Telegram Web Link
🇦🇹#የፋሲል_ከነማ_ስፖርት_ክለብ_ታሪካዊ_ቀን_ሐምሌ_13_2008_ዓ_ም🇦🇹

ዛሬ ሐምሌ 13 ነው...ወደኋላ 7 ዓመት ስንመለስ የምናገኘው ታሪክ የዛሬዋ ''ሐምሌ 13'' ቀን ፋሲል ከነማ ምናልባትም ከምስረታው ቀን ጋር የምትስተካከል አንፀባራቂና የማይረሳ ድል የተጎናፀፈባት ቀን ናት፡፡ ዛሬ በምናብ ወደ ኋላ 7 አመት ተመልሰን በአፄዎቹ መንደር ''ሐምሌ 13'' የሆነውን ሁሉ ሳይሆን አባይን በጭልፋ እንደሚባለው ያችን ታሪካዊ ቀን "የሐምሌ 13" ትውስታዎቻችን በጨረፍታ ልናስታውሳችሁ ወደድን። ታዲያ እናንተም በሀሳብ መስጫ ቦታው ላይ የእናንተን ትውስታ በፁሁፍና በምስል እንድታካፍሉን ከወዲሁ ተጋብዛችኋል።

ፋሲል ከነማ ከተመሰረተበት 1960 ዓ.ም ጀምሮ ዘርፈ ብዙ መሰናክሎችን፣ በርካታ ውጣ ውረዶችን እና የተለያዩ ስያሜዎችን በማስተናገድ በልጆቹ ፅናት አስደሳች የአሸናፊነት ጊዜዎችን በማሳለፍ አሁን ካለበት ደረጃ ደርሷል፡፡

ፋሲል ከነማ ለበርካታ አመታት ፕሪሚየር ሊግ ለመቀላቀል ጫፍ ላይ በመድረስ ሳይሳካለት በሩን እያንኳኳ የሊጉ መግቢያ በር እንዲገባ ሳይከፈትለት ሲመለስ ብዙ ዓመታትን አስቆጥሯል። ድንበር ተሻጋሪ ዓላማ የሰነቀው ፋሲል ከነማ ባሳለፋቸው ውጣ ውረዶችና መሰናክሎች ሳይበገር ያሁሉ ድካምና ጥረት ፍሬ ያፈራው ልክ የዛሬ ሰባት አመት በዛሬዋ ቀን ''ሐምሌ 13/2008 ዓ/ም'' ነበር !! ይህ ጊዜ በተለይም ጎንደር ከፍተኛ የጭንቅ ምጥ ውስጥ የነበረችበት ወቅት ሲሆን እንኳን ለሰላማዊ እግር ኳስ ጨዋታ ቀርቶ ወጥቶ ለመግባት እንኳ አስጊ የነበረበት ጊዜ ነበር፡፡
ጎንደር ከቀለሟ በተጨማሪ መዓዛዋ አፄዎቹን ዝማሬዋ ደግሞ ፋሲል ከነማን ይሰብካል። ከተማዋ የአብራኳን ክፋይ ከደሟ ጠልቃ ከአጥንቷ ፍቃ አምጣ የወለደችውን የበኩር ልጇን ፋሲል ከነማን በድል ልትሞሽር ሽር ጉዷን አሳልጠዋለች። ደጋፊዎችም ከሚኖሩበት አካባቢ ወደ አፄ ፋሲለደስ ስታድየም መትመም ጀመሩ..በሁሉም የእድሜ ክልል የሚገኙ ደጋፊዎች ድልን አጭደው የደስታ ምርትን ከሚሰበስቡበት ስፍራ ከትተዋል።

ጨዋታው በሰላም እንዲጠናቀቅ ከ400 በላይ የሚሆኑ የስታድየም አስተባባሪዎች ባለ አንፀባራቂ መለያ ልብስ ለብሰው በተጠንቀቅ ቆመዋል። እነዚህ አስተባባሪዎች በኢትዮጵያ የሊግ ታሪክ የመጀመሪያዎቹ ናቸው።

በወቅቱ አፄዎቹ ፕሪሚየር ሊጉን ለመቀላቀል ጫፍ የደረሱበት ጊዜ ነው። ከዛሬ ሰባት ዓመት በፊት በዚች ቀን ፋሲል በሜዳው ከጠንካራው ኢትዮጵያ መድህን ጋር የሚያደርገውን ጨዋታ አሸንፎ ወደ ፕሪሚየር ሊግ የሚያድግበትን ትኬት የሚቆርጥበት ቀን የነበረ ሲሆን ግን ደግሞ የፋሲልን ህልም ለማጨናገፍ በርካታ የተግባር እንቅፋቶች ነበሩ...

ጨዋታው እስኪጀምር ከተማውንና ህዝቡን ስትቃኝ የዋለችው ፀሀይ ዝናብ ላረገዘው ደመና ቦታዋን ለቀቀች..ዝናብ ያረገዘው ደመና የከበደው የሚመስለው ሰማይ ሆዱን ከፍቶ አፄ ፋሲለደስ ስታድየምና በከተማዋ ላይ አንዠቀዠቀው በዚህ ጊዜ ከወደ ቋራ መቀመጫ የሚታየው የደጋፊዎች ትይንት አይንን የሚስብና በግርምት እጅን በአፍ የሚያስጭን ነበር። ለዶፉ አንበገርም ያሉት ቋረኞቹ ተቃቅፈው የውቅያኖስ ሞገድ በሚመስል ጭፈራ ሲዘሉ ሰማዩ ከሚያወርደው ዝናብ ጋር ተደምሮ ወደ ላይ የሚያወጡት ጢስ የአርባ አራቱ ቤተክርስቲያን ካህናት ቋራን ከበው ከርቤና ዕጣን እያጠኑት ይመስል ነበር።

ከፍተኛ ዝናብ በመዝነቡ ምክኒያት ሜዳው ላያጫውት ይችላል ቢባልም ደጋፊዎች ሜዳ ላይ የተኛውን የዝናብ ቋት በጆንያ ፣ በስፖንጅ ፣ በጀሪካን ፣ በሳፋ በመጥረጊያና በተለያዩ ቁሳቁሶች ውሃውን ከሜዳው ማስወገድ ተያያዙት። ጨዋታው በአንድ ሰዓት ዘግይቶ ሲጀመር ደጋፊዎቹ ፋሲልዬ አንተን ባየው አይኔ ሌላው ለምኔ ፣ እናሸንፋለን በፋሲል ሙሉ እምነት አለን እና በሌሎች ዝማሬዎች ድጋፋቸውን ቀጥለዋል።

ጨዋታው ያለግብ በጭንቅ ቀጥሎ 77ኛው ደቂቃ ላይ ውጤትና ታሪክ የቀየረች የጭንቅላት ጎል በአመለ ሸጋው አማካይ ይስሐቅ መኩሪያ ተቆጠረች። በዚያን ቅፅበት ደጋፊዎች ያሰሙት ድምፅ ከተማዋን ከጫፍ እስከ ጫፍ አናጣት።
ጨዋታው በአፄዎቹ 1ለ0 አሸናፊነት ተጠናቀቀ!! በዚህ ጊዜ ደጋፊዎች ተቃቅፈው የደስታ እንባ አነቡ ፣ ዘመሩ ፣ በአፄዎቹ ቤት ታሪክ የፃፉ ተጫዋቾች እና ከፍተኛ የመንግስት አመራሮችን ጨምሮ በጨቀየው ሜዳ ላይ በደረታቸው ተንሸራተቱ ፣ ደጋፊዎች ሜዳ በመግባት ደስታቸውን ከተጫዋቾቹ ጋር ገለፁ ፣ ሜዳው የሰራውን የጭቃ ሸማ ለብሰው ጮቤ ላስረገጣቸው ክለብ የደስታ ምንጭ ነህ ብለው ዘመሩለት!!

አፄዎቹ ''ሐምሌ 13'' ቀንን በልባቸው ላይፍቁ አተሟት!!

የፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ ታሪካዊ የቡድን አባላት ተጫዋቾች ፣ አሰልጣኝ እና ኮችንግ ስታፉች እንዲሁም አመራሮች ለዚህች ታሪካዊ ቀን እንኳን አደረሳችሁ!!

እንኳን አደረሳችሁ!!

🇦🇹#ፋሲል_ከነማ_ከክለብም_በላይ_ነው🇦🇹

@FASILSC
የፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ ይፋዊ ጋዜጣዊ መግለጫ!!

ፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ በ2016 ዓ/ም ስለሚኖረው ዝግጅት፣ የቡድን ግንባታና ተያያዥ ጉዳዮች በተመለከተ ሰኞ ሐምሌ 17/2015 ዓ/ም ከረፋዱ 5:00 ሰዓት ቦሌ በሚገኘዉ ጁፒተር ኢንተርናሽናል ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ አዘጋጅቷል። በመሆኑም የሚዲያ አካላት በስፍራው እና በሰዓቱ ተገኝታችሁ የሚዲያ ሽፋን እንድትሰጡ በአክብሮት ጥሪ እናስተላልፋለን፡፡

ፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ!!

🇦🇹#ፋሲል_ከነማ_ከክለብም_በላይ_ነው🇦🇹

@FASILSC
🇦🇹#ፋሲል_ከነማ_በአፄ_ፋሲለደስ_ስታዲየም_ይጫዎታል!!

ፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ ደጋፊዎች ማህበር አፄዎቹ በአፄ ፋሲለደስ ስታዲየም ጨዋታቸውን እንዲያደርጉ በማሰብ ስታዲየሙን ካለበት ደረጃ በማሻሻል ጨዋታዎችን ለማካሄድ ዝግጁ እንዲሆን ለማድረግ በዘርፉ ልምድ ያላቸውን ኮሚቴዎች በማዋቀር ስታዲየማችን ለማደስ ከጎንደር ከተማ አስተዳደር ጋር በመተባበር ወደ ስራ መግባታቸውን እየገለፁ ስታዲየማችን የፕሪሚየር ሊግ እና የአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ እና ኮንፌዴሬሽን ካፕ ውድድሮችን ለማዘጋጀት ብቁ እስኪሆን ድረስ ስራቸውን ከመላው አለም ገሚገኙ ደጋፊዎቻችን እና አጋር ድርጅቶች ጋር ለማሳካት የስታዲየም እድሳት ጅማሮ ተደርጓል!!

ፋሲል ከነማ በጎንደር አፄ ፋሲለደስ ስታዲየም ላይ ጨዋታውን ማድረጉ ከሀገር ሀገር ተዟዙሩው በርካታ ጨዋታዎችን መታደም ለማይችሉ ብሎም በስፖርቱ የከተማችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይረዳን ዘንድ ሁሉም የስፖርቱ ቤተሰብ ድጋፍ እንዲያደርግ በክለባችን ስም ጥሪ እናስተላልፋለን።

. 🇦🇹#ፋሲል_ከነማ_ከክለብም_በላይ_ነው🇦🇹

@FASILSC
አሰልጣኝ ውበቱ አባተ መግለጫ እየሰጠ ነው ።
🇦🇹#አሰልጣኝ_ውበቱ_አባተ
በፋሲል ከነማ ያልጨረስኩት ስራ በመኖሩ ተመልሻለው!!

ፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ አሰልጣኝ ውብቱ አባተን ለ3 አመት በሚቆይ የውል ስምምነት የአፄዎቹ አሰልጣኝ አድርጎ ሹሟል!!

የጋዜጣዊ መግለጫውን አጠቃላይ ሁኔታ በፁሁፍ እናቀርባለን ::

🇦🇹🇦🇹#አሰልጣኝ_ውበቱ_አባተ
እንኳን ወደ ቤትህ በደህና መጣህ!!🇦🇹🇦🇹

. 🇦🇹#ፋሲል_ከነማ_ከክለብም_በላይ_ነው🇦🇹

@FASILSC
ፋሲል ከነማ አሰልጣኝ ውበቱ አባተን መሾሙን ይፋ አደረገ!

አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ምን ይጠበቅባቸዋል ?
አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ክለቡ ያስቀመጣቸውን ግቦች ማሳካት ይጠበቅባቸዋል የተባለ ሲሆን በመጀመሪያ ዓመታቸው ተፎካካሪ ቡድን ማሳየት ይኖርባቸዋል ተብሏል።

ምንም እንኳ በመጀመሪያ ዓመት ተፎካካሪ ስብስብ ቢገነባም ቡድኑ ለዋንጫ አይጫወትም ማለት እንዳልሆነ የክለቡ ፕሬዚዳንት እና የጎንደር ከተማ ከንቲባ አቶ ባዩህ አቡሃይ አሳስበዋል።

ክለቡ በ 2017 ዓ.ም የፕርሚየር ሊጉን ዋንጫ እንዲያነሳ ከክለቡ አመራሮች ለአሰልጣኝ ውበቱ አባተ ሀላፊነት ተሰጥቷቸዋል።

የክለቡን እቅድ ለማስፈፀም ሀላፊነት መውሰዳቸውን የገለፁት አሰልጣኝ ውበቱ አባተ " የእኔ እቅድ የክለቡ እቅድ ነው " ሲሉ " በስነ ምግባር የታነፁ ፣ ለምጫወተው ጨዋታ የሚሆኑ እና ወጣት ተጫዋቾችን " በዝውውር መስኮቱ እንደሚያስፈርሙ ተናግረዋል።

ፋሲል ከነማ አሰልጣኝ ውበቱ አባተን መቅጠራቸውን ተከትሎ ከሶስት እና አራት ዓመታት በኋላ በሊጉ በአማካይ በእድሜ ትንሹ ቡድን እንዲሆን መታቀዱ ተገልጿል።

የክለቡ ውጤት ማጣት ምክንያቱ ምን ነበር ?

የፋሲል ከነማ ፕሬዝዳንት አቶ ባዩህ አቡሃይ በ 2015ዓ.ም የውድድር ዘመን ክለቡ ላስመዘገበው ውጤት የተጫዋች ፣ ልምድ እና የስነ-ምግባር ከፍተትን በምክንያትነት አስቀምጠዋል።

አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ምን ያህል ያገኛሉ ?

አሰልጣኝ ውበቱ አባተ በክለቡ ለቀጣዮቹ ሶስት ዓመታት ሲቆዩ " ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ አሰልጣኞች ባልተጋነነ ዋጋ የሀገሪቱ እግር ኳስ የሚከፍለውን ክፍያ " እንደሚከፈላቸው አቶ ባዩህ አቡሃይ ገልፀዋል።

አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሀላፊነታቸው በፊት በሰበታ ከተማ ፣ ፋሲል ከነማ ፣ ኢትዮጵያ ቡና እና በሱዳን አል አህሊ ሸንዲን ማሰልጠናቸው የሚታወስ ነው።
2024/09/30 09:29:53
Back to Top
HTML Embed Code: