Telegram Web Link
ሸዋ ደብረሲና!

በሸዋ ደርበሲና የመሬት መሸራተት ተከሰተ የመሬት መንሸራተቱ የተከሰተዉም ልዩ ስሙ እንዶዴ አካባቢ ሲሆን አደጋው በመኖሪያ ቤቶች እና በእርሻ መሬት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል።አሁንም ቢሆ ን የአካባቢዉ ማህበረሰብ ከፍተኛ ትኩረት ያሻዋል!
🇳🇬 በናይጄሪያ በተከሰተው የጎርፍ አደጋ ባለፉት ሳምንታት 170 ሰዎች ህይወታቸው እንዳለፈ ዘገባዎች አመለከቱ

በሰሜናዊ ናይጄሪያ በሚገኙ አስር ግዛቶች በተከታታይ ቀናት በጣለ ዝናብ ሳቢያ በደረሰ የጎርፍ አደጋ በእርሻ መሬቶች ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱንና የሀገሪቱን የምግብ እጥረት እንዳያባብስ ስጋት መፈጠሩን የምዕራቡ ዓለም ጋዜጣ ሰኞ እለት ዘግቧል።

በተፈጥሮ አደጋው ከ200,000 በላይ ሰዎች ከመኖሪያ ቀያቸው እንደተፈናቀሉ የገለጸው ዘገባው ሰሜን ናይጄሪያ በጎርፉ በክፉኛው እንደተጎዳች አክሏል።

ጋዜጣው የናይጄሪያ ብሔራዊ የአደጋ ጊዜ አስተዳደር ባለስልጣን ቃል አቀባይ ማንዞ ኢዝኪዬል "በሚቀጥሉት ቀናት ማእከላዊ ክፍሎች እንዲሁም ወደታች ወረድ ብሎ ደቡባዊ ክፍሎችም ተመሳሳይ ጎርፍ ይገጥማቸዋል" ማለታቸውን ጠቅሶ አስነብቧል።

በናይጄሪያ በቅርቡ በተከሰተው የጎርፍ አደጋ 2,000 ሰዎች እንደተጎዱ እና ከ100,000 ሄክታር በላይ የእርሻ መሬት መውደሙን ዘገባው አክሎ ገልጿል።
Forwarded from አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ (ዮሴፍ ETHIOPIA ◈ ኢ/ዓ/ብ)
አይ አንች ከንቱ ዓለም
የሰው ልጅ አስገኝው ዝንጀሮ ነው ብለሽ
በዝንጀሮ ህመም ትተራመሻለሽ።
📌 "ጥበብ ፤ እውቀት ፤ ሀብት ፤ ወርቅ ፤ እንቁ ፤ ሥልጣኔ ፤ ኢንዱስትሪ ፤ ጀቱ  ታንኩ ፤ ኒኩለሩ  እነዚህ ሁሉ ከምንም ከምንም  አያድኑም ፡፡ በምንም መንገድ  አያድኑም፡፡

ትላንት በአንድ በሽታ በአንድ ይህ ኮቪድ በሚባል የታመሰውና ግራ የገባው ዓለም ኢኮኖሚውም በዚህ ምክንያት ደቆ ባዶ የሆነበት ዓለም ትርምስምሳቸውን ያወጣቸው አንድ በሽታ አንድ  የአንድ   በሽታ ገጽታ  ነበር ፡፡

አሁን ደሞ ከበፊቱም የከፋ እጅግ የከፋ የበሽታዎች አይነት የተፈጥሮ አደጋዎች እጅግ በዝተው ከሰባት እጥፍ በላይም እየጨመሩ እንደሚመጡ ዛሬም ለሁሉም ሰሚና ጠፊ ሁሉ ትውልድ ግልፅ ሊሆንለት ይገባል፡፡

እግዚአብሔር ያለውን ሳይፈጽም የሚቆም ነገር የለም፡፡ የተናገረው ሳይፈጸም ሳይከናወን የሚቀር ነገር የለም ፡፡ ወረፋውን ነው የሚጠብቀው ወገኖቼ ምንም የሚቀር ነገር የለም፡፡"

🇨🇬  በቀን 9 /12/2014 ዓ፡ም ከተለቀቀው፡፡
ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን የሉቃስ ወንጌል ትምህርት ክፍል ሁለት ላይ ለግንዛቤ ያህል ተቀንጭቦ የተወሰደ፡፡
📌 ጌታ ሆይ ዛሬም እንድንበት ዘንድ በመረጥኻቸው ባሮችህ በኩል የተናገርከውን ቃልህን፣ መልዕክትህን አልሰማንኽም። መልዕክታትህ ሁሉ ለስድብ ፣ ለነቀፌታ፣ ለትችት ሆኖብናል። ደስም አላሰኘንም። እነሆ በነቢዩ ኤርምያስ አንደበት የተናገርኸን ተፈጽሞብናል።
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
📹 🇮🇳 በህንድ ጉጃራት ክልል በጣለ ከባድ ዝናብ ምክንያት ድልድይ ተደረመሰ ‼️
አሁን..!

አሁን በኦሮሚያ ክልል ከገብረ ጉራቻ እና ቱሉ ሚልኪ መሀከል አንድ የህዝብ አውቶብስ ሙሉ ተሳፋሪ ከሾፌር ረዳት ጋር በታጠቁ ሀይሎች ታፍነው ተወስደዋል!
» መሪዎች ይጮሃሉ የሚሰማቸውም ያጣሉ ያደራጁት የጸጥታና የጦር ኃይል አይታዘዝም የመዳከም የመበተንም እጣ ይገጥማቸዋል። ሕዝቦች ለማንኛውም የመንግሥት ኃይል አይታዘዙም አይፈሩምም ሕግ የተባለ ሁሉ የሚያከብረው ያጣል።

» ሰላም ስሙ እንጂ ምግባሩና ምልክቱ ፈጽሞ ይጠፋል።

ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልዕክት 3 ገጽ 58 (የፖለቲካ ቀውስ) ተጻፈ መጋቢት 19/2001 ዓ.ም

አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ
🟢🟡🔴
ነሐሴ 24 | ጻድቁ #አቡነ_ተክለ_ሃይማኖት#ቅድስት_ክርስቶስ_ሠምራ፣ ክቡር #አባ_ቶማስ የዕረፍት በዓላቸው ነው።

#አባ_ተክለ_ሃይማኖት ከመድኃኔዓለም የተቀበሉት ቃልኪዳን

-☘️- እነሆ ስምህን ለሚጠራ መታሰቢያህን ለሚያደርግ ገድልህን ለሚጽፍ ለሚያነበውና ለሚሰማውም ቤተ ክርስቲያንህን ለሚሠራ በስምህ መብዓ ለሚሠጥ ለድኆችም በስምህ ለሚመጸውት በመታሰቢያህም ቀን ለሚቆርብ ስለ አንተ በጎ ሥራ ለሚሠራ ሁሉ እኔ እስከ ዐሥር ትውልድ እምርልሃለሁ"።

አባታችንም እጅግ ደስ አለው ለጌታችንም ሰገደ። ጌታችንም ከእርሱ ዘንድ በታላቅ ክብር ወደ ሰማያት ዐረገ።

ከዚህም በኋላ አባታችን በንዳድ በሽታ ታመመ። ዕድሜውም ዘጠና ዘጠኝ ዓመት ከስምንት ወር ከአንድ ቀን ሆኖት በለመለመ ዕርጅና ነሐሴ 24 ቀን ዐረፈ።

#ቅድስት_ክርስቶስ_ሠምራ ከመድኃኔዓለም የተቀበለችው ቃልኪዳን፦

-🍀- በችግሩ ወይም በጭንቁ ጊዜ በመታመን ስምሽን ቢጠራ እኔ ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ አድነዋለሁ።

-🍀- የገድልሽን ዜና የሚናገረውን መጽሐፍ የጻፈ ወይም ያጻፈ እኔ ስማቸውን በሕይወት መጽሐፍ እጽፍላቸዋለሁ። ቤተ ክርስቲያንሽን የሠራ ወይም ያሠራ ያሣነፀ ወይም ያነፀ እኔ በመንግሥተ ሰማያት ንጹሕ አዳራሽ አዘጋጅለታለሁ። በስምሽ ለተራበ ያበላ እኔ በዕለተ አርብ ከተቆረሰው ሥጋየ አበላዋለሁ። በስምሽ ለተጠማው እፍኝ ውሃ ያጠጣ እኔ በዕለተ አርብ ከጎኔ በሰሰው ደሜ አረካዋለሁ።

🍀 ሥጋሽ ከተቀበረበት ሄዶ መካነ መቃብርሽን የተሳለመ የእናቴን የማርያምን መካነ መቃብር እንደተሣለመ ይቆጠርልታል።

#ቅዱስ_አባ_ቶማስ
🌿 ከልጅነቱ ቅዱሳት መጻሕፍትን የተማረ፣

🌿 ገና በወጣትነቱ መንኖ ገዳም የኖረ፣

🌿 መርዓስ በምትባል ሃገር ጵጵስና ተሹሞ በእረኝነት ያገለገለ፣

🌿 በሐዋርያዊ አገልግሎት ብዙ አሕዛብን ወደ ክርስትና የመለሰ

🌿 በዘመነ ሰማዕታት ብዙ መከራን የተቀበለ አባት ነው።

ጨካኞቹ ቅዱሱን ለ22 ዓመታት አካሉን እየቆራረጡ ለጣዖታቸው ያጥኑ ስለ ነበር 2 እግሮቹ፣ 2 እጆቹ፣ 2 ጀሮዎቹ፣ 2 አፍንጫዎቹ፣ 2 ዐይኖቹ፣ ሁሉ አልነበሩም። ነገር ግን እንዲህም ሆኖ አልሞተም ነበር።

◈ በመጨረሻም በዘመነ መና- ፍቃን አርዮስን ካወገዙት 318ቱ ሊቃውንት እንዳንዱ ተቆጥሯል። ቅዱስ ቶማስ ጵጵስና በተሾመ በ40 ዓመቱ በዚህች ቀን ዐርፏል።


የጻድቃንን፣ የሰማዕታትን፣ የሐዋርያትንና ሊቃውንትን አክሊልም ተቀብሏል።

የአቡነ ዘርዐ ቡሩክ የአክስት ልጅ የሆኑት #አቡነ_ጊዮርጊስ_ዘግሽ ዕረፍታቸው ነው።

የተፀነሱትም ሆነ የተወለዱት በመልአክ ብሥራት ነው፡፡

ሰማዕትነት ለመቀበል ወደ ፋርስ በመሄድ ለ9 ሺህ ሰማዕታት መሪ ሆነው ጣዖትን ካጠፉ በኋላ በሰይፍ ተሰይፈው ሰማዕት የሆኑ ታላቅ አባት ናቸው።

                 #እንኳን_አደረሳችሁ
                  T.me/Ewnet1Nat
2024/09/23 12:22:44
Back to Top
HTML Embed Code: