Telegram Web Link
Audio
ገድለ አቡነ ብፁዐ አምላክ የቅዳሜ
Audio
ገድለ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ የቅዳሜ
🟢🟡🔴
የካቲት 10 | #ሐዋርያው_ያዕቆብ ወልደ እልፍዮስ ዐረፈ።

አባቱ እልፍዮስ ወይም ቀለዮጳ ይባላል። እናቱ ማርያም ትባላለች። ከ12ቱ ሐዋርያት አንዱ ሲሆን በቅዱስ ወንጌል ላይ በአብዛኛው የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብ እየተባለ ተጠርቷል። (ማቴ 10፥3፣ ማር 3፥17፣ ሉቃ 6፥15፣ ሐዋ 1፥13)

በሌላም በኩል ከታላቁ ያዕቆብ (ከዮሐንስ ፍቁረ እግዚእ ወንድም) ከዘብድዮስ ልጅ ለመለየት ሲባል ታናሹ ያዕቆብ እየተባለ ተጠርቷል። (ማር 5፥40)

የእመቤታችን እኅት (ዘመድ) የቀለዮጳ ሚስት ማርያም ልጅ በመሆኑ ‹‹የጌታ ወንድም›› ተብሏል። (ማቴ 13፥55፣ ማር 6፥3፣ ገላ 1፥19)

ሐዋርያው ያዕቆብ ወልደ እልፍዮስ ብዙ ሀገራት ላይ ዞሮ ወንጌልን ካስተማረና ብዙዎችን ካጠመቀ በኋላ ተመልሶ ወደ ኢየሩሳሌም ገብቶ በምኩራባቸው አስተማረ፡፡

ክፉዎች አይሁድም ‹‹ደሙ በእኛ ላይ ይሁን›› ብለው ከመካከላቸው አውጥተው ወስደው ለሮማው ንጉሥ ለቄሳር እንደራሴ ለሆነው ለንጉሥ ቀላውዴዎስ አቅርበውት ‹‹ይህ ሰው ስለ ቄሳር ሳይሆን ስለ ሌላ ንጉሥ ይሰብካል›› ብለው ወነጀሉት፡፡ ንጉሡም ይህን ሲሰማ በድንጋይ ወግረው እንዲገድሉት አዘዘ፡፡

ክፉዎች አይሁድም ፈጥነው ወስደው በድንጋይ ወግረው ገደሉትና ሰማዕትነቱን በዚህች ዕለት የካቲት 10 ቀን በድል ፈጸመ፡፡

የሐዋርያው የቅዱስ ያዕቆብ ረድኤት በረከቱ ይደርብን በጸሎቱ ይማረን!

T.me/Ewnet1Nat
አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ
#የካቲት_12
🟢🟡🔴
የካቲት 12 | የመላእክት ሁሉ አለቃ #ቅዱስ_ሚካኤል መስፍኑ ሶምሶንን የረዳበት በዓል ነው፨

የከበረ ሚካኤልን እግዚአብሔር ወደ ረዓይታዊ ወደ ሶምሶን ላከው። የፍልስጥዔም ሰዎች ሊገድሉት በጠላትነት በተነሡበት ጊዜ ድል እስከ አደረጋቸውና እስከ ገደላቸው ድረስ ረዳው።

ኃይልንም ሰጥቶ በአህያ መንጋጋ ከእርሳቸው አንድ ሺህ ሰዎችን ገደለ።

ተጠምቶም ለሞት በተቃረበ ጊዜ የመላእክት አለቃ ሚካኤል ተገለጠለትና አጸናው። እግዚአብሔር ከአህያ መንጋጋ አጥንት ውኃን አፈለቀለትና ጠጥቶ ዳነ።

ዳግመኛም ከሚስቱ ጋር ተስማምተው ዐይኖቹን አሳወሩ። የራሱንም ጠጉር ላጩ። አሠሩትም ከዚህም በኋላ ለጣዖቶቻቸው በዓልን በአዘጋጁ ጊዜ ሶምሶንን ወደ ጣዖቶቻቸው ቤት ወሰዱት። በዚያም ሦስት ሽህ ያህል ሰዎች ተሰብስበው ነበር።

የከበረ ሚካኤልም ተገለጠለትና ኃይልን መላው። የዚያንም ቤት ምሰሶዎች ነቀላቸው። ቤቱም በላያቸው ወድቆ ከእርሱ ጋር ሁሉንም ገደላቸው።
🍀🍀

ዳግመኛም በዚህች ቀን ታላቁ አባት #አቡነ_ሠርፀ_ጴጥሮስ ዐረፉ።

የትውልድ አገራቸው ሸዋ ደብረ ጽላልሽ ሲሆን በሕፃንነታቸው ወደ ወሎ ሄደው ሐይቅ እስጢፋኖስ ገብተው ብዙ ተጋድለዋል፡፡ከተጋድሎአቸውም በኋላ በአቡነ ኢየሱስ ሞዐ እጅ መነኰሱ፡፡

በገዳሙ ብዙ ካገለገሉ በኋላ በመልአክ ትእዛዝ ወደ ጎጃም ሲሄዱ ዓባይን የተሻገሩት አጽፋቸውን አንጥፈው እርሱን እንደ ጀልባ ተጠቅመው ነው፡፡

ጻድቁ ታላቋን ተድባበ ማርያምን ለ41 ዓመታት አጥነዋል፡፡  የንጉሡ ልጅ ሞቶ ሊቀብሩት ሲወስዱት የአቡነ ሠርጸ፡ጴጥሮስ ጥላቸው ቢያርፍበት ከሞት አፈፍ ብሎ ተነሥቶ ድኖ "አምላከ አቡነ ሠርጸ ጴጥሮስ" ብሎ ፈጣሪውን አመስግኗል፡፡

ጻድቁ ሲያርፉም መቋሚያቸው አፍ አውጥታ ተናግራለች፤ ርዕደተ መቃብራቸው ሲፈጸምም እንባ አፍስሳ አልቅሳላቸዋለች፡፡

ይህቺ ተአምረኛ መቋሚያቸው ዛሬም ጎጃም ውስጥ መካነ መቃብራቸው ባለበት በደብረ ወርቅ ገዳም ትገኛለች፡፡ ጻድቁ ደብረ ወርቅ ገዳምን እንደ መሶብ አንሥተው አስባርከዋታል፡፡

አቡነ ሠርፀ ጴጥሮስ የካቲት 12 ቀን ያረፉ ሲሆን ዐፅማቸውም በታላቋ ደብረ ወርቅ ይገኛል፡፡ ከሰማይ የወረደላቸው የወርቅ መስቀላቸውም በዚያው ይገኛል።
🍀🍀

#ቅዱስ_ጴጥሮስ ከሞት ያስነሣት #ቅድስት_ጣቢታ መታሰቢያዋ ነው። (ሐዋ 9፥36)

#ዓፄ_ዮስጦስ ዕረፍታቸው ነው። (ከ1703-1708 ዓ.ም)

👑 ልደታ ለማርያምን ያነጹ፣
👑 የፍልሠታን አድርሽኝ ያስጀመሩ፣ ብዙ ሊቃውንትን ያፈሩ፣

👑 እመቤታችንም ተገልጻ ቃል ኪዳን የገባችላቸው ደግ የኢትዮጵያ ንጉሥ ናቸው።

www.tg-me.com/Ewnet1Nat
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
📯 አይ ወራዳው ቤተ ምክነት! ይህ ሰው የብዙኃኑን ጓዶቹ አስተሳሰብና የልቦና ሀሳብ ፡ የጓዳ ምስጢር ነው ሳያፍር ይፋ ያደረገው።
#ሲኖዶሳችሁም ከዚህ ሰውየ የተለየ አስተሳሰብ የለውም !!
#ለታሪክ_ትቀመጥ !!

የካቲት / 2016 ዓ.ም

www.tg-me.com/Ewnet1Nat
" እንግዲህ ፍጹማን የሆንን ሁላችን ይህን እናስብ ፤ በአንዳች ነገርም ልዩ አሳብ ቢኖራችሁ እግዚአብሔር ይህን ደግሞ ይገልጥላችኋል ፤ ሆኖም በደረስንበት በዚያ እንመላለስ ። ወንድሞች ሆይ ፥ እኔን የምትመስሉ ሁኑ ፥ እኛም እንደ ምሳሌ እንደምንሆንላችሁ ፥ እንዲሁ የሚመላለሱትን ተመልከቱ ። ብዙዎች ለክርስቶስ መስቀል ጠላቶቹ ሆነው ይመላለሳሉና ፤ ብዙ ጊዜ ስለ እነርሱ አልኋችሁ፥ አሁንም እንኳን እያለቀስሁ እላለሁ ። መጨረሻቸው ጥፋት ነው ፥ ሆዳቸው አምላካቸው ነው ፥ ክብራቸው በነውራቸው ነው፥ አሳባቸው ምድራዊ ነው ። እኛ አገራችን በሰማይና ነውና ፥ ከዚያም ደግሞ የሚመጣ መድኃኒትን እርሱንም ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን እንጠባበቃለን ፤ እርሱም ሀሉን እንኳ ለራሱ ሊያስገዛ እንደሚችልበት አሠራር ክብር ሥጋውን እንዲመስል የተዋረደውን ሥጋችንን ይለውጣል።»                 ፊል 3:15
ስውሩ መንግሥት (ቤተ ክህደቱ) በተጠናከረ መልኩ ስራውን እየሰራ ይገኛል ። ማንም አልነቃበትም ከኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ቤተሰቦች ውጭ ማንም የጥፋት አካሄዱን አላወቀበትም ። አገር እያጠፋ እምነት እያጠፋ እያለ የፋኖውም ባራኪ የብልግናውም ባራኪ (በሁለት ቢላ የሚበላ) ሆኗል ። በኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መግለጫ (በቅርቡ ለፋኖ በተላለፈው የመፋረጃ መግለጫ) ላይ ስለ ስውሩ መንግሥት ምንነትና ክፋት ተገልጦ ተብራርቶ ተነግሮን ነበር። ሰሚ የለም እንጂ!! ልብ ያለው ልብ ይበል!! በእግር የተከሰተ ቁስል ተሎ ታክሞ ካልዳነ ወይም የመዳን ተስፋ ከሌለው ጋንግሪን ይሆንና ለእግር መቆረጥ ውሳኔ ያደርሳል ። ቤተክህደቱ እንደ አጠቃላይ መዋቅር እግዚአብሔርን ፍጹም በአደባባይ ወጥቶ በግልጽ ከካደ ድፍን 30 ዓመታት አልፈዋል ። የቀረው መቆረጡ ብቻ ነው። እሱም ደርሶለታል!!!!

👑 ሙሉውን የአባቶች መግለጫ ያላዳመጣችሁት
https://www.tg-me.com/AlphaOmega930/95564 በዚህ ማዳመጥ ትችላላችሁ ።
. ✧†✧
በጸበል ብቻ ጣልያናዊን ያሸነፉ ኢትዮጵያዊ አባት

የካቲት 12 በስፋት የሚታወቀው ፋሺስት ጣልያን በ1929 ዓ.ም ኢትዮጵያውያን ላይ ያደረገችው ጭካኔ የተሞላው ጥቃት ነው። በ3 ቀናት ውስጥ 30,000 ኢትዮጵያውያንን በእምነታቸው እና በሀገር ወዳድነታቸው ጣልያን በአካፋና ዶማ፣ በእሳት ገድላቸዋለች።

እኚህ ኢትዮጵያዊ ግን ጦር ሳያነሡ በፍጹም ፍቅር አንድ ጣልያናዊን በጸበል ብቻ ክርስቲያን አድርገዋል። እኚህ አባት #ቅዱስ_ሠርፀ_ጴጥሮስ ይባላሉ።

በአንድ ወቅት እጅግ ፈዋሽ፣ ጨዋማ እና ለመዋጥ ከበድ የሚል የሆነውን የአቡነ ሠርፀ ጴጥሮስን ጸበል በተገዳደረ በአንድ ጣሊያናዊ ዶ/ር ላይ ይህ ተአምራት ተፈጸመ፦

ጣልያናዊው ዶ/ር ማዛሊ ይባላሉ፡፡ በደብረ ማርቆስ ‹ሆስፒታል› የውስጥ ደዌ ‹ስፔሻሊስት› ሆነው በመሥራት ላይ ነበሩ። ሐኪሙ ብዙ ምእመናን የአቡነ ሠርፀ ጴጥሮስን ጠበል እየጠጡ ፈውስ እንደሚያገኙ ሲሰሙ ሁኔታውን ለመታዘብ ወደ ደብረ ወርቅ መጡ።

እንደተነገራቸውም ቁጥራቸው በጣም ብዙ የሆኑ ምእመናን እጅግ ፈዋሹን የአቡነ ሠርፀ ጴጥሮስን ጠበል ሲጠመቁና ሲጠጡ ያያሉ። በዚህም ጊዜ ‹‹…አሁን የእውነት ውኃ ሊያድናቸው ነው ወይ!?›› በማለት ማናናቅና መሳለቅ ጀመሩ፡፡

ምግብም ከበሉ በኋላ ‹‹…ደግሞ ከምድር የሚፈልቅ ይህ ውኃ ምን ያደርገኛል?›› በማለት በድፍረት ጸበሉን ጠጡ። ነገር ግን አፍታም ሳይቆዩ ወዲያው ሆዳቸው በጣም ተነፍቶ መናገርና መተንፈስ አቃታቸው። አቡነ ሠርፀ ጴጥሮስ በዶክተሩ ላይ ኃይላቸውን ገለጡ።

ከዚህም በኋላ የገዳሙ አባቶች ተጠርተው በጻድቁ ስም ጸሎትና ምሕላ አድርገውላቸው ለጻድቁ ከሰማይ በወረደላቸው በወርቅ መስቀል ዶክተሩን ቢባርኳቸው ወዲያው በትውኪያ ወጣላቸውና ፈጥነው ዳኑ።

ከዚህም በኋላ ዶ/ር ማዛሊ በአምላከ አቡነ ሠርፀ ጴጥሮስ አምነው ተጠምቀው ሔደዋል።
๏◦๏◦๏

በዛሬዋ ዕለት የካቲት 12 ቀን በዓመታዊ የዕረፍት በዓላቸው ታስበው የሚውሉት አቡነ ሠርፀ ጴጥሮስ ወደ ጎጃም ሲሄዱ አጽፋቸውን አንጥፈው ዓባይን የተሻገሩ፣ ደብረ ወርቅን እንደ መሶብ አንስተው ያስባረኩ፣ የንጉሡ ልጅ ሞቶ ሊቀበር ሲሄድ በጥላቸው ከሞት ያስነሡ ታላቅ ኢትዮጵያዊ ጻድቅ ናቸው፡፡
🍀🍀
http://www.tg-me.com/Ewnet1Nat
ላኦስ.pdf
12.3 MB
ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃናዊ መንግሥት ደብዳቤ
ለ ላኦስ መንግሥት

7/5/2016 ዓ.ም
ሰሜን ሱዳን.pdf
19.2 MB
ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃናዊ መንግሥት ደብዳቤ
ለ ሰሜን ሱዳን መንግሥት

7/5/2016 ዓ.ም
ትሪኒዳድ እና ቶቤጎ.pdf
12.3 MB
ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃናዊ መንግሥት ደብዳቤ
ለ ትሪኒዳድ እና ቶቤጎ መንግሥት

7/5/2016 ዓ.ም
ኢንዶኔዢያ.pdf
19.3 MB
ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃናዊ መንግሥት ደብዳቤ
ለ ኢንዶኔዢያ መንግሥት

7/5/2016 ዓ.ም
2024/11/16 09:52:26
Back to Top
HTML Embed Code: