Telegram Web Link
🟢🟡🔴
ታኅሣሥ 23 | ዕረፍቱ #ለቅዱስ_ዳዊት_ልበ አምላክ፨

ቅዱስ መጽሐፍ እንዲህ ይላል፦ "እግዚአብሔር ለዳዊት በእውነት ማለ፤ አይጸጸትም።" (መዝ. 131፥11) አሁን በእግዚአብሔር መጸጸት ኑሮበት አይደለም። ቅዱስ ዳዊት የማያጸጽት ፍጹም ወዳጅ መሆኑን ሲገልጥ ነው እንጂ። ጌታ ቅዱስ ዳዊትን "እንደ ልቤ የሆነ፣ ፈቃዴን የሚፈጽም፣ ባሪያየን ዳዊትን አገኘሁት" (መዝ. 88፥20) እንዳለው።

👑 ክብረ ዳዊት 👑

እግዚአብሔር ስለ ዳዊት ሲል ኢየሩሳሌምን ብዙ ጊዜ ታድጓል። ሰሎሞንና ሕዝቅያስን (ነገሥታቱን) ይቅር ያላቸው ስለ ባለሟሉ ስለ ዳዊት ነው። የሐዲስ ኪዳን የመጀመሪያዋ ቃል "የዳዊት ልጅ . . . " የምትል ናት። (ማቴ. 1፥1) ጌታችን "ወልደ ዳዊት" መባልን ወዷልና። እንዲያውም ራሱ "እኔ የእሴይ ሥርና የዳዊት ዘር ነኝ" ሲል ተናግሯል። (ራዕ. 22፥16)

👑 ዕረፍት 👑

ነቢየ ጽድቅ፣ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት እሥራኤልን ለ40 ዓመታት መርቶ አረጀ። 'ምነው ያ ኃያል የእግዚአብሔር ሰው ቶሎ አረጀ?' ቢሉ ከገድሉ ጽናት ሰውነቱ ተቀጥቅጦ ነበርና።

በዚህ ጊዜም ልጁን ሰሎሞንን አንግሦ በ70 ዓመቱ ከክርስቶስ ልደት ሺህ ዓመት በፊት በታኅሣሥ 23 ቀን ዐርፏል።

👑 ዳዊት በሰማይ 👑

🍀 በራዕየ ጎርጎርዮስ እንደ ተጻፈው ቅዱስ ዳዊትን በሰማይ 99ኙ ነገደ መላእክት ከበውት ያመሰግናል። ከርሱ ዝማሬ ግርማ የተነሣ የሰማያት ግዘፋቸው ይናወጻል።

🍀 በገድለ አቡነ ኪሮስ እንደ ተጻፈው ደግሞ ቅዱሳን ነፍሳቸው ከሥጋቸው የምትለየው በዳዊት በገና ጣዕመ ዝማሬ ነው።

🍀 በነገረ ማርያም ትምህርት ደግሞ የቅዱስ ዳዊት ቤቱ ከልዑል አምላክ መንበር ሥር ነው።

አምላከ ዳዊት ስለ ከበረው ቃል ኪዳኑ ይማረን። ከንጹሕ አምልኮው ይክፈለን። በዝቶ ከተረፈ በረከቱም አይለየን።

T.me/Ewnet1Nat
🟢🟡🔴
ዋኖቻችንን እንወቅ - ክፍል ስድስት (6)

(📌 ክፍል 1ን ለማንበብ 👈)
(📌 ክፍል 2ን ለማንበብ 👈)
(📌 ክፍል 3ን ለማንበብ 👈)
(📌 ክፍል 4ን ለማንበብ 👈)
(📌 ክፍል 5ን ለማንበብ 👈)

📌 የኢትዮጵያ ብርሃን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ማን ናቸው?

በዓሎቻቸው፦
🍀 መጋቢት 24 ቀን 1196 ዓ.ም ፅንሰታቸው፣

🍀 ታኅሣሥ 24 ቀን 1197 ዓ.ም ልደታቸው፣

🍀 ጥር 4 ቀን 1289 ዓ.ም ደግሞ በጸሎት ብዛት አንድ እግራቸው የተሰበረበት ነው። ነገር ግን የዕረፍታቸውን ቀን ይዞ በዚሁ በጥር ወር በ24 ከመነኮሱበት በዓላቸው ጋር አብሮ ይከበራል።

🍀 ኅዳር 24 ቀን ከ24ቱ ካህናተ ሰማይ ጋር በሕይወተ ሥጋ እያሉ የሥላሴን መንበር ያጠኑበት ነው፡፡

🍀 ነሐሴ 24 ቀን 1296 ዓ.ም ዕረፍታቸው ነው፤

🍀 ግንቦት 12 ቀን 1353 ዓ.ም ፍልሰተ ዐፅማቸው ነው፡፡

🍀 ሕይወትና ተጋድሎ
🌼 ልዩ ክብራቸው
🌺 ታላቅ ቃልኪዳናቸው

አጭር ዜና ሕይወታቸውን እና ትሩፋታቸውን ለማንበብ👇

📌 https://telegra.ph/የኢትዮጵያ-ብርሃን-አቡነ-ተክለ-ሃይማኖት-12-31

ልዩ ክብራቸውንና ቃልኪዳናቸውን ለማንበብ 👇

📌 https://telegra.ph/ክብር-01-01
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በአዋሽ ፈንታሌ በመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ወደ አጎራባች ስፍራዎች እየሸሹ መሆኑ ተገለጸ

#አፋር ክልል አዋሽ ፈንታሌ ከሰሞኑን በተደጋጋሚ በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ በርካታ ሰዎች አከባቢያቸውን ለቀው አጎራባች ወደሆኑ ስፍራዎች እየሸሹ መሆናቸውን ነዋሪዎች ለአዲስ ስታንዳርድ ገለጹ።

የአካባቢው ነዋሪ በመሬት መንቀጥቀጡ ምክንያት አስፋልት ሲሰነጠቅ ማየታቸውን ገልጸው አሁን ላይ ስንጣቂው እየሰፋ መምጣቱን እና ከሰዎች መኖሪያ ቤት ውስጥ ሳይቀር ውሃ ሲፈልቅ ማየታቸውን ጠቁመዋል። በተለይም በአርብሃራ እና ቦሊቃ መካከል የተሰነጠቀው አስፋልት ጥልቀቱ በጣም ትልቅ መሆኑ ገለጿል።

የአዋሻ ፈንታሌ ዋና አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ አደን በለአ በበኩላቸው የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቱ በአዋሽ ፈንታሌ ወረዳ ሳቡሬ ቀበሌ የሚገኘው የኡንጋይቱ መጀመርያ ደረጃ ት/ቤት ላይ ጉዳት መድረሱንና ትምህርት መቋረጡን አረጋግጠዋል። በተጨማሪም በዱሃ ቀበሌ የሚገኝ መስጂድ ላይ መሰነጣጠቅ አጋጥሟል ብለዋል።
📌 በምንም ነገር በሚከናወነው ሁሉ አትረበሹ፡፡ ሊሄድ የሚገባው ይሄዳል፡፡ ሊፈርስ የሚገባው ይፈርሳል፡፡ ሊወድቅ የሚገባው ይወድቃል፡፡ የሚቆመው ደግሞ ይቆማል እሱ የተከለው እንደተተከለ ነው ማንም አይነካውም፡፡ ምንም አይሆንም ፡፡ ከእግዚአብሔር ፈቃድ ውጪ የሚከናወን ነገር የለም በአሁኑ ጊዜ ፡፡

ሁሉም እግዚአብሔር የመደበለትን ሩጫ ሮጦ ሲያበቃ  ያበቃል በቃ፡፡ ለጥፋት የተሰማራውም መንግስት ይሄው  እንደምታዩት ለጥፋት ተሰማርቶ የለም !!ከነምኑ ከነምኑም በቃ የዛች  የተሰጠችውን ሩጫ ሄዶ ሲጨርስ ይቆማል፡ እጣው ነው እጣውን ይቀበላል፡፡

⚡️ ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን
የሉቃስ ወንጌል ትምህርት ክፍል -9-  ላይ የተወሰደ፡፡
#Earthquake

ዛሬ ሀሙስ ቀን ላይ ከተመዘገበው በሬክተር ስኬል 5.1 በኃላም 4.5 የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተት በኃላ በተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተት ተመዝግቧል።

እንደ አሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ መረጀ ከቀድሙ በኃላ በሬክተር ስኬል 4.5 ፣ በድጋሚ 4.5 ከዛ 4.6 ከዛም 4.9 ተመዝግቧል።

ከ5.1 በኃላ የተመዘገበው ከፍተኛው የመሬት መንቀጥቀጥ 4.9 ነው።

ሁሉም ቦታቸው ከአዋሽ የተወሰኑ ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ ነው።

ንዝረቱ በአዲስ አበባና ሌሎች ከተሞችም ተሰምቷል።
"ሸዋ አሸዋ የምትሆንበት ቀን ሲደርስ ያኔ ምድር ትንቀጠቀጣለች ❗️"

አሁን ከመሸ  2:29 አፋር ክልል አዋሽ አካባቢ በሬክተር ስኬል 5 ነጥብ 1 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን የጀርመን ጅዖ ሳይንስ የምርምር ማዕከል አስታውቋል። ንዝረቱ አዲስ አበባ ድረስ እንደተሰማ ነዋሪዎች ገልፀዋል‼️
📌 ሁሉም ነገር ማብቂያ ስላለው እግዚአብሔር እያጣደፈው ነው።
እያፈጠነው ነው ፍርዱንም እያሯሯጠው ነው የመጣው አሁን
በአጭር ጊዜ ሩቅ ሳንሄድ በአጭር ጊዜ ሁሉም ወደ ብርሃን ይወጣል
የእኛም ምንነት ወደ ብርሃን ይወጣል እግዚአብሔር ማንን እንደሚወድ ማንን እንደሰማ ከማን ጋር እንደ ቆመ ልክ እንደኤልያስ ከማን ጋር እንደ ቆመ ወደ ፊት የምናየው ይሆናል።
ስለዚህ ጽኑ በርቱ ተጽናኑ አትደነቁ በሚሆነው ነገር ሁሉ አትደነቁ ምንም ሥፍራ አትስጡት ይሆን ዘንድ ግድ ነው ይሆናል በቃ!!
⚡️ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን
ተዋሕዶ ኦርቶዶክስ ማን ናት ?
ከሚለው ትምህርት ክፍል _2  -መጨረሻ  መዝጊያው ላይ የተወሰደ።
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#USA

በአሜሪካ ሀገር በደቡባዊ ካሊፎርኒያ አንድ አነስተኛ አውሮፕላን ተከስክሶ ሁለት ሰዎች መሞታቸው ተነግሯል።

19 ሰዎችም ተጎድተዋል።

አውሮፕላኑ የተከሰከሰው ፉለርተን በተሰኘ ከተማ በአንድ የፈርኒቸር ውጤቶች ማምረቻ ህንጻ አናት ላይ ነው።

በህንጻው ውስጥ 200 የሚደርሱ ሰራተኞች ስራ ላይ ነበሩም ተብሏል።
አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ
Photo
👆👆👆👆👆👆
500 ኪ.ግ ሊሆን  የሚመዝን የጋለ ብረት #ከሰማይ መውደቁ ተነገረ‼️

በአጎራባቿ ኬንያ 500 ኪሎ ግራም ሊመዝን የሚችል ብረት ከሰማይ ወድቋል ነው የተባለው።

ቀለበታማ ብረቱ የወደቀው ሙኩኩ በተሰኘች መንደር እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን ብረቱ የ2 ነጥብ 5 ሜትር ስፋት ወይም ዲያሜትር ያለው መሆኑ ተመላክቷል።

የኬንያ ስፔስ ኤጀንሲ ብረቱ በስፔስ ላይ ከሚገኙ ሮኬቶች ተገንጥሎ የወደቀ ሊሆን እንደሚችል አስታውቋል።
=======================

📌 አባቶቻችን ምን ብለውን ነበር ❗️

እስካሁን በተላለፈው የመጨረሻ ውሳኔ ሁላችሁም እንደምታውቁት በህዋ ላይ የዘመኑ የዲያብሎስ ልጆች እና መንግስት ብዙ ሳተላይት መሳሪያዎችን ሰቅለዋል ፡፡ እነዚህም የምድሩን የጥፋት ድግስ በመረጃ እና በአቅጣጫ አቀናባሪነት የሚያገለግሉ መረጃም የሚሰበስቡ አልፎም ጠለቅ ያለ ስለላም የሚከውኑ ከዚህም ዘልቆ አውዳሚ የኒውክለር አረሮችን የተሸከሙ ጨረርን እንደ ጦር መሳሪያ የሚገለገሉ በህዋ ውስጥ በሺዎች  በሚቆጠር ቁጥር እየተሸከረከሩ ይገኛሉ ፡፡ ከዚህም በላይ ቋሚ ስቴሽኖችም ተሰቅለዋል ፡፡ ለሰው ልጅ ምን ይጠቅማሉ የሚለውን መመዘኛ ሆኖ በእግዚአብሔር ዘንድ ተመዝነው ይጠረጉ ዘንድ የተወሰነባቸው ሁሉ እንዲጠፉ እንዲጠረጉ የሚደረጉ መሆኑን መላ የአዳም ዘር እነሱን የላከ አገር እና ሕዝብ ሁሉ እንዲያውቅ ይገባል ፡፡

ቀደም በተደጋጋሚ በተላለፉ መልዕክቶቻችን እንደገለጽነው ለሰው ልጅ የማይጠቅሙ በነፍሱም በስጋውም የሚጎዱ ሰው የሰራቸው ቁሶች ሁሉ በምድር እንዳሉ በህዋ ውስጥም ያሉትንም በእግዚአብሔር ፍርድ እንዲካተቱ ተወስኖባቸዋል ፡፡ ይህ ደግሞ ቀድም በመልዕክታቶቹ ውስጥ የተነገረ ነው ፡፡ በቅርቡ ለመላው ዓለም አገራት እና ሕዝባቸው በተላለፈ የመጨረሻ ቅድመ ሁኔታ አዘል ውሳኔ በየግላቸው በደረሳቸው ደብዳቤ ላይ ስለ ህዋ የተገለጸ ውሳኔ ያላካተተ በመሆኑ ውሳኔውም አሁን የደረሰን በመሆኑ ከላይ የገለጽንላችሁን በህዋ ውስጥ ስለሚርመሰመሱ ሳተላይቶች የተወሰነውን ለሁሉም አገራት ከተበተነው ደብዳቤ ጋር አባሪ አድርጋችሁ እንድታዩት እናሳስባለን ፡፡

⚡️ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃናዊ መንግስት መግለጫ ሚያዚያ-08-2016 ዓ.ም መግቢያ
2025/01/05 01:39:23
Back to Top
HTML Embed Code: