Telegram Web Link
ይሁን ካልክ ውሰደኝ"
እወድሻለሁ ያልከኝ የእውነት ከሆነ
,,,,,እኔነቴን ወዶ ልብህ ከታመነ
አንተ ከምታውቀው ከፎቶዬ ባሻገር
ልነግርህ የምሻው አለኝ ሌላ ሚስጥር
,,ጠንቅቀህ ብታውቅም መሆኔን ሰው ሀገር
,,,,ስለኔ ማታውቀው አለ ብዙ ነገር

,,አየህ የኔ ወንድም አንተ የምታውቀው
,,,,,,የክት ለብሼ ፣
ብሶቴን አምቄ፣
,,,ስቄ ተፍለቅልቄ፣
,,,የተነሳሁትን
ፕሮፋይሌ ላይ ያየኸውን ፎቶ ነው

,,,በፎቶ እንዳየኽኝ ትጠብቅ ይሆናል
,.....ግን ተሳስተኻል
...ከነበረኝ ሁሉ ብዙው ነገር ጎድሏል
...ከስሜ ብጀምር ስሜ ገረድ ሆኗል
..በአረቦቹ ጩኽት ህሊናዬም ፈዟል
፣ዘይት የጠበሰኝ ፊቴም 2 መልክ አውጥቷል
፣፣ከላይ ታች ስሮጥ ልቤንም ደክሞኛል
....እቃ የማጥብበት ነጋ ተነስቼ
..ፈለግ አውጥተዋል አስሩም ጥፍሮቼ
...እየተንቀጠቀጥኩ የግድ ተነስቼ
...ቆሜ ምውልበት አብጠዋል እግሮቼ
.፤፤፤፤፤
...እናም ወዳጄ ሆይ ይሄ ሁሉ ነገር ሳያስደነግጥህ
....የውስጤን ማንነት ብቻ ተደግፈህ
........መንፈሴን ልታድስ ቁስሌን ልታክመኝ..
.....ፈቃደኛ ከሆንክ ይሁን ካልክ ውሰደኝ።
@Gitemenlenante
{ ባል አገባሽ አሉ }
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧
ለካስ ፍቅርም ያልቃል ይደርቃል እንደ እንጨት ይነጥፋል እንደ ሸጥ
አንዱ እየወደደ ያንዱ ልብ ሲቆርጥ
የወደዱትን ሰው ከማጣት የከፋ
ምንስ ችግር አለ?
ከምድር ወለል በላይ ከሰማይ የሰፋ
ፍቅርና አንሶላ ሲያልቅ አያምርበትም ሲሉ እሰማ ነበር
በእኔ ላይ አየሁት እውነቱን በተግባር
የህይወቴ ጣዕም የመኖሬ ተስፋ
የፍቅሬ ነፀብራቅ ብርሃን ከጠፋ
ኑሬስ ምን ልጠቀም ከቁጥር ባለፈ
ይሻለኝ ነበረ ከሙታን ማህበር ስሜ በተፃፈ
ለካስ ፍቅርም ያልቃል ይተናል እንደ ጉም ይሟሟል እንደ ጨው
ተስፋው ሲጠወልግ ናፍቆት ሲያቀጭጨው
ንፁህ ፍቅሬን ቆርጠሽ ገንድሰሽ ከነ እኔ
ወርውረሽ ጥለሽኝ በእንባ ሲጠፋ ዓይኔ
ትዝታሽ ግን አለ፦
በዛሬ ህይወቴ ትናንትን አያለሁ
ትናንት ዛሬ እንድትሆን እናፍቃታለሁ
ፍቅሬ ሠላም ሁኝ፦
በሄድሽበት መንገድ እሾህም አይውጋሽ
ያንችን ክፉ ለእኔ እንቅፋት አይምታሽ
ከእኔ የበለጠ የወደድሽውን ሰው
ልብሽን ከልቡ ገላሽን ከገላው
አምላክ ያስማማልሽ ህይወትሽ ትቃና
እድሜና በረከት ሠላምና ጤና
ፍፁም ካንች አይራቁ ሁሌም ደስ ይበልሽ
እጎዳብሻለሁ እንዳላይ ተከፍተሽ
ፍቅሬ ደህና ሁኝ፦
በመላዕክት ልሳን ከእውነት ልመርቅሽ
ከሰማይ ከዋክብት ከባህር አሸዋ ይብዛ ዘር አዝርዕትሽ
ዘለአለም ኑሪልኝ ነፅሽ እንደበራ
ጋብቻሽም ይሁን የአብርሃም የሳራ!!
@Gitemenlenante
/////ቆረጠልኝ///////
ማፍቀር መታደል ነው ሲሉ ሠማ ነበር
ተፈቅሮ ከመኖር ሠውን ከማስቸገር
ተፈቃሪ አስለቃሽ ያፈቀረ አልቃሽ በሆነበት አለም
ይብዛም ይነሥም አዲሥ ነገር የለም
አፍቅሬሽ ነበረ አስከ አሁኗ ሠዓት
በምናቤ ፍቅር በትዝታ ናፍቆት
ሐሳቤ ረዝሞ ጎጆውን ቀልሶ
ማገሩን ማግሮ ከቁሞ ምሶሶ
ምርጊቱንም መርጎ ጣራውንም ከድኖ
መሥኮት አበጅቶ የወሬ ቀዳዳ እንዳይኖረው ደፍኖ
ለሠርግ ተዘጋጅቶ ሙዜውንም መርጦ ወጭውን አስልቶ
ባጋጣሚ ፍቅር የወደፊት ተዳር በሐሣብ መሥርቶ
ባንቺ ተማምኖ ሊኖር ተወስኖ ጉልቻ ጎልቶ
ነበረ ሐሳቡ በፍቅርሽ ተማርኮ ልቤ ሞገደኛው
ዛሬ ባንቺ ክደት ቆስሎ የሚደማው
አለሁልህ እያልሽ በተሥፋ አኑረሺው
ዛሬ ቀኑ ሲደርስ ጥለሺው ልሸሺው
አልገባኝም እኔ ካንቺም እኔ አልጠበኩ
ምሠሪውን ሥራ ፈፅሞ ያላወኩ
ለካ አልተዋወቅንም ያኔ አብረን ሥንኖር
እንደምንለያይ ፍቅራችን እነሰደሚቀር
ያኔ ያለማሠቤ
ዛሬ መንገብገቤ
ያኔ ያለ ማሠቤ
ዛሬ እቺን መራቤ
በድቅድቅ ጨለማ ቅንጣት በማይታይበት
ገብቼ ስዋልል ባንቺ ናፍቆት ስሞት
የምትመጪበት ዕለት ቀኑ እንደረዘመ
አንዴም ሳንተያይ ፍቅራችን ከሰመ
ላይነድ አመድ ሆነ ደረቀ ወደመ
--=-=====
ዛሬ አንቺ ቆርጦልሽ የኔ ነገር አብቅቶሽ
ልቤን አድምተሽ ቅስሜን ሠባብረሽ
የሠራካላቴን ውስጤን ሽባ አርገሽ
ጎኔ ሳያገግም ከሌላ ሠው ጋር አዲሥ ፍቅር ጀመርሽ
እኔስ አረግምሽም ተከዳሁኝ ብዬ
የትም አልከስሽም ባንቺ ተበድዬ
ብቻ ግን ቃል አለኝ የምተነፍሠው
አንቺ እንደጎዳሽኝ ፍቅርም ጡር አለው
ይህን ከተናገርኩ በቂ ነው እላለው
ለኔስ አታስቢ ምንም እኔ አሎንም
ገና ሲጀመር አዲስ ነገር የለም
ሺ ግዜ ባፈቅርሽ መቼም ባቶጂኝም
በግድ ብዬም አልለማመጥም
በሄድሽበት መንገድ መጓዝ ቢደክመኝ
አንቺ ሲቆርጥልሽ እኔም ቆረጠል
@Gitemenlenante
" እናቷን ጨረቃ"

ለልቤ ህማም ብዕሬ አልቅሶ
ከቶ ላይቀልልኝ እንባውን አፍሶ
ሊነግርሽ አቀደ…
የኔና አንቺን ታሪክ ሊተርክ ወደደ
እናልሽ መውደዴ…
ፍቅርሽን እያልኩኝ ስላንቺ ማበዴ…
የነግርሻል ስሚው ለምን እንደማይቆርጥ እንደማይችል ሆዴ
:

ይህ የፀደይ ሰማይ ያንቺ ፊት ደማቁ
እንደ አራስ እራስ ሚያሳሳው ገላሽ ሚያሰኘው አትንኩ!
እኚያ ውብ ጥርሶችሽ መከደን ማያቁ
ባንድ ላይ አበሩ
በትንሿ ልቤ ይዘውሽ ገቡና አንድ ላይ አደሩ
በታላቁ ዙፋን አንቺን አከበሩ
እኔን ለማሸነፍ ተፈጥሮዎች ሁሉ አብረው ተባበሩ
እኔና አንቺ ብቻ በምናውቃት ያችቀን
ቃላት ባይወጡንም በመንፈስ ተዋውቀን
አንቺን በንግስና እኔን በባርነት ውል አፈራረሙን
:
ቀን በቀን ተገፍቶ
ጊዜን ጊዜ ተክቶ
ልቤ ላንቺ ፍቅር በፍቅር ተገዝቶ
የንግስናሽ አገዛዝ እጅጉን በርትቶ
የባርነት ቀንበሩ ጫንቃዬን ተጫነና
ባይተዋሩ ልቤ ካንቺ ጋር ለመጓዝ ረጅሙን ጎዳና
ፈሪው አንደበቴ መቶ እንዲናገር
የመንገስሽን ዜና ላንቺው እንዲያበስር
የዋው የኔ አግር
ይከተልሽ ጀመር
ምን ያረጋል ቅሉ…
አሽከር ላያገኛት ንግስቲቱን በግሉ
ሲያያት መፍራት ነው መስገድ ነው ባህሉ
እናም ተገድጄ…
በዘመነ ዘመን በረቀቀ አለም ወረቀት ቀድጄ
እነዳለፈ ትውልድ ዘመኑ እንዳረጀ
የኋሊት ተጉዤ
ደብዳቤ ፃፍኩልሽ እኔ አንቺን ወድጄ
:
እንደው ትዝ ካለሽ
ያ ጥንስሱ ፍቅር የት እንደደረሰ
ልብሽ ካስታወሰ
ስንት አየው ስንት አየሽ እነባዬ ታበሰ
ምን ነካሽ አለሜ…
አንድ ነበርኮ ህልምሽና ህልሜ
እኒያ ድንቅ ምሽቶች እንደምን ተረሱ
አፅናኝ ቃላቶችሽ ዛሬ የት ደረሱ
ጨረቃና ከዋክብት ምስክር የሆኑበት ኪዳንስ ተሰበረ?
ሮሚዮ ጁሊዬት ተብለን ልንኖር ምኞቴ ነበረ
ፈቃድሽ ነበረ
ታድያ በምን ጉድጓድ ዛሬ ተቀበረ
በጊዜያት ሂደት
የገነባነው ቤት
ብዙ ሌት ብዙ ቀን
ጨርሰን ገንብተን
እንዴት በአንድ ጀምበር እናፈርሰዋለን
:
አናም የኔ ንግስት
ለካስ እውነት ኖሯል
ከፈጣሪ ሌላ ሁሉም ይለወጣል
ተብሎ መነገሩ ለዋዛ አይደለም ሰዉ መጠርጠሩ
ልብሽን ስለሚያቅ ልቤ ግን ታመነ
የበደለ እንደሆን በፍ ቅር ሊቀጣ በቁሙ ሰከነ
እንደ ማርትሬዛ ባንገትሽ እንድዞር
ካንቺ ጋር ውዬ ካንቺጋር እንዳድር
ሰው ሳይሆን ማህተብሽ ባረገኝ ምን ነበር
እያለ ተመኘ ዛሬም ታመመ።

ለፍቅርሽ አምልኮ ማህሌት ቅዳሴ ሰዓታት ቆመ
የመውደድ ደመና በአይኔ ተጋርዶ
የትዝታሽ ዶፍ በላዬ ላይ ወርዶ
ቀና ስል ከሰማይ ታዘብኳት ጨረቃን
አታፍርም ስትወጣ ይዛ ድንቅ ውበቷን
አፈርትብላ
ትበተን ትፈንዳ በሙቀቷ ግላ
ይቺ ፍቅር በላ
ይቺ እውነት በላ
ለምን ዝም ትላለች ማን አየን ከሷ ሌላ
ይቺ ሀቅ በላ
ማን ስለሆነች ነው?
ደምቃ ምትወጣው?
ውበቷን በግልፅ ለኔ ብታበራው
ፍቅርሽ በሌለበት ብርሃኗ ምንድነው?
እነዳለው ገጣሚው "እናቷን ጨረቃ"
እኔም አላታለው እናቷን ጨረቃ
ይቺ ነጭ ጭቃ!

:
አፈርትብላ
ትበተን ትፈንዳ በሙቀቷ ግላ
ይቺ ፍቅር በላ
ይቺ እውነት በላ
ለምን ዝም ትላለች ማን አየን ከሷ ሌላ
ይቺ ሀቅ በላ
ማን ስለሆነች ነው?
ደምቃ ምትወጣው?
ውበቷን በግልፅ ለኔ ብታበራው
ፍቅርሽ በሌለበት ብርሃኗ ምንድነው?
እነዳለው ገጣሚው "እናቷን ጨረቃ"
እኔም አላታለው እናቷን ጨረቃ
ይቺ ነጭ ጭቃ!
@Gitemenlenante
።።።።በኔ እና በኔ አለም።።።
ፍቅር በማጣቴ ፈፅሜ ያልጎደልኩ
አፍቃሪ ሳልሻ ብቻዬን ያፈቀርኩ
አደብ ባልገዛ ልብ ከፍቶ በሚያስገባው
ሚዛን ያጣ ፍርዱ ቅስሙን በሰበረው
ቁስልስል ድምትምት ምርቅዝቅዝ ባለው
እርም የማይል ልቤ ምነው ቢበቃው
ተመከር እያልኩ ልመክረው ስዳዳ
ከማይያዝ ንፋስ ወዶ እኔስ ገባው እዳ
በሀሳብ ታቃፊ በሀሳብ ተናፋቂ
እኔነቴን ነጥቆ እሱነቱን አርቃቂ
በእኔ እና በእኔ አለም ብቻ የነገሰ
እደዘመኑ መውደድ በስሜት ያረከሰ
ጥልቀቱ የሚከብድ ከፍታው ገራሚ
ይሄው ብሶብኛል እኔ ያንተ ታማሚ
የማትጨበጠው ንፋሱ ልበል
የልቤን ኡኡታ አልሰማም ብትል
@Gitemenlenante
ፍቅርሽ ታወሰኝ

ግጥም እፅፍ ነበር ስሜቴን ማሳያ
ዛሬ ግን አቃተኝ ስለይ ከአንቺ ጉያ
አንቺ ነበርሽ ውዴ የልቤ ማደሪያ!

መለያየት መስሎኝ በአካል ሲራራቁ
ለካ እንደዛ አደለም ትዝታን ካወቁ
በሀሳብ መንጎድ ነው የፍቅር ሀቁ

አብረን ስናዘግም ከጎኔ ስር ያዩሽ
ብቻዬን ማትረው ባይናቸው ፈለጉሽ
አሁን አንቺን ብሻ ኬት አባቴ ላምጣሽ?

ጫካና ንፈሱ ሳቅሽን የሰሙት
ድንገት ዛሬ ላይ ድምፅሽን ቢያጡት
እኔን ወቀሱ! አሉኝ እሷን አምጣት!

ባንቺ ምመስላት ሙሉዋ ጨርቃ
አንጋጥጬ ባያት ድምቀቷ አበቃ
አንቺ ነበርሽ ለካ የውበቷ አለቃ!

ትላልቅ አይኖችሽ ውልብ እያሉብኝ
ስልምልም እያረግሽ በፍቅር ስታዪኝ
የማደርገው ጠፋኝ አሁን ሲታወሰኝ

በእቅፌ ስር ሆነሽ እስከጫፍ ያየነው
የደራው ከተማ ዘውትር የምንዞረው
ዛሬ ላይ ሳየው ምንም ስሜት የለው!

እኔ ነብርኩ ውዴ ፍቅርሽን የገደልኩ
ቃለአባይ የሆንኩኝ ደስታን ያልታደልኩ
እየው አሁን ፍቅሬ ቅጣቴን ተቀበልኩ!
@Gitemenlenante
ፍቅርሽ ታወሰኝ

ግጥም እፅፍ ነበር ስሜቴን ማሳያ
ዛሬ ግን አቃተኝ ስለይ ከአንቺ ጉያ
አንቺ ነበርሽ ውዴ የልቤ ማደሪያ!

መለያየት መስሎኝ በአካል ሲራራቁ
ለካ እንደዛ አደለም ትዝታን ካወቁ
በሀሳብ መንጎድ ነው የፍቅር ሀቁ

አብረን ስናዘግም ከጎኔ ስር ያዩሽ
ብቻዬን ማትረው ባይናቸው ፈለጉሽ
አሁን አንቺን ብሻ ኬት አባቴ ላምጣሽ?

ጫካና ንፈሱ ሳቅሽን የሰሙት
ድንገት ዛሬ ላይ ድምፅሽን ቢያጡት
እኔን ወቀሱ! አሉኝ እሷን አምጣት!

ባንቺ ምመስላት ሙሉዋ ጨርቃ
አንጋጥጬ ባያት ድምቀቷ አበቃ
አንቺ ነበርሽ ለካ የውበቷ አለቃ!

ትላልቅ አይኖችሽ ውልብ እያሉብኝ
ስልምልም እያረግሽ በፍቅር ስታዪኝ
የማደርገው ጠፋኝ አሁን ሲታወሰኝ

በእቅፌ ስር ሆነሽ እስከጫፍ ያየነው
የደራው ከተማ ዘውትር የምንዞረው
ዛሬ ላይ ሳየው ምንም ስሜት የለው!

እኔ ነብርኩ ውዴ ፍቅርሽን የገደልኩ
ቃለአባይ የሆንኩኝ ደስታን ያልታደልኩ
እየው አሁን ፍቅሬ ቅጣቴን ተቀበልኩ!
@Gitemenlenante
(አብርሃም ሙሉ)
.
አለማሰብሽን ፣ ፈርቼ ሳስበው
አልነበብ ሲለኝ ፣ ፊትሽ የማነበው
ልቤ ደነገጠ
አይኔ አፈጠጠ
ጆሮ ስሬ ቆመ
ጤነኛ አካሌ ፣ ታወከ ታመመ
ያኔ ሽባ ሆንኩኝ ፣ ጥለሺኝ ስትሄጂ
የሌለኝን ስትጠይ ፣ ያለውን ስትወጂ

እንባ ተናነቀኝ
ምግብ መጠጥ ምኔ !!
ማይታመን ነገር ፣
ኣምኖ ለመቀበል ፣ አቅም አጣሁ ወኔ
ጥለሺኝ ስትሄጂ
''ጥላኝ አልሄደችም ፣
እኔን ጠልታ ሌላ ፣ ችላ አልወደደችም''
አልኩኝ በመጠርጠር ፣ ከማመን ጎድዬ
ሺ ግዜ እየጮሁኩ ፣ አንዴ አብዷል ተብዬ።

''ቀን መውጫ ሰዋሽኝ ፣ እንደ አብርሀም በግ
ጥለሽኝ ስትሄጂ ፣
ራሴን አጣሁት ፣ አንቺን በመፈለግ
ክፉ ስትሆኝብኝ ፣ ስለሆንኩልሽ ደግ።''
@Gitemenlenante
ተሻገር ስትባል
:
ፍቃዱ ጌታቸው

<<ነገን አታያትም!>>
ብሎ ያለኝ ዶክተር
በቅጡ ቻው ሳይለኝ ፣ አጠገቤ ሞተ
ሳይንሳዊ እውቀቱ
የለገሰው ትንቢት ፣ ዓይኔ ስር ሻገተ
መቆም ለመሻገር ፣ ዋስ ላይሆን ታወቀኝ
ልቤም በቅፅበቷ
በሞት ላይ ተበተ!
:
ዶክተሩን ያመኑት
ለፍትሐቴ ቄስ ለእርቃኔ ከፈን ፣ ተግተው ሲያሰናዱ
የፀኑት ሊያተርፉኝ
ተዓምር እንዲሆን ፣ ደጀ ሰላም ሔዱ።

ተዓምር ገዘፈ
ነገ ዛሬ ሆነች ፣ ተገኘሁ በእቅፏ
ተነጥቄ ወጣሁ ፣ ከሟቾች ወረፋ!
:
የእድሩን ጥሩንባ ፣ የፀሐይ ሳቅ ውጦት
የወዳጅን እንባ ፣ መፍነክነክ ተክቶት
የሐሴት ፅንሰቱ ፣ ካልጋዬ ሲወለድ
አየኋት ረፍቴን
ካረዳኝ ተናንቃ ፣ አስከትላው ስትሔድ።

ሌላ ቀን
ሌላ እድል
ሌላ መኖር አቅፎኝ ፣ አዲስ ፀሐይ ፈካ
ከትንቢት ይልቃል
ከእውቀት ይመጥቃል
በሕይወት ሲፈልግህ ፣ የእጣህ በረካ።
@Gitemenlenante
። ፀፀተኝ ፀፀቴ ።
እራሴን ደብቆት በነበረው አለም
ላንቺ ለፈለገሽ መኖሩን አልካደም
።።።።።ጨለማን እረስቶ
። ፀሀይን አፍቅሯል አይዋሽም
ታዲያ የፀፀተኝ 1 ኛወው ፀፀቴ
ልቤን የሰማው ለት
። ።።።።።።። ሳላቅሽ መኩራቴ
።።።።።።።።። አውቀሽኝ ማጣቴ
ስጀምር ጨርሰሽ
አጠፋው ።። ማለቴ
ባነሱኝ ጉልበቶች
። በእንባ መደፋቴ
ባይገርምሽ ፀፀተኝ
ምነው ቢቀርብኝ ዘላለም ባልማር
ካንቺ ተጣልቼ ብታረቅስ ከግዜር
።።። አቤት የኔ ነገር
ፀፀቴም ፍቅር ነው
። ሁሌም ውሸት አልችል
።።። ። ። ይሔም👆👆
። ውሸቴን ነው
አንቺ ብትርቂውም
👇👇👇
ፀፀተኛው ልቤ በፀፀት አስቦሽ
።።።። መቼም
።።።።።።።ለዘላለም
በምሽት ትዝታው ፀሀይን አይረሳም።
ረቂቅ መላኩ
@Gitemenlenante
ፍቅርሽ ታወሰኝ

ግጥም እፅፍ ነበር ስሜቴን ማሳያ
ዛሬ ግን አቃተኝ ስለይ ከአንቺ ጉያ
አንቺ ነበርሽ ውዴ የልቤ ማደሪያ!

መለያየት መስሎኝ በአካል ሲራራቁ
ለካ እንደዛ አደለም ትዝታን ካወቁ
በሀሳብ መንጎድ ነው የፍቅር ሀቁ

አብረን ስናዘግም ከጎኔ ስር ያዩሽ
ብቻዬን ማትረው ባይናቸው ፈለጉሽ
አሁን አንቺን ብሻ ኬት አባቴ ላምጣሽ?

ጫካና ንፈሱ ሳቅሽን የሰሙት
ድንገት ዛሬ ላይ ድምፅሽን ቢያጡት
እኔን ወቀሱ! አሉኝ እሷን አምጣት!

ባንቺ ምመስላት ሙሉዋ ጨርቃ
አንጋጥጬ ባያት ድምቀቷ አበቃ
አንቺ ነበርሽ ለካ የውበቷ አለቃ!

ትላልቅ አይኖችሽ ውልብ እያሉብኝ
ስልምልም እያረግሽ በፍቅር ስታዪኝ
የማደርገው ጠፋኝ አሁን ሲታወሰኝ

በእቅፌ ስር ሆነሽ እስከጫፍ ያየነው
የደራው ከተማ ዘውትር የምንዞረው
ዛሬ ላይ ሳየው ምንም ስሜት የለው!

እኔ ነብርኩ ውዴ ፍቅርሽን የገደልኩ
ቃለአባይ የሆንኩኝ ደስታን ያልታደልኩ
እየው አሁን ፍቅሬ ቅጣቴን ተቀበልኩ!
@Gitemenlenante
እየሔዱ መጠበቅ
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
‹‹እየሄድክ ጠብቀኝ›› - ስትይኝ ሄጃለሁ፤
መንገዴ እንዳይጠፋሽ….
በየደረስሁበት፤
ድንቅ ምልክትን - አኖርልሻለሁ፤
አንቺ ላትደርሺብኝ..
እኔ ግን እየሄድሁ - እጠብቅሻለሁ፡፡
*
*
እናምልሽ ውዴ…
አክሱምን እንዳየሽ፤
ታምር እና ታሪክ - ፈፅሞ እንዳይመስልሽ፤
ጠራቢው እኔ ነኝ!
ያለፍኩት በዚያ ነው - ምልክት ይሁንሽ፡፡
አጋጥሞሽ እንደሆን…
ካንድ ውቅር ድንጋይ፤
ሰማይ ጠቀስ ሐውልት - የተፈለፈለ፡
ታምር የሚመስል - ታሪክም ያይደለ፤
አክሱም ሐውልት ላይ…
አንቺን የሚጠብቅ - የኔ ጥበብ አለ!!
ቃልሽን አክብሪ - ቃሌን አከብራለሁ፤
መንገዴ እንዳይጠፋሽ..
በየደረስሁበት፤
ድንቅ ምልክትን - አኖርልሻለሁ፤
አንቺ ላትደርሺብኝ..
እኔ ግን እየሄድሁ - እጠብቅሻለሁ፡፡
*
*
እናምልሽ ውዴ - ላሊበላን አይተሸ፤
ታምር እና ታሪክ - ፈፅሞ እንዳይመስልሽ፤
ፈልፋዩ እኔ ነኝ፤…
ያለፍሁት በዚያ ነው - ምልክት ይሁንሽ፡፡
አጋጥሞሽ እንደሆን…
ካንድ ውቅር ድንጋይ፤
ህንፃ ቤተ-መቅደስ ፤ የተፈለፈለ፡፡
ታምር የሚመስል - ታሪክም ያይደለ፤
በላሊበላ ውስጥ…
አንቺን የሚጠብቅ - የኔ ፅናት አለ፡፡
ቃልሽን አክብሪ - ቃሌን አከብራለሁ፤
መንገዴ እንዳይጠፋሽ..
በየደረስሁበት፤
ድንቅ ምልክትን - አኖርልሻለሁ፤
አንቺ ላትደርሺብኝ..
እኔ ግን እየሄድሁ - እጠብቅሻለሁ፡፡
*
*
እናምልሽ ውዴ - ትክል ድንጋይ አይተሸ፤
ታምር እና ታሪክ - ፈፅሞ እንዳይመስልሽ፤
የኔው መቃብር ነው!
ውድቀቴም እዛው ነው! ምልክት ይሁንሽ፡፡
አጋጥሞሽ እንደሆን…
ባባራ ዘመኑ፤
የራሱን መቃብር - ለመትከል የቻለ፤
መኖር የሚመስል - መሞትም ያይደለ፤
በጢያ ድንጋይ ላይ…
አንቺን የሚጠብቅ - የኔ ውድቀት አለ፡፡
ከውድቀቴ ኃላ - ባይንሽ የምታዪው፤
ታምር የሚመስል - ታሪክ የምትይው፤
ምልክት የሚሆን - መንገድ ስላልተውኩኝ፤
ከመሞቴ በፊት..
ውድቀቴን፤
ሽንፈቴን፤
ከመቃብሬ ላይ - እንዲህ ብዬ ፃፍሁኝ፡፡
ሩጫዬን ጨረስኩ፤
ሰው ነኝ - ተሸነፍኩ!!!
እናምልሽ ውዴ….
‹‹እየሔድህ ጠብቀኝ›› - ያልሽው ቃል ስህተት
ነው፤
ቃሉም ገብቶሽ እንደው…
መራመድ መሄድ ነው፤
መሮጥም መሄድ ነው፤
መብረርም መሄድ ነው፤
አንቺ እንድትደርሺብኝ …
እኔ እየሞትሁ - እጠብቅሻለው!!!
@Gitemenlenante
ሶሊያና

(ኤፍሬም ስዩም)
-----------------------------------

እኔን ከወንበር ላይ
ቀን ያየሁት እንባ
ቀን ያየሁት ደባ
እንቅልፍ አሳጥቶኝ
ወረቀት ላይ ወስዶኝ
……
እርሷን ካልጋችን ላይ
እንቅልፍ አሽኮርምሟት
ቀን ያየችው ሁሉ በቅዠት አልፎላት ……
እኔ ከቃላት ጋር ጦርነት ገጥሜ
በሰው ልጆች ጭንቀት እጅግ ተዳክሜ
በሌሊት ጭንቀቴ የቀን ስቃይ ላበርድ
ከደጋው ሃሳቤ በረሃ ስሰደድ
እንባን በፊደላት …
ፊደልን በቃላት…
ቃላትን በሃሳብ ወረቀት ላይ ልወልድ
ወረቀት ላይ ፅፌ ወረቀቱን ስቀድ …
እንዲህ እየፃፍኩኝ እያሰብኩኝ ሳለሁ
‹‹የኔ ነሽ›› የምላት …‹‹ያንተ ነኝ››
የምትል
ፍቅሬ ሶሊያና ተናገረች መሰል በቅዠቷ
መሃል …
‹‹ተመልከት ወዳጀ እኔም ካልጋየ ላይ
አንተን በመናፈቅ በስሜት ስሰቃይ ››
ቀ…ና ብየ ባያት እውነት አለው ቃሏ
ፍም መስሏል አካሏ
ከሌሊት ልብሶቿ ጡቷ ሾልኮ ወጥቷል
እጇ ተዘርግቶ እግሯ ተከፋፍቷል
እኔን በመጓጓት ደሟ ጠቆጥቶ
ፍቅሯ ተሰውቶ
ስሜቷ ተጎድቶ
አንዳች ነገር አይቶ እንደፈራ ህፃን
ፊቷ ሲሸማቀቅ ፀጉራ ሲበታተን …
ካ,ልጋው ላይ ተፅፎ አየሁት እውነቷን
ፍ...ቅ...ሬ ሶ...ሊ...ያ...ና አወራችኝ መሰል
በቅዠቷ መሃል …
አስተውል ወንድሜ …
ባንተ የቀለም ቅብ በድርሰትህ አለም
የሰዎች ጥላ እንጅ አካላቸው የለም !
ባንተ ከንቱ ድርሰት በወረቀትህ ላይ
የሰው እንባ ሳይሆን ያንተው ነው የሚታይ
በሌሊት ትጋትህ በድርሰት በግጥም በቀለም ሸራህ ላይ
እኔ ውበቱ ነኝ በፍቅርህ ስሰቃይ
ይህ ሁሉ ቢሆንም
ይህ ሁሉ ቢሆንም . . . ወዲህ እንዳትመጣ
በሌሊት ትጋትህ ሃዘን ሳይቀጣ
በ,ኔ ያልጋ ድርሰት ቅፅበታቶች አሉ
ከየሰው አለም የሚመሳሰሉ
ባንተ ቀለም ሸራ በድርሰትህ ፅሁፍ
ዘመን ይታየኛል እኔን የሚያሳልፍ
ይህ ሁሉ ቢሆንም …
የሰወችን እንባ አትፃፍ ግዴለም
የፍጥረትን ሃዘን ስለህ አትዘልቅም
እውነት አለው ብለህ ሃዘንን አታልም
((ያለቀሱም ሰዎች ሃቀኞች አይደሉም ))
ይልቅ የኔን ስሜት ያንተንም እንባዎች
ሁለቱን አሳየኝ
በድርሰት
በግጥም
በቀለም ሸራህ ላይ እኔን ብቻ ሳለኝ !
እኔን ብቻ ፃፈኝ !
‹‹ያልተደሰተች ሴት›› በሚል መፅሃፍህ
ዘ...ላ...ለ...ም አሻግረኝ
ዘ...ላ...ለ...ም ውሰደኝ
ዘ...ላ...ለ...ም አኑረኝ
‹‹የኔ ነሽ›› የምላት …‹‹ያንተ ነኝ››
የምትል
ፍቅሬ ሶሊያና ተናገረች መሰል በቅዠቷ
መሃል …
@Gitemenlenante
2024/10/02 12:35:23
Back to Top
HTML Embed Code: