Telegram Web Link
Forwarded from 🃏𝙼𝚎𝚔𝚒🀄
የኛ ሰፈር....6





የማስታወቂያ ፎርሙን እንደነገሩ ካየ በኃላ ፀሀፊዋን አሰናበታት....
" የፅዳት እና ጥበቃ ቅጥር ማስታወቂያ ነው "....አለኝ ግንባሩ ላይ የተከማቸውን የላብ እንጥፍጣፊ በብጫቂ ጨርቅ ለማፅዳት እየሞከረ
"እቀጠራለሁ"....አልኩት ገና ሳይጠይቀኝ
"እ....እ..ማለት አንቺ ኮ የማርኬቲንግ ተመራቂ ነሽ"...አለኝ ደንግጦ
"ኧረ ነኝ እንዴ አላወኩም ነበር"...አልኩት በሹፈት
"ማለቴ ለማለት የፈለግኩት ገብቶሻል እኔ..." ላስጨርሰው አልፈለግኩም
"ገብቶኛል ገብቶኛል"....በጨርቅ የሞላሁት ቦርሳዬን አንጠለጠልኩና ከመቀመጫዬ ተነሳሁ...
"መቼ ነው የምጀምረው....?"ጠየቅኩ..
"እርግጠኛ ነሽ...?"
"አዎ"....አዎንታዬን ላይ የአንገቴን ንቅናቄ ጨመርኩበት....
"የሚመጣው ሰኞ"...አለኝ ከነድንጋጤው
"አመሰግናለሁ"ብዬ እጄን ዘረጋሁለት...መልስ ሳይሰጠኝ እጁን ብቻ ሰደደ...



በእርሱ ፊት እንዳይፈስ የገደብኩት እንባዬ ገና ከድርጅቱ ሳልወጣ 'በቃሽ' አለኝ....እየተጣደፍኩ ወጥቼ ካንዱ ጥግ አስነካሁት...


አልወጣልኝም............


"ምን ሆነሽ ነው ያለቀስሽው...?".....ቤቴ ስገባ አይኔ ተነርቶ ስለነበር እናቴ በቀላሉ ማልቀሴን አስተዋለች።


ምንም ሳይወጣኝ እቅፏ ውስጥ ተደበቅኩ...ከዚህ ሰሰቀናም አለም ለአፍታም ቢሆን ዘወር አልኩ......ከዛ ከቅድሙ የቀጠለ ለቅሶዬን አስነካውት...ለምን እንደሆነ ሳይገባት ስላነባሁ ብቻ ከእኔ ጋር ተደምራ አነባች...ምንም ሳናወራ ተላቀስን....



ቀኑ ሲደርስ ማልጄ የስራ ገበታዬ ላይ ተገኘሁ...ሌሎች ሰራተኞች ሳይገቡ ማፅዳት ያሉብኝን ክፍሎች አፀዳሁ...



ከቁርስ ሰአት በኃላ የሪል ስቴት ድርጅቱ በሰራተኞች ተሞላ...መቼስ አዲስ ስለሆነ ነው እንጂ እንዲህ በጠዋት አይመጡም ነበር አልኩ ለራሴ...ወይ እነርሱ አዲስ ስለሆኑ ይሆናል.....ደግሞስ ምን አገባኝ...ምን ያልበላኝን ያሳክከኛል......


"ፅዳት"...."ፅዳት የለም እንዴ"....እያለች ትጮሀለች....ጠዋት ላይ ያለ መጥረጊያዬ እና ሽርጤ ጠብ እርግፍ ብላ ሰላም ያለችኝ ወጣት....


"አንቺ ነሽ ፅዳቷ...?" አለችኝ በግርምት
"አዎ ጠራሽኝ..."
"አትመስይም"
"ፅዳት ሰራተኛ ምን መምሰል አለበት"...
"አላውቅም ግን ጠዋት ሰላም ስልሽ ፅዳት አልመሰልሽኝም ነበር"....
"ቆጭቶሽ ነው...?"...ገርማኝ ጠየኳት
"ኧረ በጭራሽ በጭራሽ"....
"እሺ አሁን ምን ልታዘዝ...?"
"ወረቀቶቹን ሰብስቢያቸውና ቅርጫት ውስጥ አርጊያቸው"...አለችኝ ሁለት ፍሬ ወረቀት ወደተጣለበት እየጠቆመች
"የምርሽን ነው...?"....አልኳት ሳላስበው ተኮሳትሬ...
"አዎ ምነው ስራሽ አይደል"....አለችኝ ራሷን እስኪያማት እየተገላመጠች
"አዎ ልክ ነሽ ይቅርታ"...ብዬ ያዘዘችኝን ታዝዤ ብወጣ ጥሩ ነበር...
"እንጨት ውጠሻል...?"...አልኳት ግልፍ ብሎብኝ.....
"አቤት"...አለችኝ የሰማችውን ባለማመን
"ለዚህ ነው የጠራሽኝ ቆይ ይሄን ወረቀት ስላነሳሽ ክብርሽ ይቀነሳል...?ለነገሩ ቀድሞውንም ክብር ሲኖር እኮ ነው የሚቀነሰው!!!"....ስሬ ተገታተረ....
" እ ምንድን ነው ያልሽው...?"አለችኝ ያልሰማች ይመስል
ቀጠለች "ድሮም እናንተ ፊት ሲሰጥዋቹ አትቻሉም"....አለችኝ ፊት ሞልቶ የየትረፈረፈላት ይመስል....እንኳን ለእኔ ትሰጠው ለራስዋም የማይበቃ ፊት ነው ያላት....



ይቀጥላል....




Shewit dorka



https://www.tg-me.com/ethioleboled
Forwarded from 🃏𝙼𝚎𝚔𝚒🀄
ለፈገግታ  (እኔ ሰላም አልፈልግም🙄)

🍩➠ እኔ ምልክ ዶናት ገዝተህ ስትሰጣት ቀዳዳ ነው መልስላቸው ያለችህ ፍቅረኛህ ደህና ናት ወይ?

⚽️➠ ባለፈዉ ሴኔጋልና ጃፓን ሲጫዉቱ ሴኔጋል የትኛዉ ነዉ ያልከኝ ልጅ ግን
ጤነኛ ነህ? 🤔 ይባስ ብሎ
ቲቪዉ "No Signal" ሲል አይተህ ዛሬ ሴኔጋል ጨዋታ የላትም ያልከዉ ልጅ
ግን የእንግሊዝኛ ቡዳዉ ለቀቀህ ወይ?

👨‍💼 አብይ ወደየ ብሔር ብሔረሰቡ እየሄደ የብሔረሰቡን ልብስ ሲለብስ አይተሽ "ምናለ ወደ ሐመር በሄደ" ያልሽዉ ልጅ ግን ጤነኛ ነሽ??
👱‍♂👱‍♂ "የኔ ቆንጆ ኑሪ" እና "የኔ ቢጫ ወባ" ብለህ የዘፈንከዉ ልጅ ግን ቤተ መንግስት ከአርቲስቶች እኩል አልተጠራንም ብላችሁ ያኮረፍከዉ የምርህን ነዉንዴ?

📜 English የሚለውን እንጃልሽ ብሎ ያነበበው ልጅ ተመረቀ እንዴ? 😁

🤕 የቀበሌ መታወቂያ ላይ በአደጋ ግዜ ተጠሪ ሲባል አምቡላንስ ያለውን
ልጅ ሰላም በሉልኝ 🤝🤝🤝

👀 "C" በአማርኛ አንደ "ጨ" ናት ብለው ነግረውህ "Coca cola" ን ጮጫ ጮላ ብለህ ያነበብከው ልጅ ግን ትውልድ ቢረሳህ እኔ አልረሳህም 👆

"Curriculum" የሚለውን ሠርካለም ብሎ ያነበበውን ልጅ ግን በስም
ማጥፋት ወንጀል መከሰስ የለበትም?

🐔ፈረንጅ ሀገር supermarket ዶሮ ለመግዛት ሄደሽ እንቁላል አንስተሽ
where is mother?ያልሺው ልጅ ኮርተንብሻል 😎

📱ስልክሽ battery full ሲል ማንኣባቱ ነው beautiful ያለሽ? ብሎ
ሲቀጠቅጥሽ ያደረው ባልሽ እንግሊዘኛ ለመደ ወይ ? 😁


❗️

Share ➠➠➠➠ https://www.tg-me.com/ethioleboled
Forwarded from 🃏𝙼𝚎𝚔𝚒🀄
ከበዓል ማግስት ... 🙄
(እኔ ሰላም አልፈልግም🤣🤣)

😴...በራስ ምታት የሚናዉዝ ጭንቅላት

😬...የጠነዛ ጉዝጓዝ እና ጠጀ ሳር

😣...ጠላ ያትረከረካቸዉ ብርጭቆዎች

☹️...ቡና የገገረበት ስኒ

🤧...ዝንብ የሚወረዉ ስጋ

🙄...ቅራሬ የያዘ ጆግ

😷...የተጋጠ አጥንት የተሸከመ
የጠረጴዛ ስር

😪.. አልኮል አልኮል እና ላት ላት የሚሸት ትንፋሽ

😵...ማሳ ለማሳ የሚልከሰከስ የቴሌቪዥን ዜና

😱....በበአል ወጭ የሳሳ ኪስ

🤨... የማዘር ንጭንጭ

🤪... የነ ሲስተር ፌስ

Https://www.tg-me.com/ethioleboled
Forwarded from 🃏𝙼𝚎𝚔𝚒🀄
በአውስትራሊያ ባህር ጠረፍ ተማሪዎቻቸውን ይዘው በአንድ ባህር ውስጥ የሚኖር አደጋ መርዛማ የእባብ ዝርያ ላይ የተግባር ገለፃ እያደረጉ ባሉበት ቅፅበት በርካታ ልምድ የነበራቸው ሀሮልድ በድንገት በእጃቸው የያዙት እባብ ይነድፋቸዋል።
በገዳይነቱ የሚታወቀው ይህ እባብ እንደነደፋቸውበአፋጣኝ ወደ ሆስፒታል መድረስ ያለባቸው ቢሆንም በባህር ጠረፍ ላይ በመሆናቸው ከሞት ጋር መጋፈጥ ግዴታ ሆነ....

📖ዝጎራ📖
ከአለማየሁ ዋሴ እሸቴ

share🖇 @ethioleboled
Forwarded from 🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁
የኛ ሰፈር.......7



"ቀን እስኪያልፍ የአባቴ ገበሬ ያግባኝ ሲሉ አልሰማሽም"......አሉኝ ወ/ሮ አፀደ...... ሰጠሁሽ ያለችው ፊቷን ዳግመኛ ለማንም ለመስጠት እንዳይሆን አድርጌ የማስጠንቀቂያ ወረቀቴን ተቀብዬ ያለ መውጫ ሰአቴ ከስራ ወጥቼ ሰፈር ከሄድኩ በኃላ....ከዚህ ጋር አስታኮ ቸሬ በቀጣይ አንድ ጥፋት ከተገኘብኝ እንደምባረር አስጠንቅቆኛል.....

"እስካሁንም አንቺ ስለሆንሽ ነው እንጂ ሌላ ሰራተኛ ላይ ትዕግስት የለኝም"....እስካሁን ሲል የመጀመሪያ ቀኔ እንደሆነ ተረሳኝ.....

አውቃለሁ ከድህነቴ ጋር የማይሄድ አመል እንዳለኝ.......አይቶ እንዳላየ አልችልበትም...ማስመሰል አላውቅበትም.....

"የአባቴ ገበሬ ያግባኝ ነው ያሉት...?"
"ኃላሳ...ቀን ፈቅ እስኪል"...
"ምነው የኔ ባለበት ቆመ...?"
"ገና ምኑ ተነካ ልጄ..."
"ገና አልተነካም....እኔኮ መጨረሻዬ እየመሰለኝ ነው"....
"ትናንት ጠዋትሽ ላይ ነበርሽ...አሁን ረፋዱ ላይ ነሽ.....አመሻሹ ሊሰምር ነው ረፋዱ የከፋው"....አሉኝ እንደሚያነቡኝ ነገር በጥልቀት እየተመለከቱኝ....

"እሺ ምናል አመሌን ቢያሳምርልኝ"....አልኩኝ ትክዝ ብዬ
"ብለሽ ነው...አላምር ብሎ አይደለም..."
"እና ምን ሆኜ ነው...?
"በትናንት እያሰብሽ...በትናንት እየኖርሽ..."
"እማማ ትናንት የለም...አባቴ የለም...እማም ኩሩዋ የቤት እመቤት አይደለችም ሁሉንም ጠንቅቄ አውቃለሁ..."...አልኩኝ በስጨት ብዬ....ትናንቴን ብኖር እዚህ ከእሳቸው ጋር ምን እሰራለሁ...?
ተረጋግተው ምስራቸውን ማበጠር ያዙ...እኔ አፍ አፋቸውን አያለሁ...

ማውራት ሲጀምሩ ወንድሜ ለመጀመሪያ ጊዜ ቃል ሲያወጣ ከተደሰትኩት በላይ ተደሰትኩ....
"ይኸውልሽ ልጄ...."....ብለው ሲጀምሩ ሰፍ አልኩ.....
"ትናንቱን ታውቂያለሽ....ዛሬንም እየኖርሽው ነው...ግን በትናንት ሚዛን ዛሬን እየለካሽ ግራ ተጋብተሻል....ዛሬ ላይ የፅዳት ሰራተኛ ሁነሽ ሳለ ልብሽ እንደ ትናንትዋ ያቺ አባቷ እንደሚጠብቃት ልጅ እየኖረ ነው...ልብሽና እውነታውን አስማሚያቸው"....አሉኝና ምስሩን ለሶስተኛ ጊዜ መልቀም ጀመሩ።

ልክ ናቸው ወይስ ልክ አይደሉም...?ከራሴ ጋር ግብግብ....ትንሽ አርፈው ማውራት ቀጠሉ።
"ዛሬ ያደረግሺው ነገር እንደትናንትዋ ፅኑ ልክ ነው....እንደዛሬዋ ግን ሚዛን አያነሳም...ትናንት የነበርሽበት ቦታ ላይ 'ለምን' ብሎ የመጠየቅ መብት ነበረሽ...የዛሬው ቦታጋ ሲመጣ ግን 'ለምን' በ 'እሺ' ይተካል....
'እሺ ይበልጣል ከሺህ'...ያሉት ለዚህ አይነቱ እሺታ ባይሆንም በ'እሺ' መራራ ዛሬ ይታለፋል"......ብለውኝ ግንባራቸው በሀዘኔታ እንደተጨማደደ ጥርሳቸው ፈገገ.....

ሁለት ስሜት በአንድ ገፅ....ግን ያመዘነው ሀዘኔታው ስለሆነ ጥርሳቸው ወዲያው ተከደነ.....ግራ ገብቶኝ አንዴ እሳቸውን አንዴ ምስራቸውን...አንዴ አላፊ አግዳሚውን አያለሁ...
"አይንሽን ምታሳርፊበት አጣሽ...?"...ቀና ብለው እንኳን ሳያዩኝ ጠየቁ
"አይ እማማ እንዲሁ ነው"
"ምኑ ነው እንዲሁ....እንዲሁ የሚባል ነገር የለም...አይንሽን ያይከራተተ አንዳች ስሜት አለ ተናገሪውና ይውጣልሽ"......ልክ ቢሆኑም ልክ አይደሉም....አዎ አይኔን ያስቀላወጠ መጥፎ ስሜት አለ....ማርፍበት እፎይ የምልበት የለም ግን ደግሞ በአንድ ቀን ሁሉንም መዘርገፍ አልችልም....ማውራት ራሱ ታክቶኛል
"ሁሉን ቢያወሩት ሆድ ባዶ ይቀራል ነው ነገሩ"....አሉኝ አንዳች ሳይወጣኝ
"ከርሶ ሚደበቅ ምን አለ"....ከልኩኝ ለአመል ታህል ፈግጌ
"ነው ብለሽ ነው ይሁና....".....ምስሩን ለአራተኛ ጊዜ ጀመሩት

****

በንጋታው እጥር ምጥን ያለች ፀሎት ፀልዬ ፣ ቅጥን ያለች ሽሮ በልቼ ወጣሁ...."በሰላም አውለኝ" አልኩት አውርቼው ማላውቀውን ጌታ....ምን ይለኝ ይሆን....


ይቀጥላል.....





Shewit dorka


Https://www.tg-me.com/ethioleboled
Forwarded from 🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁
የኛ ሰፈር.....8




"አንቺን የመሰለች ልጅ እንዴት ፅዳት ትሆናለች..."....ብሎ ድራማውን መስራት ጀመረ...ከዚህ ቀደም አይቼው የማላውቀው አይነት አይን ያለው ወጣት....ከአይኑ ፈቅ አላልኩም...በአይኑ ወዴትም እንዳልሄድ አጥሩን ሰራ....



አይኑ ላይ እንዳለሁ "በጣም ታምሪያለሽ".
አለና መወልወያዬን አስለቅቆ እጁን አስያዘኝ....ትክ ብሎ እያየኝ ተጠጋኝ....እስከ አሁን ምንም አላልኩም....እሱም ብዙም ቃላት የሚያባክን አይነት አይደለም.....በአይኑ ያወራል....ድንገት ዝምታዬን የሚሰብር፣የእጅ እግሬን መበደን የሚያስለቅቅ አስተያየት ሳይ ባነንኩ....ከቆንጆ ህልም እንደመባነን ነገር ....ምነው ባልነቃው የሚያስብል አይነት.....



አይኑ አይኔን ጠግቦ ከንፈሬን መቀላመድ ሲጀምር ባነንኩ....አይኔ ላይ ብዙም ጊዜ ማጥፋት እንዳልፈለገ ሲገባኝ ባነንኩ...እጁም እጄን ለቆ ወገቤ ላይ ሲገኝ ደግሞ በደንብ ባነንኩ.....በእጄ መንጭቄ ወገቤን ካስለቀኩ በኃላ ተስፈንጥሬ መወልወያዬ ላይ ደረስኩ....ኮተቴን ሰብስቤ እስክወጣ ዞሮም አላየኝም....ተናደድኩ....የምር ተበሳጨው....



"ማን ስለሆንክ ነው ቆይ ልትስመኝ የምትሞክረው...?ከዛሬ ውጪ አይተኸኝ ታውቃለህ...?ምን አይነት ንቀት ነው...መሳም ስለፈለግክ ብቻ ትስማለህ...እንደዛ ነው የምታስበው...?ማፈሪያ ነህ ወራዳ".....ብለው ደስ ይለኝ ነበር....ግን ቦታዬ ይህን እንዳላረግ ያስገድደኛል...ቦታዬ ሴትነቴን ያስረሳል......ዝም አልኩ....ተለጎምኩ...ንዴቴን ዋጥኩት.... ዝም ማለቴ ለቀጣይ እርምጃው አረንጓዴ ካርድ እንዳይመስለው እየሰጋሁም ቢሆን ተዘጋሁ።



ዛሬ ያያትን ሴት ከንፈር ድረስ ማሰቡ ሳላውቀው እንድንቀው አደረገኝ....ወይስ ለከንፈር "ድረስ" ተብሎ አይወራም...አላውቅም ግን
ከንፈር ተራ ነገር ነው...?ማለት ከሳመኝ በኃላ ምን ሊለኝ ነው...?እኔስ እንደ ተራ አሻንጉሊት በማላውቀው ሰው ተስሜ ሳበቃ እራሴን እንዴት ነው ማከብረው....?


ተራ ስሜት ማራገፊያ የሆንኩ መሰለኝ....ቆይ ይሄ ነገር ሰላምታ ሆነ እንዴ....በጣም ከመቅለሉ የተነሳ ከቅርብ አመታት በኃላ ሰላም ስንባባል ራሱ ከንፈርን ከከንፈር ማጋጨት ግድ ሊሆን ነው....ካቀለልነው አይቀር ....ለማንም ከሰጠነው አይቀር.....ለመሳም ማንም መሆን ሳይሆን ወፍሮ የለሰለሰ ከንፈር ባለቤት መሆን ብቻ በቂ መሆኑ ካልቀረ.....



"በስመአብ...."...አለችና እኔ በህይወት ዘመኔ ተሳልሜ የማላውቀውን ቁጥር ተሳለመች....የሺ ናት....የስራ ባልደረባዬ....በከንፈር ሰላምታን እያሰብኩ ብቻዬን ስገለፍጥ ደርሳ


"ምነው ፅኑ"....አለችኝ ቅንድቧን አኮማትራ
"ምንም የሺ የሆነ ቀልድ ትዝ ብሎኝ"...
"አልፎም የሚያስቅ ቀልድ ኧረ ንገሪኝ እኔኮ ዛሬ እንደአዲስ የሰማሁት ቀልድ እንኳን አላስቅሽ ብሎኛል"...
"ካላሳቀሽ ለምን እነግርሻለሁ...?"
"አንቺ እያስታወሽ ከሳቅሽበትማ ያስቀኛል..."..."በያ" ...ተመቻችታ ተቀመጠች...ወይ መከራዬ ምን ልንገራት በምናቤ ሁሉም ሰው እየተሳሳመ ሰላም ሲባባል ስዬ ነው ልበላት...?
"እየጠበኩሽ ነው..."
"አያስቅም እመኚኝ"
"ግድ የለም በኔ ይሁንብሽ"
"ድሮ ጊዜ ሁለት ባልና ሚስት ነበሩ...እና ሚስትየው ሁሌ ስጋ ስትከትፍ ከመክተፊያው ላይ እንዳለ ሙጥጥ ታረገውና ለባልየው የሚቀርበው የለገዳዲ ውሀ የሆነ ወጥ ነው...ከዛ ፈታት"....ልጅ እያለሁ እናቴ ስጋ እየለቀመች ላስቸገረች ሰራተኛችን የነገረቻትን ታሪክ ቀልድ ብዬ ነገርኳት....
"በቃ"....አለችኝ በግርምት...
"አዎ እንደማያስቅ ነግሬሽ ነበር"....
"ማሳቁን ትተሽ ሚስትን ለቀጠነ ወጥ ብሎ መፍታት እንዴት ከቀልድ ይመደባል"....አለችኝ በስጨት ብላ...
"እውነታው እኮ ነው...የድሮዎቹ እንኳን ወጡ ቀጠነ ብለው ነው ሚፈቷት....የአሁኖቹ እኮ ውሀ ቀጠነ ነው ጨዋታው".....
"እሱስ አዎ....የኔውስ ብትይ አራስ ልጅ አስታቅፎኝ ከፈረጠጠ በኃላ ቆይቶ ሲጠየቅ አ ሄ ሄ..."ብላ ከንፈሯን ነከሰች
"እ ምን አለ "...አልኳት በጉጉት

"እየጠበኩሽ ነው"....
"ኧረ ተይኝ ምን ይረባሻል"....
"እሱን እኔ ልወስን".....
"ኧረ ተይኝ...ምን ሁናለች ልጅቷ"...
"ኧረ የሺ"......ቦታ ተቀያይረን ቅድም ያስጨነቀችኝን ማስጨነቅ አስጨንቃት ጀመር.....እሺ እንደማልላት ሲገባት ልትነግረኝ ወስና አፏን መጠራረግ ጀመረች።





ይቀጥላል.....




Shewit dorka



👉https://www.tg-me.com/ethioleboled
Forwarded from 🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁
የኛ ሰፈር......9





"ይኧውልሽ የኔው ከረፈፍ ገና ደም ልጅ ታቅፌ..."
"ፅዳት ኧረ ፅዳት"....ገና የሺ ወሬዋን እንደጀመረች ተጠራን....
"ያቺ በሽቃጣ ልጅ ናት የሺ እኔ አልሄድም እጣላታለሁ"
"እሺ እሺ እኔ እሄዳለሁ"
"ፅዳት እንዴ ምንድን ነው አትሰሙም እንዴ"....
"መጣሁ መጣሁ"......እየተጠዳደፈች ወጣች.......ልጅቷን ይብስ ጠላኃት...በመከራ የቃረምኩትን ወሬ ስላቆረፈደችብኝ.....

"ፅኑ  ፅኑ"....የሚል የሚለሰልስ ድምፅ ከሆነ ቦታ መጣ...አልዞርኩም....ሰሞኑን ስሜ አልመስልሽ ስላለኝ...ከዚ ድርጅት ወደ እኔ ሊመጣ የሚችለው ድምፅ "ፅዳት" የሚለው ብቻ ስለሆነ....ወይስ ከሰማይ ነው የተጠራሁት....'ተናገር ባሪያህ ትሰማለች' ልበል እንዴ....በስመአብ ይቅር ይበለኝ....ዛሬ ገና ፀልዬ ብወጣ የማስበውን እዩ...ትንሽ ብገፋበት ጥያችሁ ማረጌ ነው ፣ ከሰማዩ ጎራ መቀላቀሌ ነው ልላችሁም እችላለሁ....


"ፅኑ".....ተደገመ.... ዙሪያዬን ቃኘሁ....ያ የቅድሙ ጀዝባ በሩ ላይ አንዱ እጁን ከበሩ አናት አድርጎ አይሆኑ አቋቋም ቆሞልኛል.....ስሜን ከምኔው አውቆ ለማቆላመጥ በቃ....ስንት አይነት ሰው አለ....
"አቤት"....አልኩት ኤፊን ሳስፈራራት እንደማያት አድርጌ እያየሁት....አሁን እንደፈለግኩ መሆን እችላለሁ...ምክንያቱም ይሄ የኔ ግዛት ነው......
"ቅድም አጠፋሁ መሰለኝ..."....እንደመሸማቀቅ እያለ....

ተመስገን ትንሽ ማሰብ ይችላል ማለት ነው አልኩኝ በሆዴ.....

"ምን ልታዘዝ"....
"አንድ ነገር ፈልጌ ነበር"...
"ምን...?"....በስህተት ፊቴን እንዳልፈታው ከአይኑ ግጭት እንዳልወድቅ እየተጠነቀኩ ነው...
"ይቅርታሽን"....አለኝ ድሮ አባቴን ይቅርታ ስጠይቅ የማሳየውን ምስኪን ፊት እያሳየኝ...

ሁለት ሀሳብ ሆንኩ ምን እንደምለው ግራ ገባኝ...በቀላሉ እሺ ብዬ ባባርረው እኮ ደስ ይለኛል...እሺ ይቅርታዬን አግኝተሀል ካልኩት በኃላ ምን ያረጋል....? ይሄዳል ...?መሄዱን ይሂድ እኮ ግን አይኑም አብሮት ይሄዳል.....እምቢ ብለውስ እሺ እስክለው አይኑን ይዞ ይመጣል....ወይም ስራሽ ያውጣሽ ይለኛል....ከዛ በኃላ ደግሞ አይኑም አይኖርም......

ምን እንደምለው ሳውጠነጥን የሺ ደርሳ ገላገለችኝ....
"መንገድ ጌታው...."አለች አክብሮት በሚስተዋልበት ድምፀት
"እሺ እሺ".....ብሎ ካሳለፋት በኃላ "ደህና ዋሉ"...ብሎ አይኑን ይዞብኝ ሄደ።

የገዛ አይኑን ይዞ ስለሄደ እየተናደድኩ ነው...ለነገሩ የገዛ አይኑም አይደለም...ከየት አባቱ ገዛው.....ደግሞ እንደዚህ አይነት የሚያወራ አይን እሱ ሰውነት ውስጥ መኖር ነበረበት...?አላውቅም ግን በዚች ቅፅበት በሆነች ጊዜ ስለ እርሱ ሳስብ የሚመጣልኝ አሸን ነገር ነው.....

በዋናነት አይኑ....ድፍረቱ...ንቀቱ...ከልቡ ይሁን አይሁን ባላውቅም ይቅርታው...በቃ በቃላት ማስረዳት የማልችላቸው ሌሎች ስሜቶች....

ስሙን እንኳን የማላውቀው ሰው  ጭንቅላቴን ሲያራውጠው ዋለ...የሆነ ሰአት ላይ ራሴን መገሰፅ ጀመርኩ....ትንሽ አርፍና ደግሞ ወደ እሱ እመለሳለሁ....እንዲህ እንዲያ እያልኩኝ ቀኑ መሸልኝ....ወደቤቴ ከመግባቴ በፊት የሆነ ነገር ትዝ አለኝ...እናቴ የልጁ ወተት እና ሌሎች የቤት ወጪዎች እንደሌሉ ፈራተባ እያለች የነገረቺኝ ....

እየተጠዳደፍኩ ከቸሬ ቢሮ ተገኘሁ.....
"ፅኑ"...ኤፊ ናት....ደንግጣለች
"እዚ ምን ትሰሪያለሽ...?የምን ልብስ ነው የለበሽው ደሞ"....ልትቀጥል ስትል
"ቸሬ የማወራህ ነገር አለ"...ብዬ ሀሳቧን ቆረጥኩት...
"መቀጠል ትችያለሽ..."....ተቀመጪም የለም....
"ገንዘብ በጣም ያስፈልገኛል...ከቻልክ ከደሞዜ የተወሰነ ገንዘብ ቆርጠህ ብትሰጠኝ".....

"ምን ያሀል..."....ሲለኝ ምለው ጠፋኝ....ጉድ ደምወዜ ስንት እንደሆነም አላውቅም.....
"ደምወዜ ስንት ነው...?"....አልኩት አንገቴን በሼም አኳሀን እያሸሁ...

"2000".....ሲለኝ ቅስሜ ቋ አለ...
"አንዱን ስጠኝ..."....አልኩት ብዙም ሳላስብ

' ምን ምን' እንደምታደርግበት ማሰብ አልፈለግኩም...'ምን ምን' አልኩ እንዴ...'ምን' ብቻ በሚለው ይስተካከልልኝ....የዘንድሮ አንድሺህ አንድ ብር በሉት....ብዙም አላብራራም ያው ኢትዮጵያውያን ስለሆናችሁ በደንብ ታውቁታላችሁ....
"ይቻላል...መሄድ ትችያለሽ"... ሲለኝ አፈጠጥኩበት...
"እሺ እሺ"....አለኝና ....
"ይሄን ወረቀት ይዘሽ ፋይናንስ ክፍል ሂጂ."......ብሎ አሰናበተኝ።


"አመሰግናለሁ"....ብዬው ወጣሁ...ኤፊን ግን ምንም አላልኳትም......

ሱክ ሱክ ብዬ ወደ ፋይናንስ ክፍል ስሄድ አንዲት ልትሞት አንድ ሀሙስ የቀራት አሮጊት ሴትዮ የተስተካከሉትን ወረቀቶች እንደገና ስታስተካክል ደረስኩ....
"ሰላም"....ብዬ ወረቀቱን ዘረጋሁላት....አልተቀበለችኝም....ይልቁኑም በእጇ ጠረጴዛውን መዳበስ ያዘች....ከብዙ ፍለጋ በኃላ መነፅሯን አገኘች....ከዛም ከኩባያ ጥርሷን አውጥታ ሰካች....
"አሁን መግባባት እንችላለን"....አለችኝና ወረቀቴን ተቀበለች...

ከዛም ብዙም ጊዜ ሳትፈጅ ከወረቀቱ ስር አስፈረመችኝ እና አንድ ሺህ ብር ሰጠችኝ .......
"አመሰግናለሁ"....ብያት ወጣሁ....ሰሞኑን ይሄ ቃል የግሌ ሆኗል....ለመደብኝ መሰለኝ....






ይቀጥላል...



Shewit dorka

Https://www.tg-me.com/ethioleboled
Forwarded from 🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁
#ጽሞና
(In The Sphere of Silence)

#ደራሲ- ቪጃይ ኤሽዋረን

#ተርጓሚ- ዳንኤል ጥሩነህ

ህልምህ ዕውን የሚሆነው ውስጥህ
የሚገኘው ነገር መመልከት ስትችል ብቻ ነው። ውጪውን ከማያየውና ከማያልመው ሰው ይልቅ ወደ ውስጡ የሚመለከት እሱ ይነቃል።

     ምርጥ የተባለውን ህይወት ለመኖር የከሰል ዋጋ አለኝ ብሎ የሚያስበውን ሰውዬ እንቁ እንደሆነ እንዲያስብ ማድረግ ብቻ በቂ ነው። የትኛውም ዓይነት ድፍድፍ ማዕድን ያለብዙ ልፋት ወደ ዕንቁነት ሊቀየር አይችልም። ጥያቄው ሊሆን የሚገባው ዕንቁ መሆንን ሲፈልግ የሚጠይቀውን ዋጋ ለመክፈል ተዘጋጅቻለሁ ወይ? የሚለው ነው።


#መልካም_ንባብ👇
Forwarded from 🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁
ጽሞና.pdf
27.1 MB
ጽሞና (In The Sphere of Silence)
ደራሲ- ቪጃይ ኤሽዋረን
ተርጓሚ- ዳንኤል ጥሩነህ

         #Share
                  ➷
           @ethioleboled
📜❦ ═══ •⊰❂⊱• ═══ ❦📜
Forwarded from 🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁
ርዕስ:-ሁቱትሲ
የወጣቷ ልብ አንጠልጣይ ትውስታዎች 
 
ድርሰት:- ኢማኪዩሌ ኢሊባጊዛ
እና ስቲቭ ኤርዊን 
ተርጓሚ:- መዘምር ግርማ

በትንሿ ምስጢራዊ መታጠቢያ ቤታችን ጥጋት አንድስ እንኳን የሰውነቴን ክፍል
ሳላላውስ ተሸሽጌያለሁ፡፡ እንደኔው ሕይወታቸውን ለማትረፍ እንደተደበቁት ሌሎች ሰባት ሴቶች ሁሉ ገዳዮቹ ስተነፍስ እንዳይሰሙኝ ትንፋሼን ውጫለሁ፡፡
ድምጻቸው የሠራ አከላቴን ገማመሰው፡፡ በከሰል ፍም ላይ እንደተኛሁ፣ እሳትም
ላይ እንደተጣልኩ ተሰማኝ፡፡ መላ ሰውነቴ የሕመም ውርጅብኝ ወረደበት፡፡ ሺህ
የማይታዩ መርፌዎች ተቸከቸኩብኝ፡፡ ፍርሃት እንደዚህ የሚያርበደብድ ስጋዊ ሥቃይ ያስከትላል ብዬ አስቤ አላውቅም፡፡

ለመዋጥ ሞከርኩ፤ ጉሮሮዬ ግን ተዘግቷል፡፡ ምራቅ አልነበረኝም፤ አፌም እንደ ኩበት ደርቋል፡፡ ዓይኖቼን ጨፈንኳቸው፤ ራሴንም ለመደበቅ ሞከርኩ፤ ንግግራቸው ግን እየጎላ መጣ፡፡ ምንም ዓይነት ምኅረት እንደማያደርጉልኝ አውቃለሁ፤  በአእምሮዬም አንድ ሐሳብ ያስተጋባ ጀመር - ከያዙኝ ይገድሉኛል፡፡ ከያዙኝ ይገድሉኛል ከያዙኝ ይገድሉኛል…


#Share
                  ➷
          
@ethioleboled
📜❦ ═══ •⊰❂⊱• ═══ ❦📜
Forwarded from 🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁
ሁቱትሲ፣_ከሩዋንዳው_የዘር_ማጥፋት_የተረፈች_ወጣት.pdf
1.8 MB
ርዕስ:-ሁቱትሲ

ድርሰት:- ኢማኪዩሌ ኢሊባጊዛ
እና ስቲቭ ኤርዊን

ተርጓሚ:- መዘምር ግርማ

#Share
                  ➷
          
@ethioleboled
📜❦ ═══ •⊰❂⊱• ═══ ❦📜
Forwarded from 🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁
በጊዜያዊው ዘላለሜን አልጣ ዘመኔ አይባክን መጨረሻዬ አይበላሽ፤ከፊት ጀምሬ ከዃላ አልገኝ።
በመንፈስ ጀምሬ በስጋ አልጨርስ፤እንደገባ ይውጣ እንደወጣ ይቅር አትበለኝ፤ መልካሙ እረኛዬ ሆይ አንተ ጠብቀኝ።
ሰዉ መነሻውን እንጂ መድረሻውን አያውቅም እና የቀናውን መንገድ ምራኝ።

📖መርብብት📖
በአለማየሁ ዋሴ እሸቴ

share 🗞 @ethioleboled
Forwarded from 🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁
መርበብት.pdf
125.9 MB
Forwarded from 🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁
የኛ ሰፈር....10




የወንድ ልጅ ቤቱ የሴት ልጅ ውበት ነው ....ገጣሚው ያለው ትዝ አለኝ....
"ታምሪያለሽ"...እያለ በየቀኑ ሲቀልበኝ አይምሮዬ ላይ ይመላለሳል...ባልሰራሁት ውበት ላቡን ጠፍ አርጎ የሰራውን ገንዘቡን ያፈስብኛል....


እኔ ደግሞ እኔ ባልበላ ሌላዋ ቆንጆ ትበላዋለች....ሆነም ቀረም ብሩ በውበት ሰበብ መጥፋቱ አይቀርም....እና የመሳሰሉትን ሰበብ እየደረደርኩ ከርሴን እሞላለሁ...



"ፅኑ"....አለኝ አቤት ማለት በማልችልበት ሁኔታ ጎርሼ ሳለሁ
"እ"አልኩት ቶሎ ለመዋጥ እየሞከርኩ
"በጣም ታምሪያለሽ"....የተለመደ አድናቆቱ ነው።
"እሺ"...አልኩት እና ወደምግቤ ተመለስኩ...እስከ ዛሬ ለዚ አድንቆቱ መልሴ ለሰስ ያለ ፈገግታ ነበር...እስከ ዛሬ ማለቴ ላለፉት አምስት ቀናት ማለቴ ነው።
"እሺ ነው ያልሽው "....አለኝ በግርምት እያየኝ
"ምን ማለት ነበረብኝ..?"
"የብዙ ሴቶች መልስ አመሰግናለሁ ነው..."......ብዙ ሴት ነው ያለው...ወይ እዳው እድሜውን በሙሉ ቆንጆ ሲያበላ ነው የኖረው ማለት ነው አልኩ በውስጤ..
"ለምን አመሰግንሀለሁ ቆንጆ ስለሆንኩ..?"
"አይ ለአድናቆቱ ግን የጠበኩት ይሄን ምላሽ አልነበረም"...አለኝ ርዕሱን ለመዝጋት እየሞከረ
"የጠበከውንማ ነገርከኝ እኮ...መመስገን አይደል...?"
"ሳይሆን አለ አይደል ስለተለመደ ነው"...በውስጡ ምኗ ክችች ያለች ናት ማለቱ አይቀርም።
"ሲበዛ የውበት አድናቂ ነህ...."
"አድናቂ ብለሽ አሳነሺው...የውበት ተገዢ ሚለው በደንብ ይገልፀኛል"...አለ ትልቅ ተአምር እንደሰራ ሰው ደረቱን እየነፋ


"እስከአሁን ለምን አላገባህም...?"...አልኩት ወደሸበተው ፀጉሩ እየተመለከትኩ
"አግብቼ ፈትቼ ነው...እንዳልኩሽ ውበት ላይ አልደራደርም...ሴቶቹም አይን አዋጅ ይሆኑብኛል...አግብቼም ቆንጆ ሴት ካየሁ አልምርም...እንደው ግንኙነታችን ወዴትም ባያድግ እንኳን እንዲሁ ሳያት ለመዋል ምንም አደርጋለሁ የቀድሞ ባለቤቴ ፍቺ የጠየቀችኝ  በዚሁ ባህሪዬ ነው"



"አስር ያንተ ያልሆነ ከማየት አንድ ያንተ የሆነን ማጥበቅ አይሻልም...?" አልኩት በትኩረት እያየውት...እውነቱን ለመናገር አንቱ ብለው ነበር ደስ የሚለኝ....
"አጠብቃለሁ እሱማ...ባለቤቴን ችላ ብያት አላውቅም ነበር ....ግን ያው..."...ማብራራት ሳይጀምር ስልኩ ጠራ...
"መጣሁ መጣው የኔ ቆንጆ"....አለና ስልኩን ዘጋው...በእጁ የሂሳብ አምጣ ምልክት ለአስተናጋጁ አሳየው...
"የኔ ቆንጆ መሄድ አለብኝ "...ጥሎኝ እብስ አለ....በለው...እኔም የእሱ ቆንጆ...የደወለችዋም የእሱ ቆንጆ ሆንን...ይሄኔ ነው መሸሽ...ምንም ሳልለው ስልኩን blacklist ውስጥ ከተትኩ...


"አሌክስ እባላለሁ"....ብሎ ነው የተዋወቀኝ....አለም አየሁ ማለት ደብሮት መሰለኝ....ብቻ ለአንድዋ ቆንጆው ቤት ሊገዛ የእኛ ድርጅት ሲመጣ ነው የተዋወቅነው...የኔ ነገር 'የእኛ' አልኩ  'የእነርሱ' በሚለው ይስተካከል...ለቆንጆው ቤት በገዛበት ማግስት እኔ ጋር ደወለ... ስልኬን ከየት እንዳመጣው አላውቅም....ከኤፊ ውጪ ስልኬ ለሌላ ሰው ጠርቶ አያውቅም ...ግራ እየተጋባሁ አነሳሁት..

"የኔ ቆንጆ"...አለኝ ገና ሀሎ ከማለቴ
"ማን ልበል"...
"አሌክስ እባላለሁ"
"ስምህ ምን ያረግልኛል..."
"ዋናው ኪስህ ነው ማለትሽ ነው"
"አትለፋደድ...ማን ብለህ ነው የደወልከው"...ተናድጃለሁ
"ፅኑ"...አለኝ ለዘመናት እንደምንተዋወቅ ነገር
"ቃልም አለበት"...ስሜን ለምን ማቆላመጥ እንደሚቀናቸው አላውቅላቸውም....እንዲሁ ሳስበው ግን ቃል ስለሚከብዳቸው መሰለኝ...
"ፅኑቃል"....አለኝ በሚስቅ ሰው ድምፀት
"አቤት"...
"እንገናኝ"....ትዕዛዝ ነው...
"ማን ስለሆንክ ነው የምታዘኝ...?"
"አላዘዝኩሽም የኔ ፍቅር".....ጭራሽ የኔ ፍቅር ብሎኝ አረፈው...
"ስራፈት"...አልኩትና ስልኩን ጆሮው ላይ ዘጋሁት.......


በንጋታው አንድ ቦርጫም፣እግሩ ሳር የሚያክል፣ በአጠቃላይ ዙሪያው ገደል ሆኖ ተራራ ብቻ ያለው መሬት የሚመስል ሰውዬ ወደ እኔ መጣ....አሌክስ ተብዬው ነው.....



ይቀጥላል..



Shewit dorka



Https://www.tg-me.com/ethioleboled
Forwarded from 🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁
የኛ ሰፈር....11



"አሌክስ ነኝ"...አለኝ እያገጠጠ
"እና ምን ይፈጠር..?"...እንድጠመጠምበት ጠብቆ ነበር መሰለኝ ቅሬታው ፊቱ ላይ ተነበበ።
"ብንተዋወቅ ደስ ይለኛል"
"ባንተዋወቅስ በጣም ታዝናለህ ማለት ነው"....ከነ ሹፈት ሳቄ ነው ማወራው
"እንደዛ ማለቴ ሳይሆን ባውቅሽ ጥሩ ነው ብዬ ነው"
"ብታደርጋቸው በጣም ጥሩ የሆኑ እልፍ ነገሮች አሉ...ያው ጭንቅላት ካለህ ነው ግን ደግሞስ ጥሩነቱ ለኔ ወይስ ላንተ...?"....ጠየቅኩ
"ለሁለታችንም"...አለኝ በእርግጠኝነት
"እኔ ራሴን አውቃለሁ ባንተ መታወቁ ፋይዳ የለውም"
"ኧረ ተይ ግድ የለሽም"....
"ስራ አለብኝ እርሶ ስራ ከሌሎት እኔን ስራ አያስፈቱኝ".....ሳላስበው ሽበቱን እያየሁ አንቱታው አመለጠኝ...


"የምን አንቱታ ነው"
"አምልጦኝ ነው...ልክ ነህ አንቱታው ይከብድሀል"
"ምነው ሳታውቂኝ አቀለልሺኝ"
"ባውቅህም አላከብርህም"
"እና ምን ነበር ያልሺኝ"....እርጅናው እያስረሳው ነው መሰለኝ....
"መተዋወቅ አልፈልግም"
"አስቢበት"
"ስራ አለብኝ"....ብዬው ጥያቸው ሄድኩ....በእድሜያቸው ተነስቼ ላከብራቸው እልና በአኳሀኑ ምክንያት ለማቅለል እገደዳለሁ....አንቱ እኮ ክብር ነው...አንቱ ብለን ያወራነውን ሰው ስንሰድበው አንተ ብለን አውርደን ነው...ሁለት ፀጉር ላወጣ ሁሉ አንቱታ አይሰጥም...ልቡ እኮ እንደ 15 አመት ልጅ ወጥቼ ልፍረጥ ልፍረጥ እያለችበት ነው...ለዚህ ተፈጥሮ ለሰጠችው ክብር : ክብር ለሌለው ሰው የምን ክብር ነው....


አመሻሽ ላይ ከስራዬ ስወጣ መውጫው ጋር እንደ ቲያትረኛ እየተንጎራደደ ደረስኩ....
"የኔ ቆንጆ"...ብሎ ወደ እኔ ሲመጣ አይኔ በሆነ አልኩ...ደግሞ ጩኧቱ
"ወይኔ ጉዴ"....አልኩኝ ሳላስበው
"ምነው ምነው"...አለች የሺ ግር ብሏት
"ሰውየው ያመዋል መሰለኝ"
"ማንን ነው"...አለች በአይኗ እብድ እየፈለገች
"ወደዚህ ሚመጣው፣ቦርጫሙ፣ሽበታሙ"...ተንተባተብኩ
"እንዴ ጋሽ አለማየሁ"...አለች እየተፍነቀነቀች....እንዴ ይቺን ደግሞ እይዋት አክብራው ቁጭ አለች...እሷ ላይ አይለፋደድም ይሆናል...
"የሺ እንዴት ነሽ ልጅሽስ እንዴት ናት"
"ደህና ናት ይመስገን እድሜ ለእርሶ እና ለፈጣሪ"...ስትነጠፍ እድሜ ለፈጣሪ ብላ አረፈች
"ደህና እደሪ"....ብዬ ለመሄድ እግሬን ሳነሳ
"የኔ ቆንጆ"....አለ እኔ ከሩቅ ሰው ስጣራ የምጠቀመውን ድምፅ አውጥቶ..ወይኔ የሺን በሆነ አልኩ በሆዴ...ምኞቴ አልሰመረም....ሊከደን የደረሰ አይኑን እኔ ላይ ጥሎ ነው ሚያወራው....


ጥዬው ሄድኩ...ታምኑኛላችሁ ተከተለኝ....
"ብታውቂኝ ትወጂኛለሽ"....ኧረ ሞራል
"ለምን አትከበርም"...አልኩት እንዳከበርኩት ነገር....
"እኔ ካንቺ ምንም አልፈልግም....እንዳይሽ ብቻ ፍቀጂልኝ"
"እራት በልተሻል"....በምግብ ሊደልለኝ በማሰቡ ተበሳጨው...ግን እሱ ነው...በዚህ ጭንቅላቱ ከዚ የተሻለ ሊያስብ አይችልም...
"አዎ በልቻለሁ"
"እስቲ አባይኝ ዛሬን"...አለኝና ድሮ ሀያቴ እንደሚስቀው ሳቀ...ቀጥሎ ወደ መኪናው ጠቆመኝ.......እመኑኝ ኩርት ብዬ ነበር....የታክሲ ምንም ብር እንደሌለኝ እስከማስታውስ ድረስ...እንደተኮሳተርኩ መኪናው ውስጥ ገባሁ...



እየቀፈፈኝ አጠገቡ ተቀመጥኩ...የሽማግሌ ፍንዳታ አይጣል አያድርስ...እንዴት እንዴት እንደሚያረገው ....ማስቲካውንማ አሰቃየው...አማረብኝ ብሎ እንጨት እንጨት የሚል ቀልድ ይቀልዳል...በራሱ ቀልድ ፍርስ ይላል...እየተገለማመጥኩ አሁንም አለሁ....ጭራሽ ስትኮሳተሪ ታምሪያለሽ ብሎኝ እርፍ...በምንም አይነት ሁኔታ ውበትን የሚያሳድድ የሽማግሌ ቀላል...



አለም አየሁ ዳቦ ሲሰርቅ አየሁ...ትል ነበር ሀያቴ...አለም አየሁ እድሜ ሲሰርቅ አየሁ....ብልስ እኔ


"ፅዳት ፅዳት...ኧረ ፅዳት"...ጉሮሮዋ ሊሰነጠቅ ነው...የሺን አየት ሳደርጋት አንቺ ሂጂ እንደሆነ ገባትና ተነሳች...ደቂቃም ሳትቆይ ተመልሳ መጣች..
"ተፈልገናል"
"ያቺ በሽቃጣ ናት...?"
"ኧረ አቶ ቸርነት ናቸው..."....ተከታትለን ከክልላችን ወጣን....እኛ ቢሮው ስንገባ ያ የምወደውን አይን ይዞ ሚኖረው ሰውዬ ሲወጣ ተላለፍን....ቢሮው ስንገባ ቸሬ የስልጣን ወንበሩ ላይ የኔዋ ጉድ ደግሞ ከሱ ትይዩ ካለው ወንበር ላይ ተቀምጠው ጠበቁን...ባላንጣዬ የፊቷ ብልዝ ቀንሷል...ባየችው ቁጥር ትዝ ሳልላት አልቀርም...

"በሰላም ነው ቸሬ"..እሷን ዘልዬ ቸሬን አወራሁት...
"ይፈተሹልኝ"....አለች እኔን እኔን እያየች
"የምን ፍተሻ"....ደርቀን ቀረን




ይቀጥላል....
   

  
    ስላረፈድኩ ይቅርታ  እንኳን አደረሳችሁ  🙏


Shewit asgedom


Https://www.tg-me.com/ethioleboled
Forwarded from 🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁
የጭን ቁስል .pdf
43.1 MB
Forwarded from 🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁
"አንዱ የሌላውን ልብ እንዴት አድርጎ ለማወቅ ይችል ይሆን?ሰው ጨው አይደለም ተቀምሶ እንዳይታወቅ!ምን ብናደርግ ይሻል ይሆን? እያንዳንዱ ሰው የክፋትን መንገድ ትቶ ደግ ደጉን ማሰብ ቢጀምር ይህ ህይወት፣ይህ አለም ምነኛ ጣፋጭና ውብ፣የሰው ሞቱ ሞነኛ ክብር በሆነ ነበር! አለ።ሰው ባልገባውና በማያውቀው ነገር፣በዚች ውብ ምድር በዚች የጋራ አለም፣ያውም ለዚች አጭር ህይወት አንዱ ለሌላው እቶን እሳት፣ገሃነም ሆኖ ገሃነም የሚፈጠርበት አሳዛኝ ሁኔታ አሳዘነው።"

📓ሀዲስ📓
        . በአሉ ግርማ

share📯 @ethioleboled
Forwarded from 🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁
ሀዲስ - በአሉ ግርማ.pdf
27.5 MB
2024/09/22 17:19:16
Back to Top
HTML Embed Code: