Telegram Web Link
#ትንሹ
ትሰማኝ እንደሆን፣
እውነት ካለህማ፣
ከመኖሪያህ ዙፋን፣
ከዚያ ሰማይ ማማ፣
እጆቼን አንስቼ፣
ሳነባ ሳንቧርቅ፣
ደራሽ ያጣው ጊዜ፣
ሰው ከጎኔ ሲርቅ፣
ገና ሳልፈታ አፌን፣
በኮልታፋ አንደበት፣
ምንም በማያውቀው፣
በለጋው ልጅነት፣
ጠብቶ ባልጠገበ፣
በተራባ አንጀት፣
...........
ጥርስ ያልበቀለበት፣
ባዶ ንፁ ድዴ፣
እግሬ ባልፀናበት፣
በምልበት ዳዴ፣
ክፉ ይሁን ደጉን፣
ሳልበቃ ለይቼ፣
ይጥቀመኝ ይጉዳኝስ፣
ሳላውቀው በልቼ፣
ያልበረታው ክንዴን፣
አነሳው ወደላይ፣
ትሰማኛ እንደሆን፣
ሆነህ ከዚያ ሰማይ፣
ሳለቅስ እርር ብዬ፣
እንጥሌ እስኪታይ፣
ፊቴ በላብ ጠቁሮ፣
ገላዬ አድፎ፣
ሀይ ባይ ያጣው እንባ፣
ከጉንጬ ላይ ሰፎ፣
.......,,,,,.
ምነው ምን አርጌ፣
ምን በደል ኖረብኝ፣
ሰው ከፍቶ በኔ ላይ፣
እንዲ ጨከነብኝ፣
እባክህ አምላኬ፣
ትንሹን አስበኝ፡፡
@Gitemenlenante
ለካስ ሰው ይኖራል -
ፍላጎቱን አጥቶ
ህልሙን ተቀምቶ።
*=*****
ለካስ ሰው ይኖራል
*=*****
አፍቅሮ ሲከዳም።
የሚረዳው ሲያጣም።
*=*****
ለካስ ሰው ይኖራል
*=*****
በወዳጅ ተገፍቶ።
በኑሮው ተከፍቶ።
*=*****
ለካስ ሰው ይኖራል
*=*****
ሰርክ ተቸግሮ።
ሌት ተቀን ተማሮ።
*=*****
ለካስ ሰው ይኖራል
*=*****
እምነቱ መንምኖ።
ማንነቱ መክኖ።
*=*****
ለካስ ሰው ይኖራል
****=*****
አንሶ ተተናንሶ
ክብሩን ሚቀብርበት
ሰፊ ጉድጓድ ምሶ።
*=*****
ለካስ ሰው ይኖራል
*=*****
ህሊናውን ሽጦ
የተመካበትን ማንነት ሸቅጦ
*=*****
ደግሞም ሰው ይኖራል
*=*****
ቃልኪዳኑን ምሶ
በቃል ያሰረውን ሰንሰለት በጣጥሶ
**=******
ደጋግሞ ይኖራል ሁሉን እየቻለ
የሰው ልጅ ብረቱ ትህግስት የታደለ።
ካለመኖር መኖር ይሻላል እያለ።
@Gitemenlenante
ሰላም ውድ የ ግጥምን ለናንተ ቻናል ቤተሰቦች👥 በምንለቃቸው ነገሮች በሙሉ ደስተኛ እንደሆናችሁ እርግጠኞች ነን እናም የናንተን ደስታ ወዳጆቻችውም እንዲጋሩ የ ቻናሉን ሊንክ ሼር በማድረግና እንዲቀላቀሉን በማድረግ አብሮነታችሁን አሳዩን 😊 ሰላም ፍቅር ደስታ ከእናንተ ጋር ይሁን 😊
ሀሳብ አስተያየት ካለ በ ውስጥ መስመር (Inbox) @A_CJman ወይም በ @GitemenlenanteBOT ላይ ያጋሩን ፡፡
፨ሒዋኔን አየዋት፨፨፨
///////////////////
ሳጎራጉር ስዉል ክራሬን
ስማትር ፤
በጥልቅ ተመስጦ ዜማን
ስደረድር ፤
የመዉደዴን ፅናት የፍቅሬን
አካሄድ ፤
የትዝታን ዜማ በረጅሙ
መንገድ ፤
ስሜቴን ሰብስቤ ዉስጤን
ተከትየ ፤
እንዲህ ስል ተቀኘሁ ፦፦፦፦፦
-------------------------
<< "በምን ሰበብ ልርሳሽ
ፍቅሬ አካላቴ ፤
አመመኝ ጨነቀኝ
ከፋኝ መከዳቴ ፤
ጠናብኝ ህመሜ
የልብ ስብራቴ ፤
` እባክሽ ሂዋኔ...
ሳላዉቅ አትራቂኝ ፤
በናፍቆት አትቅጭኝ ፤
ቁሞ ሟች አታርጊኝ ፤
-አግኝቶ ማጣቱን ፤
-ወዶ መለየቱን ፤
-ታሞ መጎዳቱን ፤
ፍፁም እፈራለሁ ፤
መለየት የማይችል
ልቤን አዉቀዋለሁ ፤
በዚያች በጨረቃ
ስለፍቅር ብለሽ ፤
ምክንያቱን ንገሪኝ
ለምን ከኔ እንደራቅሽ ??? " >>
-------------------------
`

ብየ ሳጎራጉር....
ጨረቃ ሰምታለች ፤
እንባየን አይታለች ፤
የልቤን ስብራት
ሀዘኔን አዉቃለች ፤
`` ከዚያ በሗላ ነዉ...
ህመሜ ተሰምቷት ፤
መናፈቄን አዉቃ
መጎዳቴ ገብቷት ፤
በጨረቃ አምሳል
ሂዋኔን ያየዋት ፤
በጠቆረዉ ሰማይ
በዳመናዉ መሀል ፤
አይኗ ከዋክብት ነዉ
ብርሀን ይሰጣል ፤
ጥርሷ በረዶ ነዉ
ፈገግታዋ ያምራል ፤
ደም ግባቷ ዉብ ነዉ
ልብን ይማርካል ፤
`` ግና ምን ያረጋል...
ከግዜ ጋር አብሮ
ሁሉም ተቀየረ ፤
ፍላጎቷ ሞልቶ
ልቧም ተሰወረ ፤
እኔም ሌላ እንዳላይ
ዉስጤ እንዳረረ ፤
በማይለቅ ምትሀት
ልቤ ታስሮ ቀረ ::
@Gitemenlenante
*ይቅር በዪኝ*

ደስታዬን ስፈልግ ደስታሽን መንጠቄን፣
የኔን ብቻ እያልኩኝ አንቺን ማሳዘኔን፣

ሳይገባኝ ዝምታሽ ቃልሽን ስጠብቅ፣
ሳላስበው ሄደ ልብሽ ከኔ ሊርቅ፣

ይቅርታ ፍቅሬ ሆይ ማሪኝ እልሻለሁ፣
ሳቄን ስፈልገው እንባ ሆኜሻለሁ፣
ቁጣሽን ስጠብቅ ብዙ አድምቼሻለሁ፣

ያለፈውን ጊዜ ባይቀይር ይቅርታ፣
ፍቅርን ያሳምራል ውዴ ወደ ማታ፣

አንድ ቃል ተንፍሺ ዝምታሽ አይቅጣኝ፣
ገብቶኛል ጥፋቴ ባክሽ ይቅር በዪኝ፡፡
@Gitemenlenante
የማርያም ካህን ነኝ!!!!!!


ሩጩ ያልጠገብኩ፤ ገና ብላቴና፤
በአባቶቼ ቀለም ፤
ጎጆዬ የቆመ፤ መንገዴ የፀና፤
የማርያም ካህን ነኝ፤
ጠግቤ የማድር ፤
እመ ብርሃን ብዬ፤ በስሟ ጥፍጥና።
የአሮንን ጥምጣም፤
የያሬድን ዜማ፤ክህነት ተሸክሜ፤
ማህሌት የምሰሙን፤
ደብር የማቀና፤
በገሞራው ዋድላ፤ በተክሌ ዝማሜ፤
በውዳሴ ማርያም፤
በአንቀፀ ብርሃን፤ ይሽራል ህመሜ።
ሸጋው ልጅነቴን፤
ይህ ለጋ ዘመኔን ፤
ሰአሊነ እያልኩኝ፤ የምገብርላት፤
በባዶ እግሬ ሩጩ፤
በውዳሴ ቅኔ የምዘምርላት፤
የጦቢያ ባለርስት፤ ማርያም ናት ማርያም ናት።
@Gitemenlenante
((( ጃ ኖ
.የእኔን ለእኔ! .........

ምን አጥፍቼ ቢሆን : ግድፈቴን ብታቂ
ጥፍልቴን አጉልተሽ :የማትሳለቂ
ፊቴን ብቻ አይተሽ : ሀሳቤን ምቷውቂ
ምንም ይሁን ምንም : ከኔ ማትደብቂ
ከፋሽም ደስ አለሽ : ጎደለም ሞላልሽ
የቤትሽን ገበና : ሚስጥርሽን ጠባቂ
ከሰው ብትግባቢ :ከሰው ብትስቂ
ሌላ ማይታይሽ : ወረት የማታውቂ
የሀዘኔ ጠላት : ደስታዬን ፈንጣቂ
ምን እንኳ ባይጠፋሽ : ምንኳ ብታውቂ
ደግሜ ልንገርሽ : ደስ ይበልሽ ሳቂ
ከጎኔ ስትሆኚ: ትደምቃለች ሂወት
የራቅሽኝ እንደሆን :ይወርሰኛል ፅልመት
የመንገዴ መሪ : የተስፋዬ መብራት
ለብርታቴ ወኔ : ለመኖሬ ምክንያት
ሞላ አልሞላ ብለሽ : የማትርቂ ከኔ
እንዳንቺ የምኖር : የምትኖሪ እንደኔ
ደስታሽም ደስታዬ : ሀዘንሽ ሀዘኔ
ፈጣሪ ያደለኝ :የእኔን ለእኔ
የክፍተቴ ሙሊት: የወጣሽ ከጎኔ
እንኻንስ በምድር : በዚች አጭር ሂውት
ነፍስሽን ከነፍሴ : ያድርጋት በገነት ።
@Gitemenlenante
🥰🥰ልትወደኝ ነው መሠል


"ጠላትህን ውደድ" ይላል ቅዱስ ጌታ
እያለች ስትነገረኝ ስትሰብከኝ ሰንብታ
ስብከቷን አምኜ
"ወድሻለሁ " ብላት በሰው ፊት አቅልላኝ
ልትወደኝ ነው መሠል ጠለታኝ ሔደች ጥላኝ።
📚📚📚📚📚📚📚📚📚📚
@Gitemenlenante
Forwarded from ʙᴇɴɪᴛᴏ 🐰
የግጥም ችሎታና ፍቅር ላላችው ብቻ ተብሎ የተዘጋጀ አሪፍ እና ምርጥ ቻናል ከእናንተ የሚጠበቀው Join ማለት ብቻ
>>>> የሚስት ያለህ <<<<

የክረምቱ ብርድ ደመናው ቢያስፈራኝ
ሚስት ፈለኩና አቅፋ ምታሞቀኝ
ሰማዩን እያየሁ ፎቶ ተነሳሁኝ
ፖስታ ቁጥሬንም በጋዜጣ አውጥቼ
የሚስት ያለህ እያልኩ ጠበኩኝ ጓጉቼ
ሀሳቤም ተሟልቶ በላይ ከገመትኩት
አስር ሺህ ደብዳቤ ደረሰኝ በሳምንት
ሁሉንም በተራ ቸኩዬ ባነበው
ወንዶች የላኩት ነው ሚስቴን ውሰድ ብለው
😁😁😁😁😁😁😁😁😁😁
@Gitemenlenante
. ተ ረ ት ተ ረ ት .
-----------------------------
ተረት ተረት
የላም በረት
አንድ ሰው ነበረ
በሀብቱ የከበረ
ውልደቱም እድገቱም የሆነ አሜሪካ
ባለው ነገር ሁሉ ጭራሽ የማይረካ
ሲሞላለት ሆዱ 'ሀምበርገሩን' በልቶ
'ጋዴሚት' ይለዋል አልጋው ላይ ተኝቶ።

ተረት ተረት ...
አንድ ሰው ነበረ
በጣም የተማረ
በቃኝን የማያውቅ የጣልያን ተወላጅ
ሁሌም ለአዲስ ነገር ጠዋት ማታ 'ሚባጅ
'ፒዛና ፓስታውን' ጥርግርግ አድርጎ
ይተኛል ጥሩ እንቅልፍ 'ባፋንኩሎ' ብሎ።

ተረት ተረት ...
አንድ ሰው ነበረ
ህልሙ የሰመረ
ጀርመን ነው ሀገሩ
'ምርጥ ዘር' ነው ዘሩ
'ቮግ ቮረስቱን' በልቶ ሞልቶለት አዱኛ
'ሻይሰ' ብሎ ነው ሁሌም የሚተኛ።
ተረት ተረት ...
አንድ ሰው ነበረ
የተመራመረ
ጃፓን ተወለደ
በሮቦት አደገ
ቀን ሲሰራ ውሎ
ሩዙን ቀቅሎ
'ሱሺ' ጠግቦ በልቶ
'ባጋይሮ' ብሎ ያነጋል ተኝቶ።

ተረት ተረት ...
አንድ ሰው ነበረ
አጥቶ የተቸገረ
ኢትዮጵያ ተወልዶ ኢትዮጵያ ያደገ ኩራት ነው 'ራቱ ዛሬም ሆነ ነገ
ቢጠግብም ባይጠግብም ቆሎውን ቆርጥሞ
'ተመስገን' ይለዋል መደብ ላይ ተጋድሞ።

ተረት ተረት ...
እግዜር ከመንበሩ ወደ ምድር ወርዶ
ይጎበኝ ነበረ በየቤቱ ሄዶ
ከእነኚያ ከአራቱ ቆዳቸው ከነጣ
ከየአንደበታቸው መልካም ነገር ቢያጣ
ጥቁሩ ሲያመሰግን የፈለገው ሞልቶ
ያጎደለባቸው አንድ የሆነ ነገር እንዳለ ገምቶ
ሊጨምርላቸው ነጮቹጋ ሄደ አበሻውን ትቶ።

ተረቴን መልሱ
አፌን በዳቦ አብሱ።
-------------------------------
በሜሮን ጌትነት
@Gitemenlenante
#ክፉ_ነሽ_____
,
,
,
,
ማን ያምናል ስላንቺ ለማንስ ብናገር
አንቺ እኮ ለሌላው ምስኪን ነሽ ገራገር
ክፉ ነሽ እንዳልል በጎሽን አልክድም
አሳይተሽኛል ፍቅርን ከአንድ ዐለም
....
ግን ደግሞ ክፉ ነሽ
ማነዉ ጥሩ ያረገሽ
ልቤን እንደ እቃ አርቀሽ ወርውረሽ
ያ ሁሉ ልመና ምንም ካልመሰለሽ
የኔን ኡኡ ማለት ከቁብም ካልቆጠርሽ
ጉዳቴን እያየሽ ጨዋታ ካማረሸ
ዉዴ ሆይ እመኚኝ ግድየለም ክፉ ነሽ፡፡
@Gitemenlenante
2024/10/02 12:32:01
Back to Top
HTML Embed Code: