◦[ የቅዱስ ዳዊት የቀደመ መዝሙሩ ]◦
{ከቍጥር የወጣ መዝሙር ስለራሱ}
¹ ከወንድሞቼ ይልቅ እኔ ትንሽ ነበርሁ፤ በአባቴ ቤት ወጣት ነበርሁ፤ የአባቴንም በጎች እጠብቅ ነበር።
▰
² እጆቼ መሰንቆ ይመቱ ነበር፤ ጣቶቼም በገና ይደረድሩ ነበር።
▰
³ ለጌታዬ ማን ነገረው እርሱ እግዚአብሔር እርሱ ሰማኝ።
▰
⁴ እርሱ መልአኩን ልኮ አዳነኝ። የአባቴን በጎች ከምጠብቅበት ወሰደኝ፤ የተቀደሰ ቅባትን ቀባኝ።
▰
⁵ ወንድሞቼ ግን ያማሩና ያደጉ ነበሩ፤ እግዚአብሔር ግን በእነርሱ ደስ አላለውም።
▰
⁶ ልዩ ወገንን ልገጥመው ወጣሁ፤ በረከሱ ጣቶቹ ረገመኝ።
▰
⁷ እኔም ከወንዝ ሦስት ድንጋዮችን አነሣሁ፤ ግንባሩንም በወንጭፍ መታሁት። ያንጊዜም በእግዚአብሔር ኀይል ወደቀ።
▰
⁸ በላዩ የነበረውን ሰይፍ ወሰድሁ፤ የጎልያድን ቸብቸቦ ቆረጥሁት፤ ከእስራኤል ልጆችም ስድብን አራቅሁ።
▰ ▰ ▰

Forwarded from አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ (ንዋይ)
◦◆◦
እውነተኞቹ ኢትዮጵያውያን የተዋሕዶ ልጆችና መጪው ዕጣቸው፨
◦◆◦
ቀንና ጊዜ ባለፈ ቁጥር ሥጋ ለባሽ በመከራ ክብደት ይደክማል፡፡ ኃያል ጌታ ግን ለበረከቱ፣ ለምሕረቱ ያተማቸውን ልጆቹን ያጸናል፡፡ የሰጠውን ( የገባውን) ቃል ኪዳን ያከብራል፡፡
ሰው በድካም ዝሎ የተገባለትን ተስፋ ሁሉ ይተዋል፡፡ በብርቱ ድካም ዝሎ ይወድቃል፡፡ ልዑል ግን ያኔ ድካሙን ሁሉ ከድኖ፣ አድሶ፣ በብርታት ሞልቶ በደስታ እንዲቦርቅ ያደርገዋል፡፡
የታመንበት የሠራዊት ጌታ ሁሌም እስከ ዘለዓለሙ የታመነ ነው፡፡
የእግዚአብሔር ፍቅሩ፣ መታደጉ፣ በረከቱ ልቡን የሞላው ዳዊት እንዲሁ አለ፦
እግዚአብሔር ወገኖቹን እንደ አይን ብሌን ይጠብቃቸዋል፡፡ በማንኛውም የዲያበሎስ ዘዴ ይወድቁና ይጠፉ ዘንድ በፍፁም አይፈቅድም፡፡
ወገኔ የልዑል ልጅ፤ የቅዱሳን የከበሩት መላእክት ልጆች ብዙ ብትሰቃዩም ይድረሳችሁ የተገባችሁን ነጭ ልብስ ለበሳችሁ፡፡
አገራችን ኢትዮጵያ ልዑል ዙፋኑን የሚዘረጋባት፣ ልጆቹን እንቁዎቹን በዙፋኑ የሚያኖርባት፣ ድንግል ልጆችዋን በበረከቷ፣ በፍቅሯ የምታረሰርሳት፣ ኢትዮጵያ ቅዱሳን የከበሩት መላእክት ዙሪያዋን በእሳት አጥረው የሚጠብቁአት፣ የሚባርኳት ኢትዮጵያ፣ የፀናችው አንዲቷ የተዋሕዶ እምነት እንደፀሐይ የምታበራባት ኢትዮጵያ ለልዑል የሰራዊት ጌታ ሌትም ቀንም ለክብሩ ለስሙ ምስጋና እንደጅረት የሚፈስባት ድንግልና ቅዱሳን የከበሩት መላእክት፣ ቅዱሳን ሰማእታት፣ ነቢያት፣ሐዋርያት፣ ስማቸው የሚከብርባት፣ የሚመሰገኑባት ኢትዮጵያ በክብሯ ጥግ ማንም የማይደርስባት የእግዚአብሔር የስስት ልጁ ናት፡፡
ከዚህ ድንቅ አገር የተፈጠራችሁ፣ ለአባታችሁ ለልዑል፣ ለእንቁዋ ለአገራችሁ ኢትዮጵያ ዋጋ ከፍላችሁ በጭንቅ እዚህ ለደረሳችሁ ወገኖቼ እንኳን ደስ ያላችሁ፡፡ በእምነት ድሉን ተቀዳጅታችኋልና!
◆ ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልእክት 5 ◆

Forwarded from አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ (ዮሴፍ ETHIOPIA ◈ ኢ/ዓ/ብ)
"ይሁ ሁሉ የእግዚአብሔርን ስራ ማደናቀፍ ያለ ዋጋ ክፍያ ይታለፋል ማለት ስህተት ነው፡፡ የእግዚአብሔር ስራ ማንም በስጋ ጥበብና ጉልበት ሊያደናቅፈው የሚቻል አይደለም፡፡ ሲሞክርም ቅጣቱ ይሰነዘራል፡፡"
📎 ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልዕክት ቁጥር 5 ፡ ገፅ 38 * ተጻፈ መስከረም 21/2004 ዓ.ም
📎 ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልዕክት ቁጥር 5 ፡ ገፅ 38 * ተጻፈ መስከረም 21/2004 ዓ.ም
Forwarded from አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ (ንዋይ)
🟢🟡🔴
ጥቅምት 14 | በዚህች ቀን
🍀 #ቅዱስ_ፊልጶስ ዐረፈ።
በዘመነ ሐዋርያት በዚህ ስም የሚጠሩ አባቶች 2 ነበሩ። አንደኛው ከ12ቱ ሐዋርያት ሲቆጠር ዛሬ የምናከብረው ደግሞ ከ72ቱ አርድእት ይቆጠራል። ከቅዱስ እስጢፋኖስ ጋር ከተመረጡት ዲያቆናት አንዱ ነው።
ቅዱስ ፊልጶስ ያደገው የኖረውም በቂሣርያ አካባቢ ሲሆን ባለ ትዳር የልጆች አባት ነው።
ለኢትዮጵያውያን አባታችን፣ መምህራችን፣ ክርስትናን ያገኘንበት ቅዱስ ሰው ነው። (ሐዋ. 8፥26)
ቅዱስ ባኮስ ጃንደረባውን ያጠመቀ የነፍስ አባቱ ነው። ከ4 ደናግላን ልጆቹ ጋር ሲሰብክ ኖሮ በዚህ ቀን ዐርፏል።
🍀 #አቡነ_አረጋዊ ተሰወሩ።
ወላጆቻቸው ዘሚካኤል ሲሏቸው በበርሃ ገብረ አምላክ ተብለዋል። በኢትዮጵያ ደግሞ አረጋዊ ይባላሉ። አቡነ አረጋዊ ምንም የንጉሥ ልጅ ቢሆኑም በልጅነታቸው መጻሕፍትን ተምረው ነበርና ጠፍተው ገዳም ገቡ።
በዚያም በገዳመ ዳውናስ (ግብጽ) የታላቁ ቅዱስ ጳኩሚስ ደቀ መዝሙር ሆነው ከነ አባ ቴዎድሮስ ጋር ሥርዓተ መነኮሳትን ተምረዋል።
8ቱን ቅዱሳን ወደ ኢትዮጵያ እየመሩ ያመጡአቸውም እሳቸው ናቸው። የቅዱስ ያሬድና ዓፄ ገ/መስቀል የቅርብ ወዳጅም ነበሩ።
🍀 #ሙሽሮቹ_ገብረ_ክርስቶስ እና #ቅዱስ_ሙሴ ዕረፍታቸው ነው።
በተለያየ ሀገርና ጊዜ ቢሆንም ሁለቱም ከጫጉላ ቤት ወጥተው፣ ራሳቸውን ምስኪን አድርገው፣ የአባታቸው ደጅ ላይ ነዳይ ሆነው ሳይታወቁ እየለመኑ የኖሩ ተጋዳይ ቅዱሳን ናቸው።
ሙሽራው ገብረ ክርስቶስ በሃገራቸው ልሳን 'አብደል መሲሕ (የክርስቶስ ባርያ)' ይባላል። ለቅዱስ ሙሴና ለሌሎችም ሙሽርነትን ትቶ መመነንን ያስተማረ እርሱ ነው። ታላቁ አቡነ ኪሮስ አጎቱ ናቸው።
ቅ/ገብረ ክርስቶስ በአባቱ ቤት ደጃፍ 15 ዓመታት፣ ቅዱስ ሙሴ ደሞ 12 ዓመታት እየለመኑ ኖረው አርፈዋል።
T.me/Ewnet1Nat

ጥቅምት 15 | አባቶቻችን #ቅዱሳን_ሐዋርያት ከመንፈስ ቅዱስን መሞላት በኋላ ምድርን 12 ቦታ በእጣ የተካፈሉት ቀን ነው።
እሊህም፦
#ጴጥሮስ የተባለ ስምኦን፣
#እንድርያስ (ወንድሙ)፣ #ያዕቆብ ወልደ ዘብዴዎስ፣ #ዮሐንስ (ወንድሙ)፣ #ፊልጶስ፣ #በርተሎሜዎስ፣ #ቶማስ፣ #ማቴዎስ፣ #ያዕቆብ ወልደ እልፍዮስ፣ #ታዴዎስ (ልብድዮስ)፣ #ናትናኤል (ቀናተኛው ስምዖን) እና #ማትያስ (በይሁዳ የተተካው) ናቸው። (ማቴ. 10፥1)
ክብራቸውንም መድኃኔአለም በወንጌል እንዲህ ተናግሯላቸዋል።
በዚያን ጊዜ ጴጥሮስ መልሶ፦ "እነሆ እኛ ሁሉን ትተን ተከተልንህ። እንኪያስ ምን እናገኝ ይሆን?" አለው።
ጌታ ኢየሱስም እንዲህ አላቸው:- "እውነት እላችኋለሁ! እናንተስ የተከተላችሁኝ በዳግመኛ ልደት፣ የሰው ልጅ በክብሩ ዙፋን በሚቀመጥበት ጊዜ እናንተ ደግሞ በአሥራ ሁለቱ የእሥራኤል ነገድ ስትፈርዱ በአሥራ ሁለት ዙፋን ትቀመጣላችሁ።
[ማቴ. 19፥27]
🍀 #ቅዱስ_ሲላስ ሐዋርያ ዕረፍቱ ነው።
በመንፈቀ ሌሊት ግን ጳውሎስና ሲላስ እየጸለዩ እግዚአብሔርን በዜማ ያመሰግኑ ነበር፥ እስረኞቹም ያደምጡአቸው ነበር።
ድንገትም የወኅኒው መሠረት እስኪናወጥ ድረስ ታላቅ የምድር መንቀጥቀጥ ሆነ፤ በዚያን ጊዜም ደጆቹ ሁሉ ተከፈቱ የሁሉም እስራት ተፈታ።
የወኅኒውም ጠባቂ ከእንቅልፉ ነቅቶ የወኅኒው ደጆች ተከፍተው ባየ ጊዜ፥ እስረኞቹ ያመለጡ መስሎት ራሱን ይገድል ዘንድ አስቦ ሰይፉን መዘዘ።
ጳውሎስ ግን በታላቅ ድምፅ። ሁላችን ከዚህ አለንና በራስህ ክፉ ነገር አታድርግ ብሎ ጮኸ።
መብራትም ለምኖ ወደ ውስጥ ሮጠ፥ እየተንቀጠቀጠም ከጳውሎስና ከሲላስ ፊት ተደፋ፤
ወደ ውጭም አውጥቶ፦ ጌቶች ሆይ፥ እድን ዘንድ ምን ማድረግ ይገባኛል? አላቸው።
እነርሱም፦ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እመን አንተና ቤተ ሰዎችህ ትድናላችሁ አሉት።

❗️ዋኖቻችንን እንወቅ❗️(የጥያቄና መልስ መርሐ ግብር)
ውድ ቤተሰቦች፥ ዋኖቻችንን እንወቅ በሚል መርህ የቅዱሳንን ዜና ሕይወትና ገድል በጥቂቱ ማሳወቅ መጀመራችን ይታወቃል። ዋና ዓላማው ቅዱሳኑን ጠንቅቆ ማወቅ ብቻ ሳይሆን በሕይወትም እነሱን መምሰል እንድንለምድ ነው።
ለዚህም እንዲያግዘን በየዙሩ ከሚለቀቁት የቅዱሳንን ዜና ታሪኮች የተውጣጡ ጥያቄዎችን አዘጋጅተናል።
ጥያቄዎቹ የተዘጋጁበት ዓላማ ያነበብነውን ምን ያህል እንደያዝነው፣ ምን ያህል እንደተዋወቅናቸው ራሳችንን እንድንመዝንበት ነው። በተጨማሪም በነገሮች ምክንያት ልብ ሳንል ያለፍነውን ታሪካቸውን መልሶ እንዲያስተምረን ነው። ስለሆነም፦
🍀 ጥያቄዎቹን ለመመለስ መልስ ነው ያላችሁትን ፊደል ወይም ከፊደሉ አጠገብ ያለውን ክብ ◌ ምልክት መንካት ትችላላችሁ።
🍀 ጥያቄዎቹን ስትመልሱ ማንነታችሁን ሆነ መልሳችሁን ከራሳችሁ ሌላ ማንም ሰው አያውቀውም።
🍀 ትክክለኛውን መልስ ጥያቄውን ከሞከሩ በኋላ በአረንጓዴ ቀለም ✅ (ራይት) ተደርጎበት ያዩታል።
🍀 ስለ ጥያቄው ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት መልስ ከመለሳችሁ በኋላ የአምፖል (💡) ምልክቱን በመንካት ጥቆማን ማግኘት ትችላላችሁ።
🍀 መልሱን ባያውቁትም ከጥያቄው እና ከማብራሪያው ይማሩበታልና ይሞክሩት።
ሁላችሁም የቅዱሳኑን ታሪክ እና ጥያቄዎቹን እንድትጠቀሙበት እንወዳለን። የቅዱሳኑ በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን። አሜን፨
www.tg-me.com/Ewnet1Nat

አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ
❗️ዋኖቻችንን እንወቅ❗️(የጥያቄና መልስ መርሐ ግብር) ውድ ቤተሰቦች፥ ዋኖቻችንን እንወቅ በሚል መርህ የቅዱሳንን ዜና ሕይወትና ገድል በጥቂቱ ማሳወቅ መጀመራችን ይታወቃል። ዋና ዓላማው ቅዱሳኑን ጠንቅቆ ማወቅ ብቻ ሳይሆን በሕይወትም እነሱን መምሰል እንድንለምድ ነው። ለዚህም እንዲያግዘን በየዙሩ ከሚለቀቁት የቅዱሳንን ዜና ታሪኮች የተውጣጡ ጥያቄዎችን አዘጋጅተናል። ጥያቄዎቹ የተዘጋጁበት ዓላማ ያነበብነውን…
[ማሟሻ ጥያቄ 1]
ዋኖቻችንን እንወቅ❗️በሚል ዓላማ እስካሁን የቀረቡት የቅዱሳን ታሪክ ብዛት ስንት ነው?

Anonymous Quiz
22%
ሀ. 4/፬
58%
ለ. 3/፫
20%
ሐ. 5/፭
አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ
❗️ዋኖቻችንን እንወቅ❗️(የጥያቄና መልስ መርሐ ግብር) ውድ ቤተሰቦች፥ ዋኖቻችንን እንወቅ በሚል መርህ የቅዱሳንን ዜና ሕይወትና ገድል በጥቂቱ ማሳወቅ መጀመራችን ይታወቃል። ዋና ዓላማው ቅዱሳኑን ጠንቅቆ ማወቅ ብቻ ሳይሆን በሕይወትም እነሱን መምሰል እንድንለምድ ነው። ለዚህም እንዲያግዘን በየዙሩ ከሚለቀቁት የቅዱሳንን ዜና ታሪኮች የተውጣጡ ጥያቄዎችን አዘጋጅተናል። ጥያቄዎቹ የተዘጋጁበት ዓላማ ያነበብነውን…
[ማሟሻ ጥያቄ 2]
ዋኖቻችንን እንወቅ❗️በሚል ዓላማ በንጽጽርና የትምህርት ገጻችን ላይ የቅዱሳን ታሪክ እንደተለቀቀ ይታወቃል። እስካሁን ታሪካቸውና ቃልኪዳናቸው በገጻችን በአጭሩ ከተለቀቁት ቅዱሳን መካከል የማይመደበው የቱ ነው?

17%
ሀ. የቅድስት በርባራ አጭር ገድል
9%
ለ. የቅዱስ ላልይበላ (ላሊበላ) አጭር ገድል
32%
ሐ. የአቡነ እንድርያስ አጭር ገድል
43%
መ. የአቡነ አረጋዊ አጭር ገድል
አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ
❗️ዋኖቻችንን እንወቅ❗️(የጥያቄና መልስ መርሐ ግብር) ውድ ቤተሰቦች፥ ዋኖቻችንን እንወቅ በሚል መርህ የቅዱሳንን ዜና ሕይወትና ገድል በጥቂቱ ማሳወቅ መጀመራችን ይታወቃል። ዋና ዓላማው ቅዱሳኑን ጠንቅቆ ማወቅ ብቻ ሳይሆን በሕይወትም እነሱን መምሰል እንድንለምድ ነው። ለዚህም እንዲያግዘን በየዙሩ ከሚለቀቁት የቅዱሳንን ዜና ታሪኮች የተውጣጡ ጥያቄዎችን አዘጋጅተናል። ጥያቄዎቹ የተዘጋጁበት ዓላማ ያነበብነውን…
[ማሟሻ ጥያቄ 3]
ዋኖቻችንን እንወቅ❗️በሚል መሪ ቃል እየቀረቡት ያሉት የቅዱሳን አጭር ታሪኮች በምን መልኩ የተዘጋጁ ናቸው?
ዋኖቻችንን እንወቅ❗️በሚል መሪ ቃል እየቀረቡት ያሉት የቅዱሳን አጭር ታሪኮች በምን መልኩ የተዘጋጁ ናቸው?
Anonymous Quiz
6%
ሀ. በቪዲዮ ቅንብር
89%
ለ. በጽሑፍ እና በድምፅ ንባብ (ትረካ)
2%
ሐ. በአካል የጉባኤ ገለጻ
3%
መ. በ'ዩ-ቲዩብ' የቀጥታ ስርጭት
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ለ5ኛ ጊዜ መሬት መንቀጥቀጥ በድጋሚ ተከሰተ‼️
በአፋር ክልል አዋሽ 8:16 እና 8:51 ደቂቃ ላይ ከፍተኛ ንዝረት ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱ ታውቋል፣ በሌላ በኩል አዲስ አበባ ሰሚት፣አያት እንዲሁም በሰሜን ሸዋ ዞን አንኮበር፣አልዩ አምባ 9:25 ላይ የተከሰተ ሲሆን በሌሎች ቦታዎችም ንዝረቱ እንደተሰማ ተገልጿል።
በአፋር ክልል አዋሽ 8:16 እና 8:51 ደቂቃ ላይ ከፍተኛ ንዝረት ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱ ታውቋል፣ በሌላ በኩል አዲስ አበባ ሰሚት፣አያት እንዲሁም በሰሜን ሸዋ ዞን አንኮበር፣አልዩ አምባ 9:25 ላይ የተከሰተ ሲሆን በሌሎች ቦታዎችም ንዝረቱ እንደተሰማ ተገልጿል።
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ (ንዋይ)
🟢🟡🔴
ጥቅምት 17 | የሰማዕታት ቀዳሚ #ቅዱስ_እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆንነት ተሾመ።
#ቅዱስ_ፊልያስ_ሰማዕት
ሰማዕቱ የነበረበት ዘመን 3ኛው መቶ ክ/ዘ (ዘመነ ሰማዕታት) ሲሆን የግብጽ አውራጃም ጳጳስ ነበር። የመከራው ዘመን ሲመጣ በቃሉ ያስተማራቸውን እንደ በጎ እረኝነቱ በተግባር ይገልጠው ዘንድ ወደ መኮንኑ ሔደ።
ሕዝቡ በአንድነት ተሰብስበው ሳለ መኮንኑ ቁልቁልያኖስ ቅዱስ ፊልያስን 4 ጥያቄዎችን ጠየቀው። ምላሾቹ ለእኛ ሕይወትነት ያላቸው ናቸው።
1. "የእናንተ እግዚአብሔር ምን ዓይነት መስዋዕትን ይሻል?" ቢለው "እግዚአብሔርን ትሑት ልቦና፣ የዋህ ሰብእና፣ የቀና ፍርድና ቁም ነገር ደስ ያሰኘዋል" ሲል መለሰለት።
2. "የምትወዳቸው ሚስትና ልጆች የሉህም?" ሲለው ደግሞ "ከሁሉ የእግዚአብሔር ፍቅር ይበልጣል" አለው።
3. "ለነፍስህ ትጋደላለህ ወይስ ለሥጋህ?" ቢለው "ለ2ቱም እጋደላለሁ። አምላክ በአንድነት ፈጥሯቸዋልና። በትንሣኤ ዘጉባኤም ይዋሐዳሉና" ብሎታል።
4. "አምላካችሁ የሠራው ምን በጎ ነገር አለ?" ብሎትም ነበር። ቅዱስ ፊልያስ መልሶ፦ "አስቀድሞ ፍጥረታትን በጥንተ ተፈጥሮ ፈጠረ። በኋላም በሐዲስ ተፈጥሮ ያከብረን ዘንድ ወርዶ ሞተልን፣ ተነሣ፣ ዐረገ" ቢለው መኮንኑ "እንዴት አምላክ ሞተ ትላለህ!" ብሎ ተቆጣ። ቅዱሱም "አዎ! በለበሰው ሥጋ ስለ እኛ ሙቷል" ብሎ እቅጩን ነገረው።
ወዲያውም "እስከ አሁን የታገስኩህ በዘመድ የከበርክ ስለሆንክ ነው" ቢለው ቅዱሱ መልሶ "ክብሬ ክርስቶስ ነው። መልካምን ካሰብክልኝ ቶሎ ግደለኝ" አለው። በዚያን ጊዜ የሃገሩ ሰዎች "አትሙትብን! እባክህን ለመኮንኑ ታዘዘው?" ሲሉ ለመኑት።
ቅዱስ ፊልያስ "እናንተ የነፍሴ ጠላቶች ዘወር በሉ ከፊቴ! እኔ ወደ ክርስቶስ ልሔድ እናፍቃለሁና" ብሎ ገሠጻቸው። መኮንኑም ወስዶ ከብዙ ስቃይ ጋር ገድሎታል።
◦🍀◦

ግራኝን ከእነ ሰራዊቱ ያሳደደው የቅዱስ እስጢፋኖስ ሠራዊት!
ግራኝ የተባለው አሕዛባዊ ዓመፀኛ በተነሣና በክርስቲያኖች ላይ ጦርነትን በዐወጀ ጊዜ በየአውራጃውና በየመንደሩ ፍጅትና ሁከት ሆነ።
ግራኝም የረከሰች ሃይማኖታቸውን ያልተቀበለውን ኹሉ እንዲገድሉ ለሰራዊቱም ኹሉ ትእዛዝ ሰጠ። ብዙዎች ክርስቲያኖችም በግፍ በጭካኔ በሰይፍ ተገደሉ።
በእሳትም የተቃጠሉ አሉ፤ በመጋዝ የተሰነጠቁ አለ፤ ወደጥልቅ ጉድጓድ ተጥለው የሞቱ አሉ፤ ከየመንደራቸውም ወጥተው ወደተራራዎችና ዋሻዎች የተሰደዱ አሉ።
ጠንበላ በምትባል የቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን ባለችበት አውራጃም የግራኝ ሠራዊቶች ደርሰው ይኽችን የጠንበላን አውራጃ ከበቧት። የሀገሪቱም ሰዎች ወደ ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን ገብተው ሰማዕቱን ይማጸኑት ጀመር።
የግራኝም የወታደሮች አለቃ ለመሸመቅ አስቦ ወደ አንድ ዋሻ ሲገባ ዋሻው በተአምር ተደርምሶ ገደለው፤ በውስጡም ቀበረው።
ርጉም ግራኝም እሳት ይዞ ጠንበላ አውራጃ የምትገኘውን የቅዱስ እስጢፋኖስን ቤተ ክርስቲያን ሊያቃጥላት ቀረበ። ነገር ግን ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤቱን እንዲያቃጥል አልፈቀደለትምና ሊያቃጥላት አልቻለም።
ይልቁንም በቅዱስ እስጢፋኖስ ትእዛዝ በቤተ ክርስቲያኑ ጠፈር ላይ የነበሩ ንቦች ተነሥተው ከነሠራዊቱ እስከሩቅ አውራጃ ድረስ አሳደዱት። ግራኝም ከነሠራዊቱ በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ ፈጥኖ ሸሸ።
የጠንበላ ሀገር ሰዎችም ከግራኝ ያዳናቸውን የቅዱስ እስጢፋኖስን አምላክ ልዑል እግዚአብሔርን አመሰገኑ።
ሊቀ ዲያቆናት ቀዳሜ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስ ከዘመኑ ግራኞች ሀገራችንን ይታደግልን።