Telegram Web Link
🇦🇹#ፋሲል_ከነማ ስፖርት ክለብ አሰልጣኝ ውበቱ አባተን የአፄዎቹ አሰልጣኝ አድርጎ ሾሟል!!🇦🇹

ፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ ለ2016 አመት ውድድር የቡድን ግንባታ እቅዱን ቀደም ብሎ በመጀመር አሰልጣኝ ውበቱ አባተን ለሶስት አመት በሚያቆይ የውል ስምምነት አስፈርሟል::

የአሰልጣኝ ውበቱ አባተ ውል በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የፀደቀ ሲሆን በቀጣይ ከስምምነት ላይ የደረሱ ተጫዋቾች ውላቸው ሲፀድቅ የምናሳውቃችሁ ይሆናል::

ፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ ባስቀመጠው የአምስት አመት እቅድ ውስጥ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ዋነኛ አላማቸው ቅድሚያ ቡድኑን በወጣቶች መገንባት ከዛ የዋንጫ ክብሮችን ማምጣት እንደሆነ ገልፀዋል::

የጎንደር ከተማ ከንቲባ የፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ ፕሬዝዳንት አቶ ባዩህ አቡሃይ ፋሲል ከነማ ብዙ ውጣ ውረዶችን አልፎ እዚህ ስለደረሰ እኛም መሰረታዊ ስራዎችን በማስቀጠል ከደጋፊያችን ጋር የተጀመሩ የስኬት መንገዶችን በማብቃት ክለባችን ትልቅ ተቋም እናደርጋለን በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል::

#አሰልጣኝ_ውበቱ_አባተ
እንኳን ወደ አፄዎቹ ቤት በደህና መጣህ!!

🇦🇹#ፋሲል_ከነማ_ከክለብም_በላይ_ነው🇦🇹

@FASILSC
ማስታወቂያዎችን እኛ ጋር ማሰራት ምትፈልጉ @FASILKFCBOT ላይ ያናግሩን
ሀገራችን ኢትዮጵያን በዳኝነት ሙያ ከፍ አድርጋ ያስጠራች ኢንስትራክተር #ሊዲያ_ታፈሰ ለአፄ ፋሲለደስ ስታዲየም እድሳት አለሁ ከጎናችሁ በማለት 10,000 ብር አስገብታለች።

የአፄ ፋሲለደስ ስታዲየም እድሳት ላይ አሻራዎን ስላሳረፉ እናመሰግናለን🇦🇹 🙏

እስታዲየማችን ገንብተን ፋሲልን በአፄ ፋሲለደስ ማየት አልናፈቅንም ??

1000556916617 ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
9900007395047 አማራ ባንክ

#ፋሲል_ከነማ_ከክለብም_በላይ🇦🇹
ይህን ማበረታት ያስፈልጋል።

ከጥቂት ሳምንታት በፊት ፋሲል 100 ሚልየን ብር ለዝውውር መደበ ሚባል ወራ ይናፈስ በነበረ ወቅት .. የክለባችን ሙሉ ጨዋታወችን ከሜዳው ውጭ ማድረጉ እየጎዳው ነው ለሚለው የክለቡ ደጋፊዎች ያሰሙት ጥያቄ ተንተርሼ .. በቃ ለዝውውር ተመደበ ሲባል ዋናውን ጥያቅያችሁን ረሳችሁት እንዴ ብዬ ራሴ ለክለቡ ደጋፊዎች ጥያቄ ኣዘል ፖስት ኣጋርቼ ነበር። በወቅቱ ታድያ ብዙዎቹ ኮመንት የሰጡኝ የክለቡ ደጋፊዎች ኣይ ዝውውሩን ያርጉ እኛም ግን ጥያቄያችንን ኣንረሳም በተለይ የስታድየሙን ጉዳይ ኣንረሳም ኣንተውም ብለውኝ ነበር። ምንም መዋሸት ኣልፈልግም በወቅቱ ያሉኝን ምቀበልም ኣላመንኳቸውም ነበር። ግን ይህው ኣሁን ልክ ሆነው እያየዋቸው ነው። በርቱ ኣቦ ...

ይህን ክረምት እንደ ፋሲል ደጋፊዎች ለክለቡ የተጠቀመበት እስካሁን ኣላየውም። የደም ልገሳ የበጎኣድራጎት ስራ አከናውነዋል 20ሺ የክለቡ ኣባላት የተመዘገቡ ሚከፍሉ ደጋፊዎች እንዲሆን ደጋፊዎች ስራ ሰርተው ተሳክቶላቸዋል። ይህው ኣሁን ደሞ እኔን ምያስደስተኝን ስራ ሊሰሩ ጀምረዋል።

ቃል የተገባልን የእስቴዲየም ማደስ እና ለ ቤትኪንግ ብቁ ማድረግ የሚለው ኣሁን ሰሚ ኣግኝቷል። የፋሲለደስ ስታድየም እድሳት ጀምረዋል። ደጋፊውም የበኩሉን እያረገ ነው እየተደረገ ያለው ርብርብ እጅግ ኣስገርሞኛል። በንግድ ባንክና በኣማራ ባንክ በተከፈቱ ኣካውንቶች የክለቡ ደጋፊዎች ጨምሮ ሌሌች የስታድየም ጥቅም የገባቸው በሙሉ ድጋፍ እያረጉ ነው። እኔም በነገው እለት የኣቅሜን ማግዝ ይሆናል። ይህን ለማገዝ ግዴታ የፋሲል ደጋፊ መሆን ኣይጠበቅኝም። እናንተም ይህን ምታዩ ሁሉ ፋሲልን ለስታድየም እድሳቱ ኣግዙ ። ሌላም ክለብ ቢጀምር ይህን ድጋፍ ልናረግ ይገባል። ችግረኛ ሀገር ነንና ችግራችን በጋራ ማለፍ ኣለብን ባላንጣነት ከስታድየም ሊዘል ኣይገባምና ይህን ስራ ኣግዙ። የሌሎች ክለብ ደጋፊዎችስ ምን እያረጋቹ ነው ??? ኣመራሮቻችሁን ተቆጡ እንጂ ኣሁንኮ ምክንያት ኣላቹ እንደፋሲል እኛም በራሳችን ስታድየም ልንገነባ ይገባል ብላቹ ጓ በሉ እንጂ ?? ..

ዲር የፋሲል ኣመራሮች .. ስታድየም ስሩ ሚለውን የደጋፊያችሁን ጩህት መስማታቹ ያስመሰግናችዋል ግን ይህ ብቻ በቂ ኣደለም ።ምክንያቱም ደጋፊ ጩህት እንዲሰማለት ብቻ ሳይሆን እንዲተገበርለት ይፈልጋልና በቃላቹ ተገኙ። እኔም ዛሬ ጅማርያችሁን እንዳደነቁት ሁሉ .. ጨርሳችሁም ማመስገን እንጂ ምፈልገው .. ቃላቸው በሉ ብዬ መፃፍ ኣልፈልግም። ኣደራችሁን ... ።ይህን ስትሰሙ ግን ሌሎች ክለቦች ኣመራሮችና ደጋፊዎችስ ምን እያሰባቹ ነው ?? የምር ኣስቡበት።

የሚድያ ሰዎችም የውበቱ ኣባተ በ3 ኣመት ሚሰጥ 15 ሚልየን ብር ደሞዝ ብቻ ኣያሳስባቹ።ክለቡ ከዘንድሮ በጀቱ ለኣሰልጣኙ ሚከፍለው በኣመት 5 ሚልየን ብር ብቻ መሆኑ ኣትርሱ ። 15 ሚልየን በኣንድ ኣመት ሚሰጥ እስኪመስል ደሞዝ ላይ ከምናተኩር .. ይልቁንም ለ15ና ከዛ በላይ ኣመት ክለቡንም ሀገሪቷንም ልያገለግል ስለሚችለው ክለቡ ስለሚያሳድሰው ስታድየም ብዙ ብናወራ ይሻላል። ብያንስ ይህ ኣስቀንቶት ስታድየም ልስራ ሚል ክለብ ሊመጣ ስለሚችል።

የፋሲል ደጋፊዎች የ2015 ክረምት ድምቀቶች ናችሁ። እባካቹ ሌሎቻችሁም ቀጥሉ እባካቹ። ክለብ እንድያድግ ሚያረግ ስርኣት ያለው ሊግ ካምፓኒ የለንም እናማ የኳሳችን እድገት ተስፋ የደጋፊዎች ጩህት ብቻ ነውና ኣስቡበት ፕሊዝ።


ከ ግለሰቦች አስተያየት
ከ ኤርሚያስ በላይነህ እናመሰግናለን ጥሩ እይታ ነው 🙏🙏🙏
@FASILSC
@FASILSC
ለ ፋሲለደስ እስቴዲየምን ለማደስ እጃችን እንዘርጋ !!!!!
ስቴድየሞችን ማደስ፣መስራት ኢትዮጵያ እግር ኳስ እድገት አንድ አካል ነው ።

ከነጉድለቱ ሊጋችን እንዲያድግ የበኩላችንን እንወጣ ።
ስደተኛው ክለባችንን ወደ ቤቱ እና ለልጆቹ የገቢ ምንጭ እንዲሆን የበኩላችንን እንወጣ ።

@FASILSC
⚡️ 300 ሚሊዮን ብር !!

ላለፉት ሶስት አመታት "የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ" በሚል ስያሜ ሲጠራ የነበረዉ ፕሪሚየር ሊጉ ከቀጣዩ የውድድር አመት አንስቶ #የኢትዮጵያ_ንግድ_ባንክ_ፕሪምየር_ሊግ በሚል ስያሜ እንደሚጠራ የታወቀ ሲሆን ፤ ለዚህም ባንኩ ለስያሜዉ ለሁለት አመት 300 ሚሊዮን ብር እንደሚከፍል ተረጋግጧል
.
ምንጭ👉 ትርታ 97.6 ሬዲዮ
ስለወድምነታቹህ እናመሰግናለን
እግርኳስ ሊፋቅረን ሊያስተዋውቀን እጂ የፀባችን መስየ መሆን የለበትም ።

እናትዋ ጎንደር በነገስታቶኦቹአ ስም ታመስግናቹሀለች ።
ሊጋችን ከመንደር ንትርክ ወጥቶ ትልቅ የገቢ ምንጭ እንዲሆን የሁላችንም ሀላፊነት ነው ለዛ ማሳያ ስለሆናቹህ እናመሰግናለን ።
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
ሊጋችን ከአህጉራችን ተመራጩ ሊግ እንዲሆን ከልብ እንስራ
@FASILSC
@FASILSC
ሪከርድ ሰባሪወች
👉በ ስቴድየም ማደስ ማሰባሰቢያ ንጉሴ አለሙ
👉በ ደጋፊወች መታወቂያ ማደስ ነጋሽ አከለ
🔴⚪️🔴⚪️🔴⚪️
አብራቹሁን ስለሆናቹህ እናመሰግናለን
አመራሮች ለ ክረምቱ ትልልቅ ዘመቻወች በተግባር አሳይታቹህናል ቀጥሉበት በ ተጨዋች ዝውውር እና ክለብን ወደ ቀድሞ ክብሩ እንደምትመልሱት ጥርጣሬ የለንም ።። ከጎናቹህ ነን
@FASILSC
የአፍሪካ የእግር ኳስ ዉድድር የሜዳ መስፈርትን ባሟላ መልኩ ለማደስና ለማዘመን ዕሁድ በታሪካዊቷ ጎንደር ታሪካዊ ጥሪ ተደርጓል በዚህ ታሪካዊ ቀንና ታሪካዊ ጥሪ ይመለከተኛል የሚል ሁሉ እንዲገኝ ተጋብዘዋልዕሁድ ከረፋዱ 5:00 ሰዓት ስታድየም እንገናኝ

@FASILSC
2024/09/30 07:20:44
Back to Top
HTML Embed Code: