Telegram Web Link
💥📚ኢትዮ-ልቦለድ📚📖💥
Photo
👱‍♀👱‍♀👱‍♀ ቲናዬ ደወለች 📞📞📞




       📚📚ክፍል ..... 1⃣📚📚

...ቲናን ወደቀጠርኩበት ካፌ ለመሄድ ታክሲ እየጠበቅሁኝ ነው፡፡

ቲናዬን ያወቅኳት ከሁለት ቀናት በፊት ጠና የሚሠራበት ታክሲ ውስጥ በተፈጠረ ጠብ ምክንያት ነው፡፡ አታውቁትም እንጂ ጠና በአካባቢያችን አንጋፋ የታክሲ ረዳት ነው፡፡

ከሁለት ቀናት በፊት ማታ
ላይ ጠና ‹ዲጄ› ሆኖ በሚሠራበት ታክሲ ተሳፍሬ ወደ ሠፈሬ እየተመለስኩ ሳለ፣ ግማሽ መንገድ ላይ ቲናዬ እንደ ትራፊክ ፖሊስ እጇን ዘርግታ ታክሲውን አስቆመችው፡፡ ሰው በሰው ላይ ጠቅጥቆ አልረካ ያለው ጠና፣ የታክሲውን በር ከፍቶ ከአንዱ ጎረምሳ ጋር ተደላድዬ የተቀመጥኩት እኔን እንድጠጋላት ነገረኝ፡፡

ከወንበሩጥበት  የተነሳ እግሬን ለማንቀሳቀስና ምላሽ ለመስጠት ስለዘገየሁ በደምፍላት፤ ‹‹ወይ ተጠጋላት ወይ ውረድ!›› የሚል ቀጭን ትእዛዝ ሰጠኝ፡፡
ጠና ግዙፍ ሰውነቱን ለማፍታታትና የሰውነት አካላቱን ደኅንነት ለማረጋገጥ፣ ከተራ አስከባሪና ከተሳፋሪ ጋር ቡጢ ሲቃመስ የሚውል ረዳት ነው፡፡

ብዙ ዕድሜውን ያሳለፈዉ በእስር ቤት ነው፡፡
በፊት በፊት እንደ ሸንኮራ ሻጭ ከእጁ ቢላዋ አይለየውም ነበር፡፡

እንደውም መንደራችን ውስጥ ካሉት አንድ ሃኪምና ሁለት ነርሶች ይልቅ እርሱ ብዙ ሰዎችን እንደወጋ ይነገርለታል፡፡
በጠና እጅ በጥፊ ከመጣጋት፤ መጠጋትን መርጬ ለቲና ግማሽ
ቂጧን ማሳረፍያ የምትሆን ቦታ ለቀቅሁላት፡፡ በዓይኗ አመሰግናለሁ
አለችኝ፡፡

በተሳፋሪ ፊት በጠና ከፍ ዝቅ ተደርጌ እንድገላመጥ ምክንያት ስለሆነች ከፍ ዝቅ እድርጌ ገላመጥኳት፡፡

ታክሲው መንገድ ከጀምረ በኋላ በድጋሚ ልገላምጣት ፊቴን ወደ እሷ ሳዞር በግማሽ ቂጧ የጎንዮሽ ተቀምጣ፤ በአንድ እጇ ቦርሳዋን አቅፋ፤ አንድ እጇን ደግሞ ቡጢ ጨብጣ የታክሲውን ግርግዳ ተደግፋለች፡፡ እያየኋት እንደሆነ ቀልቧ ነግሯት ዞር ብላ በጨረፍታ
ተመለክታኝ ፈገግ አለች። ፈገግታዋ ቀየረኝ፡፡ ፈገግታዋን ሳጣጥም
ስታየኝ መሽኮርመም ጀመረች፡፡ ከእሷ ሰስቼ ያስተረፍኩትን ትርፍራፊ
ቦታ ከለቀቅሁላት በኋላ ከጎኔ ያለውን ተሳፋሪ እስከ ታክሲው ግርግዳ ገፍቼ ተደላድላ እንድትቀመጥ ጋበዝኋት፡፡

ዳግም ፈገግታዋን ብልጭ ስታደርግልኝ ሰውዬው ከታክሲው ተጣብቆ፤
ታክሲው እስኪለጠጥ ድረስ ተጠጋሁላት፡፡

ፈገግታዋ እንደ ቀትር ፀሐይ እየበረታ ሲመጣ፣ የጠሀይ መነጥሬን ዓይኔ ላይ ከሰካሁ በኋላ ከጎኔ ያለውን ሰውዬ ላስወርድላት ወይስ እኔ ልነሳላት የሚል
የሀሳብ ምጥ ያዘኝ፡፡ ከዛም ስለ ምጥ አወራት ጀመር፡፡

‹‹ስሜ ቲና ይባላል›› አለቺኝ ከታክሲ ስንወርድ፡፡ የድምጿ ቅላጼ ከአማርኛ ይልቅ ወደ ፈረንጅኛ ያደላል፡

‹‹ስልክሽስ ማን ይባላል?›› ‹‹ስልኬ ‹ሳምሰንግ S4 › ይባላል›› ሣቅ አለች፡፡ ትንሽ ቆመን ካወራን በኋላ ስልክ ቁጥሬን ተቀብላኝ፤ ፀባዬ ታይቶ ስልክ ቁጥሯ አንደሚሰጠኝ ቃል ገብታልኝ፤ ዛሬ ላገኛት ቀጥራኝ ተለየችኝ፡፡

ቲናዬ ከሄደች በኋላ ድምጿን የሆነ ቦታ እንደማውቀዉ ጠረጠርኩኝ፡፡
ለማስታወስ ያህል ስትሄድ በመቆምና ፈዝዞ በመቆም መካከል ሆኜ ከኋላዋ አስተዋልኳት፡፡ ግና ቄንጠኛ አረማመዷና ዳንኪረኛ ዳሌዋ፣ ድምጿን የት እንደማውቀዉ ምንም ጥቆማ ሊሰጡኝ አልቻሉም፡፡ ቶማስ ኤዲሰን ድምጽ መቅጃን ለመፍጠር ያሰበውን ያህል ካሰብኩ በኋላ ድምጿን የት እንደማውቀው ትዝ አለኝ፡፡ ድምጿ ከተከራየሁበት ግቢ ውስጥ ጠዋት ጠዋት የምሰማው የወፎች የዝማሬን ድምጽ ይመስላል፡፡

የተከራየሁበት ግቢ ውስጥ ዘወትር ጠዋት ጠዋት ያማረ የወፎችን ዝማሬ እሰማለሁ፡፡ ‘ግቢ ውስጥ በድንጋይና በሲሚንቶ አብደዉ

ከተሰሩ ቪላ ቤትና ሰርቪስ ቤቶች ውጪ ዛፍ ቀርቶ ቀጫጫ የመፋቅያ ተክል እንኳን የለም፡፡ የድንጋይ ቤት ውስጥ እንሽላሊት እንጂ ወፍ አይኖርም፡፡

**እንሽላሊቶች ደግሞ እንደ ወፍ ሊዘምሩ
አይችሉም፡፡ ‹ጠዋት፣ ጠዋት የሚሰማው የወፎች ዝማሬ ከየት የመጣ ነዉ?› የሚል ሀሳብ ከቤት ኪራዩ የበለጠ ያስጨንቀኝ ነበር፡፡ እንደውም አንድ፣ ሁለት ቀን የማለዳ ወፎቹን የዝማሬ ድምጽ ተከትዬ ወፎቹን ፍለጋ ግቢዉን አስሻለሁ፡፡ ግን ምንም
መረጃ ላገኝ አልቻልኩም፡፡**

ምናልባት አከራዮቻችን፣ ተከራዮቻቸውን ለማስደስት ጠዋት ጠዋት እየተነሱ እንደ ወፍ ይዘምሩልን ይሆናል ብዬ ነገሩን ተውኩት። ቲና እኔ በተከራየሁበት ግቢ በር አልፋ ወደ ጀርባ በሚወስደው ቅያሰ ታጠፈች፡፡

ብዙ ሲያስጨንቀኝ ለነበረ ጥያቄ መልሱንና ማረጋገጫውን አገኘሁ፡፡ የቲናን ተክለ ሰውነትና ፈገግታ ሳስበው ሞልተው እየገላመጡ የሚሄዱትን ታክሲዎች እያስቆምኩ እቅፍ አድርገህ ሳማቸው የሚል ስሜት ወረረኝ። ስሜቴን ያወቁብኝ ስለመሰለኝ በዙርያዬ ያሉትን ሰዎች ተመለከትኩኝ፡፡

ከጠሀዩና በታክሲ ጥበቃ ከመሰላቸታቸዉ የተነሳ ታክሲዎቹን አቅፌ ስሜ ቢሆን እንኳን የታክሲዎቹ በር እስካልተከፈተ ድረስ ቁብ የሚሰጣቸው አይመስሉም ፡፡ አንዳንዶቹ ታክሲ ጠባቂው ከመብዛቱ የተነሳ አንድ ወይ ሁለት ተሳፋሪ የጎደለው ታክሲ ቢመጣ እንዴት ተጋፍተው እንደሚገቡ ተጨንቀዋል፤ አንዳንዶቹ ለጠብ እንደተጋበዙ ክናዳቸዉን ሰብሰበው
በተጠንቀቅ ቆመዋል፡፡ ሰዓቴን ስመለከት ለቀጠሮዬ ሁለት ሰዓት ይቀረኛል፡፡

በነገራችን ላይ አልጨረስኩም 💃💃💃........

ግን React.ያስፈልጋል 👍
                       👇
💗💗# እንማር** 💓💓
   
         🌹 🌹
                      👇
     
 https://www.tg-me.com/ethioleboled
💥📚ኢትዮ-ልቦለድ📚📖💥
Photo
👱‍♀👱‍♀👱‍♀ ቲናዬ ደወለች 📞📞📞

       📚📚.... 2⃣📚📚

                        

..አይሰለቸኝ እኔ አንቺን ለመጠበቅ
ልቤ ጓጉቷል (ተጨንቋል) እንጂ ምክንያቱን ለማወቅ
ምክንያቱን ለማወቅ
መጣው ብለሽ
መጣሁ
ስትዘገይ እ
እሰጋለሁ

ምን አገኛ
ት ብዬ …… ስትዘገይ እኔ እሰጋለው
ደግሞ እጨነቃለው … ስትዘገይ እኔ እሰጋለው
በሩን እከፍትና ………ስትዘገይ እኔ እሰጋለው
ደጅ ደጁን አያለው ……ስትዘገይ እኔ እሰጋለው

መጥታስ ቢሆን ማን አያት ሄዶ 2x
መጥታስ ቢሆን ማን አያት
ልቤ እንጂነው ሊያገኛት ብሎ
አላርፍ ያለው ቸኩሎ

የመኪናው መንገድ ውሃና ፍሳሽ በስተግራ፤ ቴሌ በስተቀኝ ባስቆፈሩት ጉድጓድ ምክንያት ስለተዘጋጋ፣ የተቀጣጠርንበት ካፌ ለመድረስ በታክሲ
ብሄድ አርባ ደቂቃ፤ በእግር ብሄድ ደግሞ አስራ አምስት ደቂቃ እንደሚፈጅብኝ ገመትኩኝና ከአጀቡ ወጣሁ፡፡ ለስንብትና አይዟችሁ ለማለት አጅበውኝና አጅቤአቸው የነበሩ ምስኪኖችን ዞር ብዬ
ቃኘሁኝ፡፡ እራሱን የሚወደው፣ ታክሲ ተደርድረው ከሚጠብቁት እልፍ
አዕላፋት መሀል ተነጥቆ ወጥቶ ‹አንድ ሰው ብቻ!› እያለ አመልካች ጣቱን ቀስሮ፣
የታክሲ ረዳቶች እንዲመለከቱትና እንዲመርጡት ይማጸናል፡፡ እራሱን የጠላው ድሮ በስሙኒ ይሸጥ ለነበረ ገመድ አሥር ብር ከፍሎ ገዝቶ እራሱን ሊያጠፋ እያጉተመተመ ያልፋል፡፡
ለፍጥነትና ለጤንነት በእ
ግር መሄዱን
መርጬ መንገድ ጀመርኩኝ፡፡

**ቲናን እያሰብኩኝ ከቁፋሮው በተረፈ ቀጫጫ መንገድ ላይ በገመድ ላይ እንደሚሄድ የ‹ሰርከስ› ባለሙያ ሚዛኔን ለመጠበቅ እጆቼን እንደ አሞራ እየዘረጋሁና እያጠፍኩ ተራመድኩኝ፡፡ ኋላም ጫማዬን
በአቧራ በጽኑ አቆሽሼ፣ በአሥር ደቂቃ ውስጥ ካፌው በር ጋ ደረስኩኝ፡፡**

የዘንድሮ ሰው ከፊት ይልቅ እግር እግር ነው የሚያየው ብዬ ቲናዬ ቀድማኝ ወደ ካፌው እንዳልገባች አንገቴን አሾልኬ
ካረጋገጥኩኝ በኋላ ጫማዬን ለማስጠረግ አስፋልት ተሻግረው
ወዳሉ ሊስትሮዎች አቀናሁ፡፡

ጫማዬን ለሊስትሮው አደራ ሰጥቼ ቲናዬ ስትገባ ለማየት በዓይኔ የካፌውን በር መጠበቅ ጀመርኩ፡፡ የካፌው ባለቤት ይሄንን ቢያውቅ ጥበቃውን እንደሚያባርረው እርግጠኛ ነኝ፡፡ ካፌው ያለበት ሕንፃ ድሮ ተጀምሮ በቅርብ ነው ተሰርቶ ያለቀው፡፡ ይህ ሕንፃ እንደ ብዙዎቹ የአዲስ አበባ ሕንፃዎች ‹በእግዝያብሔር ያውቃል› ተጀምሮ ከዛም የታችኛውን ወለል ለባንክ በማከራየት ፍጻሜውን አሳምሯል፡፡የባንኩ ደንበኞችም ከአሁን አሁን ብሎኬት ወደቀብን፤ በሚስማር የተንቆጠቆጠ አጣና የአዲሳባ ኑሮ ያጎበጠው ጀርባችን ላይ ተሰካብን፤ ሲሚንቶ ቦነነብን ብለው ከመሳቀቅ ድነዋል::

**የባንኩ በር ላይ ‹እንኳን ለበዓሉ አደረሳችሁ› የሚል ባነር ተሰቅሏል፡፡ ለየትኛው በዓል? በቅርብ ያለፈውንና በቅርብ የሚመጣውን በዓላት አስቤ ግራ ተጋባሁ፡፡ ግራ መጋባቴን ያስተዋሉ፤ ከጎኔ ቁጭ ብለው ጫማ የሚያስጠርጉ አዛውንት፤ ‹‹ይህቺን በየበዓሉ ከሦስት መቶ እስከ አራት መቶ ብር ልታድን
የምትችል የወጪ ቅነሳ ዘዴን ሁሉም ባንኮች ይጠቀሙባታል፡፡**

እንደውም በባንኮች የጋራ ጉባዔ የተወሰነች ሳትሆን አትቀርም።

ተራ ካፌ እንኳን የበዓላቱን ሥም እየጠቀሰ ‹እንኳን አደረሳችሁ› እያለ ባነር አሠርቶ ሲሰቅልና መስታወት ላይ ሲያጽፍ፤ በዓመት ለኛ ብለው ያተረፉ ይመስል ‘እንኳን ደስ አላችሁ ይሄን ያክል ቢሊዮን ዓመታዊ ትርፍ አተረፍን፤ ይሄን ያክል መቶ ሚሊየኖች የተጣራ ትርፍ አገኘን’
የሚሉት ባንኮች፤ ከዓመት እስከ ዓመት ‘እንኳን ለበዓሉ አደረሳችሁ’ የሚል ጥሁፍ ደጃቸው ላይ ያንጠለጥላሉ፡፡››
‹‹እንደዛ በማድረጋቸው ቢሆንስ ያተረፉት?›› አልኳቸው በሆዴ፡ሽማግሌው ቀጠሉ፤**

‹‹ደግሞስ ባለ ንግድ ቤቶች ዶሮና ስጋ ከሚበላባቸው የበዓል ቀናት በተጨማሪ እንኳን ለየካቲት ሃያ ሦስት አደረሳችሁ፤ አንኳን ለሚያዝያ ሃያ ሰባት አደረሳችሁ፤ እንኳን ለመስከረም ሁለት አደረሳችሁ፣ እንኳን ለግንቦት ሃያ አደረሳችሁ የሚሉ መልካም ምኞትን የሚገልጹ ጽሑፎችን ቢለጥፉስ?›› አሉና ወደ ጫማቸዉ
ተመለሱ፡፡ሰውየው ቲናዬን ሊያስመልጡኝ ነው እንዴ? ድንገት ከእግሬ ስር ኳ ኳ የሚል ድምጽ ሰማሁ።**

‹‹ግቢ ቲናዬ!›› አልኩኝ ሳላስበው፡፡ ሊስትሮው ከገላመጠኝ በኋላ እግሬን ገፍትሮ አውርዶ አላስችል እንዳለው፣ ሌላኛውን እግሬን አንከብክቦ አንስቶ የሊስትሮው ሳጥን ላይ ሰቀለው፡፡

ሊስትሮው የሌላኛውን እግሬን
ጫማ ጠርጎ ሲጨርስ ድጋሚ አንኳኳልኝ፡፡ ከፍዬው ወደ ካፌው አመራሁ፡፡

ካፌ ውስጥ ሁለት ጥንዶች፤ ሁለት ነጠላዎችና አንድ ቤተሰብ ተቀምጠው ትኩስና ቀዝቃዛ መጠጦችን ከክሬምና ደረቅ ኬኮች ጋር እያዋደዱ ይጠቀማሉ፡፡ ካፌው ሀገራችን ውስጥ ያለውን የጥንድና የነጠላ እንዲሁም የቤተሰብ ቁጥር፣ ስብጥርና ስርጭት የሚያሳይ ‹ቻርት› መሰለኝ፡፡ በሀገራችን ተመጣጣኝ ጥንዶችና ነጠላዎች ቁጥር አለ፡፡ እነዚህ ግን በቂ የሆነ ቤተሰብ መመስረት አልቻሉም፡፡

የቲ
ናን መምጣት ማየት እንዲያስችለኝ ወደዉጪ የሚያሳየዉ መስታወት አጠገብ ካለ ወንበር ላይ ተቀመጥኩኝ

በነገራችን ላይ አላለቀም ..

👉Like
አትርሱ እንዲቀጥል
     እኔ ሺ ፊደል ተጫንኩ እናንተስ ?👍

 ቀጣዩን

Https://www.tg-me.com/ethioleboled
👱‍♀👱‍♀👱‍♀ ቲናዬ ደወለች 📞📞📞



       📚📚 ..... 3⃣ 📚📚

**የሰዉ ምሥጢር መስማት ስለማልወድና ሰዉ ምሥጢሬን እንዲሰማ ስለማልፈልግ
ካፌ እጠላለሁ፡፡**

ብዙ ጊዜ ካፌ ዉስጥ ለሌላ ሰዉ ለቀለድኩት የማያገባዉ ተስተናጋጅ ሲስቅና አንዳንዴም አብሮኝ ያለን ሰዉ ለጠየቅኩት ጥያቄ የማላዉቀዉ ሰዉ ግሩም መልስና ማብራርያ ሲሰጥ ደርሼበታለዉ፡፡

በዚህ ምክንያት ለስለስ ያለ መዚቃ የሚንቆረቆርበትና ሴት አስተናጋጅ የሌለበት መጠጥ ቤት አዝወትራለዉ፡፡ ሰዉም ስቀጥር እዛ ነዉ፡፡

እዛ እንደጣዎት ማንም ማንንም አያይም፣ አይሰማም፣ ማንም ለማያዉቀዉ አያወራም፡፡ ጨዋታዉ አብሮ ካለ ሰዉ ጋር አልያም ከመጠጥና ከሙዚቃ ጋር ብቻ ነዉ፡፡ አንድ ሻይ አዝዘህ ብዙ ተቀመጥክ አንዳይሉኝና አሥር ጊዜ እየመጡ፤ ጠረጴዛዉን እራሱ መጽዳት ባለበት ፎጣ እንዳያጸዱብኝ
በማሰብ ባለሁለት ሌትሩን ዉሃ አዝዤ ዓይኔን ከመስታወቱ ባሻገር
ካለዉ መንገድ ላይ ተከልኩኝ፡፡ ለሠላሳ ደቂቃ ያህል መንገዱ ላይ ፈዝዤ ጠበኳት - ብቅ አላለችም፡፡ ያዘዝሁት ዉሃ ሞቀ፡፡ በሰላሳ ደቂቃ ዉስጥ ቲናዬ እንዳታመልጠኝ ዓይኔን ለሦስት ጊዜ ብቻ ነዉ ያርገበገብግኩት፡፡ እሱም ቢሆን የቲናዬን ፈገግታ ዳግም ሳላይ
ዓይነ-ዉሃዬ እንዳይደርቅ በማሰብ ነዉ። ምናልባት በዛ ቅጽበት ቲናዬ ካፌ ዉስጥ ገብታ እንዳይሆን ብዬ ካፌውን ቃኘሁኝ፡፡
ቲና የለችም፡፡ ካፌ ውስጥ የነበሩት ሰዎች ተለዋውጠዋል፡፡ ቤተሰብ
ተቀምጦበት የነበረው ቦታ ላይ ኬክ ያማራት የምትመስል እርጉዝ ሴት፣ ብዙ ልጆችን የመውለድ ልምድ ያላት ከምትመስል ሴት ጋር ቁጭ ብላለች፡፡

እርጉዟ ያዘዘችው ኬክ ላይ የተከለችውን ሹካ ሳትነቅል እጇን እያወራጨች የጦፈ ወሬ ታወራለች፡፡ ሴትየዋ ወሬ ነው ያማራት ወይስ ኬክ? ምናልባት ያስረገዛት ሰው የማውራት እድል አይሰጣት ይሆናል፡፡ የምጠላውን የሰው ምስጢር መስማት ጀመርኩኝ፤
‹‹አይገርምሽም ግን ጉራው? ያቺን የመሰለች ልጅ አግኝቼለት ‹ተማሪ ናት ወይስ ሰራተኛ?› አለኝ። ‹ኧረ! ገና ተማሪ ናት› አልኩት፡፡ ‹ኮሌጅ?› ሲለኝ ‹ገና አሥረኛ ክፍል ናት፤ ብዙ ነገር አለመደችም፤ ላንተ ጥሩ ናት› አልኩት፡፡ ‹የማታ መሆን አለባት!› አለኝ። ‹አንተ
የማታ ትሁን የቀን ምን ቸገረህ? ደግሞ የቀን ነው የምትማረው፣ ቢበዛ ይሄን ዓመት እስክትጨርስ ብትታገሳት ነዉ፡፡› እለዋለሁ፣ ምን እንዳለኝ ታውቂያለሽ? ‹ምን ማለትሽ ነው? ላሳድጋት ነው ወይስ
ላገባት? የአሁን ዘመን ሴቶች እንደናንተ ጊዜ ትምህርት በአስራ ስምንት አመታቸው የሚጀምሩ መሰለሽ እንዴ? ስንት ዓመቷ ሊሆን እንደሚችል ገምተሻል? እኔ እኮ በትዳር መታሰር እንጂ ለአቅመ ሄዋን ያልደረሰች ሴት በማግባት መታሰር አላልኩሽም› ብሎኝ
እርፍ፡፡›› እርጉዟ ተንገበገበች፡፡

ከደቂቃዎች በፊት እንደኔ ሌጣቸውን ከነበሩት ሁለት ነጠላዎች መካከል አንደኛዉ ካፌውን ለቆ ሄዷል፤ ሌላኛው ደግሞ ጓደኛው መጥታ ወደ ጥንዶቹ ጎራ ተቀላቅሏል፡፡ የኔም ዕድል ከሁለቱ
አማራጮች አይዘልም፡፡ ቲናዬ መጥታልኝ ጥንድ መሆን ወይም ቀርታ ተነስቶ መውጣት፡፡ እሱን ለማወቅ ደግሞ አንድ ሰዓት የሚሆን አለኝ፡፡ ወጣቱ ጓደኛው በመምጣቷ ከቅድሙ በተለየ ፊቱ ላይ
መረጋጋትና እርካታ ይታያል፡፡ በውስጤ በረከትህ ይደርብኝ ብዬ ጸለይኩኝ፡፡
ከሠላሳ ደቂቃ በፊት ካፌ ውስጥ የነበሩት ጥንዶች ወጥተው ሄደዋል፡፡ ብቻ ቲናዬ ትምጣልኝ እንጂ ካፌ ውስጥ የተከሰተውን የጥንዶች እጥረት እንቀርፈዋለን። ዓይኔን ወደ መንገዱ ሰድጄ ቲናን መፈለግ ጀመርኩ - ብቅም አላለችም፡፡ ድንገት መንገድ ላይ
የተዋወቁ የሚመስሉ ጥንዶች ወደ ካፌው ዘለቁ፡፡ ሴቲቱ መንገድ ላይ ብዙ ስታወራው ቆይታለች መሰል ጎረምሳው ፊት ላይ መሰላቸት ይታይበታል፡፡

ዓይኖቼን ከመንገዱ ነቅዬ፣ ሰዎቹን አጅቤ አጠገቤ ካለው መቀመጫ ጋ አደረስኳቸው፡፡ አስተናጋጅ መጥቶ ትእዛዝ ተቀብሎ ከመሄዱ ሴቲቱ ወሬዋን ቀጠለች፡፡
‹‹ቅድም እንደነገርኩህ እኔ እንደሌሎቹ ሴቶች አይደለሁም!››
ጎረምሳዉ ፋታ አገኘሁ ብሎ ሊጀምረው የነበረውን ጨዋታ መልሶ ዋጠው። ማንቁርቱ ከፍ ዝቅ አለች፡፡ ልጅቱ ድምጿን ለማሳመር በአፍንጫዋ ነው የምታወራው፡፡ ‹‹በቃ እኔ ሴት ነኝና እንክብካቤ ይደረግልኝ ምናምን አልልም፡፡ ‹ላይክ› ሴት ስለሆንኩ አለ አይደል ‹አፈርማቲቭ አክሽን ኦር›…
ምናምን አልፈልግም፡፡ ምንም የተለየ ድጋፍ ምናምን አልፈልግም››
‹‹በቃ በአጠቃላይ ምንም ምናምን አትፈልጊም ማለት ነው?›› አላት፡፡
‹‹በቃ ምን መሰለህ! አኔ እራሴን ከወንድ እኩል ነኝ ብዬ አምናለሁ፡፡
እኩል ስለሆነ ነገር ደግሞ ሁልጊዜ መወራት የለበትም፡፡ ‹ኢቭን› እኛ ሴቶች ከወንዶች እኩል ነን ካልን፣ ‹ዊ ዶን ኢቭን ኒድ ማርች ኤይት ምናምን! ዩ ኖዉ? ዱ ዩ አንደርስታንድ ሚ?› ግን በቃ ለማለት
የፈለኩት ሴት ስለሆንን ብቻ ለወንድ የማይደረግ ምንም አይነት የተለየ ድጋፍ አያስፈልገንም-- በተለይ እኔ አልፈልግም፡፡

‹አም ካፔብል ኦፍ ዱይንግ ኤኒቲንግ!›››
‹‹የሴቶች ሽንት ቤትም ቢሆን መጠቀም አትፈልጊም ማለት ነዋ?›› አሳ አጥማጅ መረቡን ወደ ባህር እንደሚጥለው፣ ዓይኔን መስታወቱን አሻግሬ ወደ መንገድ ወረወርኩት፡፡ የቲናዬ መምጫዋ
ወይ መቅርያዋ ሰዓት እየደረሰ ነው፡፡ መንገዱ ላይ ብዙ ሴቶች ሲያልፉና ሲያገድሙ ቢታዩም ቲናዬ ከመካከላቸው የለችም፡፡ ለመጽናናት ስል ዓይኔን ከብቸኝነት ወደ ጥንድነት የደረጃ ዕድገት
ያገኘው ጎረምሳ ወዳለበት ጠረጴዛ ላኩኝ፡፡ ጎረምሳው መርዶ በሚያረዳ ድምጽ እያወራ ው፡፡
‹‹ሃኒዬ የምስራች!››
‹‹ምን? የምን የምስራች ነው? እሺ ምስር ብላ! ግን ደግሞ ምስር ጨጓራዬን ያመኛል ትላለህ አይደል? እሺ አተር ክክ ብላ! በቃ ደስ ያለህን ብላ!›› ተርበተበተች፡፡

አልጨረስኩም
Https://www.tg-me.com/ethioleboled
👱‍♀👱‍♀👱‍♀ ቲናዬ ደወለች 📞📞📞
    (በእውነተኛ ታሪክ የተመሰረተ)

       📚📚የመጨረሻ ክፍል 📚📚

‹‹ምን? የምን የምስራች ነው? እሺ ምስር ብላ! ግን ደግሞ ምስር ጨጓራዬን ያመኛል ትላለህ አይደል? እሺ አተር ክክ ብላ! በቃ ደስ ያለህን ብላ!›› ተርበተበተች፡፡

‹‹ችግር የለውም ሃኒዬ!›› ለአፍታ በዝምታ ከቆየ በኋላ፤
‹‹ሃኒዬ አርግዘሻል!››
‹‹ምን?! ማን? እኔ? ከማን?››
‹‹ከእኔ ነዋ! ምን ማለት ፈልገሽ ነው?››
‹‹እንዴት ሊሆን ይችላል? አላውቅልህም! የራስህ ጉዳይ!››
ተመናጭቃ በተቀመጠበት ጥላው ወጣች፡፡ ሴቷ ማርገዟን ካደች፡፡ ወንዱ በእንባ ታጠበ፡፡ ቲናዬ ስትመጣ ምናለ ካፌው እንደ ታክሲው ተጣቦ አስተናጋጁ
‹ተጠጋላት› ብሎ ቢያስጠጋኝ? አስተናጋጁ ግን የጠናን ያህል ልብ
ያለው አይመስልም፡፡ እኔ ካፌ አይቀናኝም፡፡ የእኔ እጣ ፈንታ
የተቆራኘው ከታክሲ ጋር ነዉ፡፡ ብዙ የሴት ጓደኞቼን የተዋወቅኋቸው ታክሲ ዉስጥ ነዉ። ቲናዬን የመሰለች ልጅ ግን ተዋዉቄ አላውቅም ነበር፡፡

ያውም በግድ ካልተጠጋህላት ተብዬ፡፡ ጠና ባለውለታዬ! ጠና ባለ ሁለት ጸጉሩ አንጋፋው የታክሲ ረዳት! ከአያቴ በታች በዘር ማንዘራችን የታክሲን ስራ ያልሠራ የለም፡፡ እኔ ብቻ ነኝ የዘሬ አያንዘርዝረኝ! አሻፈረኝ ብዬ የመንግስት ሥራ
የምሠራው፡፡ ኮሌጅ የሚያስተምረው አጎቴ እራሱ የታክሲ ስራ ሱስ
ተጠናውቶት ጠዋት ወደ ስራ ቦታው ሲሄድ ወደዛ አቅጣጫ የሚሄዱ
ተሳፋሪዎችን ይጭናል። ባጋጣሚ ታክሲ ውስጥ ተማሪዎቹን ካገኘ ሂሳብ አንዲቀበሉለት ያደርጋል፡፡ ሂሳብ የተቀበለለት ተማሪን ሂሳብ አያስከፍለውም፤ ‹ግሬድ›ም ከ‹ሲ› በታች አይሰጠውም፡፡ ባለ ሁለት ጠጉሩ የታክሲ ረዳት ጠናም ቢሆን በበፊቱ ወያላነቱን በአሁኑ ረዳትነቱን ከአያቴ ጋር ነው የጀመረው፡፡

እኔ እንደ ቤተሰቦቼ በታክሲ ሥራ ገቢ ባላገኝም ብዙ የሴት ጓደኞችን አግኝቻለሁ፡፡ አሁን ደግሞ ከሴቶች ሁሉ የምትበልጠውን ቲናዬን አገኘሁ፡፡ ቲናዬ ብቅ አላለችም፡፡ ሰዓቴን ስመለከት ቀጠሯችን አምስት ደቂቃ ቀርቶታል፡፡ ጨነቀኝ፡፡ እናቴ እኔን ለመውለድ ስታምጥ
ያለ ዓይነት ላብ ፊቴ ላይ ችፍፍ አለ፡፡ አምስቱ ደቂቃ ዘላለም ሆነብኝ፡፡ መንገዱን አሻግሬ ማየትና ቲናዬን መንገዱ ላይ ፈልጌ ማጣት ፈራሁ፡፡
ጥቁር የጸሀይ መነጥሬን ከሰካሁኝ በኋላ አይኔን ጨፈንኩኝ፡፡ ወደ ካፌው የሚገባ አዲስ ኮቴ ካለ ብዬ ጆሮዬን አንቅቼ ጠበቅሁኝ፡፡

አምስት ደቂቃ ከሚቀረኝ አምስት ሰዓት ቢቀረኝ ተመኘሁ። እንደማይሆን ከማወቅ በተስፋ መጠበቁ ይሻላል። አሁን ግን
አማራጭ የለኝም፤ ከደቂቃዎች በኋላ ቲናዬን ከእነ ፈገግታዋ አጠገቤ አገኛታለሁ አልያም ስለሷ አቆሽሼ ባስጠረኩት ጫማዬ ከቴሌና ውሃና ፍሳሽ ቁፋሮ የተረፈውን መንገድ በብስጭት
እየቆፈርኩኝ ወደ ቤቴ አዘግማለሁ፡፡
ስልኬ ጠራ፡፡ ቲና ደወለች መሰለኝ፡፡ የጨፈንኩትን አይኔን መግለጥ ፈራሁ፡፡ እየመጣሁ ነው ወይስ ይቅርታ ስላስጠበኩህ ልትለኝ ነው?
ደርሻለሁ በሩ ላይ ነኝ ልትለኝ ነው? ወይስ ይኸው ከቤት እየወጣሁ
ነው ልትለኝ ነው? እልል ልበል ወይስ…? ደግሞ እርሷ ባትሆንስ የደወለችው? በርግጠኝነት በዚህ ሰዓት የደወለልኝ ሌላ ሰው ከሆነ መቃብሬ ላይ አይቆምም፤ እኔም መቃብሩ ላይ አልቆምም፡፡

ነገር ግን የማንም ቀብር ላይ መቅረት አልፈልግም፤ ማንም ከቀብሬ
እንዲቀርም አልፈልግም፡፡ ስልኬን አውጥቼ ማየት ፈራሁ፡፡ ቢሆንም ቁርጤን ማወቅ አለብኝ ... እድሜዬ 38 እየተጠጋ ላለ ወደ እርጅና ለሚያመራና እናቱ አግባ አግባ እያለች ለምትወተውተው ጎልማሳ ሁሉም ነገር ይጨንቀዋል ። ስልኩን አነሳሁት ....
ᐸᐸ ሄሎ ...>> አለኝ ጎርነን ያለ ድምፅ አቤት ማን ልበል ... አልኩኝ በውስጤ ᐸᐸወይኔ ሸወደችኝ ወይኔ ሳሚ ... ተበሳጨሁ !>> አልኩኝ በልቤ ። ሰውየው ቀጠለ ...
ᐸᐸ ስልክህን ያገኘነው ከስልኩ ባለቤት Contact ላይ ነው ... ይህን ስልክ ታውቀዋለህ...?>> አዎ አልኩት ግራ በመጋባት ። ᐸᐸከስልኩ ባለቤት ጋር ዝምድና አለህ..?>> አለኝ። አዎ በማለት ጓደኛዋ እንደሆንኩ አስረዳሁት ማንነቱንም እንዲነግረኝ ጠየቅኩት ። ᐸᐸ እኔ ዶክተር አስረስ እባላለሁ የዘውዲቱ ሆስፒታል የጭንቅላት ስፔሻሊስት ነኝ ተከስቶ በነበረ የመኪና አደጋ ሆስፒታላችን ለህክምና መጥታ የቻልነውን ጥረት ብናደርግም አልተሳካም ህይወቷ አልፏል ... አዝናለሁ ።>>
ባለሁበት ፀጥ አልኩኝ ከት ብዬ ሳቅኩ😂😂😂😂 እንደገና ማልቀስ ጀመርኩ 😭😭😭 ሳቅና እምባ ተጋጩብኝ ሳቅ የቱ ነው እንባ የቱ ነው ... እባካችሁ ንገሩኝ ... ከፊቴ ያለውን ጠረጴዛ ወረወርኩት ካፌ ውስጥ ያለው ሰው ሁሉ እንደ እብድ ተመለከተኝ ... ᐸᐸቲናዬ ቲናዬ.. እያልኩ ወጣሁ ወደ ዚያች ቦታም አልመጣሁም ወደ ራሴም አልተመለስኩም ።>>
😭😭😭  ተፈፀመ  😭😭😭

ምን ተክቼ ልርሳ መውደዴን በምኔ
ሰው በሰው መተኪያ ላያገኝም ጎኔ
ያ ፅኑ ፍቅርሽ ጀግኖ ሀይሏል
ስምንም ሰባብሮ ናፍቆትሽ ሰው ጥሏል
2x

ተጫዋችነት ፈገግታዬ ጠፍቶ
ባይተዋርነት ትካዜዬ በዝቶ
ልቤን ከፍቅሬ ጋር እኔ ልኬልሽ
ትዝታን አማጥኩልሽ

ልረሳሽ አልቻልኩም ፍቅርሽ ረቶኛል
ልለይሽ አልፈቅድም ጭራሽ ሸብቦኛል
ምንድነው መፍትሔው
መላው ብልሀቱ
መላ ካንቺ ካለ
መላ በይኝ እቱ

ሰበብ ሆነ ምክኒያት ጊዜ ቦታ አይመርጥ
ፍቅርሽ ሲያብከነክን ውበትሽ ሲገለጥ
ትዝታሽ ነቃቅቶ እግሬ ተቀስቅሶ
መብሰክሰክ መንደዴን ባየልኝ ደርሶ 2x

ተጫዋችነት ፈገግታዬ ጠፍቶ
ባይተዋርነት ትካዜ በዝቶ

ከጎኔ መራቅሽን ልቤ እያወቀው
ላልተጨነቀው

ልረሳሽ አልቻልኩም ፍቅርሽ ረቶኛል
ልለይሽ አልፈቅድም ጭራሽ ሸብቦኛል
ምንድነው መፍትሔው
መላው ብልሀቱ
መላ ካንቺ ካለ
መላ በይኝ እቱ

እስቲ የተሰማችሁን ግለፁ 😭  😱

      .📚
ፍቅር እስከ መቃብር ሀዲስ አለማየሁ.pdf
5.9 MB
  📓 ፍቅር እስከ መቃብር(በPdf)
         ✍️ ሀዲስ አለማየሁ

📚 @ethioleboled
Forwarded from 🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁
በየቀኑ ባነበውም በየቀኑ ይገርመኛል
.
ከእለታት አንድ ቀን ነቢዩ ሙሐመድ ሰ.ዐ.ወ ዘንድ አንድ
ከገጠርየመጣ ኑሮው ያልሰመረለት (ድሃ) ግለሰብ ሰሃን
ሙሉ ወይን ስጦታ ያመጣላቸዋል፡፡ነቢዩም ሰ.ዐ.ወ
ስጦታውን ተቀብለው ወይኑን መብላት
ጀመሩ..የመጀሪያውን ጎርሰው ፈገግ አሉ..ሁለተኛውንም
ጎርሰው ፈገግ አሉ..ግለሰቡም እጅጉን ተደሰተ..የነቢዩ
ጓዶች (ሰሃቦች) ሁሌም ለነቢዩ ሰ.ዐ.ወ ስጦታ
ሲመጣላቸው ስለሚያካፍሏቸው ይህንን (ጣፋጭ) ወይን
እንዲያካፍሏቸው በጉጉት ይጠብቃሉ..የአላህ መልእክተኛ
ግን ሳያካፍሏቸው እያንዳንዱን የወይን ፍሬ እየበሉ እና
ፈገግ እያሉ ሁሉንም በልተው ጨረሱ.. ስጦታ አቅራቢው
እጅግ በጣም ተደሰቶ..ስጦታውንም ስለወደዱለት
አመስግኖ ሄደ..አንድ የነቢይ
ሰ.ዐ.ወ ጓድ (ሰሃባ) ጠጋ ብሎ ነቢዩን ጠየቃቸው
‹‹የአላህ መልእከተኛ ሆይ..ምነው ሳያካፍሉን?››
እሳቸውም ሰ.ዐ.ወ
ፈገግ ብለው መለሱ ‹‹ሰወዬው መደሱቱን አይታችኋል
አይደል?!..
ወይኑን ስቀምሰው በጣም ይመር ነበር..ባካፍላችሁ
አንዳችሁ  
ግለሰቡን የሚያስከፋ እና ደስታውን የሚያደፈርስበትን ነገር
እንዳታሳዩት ብየ ስለሰጋሁ ነው ብለው መለሱላቸው;;;;; ሀቢቢ  የኔ  ነቢይ  እናቴም  አባቴም  ህይወቴም  ፊዳ  ይሁንሎት።🥰🥰🥰🥰
@Meki3
Https://www.tg-me.com/ethioleboled
Forwarded from 🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁
የኛ ሰፈር....1




ማሸነፍና መሸነፍ የማይለይበት...ማግኘት የማጣትን እኩል የሆነበት...ጥላቻው ላይ የኑሮ ውድነቱ ተደምሮ አንድነት የሚቀነስበት...እንዲያም ሆኖ ሁሉም በዘመን የሚሳበብበት...

ዛሬ ደሞ ብዬ ብዬ
"እንባሽን ቢያደርገኝ
ከጉንጮችሽ ቢያወርደኝ"...እያለ አውላላ ሜዳ ላይ በሚያላዝነው ሰካራም መቅናት ጀመርኩ...ታድሎ...በዚህ ኑሮ እሳት በሆነበት ጊዜ ለአረቄ ገንዘብ ማውጣቱ ሳያንስ እንባ መሆን ይመኛል...ከዛ በጉንጮቿ መውረድ...ኑሮ መረረ...ጦርነት ከረረ...ሰላም ወረደ እሱን አይገደውም...


"መርቂልኝ እንጂ"

"ሴትዮ መተው ትችያለሽ!ከአባቴ እርሻ የቀነጠስኩት ሳር አይደለም!!!"

"ኧረ ወዲያ መልሺው እናንተ ነጋዴዎች ስትባሉ ገብጋቦች ናችሁ"

"አምጪው ድሮም እንካ ያሉት እቃ ርካሽ ነው"....ከሰካራሙ ላመል ራቅ ብለው ያሉ ገዢና ሻጮች በፊናቸው ጭቅጭቁን አድርተውታል....

"ካልሲ ባስር...ካልሲዋን ባስር...አጋጣሚ ነው ...እ ቆንጅዬ ይቺን ላንቺ."...

"ግራና ቀኙ እኩል አይደለም እኮ"

"አይንሽ አይሰራም እንዴ እየሄድሽ እየሄድሽ..ብራንዷን ባስር ...ብራንድ ለባሽ."...እዚጋ ደሞ ጉሮሮው እስኪሰነጠቅ ይጮሀል...



"ስለ አይነ ብርሀን...ስለ እመቤቴ ሰርቼ ማልበላ ...ስለ እመብርሀን ብርሀኖቼ..."...የየኔቢጤው ድምፅ ከሩቅ ይጣራል...እጄ ላይ ያለውን 1 ብር ልሰጠው አስቤ ወዲያው ደሞ ተውኩት..ትንሽነቱ አሰጋኝ።

የሆነ ነገሬ አንድ ብር ይዘሽ ከምትወጪ እንደሚታነቅ ሰው ባዶ እጅሽን ብትወጪ ይሻል ነበር አለኝ...የሆነ ነገሬ አከለና እንደውም ብትታነቂ ለሁላችንም ጥሩ ነው አለኝ። እንዲህ ውስጤ ካሉት ሰይጣናት ጋር ስነታረክ የኔቢጤው አልፎኝ ሄደ።ምናል እግዜር ይስጥልን እንኳን ብለው ብዬ በውስጤ ስቆጭ ደግሞ ቅድም ንትርኩ ያመለጠው ሰይጣን "እስቲ ለራስሽ በሰጠሽና... እኔም እንደ ወዳጆቼ ጮማ ብቆረጥም...በዚሁ ከቀጠልሽ ያለፀበል በፍቃደኝነት ብን ብዬ መሄዴ አይቀርም" አለኝ።


ቤቴ ስገባ እናቴ ለታናሽ ወንድሜ ከእኔ በላይ የምትሳሳለትን ነጠላ በወግ በወጉ ቀዳ ለሽንት ጨርቅ ስታመቻች ደረስኩ...ቀጥላም የተራቆተውን ወንድሜን ከነጠላው ጋር ላስቲክ ደምራ አሰረችለት።

"እማ" አልኩኝ እንደ ጅብራ ተገትሬ

"ምን ላርግሽ"...የእሷ መልስ ነበር...ደነገጥኩ...ነብስ እስካወቅኩበት ጊዜ ድረስ እማ ለሚለው ጥሪ ከወዬ ሌላ መልስ ያለ አይመስለኝም ነበር።ኑሮው የእናቴንም መልስ ቀየረው....
ፈራ ተባ እያልኩ "በዚህ ዘመን ሽንት ጨርቅ አይከብድም..?ኧረ ሼም ነው"አልኩኝና አንገቴን ሰበርኩ።

"ኧረ ሼም...እሺ የሞጃ ልጅ ሼም ዳይፐር ይሆናል እ ሼም እህል ይሆናል..?ገና በፈረቃ መብላት እንጀምራለን...አንቺ ሼም ስለሚይዝሽ ሼምሽን ትበያለሽ አይሻልም..?"...አለችኝ መረር ባለ ቅላፄ...

እኔም አንገቴን ለጉድ ቀብሬ ወደ ጓዳ ልገባ ስል አንድ ነገር ትኩረቴን ሳበው...የታናሽ ወንድሜ ፈገግታ አይኔን ጠለፈው...ለካ አለማወቅ እንዲህ ደስ ይላል...አለመስማት እረፍት ይሰጣል..ከሰካራሙ በላይ ቀናሁበት..



ይቀጥላል.....



ቻናሌን ምነው ፈራቹት😁



👉https://www.tg-me.com/ethioleboled
Forwarded from 🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁
የኛ ሰፈር....2




"እናቴን መቼም ይቅር አልላትም" ትለኛለች ለማኝ ሳያራ ደውላ ...ጓደኛዬ ናት...እናቷ ከዱባይ ከላከችላት እቃዎች መሀል አንዱን ስለዘነጋችባት ....

"april አይደለም አይደል....?"አልኳት ሳቄን አፍኜ

"ፅኑ እየቀለድኩ አይደለም ...ቦርሳ መርሳቷ አይደለም ያናደደኝ.. ለኔ ያላትን ቦታ ነው ያየሁት በቃ "

"ላንቺ ያላትን ቦታ"...አልኳት በግርምት

"ፅኑ አልገባሽም ".......

"ላንቺ ብላ መስሎኝ ሰው ሀገር ለሰው ሀገር የምትንከራተተው...ካንቺ ከማያልቅ የእቃ ዝርዝር መሀል አንዱን ስለረሳች ቦታሽ ተገለጠልሽ አይደል.." ንዴቴን ለመቆጣጠር እየሞከርኩ

" ትንሽ እቃ ኮ ነው ያስላኩት.."

"እሺ..ትንሽ ነው አይደል...ትንሽ ስለሆነ ለመጥቀስ አይከብድሽም "

"well ባለፈው ሽታው ገነነ አልወደድኩትም ያልሽኝን ሽቶ,
ሹራቦች (ቁጥሩ አይጠቀስም አውሺኝ ስለምላት)...
6 ጂንስ ሱሪ(ቱታ ለባሽ ሰለሆንኩ ነው ቁጥሩ የተጠቀሰው),
3 ከቱታ ጋር የማይሄድ ጫማ,
አዲሱን i-phone promax እና
የ 6 ወር የኮሌጅ ክፍያ በቃ ይቺው ናት"

"ጨረስሽ" አልኳት በታከተው ሰው ድምፅ

"አዎ ትንሽ ነው አይደል" አለችኝ ተቀለጣጥፋ....የምለውን አሳጣችኝ ለመጨረሻ ጊዜ ከአፌ የወጣው ቃል

"አታስቢ የተባልሽ ፍጥረት" የሚለው ብቻ ነው... ስልኩን ጆሮዋ ላይ ዘጋሁት...



ከተኛሁበት ፍራሽ ሳልነሳ የኔዋ መጣችና
"እስኪ ዛሬ እንፁም" አለችኝ ጆሮዬ እንኳን ሳያርፍ
"ከምንድን ነው የምንፆመው...?"...አፍጥጬ ጠየቅኩ...በውስጤ በአንደበታችን እንፁም ክፉ ሳንናገር እስከ ሆነ ሰአት እንቆይ ባለችኝ እያልኩ....

"ከምግብ ነዋ እስከዛሬ የበላነው ከአር አልዘለለ ኤድያ" አለችኝ እጇን በጥንቅር ይበል እያወናጨፈች...

"ካካካካካካ" አለመሳቅ አልቻልኩም...ከአባቴ ሞት በፊት ለሮብ አርቡ እንኳን እንደማናዝንለት ትዝ ሲለኝ....

"ቀን ሲጥል" አልኩኝ በሆዴ...እኔ ነበርኩ እናቴን ይቅር አልላትም ጨዋታ መጫወት የነበረብኝ...ይሄኔ ኤፊ ብትሆን ፍርድ ቤት ትገትራት ነበር...ፈጣሪም አውቆ ሰርቷል...በልካችን አሸክሞናል...እኛ ኮሌጅ በጥሰን አንድ የ 1ኛ ክፍል ተማሪ 2+4 ከበደው ብለን መገረም አንችልም...መታዘብም ጭምር ...ምክንያቱ ግልፅ ነው...እኛም በጊዜያችን ከብዶን ነበራ..እንዲህ ቀን ሳይጥል እኔንም በአንድ ሰሞን እንደ ኤፊ አርጎኝ ያውቅ ይሆናል....

"ብለን ብለን በሰንበት እንፁም ደግሞ ለዚ አፍ እንኳን ላልፈታ ልጅ አታስቢም...አንቺ ሳትበዪ ምንሽን ልታጠቢው ነው...?"

"ሳላስብ ቀርቼ አይደለም ልጄ እጅ አጠረኝ ታከተኝ ምን ልሁነው" እንባዋን መቆጣጠር አቃታት...እኔም አልተረፍኩም...አቅፌያት ተንሰቀሰቅኩ...ለጊዜው ላደርግላት የምችለው ይሄንን ብቻ ስለሆነ...ስሜቷን እስክቀይር ስሜቷን መጋራት...

"እማ ያልፋል" ከሳጌ ጋር እየተናነቅኩ

"አሄሄሄሄሄ እኔ እና ልጆቼ ካለፍን በኃላ ምን ያረጋል"

"ሳናልፍ አናልፍም...እኔ አለሁልሽ...ቃል እገባልሻለሁ".....

በለው!!!ስሜታዊ ሆኜ ከባድ ቃል ገባሁ.....


ቃል ገባሁ አላልኳችሁም....የመጀመሪያ ስራዬ ስራ መፈለግ...ኤፊ ጋር መደወል አለብኝ...ጆሮዋ ላይ እንደዘጋሁት ትዝ ሲለኝ መልሶ መደወሉ አሳፈረኝ...

"የምትፈልገውን ነገር ለማግኘት የማትፈልገውን ነገር ማድረግ አለብህ" የሚል motivational speech ትዝ አለኝ...ደሞ ለአፍ መቅለሉ...

አይደወል የለም ደወልኩ...
"ሄለው ኤፊ" አልኩኝ ምታየኝ ይመስል ጎንበስ ቀና እያልኩ

"ሄለው ፅኑቃል"...ስሜን ከነማዕረጉ ጠርታው እርፍ

"እ ኤፊ ባለፈው እኮ"...አላስጨረሰችኝም

"ምን ፈለግሽ..?"...በጣም ንቀት ባለው ቅላፄ

"አቤት...!" ...ለጊዜው የእናቴን እንባ ረሳሁ...ቱግ አልኩ...

"ኧረ ፅኑ ለምን እንደደወልሽ ነው ያልኩሽ ሌላ አይደለም"...ከልቧ ባይሆንም ንቀቷን ዋጥ አርጋ ይቺን ተናገረች..በክብሬ ከተመጣ ለማንም እንደማልመለስ ታውቃለች...ያው ባለኝ መሳሪያ ማለትም በምላሴ በቃሽ እስከምባል አነበንባለሁ...የኔን ምላስ የማይፈራ ከስንት አንድ ነው።

"ተገናኝተን ማወራሽ ነገር አለ።"

"oooo ዛሬ አልችልም"

"እያስፈቀድኩሽ አይደለም እየነገርኩሽ ነው..!"....ይቺን ከአማርኛ ፊልም የሰረቅዋትን ማስፈራሪያ ጣል አደረኩ ...የት አባቷ...እንደምትቦካ ስለማውቅ ሳቄን አይሆኑ ማፈን አፍኜው ነው ማወራት

"እናትሽ ሆድ ብትገቢ እንኳን አታመልጪኝም" ሚሏትን አማርኛ ልጨምርላት ወይስ "ዘጠኝ ትናንሽ ነው ማረግሽ" ብዬ ፈሷ እስኪያመልጣት ላስሩጣት....


ግን እኮ ስራ ልጠይቃት ነበር የደወልኩት...በክብሬ መጥታ ነገር አለሙን አስረሳችኝ እንጂ....ደግሞ ይሄን ሁሉ ጥጋብ በባዶ ሆድ ከየት አመጣሁት...እንጃ....ደሀ አይደለሁ አንድ አይኔን...ክብሬን ስትነካ ምን ላድርግ



ቀጣዩን ማታ 1 ሰአት ላይ ይጠብቁን....



Https://www.tg-me.com/ethioleboled
Forwarded from 🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁
የኛ ሰፈር....3


"እስቲ ችግር አታውሪብኝ" ....
አለችኝ አፏን ሞልታ...ካንዱ ሬስቶራንት ተገናኝተን ስለችግሬ ሳወራ....ያማታል እንዴ...እና ከችግር ጋር እየኖርኩ ስለ ምን ላወራ እችላለሁ...ከሱ ውጪ ምን አውቃለው...ለጊዜውም ሆነ እስከጊዜው ከችግር ጋር ተዳብለናል....ስለ እሱ አውርቼ አልጠግብም...እሱ ግን ዘመደ ብዙ ነው..ብዙሀኑን ሲያስጨንቅ ፣ ሲያስለቅስ ስለሚውል ስራ ፈቶ ስለእኔ ሲያትት አይውልም...ግን ደሞ ለእኔም አይመለስም...የምጠላው እና የምፈራው ሳልፈልግ የተጠጋኝ ባለጋራዬ ነው....

"ኤፊ ችግር ውስጥ ሆኜ ስለችግር አለማውራት አልችልም"....
"ይገባኛል ፅኑ ግን ችግርን ተወት ሲያረጉት ነው ጥሩ ካልተውሽው አይተውሽም"........አለችኝ ልሂድ ብሎኝ አትሄድም ብዬ እንዳስቀረሁት ነገር....ባነበንብባት ሙዴ ነው...ግን ጨዋ ሆንኩ....ያለመደብኝን አደብኩ...በእኔ ምላስ የእናቴ እንባ ሲረክስ ታየኝ።

"ኤፊ"......አልኳት አንዱ ቅንድቤን ከሰማየ ሰማይ ሰቅዬ ....ስኮሳተር ትደነግጣለች.....

"ooook በቃ ለቸሬ እነግረዋለሁ...የቻልኩትን እሞክራለሁ" .....ብላኝ ጅምር ላዛኛዋ ላይ ተገኘች....

"እሞክራለሁ ሳይሆን አደርገዋለሁ ነው የሚባለው"....ይሄም ካንዱ አማርኛ ፊልም የተሰረቀ ነው..
"ፅኑ ደህና ነሽ ግን ሰሞኑን ቁጣ ቁጣ እያለሽ ነው"....ትክ ብላ እያየችኝ ጠየቀች
"ደህና ነኝ ደህና ነኝ....እና ሳልረሳው ብር ከያዝሽ 2000 ብር ታበድሪኛለሽ"
"ውይ ፅኑ head set ልገዛበት የያዝኩት ነው " ....አለችኝ ክብድ ብሏት
"ችግር የለውም በቃ አትገዢማ" አልኳትና ጥብሴን በግዘፈ እንጀራ ጠቅልዬ ጎረስኩ.....እኔ ኑሮ እየዘፈነብኝ እሷ ዘፈን ስለምትሰማበት መሳሪያ ስትጨነቅ ገርሞኝ...

አኳሀኔ አስፈራት...እኔም አኳሀኗ አስፈርቶኝ አንዴ እሷን አንዴ እንዳይሰበር የምትጠነቀቅለትን ጥፍሯን እና ሰላሳ ጊዜ ወደ ቦታው የምትመልሰው ሂዩማን ሄሯን አያለሁ... አበላሌን በትዝብት ስታይ
"ምነው" አልኳት ከነ ቅንድቤ
"ምንም" ...አቀርቅራ ላዛኛዋን መቆንጠር ያዘች።


"ቆንጥሪ አንቺ ምን አለብሽ " እያልኩ በሆዴ በአፌ እብድ የሚያክል ጉርሻ ጎረስኩ.....ይሄን ጥብስ ደግሜ አላገኝ...


አውቃለሁ...ቦታችን እንደሚለያይ ...ግን ለእኔ ኤፊ ኤፊ ናት...የድሮዋ አልቃሻዋ ጓደኛዬ...


ያኔ ገና ልጅ እያለን አንዱ የኛ እኩያ ድብን አርጎ ሲስማት እሷም አረገዝኩ በቃ ከእንግዲህ ብላ ስቅስቅ ብላ ስታለቅስ ልጁን የገባበት ገብቼ ሳነክተው ፣ ደሞ ደሞ በሰው መጫወቻ ካልተጫወትኩ ብላ አሳሬን ስታበላኝ ባለቤቶቹን ደብድቤ እቃውን የግሏ ሳረገው ፣ እንዲህ እንዳሁኑ ሂውማን ሄር ሳይኖር ቁርንድድ ፀጉሯን ለማስያዝ ስሞክር ከዛ ሲታክተኝ በተልባ ለጥፌ ያን መስኮት አፏን ከፍታ እሪ ስትል በእማማ ፅጌ አስላጭቼ እፎይ ስል.....


እጅ እግራን ቡጉንጅ ሲወራት ሁሉም ልጆች ይጋባብናል ብለው ሲሸሿት ዞር ስትል እኔ ነበርኩ....ችግሬ ችግሯ እንደነበር የረሳችው ጊዜ መንገዳችን ተለየ እንጂ...ለነገሩ አጉል የሆነችው ገና ጀማሪ ስለሆነች ነው...ሲሰለቻት ማከቱን ገታ ታደርገዋለች....

ኤፍራታ የኔ ቦቅቧቃ ...ደሞ ኮ ሆዷ መላጣ ነበር... ያሁኑን አላውቅም እንጂ ....ያለ እኛ ፍቃድ መስመራችን ተለያየ...እሷ እዛኛው ጠረፍ እኔ ደግሞ ከዚህ....በመሀላችን አንድ ድልድይ


" ጓደኝነት" ...


****



በተበደርኩት ብር ኪሎ ስጋ እና ለወንድሜ ወተት ገዝቼ ገባሁ....

"ገንዘብ ከየት አመጣሽ" አለችኝ እዝን ብላ
"ለኤፊ ያበደርኩት ነበር አባ ከሚሰጠኝ ብር" አልኳትና ጥምጥም አልኩባት...ፊቴን እንድታየው እድል ከሰጠዋት ውሸቴን ስለምታውቅብኝ መደበቄ ነው...
ከእቅፏ አውጥታ "እየዋሸሽኝ ነው...?"አለችኝ አይን አይኔን እያየች
"አይ አይ እውነቴን ነው እማ"....
"ተሳቅቄ አሳቀቁሽ አይደል ልጄ ...አባትሽ ጉድ ሰራኝ ልጄ አሄሄሄ"...ብላ ማልቀስ ልትጀምር ስትል ወንድሜ ቀድሟት እሪታውን አቀለጠው.....
"ምንድን ነው ምንድን ነው አባቴ አቡቱቱቱቱ"...ብዬ መጃጃል ስጀምር ባንዴ ድዱን አሰጣልኝ....
"በይ ያዢው እስኪ የእህት ወግ ይድረስሽ እኔ ምሳ ልስራ"....ብላኝ ጉድጉድ ጀመረች.....

መክተፊያ እና ቢላዋ፣ድስት፣ቡታጋዝ፣ማማሰያ....የመሳሰሉት መስሪያ እቃዎች ሌላ ምንም የለም...አንድ ፍራሽ እና አንዳንድ ኮተት ብቻ መያዝ በሚችለው ቤታችን እንኳን ሌላ ሌላውን ስሜትንም መደበቂያ ቦታ የለም...ጭንቀቷ ባንዴ ቅልብጭ ብሎ ወጣ....


"እእእ መጣሁ እስኪ መጣሁ..."...ብላኝ ልትወጣ ስትል አስቆምኳትና ከቅድሙ ብር የተረፈኝን ሰጠኃት...የት ልትሄድ እንደነበር አውቃለሁ...ጎረቤት ሄዳ ልትዋስ....ከነዛ ሲኖራት እያሽቃበጡ ስታጣ ስም ካወጡላት ሰዎች....ደሞ ስሟን ቀይረውላታል አሉ..."የትም ወርቅ" ነበር ድሮ ድሮ ሚሏት አሁን "የለኝም" ሆኗል ስሟ....

ብዙም ባይሆን ለጊዜው ሚበቃ አስፔዛ ቢጤ ሸምታ መጣች......

ያው እንደምታውቁት የእናት ሙያ ጋር የሚደርስ የለም......ቆንጆ ወጥ ሰራች...መቼም ጥብስ ምናምን አይታሰብም........ለሶስት ቀን የሚበቃ ወጥ ሰራች...ፍሪጅ የለንም ግን home made ፍሪጅ አለን....የብረት ገንዳ እና ቀዝቃዛ ውሀ (በረዶ እንጨምርበታለን አንዳንዴ ጎረቤቶቻችንን ጠይቀን...ፊታቸው እንደተቋጠረ ነው የሚሰጡን).....እና ምን ለማለት ፈልጌ ነው ለቅርፃችን ካሰብን ደሞ ሳምንትም እንበላዋለን....በቃ እንዲህ ነው የምንኖረው...


"እንዴት እንደምነግርሽ አላውቅም"....አለችኝ በነጋታው ደውላ...ኤፊ ናት ሌላ ማን ይደውልልኛል
"ካላወቅሽ ለምን ደወልሽ...?"...ቀጠልኩ እኔ





Https://www.tg-me.com/ethioleboled
Forwarded from 🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁
ዴርቶጋዳ ሙሉ ትረካ.mp3
483.7 MB
📚ርዕስ:- ዴርቶጋዳ
👤ደራሲ:- ይስማእከ ወርቁ
💽መጠን:-483.7MB
⏰️ሰዓት:-.....
🔢ዓ.ም:-2001

@ethioleboled
Forwarded from 🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁
ቶማስ_ሳንካራ_ጥቁሩ_አብዮተኛ_@ETHIO_PDF_BOOKS_2.pdf
46 MB
📚ርዕስ፦ ቶማስ ሳንካራ ጥቁር አብዮተኛ
📝ደራሲ፦ ዳንኤል ዳኘ ቸኮል
📖ዘውግ፦....
📆ዓ.ም፦.....
📜የገፅ ብዛት፦ 156
📌አዘጋጅ፦ jonah jo

@ETHIOLEBOLED
══════════════════
Forwarded from 🃏𝙼𝚎𝚔𝚒🀄
የኛ ሰፈር....4



ከአባቴ የወረስኩት አንድና ብቸኛ ነገር ስሙን ነው....ስሙን ብቻ...ድህነቱ እንኳን ከሱ በኃላ የመጣ ነው...ምክንያቱን እንኩዋን እኔ እናቴም በውል በማታውቀው መልኩ ሙሉ ንብረቱ በአባቴ ቤተሰቦች ስም ነበር....በዚህ ምክንያት ከአባቴ ጋር ነጋ ጠባ ጭቅጭቅ ነበር....እኛ ባናምነውም እሱ የሚለን የነበረው እነሱ ላይ ዳጎስ ያለ ብድር ስላለበት እና ብድሩን ሙሉ በሙሉ እስኪከፍል ድረስ ንብረቱ ማስየዣ እንደሆነ ነው...አንድ ቀን እጨርሳለሁ አንዳለ ቀኑ ደረሰ....ከማይመለስበት ሄደ....

ቤተሰቦቹ ገና በሰልስቱ ነበር ቤቱን እላያችን ላይ የሸጡት.... ሀዘናችን ላይ ፣ ያልደረቀው እንባችን ላይ፣ያልወለቀው ጥቁር ልብስ ላይ ወሽመጣችንንም ጨምረው ቆርጠው እናከራይ ከነበረው ሰርቪስ ክፍል እንድንገባ አደረጉን.....

በዚህ ቢተዉን ጥሩ....ከ 3 ወር በኃላ የቤት ክራይ ካልከፈላችሁ ብለው ሰቅዘው ያዙን...ያኔ ነው እናቴ አባቴን ሳታገባ በፊት ከነበረችበት መንደር ለመመለስ የተገደድነው..... ሳንወድ በግዳችን ሊፈርስ 1 ሀሙስ የቀረው ቤት ላይ ሀ ብለን ኑሮ ጀመርን...በሩቅ ሆና ለበአል ገንዘብ እና የበአል እቃዎች ትልክላቸው አንዳንዴም እየመጣች ትጠይቃቸው የነበሩ ጎረቤቶቿ ስትቀርባቸው ፊታቸው የሚያስቀርብ አልነበረም....


ከአባቴ የወረስኩት ያልኳችሁ ስሙ አሁን አሁን በአደባባይ ሲጠራ ያሸማቅቀኝ ጀምሯል....ጭራሽ ብሎ ብሎ ስራ እንዳልቀጠር እንቅፋት ሆኖ አረፈ...

"የደወልኩትማ ልነግርሽ ነው።"....አለችኝ ለአፍታ እረፍት አርጋ
"እና ልትነግሪኝ ከወሰንሽ እንዴት እንደምትነግሪኝ በደንብ አስበሽ አትደውይም..?"
"ፅኑ"...
"አቤት"
"ቸሬ የስራ መስፈርቱን ታሟላለች ግን መቀጠር አትችልም ብሎኛል"....አለችኝ አምጣ አምጣ
"ሁለት አብረው የማይሄዱ ነገሮችን ነው ያወራሽው ታውቆሻል...?የስራ መስፈርቱን ካሟላሁ ለምን አልቀጠርም....?"ቱግ እንዳልኩ ድምፄ ላይ ያስታውቃል...
"እ...ማለት ...እ"...ተንተባተበች
"ኤፊ"
"ወይ"
"ተረጋጊና ያለሽን ቃል በቃል ንገሪኝ"
"እሱ ያለው የትምህርት ማስረጃው ለመቀጠር በቂ ነው...ውጤቷም አሪፍ ነበር ግን...." አቆመች
"ግን ምን....."
"ቦታ የለም"....
"ኧረ "....ብዬ ስጨርስ የስላቅ ሳቄ ተከተለኝ....
"አዎ"
"ባለፈው ሳምንት የተከፈተ ድርጅት ከምኔው ሞላ...የ ሰባት አመት ህፃን ልጅ ነው እንዴ ምመስልሽ...?"
"ሞላ እንግዲህ"
"ኤፊ እየጠበኩሽ ነው "
"ምንም አላለኝም ከዚ ሌላ"
"በአንዬ ሞት ይዤሻለሁ"...አንዬን ካነሳሁ ከእሷ የምፈልገውን እንደማገኝ አውቃለሁ...
"ኧረ በፈጠረሽ እንዴ..."
"እኮ ንገሪኛ..."
"በቃ ለዚህ መስሪያ ቤት አትሆንም ነው ያለኝ"
"ለምን...?"
"ምክንያቱ እእእ እኔንጃ "..እንደምታውቅ ድምጿ አሳበቀባት
"ኤፊ እኔ ምንሽ ነኝ..."...አሁን አንጀት ብበላ ነው የሚያዋጣኝ
"ጓደኛዬ....እህቴ ነሽ"
"አሁን ያልሽው ከልብሽ ከሆነ ምንም ሳታስቀሪ ንገሪኝ"....
"ፅኑ ይደብርሻል"....አለችኝ
"አታስቢ በይ ምንድን ነው..?"
"ምስጢር ብሎ የነገረኝ ነው በናትሽ እንዳወቅሽ እንዳያውቅ..."በልምምጥ ድምፀት ይቺን አለች
"እሺ ቀጥዪ"


ቸርነት ማለት እናቷ ውጪ ከሄደች ማግስት ፍቅረኛ ብላ የያዘችው ሰው ነው...አስተዋውቃኛለች..ከትውውቃችንም በኃላ በጣም ተግባብተናል...አንድ ላይ ስንሆን ለብዙ ጊዜ አብረው የቆዩ ጓደኛሞች እንጂ እንዲህ በቅርቡ የተዋወቅን አንመስልም...

ስራ እንድትፈልግልኝ በነገርኳት ማግስት ደስ የሚል ዝና አብስራኝ ነበር...ቸሬ የሪል ስቴት ድርጅት እንደከፈተና የትምህርት መስፈርቱን የሟሟላ ከሆነ እንደምቀጠር ...ያለ ምንም ውድድር እና ቃለመጠይቅ...

"እርግጠኛ ነሽ....?እንዴት...ምንም ውድድር የለውም...እሺ ቃለመጠይቅስ"....ብያት ነበር...የእሷ መልስ ግን

"በቃ አልፈሻል...ያለሽበትን ችግር ተረድቶ ነው...በቃ cvሽን email አርጊልኝ"....ነበር...
"ሄጄ ባስገባ አይሻልም...በዛውም ቸሬን ካገኘውት አዋራዋለሁ"
"አያስፈልግም...ተቀጥረሻል በቃ እንኳን ደስ ያለሽ...."....ይሄ ቃሏ ነው ሳምንት ሳይሞላው የተቀየረው....



"ኤፊ እየጠበቅኩሽ ነው...ከሳምንት በፊት ያልሽኝን ታስታውሻለሽ...."
"በናትሽ ፅኑ...በቃ ያኔ በስህተት ነበር"
"በአንዬ ሞት ያለሽን ቃል በቃል ንገሪኝ..."
"እእእእ የአባቷ ስም ብሄሯ ምናምን ለዚህ መስሪያ ቤት አይሆንም"....
"ምን ማለት ነው ቆይ ይሄ..."
"በቃ ይሄን ነው ያለኝ"
"አሁኑኑ የመስሪያ ቤቱን አድራሻ ላኪልኝ...ድሮም አንቺ ነሽ "....
"ምን አደረኩ እኔ...?" በግርምት ጠየቀች....
"ራሴ ሄጄ ላስገባ ስልሽ...." አላስጨረሰችኝም
"መሄድሽ ያን ያሀል ለውጥ አያመጣም...ከነሱ ከሆንሽ ውጤትሽም ለውጥ የለውም.....አድራሻቸውንም አልክልሽም እንድትሄጂ አልፈልግም...ባንቺ ምክንያት ከቸሬ ጋር መቀያየም አልፈልግም!"....የማላውቃት ኤፊ መጣች.....እኔኮ በእሷ ከመጡብኝ ከአለሙ ጋር እንኳን ለመቀያየም ዝግጁ ነኝ....ትንሽ ዝም አልኩኝ እና ቀጠልኩ...
"አድራሻቸውን እንድትልኪልኝ....አሁኑኑ...ደሞ ልሂድ አልሂድ ብዬ እያስፈቀድኩሽ አይደለም እየነገርኩሽ ነው...ደሞ ከቸሬ ጋር አንዴ አይደለም ሰባቴ ብትጣሉ ጉዳዬ አይደለም".....አልኳትና ስልኩን ጆሮዋ ላይ ጠረቀምኩት....ደግሞ ለዚ ከራሱ ጋር ለተጣላ ወፈፌ ትጨነቃለች ማፈሪያ.....


"ቤትሽ መጥቼ አምቧጓሮ ሳልፈጥር ላኪልኝ"...የሚል የፅሁፍ መልዕክት ላኩላት ስትዘገይብኝ
"ፅኑ በእግዚያብሄር ይዤሻለሁ ቸሬ ይገለኛል"...ብላ መለሰች
"ሙቺአ ቀንሽ ከደረሰ"....
"ፅኑ እየቀለድኩ አይደለም..."
"እኔም እየቀለድኩ አይደለም....ይሄን ማደርገው ለቤተሰቤ ስል ነው"
"ታውቂያለሽ ቸሬ ለኔ ምን እንደሆነ አይደል ፅኑ"
"የገቢ ምንጭሽ መሰለኝ"....ይሄ ቀልድ ያልሆነ ቀልድ ነው....እናቷ አረብ ሀገር ሰርታ ከምትልከው በላይ ከቸሬ የምትቀፍለው ጨቅ ብር ነው...

"ማነው የገቢ ምንጬ ነው ያለሽ...?"አለችኝ እንደማላውቃት አርጋ
"አትሸምጥጪ የገቢ ምንጫችን ቸሬ ቸሬ እያልሽ ብትዘፍኚ ያምርብሻል"....አልኳት ይብስ እንድትናደድ....
"ፅኑ በጣም እያበዛሺው ነው!!!".........
"እሺ በቃ አድራሻቸውን ላኪልኝ እባክሽ"....
"ማይልኝ እሺ ችግር እንደማትፈጥሪ"....
"እሱን እርግጠኛ አይደለሁም...ችግር ያለባቸው ሰዎች ጋር እየሄድኩ..."
"እንዴት ነው ምነግርሽ እንዲህ እያልሺኝ"
"ኤፊ ልዋሽሽ አልፈልግም....አንድ ኢትዮጵያ ላይ እየኖርን ባዕድ እንደሆንኩ አርገው ከሚያስቡኝ ሰዎች ጋር እንዴት እንደማወራ እንጃ....ግን I promise ያንቺን ስም እንደማላነሳ..."
"ፅኑ"
"ወይ"
"I feel sorry for u"
"U don't have to feel sorry ....i will fix it...anways thanks".....

አድራሻቸው ተላከልኝ....


ሲነጋልኝ ላጥ ላጥ እያልኩ መስሪያ ቤታቸው ተገኘሁ....የመግቢያ በሩን እንዳለፍኩ ከማን ጋር እንደተፋጠጥኩ ገምቱ....ቸሬ

"ፅኑቃል"....




ይቀጥላል....


Shewit dorka

Https://www.tg-me.com/ethioleboled
Forwarded from 🃏𝙼𝚎𝚔𝚒🀄
የኛ ሰፈር...5




ሰላምታ ከተለዋወጥን በኃላ ተያይዘን ቢሮው ገባን....የሪል ስቴት ድርጅቱ እንኳን ሌላ ፅዳት ሰራተኛም በቅጡ የለውም....
"ኤፍራታ አልነገረችሽም እንዴ...?"አለኝ ጠረጴዛው ላይ ያሉትን ወረቀቶች ለማስተከል እየሞከረ
"ስለነገረችኝማ ነው የመጣሁት"...አልኩት ዘርጠጥ ብዬ እየተቀመጥኩ....አተኩሮ ላየን እኔ አሰሪ እሱ ሰራተኛ ነው ምንመስለው
"ይኸውልሽ ፅኑ..."...ማውራት ሊጀምር ሲል ስልኩ ጠራ
"እሺ እሺ መጣሁ መጣሁ"...."አስቸኳይ ስልክ ስለሆነ ነው ያነሳሁት...ያዘዝናቸው እቃዎች ነበሩ። ደርሰናል ነው ሚሉኝ....ይቅርታሽንና 5 ደቂቃ ትሰጪኝ"...
"ይቻላል"....አልኩት በስሱ ፈግጌ...እንኳን 5 ደቂቃ 5 ሰአትስ ቢለኝ የት አባቴ እሄዳለሁ...

አምስት ደቂቃ ትርጉሙ ተቀየረ መሰለኝ....እዛው ተጎልቼ 30 ደቂቃ አለፈኝ...

"ለወጣቶች የስራ እድልን እንፈጥራለን"....የሚል መፈክር ግድግዳው ላይ ተለጥፎ ሳይ ወጣትነቴን ጠረጠርኩ...."የኢትዮጵያን ገፅታ እንቀይራለን..." ይላል ደሞ በተቃራኒው አቅጣጫ ያለው ግድግዳ ላይ ያለ ብጫቂ ወረቀት....

በለው!!!! "ኢትዮጵያ" ሲሉ ትንሽ አያፍሩም....እኔ እንደውም አሁን አሁን እገሊት የምትባል ሀገር ላይ ኢትዮጵያ የሚባል አናሳ ብሄር ያለ ነው የሚመስለኝ....ሆነም ቀረም እነርሱ ባሉት መንገድ አይሁን እንጂ በደንብ አድርገው ቀይረዋታል....



አህያ በበላ ዳዋ ተመታ


ያሉት ብኂል ትዝ አለኝ...እነ እገሌ በጋጡት እኛ ተወቀጥን...ያው እኔ እንደ አንድ እንጀራ ፈላጊ ሆኜ ሳወራ አባቴ ያወረሰኝ ስም እንዳልራብ አንዳች ሀይል አያላብሰኝም....



ፖለቲካ አልወድም ...ግን የማውቀው ነገር ቢኖር እኔ የኢትዮጵያ እንደሆንኩ ነው...ሌላ የማንም አይደለሁም......ትላንት ላይ ተረግጠናል ተገፍተናል ብለው ዛሬ ላይ እድሉን ሲያገኙ የሚረግጡና የሚገፉ ከሆነ የእነርሱ መገፋትና መረገጥም ልክ ነበር ማለት ነው....የሆነው ሆኖ ፖለቲካ አለወድም ብያችሁ የለ ...ያየሁትን እንዳላየ ሆኖ ማለፍም አልችልም.........
ሞቶ የከረመን ሬሳ በቡጢ መማታት ጀግና ያስብላል....? እጁ የተቆረጠን ሰው "እጅ ወደላይ አለዚያ እጅህን እንቀነጥሰዋለን"... ብሎ ማስፈራራት ጤነኝነት ነው....?


እስከአሁን አልመጣም....እሱ የቆየበትን ሰአት ሀበሻ 6 ልጅ ወልዶ ሁለቱን አስመርቆ ፣ ሁለቱን ውጪ ልኮ፣ ሁለቱን ድሮ ለወግ ማዕረግ ያበቃ ነበር....


"ይቅርታ ቆየሁ አይደል..." አለኝ ተመቻችቶ እየተቀመጠ...."ኧረ አልቆየህም" ብዬ ላስቀው እንዴ...?
"አይ ስራ አይደል እረዳሀለሁ..." አልኩትና ቀጣዩን መጠበቅ ጀመርኩ
"ያው ፅኑ ድርጅታችን ለተለያዩ ወጣቶች የስራ እድል እያመቻቸ ያለ ድርጅት ነው....ያንቺን cv email አርገሽልን ነበር እና ካንቺ በፊት ያስገቡ ብዙ ልጆች ነበሩ ...ስለቀደሙሽ ለነርሱ ቅድሚያ ሰጥተን ነው አንቺን በቀጣይ ማስታወቂያ የመጀመሪያ ተቀጣሪ እናደርግሻለን"


"ግን እኮ ቸሬ ቀድሜ ነው ያስገባሁት በዛ ላይ".....
"ይኸውልሽ ፅኑ እንዳልኩሽ ነው በቀጣይ ትቀጠሪያለሽ ተማመኚብኝ"......አለኝ ወሬያችንን ለመቋጨት እየተጣደፈ.....ብዙ ነገር ልለው ፈልጌ ለኤፊ የገባሁት ቃል አሰረኝ.....እንዴት ብዬ እሷን ሳላነሳ ላውጋው....ከየት ሰማሁት ልበል....?እንባዬ መጣሁ መጣሁ ሲል ጎንበስ አልኩ....ወዲያው በሩ ተቆረቆረ....ፀሀፊዋ ናት...

"ይቅርታ" አለችና ወደውስጥ ገባች...በእጇ ክምር ወረቀት ይዛለች...ከተከመሩት መሀል አንዱን መዛ አወጣችና ማውራት ጀመረች
"የስራ ማስታወቂያ ፎርሙን አዘጋጅቼ ጨርሻለሁ እያቸውና ይለጠፉ ብዬ ነው".....አለች እየተንቀለቀለች....የቸሬ ፊት የድሮውን አስር ብር መሰለ....



ይቀጥላል.....



https://www.tg-me.com/ethioleboled
2024/09/22 19:26:16
Back to Top
HTML Embed Code: