Telegram Web Link
💧🇸🇦 በሳውዲ አረቢያ ታይፍ ከተማ የጣለው ከባድ ዝናብ ያስከተለው ጎርፍ በጎዳናዎች ላይ የነበሩ መኪናዎችን ጠራርጎ ወስዷቸዋል።
በተለያዩ ግጭቶች እና ጦርነቶች ውስጥ ለዓመታት በተከታታይ በዘለቀችው ኢትዮጵያ የኑሮ ውድነቱ ብዙዎችን እያማረረ ነው ። እንደ ተመድ የሐምሌ ወር መረጃ፦ ከ133 ሚሊዮን በላይ ነዋሪ ባላት ኢትዮጵያ አብዛኛው ነዋሪ የዕለት ኑሮውን ለመግፋት እንኳ እጅግ መቸገሩን ሲገልጥ ይደመጣል ።
🟢🟡🔴
ጥቅምት 19 | ከከበሩ አባቶቻችን መካከል

🍀 ንግሥናን ከክህነት ጋር አስተባብሮ በመያዝ 40 ዓመት ሙሉ ሰማያዊ ኅብስትና ጽዋ ከሰማይ እየወረደለት የቀደሰው ጻድቁ ንጉሥ #ቅዱስ_ይምርሐነ_ክርስቶስ ዕረፍቱ ነው፡፡ ሕዝቡንም የሚባርክበት መስቀል ከሰማይ የወረደለት ሲሆን ቤተ መቅደሱን በባሕር ላይ እንዲሠራ ራሱ ጌታችን በቃሉ ከነአሠራሩ ጭምር ያስረዳው ነው፡፡

🍀 ታላቁ አባት #አቡነ_ሐራ_ድንግል ልደታቸው ነው፡፡    

ጻድቁ ከአባታቸው ከሬማው ካህን ከቅዱስ ዮሐንስ ከእናታቸው ብፅዕት ወለተ ጊዮርጊስ ጥቅምት 19 ቀን 1534 ዓ.ም ተወለዱ፡፡

ነብርና ፍየልን ያስማሙ እኚህ አባት ቅድስናቸው ማንንም ሳይመራው በራሱ በየገበሬው ሄዶ እህል የሚሰበሰብላቸው አህያ ሲሞት በሞተበት ቦታ ጸበል በመፍለቁ ታይቷል።

🍀 የገዳማቸው ዛፎች ሲያረጁ ወደታች የማይወድቅባቸው ኢትዮጵያዊው ጻድቅ #አቡነ_ሰይፈ_ሚካኤል ዕረፍታቸው ነው።

አቡነ ሰይፈ ሚካኤል በተሰጣቸው ጸጋ ርኲሳን መናፍስትን ከሕሙማን ያወጡ ስለነበር እነዚያ አጋንንትም "እዚህ እንድትኖር አንፈቅድልህም" እያሉ በገሃድ ለሞት እስከሚደርሱ ድረስ ዐይናቸውን አፈሰሱባቸው። ሆኖም ግን መልአከ እግዚአብሔር ዳስሶ ዐይናቸውን መልሶ አበርቶላቸዋል።

🍀 ስለ ጳውሎስ ሳምሳጢ #በአንጾኪያ አገር የቤተ ክርስቲያን ጉባኤ ተደረገ

ይህም ሰው በገዳም የሚኖር መናኝ ነበር። የሰይጣንን ክፉ ምክር ሰምቶ ክብር ይግባውና "መድኃኔዓለም መንፈስቅዱስ ያደረበት ተራ ሰው ነው" በማለቱ በጉባኤው ተወገዘ። ኋላም ንስጥሮስ ክህደቱን ወረሳት።

🍀 ዳግመኛም እንደበግ ለታረዱ ለመጥራ ጻድቃን ሰማዕታት መታሰቢያቸው ነው።

እነዚህም የመጥራ ጻድቃን እስከዛሬ ድረስ ቆዳቸው ከሥጋቸው አልተለያየም መግነዛቸውም አላረጀም።


www.tg-me.com/Ewnet1Nat
ኢየሱስ ክርስቶስ ካህኑ ለዓለም ንጉሠ ፅዮን ወንጉሠ ነገሥታት ዘኢትዮጵያ
ድንግል ማርያም እሙ ወእምነ ንግሥተ ፅዮን ወንግሥተ ነገሥታት ዘኢትዮጵያ

🥢 ዓለሙን ስለ ክፋታቸው ክፉዎቹንም ስለ በደላቸው እቀጣለሁ የትዕቢተኛዎችንም ኵራት አዋርዳለሁ።
ትንቢተ ኢሳያስ 13፡11

በ 19/2/2017 ድንቃ ድንቅ አስተማሪ ምስክርነት ይለቀቃል 👇👇👇
Audio
የወንድማችን ወልደ ተክለሃይማኖት እጅግ ድንቅ ምስክርነት
ከቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ = መተሐራ
19/2/2017

👉 ዛሬ በአገራችን ያለው ሁኔታ እጅግ አስፈሪ እንደሆነ እንኳን በልዑል የሚታመነው ቀርቶ የጠፋውም 
ትውልድ ግራ ገብቶት እንደ ውኃ ላይ ኩበት ሲዋልል እየታየ ነው። አገራችን ልትፈርስ ነው በዘር ልትገነጣጠል 
ነው እርስ በእርስ ልንጫረስ ነው እየተባለ ሁሉም በድንጋጤ የተዋጠበት ዘመን ነው። ሁሉም እንደሚያውቀው 
አገራችን ኢትዮጵያን ወደዚህ ደረጃ ያደረሳት ዛሬ ጥግ ይዤአለሁ የሚለው ሁሉም የሚጠራው ወያኔ በሚለው 
ስሙ እኔም የማውቀው ዘረኛ ቡድን ነው። 27 ዓመት ሙሉ ሲፈጭህ ሲቆላህ የቆየው ክፉ ወፍጮ ከአጠገብህ 
ሳይርቅ በሩቅ መቆጣጠሪያ እየተቆጣጠረህ ግራ ተጋብተህ እንደ አሻሮ ትቆላለህ፤ መፍትሄ የለውም። እሱን 
ተክቶ የመጣው ከራሱ ማኅፀን የወጣው መንግሥት ደግሞ ችግርህን ከድጡ ወደማጡ አድርጎብሃል።

👉 ከኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልዕክት ስምንት ገጽ 31 የተወሰደ ተጻፈ ተጻፈ ታህሳስ 21 2011
የእህታችን እህተ ማርያም እጹብ ድንቅ ምስክርነት
ከዱባይ
19/2/2017

👉 እውነትን  ጨብጣችሁ  እግዚአብሔርን  ጠይቃችሁ  መልስም  አግኝታችሁ  የተረጋገጠ  ተስፋን  ጨብጣችሁ ያላችሁ  የእግዚአብሔር  ቤተሰቦች  ባለድል  ናችሁ።  እውር  ዓይናማውን  ቢተቸው  እኔ  ልምራህ  ቢለው  ምንኛ ፌዝ  እንደሚሆን  ትረዳላችሁ።  ስለዚህ  ማንም  ተነስቶ  በሚደረድረው  ከንቱ  ቃል  ልባችሁን  አታስቱ!  በቅርቡ ሁሉንም  እንደቃሉ  ሲፈጸም  ታያላችሁ።  ለመሆኑ  በኢትዮጵያ  የዓለም  ብርሃን  የተገለጹ  የልዑል  የፍርድ ቃሎች  መልእክቶች  ሲፈጸሙ  አላያችሁም?  የቀሩትስ  ለመፈጸማቸው  ምልክታቸውን  እየሰጡ  የሰውን  ልጅ በእግዚአብሔር  የፍርድ  ሚዛን  ተለክተው  ሲካተቱ  እንደምታዩት  አልተረዳችሁምን?  የጥርጥር  ችግር  ካለባችሁ ልዑልን  ጠይቁ  ከሰው  ይልቅ  ከሱ  የሚሰጣችሁ  ማረጋገጫ  ይበልጣልና  መጠየቅ  መብታችሁ  ስለሆነ  ጠይቁ ተረዱ  ተዘጋጁ  በቃ!  ስላበቃ  ሁሉም  የምታዩት  የሚያስቷችሁ  የአውሬው  የዘንዶው  የሐሰተኛው  ነቢይ  ደቀ መዝሙሮች ቅጥረኞች ሆድ አደሮች በሙሉ በቅርብ በክፉ መከራና ስቃይ ሲወገዱ ታዩአቸዋላችሁ።

👉 ከኢትዮጵያ የዓለም ብርሃናዊ መንግሥት የወጣ ዘጠነኛ መልእክት ተጻፈ ታህሳስ 21 ቀን 2013 ዓ.ም
ምስክርነት_ቀለበት_እንደተሰጠን_2024_09_26_16_53_05.3gpp
325.1 KB
የእህታችን እጅግ ድንቅ ምስክርነት
ከቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ
19/2/2017

👉 ከፈጣሪዬም የተማርኩት ትምክህትን አርቆ ትሕትናን መልበስን መልካም ስለሆነ ነው እንጂ ሊነገርም ሊታሰብ የማይችል ስጦታውን ጌታ ለእኔ ለትንሹ ባርያው ሰጥቷአል። ትምክህት ከጨለማ ስለሆነ በመመካት አልናገርም መግለጽ ግድ ካልሆነብኝ በቀር። የሰው ዘር አድምጥ መሪዎችህ ገዥዎችህ በከፍታ ላይ አቁመህ የምታያቸው የምትንቀጠቀጥላቸው ጣዖቶችህ ክቡር እከሌ፣ አዋቂው፣ ባለሙያው፣ ሊቃውንቱ፣ የጦር ባለሙያው፣ ኢኮኖሚስቱ፣ ባለሃብቱ፣ ቢሊኒየሩ፣ ኢንደስትርያሊስቱ፣ የህክምና ጠበብቱ፣ መሃንዲሱ፣ የአየር ንብረት አዋቂው፣ የጦር አለቃው፣ ተመራማሪው፣ የፖለቲካ ሳይንቲስቱ፣ ኧረ ምኑ ተቆጥሮ የሊቁ፣ የአዋቂው፣ የአባይ ጠንቋዩ፣ የጦር ኤክስፐርቱ ወዘተ እኚህ ሁሉ ምን ፈየዱ? ምንስ ለወጡ? ምንስ አመጡልህ? በየአገሩ ሕዝባቸውን በመግዛት፣ በማስጨነቅ፣ ወደ ጥፋት በመንዳት ላይ ያሉ ከመንደር እስከ አገር፣ ክፍለ አሕጉር የተኮለኮሉ ገዥዎች መቼ ጊዜ ለፈጣሪ ትእዛዝ ጆሮ ሲሰጡ ታየ? የእነሱ ጥፋት ምድርን ሸፍኖ ሰማይን አዳርሷል። የዘመኑን ፊደል ቆጠሩ ሁሉን አዋቂ ሆኑ። ሰርቆ፣ ነጥቆ፣ ገሎ፣ አመንዝሮ፣ ዋሽቶ፣ አታሎ በየትኛውም ቀን ተሰማርቶ ገንዘብን ሰብስቦ ሕዝብን አስጨንቆ መኖሩ ሕልማቸውና ደስታቸው ከሆነ ዘመናት አለፈም ተቆጠረም።

👉 ከኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልዕክት ሦስት ገጽ 5 የተወሰደ ተጻፈ መጋቢት 19 2001 ዓ.ም
Audio
የእህታችን ዓመተ ጊዮርጊስ እጅግ ድንቅ ምስክርነት
ከቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ
19/2/2017

👉  ያለወላዲተ አምላክ አማላጅነት ዓለም አይድንም
👉 ያለወላዲተ አምላክ አማላጅነት ሀገር አይድንም
👉 ያለወላዲተ አምላክ አማላጅነት ቤተሰብ አይድንም ።
የወልደ_አማኑኤል_ምስክርነት_ከባህር_ዳር_፩.aac
9 MB
የወንድማችን ወልደ አማኑኤል እጅግ ድንቅ ምስክርነት
ከቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ = ባህርዳር
19/2/2017
ክፍል ፩

👉 ኢትዮጵያ የሥላሴ የክብራቸው መገለጫ እና መመስገኛ ምድር
👉 ኢትዮጵያ ርስተ ድንግል ማርያም
👉 ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን
👉 ኢትዮጵያ የዓለሙ ገዥ
የወልደ_አማኑኤል_ምስክርነት_ከባህር_ዳር_፪.aac
4.6 MB
የወንድማችን ወልደ አማኑኤል እጅግ ድንቅ ምስክርነት
ከቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ = ባህርዳር
19/2/2017
ክፍል ፪

👉 ኢትዮጵያ የሥላሴ የክብራቸው መገለጫ እና መመስገኛ ምድር
👉 ኢትዮጵያ ርስተ ድንግል ማርያም
👉 ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን
👉 ኢትዮጵያ የዓለሙ ገዥ
የወንድማችን ሰይፈ ሥላሴ እጹብ ድንቅ ምስክርነት
ከቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ = አዲስአበባ
19/2/2017

👉 ኢትዮጵያን የጠላ፥ ድንግልን ተዋሕዶን እምነት የጠላ፥ ባንዲራዋን የጠላ ሁሉ ይጠረጋል እንጂ በፍጹም
አይድንም። ማምለጫም መዳኛም መንገድ ፍጹም የለውም። በሰሜን በምዕራብ በምሥራቅ በደቡብ የመሸጋችሁ
አገራችንን እንደ አንጋሬ ቆዳ ወጥራችሁ ያስጨነቃችኋት ሁሉ በከፋ እሳት ትጠረጋላችሁ እንጂ ከእንግዲህ
ዕድሜ የላችሁም፤ የሚጠቅማችሁን ጊዜ በደል በበደል ላይ፣ አመጽ በአመጽ ላይ እየጨመራችሁ መጣችሁ
እንጂ ቅንጣት የመጸጸት ምልክት አልታየባችሁም። በመሆኑም ስታፌዙ ጊዜው አለቀ ተከደነ። የመጣውን
መቀበል ብቻ ነው።

👉 ከኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልዕክት ስምንት ገጽ 32 የተወሰደ ተጻፈ 21/4 /2011
Audio
🇨🇬 ልዩ ማሳሰቢያ ከራዕይ ዮሐንስ 20
20/02/2017 ዓ.ም
🍀🌼🌺
ጥቅምት 21| በኹለት ወገን ድንግል የምትኾን እመቤታችን ማርያም ተአምራትን አድርጋ ደቀ መዝሙር ማትያስን ከእሥራት ቤት አዳነችው።

እመቤታችን ድንግል ማርያም የወልደ እግዚአብሔር እናቱ ናትና ሁሉን ትችላለች። እርሱን ከሃሊ (ሁሉን ቻይ) ካልን እርሷን "ከሃሊት" ልንላት ይገባል። ልክ ልጇ ሁሉን ማድረግ ሲችል በትዕግሥት ዝም እንደሚለው እመ ብርሃንም ስንት ነገር እየተደረገ በእርሷ ላይም አንዳንዶቹ ስንት ነገርን ሲናገሩ እንደማትሰማ ዝም ትላለች።

የከበሩ ቅዱሳን ወንጌልን በዓለም ዞረው ይሰብኩ ዘንድ ዕጣ ሲጣጣሉ ለቅዱስ ማትያስ ዕጣ የደረሰው ሰውን ወደሚበሉ ሰዎች አገር ነበር፡፡ ይህችም ሀገር እስኩቴስ የተባለች ሩሲያ እንደሆነች የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ጸሐፊዎች ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡

ማትያስም እነዚህ ሰውን የሚበሉ ሰዎች አገራቸው እንደደረሰ ዐይኑን አውልቀው አሠሩት፡፡ ምግባቸውም የመጻተኛ ሰው ሥጋ ነው፡፡ በልማዳቸው መሠረት መጻተኛን ሰው ገና እንደያዙት ዐይኖቹን ዐውልቀው በእሥር ቤት ያኖሩታል፡፡ እስከ 30 ቀንም ድረስ ሳር እያበሉ ያስቀምጡትና በ30ኛው ቀን አውጥተው አርደው ይበሉታል፡፡

ሐዋርያው ማትያስንም በልማዳቸው መሠረት ዐይኖቹን አውልቀው አሠሩት፡፡ ሐዋርያውም በእሥር ቤት ሆኖ በዚያ ላይ ዐይኖቹን ታውሮ ሳለ በጭንቅ ወደ ጌታችንና ወደ እመቤታችን ይለምን ነበር፡፡ ነገር ግን እመብርሃንና ልጇ መድኃኔዓለም 30ኛው ቀን ሳይፈጸም ሐዋርያው እንድርያስን ወደ እርሱ ላኩለት፡፡ ማትያስም ዐይኑን ፈወሱለትና ማየት ቻለ፡፡

እንድርያስም በተዘጋው በር በተአምራት ገብቶ አሥርቤቱ ውስጥ ያሉ እሥረኞችን በስውር አውጥቶ ከከተማው ውጭ ካስቀመጣቸው በኋላ ሁለቱ ሐዋርያት ተመልሰው ሰውን ለሚበሉት ሰዎች ተገለጡላቸው፡፡

ለሐዋርያት ሞገሳቸው ጣዕመ ስብከታቸው የኾነች ክብርት እመቤታችን ለእኛም ትለመነን
2024/12/26 07:33:31
Back to Top
HTML Embed Code: