Telegram Web Link
የኛ ሰፈር....12



"ይፈተሹልኝ"......ደገመችው
"ለምንድን ነው የምንፈተሸው"...ጠየቅኩ እኔ... የሺ ምንም አላለችም...የኔን ያህልም አልደነገጠችም...
"ንፁህ ከሆንሽ ምን አስደነገጠሽ...?"...ተንከሲሷ ናት ይሄን ባይዋ
"አልደነገጥኩም...ለምን ነው ያልኩት"..
"ሀብሌ ጠፍቶብኛል...ከናንተ ውጪ ደሞ ሚወስድ አይኖርም"...አለችኝ እርግጠኛ ሆና
"ምን ምን ማለት ቆይ ሌቦች ናችሁ እያልሽን ነው እ"...ምን ለማለት እንደፈለገች በደንብ ገብቶኛል ...
"ተፈተሹና መሄድ ትችላላችሁ"...ይሄን ያለው ቸሬ ነው....ፈታሽዋ ጥበቃ መፈተሻ መሳሪያዋን ይዛ አይን አይናችንን ታያለች...የሺ ምንም አልጨነቃትም አላናደዳትምም....ብፈተሽ ምንም እንደማይገኝብኝ እርግጠኛ ብሆንም ሌባ መባሌ አንገብግቦኛል...


"ጀምሪ እንጂ"....ብላ ፈታሿ ላይ አንባረቀች
"እሺ እሺ...ግን እመቤት ማሽኑ አይሰራም"...አለች እየፈራችም እየተባችም
"እና ካልሰራ ለምን ይዘሺው መጣሽ..?"...ከቅድሙ ይበልጥ ጮኧችባት
"ይሰራ ነበር እኮ"...ጥበቃዋ 'ነበር' የግሏ ነው...
"አሁን ግን አይሰራም አይደል"...አላት ቸሬ
"አዎ ጌታዬ"...አለች አንገቷን ቀብራ
"ስለዚህ የማይሰራ ነገር ይጣላል...ወይም ይጠገናል"...አላት ድምፁን ቀስ አድርጎ ....በለው ቸሬ ነው ይህንን ያለው..?ማመን ከበደኝ....'በነበር' ፖለቲካ እያሰቃየኝ ከሱ ነው ይህ ቃል የወጣው...ፊልምም መሰለኝ...ግን ደግሞ ፊልም የእውነተኛው አለም ነፀብራቅ ነው...የድሮዎቹን ፊልም ማለቴ ነው...ይሄ ፊልም አይደለም...ህልም ነው....ወይም ፕራንክ....ትናንቶቹ ላጠፉት ጥፋት የዛሬዎቹ የምንቀጣበትን አስቀያሚ ፖለቲካ እየኖረ፣ዛሬ ላይ ትናንትን እቀዘፈ...'በነበር' እየዋዠቀ ስለምን እንደሚያወራ እዩልኝ...
"ለጊዜው በእጅሽ ፈትሻቸው"
"እሺ ጌታዬ"....አለችና ወደ እኔ ቀረበች
እጄን በመስቀል አምሳል ዘረጋሁላት...በረበረችኝ ማለት ይቻላል ....የሺን ገርመም ሳረጋት ከተንከሲሷ ጋር በአይን ያወራሉ...ቸሬ ስቅቅ ብሎ ያየኛል...አይኑ ፍርሀት አለው...የየሺ አይን ደግሞ እስከዛሬ ያላየሁበት ነገር አለው....

ኪሴ ላይ ትንሽ ቆየች....ከኪሴ የአንገት ሀብል ይዛ ስትወጣ ምድር ተከፍታ እንድትውጠኝ ተመኘሁ...ከየት መጣ...?ማን ከተተው...?
"ይኧው ይኧው"....ብላ ጮኧች ጠላቴ
"ኧረገኝ".....የሺ ቀጠለች...ቸሬ ፈጠጠ...እኔ ቃላቶች አልታዘዝሽ አሉኝ.....
"እ...እ..እኔ አልሰረቅኩም"...አልኩ የሞት ሞቴን...
"እና እግር አለው...እ ዘሎ ገባ"...ደስ አላት...የሆነ ፊልም ዳይሬክት አርጎ እንደተሳካለት ሰው...የዘመናት ህልሙ እንደሰመሰለት ሰው ተደሰተች።
የሺን አየኃት...አይኗ ከአይኔ ሲጋጭ ደንግጣ ስብር አደረገችው...እስክታየኝ ጠበኳት..ልታየኝ አልፈለገችም...ወይም አልቻለችም መሰለኝ ተሳስታም ቀና አላለችም...

"ከፅኑ በቀር ሁላችሁም ውጡ "...ቸሬ አዘዘ
"አቶ ቸርነት የተሰረቀው የኔ ንብረት ነው ሰርቃኛለች እኔ ለምን እወጣለሁ...? "
"ውጡ አልኩ እኮ"...እንደመጮህ አለ።....ተግተልትለው ወጡ...ከማዕረግ ወንበሩ ተነስቶ ወደእኔ መጣ...
"ቸሬ...እኔ.."....ከዚህ በላይ መቀጠል አልቻልኩም....እንባዬ አነቀኝ...ቸሬ ያውቀኛል...እንዳላረግኩት ያውቃል....ፈርቻለሁ እርሱም  ፍርሀቴ ገብቶታል...
"እንዳላረግሺው አውቃለሁ"
"አመሰግናለሁ"....ብዬ አቀፍኩት...ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ...


"አሁን እባረራለሁ ማለት ነው...?እ..እ ቸሬ እናቴንና ወንድሜን ምን ላርጋቻው..እ...እኔ እኮ"....አሁንም አልቀጠልኩም...
"አይዞሽ አትባረሪም..."
"ድራማ ነው ቸሬ እሷ ናት ያደረገችው"...
"አውቃለሁ እና እኛስ ድራማ ብንሰራ ምን ይለናል"....አለኝ አይን አይኔን እያየኝ
"እ...ማለት አልገባኝም"......በሩን ከፈተው....እንዲገቡም ጋበዛቸው...ዘላ ገባች ....
"እንድትቀጣልኝ እፈልጋለሁ ይሄ ሁለተኛ ጥፋቷ ነው "...አለች አይኗን ከኔ ሳትነቅል
"እሺ እሺ"....ከፅዳት ሰራተኝነቴ ምሰናበትበትን ወረቀት በእጄ ሰጠኝ....
"ተባረሻል"....አለኝ እሷን እሷን እያየ....ደስ አላት የሚለው ቃል ትንሽ ነው...ፈነደቀች...የሺ ቀናም አላለችም....እኔ እንደተባረረ ሰው አልሆንኩም....


"እሺ "....ፈገግ አልኩ...መፈገጌ ረበሻት...ደስታዋ ክስም አለ...ማሽላ እያረረ ይስቃል አይነትም ሳይመስላት አይቀርም...ግን በአንድ ፈገግታ ሙሉ ባይሆንም ግማሽ ደስታዋን በረዝኩት...እያየኃት ወጣሁ...


ሰፈር ስደርስ ሰፈሩ ጭስ በጭስ ሁኗል... ከተሰበሰበው ሰው መሀል ግማሹ አፉን ይዞ ያወራል...ግማሹ ውሀ ከቦታው ይዞ ይሮጣል...ተደበላልቋል...ወደ ቤቴ ስቀርብ አይኔን ማመን አቃተኝ....ተቃጥሏል...እናቴን ከውስጥ ጎትተው ሲያወጧት ደረስኩ....ራሷን ስታለች...
"እናቴ እማ እናቴ"....ብዙም ማውራት አልቻልኩም....እጄ ተንቀጠቀጠ...ትንሽ ትንሽ ለመተንፈስ ትጥራለች...
"ል...ልጄ...ው..ስ...ጥ"....አለች ጣር ውስጥ ባለ ሰው ቅላፄ
"ወንድሜ"......ዘልዬ ገባሁ.....



ይቀጥላል....





Shewit dorka


Https://www.tg-me.com/ethioleboled
የኛ ሰፈር....13



ዘልዬ ከገባሁበት አንድ የማን እንደሆነ የማላውቀው እጅ መንጭቆ አወጣኝና ከእናቴ ጋር ደመረኝ....

"ወንድሜ ውስጥ ነው ...ይሰማሀል አይደል ወንድሜ"...."አመት ያልሞላው ልጅ ውስጥ አለ"...መጮህ በምችለው ልክ ጮሁኩ...

"ተረጋጊ ተረጋጊ "...አለኝ የእዛ እጅ ባለቤት....
"ያምሀል እንዴ ሰውዬ እንዴት ነው የምረጋጋው ቤቱ እየነደደ ነው "...ጩኸቴ ላይ ትግልም አከልኩበት...

"ልቀቀኝ...."...የብረት ዘነዘና የሚያስንቀው እጁ በእኔ ጥረት ሳይሆን በእርሱ ይሁንታ ከላዬ ተነሳ....እኔን ቀድሞኝ ወደ እሳቱ ተፈተለከ...እናቴም ከአንዱ ጎረምሳ ጋር ልቀቀኝ አትልቀቀኝ ትግል ውስጥ ናት......."እንዴት ልጇን ጥላ ወጣች ጉድ እኮ ነው..."..."መትረፉንም እንጃ ያልታደለ አዬዬዬ ወልዶ ለእሳት"..እሳቱ ላይ ጭድ የሚጨምሩ የሰፈራችን የትልቅ ትንሾች አፋቸውን በነጠላ ሸፍነው ሀሜቱን እና ተስፋ ማስቆረጡን ተያይዘውታል...አቅም ያላቸው ከእሳቱ እና ከእኛ ጋር ይታገላሉ...አቅም የከዳቸው በምላሳቸው ሰው ይገላሉ...

"ኧረ ይሄ እሳት ወደ እኔም ቤት እየተጠጋ ነው..."...ከመሀላቸው አንደኛዋ ናት ይሄን ባይዋ
"ኧረ ኡኡኡኡኡኡኡ".....ጩኧቷን አስነካችው እና ከመሀላቸው ተነጠለች....
"ኧረ ይሄ ለኛም ይተርፋል"....ቀጠሉ ሌላኛዋ....እንዲህ እንዲያ እያለ የሀሜቱ ጀማ ተበተነ...

"ወንድሜ".......ይዞት ሲመጣ ከዚህ በፊት ተሰምቶኝ የማያውቅ ስሜት ተሰማኝ...የሆነ አካሌ ክፉኛ እንደታመመ ነገር...የሆነ አካሌን ንጥቅ አርገውኝ እንደሄዱ ነገር....

"ልጄ ".....እናቴም ቀጠለች....

"ተረጋጉና ተከተሉኝ "...አለ ቅድም ያልኳችሁ ሰው...

"ልጄን ልየው...ልጄን ይዘህ ወዴት ነው የምትሄደው...".......

"ወንድሜን ".....እኔም ተከተልኩ...

"ሆስፒታል መሄድ አለብን "...አለና ወንድሜን አስታቅፎን የሆነ መኪና ውስጥ እንድንገባ ጋበዘን....ተግተልትለን ገባን....

የኔ ትንሽ ወንድም በጣም በትንሹ ይተነፍሳል....እሳቱ አላገኘውም...ጭሱ ግን ከሱ አቅም በላይ ነበር....እናቴም እኔም ማልቀስ ማቆም አልቻልንም....


"እንዴት ጥለሽው ትወጫለሽ ቆይ ምን ማድረግሽ ነው"....እናቴ ላይ መጮህ ጀመርኩ.....

"እኔ ፍግም ልበል...እኔን ይነቀኝ...እኔ..እኔ"....መንሰቅሰቅዋ ባሰ...
"እባክህ ወንድሜ ፍጠን ፍጠን"
"እሺ ደርሰናል ተረጋጉ"....ከመኪናው እስክንወርድ ድረስ እንዴት በዚህ ፍጥነት እንደደረስን አልገባኝም ነበር...

ለካ ዞሬ ለማየት ከሚያሳሳኝ እኔ ነኝ ያለ ሆስፒታል ኖሯል የወሰደን...ሌላውን ትታችሁ የሚረገጠው መሬት ከሚያበራበት ሆስፒታል....እንጀራ ተነጥፎ ቢበላበትም ከማይቆጭ መሬት....ለቤታችን በጣም ቅርብ የሆነ ለኑሮዋችን ግን በጣም የራቀ ሆስፒታል....

የህፃናት ክፍል ተብሎ ቀስት ወደ ጠቆመበት ቦታ ታጠፍን...

"ይቅርታ የኔ እህት ካርድ ሳታወጪ መግባት አትችይም" አለችኝ ...ካርድ የተሰደረበት ቦታ የቆመች ወጣት...
"ወንድሜ ሊሞትብኝ ነው "....አልኳትና ያልኩትን መልሼ አስተዋልኩት...'ሊሞትብኝ ነው'...ምን አልባት አንድ ሰአት...እርሱም እድለኛ ከሆንኩ ...ወይም አንድ ደቂቃ ይሆናል የቀረው...ወይም አንድ ሰከንድ...አላውቅም....

"ይቅርታ የኔ እህት ይሄ የሆስፒታሉ ህግ ነው"....አለች ፈርጠም ብላ....

"እናንተ ሂዱ....እኔ እዚ ያለውን ነገር እጨርሰዋለሁ"...አለን የቅድሙ ሰው...

ይሄን እንዳለን ተንደርድረን ገባን...ወንድሜን ተረክበው እኛን አስወጡን......

"ወንድሜ እንዳትሄድ አይ አትሄድም አትሄድም".....እናቴን ለራሷ ትቻት ብቻዬን ሳነበንብ የቅድሙ ሰው ጣጣችንን ጨራርሶ መጣ....እሱን ሳየው የካርድ ክፍልዋ ንግግር አእምሮዬ ላይ ውልብ አለ....


     "ህጉ አይፈቅድም"....


በየትኛው መመዘኛ ነው ህግ ከህይወት የሚበልጠው....ማነው ከህይወት በላይ ያደረገው...ማነው ስልጣን የሰጠው...የትኛው ነው
ሚቀድመው...ህጉን ያወጡት ሰዎች ህይወት አልባ ነበሩ እንዴ....ማነው ህግን በህይወት ላይ ያነገሰው...?ሆስፒታሉ የተከፈተው የሰውን ህይወት ለማትረፍ ነው አይደል...እና ምንድን ነው የሰውን ህይወት ከሚቀጥፍ ህግ ጋር ማዳበል....


"ተረጋጊ የኔ እህት..."...አለኝ ጀርባዬን መታ መታ እያደረገ...ይሄን አመታት አልወደውም...ብዙ ጊዜ  ያጣን ሰው ማፅናኛ ከአፍ ያልሆነ 'አጥተሻል ቻይው' ነው የሚመስለኝ....እኔ ደግሞ ወንድሜን አላጣሁትም...አላጣውምም...ደንዝዤ የምለው ጠፋኝ...ዝም ብዬ አለቅሳለሁ....ቃል አልታዘዝ ሲል እንባም ቋንቋ ነው....ይሄ ቋንቋ ሚገባው ደግሞ የእኔን አይነት የእንባ መግባቢያ የሚጠቀም እኔን መሳይ ሰው ነው....

"እናቴ"....አልኩና ከተወተፈችበት ጥግ ተንደርድሬ አቀፍኳት......

"ልጄ ልጄ...."....ከአፏ የሚወጣው ይሄ ብቻ ነው....



ይቀጥላል....



Shewit dorka





Https://www.tg-me.com/ethioleboled
የኛ ሰፈር....14



"የህፃኑ ቤተሰቦች ናችሁ...?"...አለች አንዲት ነርስ የምትመስል ሴት...
"አዎ አዎ ነን"....ተቅለብልበን እኩል መለስን....
"ህፃኑ የመተንፈሻ አካሉ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ስለደረሰ በመሳሪያ እየታገዘ እንዲተነፍስ እና..."

"ይተነፍሳል አለ ልጄ...?".....እናቴ አላስጨርስ አለቻት....

"ምንም ነገር ሊፈጠር ይችላል...ራስዎትን ማረጋጋቱ ነው ጥሩ..."....መለሰች ነርሷ...

"ምንም አይፈጠርም ...ምንም አይሆንም"....ርግጠኝነቴን ከየት እንዳመጣሁት ባላውቅም እንዲሆን የምፈልገው ኑረቱን  በአፌ መድገሜ አንዳች እረፍት ሰጠኝ....

"አሁን ማየት እንችላለን...?"....ጠየቅኩ እኔ....

"አሁን ለህፃኑ ደህንነት ሲባል መግባት አትችሉም..."....አለችንና ጥላን ሄደች።

"እባካችሁ ተረጋጉ".....ይሄን ያለው ያ ሰው ነው.......እናቴን ደገፍ አርጎ ቅርብ ካለ ወንበር አስቀመጣት....ቀና ብዬ አየሁት...ከዚህ ቀደም አይቼው አላውቅም... ሲጀመር እሱን የሚመስል ሰው እኛ ሰፈር ምን ሊሰራ መጣ...?

እንደው በአጋጣሚ ቢገባ እንኳን ከምኔው ሲኦል ወረድኩ ንሰሀ ሳልገባ ምናምን ብሎ ስጋውን ረስቶ ስለ ነፍሱ መፀለይ ይጀምር ይሆናል እንጂ ከእኛ ጋር ምን ያንጦለጡለዋል...? .....እኛን ሲያየን ሸሽቶ መሮጥ አልነበረበትም...? ከአጠገባችን ሲቆም ማፈር አልነበረበትም...?

ከእግር እስከ ራሱ ገረመምኩት......ግርማ ሞገስ አለው...መልክ ሳይሆን ሀብታም መሆን የሚያላብሰው ወዝ አለው...የእኛ ሰፈር ሰዎች የማይለብሱት አይነት ልብስ ለብሷል...ጅንስ በሸሚዝ ሆኖ  ከነጫማው 'አታፍጥጡብኝ እናንተ አታውቁኝም...ባይሆን ትፉብኝ እንዳትበሉኝ' ...የሚል ሙጢ ልብስ...ማን እንደሚባል  የማላውቀውን ሽቶ ተነስንሷል...ከእኛ ጋር መሯሯጡ ጠረኑን አልቀየረውም....እኛ ድሮውንም ፍየል ፍየል ነበር የምንለው አሁን ሌላ እስከ አሁን ስም ያልተሰጠውን ከባድ ሽታ መሽተት ጀምረናል.. ምን ልበላችሁ በቃ ፅድት ያለ ሰው ነው...


"ማን እንበል ግን".....አልኩት በተዘጋው ድምፄ....
"ሄኖክ እባላለው"....መለሰልኝ...
"በጣም አሸገርንክ የኔ ወንድም በጣም እናመሰግናለን"....አልኩት...
"ምንም አይደል"
"ከዚህ በላይ አናሸግርህ.."...አልኩት እንዲሁ ሂድ አይባልም ብዬ.....ትንሽ አርፌ ቀጠልኩ...
"የከፈልከውን ገንዘብ ንገረኝና ልላክልህ"...አልኩት ከየት እንደምልክለት እያሰብኩ...የፈረደባት ኤፊ ጭንቅላቴ ላይ መጣች...

"ችግር የለውም አታስቢ....ባይሆን ራስሽን አረጋጊና ስለወንድምሽ ጤንነት ብቻ አስቢ..."......ኧረ ካልከፈልኩህ ብዬ መገገም አልችልም...አቅሜን አውቃለኃ....

"አንዴ እንዳየው ፍቀዱልኝ እባካችሁ"....እናቴ ሚወጣ የሚወርደውን ነጭ ለባሽ ሰቅዛ እየያዘች ነው.....

"እባክዎትን የኔ እመቤት ለልጁ ደህንነት ሲባል ነው"....የሁሉም ነጭ ለባሾች መልስ ነው።

"እባክህ ዶክተር"....አለችው ተረኛ አላፊውን ነጭ ለባሽ...ከዛም እጁን ይዛ ሙጥኝ አለችበት.....የማትገባበትን ብዙ ምክንያት ቢደረድርም አልመለስ አለች...እኔም ላስቆማት አልፈለግኩም...እንድታየው እፈልጋለሁ....በመጨረሻም እጁን እንደያዘች ወደ መስኮቱ አስጠጋትና እጁን አስለቅቆ ጥሏት ሄደ...ልትከተለው ስትሞክር

"እባክዎትን እመቤት ልጆትን የሚፈልጉት ከሆነ"....ሲላት ቀጥ ብላ ቆመች.....በሩን በጣም በትንሹ ከፍቶ ገባ...ቀጥሎም የመስኮቱን መጋረጃ ላመል ከፈት አርጎት ወጣ።

ወድያው መስኮቱ ላይ ተሰየምን...ወንድሜ ተኝቶ አይደለም አይቶ የማያውቀው አልጋ ላይ ተኝቶ በማሽን እርዳታ ይተነፍሳል....በቅጡ መኖር ሳይጀምር ለመኖር እየታገለ ነው...

እናቴ ራሷን መሸከም አቃታት...ተዝለፈለፈች.....

"እንዴት ጥለሽው ትወጫለሽ ...?ምን መሆንሽ ነው"....ጮህኩባት...

"ራሷን ስታ ነው ያገኘናት...ቤቱ በጭስ ታፍኖ ስለነበር ህፃኑን አላየነውም..."....እሷን ወክሎ ሄኖክ መለሰ።
"ምግብ መብላት አለባችሁ...ለህፃኑም የምትተርፉት እናንተ ደህና ስትሆኑ ነው.."
"አላሰኘንም ይቅርብን "....እናቴንም እኔንም ወክዬ መለስኩ።
"ባይሆን ከዚ በላይ አናሸግርህ በጣም እናመሰግናለን።"....ሂድ ማለቴ ነው በሱማልኛ...
"አላሸገራቹኝም....ትንሽ ልቆይ"....መለሰ።


ከደይቃዎች በኃላ የታሸገ ምግብ እና ውሀ ይዞልን መጣ...እኛ መስኮቱ ላይ ተለጥፈን መሄዱንም አላስተዋልንም ነበር...

ቅርብ ካገኘነው ወንበር ተቀምጠን ስንቀማምስ ወደ ጆሮዬ የገባውን  ድምፅ ማመን አቃተኝ...ፈጣሪዬ ጆሮሽ ነው በለኝ እያልኩኝ ድምፁ ተደገመ...

"የኔ ቆንጆ"....እየዘገነነኝ ስዞር የኔው ጉድ ነው...ያ የሽማግሌ ቀላል ...
"የኔ ቆንጆ ደህና ነሽ"...ብሎ ሊያቅፈኝ ሲሞክር ከትከሻው ቀድሜ ከቦርጩ ጋር ተላተምኩ....እናቴ ደንግጣ ታየኛለች...


**



ደርቄ ቀረሁ....የእናቴ አይን ብቻውን "ማነው ይሄ ሽማግሌ"...እያለኝ ነው...እንደተፋጠጥን በመሀላችን ዝምታ ነገሰ...

"እዚ ምን ትሰራለህ...?"...እንዲህ ስል የእናቴ አይን ተጎለጎለ....ስህተት ስሰራ እንደምታየኝ አየችኝ....አሁንም አይኗ ብቻውን "ትልቅ ሰው አንተ አይባልም..ምን መሆንሽ ነው...."...ያለኝ መሰለኝ....

"ልጄን ትንሽ አሟት"....እንዳለኝ ደርበብ ያለች ሴት ጠራችው....
"እመለሳለሁ የኔ ቆንጆ"....ብሎኝ ሲሄድ የእናቴ አይን ባሰበት...ልትናገር ፈልጋ የሆነ ነገር እንደያዛት ሆነች....ሄኖክ አብሮን መቆሙ ልሳኗን እንደዘጋው ገብቶኛል....

"መሄድ አለብኝ "...አለ ሄኖክ ....ነገራችን ይግባው አይግባው አላውቅም....

"እባክህ አትሂድ "....አልኩት በልምምጥ ድምፀት...ኑረቱን ፈልጌ ሳይሆን ከእናቴ ጥያቄ ለመሸሽ...ይሄን ጊዜ የእናቴ ፊት ከበርበሬም ቀላ...


አትሂድ ስለው አንዴም ሳያስብ...
"እሺ አልሄድም"....ብሎ አሳረፈኝ....በጣም በስሱ ፈገግ አልኩለት...እርሱም የእኔን ያህል ፈገገ....

"የኔ እመቤት ለአስታማሚ የተዘጋጀ ክፍል አለ ..እዛ አረፍ ይበሉ "...አለ አንዱ ነጭ ለባሽ...ወንበሩ ላይ ተጣጥፋ ወደ ተቀመጠችው እናቴ እያየ....ይሄን ሲል

"ልጄ እንዴት ነው...?"....አለችው  ያወራውንም ከቁብ ሳትቆጥር...
"ምንም አይልም.... "...ብሎ ዝም አለ...
"ማለት ለውጥ አለው...?በደንብ ይተነፍ.."...አላስጨረሳትም
"ወደ ማፈፊያው እንሂድ እባክዎት"....ማውራት ያልፈለገው ነገር እንዳለ ግልፅ ነው....እንማይመልስላት እርግጠኛ ስትሆን የግዷን ተነሳች።


እስክትተኛ አጠገቧ ተቀመጥኩ....እንቅልፍ ሸለብ ሲያረጋት ወንድሜ ወደማይበት መስኮት አመራሁ....

"ያስፈራል አይደል"...አለኝ ሄኖክ አጠገቤ  መሆኑን ያወቅኩት ድምፁን ስሰማ ነበር...
"በጣም"....አልኩት ከልቤ.
"ለእሱ የቱ ሚያስፈራ ይመስልሻል "....ጠየቀኝ...
"የቱ ስትል"...
"ከሞትና ከህይወት"....
"ከሞትና ከህይወት"....
"ምኑን ያውቀዋል....ፍርሀትንስ ከየት ያውቃል..."...ግራ ገብቶኝ ጠየቅኩ...
"እሺ አንቺ እሱን ሆነሽ ፍሪለት ብትባዪ የቱን ትፈሪለታለሽ"....
"ሞቱን "...ከጉሮሮዬ ሳወጣው እየዘገነነኝ ይሄን አልኩ....
"ለአንቺ አይደለም ያልኩሽ....እሱን ሆነሽ ምረጪለት..."....
"ከጡት ውጪ የማያውቅ ልጅ ምን ሊያስብ ይችላል ብዬ ልምረጥ...?"
"አልተግባባንም ማለት ነው"...አለኝ በጨዋታችን ተስፋ ቆርጦ....
"ገብቶኛል መመለስ ስለማልፈልግ ነው"..


"እሺ አላስገድድሽም"....
"አንተ በእኔ ቦታ ብትሆን የቱን ትመርጥለታለህ "....
"መልሴ ሊያናድሽ ይችላል..."
"ግድ የለም"
"ሞቱን"...ሲለኝ የጠበኩት መልስ ቢሆንም ልቤ ትርክክ አለ...
"ለምን "...አልኩት ልውጣ ልውጣ ከሚል እምባዬ ጋር እየታገልኩ...
"ለራሴ እመኘው ስለነበር "
"ምኑን ሞትን...?"...አልኩት ደንግጬ
......በአፉ ሳይሆን በአንገቱ አዎ አለኝ...
"ለምን"....
"እሱን እንኳን ሌላ ቀን"....ሲለኝ የማይጠየቅ ጥያቄ እንደጠየቅኩ ገባኝ ...ያለ ቦታዬ የገባሁ ምናምን ብቻ ቀጥሎ ምን ማለት ግራ እስኪገባኝ ድረስ ተምታታሁ...


በሌላ በኩል መልሱ እውነት ያለው እና ሁሉም ሰው ላይ ሚሰራ መሰለኝ...ሁላችንም በሆነ ጊዜ ላይ ምነው መኖር ሳንጀምር በሞትን  ማውራት ሳንጀምር ዝም ባልን ብለን እናውቃለን...ባይሆን እንኳን ይሄ የሞት ስሜት መልኩን ቀይሮ ህይወታችን ውስጥ ገብቶ ያውቃል...እንዴት ማለት ጥሩ....

...ያፈቀርነው ሲከዳን ምነው ባላወቅኩት...አምነን ንብረታችንን በጄ ያልነው ሲሸመጥጠን ምነው ባላመንነው...ያጎረስነው እጅ ሲነክስ ምነው ባላጎረስኩ...ምነው ባልወጣሁ...ምነው ባልወረድኩ...ምነው እንደዚህ ባላደርግ...ምናል የዛን እለት እጄን በቆረጠው.....በብዙ ምነው ባልሆነ የተከበብነው ያጣነው ነገር ስሜቱ ሞት ሞት ስለሚሸት ነው...ዱካው ስለማይጠፋ ነው....ጠባሳው ስለማይሽር ነው.....


ነገ ላይ ወንድሜ ይሄንን ሲሰማ ምነው ተቃጥዬ በቀረሁ የሚያስብል ስሜት ውስጥ ይገባ ይሆን....ለሱ ህይወት ታምርለት ይሆን...የእሱ ጊዜ ህይወት እንደ ስሟ ትሆን ይሆን....ፊቷን ካዞረችበት ትመልስለት ይሆን....


ከመስኮቱ ትይዩ ካለው ወንበር ተቀመጥን....
"እየመሸ ነው"....አልኩት
"ሂድ እያልሽኝ ነው....?"...ያሰብኩትን አለው...."ቅድም አትሂድ ያልሺኝ እስከሚመሽ ነበር...?"...ጥያቄ ደገመ።
"አይ እንደዛ ማለቴ ሳይሆን ቀኑን ሙሉ ያዝንክ ቤተሰብ ምናምን"....
"እንደዛ የሚባል ነገር የለም"...አለኝ በተቀየረ የድምፅ ቅላፄ ...ደነገጥኩ...ምን እንደምለው  ግራ ገባኝ...
"አትሂድ በይኝ"...አለኝ ልምምጥ ባለው ድምፅ....ደነገጥኩ...አትሂድ ከአትሂድ ውጪ የተለየ ትርጉም ያለው መሰለኝ...
"ለምን"...
"ግድ የለሽም በይኝ "....ቃላቶች አሻፈረኝ አሉኝ...በቃ ልጉም አልኩ...አይኔን አተኩሮ ሲያየኝ ይብስ ፊደል እንደማያውቅ ህፃን ልጅ ሆንኩ...


"ምን ይጠቅምሀል...በማታውቀው ሰው አትሂድ መባሉ ምን ይረባሀል...?ቃላቶች እኮ ለብቻቸው ከቃላት የዘለለ ትርጉም የላቸውም...ያ ቃል ከማን ነው የመጣው የሚለው ነው ዋጋ ሚሰጠው...እኔ ላንተ ምንም አይደለሁም...ይጠቅመኛል ካልከኝ ችግር የለብኝም.... ሺ ግዜ እልሀለሁ...ስሜት የሌለው ቃል በፈለከው ቁጥር ልክ እልልሀለሁ "....አልኩት አይን አይኑን እያየሁ...
"ልክ ነሽ ግን አልሂድ እባክሽ"...
"ለምን እዚ መሆኑን ፈለግክ...እስከአሁን ያደረግክልን ነገር ከበቂ በላይ ነው በጣም እናመሰግናለን..."
"ሰው ርቦኛል"....አለኝ አንገቱን ሰብሮ.........


ይቀጥላል....



Shewit dorka

Https://www.tg-me.com/ethioleboled
. #ለሴቶች
👩እራሳችንን እናድስ👩‍🦱

#ስሜትሽን በአደባባይ አታሳዪ
#ወንድን አትከተዪ ስለ ክብርሽ አስቢ
#የኖሩልሽን የሚያኖሩሽን ቤተሰብሽን አስቀድሚ
#ትኩረትሽ ራስሽ ላይ ይሁን
#ደፋር እና ቆራጥ ሁኚ
#መፅሐፍትን አንብቢ(ያንፁሻል)
#ሰውነትሽን አክብሪ (አትገላለጪ)
#ሰዎች ስለ እኔ ምን አሉ የሚል ጭንቀት አስወግጂ
#makeup በራስ መተማመንሽን እንዲቀንስ አትፍቀጂለት

👱‍♀የኔ ቆንጆ👱‍♀

ሞኝ፣የዋህ እና ጥሩ ወንድ ነው ብለሽ ከምታስቢው ሰው በላይ ልብሽን የሚሰብር የለም።
አስታውሺ ልብሽ ከአንዴ በላይ እንዲሰበር አትፍቀጂ። ከህመምሽ ተማሪ ማንም ሊሰብረው የማይችል ልብ ፍጠሪ።

#ጠንካራ ሁኚ

ትልቅ አላማ ካለሽ ካሰብሽበት ትደርሻለሽ።ብዙ ህመሞችን እና ስብራቶችን ትችያለሽ።
ስኬት ጊዜ ይፈልጋል ትዕግሥት ያሻዋል።ፅናት ይኑርሽ


-->ደካማ ማንነቶችን ለማደስ የሚሆኑ መፅሐፍት (ለወንዶችም)
*📖how to think like a roman emperor📖
*📚power📚
*📒surrounded by idiot📒
*📓influence📓
*📚the subtle art of not giving a fuck📚
(recommended by herhim32)
ሸምታችሁ አንብቧቸው ትለወጡበታላችሁ።
{@Meki3}

share📒 @ethioleboled
የልዕልት ፀሐይ ኃይለሥላሴ እና የኮሎኔል አብይ አበበ የጋብቻቸው ስነስርዓት ሲፈፀም ፤

ሚያዝያ/ 1934 ዓ.ም
አዲስ አበባ
የኛ ሰፈር....15



"ሰው ይርባል እንዴ...?"....በአግራሞት ጠየቅኩ....አጠያየቄ 'በሞላ ሰው እንዴት ሰው ቸገረህ ያውም ሰው የሚፈልገውን ነገር ሁሉ ይዘህ'....አይነት ነገር ነው።
"ሰውማ ሞልቷል"...አለኝ መልሶ...
"አሁን ራበኝ አላልክም...?"...ግራ እንደተጋባሁ ይሄን አልኩ።
"እየቀለድኩ ነበር"....አለና የጅል ሳቅ ሳቀ...የሀብታም ቀልድ እንዲህ ነው ማለት ነው...?ወይስ ያለውን እውነት በጥርሱ እየሸፈነ ነው...?

"ሂድ ነበር ያልሺኝ አይደል...እሺ ደህና እደሪ...ለወንድምሽ መልካም እድል..."....አለኝና መልሴንም ሳይጠብቅ ተነስቶ ሄደ...እኔም ከተቀመጥኩበት ሳልነሳ በአይኔ ሸኘሁት...ሲጀመር ተነስቼ እንድሰናበተው መች እድሉን ሰጠኝ....?ራሱ ጠይቆ ራሱ መልሶ ውስጤን በጥያቄ አራውጦት ሄደ።

ማነው ይሄ ሰው...?ምንድን ነው ሚያወራው...?ለምንድን ነው እየረዳን የነበረው...?.....

ኃላ ላይ የውስጤን ጥያቄ ንቄ ትቼ ወደ መስኮቱ አማተርኩ....የወንድሜ የህይወት ክር እየቀጠነ ነው መሰለኝ ተጭ ለባሹ ሁሉ እሱ ወዳለበት ክፍል ይሯሯጣል.....

"ምን ተፈጥሮ ነው...?ወንድሜ ደህና አይደለም እንዴ...?"......የወፈሩትን ዶክተር የቀጠኑትን ደግሞ ነርስ እያልኩ በመሰለኝ ማዕረግ እየጠራሁ የጥያቄ ናዳ አወርድባቸዋለሁ።

"እባክሽ ስራችንን እንስራበት "...አንዲቷ ናት ያለችኝ....
"ተረጋጊ እመቤት"...አንደኛው ደግሞ እመቤት አርጎኝ ቁጭ አለ....በዚህ በዚህ ቦታ እንኳን ትባል ብሎ መሰለኝ...
"እባክዎትን ይረጋጉ"....አለኝ ደግሞ ሌላኛው...እንዲሁ እኔም የምላቸው ግራ እየገባኝ እነርሱም ማን ብለው እንደሚጠሩኝ ሳይወስኑ እየተራወጡ ነው።

እናቴ መተኛቷ ጠቀማቸው እንጂ መቆሚያ መቀመጫ ታሳጣቸው ነበር።

"ወንድሜ ደህና ነው...?...አንዳችሁ አናግሩኝ እባካችሁ "


ሚሰማኝ ሰው አጣሁ.....ተደግፌ ማለቅስበትም እንደዛው... አንድ አንዴ ሲሸንጠኝ በሰላም አውሎ እንዲያስገባኝ ብቻ የማናግረውን ጌታ
'ወንድሜን አደራ'...አልኩት...
'ከእኔ እድሜ ቀንሰህም ቢሆን ለሱ ስጠው' ...ጨመርኩ ፀሎት።
አሁንም አላረፍኩም... ፀሎት ሳይሆን ትዕዛዝ የሚመስል ፀሎት መፀለዬን ተያይዤዋለሁ....የእኔ እድሜ የጠቀመኝ  ይመስል ለሱ ስጥልኝ አልኩት...እድሜዬ ቢቀነስልኝ ምን ያህል ደስ እንደሚለኝ ሳስብ ፀሎቴን ታዘብኩት....አሁንም ግራ የሆነ ፀሎቴን አላቆምኩም...
'እናቴ እና እኔ ይሄንን መቀበል አንችልም አትውሰድብን '...
ቢወስደው ከስንት አይነት ነገር እንደሚገላገል ሳስብ መልሼ ፀሎቴን መረመርኩ...ወዲያው ሄኖክ ያለኝ ነገር አእምሮዬ ላይ ደውሉን ደወለ....

"የቱ ነው ለሱ ሚጠቅመው...?"...አልነበር ያለኝ....የእኔ ህይወት የእኔ ነው....የእርሱን አላውቅም.....እማማ አፀደ ያሉኝ ነገርም በተራው ጭንቅላቴ ውስጥ አቃጨለ...

"አመሻሹ ሊያምር ነው ረፋዱ የከፋው".....

ምን ብዬ እንደምፀልይ ግራ ገባኝ....ከነዚህ ሁለት ሰዎች ተነስቼ ከቅድሙ የተሻለ ፀሎት ፀለይኩ...

'ለሱ የተሻለውን እንደምታደርግ አምናለሁ....የፈቀድከውን አድርግ ቢሆንም ግን ምኖርለት ምክንያት እንዳላጣ ነገንም እንዳልፈራ እባክህ አትውሰድብኝ... እናቴም ይህንን መሸከም አትችልም...ደሞ እኮ ታውቀናለህ...እንዴት እየኖርን እንደሆነ...ለጎደለው ሆዴ አማርሬህ አላውቅም አይደል...እስከአሁን በሰላም እንድታውለኝ እንጂ ሌላ ጠይቄህ አላውቅም አይደል ...ስለ ውሎዬ የምለምንህ እኮ ለወንድሜ እና ለእናቴ ስል ነው...ለምን ተራብን ብዬህ አውቃለሁ...? አሁንም ቢሆን ብዙ ልጨቀጭቅህ ፈልጌ አይደለም ...ይሄ ላንተ ቀላል ነው ብዬ ነው....ድሮ 10ኛ  ክፍል እያለሁ መቀመጫዬን አሳምርልኝ ያልኩህን ፀሎት እንደሰማኸኝ አውቃለሁ....አሁን ላይ መቀመጫዬ ሳይሆን መጨረሻዬ ነው ሚያሳስበኝ...ወንድሜን እንዳላጣው...ከዚህም እንዳልጎል አደራህን..'....ሳላስበው ፀሎቴ ረዘመ.....

ፀሎቴን ከጨረስኩ በኃላ ወደመስኮቱ ይበልጥ ቀረብኩ.... የነጭ ለባሾቹ ሩጫ ቀጥ ብሏል...ከደቂቃዎች በፊት እንዳልተራወጡ አሁን ለጉድ ተረጋግተዋል...ሰውነቴ ውሀ ሆነ...ተርበተበትኩ...


ተከማችተው ያሉትን ነጭ ለባሾት ተሻግሬ ወንድሜን ማየት አልቻልኩም...መስኮቱን መደብደብ ስጀምር አንዱ እየተጣደፈ ወደኔ መጣ...የእርሱ ከመሀላቸው መነጠል አንድ ነገር እንዳይ ረዳኝ...ወንድሜን ይረዳው የነበረው መተንፈሻ ማሽን እየሰራ አይደለም... ተነቅሏል...ይሄን  ባስተዋልኩ ቅፅበት የጭ ለባሹ ፊት ለፊቴ ተደቀነ...ፊቱ ላይ ተስፋ መቁረጥ ይነበባል...ግን ማንበብ አልፈለግኩም...ያየሁትንም ምሰማውንም ሳይሆን የምፈልገውን ብቻ ነው ማመን ምፈልገው...


"የቻልነውን ሞክረን ነበር በጣም አዝናለሁ".....ሲለኝ ወሽመጤ ብጥስ አለ...እንዲህ ብሎኝ ሊሄድ ሲል ጋውኑን አንቄ አስቆምኩት...

"ምን ማለት ነው ...?ምንድን ነው ...?በጣም አዝናለሁ ምን ማለት ነው...?ሀዘን ምን እንደሆነ ታውቃለህ...የቻልነውን አድርገናል ምንድን ነው....?ይሄን ያህል ነው የምትችለው...?ለደቂቃዎች መሮጥ ነው የምትችለው...".....እውነቱን ለመናገር የምናገረውን አላውቀውም...እሱም የከፋት ናት ይውጣላት ብሎ ነው መሰለኝ የእርሱን እጅ ሩብ በምታክል እጅ ፡ እጅ ሰጥቷል....እየታገለኝ አይደለም....

"መልስልኝ ምንድን ነው ያደረጋችሁት....ወንድሜን አምጣው...." ......ሳላስበው መጮህ ጀመርኩ....


"ልጄን ልጄን "....ጩኧቴ እናቴም ጋር ደረሰ....

"እማ ወንድሜ"......ከዚህ በኃላ እምባ ነው....ተያይዘን ተላቀስን....

"በቃኝ አለ.... ወንድሜ ሄደ...."
"አልሞተም ልጄ አልሞተም....."....እናቴ እንደ እብድ አረጋት......
በዚህ ሁሉ መሀል የፀለይኩት ፀሎት ትዝ ብሎኝ አምላኬን እወቅሰው ገባሁ...


"ምንድን ነው ያልኩህ....አትውሰድብኝ ምን ማለት ነው....?ቆይ ምንድን ነው ችግርህ... ".....ስሜታዊ ሆኜ ፈጣሪን ተዳፈርኩ...ባልዳፈርስ ምን ይቀርብኛል...ገነት ነው ሚቀረው...?.ምን ነገ አለኝ ብዬ ነው ስለ ገነት ማስበው... የእኔ ምላቸውን ሰዎች ያጣሁ ለታ ነው ገነቴን ያጣሁት..



'የተሻለውን አድርግ'....ነበር ያልኩት....ለሱ የተሻለውን ነበር የለመንኩት...ለሱ የተሻለው ይሄ ነው ማለት ነው...? የፈቀድከውን አድርግ ካልኩት በኃላ አሁን ምን አድርግ ነው የምለው...
ፀሎቴ የፈቀድከውን አድርግ ግን እኔ የምልህን አድርግ አይነት ስለነበረ ነው እንደዚህ የሆንኩት...?


የእርሱ ፍቃድ ወንድሜን መውሰድ ይሆናል ብዬ አላሰብኩም ነበራ...ፍቃዱ ላይ የእኔና እናቴ ስሜትም ከግምት ውስጥ ይገባል ብዬ ነበራ....መንጠቅ ይፈቅዳል አላልኩም ነበራ...



ሳቁን ማየት ምን ያህል እንደሚያሳርፈኝ አልገባውም....ኑረቱ ምን እንደሚያጠነክረኝ አልገባውም...አልገባውም...መነጠቅ ምን እንደሆነ አልገባውም...ሁሉም የእርሱ ስለሆነ የፈለገውን የማድረግ መብት ያለው ነው ሚመስለው...?ምንም እንደማላመጣ ስለሚያውቅ አይደል....ሁሉን እያወቀ ምን እንደሚሰማን እንዴት አያውቅም...?ወይስ የራሳቸው ጉዳይ ነው...? ሊነጥቀን ለምን ሰጠን......እንደልቤ ፈጣሪን እመረምር አብጠለጥል ጀመርኩ...ከዚህ በላይ ምን ይመጣል ብዬ ልፍራ....?....እንዳሻው እያረገ ለምን እንዳሻኝ የመናገር መብትን ለምን እነፈጋለሁ....


ይቀጥላል....


Shewit dorka
የኛ ሰፈር....16




አልገባውም እንጂ ችግሬ የወንድሜ ወተት አይደለም...አልገባውም እንጂ ችግሬ እናቴ አይደለችም....ችግሬ የእርሱ ነጠቃ ነው....ከአባቴ ጀመረ አሁን ደግሞ ወንድሜን.....

"የህፃኑን ሬሳ ጠዋት መውሰድ ትችላላችሁ".....አለኝ አንዱ ዶክተር ይሁን ነርስ ያለየሁት ሰው
"ውሰደው".....
"ማለት እመቤት የወንድምሽን ሬሳ...".....ሳላስጨርሰው ከሆስፒታሉ ወጣሁ....እግሬ እንዳመራኝ መራመድ ጀመርኩ....ምንም ነገር ወደማልሰማበት...ከጥያቄዎቹ ከማመልጥበት....ዝም ወደምልበት...


ከሆስፒታሉ እየራቅኩ በመጣሁ ቁጥር ፣ በሸሸሁ ቁጥር ባመለጥኩ ቁጥር እንዲቀለኝ ጠብቄ ነበር.......ግን አልሆነም....ከወንድሜን በድን በራቅኩ ቁጥር በእርምጃዬ ልክ ውስጤን ስርስር የሚያረግ ስሜት ማስተናገድ ጀመርኩ....አልሆነልኝም....ከራስ ወዴት ይሸሻል...ከአንዱ ጥግ ተደግፌ ማልቀሴን ተያያዝኩት....ድንገት የሆነ እጅ ጀርባዬ ላይ ተርመሰመሰ....ዳበስ ዳበስ ካደረገኝ በኃላ በስሱ መታ መታ ያደርገኛል..... ባለፈው ያልኳቹ አይነት አመታት 'አይዞሽ አጥተሻል' ነገር ሲሆንብኝ ሄኖክ መጣልኝ....ግን እኮ እሱ ሄዷል....ዞሬ ማየት ራሱ ትልቅ ስራ ሆነብኝ ...አንገት የሌለኝ ያህል ሰነፍኩ...

"አይዞሽ"....አለኝ ባለ እጁ በመዞሬ ጉዳይ ተስፋ ቆርጦ...ሄኖክ ነው...አልሄደም ነበር ማለት ነው....


"ወንድሜ ወንድሜን አጣሁት....እ..እ..እ...".....መቀጠል አልቻልኩም....ማጣት የመጀመሪያዬ ይመስል አዲስ ሆንኩ...

ወደራሱ ስቦ እቅፉ ውስጥ ወሸቀኝ....እኔም አልቅሼ እንደማላቅ አለቀስኩ....

"አይዞሽ ለበጎ ነው"....ይሄን ሲለኝ እቅፉን ገፍትሬ ወጣሁ...
"ምኑ ነው ለበጎ...?ንገረኝ እስኪ....እንዲሁ ቃላት አመረልኝ ብለህ ነው ወይስ ባንተ ተራ ቃላቶች ሀዘኔ ሚሰክን መስሎህ ነው....ንገረኝ ለማን ነው ለበጎ ....ምታወራውን ታውቃለህ...? አንድ ፍሬ ልጅ መተንፈስ ስላቆመ ነው በጎነቱ....".......ብሶቴን ተወጣሁበት....እርሱም ዝም ብሎ ይሰማኛል.....እኔም ማውራቴን ቀጥያለሁ....

"ሰው ይርባል ስትል ነበራ....አላፊ አግዳሚው ነው ሚርበው ወይስ ህይወትህ ውስጥ ስም ያላቸው ሰዎች...ስማኝ ወንድሜ ርቦኛል....ገና በድኑን አፈር ሳላለብስ ጠምቶኛል....ገና ሳልቀብረው ሳቁ ናፍቆኛል...እ..እ ".....ሳጌ አላስወራ አለኝ.....አሁንም ጎትቶ አቀፈኝ....ተወራጨሁ....እርሱም እጅ አልሰጠም...ታገለኝ...ከዛም ተሳክቶለት ሰበሰበኝ እና ከእቅፉ ጨመረኝ...


በነጋታው የወንድሜን በድን ተረከብን.... ....በሄኖክ እርዳታ ከቀብር ጋር የተገናኙ ነገሮች አለቁልን.....አሁን ገብቼ ከማላቀው ቤተክርስትያን ቀብር ማስፈፀሚያ ቦታ ላይ ነኝ....ሰምቼ የማላውቀው ፀሎት እየተፀለየ ነው....የሆነ ልምምጥ ያለው ፀሎት....አስቁሜያቸው ለምን ፈጣሪን ትለማመጣላችሁ ልላቸው ነበር....ኃላ ሰምተውኝ ገነታቸው ቢቀርስ ብዬ ተውኩት እንጂ...

ሰፈርተኛው እያለቀሰ ነው....እናቴ ልጄ አፈር አይገባም ብላ እየጮኧች ነው....ኤፊ ጥቁሯን ግጥም አርጋ ለብሳ ሻርፗን በእጇ አፍንጫዋ ላይ ሸፍና እኔን እኔን ታያለች.....ፀሎቱ ሲያልቅ  ወደ ጉድጓዱ አስጠጉት....ከዚህ በኃላ ምን እንደተፈጠረ አላወቅም....ስነቃ ከፈራረሰ ጣሪያ ስር ራሴን አገኘሁት....



ትንሽ ቆይተው ድንኳን ደኮኑ እና እኔንና እናቴን ውስጥ ከተነጠፈው ፍራሽ ላይ ጎለቱን....


"አልቅሺና እርምሽን አውጪ " ይለኛል ተለጉሜ ያየኝ ሁሉ....ደንዝዣለሁ ወይም እንባ ጨርሻለሁ.....




*

"ልጄን ልጄን እኔን አፈር ይብላኝ እኔን"......የአባቴ ዘመዶች እያንጎራሩ ገቡ.....ከመሀላቸው ደረት ሚደቃም አለ..የምራቸውን ነው....? ወይስ  ፊልም ጀምረው ነው....?

የአባቴ ታላቅ እህት እንደ ፋርማሲ እባብ ተጠምጥማብኝ ማልቀስ ጀመረች....ምንም ለማለት አቅሙ አልነበረኝም...ታቀፍኩላት...ፊልሟንም ሳላቅማማ ታደምኩ...በነገራችን ላይ ጥሩ ተዋናይ ናት...

"የኔ አንድ ፍሬ ምን አገኘህ ".... አለች አንደኛዋ....ምን ሊያገኘው ይችላል...ደልቶት አይደል የሞተው....ተመችቶት....ተንደላቆ....

"ምግብ መብላት አለባችሁ "....ከኃላ ሆኖ ሄኖክ ያወራል...ለምን አይሄድም...?

"ፅኑ ቃል "....ጠራኝ.....የግዴን ዞርኩለት...
"እባክሽ ለእናትሽ ስትዪ"...እዚህ ምድር ላይ አንድ በቀረኝ ነገር ጠየቀኝ....ቢሆንም መልሴ ከአልበላም አልዘለለም....አንገቴንም ከነበረበት መለስኩት.....አንገቴን ተከትሎ በሳህን ምግብ ይዞልኝ መጣ....ሳህኑን አልቀበል ስለው አንድ ጉርሻ ወደ አፌ ሰደደ....ሽታው ብቻ ወደላይ ሊለኝ ቃጣው....የምግቡን ሽታ ተከትሎ ፊቴ ሲጨማደድ ምግቡን ከአፌ አራቀልኝ....በእኔ ተስፋ ቆርጦ ወደ እናቴ ሄደ...ገና ምግቡ ሲጠጋት

"ልጄን አፈር አብልቼ እኔ እህል ልብላ....ልጄን...ልጄን ....ልጄን ቀሙኝ....እሳት በላኝ...ልጄን".....እንደ አዲስ ጀመረች....ለያዥ ለገናዥ አሰቸገረች.....እኔም ከድንዛዜዬ ነቅቼ ከሷ ጋር ተደመርኩ.....

"ተዋቸው ይውጣላቸው....አዬዬዬዬ ያልታደሉ"....ተባለልን...
"ተገላገለ"....ተባለለት ለወንድሜ.


ብለን ብለን አልቅሰን አልቅሰን ሲደክመን ቁጭ አልን..እድርተኛው ጉድጉዱን አድርቶታል ...ሰዉ አፍ ለአፍ ገጥሞ ያወራል ....የሰፈራችን ጎረምሶች ጫት እየቃሙ ካርታውን አድርተውታል..እኛን ለማፅናናት የመጣ ሰው በቁጥር ሆነብኝ....ሁሉም የራሱ ስራ ላይ ነው...በመሀል የንሰሀ አባታችን ቆመው ነጠላቸውን በወጉ ማስተካከል ጀመሩ... ከዛም ወጥ ይመስል ከተሰበሰበው ህዝብ መሀል ቆሙ....

"በስመአብ ወወልድ...."..ሰላምታ ሰጡን..
"የእግዚአብሄር ቤተሰቦች "...ሲሉ ስብከቱ ላይ እኔና እናቴ እንደሌለንበት ገባኝ.....

"የሰው ልጅ ይወለዳል ያድጋል ይሞታል"...ሲሉ የቄሱን ጤንነት ጠረጠርኩ...አስቁሜ እንዳላደገ ላስታውሳቸው እንዴ..

የእርሱ ታሪክ ተወለደ ሞተ እንደነበረ ልንገራቸው እንዴ....ቆይ "ለምን" ልበላቸው እንዴ...

"እንደ ሀሳቡ ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንደሆነ እናምናለን "..እሳቸውም ደገሙት...ለበጎ ነው...

"እንደ ሀሳቡ ለተጠሩት..."..እኛ እንደ ማን ሀሳብ ተጠርተን ነው መቀበል የከበደን...? ከዚህ ጥቅስ በኃላ ስለ ፃድቁ እዮብ መስበክ ጀመሩ....ሀብቱን ፣ ልጆቹን ፣ ጤናውን አጥቶ...

"እግዚአብሔር ሰጠ  እግዚአብሔር ነሳ" ብሎ ስቃዩን በፀጋ ስለተቀበለ ፃድቅ..ስለ ኢዮብ ስሰማ እንደ እኔ ሰው እንደነበር ማሰብ አቃተኝ...

የእኔ ሙግት ለምን ሰጠን ነው..ለምን ለወራት ብቻ እንዲተነፍስ ተፈቀደለት..ግን መልሱ ያለው ራሱ ጋር ብቻ ነው..ሲነሳን አብሮ የመነጠቃችንን ምክንያት እንድናቅ አይፈቅድልንም..

**

ወንድሜ ከሄደ ድፍን አንድ ሳምንት ሆነው....ተነሳን ፈረጥን  ጮህን ግን ምንም የተቀየረ ነገር የለም...አሁን አፋችንን ዘግተናል....የአባቴን ቤተሰቦች ተከታታይ ፊልም ስናይ ከረምን....ድንኳኑ ሲፈርስ ሰዉም ቤት ቤቱ ሲገባ እነርሱም እግዜር ያፅናቹ ብለው ወደየቤታቸው ሄዱ.... ይታያችሁ የተቃጠለ ቤታችንን አይተው እንዳላየ ሆነው እንደ ዘመድ ሳይሆን እንደ ማንም ጥለውን ሄዱ....አያፍሩም እኮ ስንሞት ሊያለቅሱልን ይመጣሉ...ይመጣሉ..ካፈርኩ አይመልሰኝ ነው ጨዋታው...በደንብ ይመጣሉ።
"ዝም ያለው ዘመዴ እኔ ሳጣጥር
ሞተ ሲሉት መጣ አልቅሶ ሊቀብር"....ያሉት ወደው አይደለም.... በቁምህ ሞተህ ዝም ብለው መተንፈስ ስታቆም ይንጋጋሉ...ለምን አረፈ ነው መሰለኝ....


"ለጊዜው እኔ ቤት ቆዩ"....ይሄን ያለው ሄኖክ ነው...ሰዉ ተበትኖ እሱ፣ እኔ ፣ እናቴ፣ኤፊ እና ቸሬ ብቻ ቀርተን...ይሄን ያለው ኤፊ እና ቸሬ እንደ ማንኛውም ሰው "እግዜር ያፅናችሁ"....ብለው ከመቀመጫቸው ሲነሱ ነው...ይሄን ሲል ግራ የመጋባት አስተያየት ተያዩ...እኔ ግን ከእርሱ ንግግር የእርስዋ መሄድ ነበር ግራ ያጋባኝ....ተያይተው ሲያበቁ ሁለቱም በየተራ አቀፉኝ...ከዛም ቸሬ በእጄ ለመያዝ የማይቸግር ገንዘብ ቀስ ብሎ አሰጨበጠኝ...ልክ እባብ እንዳስጨበጠኝ ነገር ዘግንኖኝ ጣልኩት....ደነገጠ...
"ምነው ፅኑ"
"ይዘኧው ውጣ...ውጣልኝኝኝ"...አንዴ ሳንባርቅበት በቅፅበት የደነበረ በሬ መሰለ....ቤቱ መቃጠሉ በጀው እንጂ በዚህ አኳሀኑ በሩን በቀላሉ አያገኘውም ነበር.....ኤፊም የእርሱን እግር ተከትላ ወጣች....



"ሄኖክ እስከ አሁን ላደረግክልን ነገር ፈጣሪ ይክፈልህ አሁን ግን እባክህን ሂድ"...አልኩት እንደማልከፍለው እርግጠኛ ስሆን...'ፈጣሪ' ያልኩት ምርቃት ይሁን እርግማን እንጃ...እርሱ ምን ሊሰጠው ይችላል ሊነጥቀው እንጂ...ቢሆንም ስለሚባል ብቻ አልኩት...

"እባካችሁ እንሂድ"...
"ከዚህ በላይ ልናሸግርህ አንፈልግም ሸክም መሆን ደክሞናል"...ስሜቴ ስሜቷ ነው መሰለኝ ሳወራ እናቴ ዝም ብላ ታዳምጣለች አትቃረንም...

"እዚህ ጥያችሁ አልሄድም ህሊናዬ አይፈቅድም"....

"እኛ ደግሞ ከዚህ በላይ እንድናሸግርህ ህሊናችን አይፈቅድም..."...

"ከዚ ወዴትም አልሄድም"...ብሎ  መሬቱ ላይ ዝርፍጥ አለ...ይሄን ጊዜ እናቴ ማውራት ጀመረች...

"ልጄ በዚህ ሰዉም ኑሮውም በከፋበት ዘመን ከልቡ ሰው የሆነ ሰው እንዳለ እንዳስታውስ አድርገኧኛል...ማንም በሌለበት ጊዜ ፈጣሪ አንተን ልኮልናል...ምክንያትህ ምንም ይሁን ምን ያደረግከው መልካም ነገር  ለእኔም ለልጆቼም በጣም ትልቅ ነገር ነበር...ይበቃል ልጄ... እግዚአብሄር እጥፍ አድርጎ  ይስጥህ...የሮጠ አይቅደምህ...የያዝከውን ይባርክልህ...ሚካኤል በክንፉ ከልሎ ከመጥፎ ነገር ይሰውርህ...."

"ግን እኮ ማዘር"...
"ምንም ግን የሚባል ነገር የለም...ለኛ ህይወት ትግል ነው...እንድንታገል ፍቀድልን...መንገዳገዳችን በዝቶ መውደቂያችን ከቀረበ እመነኝ የቀረችዋን ልጄን ለዚህ ክፉ ሞት አልሰጣትም...እኔው ራሴ እንድትወስደን እጠይቅሀለሁ...እየመጣህ ከጠየቅከን ለኛ በቂ ነው...አሁን ሂድ እባክህ.... ".....ከዚህ በኃላ ምንም አላለም....




ካቆምንበት እየደረስን ነው ቤተሰብ....💃🕺ቀጣዩን ነገ ጠዋት 😊




Shewit dorka


Https://www.tg-me.com/ethioleboled
የኛ ሰፈር....16



ሄኖክ እያንገራገረ ሄደ.......


"ፈትለ ወርቅ ...ፈትልዬ"......ወ/ሮ አፀደ ናቸው....መልስ ሲያጡ ከቃጠሎ ከተረፈች ጎጆአችን ዘለቁ....

"በስመአብ ወወልድ....."....አማተቡ...
"ፈትልዬ ምነው እናቴ በሞላ ጎረቤት ብቻችሁን እዚ..."....ከልብ በሚመስል አዘኔታ ነው ይህን ያሉት...
"ወዴት እንሂደው...ምን መጠጊያ አለን...ዘመድስ የስም ዘመድ ነው...ባዳ በምን እዳው..."....
"መወለድ ቋንቋ ነው ምን ትላለች....በሉ እኔ ጋር እንሂድ..."....እንዲህ ብለው ሲያበቁ እጃቸውን ግጥም አርጋ ያዘቻቸው....
"ልጄን አደራ ....ልጄን ...የቀረችኝን..."....ከዚህ በኃላ ትከሻቸው ላይ ረዘም ላለ ደቂቃ ቆየች...


ከቃጠሎ የተረፉ አንድ አንድ ልብሶች እና እቃዎች ይዘን ወጣን....ወንድሜን እና ሳቁንም እዛው ጥለነው ወጣን....ላንመልሰው ቀብረነው እንደመጣን ላንመለስ ከዛ ቤት ወጣን...


ወ/ሮ አፀደ የሚተዳደሩት ልጃቸው አረብ አገር ሰርታ በምትልክላቸው ገንዘብ ነው...በዛ ገንዘብ የእሷኑ ልጅ አስተምረው ፣ የቤት ኪራይ ከፍለው ፣ የቤት ወጪ ችለው በተአምሩ የሚኖሩ ተአምረኛ ናቸው። በዚ ኑሮ ላይ እኔና እናቴ ሆዳችንን ፣ እጅ እና እግራችንን ይዘን ገብተን እንዴት ይዘለቃል...?


እሳቸው ቤት በገባን በሳምንቱ ወደ ድርጅቱ አመራሁ....ከዛ ሌባ ከተባልኩበት ስፍራ....እንዲሁ ክብረ ቢስ ሆኜ ሳይሆን ለእናቴ ብዬ....እንዲሁ በባዶ ተስፋ ሳይሆን ቸሬ ስለገባልኝ ቃል ብዬ .....
"ድራማ እንስራ"...አልነበር ያለኝ....
"እንዳላደረግሺው አውቃለሁ"...አይደል ያለኝ.....ጥቁሬን ገጥሜ ማልጄ ከቸሬ ቢሮ ተገኘሁ...



"እዚህ ምን ትሰሪያለሽ"....እንዲህ ሲለኝ ጆሮዬን ማመን ተሳነኝ...
"ምን ማለት ቸሬ...ከሁለት ሳምንት በፊት የተነጋገርነው"......
"ooo i remember ....ከሳሽስ ላይ ድራማ ልንሰራ...."....የስላቅ ሳቅ ሲስቅ ሰውነቴ ውሀ ሆነ....
"ድራማ ነበር ያልኩሽ አይደል....የድራማው ዋና ገፀ ባህርይ ደግሞ አንቺ ነሽ....ከሷ ቢሮ ካለው ክፍት ቦታ ልመድብሽ ነበር አይደል የተስማማነው..."....አንገቴን በይሁንታ ነቀነቅኩለት...ፍርሀቴ ከቅድሙም ባሰ...
"በጣም አርፍደሻል"....ሲለኝ የፈረደበት ወሽመጤ ቅንጥስ አለ....
"ፈልጌ እንዳልቆየሁ ታውቃለህ አይደል..."....ይሄን ስለው ፍርሀቴ ወደ ንዴት ተቀይሮ ነበር....
"አውቃለሁ ግን የድርጅቱ አሰራር ተቀጣሪ አስፈላጊውን ፍቃድ ጠይቆ እና"...
"አልቀጠርከኝም ነበር እኮ....ቃልህን ብቻ ነው የሰጠኧኝ...እኔም ቃልህን አክብሬ ነው የመጣሁት..."....ሳላስበው ጮህኩበት...


"ከአለቃ ጋር በቃል መጓዝ አግባብ ነው...?"....
"አለቃዬ ብቻ አይደለህም ቸሬ ጓደኛዬም ጭምር ነህ ለዛ ነው ያመንኩህ"...
"ጓደኝነትሽ ለኤፍራታ ብቻ ነው!!"....ቦታሽን እወቂ አይነት አስተያየት አየኝ....ጉራ በንቀት የሆነ አስተያየት......
"እሺ አለቃ....በነጋታው መጥቼ ነገሮችን እንዳላስተካክል ለቅሶ ላይ ነበርኩ...እባክህን"....
"ይቅርታ ክፍት ቦታ የለም።"....ይሄን ያለኝ ጊዜ ነው ለገላጋይ እስካልመች ድረስ መስሪያ ቤቱን በአንድ እግሩ ያቆምኩት....



"ጥበቃ...ጥበቃ..አስወጧት....እብድ ናት መሰለኝ...."....ቸሬ ከማውቀውም በላይ ከፍቷል....በዚህ ሁለት ሳምንት ምን ተፈጠረ....መቼ ነው የሳጥናኤል አሰልጣኝ የሆነው....?....
"እንዳትነኪኝ"....ጥበቃዋ ላይ አንባረቅኩ...ደግማ ልትይዘኝ ስትል አሽቀነጠርኳት....ማን ላይ ትበረታለህ ሲባል ሚስቴ ላይ አይደለ ያለው...እሷ ላይ በረታሁ....ስትወድቅልኝ እላይዋ ላይ ተከምሬ እንደ እባብ እቀጠቅጣት ጀመር...ብሶቴን ፣ መጥፎ እድሌን ፣ ስብራቴን ያገኘሁት ያህል ተሰማኝ....ቸሬ ተነሰቶ ከላይዋ መንጭቆ እስኪያስነሳኝ ድረስ ድብደባዬን አላቆምኩም....

"ጥበቃ ጥበቃ...."...ጉሮሮው እስኪሰነጠቅ ድረስ ጮኧ....የቀሩት ጥበቆች ተንጋግተው መጡ....ከአምስት የማያንሱ ጥበቆች አፈሱኝ....ታገልኳቸው...
"አብቅቷል".....አለኝ በድል አድራጊነት መንፈሰ....መባረሬ ካልቀረ ብዬ ፊቱ ላይ ተፋሁበት....አበደ ቀላል ነው....ሊመታኝ ቃጣው....
"አስወጧት..."...ጮኧባቸው......





"እኔ ምልሽ ልጄ"....እናቴ ናት....
"ወይ"....
"ከዛ ድርጅት ውጪ ሌላ ስራ ቦታ የለም እንዴ ምነው የሙጥኝ አልሽ...."....ከአባቴ ሞት በኃላ ሎሽን ነክቶ የማያውቅ እጄን እየዳበሰች...
"ቃል ገብቶልኝ ነበር".....
"እንዳልሽውም 'ነበር' ነው...አሁን ያ ቃል የለም እኮ...ቃሉን አጠፈ እኮ...በቃሽ"...እንዲህ ብላ ደረቷ ላይ ለጠፈችኝ....ተበጥሮ የማያውቅ ፀጉሬን እየነካካች በስሱ ሳመችኝ....
"እና ምን ላርግ..ከበቃኝ በኃላ ምን ላርግ...ሸክም መሆን ሰልችቶኛል...አንቺ አልሰለቸሽም.?"
" ሄኖክ መጥቶ ነበር"...አለችኝ ጥያቄዬን ትታ...
"እና ከምናወራው ወሬ ጋር ምን አገናኘው...?"
"የተወሰነ ገንዘብ ሰጥቶናል"....
"ተቀበልሽው....? "
"አዎ"...አለችኝ አንገትዋን ሰብራ..


"እስከ አሁን እኛ ላይ ያወጣው ሳያንስ አሁንም...."....ኤፊ ላይ ስናደድ እንደማያት ሆኜ አየኃት........
"ይሄ አስተያየት ያንቺ አይደለም"...አለችኝ ደንግጣ..."ነውር አልሰራሁም ልጄ...አልሰረቅኩም...እስኪያልፍ ያለፋል...እንዲህ ሆነን አንቀርም...የእርሱንም ውለታ የምንከፍልበት ጊዜ ይደርሳል...የሰጠንን ገንዘብ ጉሊት ቢጤ ልጀማምርበት አስቤያለሁ...አንቺ በልጅ  አቅምሽ ለእኔ ሆድ ስትሟሟቺ ቁጭ ብዬ ማየቱ ሰለቸኝ...አንገሸገሸኝ ልጄ".....ብላ ማልቀስ ከመጀመርዋ ወ/ሮ አፀደ ደርሰው እንባዋን ቆረጡት...


**



"ፈትልዬ...ፅኑቃል ... ኑ እንጂ ገበታ ቀርቧል...".....ወ/ሮ አፀደ ናቸው... በተአምራቸው በቀን ሶስቴ ይመግቡናል....አሁንም አጠራራቸው  እንድንበላ ነው....እየተሳቀቅንም ቢሆን እንበላለን...ሆድ መጥፎ ነው.....እንደው አንዳንዴ ብንጠቅማቸው ብለን ከቀን ፕሮግራም አንዱን እንዘላለን....


እንዲህ እንዲያ እያልን ተጨማሪ አንድ ሳምንት እሳቸው ቤት ቆየን...እናቴም በዚህ አንድ ሳምንት ጉሊት ለመጀመር የሚያስፈልጋትን ሁሉ አሟላች....
በአንዱ ማለዳ የወ/ሮ አፀደ በር ተቆረቆረ.....
"ማነው...ኧረ ማነው..."...በቅጡ ሳይነቁ መነፅራቸውን ፍለጋ መንተፋተፍ ያዙ.....እኔው እየተጫጫነኝ ተነስቼ ከፈትኩላቸው....ፖሊሶች ናቸው.....


ደርሰናል......



Shewit dorka



Https://www.tg-me.com/ethioleboled
የኛ ሰፈር....17




እግዜሩ ሲደክመው ሰዉ....ሰዉ ሲደክመው እግዜሩ እያሉ ነጠቃውን አጧጡፈውታል....ሁሉም ጨክኗል...ከፍቷል...


አባቴ በህይወት እያለ በነበረበት ብድር ምክንያት እናቴን አሰሯት....የአባቴ ብድር ከእናቴ ጋር ምን እንደሚያገናኘው ሳይገባኝ ወሰዷት...እንዴት ፣ ለምን ብልም መልስ የሚሰጠኝ ብቻ ሳይሆን መልስ ያለውም የለም....


አበዳሪው ገንዘቡ እናቴ ጋር እንደሆነ ሲናገር በፍፁም እርግጠኝነት ነው...ከዛ ቁርቁዝ ካለ ቤት 1 ሚሊየን ብር የያዘች የተበዳሪ ሚስት አለች ብሎ ሲናገር ከልቡ ነው...በየትኛው ልቡ እንደሆነ ባላውቅም ከልቡ ነው...

አንድ ሚልየን ብር ሲባል ከመስማት ውጪ አይታና ነክታ የማታውቀውን ምስኪን ሴት ወሰዷት....እርሷ ነበረች የቀረችኝ....ሄደች።


"ልንወስድሽ ነው የመጣነው ምን ማለት ነው ...?"...'ልንወስድሽ' ሌላ ትርጉም ያለው እንደሆነ ልጠይቅ ይሆን አልኩ...መውሰድ ከመውሰድ ውጪ ምን አይነት ትርጉም ይኖረዋል....አላውቅም ...

"የቀረውን ጣቢያ መጥተሽ መጠየቅ ትችያለሽ እባክሽን " ...'ጣቢያ ማለት'...አልኩ ደግሜ...የፖሊሱን አኳሀን ላየ ሬድዮ ጣቢያ ለቃለ መጠይቅ የሚወስዳት እንጂ ወንጀለኛ ነሽ እያለ ዘብጥያ የሚያወርዳት አይመስልም... ቀለል አርጎ ሚያወራው......እየተክለፈለፍኩ እናቴን የወሰዷት ጣቢያ  ሄድኩ.....

"እናትሽ ተጠርጣሪ ናት...ወንጀለኝነቷ ገና አልተረጋገጠም"...አለኝ ከነሱ አንዱ....
"ሲጀመር ከመቀፍደዳችሁ በፊት መጥሪያ ልትሰጧት ይገባ ነበር ... ከሳሽ ነኝ ያለውን ሰው ደግሞ..."...አላስጨረሰኝም....
"ስራችንን እየነገርሽኝ ነው"...እንደመኮሳተር እያለ...
"እንደዛ አላልኩም የኔ ወንድም.."
"ኢንስፔክተር"....ብሎ ማዕረጉን አስታወሰኝ...

"እሺ ኢንስፔክተር...ሳይነጋ መጥቶ የሰው እናት መውሰድን የትኛው አሰራር ነው የሚፈቅደው...".....ቢያንስ እንዴት እንደሚኬድ ካላወቀ ፊልም ላይ አያይም እንዴ አልኩ በሆዴ...
"ከቀድሞ ቤታችሁ መጥተን አስፈላጊውን መረጃ ወስደን ነው ወደ እናትሽ የመጣነው..."
"ማነው እንደዚህ አይነት መረጃ የሰጠው...?"
"ይቅርታ እመቤት ይሄን መናገር አልችልም..."
"ማለት እናቴ ላይ ጠቁመው ነው...እ...እ...".....ሰሞኑን ያለከልካይ ከሚወርደው እንባዬ ጋር ተናነቅኩ.....
"ተረጋጊ እመቤት".....ከመሬት ተነስተው እመቤት ሚያረጉኝ ነገር አለባቸው ደሞ....

ምንም የሚያረጋጋ ነገር በሌለበት 'ተረጋጊ' የሚሉትም ነገር አለ....


እናቴን የያዛት ፖሊስ አሁንም እንደያዛት ነው...ከጥያቄው በኃላ ይለቃታል ብዬ ባስብም አሁንም እጁ እሷ ላይ ነው...ከጣቢያው ሳይወጣ ይዟት በሌላ አቅጣጫ ታጠፈ....

"ወዴት ነው ምትወስዳት...ለጥያቄ ነው የምንወስዳት አላላችሁም...?"...ከኃላቸው እየተከተልኩ ጠየቅኩ....
"ወደማረፊያ ቤት"....መለሰልኝ....እናቴ አንገቷን እንደደፋች ናት....
"ምን ማለት ነው ማረፊያ ቤት "...የተለመደው ጩኧቴን እየጮህኩ ነው...
"ሂደቱን እየተከተልኩ ነው እመቤት እባክሽን"....
"ያንተን ሂደት ቀቅለህ ብላው"....ይሄን ካልኩት በኃላ ነው ፖሊስ እያወራው እንደነበር የታወሰኝ....እናቴ ላይ የሙጥኝ ያሉት እጆቹ እሷን ለቀው እኔ ላይ ተከመሩ...አንጠልጥሎ ከባዶ ክፍል ወረወረኝ እና ቆለፈብኝ.....አልታገልኩትም አልተወራጨሁም...አንድ ነገር ብቻ እንዲያረግልኝ ተማፀንኩት እንጂ...
"እናቴን ልቀቋት...እኔን እንደፈለጋችሁ አድርጉኝ....እናቴን አትሰሯት እባክህ ይሄን ብቻ አድርግልኝ...እናት የለህም...እ"

"እናቴን ባስብም ምንም አላደርግልሽም...ምንም ነገር ከህግ በላይ ሊሆን አይችልም".....



*


የተቆለፈው በር ቀትር ላይ ወለል አለ....

"አትወጪም...?..ተመችቶሽ ነው...?"...አለኝ ከፋቹ....
"ደግመህ ቆልፈውና የእናቴን ክፈተው.."
"እባክሽ እመቤት ትወጪ "...መልስ ሲያጣ ገባና ክንዴን ይዞ አንጠልጥሎ አወጣኝ....
"እባክህን እናቴን"....
"ያንቺ እዚ መሆን እናትሽን ነፃ አያደርጋትም...ህግ ነው ይሄ ጨዋታ አይደለም"....
"እስከ መቼ ነው የምታስሯት..."
"የፍርድ ሂደቱ እስኪፈፀም....አንቺም ማድረግ ያለብሽን ነገር አድርጊ... ጠበቃም ያስፈልግሻል... "
ደሞ ሌላ ስራ.....
"ልብስ እና ምግብ ማምጣት ትችያለሽ..."...ለካ እሱም አለ...
"እሺ አመጣለሁ...አሁን እናቴን ማየት እችላለሁ..?"...
"አትችይም"....ቁርጥ ያለ መልስ ሰጠኝ....


****


"ልጄ ምን ጉድ ነው"....አለችኝ እናቴ ምግብ እና ልብስ ከወሰድኩላት በኃላ በተሰጠችን ጥቂት ደቂቃ.....
"አላውቅም እማ አላውቅም....ግን እመኚኝ ከዚህ ትወጫለሽ እመኚኝ..."...
"ልጄ አልመሰለኝም...አልመሰለኝም..."....

....እጄን አጥብቃ ስትይዘኝ የአባቴን ሞት የሚያስታውስ ስሜት ተሰማኝ....
"አባትሽ ጉድ ሰራኝ...በተነን አባትሽ በተነን..እ...እ.."....ማልቀስ ጀመረች...እኔም እጇን አጥብቄ ይዜ መነፋረቄን ተያያዝኩት...

"መቀራረብ አይቻልም.!!!."...አጠገባችን የቆመው ፖሊስ ጮኧብን...እጄን ለቃ በስስት ታየኝ ጀመር....እኔም ከነ እንባዬ አያታለሁ...ታየኛለች...በዛ ዝም ባለ ድባብ

"ሰአት አልቋል"....ተባልን....

****

የጠ
በቃ ገንዘብ አይቀመስም....እንደተጠየቅኩት ገንዘብ ብዛት መርታትና መረታት ያለም አይመስልም....እንደ ብሩ መጠን መርታትና መርታት ብቻ ያለ ነው ሚመስለው... እናቴ ዳግም ተመልሳ ከዛ መቀመቅ ማትገባ....


ሳልወድ በግዴ ሄኖክ ጋር ደወልኩ...ጠበቃ የምቀጥርበት ገንዘብ ልጠይቅ...ተባበረኝ ልለው...ደወልኩ...ተነሳ...የሴት ድምፅ ነው....መጨረሻው

"ተሳስተሻል..." የሚል....ስልኩ ተዘጋ።



ይቀጥላል....



Shewit dorka




https://www.tg-me.com/ethioleboled
ዛሬ ከሰሞኑ የተፈፀመ አንድ አስተማሪ ታሪክ አነበብኩ

ነገሩ አንድ ትምህርት ቤት ውስጥ ነበር የሆነው ፕሮፌሰሩ ሁሉንም ተማሪዎች ከታች በምስሉ በምታዩት መልክ ፊኛ እየነፉ ስማቸውን እንዲፅፉበት አደረጉ።ቀጥሎ ሁሉም ፊኛዎች ወደ አዳራሽ ተለቅቀው እያንዳንዱ ተማሪ የየራሱን ስም(ፊኛ) እንዲፈልግ ታዘዘ።5 ደቂቃ ተሰጣቸው ምንም ያህል በችኮላ ቢፈልጉም ማንምየራሱን ፊኛ ማግኘት አልቻለም ጊዜውም አለቀ።

ፕሮፌሰሩ ቆይቶ ደግሞ ተጨማሪ 5 ደቂቃዎች በመስጠት ሁሉም ተማሪ ያገኘውን የሌላ ሰው ፊኛ ለባለቤቱ እንዲሰጥ አደረገ። አስገራሚ ውጤት ታየ ተማሪው በሙሉ እየተጠራራ አንዱ ለሌላው እያቀበለ 5 ደቂቃው ሳይገባደድ ሁሉም የየራሱን ፊኛ ተቀበለ።ፕሮፌሰር ነገሩን ከሕይወት ልምድ ጋር ያቆራኘበት አግባብ ነው ያስደሰተኝ።

"አያችሁ የናንተ ደስታና የልብ መሻትም እንደ ፊኛው ናቸው።

የራሳችንን ደስታ(ፊኛ)"

ብቻ ባሳደድን ቁጥር ልናገኘው አንችልም
ወይም እስክናገኘው ይቆያል።ይልቅዬ ለሰዎች ደስታ ፍላጎት ባሳየን በተባበርን መጠን ለራሳችንንም ደስታን በቀላሉ እንጎፀፋለን"

Https://www.tg-me.com/ethioleboled
📌ማጋራት አይዘንጋ!
@ETHIOLEBOLED
@ETHIOLEBOLED
📲Iphone 15ን ለመግዛት የተሰለፈ ህዝብ ነው አሉ🙈

እኔ ግን ለቻርጀሩ ነው ባይ ነኝ😁

                   🦋#Share🦋
👩‍💻 @ethioleboled
#EthioTechs_News📑

♦️ Telegram በትላንትናው እለት Anonymous Sudan በመባል በሚጠሩ ቡድኖች ጥቃት እንደደረሰባቸው አስታውቀዋል።

♦️ቡድኑም ባስተላለፈው መልዕክት በትላንትናው እለት September 22/2023 የ telegram መሰረተ ልማቶች ላይ ጥቃት እንደፈፀሙ አስታውቀዋል። ጥቃቱም ንጋት ላይ ለ50 ደቂቃ ያህል የቆየ ሲሆን የTelegram official website እና telegram bot API ላይ የተወሰነ ችግር ፈጥሮ ነበር።

♦️የጥቃቱ ምክንያት የነበረው ብዙ ሺህ ተከታይ የነበረውን የቡድኑ Telegram channel ban በመደረጉ ነው።

🦋#Share🦋
👩‍💻 @ethioleboled
የኛ ሰፈር....18



መቼ እንደሆነ በውል ባላስታውስም ከዚህ በፊት አቅሙ ለሌላቸው ሰዎች መንግስት ጠበቃ እንደሚቀጥር ጭምጭምታ ሰምቼ ነበር...እንደውም "ችሎት" ድራማ ላይ ይመስለኛል የሰማሁት.......


ስንቅ በማመላልስበት ወቅት ከአንድ የህግ ሰው ጋር ስለዚህ ጉዳይ ተማክሬም ነበር...


በአቅሜ ጉዳይ አንዳንድ መረጃዎች ከሰበሰቡ እና ካረጋገጡ በኃላ በድህነታችን ተስማምተው እንደተባለውም የመንግስት ጠበቃ በነፃ ቆመላት....ፈጣሪን ከብዙ ጊዜ በኃላ "ተመስገን" አልኩት...እንዲህ ሳባብለው እና የሰራትን ጥቂት ነገር ሳገዝፍለት ቀጣዩም ይሰምርልኛል ብዬ በማሰብ...እለማመጠው ገባሁ።


የምፅአት ቀኗ ደረሰች...የፍርድ ቀን ።

እሳት የላሰ ጠበቃ የቀጠረው የእናቴ ከሳሽ ከአገባቡ ጀምሮ ድል አድራጊነት ይነበብበት ነበር...እንደሚያሸንፍ እርግጠኛ የሆነ ፊት...ባሁኑ አልፀለይኩም...ወንድሜ ላይ የሰራሁትን ስህተት ለሁለተኛ ጊዜ መድገም አልፈለግኩም....


የፍርድ ሂደቱ ጀመረ....እናቴን እንዳየኃት ሆዴ ተንቦጫቦጨ...በአይኔ 'ሁሉም ነገር ይስተካከላል አታስቢ አልኳት'....አይኗ ውስጥ የማየውን ፍርሀት ጨርሶ ባላባርርላትም ትንሽ እንዲያፈገፍግ ምክንያት የሚሆን አስተያየት ነው ያየኃት....



የፍርድ ሂደቱ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ እኔ ከራሴ ጋር አልነበርኩም... ሁሉም ነገር ጥያቄ ሆኖብኝ ነበር...ሙሉ ሰአቱን ምንድን ነው ጉዱ እያልኩ ነበር...ከሰነድ ማስረጃዎች ጀምሮ እስከ ቃል ምስክሮች ሁሉም የእናቴን ወንጀለኝነት የሚያረጋግጡ ነበሩ።...የእናቴ ጠበቃ ደግሞ እጅ እና እግሩን ብቻ ነው ይዞ የመጣው ብል ማጋነን አይሆንም....ይሄ ለእኛ የፍርድ ቀን ሳይሆን የእርድ ቀን ነበር።


ውሳኔው ደግሞ ተበጥሶ ያለቀውን ወሽመጤን ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከስሩ ቆርጦ የሚጥል ሆነ....የአምስት አመት ፅኑ እስራት ወይም የአምስት መቶ ሺህ የገንዘብ ቅጣት.....ከዚህ በላይ የማየውንና የምሰማውን መሸከም አልቻልኩም.....ተዝለፍልፌ ወደቅኩ።



*



በአንድ ለሊት እስከ 10,000 አገኛለሁ.."
....እልፍ ስል ነው የሰማኃት...ሰምቼም አላለፍኳትም...
"ምንድን ነው የምትሰሪው...?"....ጠየቅኩ...
" አቤት.."....
"ይቅርታ እናት ስራሽ ምንድን ነው.."....
"ታውቂኛለሽ..?"...ባውቃት ለምን እጠይቃታለሁ...ባውቃትማ ስራዋንም አውቅ ይሆን ነበር.....
"እንተዋወቅ..."....አልኳት ፈገግ ብዬ...ያለመደብኝን ተግባቢ ሆኜ...
"ዊንታ እባላለሁ..."

"ፅኑ ቃል" ....
"እና ለመተዋወቅ ምን አነሳሳሽ...? "....
"ስራሽን ከመጠየቄ በፊት ላውቅሽ ይገባል ብዬ ነው"....
"ስሜን ስላወቅሽ ብቻ እንዳወቅሽኝ ነው ሚሰማሽ..."...አለችኝ ኮስተር ብላ...
"አይ አይደለም...ግን ስለስራሽ ማወቅ ፈልጌ ነው...በአንድ ለሊት 10,000 ምናምን ስትዪ የሰማሁ መሰለኝ"... ፈራ ተባ እያልኩ ወደ ጉዳዬ ገባሁ...
"ምን አይነት ስራ ነው...? የግል ነው ወይስ ተቀጥረሽ...?"...ጥያቄ አከታተልኩ...ተንገበገብኩ....


በምናቤ ስንት ወር ብሰራ አምስት መቶ ሺህ ብር እንደሚሞላልኝ እያሰብኩ ነው...አፍ አፏን እያየሁ መልሷን እጠባበቃለሁ...እሷ ግን ተረጋግታለች...
"በደንብ ሰምተሽኛል ግን...?"
"አዎ ሰምቼሻለሁ"...
"ለሊት ነው ያልኩት"...
"ችግር የለውም ሰአቱ መቼም ቢሆን...ክፍት ቦታ ካለ እባክሽ"....



"ጤነኛ ነሽ ግን...?"....ይሄን ስትለኝ እንደለመድኩት ልውለበልባት ነበር...በነበር ቀረ እንጂ....
"ምነው ጤነኝነቴን ሚያጠራጥር ምን አየሽብኝ...?"...
"ጤነኛ የሚያስብል ነገር ነው ያጣሁብሽ.."...አለችኝ ፈርጠም ብላ...ኧረ ንቀት አልኩኝ በሆዴ...ንዴቴን ዋጥኩት...ስሜቴን በደልኩት...
"እሺ እብድ ነኝ... አታስቢ አልጎዳሽም...ድንጋይ ይዤ ካንቺ ጋር የምሯሯጥበት አቅም የሌለኝ በጣም ስራ የሚያስፈልጋት ምስኪን እብድ"...ንዴቴን በቃላት አልቀምረው እንጂ ድምፄ ላይ ቅልብጭ ብሏል...ደነገጠች...ከዛም አጠገቧ እንድቀመጥ በአይኗ ነገረችኝ...እኔማ እንደመልሴ ጥላኝ ምትሮጥ መስሎኝ ነበር....


"ስራው አይሆንሽም"....
"ለምን..."
" ጥሩ ስራ አይደለም"....
"በአንድ ለሊት 10,000 እንዴት ነው መጥፎ ሚሆነው..?"
"ብሩን ብቻ አይደለም ማየት ያለብሽ.. ስራውንም በደንብ መጠየቅ አለብሽ"...
"ምንድን ነው ስራው ብዬ ጠይቄሻለሁ..ደግሞ ስራው ምንም ቢሆን እስር ቤት ከምትማቅቀው እናቴ ህይወት አይበልጥም...በምንም አይነት መመዘኛ እሷን የሚተካ ነገር የለም...እናቴ ናት...አንድ የቀረችኝ አይኔ...አንድ አይን ያለው በአይን አይጫወትም አይደል ...በይ ንገሪኝ ስራው ምንድን ነው?"
"ሴተኛ አዳሪነት"...ስትለኝ እንደ ሎጥ ሚስት ደርቄ ቀረሁ...የጨው ሀውልት ሳይሆን የድንጋይ ሀውልት ሆንኩ....


"ጥሩ ስራ አይደለም ብዬሽ ነበር..."....አለችኝ መደንገጤን አይታ......ምን እንደምላት ግራ ገባኝ...
"አጣብቂኝ ውስጥ እንዳለሽ ግልፅ ነው..ይሄ ስራ ምርጫ ስታጪ የምትገቢበት ነው...የቱ እንደሚበልጥ በደንብ አስቢ...."
"ምንድን ነው የማወዳድረው...?"..የሞት ሞቴን ይቺን ጠየቅኩ....
"ያንቺ ክብር ወይስ የእናትሽ ፍቅር...?....
"በሁለቱም አልደራደርም"....መለስኩ ...
"ክብርሽን ታቅፈሽ እናትሽ ላይ ከፈረድሽ ምርጫው ያንቺ ነው...እየገፋፋሁሸ አይደለም...ስራውን እኔም አልወደውም...ግን አባቴን ማስታመሜን እና ለአባቴ መድሀኒት መግዛቴን እወደዋለሁ...በደንብ አስቢበት ክብር እናት ሊሆንሽ አይችልም....ሁለት ወዶ አይሆንም...ልጅም ወዶ ምጥም ፈርቶ."....ሁለት ለመምረጥ የሚከብዱ ነገሮች ....



እየገፋፋሁሽ አይደለም ብላ እየገፋፋቺኝ ነው....እናት አንድ ናት...ክብር ስንት ነው...?ሰው ሆኖ እንደ እቃ ገበያ ላይ መውጣት ስንት ፍሬ ነው...ተሽጬ እናቴን ከማገኛት እና ሳልሸጥ ከማጣት...?
ባደርገው እናቴን አግኝቼ እኔን አጣለሁ..... እናቴም ታጣኛለች...እናቴስ የቱን ትመርጣለች...? ከልጇ እና ከነፃነቷ...
አንድ ነፃነት...? በስንት ክብር...?
አንድ እናት ....?በስንት ክብር...?

  የእናት ፍቅር ወይስ የራስ ክብር...?...እንደተለመደው አጣብቂኝ ውስጥ ገባሁ...የቱን ልምረጥ...እናቴን ወይስ ክብሬን....



አላለቀም......አስተያየታችሁን እፈልጋለሁ ቤተሰብ🙏







Shewit dorka


Https://www.tg-me.com/ethioleboled
የኛ ሰፈር....19




"ምርጫ የሌለው ምርጫ"...ደራሲዋ ያለችው ትዝ አለኝ...ምርጫ የሌለው ሌላ ምርጫ...ይሄ ክብር የእኔ ክብር ብቻ ነው...? የእናቴ ነፃነትስ የእሷ ነፃነት ብቻ ነው...?


አላውቅም...'ምርጫ ስታጪ የምትገቢበት ነው'...አይደል ያለችኝ....ምርጫ እስከማጣ መጠበቅ ሊኖርብኝ ነው....


ምርጫ አንድ..የአባቴ ቤተሰቦች...


እስከ ሚመሽ አውጠነጠንኩ...መሽቶም እስኪጋ ቀጠልኩ...ለሊቱ ያለ እንቅልፍ አለቀ...ክብር ወይስ ፍቅር በሚል ውስጣዊ ድምፅ ....ለራሴ ብቻ የሚሰማ ድምፅ ...ጆሮዬ ላይ የማይደርስ ከራስ ለራስ የመጣ ድምፅ...እናትሽን ወይስ አንቺን...በያ ምረጪ...ጊዜ የለሽም...ያጣድፈኛል.... እንዲሁ ስሟገት አዳር አይሉት አዳር አደርኩ...



አዳሬ ያለቀ ሲመስለኝ የአባቴ ቤተሰቦች ቤት ማልጄ ሄድኩኝ....ከደረስኩ በኃላ ሰአቴን ሳየው 12:30 ይላል....ቢያንስ አንድ ሰአት እስኪሆን ልጠብቅ አልኩ....መታገስ ሲያቅተኝ እያምታታው አንኳኳሁ...የምጠብቃት 30 ደቂቃ ብቻዋን ዘመን ሆነችብኝ...ገና ከማንኳኳቴ በሩ ወለል ብሎ ተከፈተልኝ...ጥበቃው በሩ ስር ተለጥፎ እየጠበቀኝ የነበረም መሰለኝ...እኔን ከማየቱ በሩን አስታቀፈኝ...ጠረቀመብኝ...አኳሀኑን ላየ አር የነካው እንጨት የጨበጠ እንጂ እንደሱ አይነት ሌላ ፍጡር ያየ አይመስልም...ዘገነንኩት....



በሩን ደበደብኩ....

"ምንድን ነው ጉዱ"...
"ኧረ ደረጄ ምንድን ነው....ማነው ሳይነጋ..."....ከውስጥ ድምፅ ይሰማል...
"ያቺ ወሮ በላ ናት...."...ጥበቃው መለሰ....
"ክፈተውና ወሮበልነቴን ላረጋግጥልህ...ሽንታም...ክፈተው..."
በኔ ጩኧት ሳይሆን በነሱ ይሁንታ ተከፈተልኝ...ሲከፈት የገነት በር የተከፈተ ያህል ሀሴት ተሰማኝ...ተዘግቶ ሲከፈት ለመግባት ያጓጓል አይደል...መልሶ ይዘጋብኝ ይመስል  ዘልዬ ገባሁ...


...እንደገባሁ ከአባቴ ቤተሰቦች ጋር ተፋጠጥን....
"ስነስርአት ለምን አይኖርሽም...?"...አክስቴ ጀመረች...
"ባለቤቱን ካልናቁ አጥር አይነቀንቁ"....አጎቴ ቀጠለ....
"ምን ፈለግሽ...?"...እኩያዬ ተጨመረች...የአክስቴ ልጅ ናት....

"በምትወዱት ሁሉ ልለምናችሁ...በፈጠራችሁ...እናቴን አትውሰዱብኝ...አትቀሙኝ...ምንም ማንምም አልቀረኝም..."...
"ምንድን ነው ምታወራው...?"....ጠየቀች እኩያዬ...
"ወደ ውስጥ ግቢና እንነጋገር"....አለ አጎቴ...አይኔን አላሸሁም...ተከታትለው ሲገቡ እኔም ተከተልኳቸሁ...



"ምንድን ነው የምትይን"....አክስቴ ጠየቀች....
"እናቴን አስረዋታል...እናንተ ከሆናችሁ የጠቆማችሁት እባካችሁ...."
"ለምን አትተይንም...?....አጎቴ ነው ይህን ባዩ....


"እናንተ ናችሁ አልተው ያላችሁን...."....የፈረደበት ጩኧቴ መጣ...
"ማን ነው ገና ሳይነጋ የሰው ቤት መጥቶ እየበጠበጠ ያለው"....አለች አክስቴ...
"እንድመጣ ያደረጋችሁኝ ራሳችሁ ናችሁ"...
"በደፈናው ከምትወቅሺን አጥፍታችሁብኛል ካልሽ ክሰሺን"...አለ አጎቴ...እንደማልከሰው ጠንቅቆ ስለሚያውቅ....ባሁኑ አልተሞኘሁም...ንዴቴን ውጬ ተስፈንጥሬ እግሩ ላይ ተደፋሁ....
"እባካችሁን እናቴን አትውሰዱብኝ...በአባዬ አጥንት ይዣችኃለሁ"....ቁጣዬ የትም እንደማያደርሰኝ ሲገባኝ እግሩ ስር ተደፋሁ....እናቴን ስል ከስሩ ተገኘሁ...




እንደዚህ አይደል...ሲገድ አይደል የተጠላ የሚወደደው...ሲገድ አይደል እሬት የሚጣፍጠው...ሲገድ አይደል መቃብር ሚሞቀው...ሲገድ እኮ ስሜትን ማባበል ይቀራል...ንዴትን መናደድም ዘበት ይሆናል..."እኔ እንዲህ ነኝ"...ብሎ ማውራትም ይቀራል...ያኔ እኛ እኛ ሳንሆን ያስገደደንን ነገር እንሆናለን...ሁሉም ይቀርና የግዳችንን እንኖራለን...ያስገደደንን ነገር ከረሳን ደግሞ ፈተናውን እንወድቃለን...ስንወድቅ ደግሞ ብቻችንን አይደለም...የምንወዳቸውንም ሰዎች ይዘን ነው የምንወድቀው...ገደሉ ከልቡ ገደል ከሆነ ገደል ውስጥ እራሳችንን ከምንወዳቸው ሰዎች ጋር እናገኘዋለን... መውጫ ገመድ የሌለው ...በዙሪያው ብዙ ጆሮ ለምልክት ያህል የተሰጣቸው ለእኛ ጩኧት ጆሮ የሌላቸው ሰዎች ከከበቡት ገደል ውስጥ እንረሳለን...ያኔ ሰው መሆናችንን እንረሳለን....



አሁንም እግሩ ስር ነኝ...ይሄም እኮ አንድ ምርጫ ነው...

"ምርጫ ስታጪ "...አይደል የተባልኩት...ነገ እራሴን ካንዱ ጉያ ገላዬንም መጫወቻ ከማድረጌ በፊት የምመርጠው ምርጫ...ይሄ ምርጫ እንደ እቃ አልጋ ላይ ከመወርወር ካተረፈኝ ምንስ ቢመር...ይሄ ምርጫ እራሴን ሳላጣ እናቴን ከሰጠኝ ምንስ ቢያሳፍር......




የተወሰኑ ክፍላት ብቻ ናቸው ሚቀሩን......




Shewit dorka

Https://www.tg-me.com/ethioleboled
ለፈገግታ😁




Based on true story😁



ሰሞኑን የፅኑ ቃል ነገር ላስጨነቃችሁ አንባብያን



ሰላም ትባላለች...አብሮ አደጌ ናት...ትናንትና በበራችን እልፍ ስትል ሲያንቀለቅለኝ መጥራት...ከዛ እሷም ሱቅ እንደተላከች እና አብረን እንድንሄድ መጠየቅ...እኔም እሺ ማለት....

ሱቅ ሳንደርስ ስልኳ ጠርቶ ማውራት ጀመረች....ችግሩ የተፈጠረው ይሄን ጊዜ ነው...ሱቁ ጋር ስንደርስ እንድናልፈው በአይኗ ምልክት ሰጠችኝ...ከስልኩ ጥሪ በፊት ወሬያችንን ስንቀድ ምን እንደተላከች አልጠየቅኳትም ነበር...በውስጤ በቃ አብዲ ሱቅ የሌለ ነገር ተልካ ይሆናል ብዬ ደመደምኩ...(በ 22 አመታችን ሱቅ የምንላክ ብርቅዬ ወጣቶች ነን በዚህ አጋጣሚ😁)....ከዛላችሁ ብንጓዝ ብንጓዝ ጀለስ ምንም አትልም... ሰፈራችን አውቶቢስ ተራ ነው...ከአስፋልቱ ገባ ብሎ....ወደ ስድስት ሱቅ አልፈን አዲሱ ሚካኤል ደረስን...አሁንም ልጅት ደዋዩ የሚያያት ይመስል እየተሽኮረመመች ታሽካካለች...ታምኑኛላችሁ ፓስተር ደረስን...አሁንም የተቀየረ ነገር የለም... ጳውሎስ ሆስፒታልን ማለፍ ስንጀምር ስልኩ ተዘጋ...


"ወይኔ ቻርጅ ዘጋብኝ"....ብላ ስትበሳጭ እኔ ደግሞ

"ተመስገን"  አልኩኝ...

"በዚህ አያያዛችን ቡራዩ መድረሳችን ነበር...ያምሻል እንዴ ምንድን ነው ምንገዛው ይሄን ያህል...."

"በቃ አብዲ ሱቅ እንሂድ...."...አለችኝ አይኔን ማየት እያፈረች....

"አብዲ ...አብዲ...የኛ አብዲ..."...ጆሮዬን ማመን አልቻልኩም....አብዲ ማለት እኮ በራችን ላይ ያለ ሱቅ ነው...

"ምን መሆንሽ ነው...ያምሻል...እንዴ እሺ ለምን ስናልፈው ዝም አልሽ...እዚ ድረስ....".....የምሬን ነው የተበሳጨሁት....መልሷን ስሰማ ግን የተበሳጨሁትን ያሀል አሽካካሁ...

ምን ብትል ደስ ይላችኃል....😁


"እና ስልኩን ሳልዘጋው የ 10 ብር ስኳር ልበልልሽ ደፋር..."....😂


እንደዚህ አይነት ጓደኛ አይስጥ😂😂😂😂



Shewit dorka




https://www.tg-me.com/ethioleboled
2024/09/22 19:22:51
Back to Top
HTML Embed Code: