Telegram Web Link
አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ
Photo
‹‹የጥቁሩን አህያ ራስ ነጩ እህያ ላይ፣ የነጩን አህያ ራስ ጥቁሩ አህያ ላይ››

አቡነ ቶማስ የመርዓስ ሀገር ኤጲስ ቆጶስ ሲሆኑ ታላቅ ሰማዕትነትን የተቀበሉ ሃይማኖት ምግባራቸው እጅግ የቀና ታላቅ አባት ናቸው።

ከሃዲው ዲዮቅልጥያኖስ በነገሠ ጊዜ ክርስቲያኖቹን ሲያሠቃዩ በነበረበት ወቅት ከንጉሡ መኳንንት አንዱ ወደ መርዓስ ሄዶ አቡነ ቶማስን በጭፍሮቹ አሲያዛቸው።

አባታችንን እንደያዟቸው ደብድበው በምድር ላይ እየጎተቱዋቸው ደማቸው እየፈሰሰ ወሰዷቸው።

መኰንኑ ‹‹ለአማልክት ስገድ›› አላቸው። አቡነ ቶማስም ‹‹ከእግዚአብሔር በቀር የሚሰግዱለት አምላክ የለም›› አሉት።

መኰንኑም እጅግ የበዙ ጽኑ ሥቃዮችን አሠቃያቸው። የነዳጅ ድፍድፍ አፍልተው በሰውነታቸው ላይ እንዲሁም በአፍና በአፍንጫቸው ጨመሩባቸው። ቶሎ ብለው እንዲሞቱ ሳይሆን በሥቃይ ሆነው እንዲቆዩ በማድረግ ለ22 ዓመታት በጨለማ ውስጥ እያሰሩ አሠቃዩአቸው።

ከሃዲያኑም በየዓመቱ ወደ እስር ቤቱ እየገቡ አንድ አካላቸውን ይቆርጣሉ፡፡ እጆቻቸውንና እግሮቻቸውን በየተራ ቆራረጧቸው፡፡ አፍንጫቸውን፣ ከንፈሮቻቸውን፣ ጆሮዎቻቸውን ሁሉ በየተራ እየቆረጡ ለ22 ዓመታት ጣዖታቸውን ሲያጥኑበት ኖረዋል፡፡

አንዲት ደግ ክርስቲያን ሴት ግን የተጣሉበትን ጉድጓድ አይታ ስለነበር በድብቅ ሌሊት እየሄደች ትመግባቸው ነበር፡፡

ደገኛውና ጻድቁ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ በነገሠ ጊዜ ይህች ሴት ሄዳ ስለ አቡነ ቶማስ ነግረችውና አባታችንን ከተጣሉበት ጉድጉድ አወጣቸው፡፡

ቆስጠንጢኖስ የከበሩ 318 ኤጲስ ቆጶሳትን በኒቅያ አገር እንዲሰበሰቡ ሲያደርግ አንዱ አቡነ ቶማስ ነበሩ፡፡ ወደ ጉባዔውም ሲሄዱ ደቀ መዛሙርቶቻቸው በቅርጫት አድርገው በአህያ ጭነው ወደ ጉባኤ ኒቂያ ይዘዋቸው ሄደዋል፡፡

በመንገድም ሳሉ ዐላዊያኑ አግኝተዋቸው አህዮቻቸውን ሌሊት ራስ ራሳቸውን ቆርጠው ጣሉባቸው፡፡ አቡነ ቶማስም ራሳቸው የተቆረጡትን አህዮች አምጡልኝ ብለው የጥቁሩን አህያ ራስ ከነጩ፣ የነጩን አህያ ራስ ከጥቁሩ ገጥመው ቢባርኳቸው ሁሉም አህዮች ከሞት ተነሥተዋል፡፡

ከጉባዔውም ሲደርሱ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ጽድቃቸውን ዐውቆ ‹‹አባቴ በረከትዎ ትድረሰኝ›› በማለት በዐላዊያኑ የተቆራረጠ አካላቸውን ዳሶ ተባርኳል፡፡

አቡነ ቶማስ ዘመርዓስም ከሌሎቹ ኤጲስ ቆጶሳት ጋር ሆነው አርዮስን መክረውና አስተምረው እምቢ ቢላቸው አውግዘውት ወደ ሀገራቸው እንደተመለሱ ነሐሴ 24  በሰላም ዐርፈዋል፡፡

የአቡነ ቶማስ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን።
🟢🟡🔴
ነሐሴ 26 | #አቡነ_ኢየሱስ_ሞዐ እና #አቡነ_ሃብተ_ማርያም የፅንሰታቸው በዓል ነው።

#አቡነ_ኢየሱስ_ሞዐ
አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ የተወለዱት ጎንደር የድሮው ስማዳ (ዳኅና) አካባቢ ሲሆን ወላጆቻቸው ዘክርስቶስና እግዚእ ክብራ ይባላሉ።

የተፀነሱት ነሐሴ 26፣ የተወለዱት ግንቦት 26 በ1210 ዓ.ም ነው። አንዳንድ ምንጮች በ1196 ዓ.ም ያደርጉታል።

በከፋች ዮዲት ጉዲት ለ40 ዓመታት በሃገሪቱን ክርስትና ተዳከመ። ባዕድ አምልኮም ነገሠ።

አቡነ ኢየሱስ ሞዐ (ትርጉሙ ኢየሱስ ክርስቶስ አሸነፈ ማለት ነው) ደግሞ ሃይማኖታቸው የቀና ከ800 በላይ ክርስቲያኖችን ሰብስበው በሃገሪቱ ትልቅና የመጀመሪያው ሊባል የሚችል ቤተ መጻሕፍት አደራጁ።

አርድእትን በቅድስናና በትምህርት አብስለው አመነኮሱና "ሒዱ ሃገሪቱን ታበሩ ዘንድ ተጋደሉ" ብለው አሰናበቷቸው።

ከእነዚህ መካከልም፦
◆ አቡነ ተክለ ሃይማኖትን
◆ አቡነ በጸሎተ ሚካኤልን እና
◆ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫን መጥቀስ እንችላለን።

በዚህም ምክንያት ጻድቁ "ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን - አእላፍ ቅዱሳንን የወለደ" ሲባሉ ይኖራሉ።

#አቡነ_ሃብተ_ማርያም
ቅዱስ አባታችን ፅንሰታቸው ነሐሴ 26፣ ልደታቸው ግንቦት 26፣ ዕረፍታቸው ኅዳር 26 ነው፡፡

ጻድቁ መካነ ሙላዳቸው ሽዋ (የራውዕይ) ውስጥ ሲሆን አባታቸው ፍሬ ቡሩክ፣ እናታቸው ደግሞ ቅድስት ዮስቴና ትባላለች። በተለይ ቅድስት ዮስቴና እጅግ ደመ ግቡ፣ ምጽዋትን ወዳጅ፣ ቡርክት ሴት ነበረች።

ልትመንን ከቤቴ ብትወጣም በባሕታዊ ትእዛዝ ተመልሳ ጻድቁን ወልዳ አሳድጋ እንደ ገና መንና በተጋድሎ ኑራ 7 አክሊላትን ተቀብላ ዐርፋለች።

#ብፅዕት_ሣራ
በዚህ ቀን በዚህች ቀን ለአብርሃም ሚስት ለተመሰገነች ሣራ መታሰቢያዋን እናደርግ ዘንድ የቤተ ክርስቲያን መምህራን አባቶች አዘዙ።

T.me/Ewnet1Nat
ሶማሊያ

የሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዛሬ ወደ ግብፅ ካይሮ አቅንተው ከግብፅ አቻቸው ጋር ውይይት አድርገዋል!

ውይይቱ ምን ላይ ያተኮረ ነው የሚለው በግልፅ ባይታወቅም በሁለቱ ሀገራት የደህንነት ጉዳዮች ላይ እንደተወያዩ የሀገሪቱ የዜና ምንጮች ዘግበዋል።

ግብጽ ከቀናት በፊት የጦር መሳሪያ ወደ ሶማሊያ ማጓጓዛ የሚታወስ ነው።

በተመሳሳይ ዜና የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሀመድ ከሀገሪቱ የጦር መሪ ጋር ውይይት ሲያደርጉ ውለዋል ።
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Audio
ገድለ አቡነ ኢየሱስ ሞዓ
Audio
መልክአ ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ
🟢🟡🔴
ነሐሴ 27 | ከ7ቱ የመላእክት አለቃ አራተኛ የሆነ #የቅዱስ_ሱርያል የበዓሉ መታሰቢያ ነው።

የመላእክት መዓርግ ሲነገር ቅ/ሚካኤል፣ ቅ/ገብርኤል፣ ቅ/ሩፋኤል ብሎ ቀጥሎ የሚመጣው ሱርያል ነው።

🍀 በሊቀ ካህናት ኤሊ ዘመን፥ #ነቢዩ_ሳሙኤል በቤተ መቅደስ ሳለ የተጠራበት የመታሰቢያው ዕለት ነው።

አባቱ ሕልቃና፣ እናቱ ሐና ይባላሉ። እነርሱም ከሌዊ ነገድ ከካህኑ አሮን ወገን ናቸው። ሐናም መካን ነበረች። ክብር ይግባውና ወደ እግዚአብሔር እያለቀሰች አዘውትራ ስለ ማለደች ይህን የተባረከ ልጅ ሰጣት።

ከዚህም በኋላ ገና ስትፀንሰው እንደተሳለች ወደ እግዚአብሔር መቅደስ አቀረበችው። ካህኑ ኤሊንም በመላላክ የሚያገለግለው ሆነ።

የካህኑ የኤሊ ልጆች ግን ክፉዎች ነበሩ። እግዚአብሔርንም አይፈሩም ነበር፤ በቅዱስ መሥዋዕቱም ላይ በደሉ። ይህ ሕፃን ሳሙኤል ግን በኤሊ ፊት ለእግዚአብሔር ሲያገለግል ኖረ። በነዚያ ወራቶችም ቃለ እግዚአብሔር ውድ ነበር፤ የሚታይ ራእይም አልነበረም።

ይህም ነቢይ ሳሙኤል በሕይወት በኖረበት ዘመን ሁሉ እስራኤልን አስተዳደራቸው። ከዚህም በኋላ ሰኔ ዘጠኝ በሰላም አርፏል።

🍀 ታላቁ ጻድቅ #አቡነ_ዘርዐ_ቡሩክ ልደታቸው ነው።

በትንቢት የተወለዱት እኚህ ጻድቅ አባታቸው ደመ ክርስቶስ ዐይነ ሥውር የነበረ ሲሆን አቡነ ዘርዐ ቡሩክ በተወለዱ ጊዜ ግን የአባታቸውን ዐይን አብርተውለታል።

በሰባት ዓመታቸውም «ይህን ዓለም ክፋቱን እንዳላይ ዐይኖቼን አሳውርልኝ» በማለት ዐይናቸውን እንዲያጠፋላቸው አምላካቸውን ለምነው እንደፈቃዳቸው ዐይነ ሥውር ሆነዋል።

ነገር ግን ከሰባት ዓመት በኋላ በ14 ዓመታቸው ጌታችን "ለዓለም የምታበራ ብርሃን አደርግሃለሁና ዐይንህም ይብራ" በማለት ዐይነ ብርሃናቸውን መልሶላቸው እንዲያዩ አድርጓቸዋል።

www.tg-me.com/Ewnet1Nat
2024/09/23 14:32:27
Back to Top
HTML Embed Code: