Telegram Web Link
​​🌹ውዴ አንቺን ብከዳ 📖

................

ምድርና ሰማይ
በአንድነት ተስማምተው
አፍነው ይግደሉኝ
የእውነትን ቃል ጥሰው

ውዴ እኔ አንቺን ብከዳ..
ቁጣ ያዘለ አየር
እስትንፋሴን ነጥቆ
ወደዚያው ያሻግረኝ
የሞት ካባ አጥልቆ

ውዴ እኔ አንቺን ብከዳ...

ገላዬ ይበስብስ
በፍቅርሽ ልቀጣ
ከከበረ አካሌ ትል እስኪወጣ
የምፅዐት ቀን ደርሶ
መክዳት ግድ ቢሆን
አዋጅም ቢወጣ
ፍፁም አልለይሽ የመለየት ሀሳብ
ካንቺ እንኳን ቢመጣ።።።
@Gitemenlenante
"ዕድሜ" ለኮሮና
መለያየት ሞት ነው ~ ብዬ እንዳልዘፈንኩኝ፤
ካንቺ ያስቀድመኝ ~ ብዬ እንዳልማልኩኝ፤
እንቅፋት አይንካሽ ~ ብዬ እንዳልተሳልኩኝ
ክንዴን ሳልንተራስ ~ ብዬ እንዳልፎከርኩኝ፤
እኔ አይደለሁማ ~ .ብዬ እንዳላዜምኩ፤
ክፉሽን እንዳላይ ~ ብዬ እንዳልተቀኘሁ፤
መዝፈኔን ረስቼ፥
ማህላ ዘንግቼ፥
ስለቴ ተዳፍኖ፥
ፉከራዬ መክኖ፥
ዜማዬ ተዛብቶ፥
ቅኝቴ ፈር ስቶ፥
በጥላ ቢስ ወሬ ~ በነጠላ ዜና፤
በአካል ተራራቅን ~ "ዕድሜ" ለኮሮና።
~~~~~~~~~~~~
መጋቢት 29፤ 2012
በናታን ዘ ማሪያም
@Gitemenlenante
🌹🍃🕊​...#የፍቅር_ፀብ

ባብሮነታችን ውስጥ
ጥላቻ ባይኖርም - መናናቅ ነበረ
በመናናቃችን
መለያየት መጣ - አብሮ መኖር ቀረ
አብሮ መብላት ቀረ
አብሮ መዋል ቀረ
አብሮ ማደር ቀረ
ቀረ
ቀረ
ቀረ
ሁሉም ነገር ሲቀር - ናፍቆት ተጀመረ
በናፈቅሽኝ ጊዜ - እንዲህ ስል ነበረ
እንኳን ተለያየን - እንኳን አብረን በላን
እንኳንም ናፈቅሽኝ - ፍቅር ነው ያጣለን፡፡
ባብሮነታችን ልክ
መናናቅ ልብ ላይ - ያኔ የተሰቀለ
አሁን የሚታየኝ
ናፍቆት የምንለው - ናፋቂ ፍቅር አለ፡፡
እንኳን ተለያየን!

( በላይ በቀለ ወያ )
@Gitemenlenante
° ° ° 💔ልቤን ያቆሰለ💔 ° ° °

አልወድህም ስልህ መውደዴን ደብቄ
በጥዑም አልባ ቃላት፣
ልቤን ከናፍሬን በእልፍ አራርቄ
አልወድህም ስልህ ፍቅር እንዳይመስልህ
በአልወድህም ቃላት ልቤን ያቆሰለ
እልፍ መውደድ አለ
@Gitemenlenante
🌹🍃🕊...​#ሱሰኛ_ነኝ

አዎ ሱሰኛ ነኝ ሱሴ እልፍ የበዛ፣
አንድ ሁለት ካላልኩ ፊቴ የማይወዛ፣
ቀኔ የማይበራ ሚጨልም ደንጋዛ፣
አይኔ ማይከፈት እንዲሁ በዋዛ፣

አጨሳለሁ ገና መቼ ተጨሰና፣
የፊደል ጭራሮ መች ተለኮሰና፣
የቃላት ቅርንጫፍ መች ተማገደና፣

በጭሱ ናውዤ በዜማው ሰክሬ፣
አልችልም ልላቀቅ ክፉኛ ታስሬ፣
አዎ ሱሰኛ ነኝ ውስጡ ተነክሬ፣
ድንገት ያጣው ጊዜ አልችልም ዳክሬ፣
ምርኩዝ አያነሳኝ ምቀር ተሰብሬ፣
አዎ ሱሴ በዝቷል ጠልቆ ከደም ስሬ፣

ቃል ከቃል ሲጋጠም በሚፈጥረው ግለት፣
ስቃጠል ኖራለሁ ካጣው ስለምሞት፣

የፊደል ስደራ የወግ አቀማመጥ፣
የቃሎቹ ጉልበት ሲጮሁ ብለው ፀጥ፣
ወኔ ቢስ ሲሰማው የሚያረገው ሸነጥ፣
የሀረግ ሹል ስለት የብዕር ረመጥ፣
ያቅበዘብዘኛል ብሎኝ አላስቀምጥ፣

አዎ ሱሰኛ ነኝ የቃላት ግጥምጥም፣
የቤት መቺዎቹ እኛ ያሉት ፍርጥም፣
ጊዜ ማይሽራቸው ስንቱን ቢሽሩትም፣
አዎ ሱሰኛ ነኝ እኔማ የግጥም::

@Gitemenlenante
🌹🍃🕊...​#ስሞት_ዝም_በይኝ!!

አፎይ እሰይ ልበልበት
ነፍሴም በፀጥታ
ሁሉን ነገር ትታ
እንዲያው ትረፍበት
አይንሽን ሳላየው
ድምፅሽን ሳልሰማ
ከሰው አፍ እርቄ
ማፍቀሬን ደብቄ
መስኮቴን ዘግቼ
ስምሽን ሳልጠራ
ወሬሽን ሳልሰማ
ዝም ጭጭ እንዳልኩኝ
አራሴውልሰዋ፤
:::::::::::::::::::::
እናም አትምጪብኝ
ልቤን አታጓጊው
ከሀጢያት ለመንፃት
ባዶ ተስፋ አትስጪው
መሔጃዬ ሲቀርብ
ሆዴን አታባቢው
የእስከዛሬው ይብቃ
ዳግም አትበድይኝ
ብቻ እረፍት እንዳገኝ
እንዲሁ እንዳለሁኝ
ችላ ችላ ብለሽ
ስሞት ዝም በይኝ!!
:::::::::::::::::::::::::
የኔ ፍቅር
የልቤ ላይ ንግስት
እኔን የገዛሽኝ
የፍቅሬ አመቤት
ሁሌ ምትማርኪኝ
የአይኔ አራብ ስስት
ከዚህ ከደሳሳው
ዘማማው ጎጆዬ
መተሽ ከማታቂው
ገብተሽ ከጓዳዬ
እድል ስጠኝ አትበይ
ጊዜም ስጠኝ አትበይ
ሂጂልኝ ከፊቴ
በሬንም አትግፊ
ከቶም አታንኳኪ
እኔ ብቸኛ ነኝ......
እንደድሮው ሆድሽ
እንዳዛኙ ልብሽ
እራስሽ እራቂኝ
ጣል ጣል አድርጊኝ
እፎይታን እንዳገኝ
ስሞት ዝም በይኝ፤
:::::::::::::::::::::::::
አዎን የኔ ገዳይ
ልትስቂ በእንባዬ
ልታርፊ በሞቴ
የአዞ አንባ አድርገሽ
ሆዴን አታራሪው
ላይጠቅምሽ ላትጠቅሚኝ
ስቃዬን አታብዢው
እናም ሆዴ.....
ደቂቃም አትቆዪ
ዘግይተሻልና
ወደቤትሽ ሂጂ
ሌላም አላስቸግር
በዚህ ብቻ እርጂኝ
ጊዜው ስለሄደ
ቀኑም ስለመሸ
እረፍትን እንዳገኝ
ለፅድቅ እንዲሆንሽ
ስሞት ዝም በይኝ!!!!!
@Gitemenlenante
❤️ፍቅር ማለት ውዴ ❤️

ፍቅር ማለት ውዴ ፨
የህልሙ ዘራችን የዕውን ፍሬ አፍርቶ ፤
ቆንጅየ ልጅ ወልደን...
እሱም ፍቅር ሊማር አንደበት አውጥቶ ፤
ፍቅር ማለት.... እማ? ብሎ ቢጠይቅሽ ፤
ይህንን ንገሪው ሳትፈሪ ሳይጨንቅሽ ፤
........"ፍቅር ማለት ልጀ........
የተራ ሆሄያት ባዶ ጥርቃሚ ፤
የሶስት ፊደል ጥምረት የቀል ልቅምቃሚ ፤
የደቂቃ ስሜት.......
ወይ ጊዜያዊ ጥቅም አይደለም ምስጢሩ ፤
መስጠት+መስጠት +መሰጠት .....በቃ ሁሌም መስጠት
እናም ልጀ ይህ ነው የፍቅር ቀመሩ ፤...."
ብለሽ ንገሪልኝ እንዲገባው አርገሽ ፤
ፍቅርን ሠጥቶ .....
ምላሽ እንዳይጠብቅ በደንብ አስጠንቅቀሽ ፤
...........ደግሞም እንዲህ በይው.........
......ፍቅር ማለት ልጀ...
በአንዲት ውብ ማሳ ውስጥ..
ከአረም ከቁጥቋጦ ፈፅሞ በራቀች ፤
ከአንድ ገበሬ እጅ..
በፅናት ተዘርታ በዕምነት የበቀለች ፤
........... .............ፍቅር ቡቃያ ነች ፤
የአለምን ሃይሎች አጣምሮ ያደላት ፤
የተንኮል ገሞራ .....
የሃሜት አውሎ ንፋስ ገፍትሮ ማይጥላት ፤
ገንዘብ ጎርፍ ሆኖ.....
ስሯን ቢያጥለቀልቅ ፈፅሞ ማይነቅላት ፤
ፍቅር ቡቃያ ናት..........."
......ብለሽ ንገሪልኝ....
ግን ይህን ሁሉ ቃል ከአንደበትሽ ሰምቶ ፤
....ፍቅር ማለት እማ ????
ብሎ ከጠየቀሽ ሳይረዳው ቀርቶ ፤
....ይህንን ንገሪው
"ገበሬው አምላክ ነው ማሳዋ ልባችን ፤
ዘሩ የፍቅር ቃል ቡቃያው ልጃችን ፤"
እንዲያውም እንዲያውም....
ከተራ ቃላት ጋር ምን አፈታተነን ፤
ፍቅር ማለት ውዴ!!!! በቃ እኔና አንች ነን
@Gitemenlenante
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሰላም🖐👋 ውድ የ ግጥምን ለናንተ ቻናል ቤተሰቦች👥 ሰላም ለእናንተ ይሁን እንዲሁም ለመላ የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ 1441ኛው የ ኢድ አል አድሀ አረፋ በአል በሰላም አደረሳችሁ
🌹🍃🕊...​#ለዚህ_ነው_ማላምንሽ

ቃላት አሳምረው፣
ስለ ዝናብ ውበት አድንቀው የፃፉ
ዝናብ የመጣ 'ለት፣
ዣንጥላ ዘርግተው ተጠልለው አለፉ

ልክ እንደዚህ ሁሉ
ንፋስ ነው ዘመዴ ምናምን የሚሉ
ንፋሱ ሲነፍስ መስኮት ይዘጋሉ

ያንቺም ልብ እንዲህ ነው፣
ይቀበል ይመስል ፍቅር ፍቅር ብሎ
ፍቅር ያካፋ ቀን ያልፋል ተጠልሎ
@Gitemenlenante
ቅድም ስትደውይ…
‘’መንገድ ላይ ነኝ’’ ያልኩሽ መንገድ ላይ ሆኜ ነው
የምሄደው ደግሞ ወደ አንች ልብ ነው
አወይ የኔ ነገር ቀልቤን ማን ሰረቀው?
ለካንሳ ልብሽ ከኔ ልብ ጋር ነው
በቀደም በሌሊት…
‘’እንቅልፍ አጣሁ’’ ብለሽ ስትነግሪኝ ደግሞ
እንቅልፍን አየሁት ከጎኔ ተጋድሞ
እልህሽን ልወጣ ንዴትሽን ላበርድ
ከእንቅልፍ ጋር ተኛሁ ሌቱ ቀን እስኪወልድ
ጉንፋን ያመመሽ ቀን…
ጉንፋን ከረሜላ ስበላ ነበረ
ከረሜላው ሟሙቶ ጉንፋን ከኔ ቀረ
በዚህ ምክንያት ነው…
ልብሽ ከልቤ ጋር እንዳለ እያወኩኝ
ጉንፋን ቀልቤን ሰርቆት
ልብሽን ፍለጋ መንገድ የጀመርኩኝ
አንች ሴት ልንገርሽ
መቶ ሺ ሚሊዮን
ዘጠና ዘጠኝ ሺ ሲባዛ በዘጠኝ
ቢሊዮን ከፍ ብሎ እወድሻለሁኝ !!!
@Gitemenlenante
#### የናፈቅከኝ ለታ…#####
---------------------------------
የናፈቅከኝ ለታ…
ሳር ቅጠሉ ሁሉ አንተን ይመስለኛል
ከፊት ከኋላዬ ጎኔ የተቀመጥክ መስሎ
ይሰማኛል።
የናፈቅከኝ ለታ…
የድምፅሕ ወለለት…
በእኩለ ሌሊት ገዝፎ ይሰማኛል፣
ባንቀላፋሁበት…
እንደ ዶሮ ጩኸት፣
እንደ ደብር ደውል፣
እንደ ወፍ ዝማሬ፣ ይቀሰቅሰኛል።
የናፈቅከኝ ለታ…
የሞቀው አልጋዬ…
እንደ ምድር ዋልታ
እንደሙት ሰውነት
እንደደጋን ቆፈን ይቀዘቅዘኛል፣
ለስላሳው አንሶላ
እንደ ደረቅ ቁርበት ይኮሰኩሰኛል።
የተመቸው ነገር ምቾት አይሰጠኝም፣
የጣፈጠው ምግብ
ጣዕሙ አይገባኝም።
( ውሃ እንኳ ያንቀኛል።)
አይገርምም?!
የናፈቅከኝ ለታ…
ጨዋታው ለዛ ቢስ
ሙዚቃው ሁካታ
ፀሐይዋ በረዶ
ቅዝቃዜው እቶን ሆኖ ይሰማኛል፣
ከተፈጥሮ አጋጭቶ
ከሰውኛ ህግጋት ገፍቶ ያስወጣኛል።
የናፈቅከኝ ለታ…
የጨረቃ ውበት አይስብ አይማርከኝ
የከዋክብት ብርሃን ከሉን አይገፍልኝ
ብቻ አንተን ብቻ አንተን አንተን እላለሁኝ።
ዳሩ ምን ዋጋ አለው…
ፀጉርህን ዳብሼ አቅፌ እንዳልስምህ
ድምፅህን እንዳልሰማ ናፍቄ እንዳላይህ
እልፍ ርቀኸኛል!
ህልም ሆነህብኛል!
ቢሆንም…
ወድሃለሁና ትናፍቀኛለህ
በሠዓት በደቂቃ ትዝ ትለኛለህ።
`ወድሃለሁና እናፍቅሃለሁ
ያውም ደስ እያለኝ፣
ተስፋ አለኝ ባንተ ደርሰህ እስክታክመኝ።
ደግሞ…እጠብቅሃለሁ!
ተከተይኝ በለኝ…
እስከዓለም ጥግጋት…
እስከዓለም ፍፃሜ…
ማቄን ጨርቄን ሣልል…እከተልሃለሁ!
ትናፍቀኛለህ…ውዴ…እወድሃለሁ!
@Gitemenlenante
2024/10/02 10:24:26
Back to Top
HTML Embed Code: