Telegram Web Link
ሃይቲ.pdf
12.2 MB
ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃናዊ መንግሥት ደብዳቤ
ለ ሃይቲ  መንግሥት

7/5/2016 ዓ.ም
ሆንዱራስ.pdf
12.1 MB
ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃናዊ መንግሥት ደብዳቤ
ለ ሆንዱራስ   መንግሥት

7/5/2016 ዓ.ም
ሉቶኒያ.pdf
20.7 MB
ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃናዊ መንግሥት ደብዳቤ
ለ ሉቶኒያ መንግሥት

7/5/2016 ዓ.ም
ሉክሰምበርግ.pdf
20.5 MB
ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃናዊ መንግሥት ደብዳቤ
ለ ሉክሰምበርግ  መንግሥት

7/5/2016 ዓ.ም
ሊባኖስ.pdf
19.5 MB
ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃናዊ መንግሥት ደብዳቤ
ለ ሊባኖስ መንግሥት

7/5/2016 ዓ.ም
ሊቼኒስታይን.pdf
12.3 MB
ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃናዊ መንግሥት ደብዳቤ
ለ ሊቼኒስታይን መንግሥት

7/5/2016 ዓ.ም
ላቲቪያ.pdf
20.7 MB
ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃናዊ መንግሥት ደብዳቤ
ለ ላቲቪያ  መንግሥት

7/5/2016 ዓ.ም
ላይቤሪያ.pdf
12.4 MB
ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃናዊ መንግሥት ደብዳቤ
ለ ላይቤሪያ   መንግሥት

7/5/2016 ዓ.ም
ሌሴቶ.pdf
12.4 MB
ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃናዊ መንግሥት ደብዳቤ
ለ ሌሴቶ   መንግሥት

7/5/2016 ዓ.ም
ማሊ.pdf
12 MB
ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃናዊ መንግሥት ደብዳቤ
ለ ማሊ  መንግሥት

7/5/2016 ዓ.ም
#የካቲት_4
የአይቬሮኗ የአምላክ እናት
አቃቢተ ኆኅት (ደጅ ጠባቂዋ) ሥዕል

ይህችም ጉንጯ እውነተኛ ደም የሚደማው የእመቤታችን ሥዕል ናት፨
አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ
#የካቲት_4 የአይቬሮኗ የአምላክ እናት አቃቢተ ኆኅት (ደጅ ጠባቂዋ) ሥዕል ይህችም ጉንጯ እውነተኛ ደም የሚደማው የእመቤታችን ሥዕል ናት፨
🌹🌹
ተአምር አድራጊዋ የእመቤታችን ሥዕል
▰ ▰ ▰

በዚህች ዕለት ሉቃስ የሣላት ከጒንጯ ደም የሚፈስሳት ተአምር አድራጊዋ የእመቤታችን ሥዕል የምትታሰብበት በዓሏ ነው።

ይኸውም ከ829-842 ዓ.ም በቤዛንታይን የነገሠው ንጉሥ ቴዎፍሎስ በቅዱሳት ሥዕላት ላይ በክፋት ተነሳሥቶ ዐዋጅ በማወጁ ወታደሮቹ በርሱ ትእዛዝ በእያንዳንዱ ቤት እየዞሩ ቅዱሳት ሥዕላትን ለማጥፋት ፍተሻ ያደርጉ ነበር።

በኒቅያ ከተማ አቅራቢያ አንዲት የተቀደሰች ሴት ነበረች። ቅዱስ ሉቃስ የሣላት የአምላክ እናት የቅድስት ድንግል ማርያም ውብ ሥዕሏን በቤቷ ውስጥ ደብቃ በማኖር በሥዕሏ ፊት መብራትን እያበራች ከልጇ እንድታማልዳት ትማፀን ነበር፡፡

የከሓዲው ንጉሥ ወታደሮቹም የአምላክ እናት ሥዕል በቤቷ እንዳለች በማወቃቸው ወደ ቤቷ በድንገት ዘልቀው ገቡ። ከመካላቸውም አንዱ ወታደር የእመቤታችንን ሥዕሏን በያዘው ጦር ጒንጯ ላይ ወጋት፡፡ ኾኖም ግን በእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ ይኽ ክፉ ሥራው በተአምር ተተክቶ፤ ከተወጋው ከአምላክ እናት ፊት ላይ ደም ይፈስስ ጀመር፡፡

ይኽን ግሩምና ድንቅ ተአምር ባዩ ጊዜ ወታደሮቹ ደንግጠው ሸሽተዋል። ሴቲቱም ይኽነን ድንቅ ተአምር ባየች ጊዜ ሌሊቱን ሙሉ በሥዕሏ ፊት መብራትን አብርታ በአምላክ እናት በቅድስት ድንግል ማርያም ሥዕል ፊት ስትጸልይ ዐደረች። በነጋታውም በእግዚአብሔር ፈቃድ ከጒንጮቿ ደም የፈሰሳትን የአምላክ እናት ሥዕሏን በባሕሩ ላይ እንድታስቀምጥ ታዘዘችና አስቀመጠቻት።

ሥዕሏም በባሕሩ ላይ በመንሳፈፍ በማዕበሉ እየተነዳች ያለምንም መስጠምና መርጠብ ወደ ምዕራብ አቅጣጫ ጉዞዋን አድርጋ ወደ አቶስ ደረሰች፡፡ ጊዜያቶች ካለፉ በኋላ ከዕለታት በአንዳቸው ምሽት በአቶስ ተራራ የአይቬሮን ገዳም መነኮሳት የብርሃን ምሰሶ በባሕሩ ላይ ተተክሎ እንደ ፀሓይ ሲያበራ ተመለከቱ፡፡

ይኽም ተአምር ለተካታታይ ቀናቶች በመቀጠላቸው በዚያ የተቀደሰ ተራራ በምናኔ ያሉ አባቶች ኹሉ በአንድ ላይ ተሰባስበው በማድነቅ የብርሃን ምሰሶ ወደተተከለበት የአምላክ እናት ሥዕል በላዩ ላይ ወደ ተንሳፈፈበት ወደ ባሕሩ በመውረድ ወደ ሥዕሏ ለመጠጋት ቢሞክሩም ሥዕሏ ወደ ኋላዋ እየተመለሰች ሊያነሷት አልተቻላቸውም፡፡

በዚያው የአይቮሪዮን ገዳም ረድእ (የጉልበት አገልጋይ) ኾኖ የሚኖር አባ ገብርኤል የተባለው መነኩሴ ብቻ ሥዕሏን ከባሕር ውስጥ ማንሣት የሚችል እንደኾነ የአምላክ እናት ለመነኮሳቱ ገለጠችላቸው።

በተመሳሳይም ለአባ ገብርኤል እመቤታችን ተገልጣለት “ወደ ባሕሩ ኺድ፤ ማዕበሉንም ሳትፈራ በባሕሩ ውስጥ በእምነት ተጓዝ፤ እናም ኹሉም ለዚኽ አንተ ላለኽበት ገዳም ያለችን ፍቅርና ርኅራኄ ምስክር እንዲኾኑ፤ ሥዕሌን ከባሕር አውጣ” በማለት ነገረችው፡፡

ከዚያም በአቶስ ተራራ ያሉት መናንያን ኹሉ አባ ገብርኤልን ይዘው ልብሰ ተክህኖ ለብሰው፣ እያመሰገኑ፣ በማዕጠንታቸው ዕጣን እያጠኑ የብርሃን ምሰሶ ወደተተከለበት የአምላክ እናት ሥዕል ወዳለበት ወደ ባሕሩ ኼዱ።

አባ ገብርኤልም በደረቅ መሬት እንደሚጓዝ ያለምንም ፍርሃት ወደ ባሕሩ ውስጥ በመግባት በናፍቆት ኾኖ የአምላክ እናት የቅድስት ድንግል ማርያምን ሥዕሏን በደረቱ ታቅፎ ተሳለማትና ወደ ባሕር ዳርቻ ይዟት ወጣ። እነርሱም በደስታ ኾነው እጅ ነሷት፡፡

ከዚያም ማግሰኞ በጠዋቱ ሥዕሏ ባረፈበት ቦታ ላይ በሚያመሰግኑበት ጊዜ ቀዝቃዛና ጣፋጭ ውሃ ከምድር ላይ ፈለቀላቸው፡፡ ከዚያም የእመቤታችንን ሥዕሏን በታላቅ ክብር በምስጋና ይዘው በመኼድ ወደ ቤተ መቅደስ አግብተው በመንበሩ ላይ አስቀመጧት፡፡

ነገር ግን በነጋታው መነኮሳቱ ወደ ቤተ መቅደስ ገብተው መብራት ሲያበሩ የእመቤታችን ሥዕሏን ባስቀመጡበት ቦታ አላገኟትም። ይልቁኑ በመግቢያው በር ባለው ግድግዳ ላይ ተሰቅላ አገኟት።

እነርሱም መልሰው ቦታዋ ላይ ቢያኖሯትም ተመልሳ በገዳሙ መግቢያ ላይ ተሰቅላ ያገኟት ነበር፤ ከዚያም እመቤታችን ለአባ ገብርኤል ተገልጻለት፦
   “ለወንድሞች እንዲኽ ብለኽ ንገራቸው፤ ከዚኽ በኋላ ሥዕሌን ማግባት የለባቸውም፤ የእኔስ ፈቃድ በእናንተ ልጠበቅ ሳይኾን እኔን በምልጃዬ ጥላ በዚኽም ዓለም በወዲያኛውም ዓለም ልጋርዳችኊ እንጂ፤ ሥዕሌን በገዳሙ በምታዩበት ጊዜ ኹሉ የልጄ ምሕረትና ጸጋ ከእናንተ አይቋረጥም” አለችው፡፡

በዚህ ምክንያት ሥዕሏ በነገረ መለኮት ሊቃውንት "አቃቢተ ኆኅት" (ደጃፍን የምትጠብቅ) Panagia Portaitissa ("She who resides by the door" or "Keeper of the gate" ትባላለች።

ለአባ ገብርኤል የተለመነች እና በረከቷን እንዳሳደረችበት ዛሬም የምልጃዋ ጥላ በዚኽም ዓለም በወዲያኛውም ዓለም አይለየን።

T.me/Ewnet1Nat
ኢትዮጵያ.pdf
15.2 MB
ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃናዊ መንግሥት ደብዳቤ
ለ ኢትዮጵያ መንግሥት

7/5/2016 ዓ.ም
🟢 🟡 🔴
የካቲት 6 | ቅድስት ማርያም እንተ ዕፍረት (ባለ ሽቱዋ ማርያም)

በዚህችም ቀን ጌታን ሽቱ ለቀባችው ማርያም የዕረፍቷ መታሰቢያ ነው። ይችም ቅድስት አስቀድማ ኑሮዋን በዝሙት ያሳለፈች ኃጢአተኛ ነበረች።

እርሷም ጎልማሶችን ወደርሷ ትማርካቸው ዘንድ በየራሱ በሆነ ሽልማትና ጌጥ ትሸለም ነበር።

በአንዲትም ዕለት እንደ ልማድዋ ተሸልማ አጊጣ፣ ሽቱም ተቀብታ፣ ፊቷን በመስታዋት ተመለከተች።

የጉንጯ ቅላትና ደም ግባቷ የዓይኗም ወገግታና ጥራት ማማሩን አይታ እያደነቀች አንድ ሰዓት ያህል ቆየች። ከዚህም በኋላ በጎ ኀሳብ በላይዋ መጣ። ሞትንና የዚህን ዓለም ማለፍ አሰበች።

የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስም ኃጢአተኞችን እንደሚቀበልና ኃጢኣትንም እንደሚአስተሰርይ ሰምታ ገንዘቧን ወስዳ የአልባስጥሮስን ሽቱ ገዝታ በስምዖን ዘለምጽ ቤት ለምሳ ተቀምጦ ሳለ ወደ ጌታችን ሔደች።

ከእግሩ በታችም ሰግዳ ያንን ሽቱ ቀባችው። እግሮቹን በዕንባዋ አጠበችውና በራስዋ ጠጉር ወለወለችው።

ጌታችንም የፍቅርዋን ጽናት አይቶ ኃጢኣቷን በደሏን ተወላት። የመንግሥት ወንጌልም በሚሰበክበት ይህን ያደረገችውን እንዲአስቡ አዘዘ።

(በስሟ መማጸን፣ በአቅም መዘከር ዋጋ አለው)
🍀
T.me/Ewnet1Nat
🍀🍀
ልመናዋ ክብሯ ከአገልጋዮቿ ጋር ይሁንና ይህች ንዕድ ክብርት ማርያም እንተዕፍረት ያደረገችው ተአምር ይህ ነው፡፡

ቅድስትና ብፅዕት የምትሆን ይህችን ማርያም እንተዕፍረት የምትወዷትና የምታከብርዋት የቤክርስተያን ልጆች አባቶቼ እና ወንድሞቼ ሆይ ለወዳጇ ለአንድ ዲያቆን ያደረገችለትን ስሙ!

በአንዲት አገር አንድልጅ ነበር፡፡ ያም ልጅ ከእለታት አንድ ቀን የዲቁና ሹመት ለመቀበል ገብርኤል ወደሚባል ጳጳስ ይሄድ ዘንድ ተነሣ፡፡ ከጓደኞቹ ከአምስቱ ዲያቆናት ጋር የዲቁናውን ማዕረግ ተቀብሎ ሲመለስ ያ ልጅ ጥኑ በሽታን ታመመ፡፡ መንገዱንም በእግሩ መሄድ ተሳነው፡፡

ወንድሞቹ /ጓደኞቹ/ ዲያቆናት እንዲህ አሉት፡፡ ወደ አገራችን እንደርስ ዘንድ እኛ ትተንህ ልንሄድ ነውና ሥንቃችንን ከፍለህ ስጠን አንተ ግን ፈጽመህ ታመሃል። ስለዚህ ከአንተ ጋር መቆየት አንችልም፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር ይርዳህ፡፡

እነዚህም ዲያቆኖች እንደዚህ ብለው ይህን ከተናጉ በኋላ በጤንነታቸው እየታጀሩ ያን ዲያቆን ትተውት ሄዱ፡፡ ያም ልጅ ከመንገድ ዳር ከዋርካ ዛፍ በታች /ሥር/ ተኝቶ በጎዳና መካከል እያለቀሰ ከአንድ ዲያቆን ጋር ቀረ፡፡

ወደ አያቱ ዛር እንዲህ እያለ ይለምን ጀመር፦ አንተ የአያቴ ዛር ሆይ ከዚህ ፅኑ በሽታ ያዳንከኝ እንደሆኑ ለአንተ የሚጎዘጎዝ ሣር አጭድልህኣለሁ፡፡ በዚህ በአያቱ ዛር ከተማፀነ በኋላ ይችውም የአባቱ እናት ናት፡፡ የሚረዳው ከደዌውና ከጽኑ በሽታው የሚያድነው አላገኘም፡፡

ዳግመኛ ፈጽሞ አለቀሰ። አበቶቼን የረዳሻቸው ቅድስት ማርያም እንተዕፍረት ሆይ እንደዚህ እኔንም ከዚህ በሽታ ፈውሺኝ እያለ ብዐዓት ገባ ይህን ተናግሮ እንባውን ወደ ሰማይ ረጨ፡፡

የዚያን ጊዜ ከበሽታው ድኖ እግዚአብሔርን እያመሰገነ ቅድስትና ብፅዕት የምትሆን የማርያም እንተ ዕፍረትም ድንቅ ሥራ እያደነቀ መንገዱን ሄደ።

ቅድስትና ንዕድ ክብርት የምትሆን የማርያም እንተዕፍረት ልመናዋ በረከቷ ከወዳጆችዋ  ጋር እንዲሁም ከመላው ክርስቲያን ጋር ይሁን ለዘለዓለም ዓለም አሜን፡፡

T.me/Ewnet1Nat
ለኢትዮጵያ መንግሥት፥ በኢትዮጵያም ውስጥ ላላችሁ ማናቸውም የመንግሥት ጠላትነትን ለመመከት የተሰለፋችሁ ሁሉ፥ ኢትዮጵያን ለማፍረስ እየደከማችሁ ያላችሁ ሁሉ፥

በጥቅሉ የኢትዮጵያ ጠላት የሆናችሁ ሁሉ፥ በመሰላችሁ መንገድ መፍትሔ ለማምጣት የምትሮጡ ሁሉ


#በግድም_በውድም
#ለኢትዮጵያ_የዓለም_ብርሃናዊ_መንግሥት_ትንበረከካላችሁ። ለመትረፍም ትለምናላችሁ!

ይህ ከላይ ያያችሁትን ሁሉ የእግዚአብሔር ትእዛዝ ለማስፈጸም፥ በተለይ የከበረው መልአክ ሊቀ መላእክት #ቅዱስ_ገብርኤል ከነሠራዊቱ ከዚህ ደብዳቤና ከሌሎቹም 6 ዓይነት ደብዳቤዎች ጋር ለአፈጻጸሙ ተነቃንቋል።

በተጨማሪም ሁሉም ሊቃነ መላእክት ከነሠራዊታቸው የተሰጣቸውን አምላካዊ ትእዛዝ ለመፈጸም ተነቃንቀዋል። የሰው ዘር በሙሉ ከዚህ በሗላ ታየዋለህ። ውጤቱንም በግብር በዓይንህ ታየዋለህ።

ይህን ደብዳቤ፥ ያየኸውም ያላየኸውም፣ በስሚም የሰማኸውም፣ ፍጹምም ያላደመጥከውም
በነዚህ ምግባርህ ሳቢያ ከፍርድ የሚያስጥልህ አይደለም! ይልቅስ ፍርዱ ባንተው ላይ የሚበረታ ሆኖ ይደመድምሃል።

በስተመጨረሻ ልታውቁት የሚገባው እንደቀደመው ድርጊታችሁ አሁንም በትዕቢታችሁ፣ በንቀታችሁ
የምትገፉ ከሆነ፥ መልካም ነው #ለውጤቱ_ተዘጋጁበት። ደብዳቤውን ጊዜ ወስዳችሁ ስለተመለከታችሁት እናመሰግናለን።

በስተመጨረሻም እዚህ ሰዓት ላደረሰን ቸሩ አምላካችን #የአብርሃሙ_ሥላሴ፣ እንዲሁም ድንግል እናታችን ቅድስተ ቅዱሳን፥ በሰማይም ንግሥት በምድርም ንግሥት ለሆነችው እመቤታችን ማርያም ምስጋና እንደማያቋርጥ ጅረት ይፍሰስላቸው! አሜን።

— የሥላሴና የድንግል አገልጋይና ባርያ፥
#ከሥላሴ መክበሪያና መመስገኛ፥ ከርስተ ድንግል ቅድስት አገር #ኢትዮጵያ

📍ብርሃናተ ዓለም የኢትዮጵያ ብርሃናዊ መንግሥት፥ የመንግሥት ምክር ቤት ዋና ሰብሳቢ፨

ጥር 7 2016 ዓ.ም ከወጣ ደብዳቤ የተወሰደ፨
🟢🟡🔴
የካቲት 8 | #መድኃኔዓለም ከከበረ ልደቱ ከአርባ ቀኖች በኋላ ወደቤተ መቅደስ የገባበት በዓል ነው፨

እዚያም ጻድቁ ስምዖን አገኛቸውና ሕፃኑን ታቅፎ አመሰገነ። የጥንት ታሪኩም፦

ይህም ስሞዖን ይተረጒም ዘንድ የነቢዩ ኢሳይያስ መጽሐፍ ደረሰውና እነሆ ድንግል ትፀንሳለች ወንድ ልጅንም ትወልዳለች ስሙንም ዐማኑኤል ትለዋለች ከሚለው ደረሰ።

“ይሄስ እንደምን ይሆናል? ሴት እንጂ እንዴት ድንግል ይወልዳል?” ብሎ ተጠራጠረ።

ይህንንም ሲያስብ እንቅልፍ መጣበትና አንቀላፋ የእግዚአብሔርም መልአክ ተገልጦ “የተጠራጠርከውን ከድንግል የሚወለደውን እስከምታየውና እስከምትታቀፈው ሞትን አትቀምስም” አለው።

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እስከተወለደና በዚች ዕለት ወደ ቤተ መቅደስ እስከ አስገቡት ድረስ ስምዖን ሦስት መቶ ዓመት ኖረ።

ሕፃኑን ጌታችንንም በታቀፈው ጊዜ ታውረው የነበሩ ዓይኖቹ ተገለጡ። ሁለመናውም ሐዲስ ሆነ። መንፈስ ቅዱስም የምትጠብቀው የነበረ ሕፃን ይህ ነው ብሎ ነግሮታልና።


እግዚአብሔርንም አመሰገነው። እንዲህም አለ፦
“ባርያህን በሰላም አሰናብተው። በአንተ ምክንያት በዚህ በኃላፊው ዓለም ሕይወት ታሥሬ ኑሬአለሁና እነሆ አሁን መጥተህ አየሁህ። ወደ ዘላለም ሕይወት እሔድ ዘንድ አሰናብተኝ። ዓይኖቼ ትድግናህን አይተዋልና። በወገኖችህ ሁሉ ፊት ያዘጋጀኸውን ለአሕዛብ ብርሃንን ለወገኖችህ እስራኤልም ክብርን ትገልጥ ዘንድ።”

እመቤታችንን እናቱ ድንግል ማርያምንም እንዲህ አላት ይህ ልጅሽ ከእስራኤል ውስጥ ለብዙዎች ለመውደቃቸውና ለመነሣታቸው በሚፈረድባቸውም ገንዘብ ለምልክት የተዘጋጀ ነው።

ዳግመኛም በመከራው ጊዜ በልቧ የሚያድርባትን ኅዘን አስረዳት። እንዲህም አላት። "በአንቺ ግን በልብሽ የሚከፋፍል ፍላፃ ይገባል" ከዚህም በኋላ በሰላም አረፈ።

#ቅድስት_ሐና ነቢይትም መታሰቢያዋ ነው።
🍀
🌹
#የካቲት_8 የሚነበብ
#ተአምረ_ማርያም


ልመናዋ ክብሯዋ በእኛ ለዘለዓለም በእውነት ይደርብንና አምላክን የወለደች በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናች የክብርት እመቤታችን ያደረገችው ተዓምር ይህ ነው።

ከዕለታት ባንድ ቀን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እናቱን “በእኔ ምክንያት ካገኙሽ ኃዘኖች ማናቸው ኃዘን ይበልጣልን” አላት።

እመቤታችንም “ፈጣሪዬ ጌታዬ ሆይ፥ በእኔ ዘንድ እኚህ አምስቱ ኃዘኖች ይበልጣሉ” አለችው።

1. ከአምስቱ አንዱ አይሁድ እንዲገድሉህ በቤተ መቅደስ #ስምዖን ትንቢት በተናገረ ጊዜ ነው። (ዛሬ) (ሉቃ 2፥35)

2. ሁለተኛውም ሦስት ቀን በቤተመቅደስ ፈልጌህ ባጣሁህ ጊዜ ነው። (ሉቃ 2፥42)

3. ሦስተኛውም እግርህንና እጅህን አሥረው በጲላጦስ አደባባይ የገረፉህን ግርፋት ባሰብኩ ጊዜ ነው። (ዮሐ 19፥1)

4. አራተኛውም በዕለተ ዓርብ ራቁትህን ቸንክረው በሁለት ወንበዴዎች መካከል እንደሰቀሉህ ባሰብኩ ጊዜ ነው አለችው። (ዮሐ 19፥18)

5. አምስተኛውም ወደ ሐዲስ መቃብር ውስጥ እንዳወረዱ ባሰብኩ ጊዜ ነው። (ዮሐ 19፥41)

ጌታችንም እናቱን ድንግል ማርያምን ❝በእኔ ምክንያት ያገኙሽን እኒህን ኃዘኖችና መከራዎች በሰላመ ገብርኤልና አቡነ ዘበሰማያትን እየደገመ ያሰበውን ኃጢአቱን እኔ አስተሰርይለታለሁ፡፡ መንግሥተ ሰማያትንም አወርሰዋለሁ❞ አላት፡፡

❝ እናቴ ሆይ ከሞቱ አስቀድሞ በሦስተኛው ቀን ካንቺ ጋር መጥቼ እገለጽለታለሁ ❞

ይህን ሲናገር #ቅዱስ_ደቅስዮስ ሰምቶ ምእመናን ያነቧት ዘንድ በእመቤታችን ተዓምር መጽሐፍ ውስጥ ጻፈው፡፡

ልመናዋ ክብሯዋ የልጇ ቸርነት በእኛ ለዘለዓለም በእውነት ይደርብን።
🌹

T.me/Ewnet1Nat
አስተውለን ይሆን

📌 ይህችን ቀን ለንስሐ እና ለሥራ ማግኘት መታደል መሆኑን አስተውለን ይሆን?

📌 መርጦ የጠራቸውን፥ እስኪቃ˙ኑ ድረስ በፍቅር አስተምሮ ካልተለወጡ በግሣጼ እንደሚጎበኛቸው አስተውለን ይሆን?

📌 የእግዚአብሔር ዳኝነቱ በየግላችን ሚዛን እንደሚለካ አስተውለን ይሆን?

📌 ለግል ይሁን ለጋራ ጉዳይ የፍትሕ መዘግየት ምክንያቱ አለመመለሳችን መሆኑን አስተውለን ይሆን?

📌 በትምክህት ውስጥ ሽንፈት፣ በትሕትና እና በእምነት ደግሞ ድል እንዳለ አስተውለን ይሆን?

📌 ማስተዋል እና ጥበብ እጅግ እንደሚያስፈልጉ አስተውለን ይሆን?

📌 ቃልኪዳኑ ሞገስ፣ ምሕረቱ ነፃ አውጪ እንደሆነ ከልብ አስተውለን ይሆን?

📌 በየትኛውም ጊዜ፣ ዘመንና ሰዓት፣ ምክንያት ሳያበጅ፣ ለአፍታም የማይለየን የፈጠረን አምላክ እግዚአብሔር ብቻ እንደሆነ አስተውለን ይሆን?

"በእግዚአብሔር ዘንድ ጥበብና ኃይል አለ። ለእርሱ ምክርና ማስተዋል አለው።”
             ኢ
ዮብ 12፥13

አቤቱ ማስተዋል እና ጥበብ ስጠን!

©️ገኒ ታደሰ
2024/11/16 07:27:28
Back to Top
HTML Embed Code: