Telegram Web Link
የኔቶ አባል ሀገራት ህዝባቸውን ለጦርነት በማዘጋጀት ላይ ናቸው

ዜጎች ለጥቂት ጊዜያት ሊያገለግሉ የሚችሉ መሰረታዊ ግብአቶችን ገዝተው እንዲያከማቹ ታዘዋል።
👇👇👇
📌 እኛ ከእንግዲህ ድርሻችንን ተወጥተናል።

እግዚአብሔር ያዘዘንን ገልጸናል። አድርሰናል።

ግዳጃችንን ተወጥተናል።

እንግዲህ ወገኖቼ እዳ የለብንም።

የፍቅር እዳ የለብንም።

የታዘዝንበትም እዳ የለብንም።

ሁሉንም ነገር በጊዜውና በሰአቱ በዚህ ክፉ ሰአት ውስጥ ሁሉ
ሊደርስ ወደ ሚገባው ሁሉ አድርሰናል ማለት ነው።

ከእንግዲህ በየበዓታችን ሆነን መጪውን የእግዚአብሔርን እርምጃ ማየት ብቻነው።

ኖህ በመርከቡ አይደል! የተካተተው?
አዎ እኛም በእምነት መርከባችን ተካተን  ውጤቱን መከታተል ብቻ ነው።

መቼም ለምታስተውሉ አለም ወዴት እየሄደች እንደሆነ ግልጽ እያየን ስለሆነ
ምንም ድብቅም ስለሌለ።
ከእንግዲህ ለአዳም ዘር አስተዋሽ አያስፈልገውም ።ፍርዱ ሁሉ ከደጁ ነው።
የቁጣው እሳት ሲያጠልመው ሲለበልበው ሲያቀልጠው ያኔ የእግዚአብሔር ፍርድ ነውና ይገበዋል።በ ፍርዱም ይካተታል።
እኛ ደግሞ እግዚአብሔርንን እያመሰገንን በየበዓታችን መቀመጥ ነው።
እኛ የኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ቤተሰቦች
ልንበረታ ይገባል
ከነበረን የእምነት ጥንካሬ ልንላላ አይገባም።እውነትን ከተረዱ በኋላ ወደ ኃላላ በሚያፈገፍግ ነፍስ እኔ ደስ አልሰኝም አዝናለሁ ነው የሚለው ቸሩ መድኃኔዓለም ስለዚህ ይህንን ቃል እያስታወሳችሁ በጀመራችሁበት መንፈሳዊ ጥንካሬ ተመላለሱ።ምንም አይነት ፈተና ቢገጥማችሁ ምንም አይነት ችግር ቢታይ በእምነት እለፉት እንጂ ከእምነታችሁ አትጉደሉ።
⚡️ለአለም መንግሥታት እና ሕዝብ ይደርሱ ዘንድ በቀን 7/5/2016 ዓ,ም ከኢትዮጵያ የዓለም ብርሃናዊ መንሥት ከተጻፉት ደብዳቤች መካከል
በንባብ  ከተላለፈው ክፍል 1 መግቢያ እና ማብራሪያ ላይ የተወሰደ።
🇮🇱🇵🇸 እስራኤል በዌስት ባንኳ ጀኒን ከተማ መሰረተ ልማቶችን አወደመች

ከሰኞ ምሽት ጀምሮ የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት ጀኒን ከተማ እና ካምፖችዋ ላይ ጥቃት ፈጽሟል።

በፍልስጤማውያን ታጣቂዎች እና በእስራኤል ኃይሎች መካከል ያለው ግጭት የቀጠለ ሲሆን እስራኤሎች በዶዘሮ ተሽከርካሪዎች የከተማዋን ዋና ዋና መንገዶችና መሠረተ ልማቶች አፈራርሰዋል።
🟢🟡🔴
ኅዳር 12 | በእግዚአብሔር ጌትነት ዙፋን ፊት ሁልጊዜ በመቆም ለፍጥረቱ ሁሉ የሚማልድ፣ በሰማያትም ለሚኖሩ ኃይሎች ሁሉ አለቃቸው ለሆነ #ቅዱስ_ሚካኤል የተሾመበት የበዓሉ መታሰቢያ ነው።


ዳግመኛ በዚህች ዕለት #ቅዱስ_ሚካኤል #ኢያሱ_ነቢይን የተራዳበት መታሰቢያ ነው።

ይህም በንጉሥ ጭፍራ አምሳል በታላቅ ክብር ሁኖ የነዌ ልጅ ኢያሱ ያየው ነው ከእኛ ሰዎች ወገን ነህን ወይስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህ አለው። እኔስ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ነኝ አሁንም ወዳንተ መጥቻለሁ አለው።

ኢያሱም ወደ ምድር በግንባሩ ተደፍቶ ሰገደለትና በእኔ በባሪያህ ዘንድ ምን አቁሞሃል አለው። የእግዚአብሔር የሠራዊቱም አለቃ ሚካኤል ኢያሱን የቆምክባት ምድር የከበረች ቦታ ናትና ጫማህን ከእግርህ አውልቅ አለው ኢያሱም እንዳለው አደረገ።

እግዚአብሔርም ኢያሱን እንዲህ አለው፦ በውስጧ ያለውን ንጉሧን ከኃያላኑና ከአርበኞቹ ጋር በእጃችሁ ኢያሪኮን እነሆ አስገባታለሁ።

ይህም የከበረ መልአክ ከቅዱሳን ሰማዕታት ጋር በመሆን ገድላቸውን እስከሚፈጽሙ የሚያጸናቸውና የሚያስታግሣቸው ነው ።

ስለ ልዕልናውና አማላጅነቱ በየወሩ በ፲፪ ቀን ለመታሰቢያው በዓል ተሠራለት።

እርሱ ስለ እኛ የምድሩን ፍሬ ይባርክልን ዘንድ ዝናሙንም በጊዜው እንዲአወርድልን የወንዙንም ውኃ እንዲመላልን ነፋሱንም የምሕረት ነፋስ እንዲአደርግልን ሁሉንም የተስተካከለ እንዲአደርግልን ወደ እግዚአብሔር በጸሎት ይማልድልናል።


#ቅዱሳን_ዱራታኦስ_እና_ቴዎብስታ የቅዱስ ሚካኤል ወዳጆች ናቸውና በዚህች ዕለት ይታሰባሉ።


በዚችም ቀን የኢትዮጵያ ንጉሥ #የጻድቁ_በእደ_ማርያም የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው። እኚህም የመጀመርያውን #መልክአ_ማርያም የደረሱ ናቸው።
 ◦🍀

+ የመጥምቁ
#ቅዱስ_ዮሐንስ ራስ በደብረ ማህው የታየችበት ዕለት መሆኑን ስንክሳሩ ይጠቅሳል፡፡
አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ
👆👆👆 ዋኖቻችንን እንወቅ ❗️
#ክፍል_4

መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ማን ነው?

በድምፅ ንባብ (በትረካ) የተዘጋጀው ነገ (ኅዳር 12/2017) በአመታዊ መታሰቢያው ዕለት ይለቀቃል !

#እንኳን_አደረሳችሁ !
💚💛❤️ ኅዳር 12. በዓለ ሲመቱ ለክቡር ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ሚካኤል

እንኳን አደረሳችሁ !
Audio
AudioLab
🟢🟡🔴
ዋኖቻችንን እንወቅ - ክፍል አራት (4)

በድምፅ ንባብ (በትረካ)

(📌 ክፍል 1ን ለማዳመጥ 👈)
(📌 ክፍል 2ን ለማዳመጥ 👈)
(📌 ክፍል 3ን ለማዳመጥ 👈)

መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ማነው?

🌿 ሕይወቱና ተጋድሎው
🌻 ቃልኪዳኑና
🌹 ሰማዕትነቱ
...

📌 ቁጥር 1) ከዚህ ሥር አጭር ዜና ሕይወቱንና ከመድኃኔዓለም የተቀበለውን ልዩ ቃልኪዳን በፅሑፍ ያንብቡ👇

🫴 https://www.tg-me.com/Ewnet1Nat/14510

PDF ገድለ ዮሐንስ መጥምቅ (በ1988 ዓ.ም የታተመ)👇

https://www.tg-me.com/kidusan_page/50
🟢🟡🔴
ኅዳር 13 | በዚህች ቀን #የቅዱሳን_አእላፍ_መላእክትን የበዓላቸውን መታሰቢያ እናደርግ ዘንድ የቤተ ክርስቲያን መምህራን አዘዙን።

እሊህም ሥጋ የሌላቸው ረቂቃን የሆኑ ለዓለሙ ሁሉ የሚማልዱ ናቸው።

ይህ ዕለት በሊቃውንት አንደበት "አእላፍ" እየተባለ ይጠራል። በሃይማኖት  በተልእኮትና በምስጋና የሚኖሩ 99ኙ ነገደ መላእክት በአንድ ላይ የሚከበሩበት ቀን ነው።

እግዚአብሔር ቅዱሳን መላእክትን ሲፈጥራቸው በነገድ መቶ (100)፣ በክፍለ ነገድ አሥር (10) አድርጓቸዋል። አቀማመጣቸውንም በ3 ሰማያትና በ10 ከተሞች (ዓለማት) አድርጓል።

መላእክት ያሉባቸው ከተሞች ከታች ወደ ላይ "ኤረር፣ ራማና ኢዮር" ይባላሉ። አሥሩ ክፍለ ነገድ ደግሞ ከነዋና ሊቃነ መላእክታቸው ይህንን ይመስላሉ፦

1. አጋእዝት (የቀድሞ አለቃቸው ሳጥናኤል፥ አሁን የተረፉት #በቅዱስ_ሚካኤል ሥር ናቸው)

2. ኪሩቤል (አለቃቸው ቅ/ኪሩብ)

3. ሱራፌል (አለቃቸው ቅ/ሱራፊ)

4. ኃይላት (አለቃቸው ቅ/ሚካኤል)

5. አርባብ (አለቃቸው ቅ/ገብርኤል)

6.መናብርት (አለቃቸው ቅ/ሩፋኤል)

7. ሥልጣናት (አለቃቸው ቅ/ሱርያል)

8.መኳንንት (አለቃቸው ቅ/ሰዳካኤል)

9. ሊቃናት (አለቃቸው ቅ/ሰላታኤል)

10. መላእክት (አለቃቸው ቅ/አናንኤል) ናቸው።

ከእነዚህም አጋእዝት፣ ኪሩቤል፣ ሱራፌልና ኃይላት መኖሪያቸው በኢዮር (በ3ኛው ሰማይ) ነው።

አርባብ፣ መናብርትና ሥልጣናት ቤታቸው ራማ (2ኛው ሰማይ) ነው።

መኳንንት፣ ሊቃናትና መላእክት ደግሞ የሚኖሩት በኤረር (በ1ኛው) ሰማይ ነው።

ዕረፍት ብሎ ነገርን አያውቁም። ዕረፍታቸው ምስጋና፣ ምስጋናቸው ዕረፍት ሆኖላቸዋልና። በተጨማሪም መልአክ ማለት ተላላኪ (አገልጋይ) ነውና ከፈጣሪ ወደ ሰው ልጆች ለምሕረትም ለመዓትም ይላካሉ።
🍀

www.tg-me.com/Ewnet1Nat
🟢.ስደተኛ ይብዛብሽ ።

🟡.ልጆችሽ እረግተው አይቀመጡ ።

🔴.እንደተንከራተቱ ይኑሩ።

🟢.ሕይወታቸው በስደት ይለቅ።

🟡.ያንችን ትንሳኤ እንዳያዮ ለዘላለም ረገምኳቸው።

🔴.በረከትሽ ፈጽሞ አይድረሳቸው።

🟢.ሚስጥርሽም ይሰወራቸው ።

🟡.ያንች የሆነውን ሁሉ ጠላቶችሽ ይጠቀሙበት።

🔴.ልጆችሽ ግን ይሰወራቸው።

🟢.የባዕዳን ሃይማኖት እና ትምህርት ይውረራቸው።

🟡.የቅዱሳንሽ ቃል ኪዳን አይድረሳቸው ።

🔴.በፍቅረ ንዋይ አይናቸው ዝንተ ዓለም እንደታወረ ይኑር

በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

🟢.ኢትዮጵያ የሥላሴ የክብራቸው መገለጫና መመስገኛ ምድር ።

🟢.ኢትዮጵያ ርስተ ድንግል ማርያም

🟡.ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን

🔴.ኢትዮጵያ የዓለሙ ገዢ
     
➻ሠላም እንዴትሰነበታችሁ እኛ ደና ነንን ልዑል እግዚአብሔር የተመሠገነ ይሁን።ዛሬ አንድ የእግዚአብሔር አገልጋይ ቅዱስ አባት ገድላቸው ላይ የተገለጸውን እስኪ አንብበነው እንማርበት ከበረከታቸውም እናገኝ ዘንድ እንማጸናቸው።

➻እንደ ነብዩ ኤርምያስ በእናታቸው ማህፀን የተመረጡ ናቸው ብሉይንና ሀዲስ ኪዳንን ያጠናቀቁት በ12 ዓመታቸው ገዳም ለመግባት ወስነው ወላጅ እናታቸውን አሰናብችኝ ብለው ጠይቀዋል ቅድስት እናታቸውም መርቀው ሸኟቸውና ትግራይ ውስጥ ወደ ሚገኘው ደብረ ፀራቢ ወደ ሚባል ገዳም ገቡ።

➻ የገዳሙ አስተዳዳሪ አቡነ በኪሞስ የምንኩስና ቀንበሩና ሸክሙ እጅግ የከበደ መሆኑን በመንገር ወደ እናታቸው እንዲመለሱ ቢነግሯቸውም አቡነ ፊልጶስ ግን ለምንኩስና የታጩ ሙሽራ መሆናቸውን ነግረዋቸው ከብዙ ፈተና በኋላ ጽናታቸውን አይተው አመንኩሰዋቸዋል።

 ➻በገዳሙ እንጨት እየለቀሙ ውኃ እየቀዱ የክርስቶስን ሕመሙንና ሞቱን እያሰቡ በፀሎት ከኖሩ በኋላ ጌታችን ተገልጦ ወደ ሽሬ እንዲሄዱ ከነገራቸው በኋላ በሽሬ አዲ አቦ በተባለ ስፍራ ሂደው ብዙ አስደናቂ ታምራትን ካደረጉ በኋላ ወደ ደብረ ቢዘን እንዲሄዱ ተነግሯቸው የእሳቸውን በረከት ለመቀበል ከመጡት 16 መነኮሳት ጋር ወደ ደብረ ቢዘን ሄዱ።

    ➻ጻዲቁ የሐይቅ እስጢፋኖስን ባህር በታምራታቸው ያቃጠሉ አባት ናቸው።
በንጉሡ በአፄ ዳዊት ዘመን ሰንበት አንዲት ናት እያሉ በሰንበት ስራ እንደሚሰሩ ሰምተው ሰንበት አንዲት ናት የሚሉትን ሁሉ ተቃወሟቸው ከግብፅ የመጡት ጳጳሳትም ቀደም ብለው ከአባ ጊወርጊስ ዘጋስጫ አሁን ደግሞ ከአቡነ ፊልጶስ ጋር ንጉሡ አፄ ዳዊት አከራከሯቸው ጳጳሱም ተረቱ ።

➻ክፉዎችም በአቡነ ፊልጶስ ላይ በክፋት ተነሱባቸው በአቁማዳ ጠቅልለው ሀይቅ ውስጥ ጣሏቸው።በዚህ ጊዜ እሳቸው የተጣሉበት ባህር በእሳት ተቃጥሎ እንዲታይ አደረጉ።በጽኑ ሥልጣን ህዝቡንም መንግሥቱንም ረገሟቸው።

🟢.ስደተኛ ይብዛብሽ ።

🟡.ልጆችሽ እረግተው አይቀመጡ ።

🔴.እንደተንከራተቱ ይኑሩ።

🟢.ሕይወታቸው በስደት ይለቅ።

🟡.ያንችን ትንሳኤ እንዳያዮ ለዘላለም ረገምኳቸው።

🔴.በረከትሽ ፈጽሞ አይድረሳቸው።

🟢.ሚስጥርሽም ይሰወራቸው ።

🟡.ያንች የሆነውን ሁሉ ጠላቶችሽ ይጠቀሙበት።

🔴.ልጆችሽ ግን ይሰወራቸው።

🟢.የባዕዳን ሃይማኖት እና ትምህርት ይውረራቸው።

🟡.የቅዱሳንሽ ቃል ኪዳን አይድረሳቸው ።

🔴.በፍቅረ ንዋይ አይናቸው ዝንተ ዓለም እንደታወረ ይኑር

➻ይህ ውግዘት ለቀድሞዋ ኢትዮጵያ ለአሁኗ ደግሞ ኢትዮጵያና ኤርትራ (ባህረ ነጋሽ) ልጆች የተላለፈ እርግማን ነው።

 ➻ በዚህ ጊዜ ንጉሡም ህዝቡም ሁሉም ተረበሸ።
እንደ ምጽአት ቀን ያስፈራ ነበር። እርግማናቸው ከመባርቅት ጎልቶ በሚያስፈራ ነጎድጎድ ይሰማ ነበር።

 ➻.ዛሬም ድረስ በሐይቅ እስጢፋኖስ ባህር ዳርቻ ላይ የተቃጠሉ ድንጋዮች ይገኛሉ።

➻.በወቅቱም የንጉሡ ሚስት በዋናተኞች አስፈልጋ ከሐይቁ ውስጥ አሰወጥታቸው እግራቸውንም አጥባቸው ስትጨርስ የእግራቸውን እጣቢ ጠጣችው።ወዲያውም ከማህፀንሽ ፍሬ ታላቅ ጻድቅ ይወጣል ብለው ትንቢት ተናግረዋል።በትንቢቱም መሰረት ንጉሡ አፄ ዘርዓያዕቆብ ተወለደ።

➻.በወቅቱ በተፈጠረ አለመግባባትና ክፉዎችም በባህር ውስጥ ስለጣሏቸው እርግማንን በህዝቡ ላይ አምጥተዋል።
ንጉሡ አፄ ዳዊትም አቡነ ፊልጶስን ከልብ ይቅርታ ጠይቀው ወዲያውም ታርቀዋል።
በዘመናቸውም ርሃብ ስለነበረ ፃዲቁን ከገዳማቸው አስጠርተው ምን ባደርግ ይሻለኛል ብለው አማክረዋቸዋል።
ጻዲቁም የጌታችንን መስቀል ያስመጡ ብለው መከሯቸው ንጉሥ አፄ ዳዊትም በአቡነ ፊልጶስ ምክር መሠረት ከእየሩሳሌም መስከረም 10 ቀን አስመጥተውታል።

➻.አቡነ ፊልጶስ በደብረ ቢዘን ገዳም በታላቅ ተጋድሎ ኑረው ከጌታችን ዘንድ ታላቅ ቃልኪዳን ተቀብለዋል።
ላንተ የተሰጠህ ቃል ኪዳን ለማንም አልተሰጠውም
➻.ክብርህ ገናና ነው።

➻.በቃል ኪዳንህ ለተማፀነ የማልፈጽምለት የለም።
➻.ገዳምህን ዘወትር በበረከት ደመና ከብቤ አኖረዋለው ።

➻.ምሕረትን ፈልጎ ደጅህን ለረገጠ አንተን ባከበርኩበት ልክ አከብረዋለሁ።
➻.አስተዋይ ልቦናን እሰጠዋለው።

➻.የኢትዮጵያን ምስጢር እገልጥለታለው ብሎ ጌታ ቃል ገብቶላቸዋል ።

➻.ነሐሴ 5 ቀን በታላቅ ክብር አርፈዋል !!!
           
➻.እንግዲህ ዛሬም እየሆነ ያለውን ማየት ነው እየተፈጸመ ነው እንሰደዳለን :ሀገር እንጠላለን ከውስጥ ይልቅ ውጭነት ይማርከናል ።

➻.እንደ ሀገር እንደ ህዝብ ታመናል ብሎ የሚመረምር ትውልድ እንኳ ጠፍቷል።

 ➻. የእውነተኛ አባቶቻችን ውግዘት ምን ያህል ከባድና ለቅጣት እንደሚዳርግ ከዚህ መረዳት ይቻላል።ዛሬም በዚህ ዘመን የተላለፈውን የአባታችን ሊቀ ሊቃውንት አለቃ አያሌው ውግዘትን የማናከብር ከሆነ ከዚህ የከፋ መከራ ውስጥ እንገባለን ማለት ነው።ያው እንደምናየው ህዝቡም እያከበረው አይደለም ያው የሚሆነውን ማየት ነው እንግዲህ።
➻. እግዚአብሔር ይመስገንና እኛ ግን እውነትን ሰምተናል በኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን እውነት እስከመጨረሻው ያጽናን!
➻.የጻዲቁ አቡነ ፊልጶስ በረከታቸው ይደርብን።

➻.በአንድ ወንድም ምክንያት ገድላቸውን ሠማሁና ለሁሉም አስተማሪ ስለሆነ ነው ያጋራሁአችሁ


.ሠላመ እግዚአብሔር ቅን፣ የዋህ፣ ትሁት ከሆነ ኢትዮጵያን ከልቡ ከሚወዳት ጋር ይሁን።
13/03/2017 ዓ.ም
📌  ዓለምም ታመሰ ተቆላ ተፈጨ ኢትዮጵያም እንዲሁ በምታዩት መልኩ ተጨነቀች ተጠበበች ፍጅቱም ጦርነቱም እልቂቱም ዘረኝነቱም ርሃቡም አጥለቀለቃት።

📌 ደጋግመን እንደተናገርነው ኢትዮጵያ ቀድማ ነጻ ትወጣለች ከላይዋ ላይ የበቀለው የጨለማው ኃይል ሁሉ  በአብዛኛው በእግዚአብሔር ኀይል ቀሪው በታማኝ ባሮቹ ሰይፍ ተጠርጎ ይወገዳል።

🌍 ዓለም ደግሞ እግዚአብሔር ለሚተክለው የኢትዮጵያ የዓለም ብርሃናዊ መንግሥት እየተረገጠች እየተፈጨች እየተቆላች በእሳት እየተበላች የሚትርፉት ጥቂት ሳይወዱ በግድ እጃቸውን ለእግዚአብሔር በሚሰጡ ሰዎች በስተቀር የተቀረው እየተበላ ለዛም እጃቸውን የሰጡትን ሰዎች ተቀብሎ በመላው ዓለም የኢትዮጵያ የዓለም ብርሃናዊ መንግሥቱን አገዛዝና  እና አስተዳደሩን አስፍኖ ይቆማል።

❗️ይህ ሲታይ ሲፈጸም ነው ከዚያን በኃላ የእግዚአብሔር ሰይፍ እና ቁጣው መቀዝቀዝ መብረድ ቀስ በቀስ መቀነስ የሚጀምረው እግዚአብሔር ይህንን እውነት ፈቃዱን ሳያረጋግጥ "ይቀራል፣ ሰላም ይመጣል፤ በዚህ እንዲህ አድርገን ሰላም እናመጣለን፤ በዚህ እንዲህ ተደርጎ እረፍት  እናደርጋለን፤ እድገት እናደርጋለን በዚህ..." ይህን ተረታችሁን እሱ እዛው ቀረ በቃ !!

🔥 አበቃ የሱ እድሜ አብቅቷል ! ተዘግቷል የእግዚአብሔር ሕዝብ ዘመን ደግሞ የብርሃን ዘመን ይመጣል ።

ያ ደግሞ ፈቅዳችሁ የምታደርጉት አይደለም እግዚአብሔር የሚጠረገውን ጠራርጎ የሚጸዳውን አጽድቶ ለሕዝቦቹ ምድሪቱን ያስረክባል።

☀️ በረከት ፣ሰላም ፣ ፍቅር ፣ ቸርነት ፣ በጎነት ከሱ ትፈሳለች። ለዓለም ብርሃን ይሆናል ከኢትዮጵያ የሚፈሰው ብርሃን
እግዚአብሔር በምድሪቱ  ይከብራል ድንግል ትከብራለች ።

የኢትዮጵያ ተዋሕዶ ኦርቶዶክስ እምነት  ደግሞ ለዓለም ሁሉ ብርሃን ሆና ታበራለች። ለሕይወትም ለነፍስም ለሥጋም የሚሆነውን ቃል ሁልጊዜ ያለማቋረጥ ትመግባለች ።

🇨🇬 ኢትዮጵያ በተረጋገጠ በተደላደለ መልኩ ዓለምን እየገዛች ታስተዳድራለች ።

ይሄ ቃል አይናወጽም ይህ እስከሚፈጸም የእግዚአብሔር  ቃል ይህ ቃል እስከሚከናወን ድረስ የጥፋቱ እርምጃ ይቀጥላል።

♻️ መቅሰፍቱ ይቀጥላል መጠኑ ይጨምራል በ7፣ በ49፣ በ400 በምን... እያለ ይቀጥላል ሙልጭ ብለህ እስክትጠናቀቅ ድረስ ይሄንን ደጋግመን ልናረጋግጥላችሁ እንወዳለን ከወዲሁ❗️

🔜 ልብ ብለህ አድምጥ ከዚህ ውጪ የሚመጣ አለ ብለህ የምትደክም ወይም የእግዚአብሔርን ፈቃድ የምትጻረር ከወዲሁ እርግጠኛ ሁን ! መጥፋትህን አረጋግጥልሃለው። እኔ የሥላሴ ባርያ የድንግል ባርያ  አሁንም ደግሜ እነግርሃለው መጥፋትህን አረጋግጥልሃለው።

🔈 ትከናወናለህ ትጠረጋለህ ትሰናበታለህ።
ዓለማችንም ኢትዮጵያም በኢትዮጵያዊነት በተዋሕዶ ኦርቶዶክስ እምነት በእውነተኛይቱ  እምነት ፤ በአረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ በቃልኪዳኑ ምልክት እንዲሁም በቃል ኪዳኑ ቃሎች፦

🟢 ኢትዮጵያ የሥላሴ የክብራቸው መገለጫና መመስገኛ ምድር
🟡 ኢትዮጵያ ርስተ ድንግል ማርያም
🔴 ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን
🔴 ኢትዮጵያ የዓለሙ ገዢ

እነዚህ ማንኛውንም የአዳም ዘር በኢትዮጵያም በመላው ዓለምም ኖርክ እምትበጠርበት የእሳት ወንፊት ይህ ቃል ነው እምትለካበት ሚዛን ይሄው፦  ቃሉነው ❗️

💯 የከበረው የእግዚአብሔር ቃል በቃ አበቃ ሌላ መንገድም ማምለጫም መፍትሔም የለም ።

📝 ከ1--10 የተጠቀሱት መልእክታቶች ትምህርቶች  መግለጫዎች በሙሉ አንዳቸውም ሳይቀሩ ነጥቧም ሳትጎል
የእግዚአብሔር ውሳኔና ትዕዛዝ ነውና ይፈጸማል  ይከናወናሉ፦

🔐 ጠፊውም እየጠፋ ተራፊውም እየተጸጸተ የጠላችኋቸውም የናቃችኋቸው ያሳደዳችኋቸው ብርቱ መከራን ያፈሰሳችሁባቸውም የኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ቤተሰቦች እና የዋህ ትሁት ቅን  ሕዝቦች በኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ቀዳማይ እረኞች እየተመሩ ደግሜ ነው የምነግርህ እየተመሩ! በእግዚአብሔር ምህረትና ቸርነት ጸጋ  ተከበው በድንግል እቅፍ ሆነው፡ በሊቃነ መላእክቱ ታጅበው ምድርን እያንቀጠቀጡ ይመጡልሃል❗️ አሁንም ነው የምነግርህ ይመጡልሃል❗️ እኔ የሥላሴ ባርያ እየነገርኩህ ነው። የድንግል ባርያ እየነገርኩህ ነው።

የዛሬ 18 ዓመት ጀምሬ አይደል እየገርኩህ ያለውት አሁንም እየነገርኩህ ነው ይህንን እውነት ዛሬም ደጋግመን የምናዳኝብህና የምናረጋግጥልህ እኛ እኛ የኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን  ቀዳማይ እረኞች ነን።

⚡️ ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መግለጫና የጥያቄዎቻቹ መልስ ክፍል- 5 --1:00 ስዓት ደቂቃ 14 -38 ሰከንድ ጀምሮ ካለው መግለጫ የተወሰደ።
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🇪🇸 🌥 በቅርቡ በጎርፍ በተመታችው የስፔኗ ቫሌንሺያ ከተማ ያልተለመደ የሰማይ ገጽታ ታይቷል
👉 በምንዝርና፣ በውሸት፣ በጭካኔ፣ በሌብነት፣ በነፍሰ ገዳይነት፣ የተበከልክ ሥራህም ያደረግህ ወንድም ሆንክ ሴት በፈጣሪ እሳት ትበጠራለህ። ማንም የሚያመልጥ የለም። መልካሙን ዘመን የሚያዩት በፈጣሪአቸው ሕግ የተመሩ፣ የኖሩ፣ ሲወቀሱ ፈጥነው ንስሐ የገቡ ብቻ ናቸው። ከጥፋት ወደ ጥፋት ለምትነጉደው፣ ተግሳጽና ምክር ለናቅከው፣ ለጠፋኸው ትውልድ፣ የጨለማ ልጅ ከጨለመ ሥራው ጋር ጨለማው ሲጠረግ አብሮ ይወገዳል። የብርሃን ልጅ ደግሞ በብርሃን ዓለም ተባርኮ ይኖራል።

👉
ከኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልዕክት ሁለት ላይ የተወሰደ!
2024/12/27 11:42:20
Back to Top
HTML Embed Code: