Telegram Web Link
ፋሲል ከነማ ደጋፊወች ማህበር 👏👏👏

የፋሲል ከነማ ደጋፊዎች ማህበር
2,000,000 ሁለት ሚሊዮን ብር
በመለገስ አሻራቸውን አሳርፈዋል

አፄውን ሜዳው ላይ ለማየት ጓጉተናል። በቀዩ እና ነጩ ጃኖ ቀለማችን ሜዳ ሙሉ ቤተሰባዊ ፍቅር ዘርተን ህይወት ስለተገበረው ክለባችን እየዘመርን የረዥም ጊዜ ናፍቆታችን እንወጣለን።🇦🇹
ና ና ና ና
ፋሲሌን ና በለው
ቋራላይ ሁነን እየጠበቅን ነው
ና ናና ና ና ና
ፋሲሌን ና በለው
ምንቲ ላይ ሁነን እየጠበቅንህ ነው
🔴⚪️🔴⚪️🔴⚪️
@FASILSC
@FASILSC

#ፋሲል_ከነማ_ከክለብም_በላይ_ነው_የምንለው_በምክንያት_ነው

👏👏👏👏👏👏🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹
ቆይታ ከ ሀብታሙ ተከስተ ጋር

👉እግርኳስን ቀለል አድርጎ ከሚጫወቱ ተጫዋቾች መካከል አንዱ እንደሆነ ይነገርለታል፤ ብዙዎች የመሀል ሜዳ ሞተር ብለዉ ይጠሩታል

👉የቆይታችን የጀመርነዉ በዚህ ጥያቄ ነበር፤ በ 2015 ከክለብህ ጋር አልታየህም በምን ምክንያት ነዉ? እንደታመምክ ብዙዎች ሰምተዋል አሁንስ እንዴት ነህ? ብለን ጠይቀነዋል፤ የመሀል ሜዳ ተጫዋቹ ሀብታሙ ተከስተ ምላሹን እንዲህ ሲል ገልፆልናል

" ትንሽ ህመም አሞኝ ነበር ስለ ታመምኩ ነዉ ከቡድኑ ጋር 2015 ያላሳለፍኩትስ፤አሁን እግዚአብሔር ይመስገን ጥሩ ላይ ነኝ ቀለል ያሉ ልምምዶችን ቤት ዉስጥ እየሰራሁ ነዉ" በማለት ተጫዋቹ ምላሹን ሰጥቶናል::

👉በፋሲል ከነማ ትቆያለህ ? ቀጣዩ የሸገር አሬና ጥያቄ ነበር።

ተጫዋቹም " አዎ እቀጥላለሁ 2014 ላይ ነበር ፊርማየን ያስቀመጥኩት 2015 እና 2016 እንድጫወት እና ቀሪ ኮንትራት አለኝ 2016 ለፋሲል ከነማ እጫወታለሁ" በማለት ምላሹን ሰጥቶናል።

👉በ2016 ከፋሲል ከነማ ጋር የምትቀጥል ከሆነ በግልህ እንዲሁም እንደ ቡድን ምን ለማሳካት አስበሀል?

" ከእግዚአብሔር ጋር ቀጣይ አመት ለዋንጫ ነዉ ምጫወተው ቡድናችን በጥሩ ደረጃ ገምብተን እንደ በፊቱ እንደ ድሮ ክብራችንን ለዋንጫ እና አስፈሪ ስብስብ እንዲኖረን ፍላጎታችን በግል ደግሞ አንድ አመት ከእግር ኳስ እርቄ ስለነበር በደምብ ሰርቼ ተመልካች በሚያዉቀኝ ልክ ለመገኘት ጠንክሬ መስራት ነዉ የኔ እቅድ"

አዘጋጅ - ናትናኤል ፋንታሁን
ሐምሌ 21/2015
ምንጭ - ሸገር አሬና ስፖርት
@FASILSC
@FASILSC
ሱራ ና ይሁን

ለብሔራዊ ብድናችን ልምምድ ላይ

@FASILSC
ከወንፊት ተራራ ላይ ሁኖ ለሀገራችንን የኳስ ፍቅር ያሳየን ሽሬ ድረስ በመሄድ የደጋፊ ምንነትን ያሳየን ; አዳማ ላይ ውብ ሃገሬ ውብ ሀገሬ ባች እኳነው መከበሬ ብሎ በእምባ ያራጨን ;ዝናብ ብርድ ያልበገረው ; ሊጋችንን ከ አንድ ቲም የበላይነት ያላቀቀ; በእግርኳሱ ባህልን እሴትን ታሪክን ያካፈለን ; ብቻ በአፄወቹ ተሰይሞ ከነገስታቶች መናገሻ ንግስናውን በጃኖ ያለበሰን ወደሜዳው እንዲመለስ እና የከተማችን ኢካኖሚ ዋልታ እዲሆን እጃችንን እዘርጋ ።

አብረን ስለሆንን እናመሰግናለን
we are emperors 💪
🇵🇪🇵🇪🇵🇪🇵🇪
#የፕሮግራም_ለዉጥ
ለመላዉ የፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ ደጋፊዎች እና የስፖርቱ ማህበረሰብ በነገዉ ዕለት ሊካሄድ ፕሮግራም ተይዞለት የነበረዉ የአፄ ፋሲለደስ ስታድየም ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በተለያዩ ምክኒያቶች ወደ ሌላ ቀን የተላለፈ በመሆኑ የቀን ቅያሪዉን እና የሚጀመርበት ቀን በቅርብ ቀናት የምናሳዉቅ ይሆናል::

@FASILSC
ፋሲል ከነማ /አፄዎቹ/ የኛ
Photo
አጼ ፋሲለደስ ስታዲየም

በከተማዋ እምብርት ላይ የሚገኘውና በ1960ዎቹ እንደተገነባ የሚነገርለት እድሜ ጠገቡ አጼ ፋሲለደስ ስታዲየም ሰላሳ ሺ የሚደርሱ ተመልካቾችን የማስተናገድ አቅም እንዳለው ይገመታል። ስታዲየሙ በአብዛኛው ለእግርኳስ ግጥሚያዎች የሚያገለግል ቢሆንም አልፎ አልፎ የአትሌቲክስ ውድድሮችና ማህበራዊ ጉዳዮችንም ያስተናግዳል።

በጎንደር ከተማ አስተዳደር ወጣቶችናስፖርት መምሪያ ባለቤትነት የሚተዳደረው ይህ ስታዲየም በተለይ ለፋሲል ከነማ ደጋፊዎች ከስቴዲየምነት በላይ ልክ እናታቸው ቤት ፍቅር የሚዘግኑበት ፡ ደስታን የሚመገቡበት ፡ ሀዘንን የሚካፈሉበት እርስ በእርስ የሚደጋገፉበት ፡ የጠፋ የሚገኝበት ፡ የተጣላ የሚታረቅበት ፡ ጀግና የሚወደስበት ፡ ችግር የሚፈታበት ፡ ሀዘን የሚረሳበት ስታዲየም ነው። ፋሲል ከነማ በአጼ ፋሲለደስ ስታዲየም ጨዋታ ሲኖረው የአጼዎቹ ደጋፊዎች በስታዲየሙ ይፈሳሉ። ጎንደር በቀይና ነጭ ቀለማት ትደምቃለች ወጣት ፡ ሽማግሌ ፡ ህፃናት ፡ ሴት ፡ ወንድ በስታዲየሙ ዙርያ ክለባቸውን ለመደገፍ ይሰበሰባሉ። በአባቶቻችን የባህል ልብስ በሆነው ጃኖ ማልያ ተውበው በቀይ እና ነጭ ባንዴራ አጊጠው አንጋፋው ቡድናቸውን በአንጋፋው ስታዲየም ይደግፋሉ።

ጎንደርን እንደቆረቆሯት በሚታመኑት ንገሱ አጼ ፋሲለደስ ስም የተሰየመው ፋሲለደስ ስታዲየም - በዙሪያው ተመልካቾች ወደ ሜዳ የሚገቡበት እና የሚወጡበት አራት በሮች
- አራት የመቀመጫ ክፍሎች
- የተጫዋቾች መልበሻ ክፍል
- ለሚዲያ አካላት ግልጋሎት የሚውሉ ክፍሎች
- ለተመልካች የሚሆኑ መፀዳጃ ቤትና መለስተኛ የሩጫ ትራክን በውስጡ ይዟል።

የአጼው ፋሲለደስ ስታዲየም የአጥር ስራው በ1966 ዓ.ም በጣሊያናዊ መሐንዲስ ጆሜትሪ ማካኛ የተከናወነው ሲሆን የተመልካች መቀመጫዎች ደግሞ በ1980ዎቹ መጀመሪያ አካባቢ እንደታነፁ መረጃዎች ያመለክታሉ። ከዚህም ሌላ ስታዲየም ተገንብተው ያላለቁ ሁለት መቀመጫ ክፍሎች አሉት።

በነገስታቶች ስምና በፋሲል ከነማ መለያ ቀለማት ያሸበረቀው ስታዲየም ከሀገራችን ስታዲየሞች ለየት የሚያደርገው ተመልካቾች የሚቀመጡበትን ቦታ ከጎንደር ነገስታቶች ታሪክ በመነሳት የተሰየሙ መሆናቸው ነው። እነዚህ የስታዲየም ክፍሎች ቴዎድሮስ (ጥላ ፎቅ) : ቋራ(ካታንጋ) : ምንትዋብ (ዳፍ) : እና ዞብል(ሚስማር ተራ) በመባል ይጠራሉ። እንዲሁም በርካታ ክፍሉ በተራራ የተከበበው ስታዲየም ጨዋታ በሚካሔድበት ወቅት ከስታዲየሙ ዙርያ በሚገኙ ተራሮች ላይ በመሆን ጨዋታዎችን የሚከታተሉ ተመልካቾች አይጠፉም። ይህም የስታዲየሙ አምስተኛ ክፍል እስኪመስል ድረስ በቁጥር በርካታ የሆኑ ተመልካቾችን በወንፊት ተራራ መመልከት የተለመደ ሁኔታ ነው።

ይህ ስታዲየም እስከ 1996 ድረስ ሦስት የመቀመጫ ክፍሎች ብቻ የነበሩት ሲሆን በ1996 ከሰሜን ጎንደር ወረዳዎች በሙሉ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ በአሁኑ ሰዓት ቴዎድሮስ በመባል የሚጠራውን የመቀመጫ ክፍል ሊገነባ ችሏል። በ2003 ዓ.ም የሜዳው ክፍል ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ ታድሶ አሁን ያለውን ገፅታ እንዲይዝ ሆኖል።

ከላይ እንዳያችሁት አብዛኛውን ነገሩ የተሟላ ስታዲየም ነው : ዛሬ ላይ ትንሽዬ እድሳት ነው የሚያስፈልገው። አብዛኛውን ስራ ከእኛ በፊት የነበሩ በሚገባ ሰርተው ተንከባክበው እዚህ አድርሰውታል ዛሬ ላይ ደግሞ የእኛ ተራ ደርሶል ስለዚህም ለከተማችን ትልቅ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴን የሚያፋጥን እና የከተማዋን እውቅና ከፍ የሚደርግ ተግባር ስለሆነ : በርካታ ውድድሮች በዚህ ከተማ እንዲካሄድ ሁላችንም በምንችለው አቅም ይህን ሀሳብ ይዘው የተነሱትን አንድ እርምጃ ከፍ እንዲሉ ብሎም እንዲጨርሱ የተቻለንን ድጋፍ እናድርግ። በጎንደር እና አካባቢዋ ያሉትን ብቻ ሳይሆን በመላው ሀገሪቱ የምትገኙ በስፖርቱ ዙሪያ ያላችሁ እንዲሁም ለከተማዋ አንድ ከፍታ የምትመኙ ሁሉ ይመለከተናል እና እዚህ ስራ ላይ አሻራችን እናሳርፍ።

የሀገራችን እግርኳስ አንድ ደረጃ ከፍ ብሎ dstv ይዞ ከመጣ እኛ ደግሞ ከ13 አመት በፊት 2003 ዓ.ም እንደተቀመጠ ያለውን ስታዲየም አንድ ደረጃ ከፍ ማድረግ አለብን።

ምንጭ : የክለቡ የመጀመሪያ መጽሔት / 1ኛ ዕትም
22-11-2015 Seblewongel Kassahun

@FASILSC
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አሰልጣኝ ውበቱ አባተ እንኳን ደህና መጣህ!!

ፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ አሰልጣኝ ውበቱ አባተን የአፄዎቹ አሰልጣኝ አድርጎ ከሾመ በኃላ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ከቡድናቸው ጋር የሚቀጥሉ እና የማይቀጥሉትን ተጫዋቾች በመለየት ያሳወቁ ሲሆን በለቀቁ ተጫዋቾች ምትክ አዲስ ተጫዋቾችን ወደ ስብስባቸው እየቀላቀሉ ይገኛሉ:: በቀጣይ በፈረሙ እና ወደ ስብስቡ የሚቀላቀሉ ተጫዋቾችን የፊርማ ውላቸው በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ሲፀድቅ በገፃችን የምናሳውቃችሁ ሲሆን ይሄን የተጫዋቾች ዝውውር ሂደት በትዕግስት እንድትጠብቁን ከታላቅ አክብሮት ጋር መልዕክታችንን እናስተላልፋለን::

ዳሽን ቢራ የፋሲል ከነማ የሁልጊዜም አጋር!!

. 🇦🇹#ፋሲል_ከነማ_ከክለብም_በላይ_ነው🇦🇹

@FASILSC
ፋሲል ከነማ ጌታነህ ከበደን በይፋ አስፈርሟል

የቀድሞው የብሄራዊ የፊት መስመር እንዲሁም የደደቢት, ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ባለፉት አመታት የወልቂጤ ከነማ ተጫዋች አፄዎቹን ተቀላቅሏል

ተጫዋቹ በብዙ ክለቦች ስሙ የተነሳ ቢሆንም ዛሬ ጠዋት ለሁለት አመት ለፋሲል ፈርሟል

እንኳን ደና መጣህ የተሳካ ጊዜ እንዲሆንልህ እንመኛለን🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹


@FASILSC
እንኳን ደና መጣህ 🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹


@FASILSC
የቅድመ ዝግጅት ጥሪ🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹

ክለባችን ፋሲል ከነማ ለ2016 ዓ.ም የፕሪሚየር ሊግ ውድድር ተጠናክሮ ለመቅረብ የተለያዩ ዝውውሮችን በማከናወን የቆየ ሲሆን ከ ሀሙስ ነሀሴ 11 ጀምሮ ታደሰ ኢንጆሪ ሆቴል መቀመጫውን በማድረግ የቅድመ ውድድር ዝግጅቱን ያደርጋል።

ስለሆነም አዳዲስ ክለባችን የተቀላቀላችሁ እና ውል ያላችሁ ተጫዋቾች ከላይ በተጠቀሰው ቀን በመገኘት ሪፖርት እንድታደርጉ ስንል ጥሪ እናስተላልፋለን በቆይታችሁም መልካም የዝግጅት ጊዜ እንዲሆንላችሁ እንመኛለን።


@FASILSC
#የዝውውር ዜና

አፄዎቹ በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ እየተመሩ ለ2016 ዓ.ም ተጠናክረው ለመቅረብ ዝዉዉሮችን በማድረግ የቆዩ ሲሆን መነሻውን በዳሽን ቢራ ስፖርት ክለብ አካዳሚ አድርጎ የተለያዩ ክለብም ተጫውቶ እንዲሁም ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን እና ላለፉት ሁለት አመታት ለቅዱስ ጊዮርጊስ ቤት ተጫውቶ ውጤታማ የነበረውን የመስመር አጥቂ ተጫዋች አማኑኤል ገ/ሚካኤልን ለ 2 አመት ውል የግላቸው አድርገዋል።

አዲሱ የክለባችን የመስመር አጥቂ አማኑኤል እንኳን ደና መጣህ ወደ ታላቁ ፋሲል ከነማ እያልን በቆይታህም መልካም የዝግጅት እና የውድድሮ አመት እንዲሆንልክ እንመኛለን🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹



@FASILSC
#የዝውውር ዜና🇦🇹
አፄዎቹ በአሰልጣኝ ውበቱ እየተመሩ 2016 ዓ.ም ተጠናክረው ለመቅረብ ዝውውሮችን እያደረጉ ሲሆን መነሻውን በአዳማ ታዳጊ ቡድን አድርጎ እንዲሁም በአዳማ ዋና ቡድን ስኬታማ ጊዜ ያሳለፈው ሁለገቡን የመስመር ተከላካይ እዮብ ማቲያስ ለ2 አመት ውል የግላቸው አድርገዋል።

አዲሱ የክለባችን የመስመር ተከላካይ እዮብ እንኳን ወደታላቁ ፋሲል ከነማ በደና መጣህ እያልን በቆይታህም መልካም የዝግጅት እንዲሁም የውድድር አመት እንዲሆንልክ እንመኛለን።🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹


@FASILSC
#የዝውውርዜና🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹

አፄዎቹ በአሰልጣኝ ውበቱ እየተመሩ 2016 ዓ.ም ጠንክረው ለመቅረብ ዝውውሮችን በማድረግ የቆዩ ሲሆን ላለፉት 2 አመታት በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤት እንዲሁም በዋልያዎቹ ስኬታማ ጊዜ ያሳለፈውን የተከላካይ መስመር ተጫዋች ጋቶች ፖኖምን ለ 1 አመት ውል አስፈርመዋል።

አዲሱ ፈራሚያችን የተከላካይ አማካኝ መስመር ተጫዋች ጋቶች እንኳን ደና መጣህ ወደ ታላቁ ፋሲል ከነማ እያልን🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹

በቆይታህም መልካም የልምምድ እና የውድድር ጊዜ ይሁንልክ።


@FASILSC
#አፄዎቹ በሀዋሳ ቅድመ ዝግጅታቸውን እያደረጉ ይገኛሉ!

ለ2016 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ ጠንካራ ተፎካካሪ ሆነው ለመቅረብ በዝውውር የነቃ ተሳትፎ በማድረግ አስፈላጊ ባሏቸው ቦታዎች ላይ ዝውውሮችን ፈፅሟል::

ከነሃሴ 11 ጀምሮ መቀመጫቸውን በሀዋሳ ከተማ በታደሰ ኢንጆሪ ሆቴል በማድረግ ዝግጅታቸውን በቀን ሁለት ጊዜ ጠንካራ ልምምድ በማድረግ ላይ ይገኛሉ::

አፄዎቹ ዝግጅታቸውን በተሟላ መልኩ እያደረጉ ሲሆን በጉዳት ልምምድ አቁመው የነበሩት ጌታነህ ከበደ እና ሱራፍኤል ዳኛቸው ካጋጠማቸው ጉዳት አገግመው ከቡድኑ ጋር ልምምድ መጀመራቸው ታውቋል::

በተየያዘም ዜና በዛሬው እለት ለ አፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ለብሄራዊ ቡድን አገልግሎት 4 የክለባችን ተጫዋቾች ጥሪ ተደርጎላቸዋል::
ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዎቾችም : አለምብርሃን ይግዛው ሱራፍኤል ዳኛቸው ጋቶች ፓኖም እና ምኞት ደበበ ናቸው::

ዳሽን ቢራ የፋሲል ከነማ የሁልጊዜም አጋር!!

. 🇦🇹#ፋሲል_ከነማ_ከክለብም_በላይ_ነው🇦🇹
#የዝውውር ዜና🇦🇹🇦🇹🇦🇹🇦🇹

አፄዎቹ በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ እየተመሩ 2016 ዓ.ም ተጠናክረው ለመቅረብ ዝውውሮችን በማድረግ የቆዩ ሲሆን ያለፉትን ሁለት አመታት በቅዱስ ጊዮርጊስ ጥሩ ጊዜን ያሳለፈውን የመሀል ተከላካይ ምኞት ደበበን ለ2 አመት ውል የግለቸው አድርገዋል።

አዲሱ የክለባችን የተከላካይ መስመር ተጫዋች ምኞት ደበበ እንኳን ወደ ታላቁ ፋሲል ከነማ ቤት በደና መጣህ እያልን በቆይታህም መልካም የልምምድ እና የውድድር አመት እንዲሆንልክ እንመኛለን።


@FASILSC
2024/09/30 09:28:58
Back to Top
HTML Embed Code: