሎች የቻናላችን ቤተሰቦች በማጋራት ማስተዋወቅ የምትፈልጉ በ Inbox ከታች ባለው Username ልታናግሩኝ ትችላላችው
@AS_CJman 👈ልታናግሩኝ ትችላላችው
የገጣሚ ጺዮን {#Tsion} ስራ ለማየት ለማንበብ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
እማማ

ያለን እጅግ በዝቶ ሞልቶ ቢከመርም፥
እንኳን ዘመድ አዝማድ መንገደኛው ሁሉ፤
ከኛ ማእድ ጠግቦ እረክቶ ቢኖርም፥
እኛ ልጆቿ ግን እንኳን በልተን ልንጠግብ
እንኳን ተርፎን ሊፈስ ቀምሰን የምናድረው
ሰርተን ማቅረብ ከብዶን ረሃብሊገለን ነው
እናት ምን እንዳላት ለልጆቿ ስትል ምን እንዳሰናዳች
ለ አብራኳ ክፋይ ምን እንዳስቀመጠች
ታሪኳን ጠያቂ አንድ ልጅ ብታጣ
ቁጭ ብሎቢያንቋርር ቢቋምጥ ቢንጣጣ
ሳይሰራ ቢመኝው እንዲያው ከየት ይምጣ
ጎረቤቱ ብለህ ታሪኳን ጠያቂ
የህይወት ጉዞዋን ከስር መሰረቱ
ከውልደቷ አንሰቶ እስከነ ጽንሰቱ
እህ ብሎ አድምጦ ሰነድ አገላብጦ
ቁጭ ብላ ስተርክ እያያት አፍጥጦ
ሁሉን ቀስሞ ቀስሞ ከአብራኳ ክፋይ
ከስጋዋ ክፋይ በላይ ለሷ አሰቦ
ዘመዶቹን ሁሉ ቢመጣ ሰብስቦ
ዝናዋን የሰሙት ሁሉም ቋመጡላት
ጥንት ስንት ደሞ ፈሶ ቢመኙ ሊከቧት
አልቻል በሎቸው በልጆቿ ብቃት
የወኒያቸው ማማ እላይ በደርሱ
በናታቸው ፍቅር እንኳንስ በቃላት
በፊደል ሊወሱ
እንዲያው ለማሰበም ከቶ በሚያሳሱ
በውድ ጀግኖቿ በሺ ሚጠበቁ
ሁሉም ደጃፎቿ
ከደጃፏ ቀርቶ ጭራሽ ከቅዬዋ
አፉን አሰግስጎ ልጆቿን ሊበላ
ቢመጣ አሰፍስፎ ወገን አሰልፎ
በጥቂት የሚሸሽ ደካማም አልነበር
እስከጥግ ገፍቶ ለ እናቱ ክብር
ሞቱን እንኳን ሳይቀር ከቁቡ ሳይቆጥር
እንኳን ለቀረቧት ላሰቧትም ከቶ ማስፈራሪያ ነበር
ገፍቶ መለሳቸው የተኑሱባትን
በህልውናዋ ያመሰጠሩትን
የግላቸው አርገው ልጆቿን ሊክዱ
አጎንብሰው መተው አጥበዋት ሊሄዱ
ያልሙትን ሁሉ በአጭሩ የቀጡ
ለ'ናታቸው ጓዳ ክብርን የሰጡ
ማንነቷን አውቀው ከማአዷ ጠግበው
ያላት ላይ ጨምረው ቢሰቅሏት አርዘመው
ዛሬ ላይ እንዳትወድቅ ቢጥሩ ከድሮ
ባረገዘች ቁጥር ባእድ ተመሳጥሮ
እንዳያጨናግፍ ጽንሷን አጭበርብሮ
አላሰበም መሰል ለዛሬዋ እማማ
ብትጮህ ብትለፈልፍ አጥታ የሚሰማ
ጉሮሮዋ ደርቆ አቅሟ ሲከዳት
ጉልበቶቿ ዝለው እጇ ሲርበተበት
ማን ይደግፍ ከቶ አለሁልሽ ይበል
በአፉ እየቀባ ያታልላት ጀመር.....
#Tsion
@Gitemenlenante
::::::::::::::::አቻ::::::::::::::::::
እኔና አንተ ማለት
በራሳችን ጊዜ ፍጹም ሳንተያይ
የፈረቃ ቅጥሮች ጨረቃ እና ጸሀይ
የሩቅ ለሩቅ ጓዶች ምድር እና ሰማይ
እሳት እና ውሀ ጸብ እና ገላጋይ
ቬኑስ እና መሬት
በጋ እና ክረምት
አንድ ሆነን አንድ የሆንን
እኔና አንተ እንዲህ ነን
@Gitemenlenante
2024/10/02 06:27:34
Back to Top
HTML Embed Code: