Telegram Web Link
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
💥📚ኢትዮ-ልቦለድ📚📖💥
Photo
.              ♥️●●●ነጠብጣብ●●●♥️

       

                            
#ክፍል_4

...🖊የኢክራምን ስልክ የሪም እድሜ ይርዘምና ምንም ሳልለፋ አገኘሁት። በነጋታዉ ኢክራምን ለመጀመሪያ ጊዜ በስልክ ላወራት ደወልኩ። ስታወራ ደስ ትላለች። አዳማጭ ብቻ ሆና አታስጨንቅም።

አስራስድስት ደቂቃ አወራን ፣ ከማላዉቃት ሴት ጋር ያዉም ለመጀመሪያ ጊዜ እያወራን ይህን ሁላ ደቂቃ ማናገሬ ገርሞኛል። በሁለተኛዉ ቀን ደዉዬ ስናወራ "ኢክሩ ግን ትኮሪያለሽ አይደል?" አልኳት።
"ምነዉ? ምናጠፋሁ?" አለችኝ ግራ እየተጋባች።

"አንቺ መች ታስታዉሺኛለሽ፣ ኧረ አንቺም ፈልጊኝ!!" አልኳት። ሁሉም ነገር እኮ በአንድ ወገን በኩል ብቻ ሲሆን ያስጠላል። ሰጥቶ እንደመቀበል የሚያስደስት ነገር የለም።

አንዳንዶች ሁሌ እንድትሰጧቸዉ ብቻ ይፈልጋሉ። እነሱ ግን በምላሹ ምንም አይሰጧችሁም። ይሄ የወዳጅነት ትስስርን ይነቀንቃል።

እኔም እኔ ብቻ ስደዉል እኔ ብቻ ፈላጊ እንደሆንኩ ስለተሰማኝ ነዉ እንዲህ ያልኳት።
ኢክሩ እየተቅለሰለሰች "ኧረ አልኮራም፣ እደዉላለሁ ችግር የለዉም ፈዉዛኔ!!" አለችኝ።
ከዚህ ቀን ጀምሮ በተራ መደዋወል ጀመርን።

እኔ ዛሬ ከደወልኩ እሷ ነገ ትደዉላለች። በስልክ በምናወራበት ሰአት ስለሷ አንዳንድ ነገሮችን አወቅኩ። አባቷ በህይወት የለም። ወንድምም ሆነ እህት የላትም። ከእናቷ ጋር ብቻቸዉን ነዉ የሚኖሩት። ብቸኛ ወዳጇ ፊልም ነዉ። ሲደብራት ተከታታይ ፊልሞችን ዲሽ ላይ ትከታተላለች። ፊልም ነዉ ያሳደጋት። ፊልም እያየች አድጋ ነዉ እኔም ላይ ቆንጆ ፊልም የሰራችብኝ!! ያየችዉን ነዉ የተገበረችብኝ!!
.
ኢክራም ታሪኳን ስትነግረኝ ምናልባት በህይወቷ ዉስጥ ያጣችዉን ወንድሟን ሆኜ ብቸኝነቷን ላስረሳት አሰብኩ። የጅንጀና ሙዴ ሁሉ ተጦለበ። በቃ ንፁህ ወንድሟ ለመሆን አለምኩ።

አንድ ቀን ማታ ላይ ኡስማን ከሚባል ጓደኛዬ ጋር ወደ ሰፈር እየገባን ስሟን ሳልነግረዉ ታሪኳን አጫወትኩትና ከኔ ይልቅ እሱ ሴት መንከባከብ ስለሚችል እንደዉም ባስተዋዉቃቸዉና እሱ ቢንከባከባት ደስ እንደሚለኝ ነገርኩት።

ኡስማን ደግሞ በጣም የምወደዉ መስጂድ የተዋወቅኩት ጓደኛዬ ነዉ።
ታሪኳን ከነገርኩት በኋላ እሱም ልቡ ተነክቶ "ፈዉዛኔ እቺን ምርጥ ሀብታም ፈልጎ አሁኑኑ መዳር ነዉ!!" አለኝ። በሰፊዉ እንደምናወራበት ተነጋግረን ከኡስማን ጋር ተለያየን። ከዛ በኋላ ግን ከኡስማን ጋር ስለሷ አዉርቼ አላዉቅም።

ኡስማን ወንድ ነዉ ግን እዉነት ለመናገር ለሴት ከንፈሯ ሲያምር ምናምን እንደምንለዉ ፀጉሩ፣ መልኩ በአጠቃላይ የሚያምር ልጅ ነዉ። በጣም ደግሞ ተግባቢ ነዉ። በጣም ብዙ ሴቶች የሚመኙት ወንድ ነዉ። ኢክሩን እንዲንከባከባት ያሰብኩት ከዚህ በፊት ካለዉ ልምድ ተነስቼ ነበር።

ዉስጤ ላይ ያደረዉ የወንድምነት መንፈስ ከኔ ሴት በመንከባከብ ለተሻለ ወንድ አሳልፎ እስከመስጠት ወስዶኝ ነበር። የፈጣሪ ጥበብ ግን ይገርማል ትናንተ ስለማላዉቃት አንድ ሴት ዛሬ ከማንም በላይ የምጨነቅ ፍጡር እንድሆን አደረገኝ።
.
ከኢክራም ጋር ግንኙነታችን ከስልክ በአካል ወደመገናኘት ሊያድግ ቀን ቆረጥን። አርብ ዕለት ማታ አንድ ሰአት ላይ ሰፈራችን በሚገኘዉ አስፓልት ላይ ዎክ ለማድረግ ተቀጣጠርን።

ከሴት ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ ለመገናኘት ስትቀጣጠሩ የሆነ የሚጨንቅ ነገር አለዉ። ልጅቷ ተጫዋች ናት ወይስ አንገቷን ከማነቃነቅ ዉጪ ምንም የማታወራ ልጉም የሚለዉ ያስጨንቃል። እኔ ግን አንድ ቀን ታክሲ ዉስጥ ስላገኘኋት ነዉ መሰለኝ ብዙም አልተጨነቅኩም። ይልቁንስ ስለዉበቷ ነዉ የማስበዉ ፣ ስትሽኮረመም በአይነህሊናዬ ይታየኛል።

ከዛም በስልክ ያወራነዉ ታሪኳ ትዝ ይለኝና ስሜቴን አፍነዋለሁ። ከሴት ጋር ተቀጣጥሮ የመንዘላዘል ልምድ የለኝም። አሁን ግን መንዘላዘልም በሉት ምን ከኢክራም ጋር ለመገናኘት ተቀጣጥሬያለሁ።
.
ጁምዓ ደረሰ!! ማታ ላይ ኢክራም ከሪም ጋር ሆና የተቀጣጠርንበት ቦታ ላይ ተገናኘን። እኔ ግን ግራ የሚገባኝ ሴቶች ለምንድነዉ የመጀመሪያ ቀን ስትቀጥሯቸዉ ከጓደኛቸዉ ጋር የሚመጡት? እኔ ግን ስገምት ደህንነት የሚሰማቸዉ አይመስለኝም።

ምናልባት ወንዱ አደብ ከሌለዉ ስርዓት ለማስያዝ አሊያም አብሮ ለመጮህም ሊሆን ይችላል ሁለት ሆነዉ የሚመጡት። ኢክራም ቤት ስትመለስ ሪም ጋር ነበርኩ ለማለት አቅዳ ነዉ በድፍረት በማታ ያገኘችኝ። ከዛ ቀን በኋላ እስክንለያይ ድረስ በዛ ሰዓት አግኝቼያት አላዉቅም። እስከምሽቱ ሁለት ሰዓት ያመሸነዉ የዛኔ ብቻ ነዉ።

ኢክራምን ገና ከሩቅ ሳያት ልቤ "የምን ወንድምነት ነዉ? እያት እስኪ ያስችልሀል?" እያለ ሞገተኝ። ልቤን አደብ አስገዝቼ እነ ኢክራምን ተቀላቀልኳቸዉ። ሁለቱም የለበሱት ሺቲ ነዉ። ኢክራም ከላይ ጃኬት ደርባለች። በጅልባብ ስላልመጣች ጌታዬን አመሰገንኩ።

ሺቲ እና ድሪያ ልዩነቱ ምን እንደሆነ አላዉቅም። የልብሱ ስም ሺቲ እንደሚባል ኋላ ላይ ነዉ ኢክሩ ራሷ የነገረችኝ። ንፋሱ የለበሰችዉን ሺቲ ገላዋ ላይ ሲለጥፈዉ የሰዉነቷ ቅርፅ ወለል ብሎ ታየኝ። መጠነኛ መቀመጫ አላት ፣ ወገቧ ከመቀመጫዋ እጅጉን ቀጥኖ ስምንት ቁጥር ሰርቷል።

ንፋስን ቅርጿን እንዳይ ስፖንሰር ስላደረገኝ ከልብ አመሰገንኩ። ወዲያዉ ሪም ተሰናብታን ሄደች።
እኔና ኢክሩ ብቻ ፣ ማታ ላይ ፣የመንገድ መብራት ባስጌጠዉ ዉብ ጎዳና ላይ አብረን ቀረን። ግን አልተፈራራንም አንዳንችን በአንዳችን መኖር ምቾት ተሰምቶናል። ምናልባት በህይወቴ እስከዛሬ ካደረግኳቸዉ ዎኮች ዉስጥ የህይወቴን ልዩ ታሪክ የመሰረተዉ ዎክ ይሄ ይመስለኛል።
"ኢክራም" አልኳት መንገድ መንገዱን እያየሁ።
"አቤት ፈዉዛን" አለችኝ አንገቷን ወደኔ አዙራ።
"ባለፈዉ ታክሲ ዉስጥ ስንገናኝ ጅልባብ ነበር የለበስሽዉ ዛሬ እንዴት አወለቅሽዉ?" አልኳት።
ፈገግ አለች እና እጆቿን እያፋጨች "ጅልባብ ሀይማኖታዊ ልብስ ነዉ!! እስልምና ደግሞ በጋብቻ ካልተሳሰርኩት ወንድ አሊያም ዘመዴ ካልሆነ ሰዉ ጋር እንዲህ እንድሆን አይፈቅድም።

በአጭሩ የሀይማኖት ልብስ ለብሼ እምነቴ የከለከለኝን ነገር ላለማድረግ ብዬ ነዉ!! ሀይማኖታችንን ላለማሰደብ!!" አለችኝ።
በመልሷ በጣም ደስ ተሰኘሁኝ።

እኔም ለጅልባቧ እና ለሀይማኖቷ ባላት ክብር አደነቅኳት።
ፈገግ ብዬ "ሁሌም እኔን ስታገኚኝ ጅልባብ ባትለብሺ ደስ ይለኛል።" አልኳት።
"ይኸዉ ልክ እንደዚህ በሺቲ እመጣለሁ።" አለችኝ አንገቷን በሀፍረት እየሰበረች
በልቤ በጣም ሳቅኩ ፣ ደስ አለኝ!! በሺቲ እመጣለሁ ስላለችኝ አይደለም። ግን በንግግሯ ዉስጥ ከዚህ በኋላም እንገናኛለን የሚል መልዕክት ነበር።
"ኢክሩ ባለፈዉ ግን ለምንድን ነበር ታክሲ ዉስጥ እያየሽኝ የሳቅሽዉ?" አልኳት ትልቅ ነገር እንዳስታወሰ ሰዉ ወደሷ እየዞርኩ

"እንዴ ፈዉዛኔ ታክሲዉ ዉስጥ ስትቃለድ የነበረዉ እኮ ከሴቶች ጋር ነበር። እኔ ደግሞ በጣም ኮስታራ ስለምትመስለኝ ሴት የምታናግር ራሱ አይመስለኝም ነበር።" አለችኝ ልክ እንደባለፈዉ እየሳቀች


ይቀጥላል
...
❤️በቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ከወደዱት Like ተጫኑ
 
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
ቁጥብ ናት የተሰማትን ሁሉ የማትናገር ። መንገደኛ ሁላ የማይደፍራት ፣ ቁስ ያለው ስታይ ቀልቧ ስፍስፍ የማይል ሁነኛ ነብስ ያላት ቋንጆ ልጅ ነች።

ዝም ብላ ሰው ላይ አትፈርድም ። ስትስቅ ደስ ትላለች ። አራዳነት ስለሚያጠቃት ጨዋታ ይገባታል ። እኔ እንደወደድኳት አልወደኝ ብላ ነበር ። እወድሻለሁ ስላት እሺ ነበር የምትለኝ ።

አስሬ አትደውልልኝም ነበር፦

ከደበራት ድብርት ላለማጋባት ዝም ትላለች። እንደደበራት በከንፈሯ ነው የማውቀው ። ከንፈሯን ለቀቅ ነገር ታደረገዋለች ።

በሂደት ቀስ እያለች ወደደቺኝ

ሁኔታዬ ያሳስባት ጀመር ። ደና ነህ የምትለኝ ለምዶባት አይደለም ደህንነቴን ለማወቅ ነው። ለህልሜ መሳካት ማገር እያቀበለቺኝ ነው ።

ስትናፍቀኝ ናፍቆቷን ታሳየኛለች ። መውደዷን በየሁኔታዋ አየው ጀመር ። መውደዶን በየአጋጣሚው ስራዬ ብላ ደውላ ትነግረኛለች ።

የምትወልድልኝን የሰባት ልጆች ስም ትነግረኛለች ። የአንዱንም ልጅ ስም እኔ ማውጣት እንዳለብኝ አላወቀችም መሰለኝ ።

በዚህ ኑሮ ሰባት ልጅ የምወልደው በእኛ ጥንካሬ ኑሮ ስለማይረታን ነው ብላ ትጎርራለች ።

<<ጭንቅላት በኔ መልክ ባንተ ቢወጡ አሪፍ ነው >> ትላለች።
<<ፉንጋም ሰነፍም ከሚሆኑ ። ጭንቅላት በኔ መልክ ባንቺ ቢወጡ ይሻላል>> እላታለሁ

እገልሃለሁ... ብላ አነገቴ ስር ገብታ ትነክሰኛለች ።

ንክሳቷ አንገቴ ላይ ምልክቱን ያኖራል ህመም የሌለው የንክሻ ምልክት ። ፍቅር ከሆነ ንክሻ ራሱ ትዝታ ነው ።
ሃዬ ፦
ፍቅር ለዘላለም ይኑር
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
💥📚ኢትዮ-ልቦለድ📚📖💥
Photo
           ♥️●●●#ነጠብጣብ●●

        
#ክፍል_5

እንዴ ፈዉዛኔ ታክሲዉ ዉስጥ ስትቃለድ የነበረዉ እኮ ከሴቶች ጋር ነበር። እኔ ደግሞ በጣም ኮስታራ ስለምትመስለኝ ሴት የምታናግር ራሱ አይመስለኝም ነበር።" አለችኝ ልክ እንደባለፈዉ እየሳቀች

ብዙዎች የሚታሰቡት እነሱ እንደሆኑት አይደለም። ተመልካቹ እንደሚስላቸዉ ነዉ። እንደኔ እኮ ተጫዋች የለም ግን ኮስታራ መሰልኳት። ይገርማል!!

.
ሁለት ሰአት ሊሆን ሲል ከኢክሩ ጋር ተለያየን። ቤቷን ስለማላዉቀዉ እስከቤቷ አልሸኘኋትም። የሰፈራችን መስጂድ ጋር ስንደርስ አዛን እያለ ነበር።

አዛን ማለት ሁሌም ከመስጂድ የሚሰማዉ "አላሁአክበር" የሚለዉ የስግደት ሰዓት መድረሱን መጠቆሚያ ድምፅ ነዉ። እሷ በቅያሱ ታጥፋ ሄደች እኔ መስጂድ ገባሁ። መስጂዱ አካባቢ ያሉ ሰዎች እንዳያዩን ሁለታችን ም እየተጠነቀቅን ነበር። በተለይ እኔ በጣም ብዙ ሰዉ ስለሚያዉቀኝ ከሴት ጋር በማታ መታየቴ ጥሩ አርአያ አይደለም።
ስግደቱ ካለቀ በኋላ ማታ ላይ ወደቤት ገብቼ ኢክሩን ማሰብ ጀመርኩ።

የሆነች ትልቅ ባህር ዉስጥ የተጣለች ትንሽዬ አሳ መሰለችኝ። ሰዉ በሞላበት ሀገር ዉስጥ ሰዉ የምትራብ ሚስኪን ፍጡር!! የእዉነት በጣም አሳዘነችኝ። የብቸኝነት ብርዷን ገፍፌ በሷነቷ ዉስጥ ትንሽ ሙቀት ለመፍጠር ለራሴ ቃል ገባሁ። ሰዉ ነኝ ስሜቴን ልቆጣጠረዉ እንጂ እሱ እንዲቆጣጠረኝ ልፈቅድለት አይገባም። ምንም ወንድነቴ ቆንጆ ከንፈሮቿን እንደቀስምለት ቢማፀነኝም ከሷ ጋር ክፍተቷን ለመሙላት በወንድምነት መቆየቱ የተሻለ እንደሆነ አሳመንኩት።

ግን ቀላል አልነበረም ከራስ ጋር መደራደር ይከብዳል። እዉነት ሰዉ መሆኔን ለማረጋገጥ ግን በየቀኑ የሚያማልሉ መልዕክቶችን የሚልኩልኝን ሴቶች ገፍቼ ለቀረብኳት ኢክራም ወንድም ለመሆን ወሰንኩ። የወንድነቴን ልመና እምቢ አልኩት። እምቢ የማለት አቅም አለኝ ብያችሁም አልነበር? ይኸዉ ወንድነቴን እምቢ አልኩት።

            
            ...🖊ለመጀመሪያ ጊዜ ዎክ ካደረግን በኋላ ማክሰኞ የኔ እና የኢክራም ዉድ ቀን ሆነች። ማክሰኞ ኢክራም ከሀይማኖታዊ ትምህርት ነፃ የምትሆንበት ቀን ነዉ። ሌሎቹን ቀናት ጁምዓን ሳይጨምር መስጂድ ሀይማኖታዊ ትምህርቶችን ትማራለች። ሁሌም ማክሰኞ አስር ሰዓት ላይ ተገናኝተን እስከ አስራሁለት ሰአት ድረስ አብረን እናሳልፋለን።

አስራሁለት ሰዓት ሲሞላ እናቷ ከስራ ስለምትመጣ ወደ ቤቷ እሸኛታለሁ። እናቷ ከስራ አርፍዳ የምትመጣ ቀን ኢክሩ እስከ አንድ ሰአት ድረስ ከኔ ጋር አርፍዳ ወደ ቤቷ ትገባለች። ከኔ ከተለየች በኋላ ወደ ቤቷ ስትገባ እናቷ እስከምትመጣ ድረስ ብቻዋን ቤት ዉስጥ እንደምትቀመጥ ሳስበዉ ለሷ እኔ እታመማለሁ።

ከብቸኝነት በላይ ህመም የለም። የሚያዳምጠን ሰዉ ከማጣት በላይ ስቃይ አይኖርም።
.
አንድ ቀን ከኢክሩ ጋር ሁሌም ወደምንቀመጥበት ከሰፈራችን ትንሽ ዝቅ ብሎ ወዳለዉ ሰፊ የሳር ሜዳ ሄድን። ሜዳዉ ላይ ኳስ የሚጫወቱ ልጆች አሉ። ከሜዳዉ ራቅ ብሎ ደግሞ ልክ እንደኛ የአካባቢዉን ከሰዉ አይን የራቀ መሆን ፈልገዉ የመጡ ጥንዶች ተቀምጠዋል። ሁሌም እንደምናደርገዉ ከክቡ የድንጋይ ቋጥኝ አጠገብ ያሉ መቀመጫዎች ላይ ተቀመጥን። ኢክሩ ድብር ብሏታል።

ቀስ ብዬ "ኢክሩዬ ስለምን እያሰብሽ ነዉ?" አልኳት። እንባ እየተናነቃት "ፈዊ እናቴ ላይ ሸክም እንደሆንኩባት እየተሰማኝ ነዉ።" አለችኝ።
እየሳቅኩ "ኢክሩዬ እናት ላይ እንዴት ሸክም ይኮናል? እናቶቻችን እኮ ሁሌም እኛን ለመንከባከብ አይታክቱም።" አልኳት። አንገቷን በአሉታ እየነቀነቀች እንዳልተረዳኋት ገልፃልኝ ማብራራቷን ቀጠለች።

"ፈዊ እናቴ በጣም ወጣት ናት። አንድ ላይ ብታየን እህትማማቾች እንጂ እናት እና ልጅ አንመስልህም። እሷ የማታገባዉ ባል ጠፍቶ አይደለም ግን እኔን ከእንጀራ አባት ጋር ማኖር ከብዷት ነዉ። እራስ ወዳድ እንደሆንኩ ይሰማኛል ፣ በእናቴ መቅለጥ ነዉ እየፈካሁ ያለሁት።" ንግግሯ በእንባ መታጀብ ጀምሯል።

ወይኔ ሰዉ ሲያለቅስም እንዲህ ያምራል? ወንድነቴን አደብ አስገዝቼ በለቅሶ የታጀበ ንግግሯን ማዳመጤን ቀጠልኩ።

"ፈዊ እኔ ባገባ እኮ ማማ ያለስጋት አግብታ መኖር ትችል ነበር። ግን እኔ አሁንም እንደ ልጅ እየተጨማለቅኩ የሷን ህይወት እየቀማኋት ነዉ።" ብላ እንባዋን መጥረግ ጀመረች።

አሁን የኢክራምን ዉበት ያየ በዚህ ሁሉ ችግር ዉስጥ እየተፈተነች ያለች ይመስለዋል? በፍፁም አይመስለዉም። ኢክሩ ከተረጋጋች በኋላ ጭንቀቷን እንድትረሳዉ ብዬ ስላሳለፍነዉ የፍቅር ታሪክ እንድንጨዋወት ጠየቅኳት።

እሷ ከዚህ በፊት ብዙ ያፈቅሯት የነበሩ ልጆች የነበሩ ቢሆንም የሚነገር የፍቅር ታሪክ እንደሌላት ነገረችኝ። እኔ በልጅነቴ ስላፈቀርኳት መርየም ስለምትባል ልጅ አጫወትኳት። ታሪኩን ከነገርኳት በኋላ
"ኢክሩዬ ለመርየም ካደረግኳቸዉ ነገሮች ዉስጥ የቱ እንደሚገርመኝ ታዉቂያለሽ?" አልኳት። እንድቀጥልላት ምልክት ሰጠችኝ "ሰባተኛ ክፍል እያለሁ ነዉ።

አንድ ቀን ናቲ የሚባል ጓደኛችን አስተማሪ ገርፎት ክፍል ዉስጥ እየተንሰቀሰቀ ያለቅሳል። መርየም እና ጓደኛዋ ናቲን ሲያባብሉት አየሁ። መርየም አይዞህ እያለች ስትንከባከበዉ ሳይ ናቲን መሆን ተመኘሁ። በቀጣዩ ክፍለጊዜ ሰበብ ፈልጌ ከአስተማሪ ጋር ተጣላሁ። ግን አስተማሪዋ አልገረፈችኝም።

ተቆጥታኝ አለፈችኝ። እኔ ግን አላማዬ የመርየምን ማፅናኛ ማግኘት ስለነበር ተንሰቅስቄ አለቀስኩ።" ኢክራም ሳቅ እያፈናት "እና መርየም አባበለችህ?" አለችኝ። "ባክህ ዝም በል" አለችኝ ስላት ኢክሩ እንባዋ ከአይኗ እስኪፈስ ድረስ እየተንከተከተች ሳቀች። ኢክሩ ስትስቅ በጣም ታምራለች። በዛ ላይ ደግሞ ሳቋን ሊያጅቡ እንባዎቿ ከዉብ አይኖቿ ሲፈሱ በጣም ለየት ያለ ዉበት አላት። ኢክሩን እንደዛ ቀን ስትስቅ አይቻት አላዉቅም። ሌላም እንደዚህ የሚያስቅ ታሪክ በኖረኝ እና ነግሬያት እንዲህ ስትፍለቀለቅ ባየኋት ብዬ ተመኘሁ።
.

ከኢክራም ጋር ወንድሟ ሆኜ ሀዘኗን እየተካፈልኳት እና ጭንቀቴን እያማከርኳት ለሁለት ወር ቆየን። አንድ ቀን እንደለመድነዉ ተገናኝተን ተጨዋዉተን ከተለያየን በኋላ ኢክሩ ፌስቡክ ላይ የሚያስደነግጥ መልዕክት ላከችልኝ።

"ፈዊ የእኔ እና አንተ ሁሌ መገናኘት ጥቅሙ አልታይሽ ብሎኛል። ቢቀርብን የሚሻል ይመስለኛል።" ይላል መልዕክቷ!! ግራ ገባኝ ኢክሩ ከኔ ጋር ስትሆን ሁሌም ደስተኛ ነበረች። ዛሬ ምን ተገኘና በቃኸኝ አለችኝ? ዉስጤ ተረበሸ። እኔ ሳዉቅ ለሷ ጥሩ ወንድም ነበርኩ። ቢሆንም አልተበሳጨሁባትም በአካል አግኝቼ ላዋራት ወሰንኩ። ደወልኩላት እንደተለመደዉ እየተፍለቀለቀች አናገረችኝ። ላናግራት እንደምፈልግ ነግሬያት በነጋታዉ ሰፈራችን ዉስጥ ያለዉ ቤተ መፅሀፍ ለመገናኘት ተቀጣጠርን።
.
በነገራችን ላይ የኛ ሰፈሩ ቤተ መፅሀፍ ማንበቢያ ከሚባል ይልቅ የወንድና ሴቶች መቀጣጠሪያ ቢባል የሚገልፀዉ ይመስለኛል። ለማንበብ ከሚመጣዉ ሰዉ በቁጥር የማያንሱ ቤተ መፅሀፍ ተቀጣጥረዉ የሚገናኙ ጥንዶች አሉ። የሰዉ ልጅ ለአንድ አላማ የተለያዩ ቦታዎች ይሄዳል አላልኳችሁም ነበር? ይኸዉ ቤተ መፅሀፍ እንኳ አልተረፈም። መጣበሻ ሆኗል።

እኔና ኢክሩ ቤተ መፅሀፍ የተቀጣጠርነዉ እኔ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተናዬን የምወስድበት ጊዜ ስለተቃረበ እና በንባብ ተጠምጄ ስለነበር ነዉ።

በነጋታዉ ኢክሩ ደዉላ ከቤተ መፅሀፉ እንድወጣ ነገረችኝ። ስወጣ በር ላይ ቆማለች። የቤተ መፅሀፉ አጥር ላይ ወዳለዉ መቀመጫ ሄደን ስ
"

ይቀጥላል

እኔ ሺ ፊደልኩ ተጫንኩ እናተስ?👍👍👍 ተጫኑ
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
ከዮቶር መፅሀፍ የተወሰዱ ሀሳቦች...

-ሰላም ካላቸው ወይ ያሰቡበት ላይ ደርሰዋል ወይ የሚሄዱበት የላቸውም
-ነፍሳችንና ስጋችን የሚያዜሙት ዜማ ህብረት ከሌለው ውበትም ሆነ መልዕክት ሊኖረው አይችልም
-ብዙ ሰዎች የራሳቸው ማንነት ላይ ከማተኮር ይልቅ የሌሎች ሰዎች ሰዎች ማንነት ላይ በማተኮር እድሜያቸውን ያባክናሉ
-አብረን ያፈካነው ቀን እኮ ነው አንቺን የገለፀሽ። እነዚህ ሰዎች የዚ ቀን ፀሀይ ሲያበራሽ ነው የተመለከቱሽ። እንደኔ በጨለማ ውስጥ አብረውሽ ሊጓዙ የሚችሉ አይነት አይደሉም
-ጀግና ጥሩም ሆነ መጥፎ ያው ጀግና ነው
-እውነትን እየተረዳህ በመጣህ ቁጥር ስቃይ ከውስጥህ ይሟታል ብላ ነፍሴ ሹክ አለቺኝ
-ምንም ብወደው ልኖርበት የማልፈቅደው ቤት ውስጥ እየተላተምኩ እየተፈጠፈጥኩ ከምኖር ልኖርበት የምፈቀደውን ሌላ ቤት መስራት ይጠበቅብኛል
-ከንቱ ፍራቻ ብለን የጠራነው የሰው ልጅ ደመ ነብሱን ከማዳመጥ ስለቦዘነ በራሱ ላይ የፈጠረው የፍራቻ ስሜት ነው
-ካለሁበት ተነስቼ አንድ እርምጃ ወደፊት በተራመድኩ ቁጥር የጨለማው ግድግዳም ወደኋላ አንድ እርምጃ ይሸሻል
-ፍራቻዬን በድርጊት አሸንፌዋለሁ
-እናንተ ወጣቶች የቁሳዊው አለም ሰዎች ናችሁ እኛ ሽማግሌዎቹ ደግሞ የመንፈሳዊው አለም ሰዎች ነን
-በእናንተ ውስጥ እርካታና ሰላም ጠፍቷል። ብዙ ትሮጣላችሁ እንጂ የእርካታን ደጅ አትረግጡም
-የሰው ልጅ አስቀድሞ በነፍሱ በሰውነቱ እና በማንነቱ  ላይ ቀድሞ ካልሰለጠነ ምኑን ነው ሰለጠነ የምንለው? ቁሳቁሱን ነው?
-በመንፈስ ስትሰለጥን በማንነትህ ላይ ስልጣን ይኖርሀል
-ሀይልና ገንዘብን ቅድሚያ ባደረገ ግስጋሴ ውስጥ ከፍቅር ይልቅ ጥላቻ ይነግሳል
-ሰዎችን ጥገኛ የማያደርግ ምስጢራዊ እገዛ መልካም ነው
-ሁሉም ነገር በለውጥ ውስጥ የሚያልፈው እኮ በፍቅር ሳቢያ ነው
-እጅህ ላይ ያሉትን ተአምራት ሳትጠቀም ሌላ ተአምር ከሰማይ ለምን መጠበቅ ያስፈልግሀል
-የሰው ልጅ እምነት እርግጠኝነት ይጎድለዋል
-የአንድ እቃ ወይም ጉዳይ ዋጋ የሚለካው ባረፈበት ሰው ማንነት ላይ ነው
-ሀሳባችን በራሱ የህወታችንን ጉዟችንን የሚቀርፅ ሀይል ነው
-ራሳችንን በሌላኛው ሰው ቦታ ላይ አድርጎ ማሰብ ጉድለትን ማረሚያ መንገድ ነው
-ፍቅር ነፍስን ከነፍስ ከማቆራኘት አቅም እንዳለው አታውቂም?
-በገፍ ታፍሶ የተሰጠሽን ፍሬ ሳስተሽ ስለማትጠቀሚበት የምታባክኚው ይበዛል። ተቆጥቦና ተቆጥሮ የተሰጠሽ ፍሬ ግን ውድ ነው።
-ህይወት በጣም ትገርማለች በdestiny ላይ የቱጋር እንኳን ስህተት እንደፈፀምክ ሳይገባህ እንዲሁ ፊትህ ያገኘኸውን ብቻ ዝም ብለህ ትኖራለህ

https://www.tg-me.com/ethioleboled
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
በቅርቡ ፈገግ ትልና
ይሔ
ከጠየኩህ በላይ ነው ብለህ ፈጣሪህን ታመሰግናለህ!
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
💥📚ኢትዮ-ልቦለድ📚📖💥
Photo
   ♥️●●●#ነጠብጣብ●●

        
#ክፍል_6


በነጋታዉ ኢክሩ ደዉላ ከቤተ መፅሀፉ እንድወጣ ነገረችኝ።

ስወጣ በር ላይ ቆማለች። የቤተ መፅሀፉ አጥር ላይ ወዳለዉ መቀመጫ ሄደን ስለላከችልኝ መልዕክት ማብራሪያ እንድትሰጠኝ ጠየቅኳት።

"ፈዊ መገናኘታችን ትርጉሙ አልገባኝም። በስልክ ከተደዋወልን የሚበቃ ይመስለኛል።" አለችኝ። ስታወራ ይብቃን ሳይሆን እንቀጥል የምትል ነዉ የምትመስለዉ።

ትኩር ብዬ ተመለከትኳት ፣ በረዥሙ ተነፈስኩና "ኢክሩዬ አብሬሽ በወንድምነት ያሳለፍኩት ጊዜ በጣም ደስ ይል ነበር። አንቺ በቃኝ ካልሽ ግን ዉሳኔሽን አከብራለሁ።" ብዬ እስከ ቤቷ ድረስ እንደተለመደዉ ሸኝቼ ተሰናበትኳት። ከዚህ ቀን ጀምሬ ኢክራም ጋር መደወል አቆምኩ።

በሰዓቱ ለፈተና እየተዘገጃጀሁ የነበረ መሆኑ ብዙም ስለ ኢክራም እንዳላስብ ረዳኝ። ሰዉ መለማመጥ አልወድም። ኢክራም ከበቃት በቅቷታል አለቀ።

ደግሞ ምንም የተለየ ነገር አልነበረንም።
ግን የእኔ እና እሷ የመገናኛ ዉድ ቀን ማክሰኞን በጉጉት ትናፍቅ የነበረችዉ ኢክራም ይብቃን ያለችበት ምክንያት ምንድነዉ? ኢክሩ ልታገባ ነዉ? ፍቅረኛ ልትይዝ ነዉ? ለምን? ምክንያት እንዳለዉ ገብቶኛል። ግን ምን እንደሆነ አላዉቅም።

  
.           

.🖊ከኢክራም ጋር መገናኘት ካቆምን ጥቂት ቀናት አለፉ። እኔም ለፈተና ዝግጅት ቤተ መፅሀፍ ማዘዉተር አበዛሁ። በዚህ አጋጣሚ እንደኔዉ ተፈታኝ ከነበሩ ሁለት ሴቶች ጋር በጣም ተግባባሁ። ረዊና እና ሁዳ ይባላሉ። ረዊና ወፈር ብላ ቀላ ያለች ፣ የደስ ደስ ያላት ቆንጆ እና ትሁት ናት። ጉንጯ ላይ ስርጉድ አላት። ሲስቁ ጉንጫቸዉ የሚሰረጉዱ ሴቶች ልቤን ነዉ የሚያሰረጉዱት።

ሁዳ ደግሞ ቆማ መሄዷ በራሱ ተዓምር የሆነ በጣም ቀጫጫ ልጅ ናት። ከረዊና እና ሁዳ ጋር ያለን ቅርበት በጣም እየጠበቀ መጣ። ቤተ መፅሀፍ መጥተዉ ይደዉሉልኛል። አብረን ዉለን ከምሽቱ ሶስት ሰዓት ሲሆን እንለያያለን። አብረን መሆናችን ደስ የሚል ደስታ ይሰጠናል። አንዳንዴ በህይወታችሁ ዉስጥ በድንገት የተከሰቱ ሰዎች ሳታስቡት የማይረሳ ትዝታ ጥለዉባችሁ ያልፋሉ።

ከነሁዳ ጋር አንዳንዴ የቤተ መፅሀፍቱ ግቢ ዉስጥ እንገናኝና ቤተ መፅሀፉ ዉስጥ ሳንገባ ቀኑን ሙሉ አብረን እንዉላለን። ምሳ ሰዓት ላይ የረዊና እህት እምነት ከቤት ምሳ ቋጥራ ይዛልን ትመጣለች። እምነት ቀይ ፣ በጣም ቆንጆ ፣ የሰዉነት ቅርጿ በጣም የሚያምር ዉብ ልጅ ናት። ቁንጅና ከቤት ነዉ መሰለኝ። በጊዜዉ እሷ የአስራ አንደኛ ክፍል ተማሪ ነበረች። እምነት ወሬ መቋጠር አይሆንላትም። እራሷ "ሚስጥር አትንገሩኝ መያዝ አይሆንልኝም" ትል ነበር።
.
አንድ ቀን እንደተለመደዉ ቤተ መፅሀፍ እያነበብኩ እያለ አንድ የማላዉቃት ልጅ ዉጪ ኢክራም እየጠራችኝ እንደሆነ ነገረችኝ።

ልጅቷ የኢክራም አብሮ አደግ ጓደኛዋ እና ዘመዷ ነበረች፤ ስሟ ሪሀና ነዉ። ከቤተ መፅሀፉ ኢክራምን ለማግኘት ወጣሁ። በር ላይ ብሩክን አገኘሁት። ብሩክ ሰላምታ እንኳ ሳይሰጠኝ አሁን መጥታ የጠራችኝ የኢክራም ጓደኛ እንደሆነች እና እንዳጣብሰዉ ጠየቀኝ። የብሩክ ፍጥነት ገርሞኛል።

ግን በሰዓቱ ብሩክ የፍቅር ህይወት ዉስጥ መግባት ይፈልግ እንደነበር ስለማዉቅ ብዙም አልደነቀኝም። ፍቅረኛ መያዝ ፋሽን ስለሆነ ሁሉም ስለተፋቀረ ሳይሆን ፍቅረኛ አለመያዙ ከሌሎች እንዳይነጥለዉ ብሎ ፍቅረኛ ይይዛል።

ለምን ብለን ብንፈትሽ ከመንጋዉ ላለመለየት ከሚል ምክንያት ዉጪ ምንም አናገኝም።
ኢክራም ግን ግንኙነታችንን እንድናቀዘቅዘዉ ከጠየቀችኝ በኋላ ዛሬ ለምን ልታገኘኝ እንደመጣች ግራ ገብቶኛል። ሪሀና እየመራችኝ ኢክራም እየጠበቀችኝ ወዳለበት የቤተ መፅሀፉ ጀርባ አመራሁ። ኢክራም ዛፍ ተደግፋ ቆማለች። አሁንም ያ አስደንጋጭ ዉበቷ አብሯት አለ።
.
ሪሀና ኢክራምን ካሳየችኝ በኋላ በነፃነት እንድናወራ ትታን ሄደች። ከኢክራም ጋር መደዋወል ካቆምን ከሁለት ሳምንታት በላይ ተቆጥረዉ ነበር።
ኢክሩ እየተፍለቀለች "ፈዊዬ አኩርፈኸኛል አይደል?" አለችኝ። ዘንድሮ እኮ አልቻልንም ጎበዝ!! በራሷ ጊዜ መገናኘታችን ጥቅሙ አልታየኝም እናቀዝቅዘዉ ያለችኝ እሷዉ እራሷ ነበረች። "አኩርፈኸኛል አይደል?" ብላ ጥፋቱን ወደ እኔ ስትጠመዝዘዉ ተመልከቱ።

ፈገግ አልኩና "ኢክሩዬ አላኮረፍኩሽም ፣ መገናኘታችን ጥቅሙ አልታይ አለኝ ፣ ይብቃን ያልሽኝ አንቺዉ ነሽ። እኔ ደግሞ የሰዉን ፍላጎት መጠበቅ ላይ ጎበዝ ስለሆንኩ ዉሳኔሽን እያከበርኩ ነዉ።" አልኳት።

ኢክሩ አይኖቿን እያስለመለመች ዝም ብላ አየችኝ እና "ፈዊ የሆንክ ጢባራም ነገር ነህ። ታዉቃለህ ግን እኔ ጢባርህን እወደዋለሁ።" አለችኝ።
ይሄ ነገር ወዴት ወዴት ነዉ? ኢክራም ጢባሬን ትወድልኛለች? ምን ለማለት ፈልጋ ነዉ? ሰሞኑን ያመጣችዉ ፀባይ ግራ ነዉ የሆነብኝ። ሲላት ይብቃን ፣ ሲላት ጢባርህን እወድልሀለሁ።
.
ወደ ቤተ መፅሀፍ ተመልሼ ንባቤን መቀጠል ስለነበረብኝ ኢክራምን ትንሽ መንገድ ሸኝቻት ተመለስኩ።

አሁን የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ለመፈተን የቀረኝ ጊዜ ሁለት ወር አይሞላም። ፈጣሪ ምስጋና ይግባዉና ረዊናን እና ሁዳን ከተዋወቅኩ ጀምሮ ቤተ መፅሀፍ ስመጣ አይደብረኝም።

የረዊና እህት እምነትም አንዳንዴ አብራን ትሆን ስለነበር አስደሳች ጊዜ ነበር የምናሳልፈዉ። እናነባለን ፤ በደንብ ደግሞ እንዝናናለን። ለመዝናናት የትም መሄድ አይጠበቅብንም። በወሬያችን ቤተ መፅሀፉን ከማንበቢያነት ወደ መዝናኛነት እንቀይረዋለን።
ከብሩክ ጋር በብዛት መገናኘት አቁመናል።

ድሮም በብዛት አንገናኝም ነበር። እኔ ቤተ መፅሀፍ ነዉ የምዉለዉ። እሱ ደግሞ ቤተ መፅሀፍ መግባት በራሱ ያመዋል። እንደኔዉ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ወሳጅ ቢሆንም እምነቱን በአስኮራጆቹ ላይ ጥሏል። ሄኖክን በዚህ የፈተና ዝግጅት ሰሞን በፍፁም አግኝቸዉ አላዉቅም ነበር።
.
ቅዳሜ ቀን ይመስለኛል። የማላዉቀዉ ስልክ ተደወለልኝ። አነሳሁት።
"ፈዉዛን ሪሀና ነኝ የኢክራም ጓደኛ አወቅከኝ? " አለችኝ በጣም በቀጭን ድምፅ።

"አዎ አዉቄሻለሁ ባለፈዉ ቤተ መፅሀፍት መጥተሽ የነበርሽዉ ነሽ አይደል?" አልኳት።
"አዎ ፈዉዛን በአካል አግኝቼ ላናግርህ ፈልጌ ነበር ይመችሃል እንዴ?" አለችኝ።
"ቤተ መፅሀፍት ነዉ ያለሁት እዚህ መምጣት ትችያለሽ?" አልኳት።

በአስር ደቂቃ ዉስጥ እንደምትደርስ ነግራኝ ስልኩን ዘጋችዉ። እንዳለችዉም ለመምጣት ከአስር ደቂቃ በላይ አልፈጀባትም። ሪሀና ቀጠን ያለችና የደስ ደስ ያላት ልጅ ናት።

ስታወራ በጣም ትፈጥናለች።
መጥታ ስትደዉልልኝ ከቤተ መፅሀፍቱ ወጥቼ አገኘኋት።
"እሺ ሪሀና ለምን ነበር የፈለግሽኝ?" አልኳት።
እየተቅለሰለሰች "ፈዉዛን ስለ ኢክራም ነበር ላወራህ የመጣሁት። ለኢክሩ ምን አይነት ስሜት አለህ?" አለችኝ።
"እኔ አክራምን እንደወንድም እወዳታለሁ።

ለሷ መልካም ስሜት ነዉ ያለኝ።" አልኳት።
"ይኸዉልህ ፈዉዛን ኢክራም ወሬዋ ሁሉ ስላንተ ሆኗል። አብረን ዎክ ስናደርግ እራሱ ካንተ ጋር ዎክ ስላደረጋችሁበት ጊዜ ምናምን ብቻ ነዉ የምታወራኝ።

እኔ እሷ የወደደችህ ይመስለኛል።" አለችኝ።
ፈገግ ብዬ "ኢክራም እራሷ ናት መጥተሽ እንድትነግሪኝ የላከችሽ?" አልኳት

"

አላለቀም እስኪ እንደወደዳችሁት አብሮነታችሁን በ Like አሳዩኝ
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
እመኑኝ

አለምን በ6 ቀን ሰርቶ የጨረሰ አምላክ የናንተን ሕይወት ለማስተካከል ብዙ ግዜ አይፈጅም!
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
.   ♥️●●●ነጠብጣብ●●●♥️

   
#ክፍል_7


"ይኸዉልህ ፈዉዛን ኢክራም ወሬዋ ሁሉ ስላንተ ሆኗል። አብረን ዎክ ስናደርግ እራሱ ካንተ ጋር ዎክ ስላደረጋችሁበት ጊዜ ምናምን ብቻ ነዉ የምታወራኝ። እኔ እሷ የወደደችህ ይመስለኛል።" አለችኝ።
ፈገግ ብዬ "ኢክራም እራሷ ናት መጥተሽ እንድትነግሪኝ የላከችሽ?" አልኳት።

"አይ አይደለም እኔዉ ራሴ ነኝ የመጣሁት። የሷን ሁኔታ ስገምት ያፈቀረችህ ይመስለኛል። አንተ ጋርም ተመሳሳይ ስሜት ካለ በቃ ጠይቃት እና ፍቅረኛ ሁኑ።" ተነፈሰችዉ። እንደጓደኝነቷ የኢክራምን ጥቅም ባስከበረ መልኩ ነዉ እየተደራደረችኝ ያለችዉ። ደግሞ ዉጤቱን በፍጥነት ለማወቅ ነዉ የፈለገችዉ።

ስልኳን እየሰጠችኝ "ይኸዉ እንካ ደዉልና እንደምትወዳት ንገራት" አለችኝ። የሪሀና ፍጥነት እያስደመመኝ ነዉ። ስልክ ለመደወል ፈቃደኛ እንዳልሆንኩ ነገርኳት። በነጋታዉ ከኢክራም ጋር እንደሚመጡ ነግራኝ ተሰናበተችኝ።
.
ቆይ እኔ ኢክራምን አፈቅራታለሁ እንዴ? ከራሴ ጋር ሙግት ዉስጥ ገባሁ። የሰሞኑ የኢክራምን የፀባይ መቀያየር አስታወስኩ። የኔና የአንተ ግንኙነት ትርጉሙ አልታየኝም ስትለኝ ግንኙነታችንን ትርጉም እንስጠዉ እያለችኝ መሆኑ እንዴት እንዳልገባኝ ገረመኝ።

ለኢክራም ዉስጤ ላይ መልካም ወንድማዊ ፍቅር እንጂ የተለየ ስሜት የለኝም። የኢክራምን ዉበት ሁሌም አደንቅ ነበር ግን ከወንድነት ስሜቴ እንጂ ከፆታዊ ፍቅሬ የመነጨ አልነበረም።
.
በነጋታዉ ኢክራም እና ሪሀና አንድ ላይ ሆነዉ ቤተ መፅሀፍ መጡ። አብረዉ እንደሚመጡ አስቀድማ ነግራኝ ስለነበር ለብሩክ ደዉዬለት መጥቷል። ብሩክ ሪሀናን እንዳጣብሰዉ ጠይቆኝ ስለነበር እድሉን ተጠቅሜ ማገናኘቴ ነዉ እንግዲህ።
ብሩክ እና ሪሀና አንድ ላይ ፣ እኔ እና ኢክራም አንድ ላይ ጥንድ ጥንድ ሆነን የቤተ መፅሀፍቱ ግቢ ዉስጥ እነሱ በላይኛዉ የቤተ መፅሀፍቱ አጥር በኩል ፣ እኔና ኢክሩ ደግሞ በታችኛዉ በኩል ተቀምጠናል።

የሪሀና የዛሬዉ እቅዷ እኔ ኢክራ ምን እንደምወዳት እንድነግራት ማድረግ ነዉ። እኔ ጋር ግን ለኢክራም ፆታዊ የፍቅር ስሜት የለም። ግን የፍቅር ጥያቄዉ ከሷ ከመጣ ለመቀበል እና በወንድምነት የጀመርኩትን ብቸኝነቷን የማስረሳት ፕሮጀክት በፍቅረኝነት አጠናክሬ ለመቀጠል ወስኛለሁ።
ከኢክሩ ጋር ማዉራት ከጀመርን የቆየን ቢሆንም ሁለታችንም ስለፍቅር ጥያቄዉ አላነሳንም ነበር። ሪሀና ከፊት ለፊቴ ከብሩክ ጋር እንደቆመች ስልክ ደወለችልኝ።
"ወዬ ቀዉሷ"
"እ ፈዉዛን ጠየቅካት?"
"አይ" አልኩ አልጠየቅኳትም ካልኩ ኢክራም ይገባታል ብዬ መጠንቀቄ ነዉ።
"ፈዉዛን በቃ አሁን ጠይቃት። አሁን!!" አለችኝ።

ስልኩን ዘጋሁት እና ከኢክራም ጋር ወሬዬን ቀጠልኩ። እሷ ካልጠየቀችኝ ላለመጠየቅ ወስኛለሁ።
ብሩክ እና ሪሀና ዛሬ የተዋወቁ አይመስሉም። በጣም ጠልቀዉ ገብተዋል። እኔና ኢክሩ ወሬያችንን ጨርሰን ከተቀመጥንበት ተነሳን። ብሩክ እና ሪሀና አሁንም በወሬ ተመስጠዋል።
"ኧረ በቃችሁ በአንድ ቀን እንዲህ ትሰምጣላችሁ እንዴ?" ብዬ አቋረጥኳቸዉ።
ከተቀመጡበት ተነስተዉ እኛ ወዳለንበት መምጣት ጀመሩ። ኢክራምን ሪሀና የት እንደምትማር ጠየቅኳት።

መደበኛ ትምህርት እንዳቋረጠች እና አሁን የፀጉር ሙያ እየተማረች እንደሆነ ነገረችኝ።
እነ ብሩክ ከተቀላቀሉን በኋላ ኢክሩን እና ሪሀናን ለመሸኘት የቤተ መፅሀፍቱን ግቢ ለቀን ወጣን። ሪሀና ኢክሩን ስላልጠየቅኳት በጣም ተበሳጭታብኛለች። አይኗ ያሳብቃል። ሸኝተናቸዉ ስንመለስ ብሩክን ስለሪሀና ጠየቅኩት።

በጣም እንደተመቸችዉና በጣም እንደተግባቡ ነገረኝ። ጓደኛዬን የፈለጋትን ልጅ ስላስተዋወቅኩት በጣም ደስ አለኝ።
የፍቅር ጥያቄዉ እንደተዳፈነ ሊቀር ነዉ? ወይስ ኢክሩ እራሷ ድፍረት አግኝታ ትጠይቀኛለች? ቀጣዩ ምን እንደሚሆን ለማወቅ በጣም ጓጉቻለሁ። በጣም!!...

...🖊ማታ ከቤተ መፅሀፍት ተመልሼ ቤት ሳሎን ዉስጥ ተቀምጫለሁ። ቤት ሁሉም ቴሌቭዥን እያዩ ነዉ። እኔ ፌስቡኬን ለመጎርጎር ስልኬን አወጣሁ።

ፌስቡክ ላይ ስገባ አንድ መልዕክት አለኝ። ከፈትኩት ኢክራም ነበረች።
"ፈዊ ሪሀና ያለችህን ነገር ነግራኛለች። እኔ አልነበርኩም እንድትነግርህ የላኳት። ግን እዉነቷን ነዉ። ላንተ የተለየ ስሜት አለኝ። እና ምን ትላለህ?" ይላል።
ትንሽ ላስጨንቃት ፈለግኩ "ኢክሩዬ ምን ለማለት ፈልገሽ ነዉ?" ያልገባኝ ይመስል።

"ፈዉዛን እኔ አፍቅሬሀለሁ። እና አንተ ለኔ ምን አይነት ስሜት አለህ?" አፈረጠችዉ።
መለመን ግን ደስ ሲል ፣ሊያዉም እንደ ኢክሩ ባለች ቆንጆ!! የፍቅሬ ምርኮኛ ሆና አፈቅርሀለሁ ስትለኝ ፣ የኔ ለመሆን ይሁንታዬን ስትለምነኝ ። ጥርሴ ሳይሆን ልቤ መሳቅ ጀምሯል።

ሲፈጥረኝም መለመን እወዳለሁ። ግን መለመን የምወደዉ የበላይነቱ በኔ እጅ ላይ እንዲሆን ነዉ። የበላይነቱ በእኔ እጅ ላይ እንዲሆን የምፈልገዉ ደግሞ መልሱን ይሁንታ ለማድረግ ነዉ። አዉቅላችኋለሁ ከሚሉት ወገን ነኝ።
.
ዘፋኙ "አሸነፈ ልቤ ሸጋ ልጅ ወደደ
በፍቅር ሰከረ በደስታ አበደ።" አይደል ያለዉ። አስቡት እሱ እኮ ሸጋ ልጅ ወዶ ነዉ እንደዚህ ያዙኝ ልቀቁኝ የሚለዉ። እንደኔ ሸጋ ልጅ ብትወደዉ ምን ብሎ እንደሚዘፍን እንጃለት።

እሺ ኧረ ከሸጋም ልጅ ኢክሩ ብታፈቅረዉ ምን ሊዉጠዉ ነዉ? ስገምት ሙስሊም ከሆነ ፈጣሪዉን ለማመስገን እንደ መልአክቱ በግንባሩ እንደተደፋ ትንሳኤ ይደርሳል። ክርስቲያን ከሆነ ደግሞ አለም በቃኝ ብሎ ይመንናል። እንዴ በአይንአፋሯ ኢክሩ እኮ ነዉ የተፈቀረዉ፣ በዉቧ ኢክሩ!! ለየት ያለ ስሜት አለዉ። ከዚህ ሁሉ አድናቆቴ ጋር ግን ለኢክሩ የፍቅር ስሜት አልነበረኝም።
.
ኢክራም መልስ ሳልሰጣት ስዘገይ "እ?" ብላ ላከችልኝ። መልሱን አፍጥነዉ ማለቷ ነዉ እንግዲህ። ከዚህ በላይ ልቧን መስቀል ወንጀል እንዳይሆንብኝ ለመልሴ የምትሆን ቆንጆ እንግሊዘኛ የፍቅር አባባል ከጎግል ኮፒ አድርጌ ላኩላት።

ጎግል ዉሎ ይግባ እንጂ የሴቶቹን ቀልብ ለማቅለጥ ምርጥ ምርጥ የእንግሊዘኛ አባባሎች ኢንተርኔት ላይ ሞልተዋል።
ኢክሩ በደስታ ሳታብድ አትቀርም። እንግዲህ እኔም እንደመንጋዉ ባለፍቅረኛ መሆኔ ነዉ።

ያቺ ለሊት ባለፍቅረኛ ሆኜ ያደርኩባት የመጀመሪያዋ ለሊት ነበረች። ልዩ ከመሆን ዙፋኔ ዝቅ ብዬ መንጋዉን የተቀላቀልኩባት ለሊት!!
ትራስ አቅፌ መንከባለል ሁላ አምሮኝ ነበር። ቤት ሰይጣን ተጠጋዉ ብለዉ ቁርዓን እንዳያስቀሩብኝ ፈርቼ ተዉኩት። ምክንያቱም ቤት ሲያዉቁኝ በጣም ፎርማል ነኝ።

ልጅ ልጅ አያጫዉተኝም። ብታዩኝ እኮ ጠይቄያት እሺ ያለችኝ ነዉ የምመስለዉ። በዚህ አይነት እሷ እንዴት እንዴት እየሆነች እንዳደረች ፈጣሪ ነዉ የሚያዉቀዉ።

እንግዲህ እስካሁኗ ሰአት ድረስ እኔና ኢክሩ ፍቅረኛ መሆናችንን ያወጋነዉ በፌስቡክ ነዉ። በነጋታዉ ወደማታ ገደማ ኢክራም ደወለችልኝ።

አሁን የማወራዉ በወንድምነት ከማዉቃት ኢክራም ጋር ሳይሆን ለመጀመሪያ ጊዜ ፍቅረኛዬ ከሆነችዉ ኢክሩ ጋር ነዉ። የመጀመሪያዬ ስል መርየምስ ትሉ ይሆናል እኮ!! መርየምን እወዳት ነበር እንጂ ከሷ ጋር የፍቅር ግንኙነት ዉስጥ አልገባሁም ነበር።

ስልኩን አነሳሁትና ያዉ ፍቅረኛዬ እንደመሆኗ አነጋገሬን ወደ የኔ ቆንጆ ምናምን አሳድጌ አወራኋት። መጨረሻ ላይ ልሰናበታት ስል የፍቅር ጥያቄዋን መቀበሌን ማረጋገጫ እንዲሆናት ብዬ "እወድሻለሁ" አልኳት




አላለቀም እንደተለመደው በቶሎ እንዲቀጥል Like እያረጋችሁ እለፉ
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
💥📚ኢትዮ-ልቦለድ📚📖💥
Photo
●●●ነጠብጣብ●●●♥️

   
#ክፍል_8


መጨረሻ ላይ ልሰናበታት ስል የፍቅር ጥያቄዋን መቀበሌን ማረጋገጫ እንዲሆናት ብዬ "እወድሻለሁ" አልኳት።

የእዉነት እንዲህ መሟዘዝ አይመቸኝም ግን የሷን ስሜት ለመጠበቅ ብዬ ያደረግኩት ነበር። ፍቅር የቃላት ጨዋታ አይደለም። ማንነትን የመቀበል ጉዳይ ነዉ። ትናንት የማታዉቃትን ሴት የእኔ የምትልበት ቀመር ነዉ።

ኢክራም ስቃ አላባራችም። "አትሟዘዝ ባክህ!! እኔ እወድሻለሁ ምናምን መባባል ደስ አይለኝም።" አለችኝ።
ኦኬ ተግባሩ ነዋ የሚመቻት!! በዚህ ጉዳይ ላይ አንድ ሰፈር መሆናችን ደስ ብሎኝ ተሰናበትኳት። እንግዲህ ከዚህ በኋላ ነበር አሁን እኔ መሰበሬን ለመርሳት የመጣሁበት ካፌ መመላለስ የጀመርነዉ።

ከፊት ለፊቴ ተቀምጠዉ የሚሳሳቁት ጥንዶች አሁንም በወሬ እንደሰመጡ ናቸዉ። አስተናጋጇ ረሂማ አጠገቤ መጥታ "ምነዉ ሳፊዉ ወተቱ ላይ ችግር አለ እንዴ?" አለችኝ ሳቋ እየፈነዳ።

ይህቺ ልጅ ፈዉዛን የሚለዉን ከነጭራሹ ትታ ሳፊዉ ትለኝ ጀመር ማለት ነዉ?
ያዘዝኩትን ወተት አልነካሁትም ነበር። ረሂማ አክብሮቷ እና ተጫዋችነቷ ከስራዉ ጋር የተስማማ ነዉ።
"አይ ችግር የለዉም ኮካዬ ሀሳብ ዉስጥ ሰምጬ ቀዘቀዘ" አልኳት።
ወዲያዉ ወተቱን አሙቃ ልታመጣልኝ ይዛዉ ሄደች። እኔም ወደ ሀሳቤ ተመለስኩ።
.
እንግዲህ ኢክራም እና እኔ ፍቅረኛሞች ስንሆን በመካከላችን ሚስጥር የሚባል ነገር ጠፋ። ምንም አልደብቃትም። እሷም ምንም አትደብቀኝም። የሆነ ትልቅ ሰላም ልቤ ዉስጥ ሲሰፍን ይሰማኛል። ሌላ ቤተሰብ ያገኘሁ ያህል ነዉ የተሰማኝ።

ስናፈቅር ግን የሆነ ጅል የሚያደርገን ነገር አለ አይደል? እኔ ህፃን ሆኜ እንኳ የህፃናት ጨዋታ የማይጥመኝ ልጅ ነበርኩ። አሁን ግን ከኢክራም ጋር እንደመጃጃል የሚያስደስተኝ ነገር የለም።
በነገራችን ላይ እኔና ኢክሩ ጋር እንደ ፍቅረኞች አለ አይደል መጎነታተል መሳሳም ምናምን የለም። እሱንም እሷ እስክትጀምር እየጠበቅኩ ይሁን አላዉቅም።

ሁለታችንም መስጂድ ጀመዓዎች(ህብረቶች) ላይ ስለምንሳተፍ እምነታችን ላይም ጠበቅ ያልንበት ሰዓት ስለነበር እንኳን ሌላ ነገር ቀርቶ አንጨባበጥም ነበር።

ከኢክሩ ጋር ስለ ህይወታችን እናወራ፣ ምክር የሚያስፈልገዉ ጉዳይ ሲገጥመን ደግሞ ሳንደባበቅ እንወያይ ነበር። ኢክሩ ላይ ስሜቴን ለማስተናገድ ብዙም ትኩረት አልሰጥም ነበር። እሷን የሚያስደስታትን ነገር ማድረግ ፣ የሷን ስሜት መከተል የህይወቴ ሀሁ ሆነ። ፍቅረኛሞች ይሳሳማሉ!! እኔና ኢክሩ አንሳሳምም ግን ፍቅረኞች ነን። ፍቅረኛሞች ይተቃቀፋሉ እኔና ኢክሩ አንተቃቀፍም ግን ፍቅረኞች ነን!!

ህይወታችን ነገን በማለም ተወጥናለች። ስለመጋባት ነዉ የምናልመዉ። ምንም እንቅፋት ይኖራል ብለን ማመን አንፈልግም። ገና ተማሪዎች ነን ግን እንደምንጋባ እናምናለን ሊያዉም በቅርብ ጊዜ ዉስጥ!!
.
ስናፈቅር እንታወራለን መሰለኝ። እኔና ኢክሩ እንቅፋቶቹ ሁሉ አይታዩንም። አንዳንዴ ስለ ልጆቻችን ብዛት ረዥም ሰአት እንከራከራለን።

ኢክሩ እንደነገርኳችሁ የፊልም ሱስ አለባት ያዉ ብቸኛ ወዳጇም እሱ ነበር። ስንጋባ ፊልም መከታተል እንደምታቆም ነገርኳት። እሷም ወዲያዉ ስንጋባ እንደምታቆም ቃል ገባችልኝ። ቆይ ግን ምን አይነት ጋሬጣ ለመጋባት የሚጎድሉንን ነገሮች ጋርዶብን ነዉ? አሁን ላይ ሳስታዉሰዉ በጣም ይገርመኛል።

አንድ ቀን እኔና ኢክሩ እያወራን ኢክሩ መሀል ላይ ኮስተር አለችና "ፈዊ ግን ሁሌ ስደዉልልህ እቤት ሆነህ አታዉቅም። ለምንድን ነዉ ቤት የማትቀመጠዉ?" አለችኝ።
"ኢክሩዬ እኔ ቤት መቀመጥ አይሆንልኝም። የምሄድበት ባይኖር እንኳ ዉጣ ዉጣ የሚለኝ ነገር አለ።" አልኳት።
"ስንጋባ ግን ከስራ መልስ ሁሌም ቤት ነዉ የምትሆነዉ እሺ!!" አለችኝ እየተቆጣች።
"እሺ የኔ አይጥ ካንቺ ጋር ብቻ ነዉ የምሆነዉ የትም አልሄድም።" አልኳት እየሳቅኩ።
.
በቃ ለመጋባት ሳምንት የቀራቸዉ ጥንዶች ነበር የምንመስለዉ። ለመጋባት የነበረን ጉጉት ይመስለኛል ለመሳሳም እና ለመሳሰሉት እንዳንቸኩል ያደረገን። አሊያም ለእምነታችን የነበረን ክብር እምነታችን እነዚህን ተግባሮች የሚፈቅድበትን ትዳር የተባለ ተቋም ለመመስረት እንድናልም አደ ረገን።

ከኢክሩ ጋር ጣፋጭ ጊዜ እያሳለፍን ቀናት ደግሞ መቁጠራቸዉን ቀጥለዉ ፤ እኔ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና መፈተን ጀምሬ ሁለት ቀናት ተፈትኛለሁ። ፈተናዉ የተጀመረዉ ሀሙስ ቀን ስለነበር ሀሙስ እና አርብ ተፈትነን ቅዳሜ እና እሁድ አርፈን ሰኞ እና ማክሰኞ ነበር የሚቀጥለዉ።

እሁድ ቤተ መፅሀፍት ግቢ ዉስጥ እንደተለመደዉ ከረዊና እና ከሁዳ ጋር ተቀምጠን እየተጨዋወትን ነዉ። ኢክራም ልታገኘኝ ወደ ቤተ መፅሀፍ መጣች። ኢክሩ ስትደርስ ከነረዊና ገንጠል ብዬ ተቀበልኳት። ኢክሩ ትንሽ ግራ የመጋባት ስሜት ይታይባታል።
.
ሰላምታ ተሰጣጥተን እንደቆምን
"ፈዊ ከኔ ሌላ ብዙ ሴቶች አሉ።" አለችኝ።
ፈገግ ብዬ "ሞልተዋል እንዳንቺ ቆንጆ አይደሉም እንጂ!!"

ኢክሩ አመረረች "ምናልባት እኔ ያንተ ባልሆን ሌላ ሴት አግባ እሺ!!" አለችኝ። ይህቺ ልጅ ዛሬ ምን የሚል ፊልም አይታ መጥታ ነዉ እንዲህ የምትቀባጥረዉ? እኔ ለንግግሯ ትኩረት መስጠት አልፈለግኩም አይን አይኗን እያየሁ
"ኢክሩዬ እኔ አንቺን ካላገባሁ ሌላ ሴት አላገባም።" አልኳት።

"ይኸዉልህ አግባ!! ከኔ የተሻሉ ቆንጆ እና ጥሩ ሴቶች አሉ። የሚፈጠረዉ አይታወቅም" አለችኝ። ዛሬ ምን እንደነካት ግራ ገብቶኛል።
በረዥሙ ከተነፈስኩ በኋላ "ኢክሩ እኔ ወደፊት ትዳር የሚባል ነገር ላለመመስረት ለራሴ ቃል በገባሁበት ሰአት አንቺ ወደ ህይወቴ መጣሽ። ከዛ ለትዳር እንድጓጓ አደረግሽኝ። አንቺን ካላገባሁ ማንንም አላገባም። ይሄ ደግሞ ከመጀመሪያዉም የኔ አቋም ነበር።" አልኳት።

ኢክሩ መልስ ሳትሰጠኝ ፈገግ ብላ እንድሸኛት ጠየቀችኝ። መጀመሪያ እነረዊናን እንድትተዋወቃቸዉ ወደ ተቀመጡበት ቦታ ይዣት ሄድኩ።
.
የረዊና እህት እምነት ምሳ ይዛ መጥታ ከነረዊና ጋር ተቀምጣለች። ሁሉንም አስተዋዉቂያት ሸኘኋት።
ሸኝቼያት ስመለስ ረዊና እና እምነት የኢክራምን ቁንጅና እያደነቁ መቀመጫ አሳጡኝ። እኔ ግን የማስበዉ ስለዛሬዉ የኢክራም እንግዳ ፀባይ ነዉ። "ከኔ ሌላ ሴት አግባ!!" "ከኔ ሌላ ቆንጆ እና ጥሩ ሴቶች አሉ!" ምን ለማለት ፈልጋ ነዉ? የፍቅር ግንኙነት ከጀመርን ሁለት ወራት ሊሞላ ነዉ። እና ምን ተፈጠረ?...


አላለቀም ነገ 2 ክፍለ በተከታታይ እናቀርባለን እስከዛ Like 👍👍👍👍 እነተጫናችሁ እለፉ
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
💥📚ኢትዮ-ልቦለድ📚📖💥
Photo
.              ♥️●●●ነጠብጣብ●●●♥️

           

                            
#ክፍል_9

...🖊የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ጨርሰን ሁላችንም በደስታ አብደናል። ረዊና ሁዳ እና እኔ በያለንበት ነፃነት ተሰምቶናል። አሁን ዉጤቱን የምንጠባበቅበት ጊዜ ነዉ። ከዚህ ሁሉ ደስታ መሀል ደግሞ ያሳዘነን ነገር አለ።

ከዚህ በኋላ እንደከዚህ ቀደሙ ቤተ መፅሀፍት ተሰብስበን የምናሳልፋቸዉ ዉብ ቀናት አይኖሩም። ለማንኛዉም ላለመጠፋፋት ተመካክረን በፈተናዉ ማለቅ አብደናል።
ኢክሩ ደዉላ "እንኳን ከኔ እኩል ነፃ ለመሆን አበቃህ!!" አለችኝ። እሷ ከኔ ቀድማ ነበር የመሰናዶ መግቢያ ፈተና የወሰደችዉ። ኢክሩ በነጋታዉ ረቡዕ ዕለት እንደምንገናኝ ነግራኝ ስልኩን ዘጋችዉ።

ኢክሩ ግን አንዳንዴ ሳስባት እናት ነገር ናት እኮ! ስለአንድ ጉዳይ ስጨነቅ የምትሰጠኝ ምክሮች ሁሌም ወኔ ይሆኑኝ ነበር። ትልቁ ችግሯ የነበረዉ ካፌ መግባት አይመቻትም ነበር። በኋላ ላይ ነዉ እንደምንም እያሳመንኳት ወደዚህ ካፌ መመላለስ የጀመርነዉ።

እሱንም እኔን ወጪ ላለማስወጣት ብላ ነበር። ከኔ እኔን እንጂ ሌላ ምንም አትፈልግም። እኔም ከሷ ኢክራምን እንጂ ምንም አልፈልግም። ዛሬ ደስታ አፍኖኛል። ፈተና ጨርሻለሁ ምንም የሚያስጨንቀኝ ነገር የለም።
ማክሰኞ ከከሰዓት በኋላን ከብሩክ ጋር ፈታ እያልን አሳለፍነዉ።

ረቡዕ ጠዋት ላይ ኢክራም እና ሪሀና ደዉለዉ እንድንወጣ ነገሩን። በሰዓቱ እኔም እነ ብሩክ ቤት ስለነበርኩ ከብሩኬ ጋር ሆነን አገኘናቸዉ። በነገራችን ላይ ብሩኬ እና ሪሀና የሌለ ፎንቃ ዉስጥ ሰምጠዋል። እንደዉም እነሱ መጎሻሸም መሳሳሙንም በደንብ እያስተናገዱት ነዉ። እኔ ከኢክራም ጋር ለመሳሳምም ሆነ ለመጎሻሸም ብዙም ፍላጎት የለኝም ፤ እሷም ላይ አላየሁም።

እኔና ኢክራም አንድ ላይ ፣ብሩኬ እና ሪሀና አንድ ላይ ፤ጥንድ ጥንድ ሆነን ከነ ብሩኬ ቤት ወደኛ ቤት በሚወስደዉ መንገድ አድርገን ከአንድ ትምህርት ቤት ጀርባ ላይ ያለ ከፍታ ቦታ ላይ ተቀመጥን።
.
ኢክሩ ፊቷን ለቀቅ ጨምደድ ታደርገዋለች።የዉሸት ፈገግታ ፊቷ ላይ ይታየኛል። ሪሀና እና ብሩኬ ከኛ ትንሽ ፈቀቅ ብለዉ ተቀምጠዋል።
ኢክራም መሬቱን በስንጥር ትጭራለች።ግራ አጋባችኝ!
"ፈዊዬ እኔ እወድሀለሁ።" ንግግሯ በእንባ የታጀበ ነዉ። መሬቱን በሀይል እየጫረች መናገር ቀጠለች

"ፈዊዬ እኔ እራስወዳድ ልመስልህ እችላለሁ። ግን ወድጄ አይደለም።"
"ኢክሩዬ ተረጋጊና ምን እንደተፈጠረ ንገሪኝ።"
"ፈዊ ላገባ ነዉ!!" መብረቅ አናቴን የፈረከሰዉ ነዉ የመሰለኝ ደርቄ ቀረሁ።
"ኢክሩ እንዴት?"
"ፈዊ የቤተሰቤን ሁኔታ ታዉቃለህ። እኔ ካላገባሁ እናቴ ህይወት የላትም። አሁን ማግባት እንዳለብኝ ወስነዋል። እኔም እነሱን ከዚህ በላይ ማስጨነቅ አልፈልግም።

" ድምጿ በሳግ ታፍኗል።

ከነዛ ዉብ አይኖቿ መንታ መንታ እንባዎች እየተሽቀዳደሙ አገጯ ስር ይሸሸጋሉ። ስታለቅስ እንባዎቿን እያየሁ አዳምጣታለሁ። ለቅሶዉን አላቋርጣትም። በእንባዋ ዉስጥ ብዙ ታሪክ ይነበበኛል። አባትን ማጣት ፣ የድሀ ልጅ መሆን ፣ ብቸኝነት፤ ብዙ ብዙ በእንባዋ ዉስጥ የተከተቡ ድርሳናት አሉ።

ራሴን ማረጋጋት እንዳለብኝ ወሰንኩ። እንደምንም ራሴን አረጋግቼ
"ኢክሩ ሁሉም ነገር ይገባኛል። አንቺ ፈልገሽ ያደረግሽዉ ነገር የለም። እረዳሻለሁ ህይወትሽ ይገባኛል። አይዞሽ ለመልካም ነዉ።"አልኳት።

ኢክሩን ከዚህ በላይ ፊቴ ስታዝን ማየት አልፈለግኩም ፤ ሁሉንም ረስታዉ የመጨረሻ ቀናችንን እንድናስዉበዉ ፈለግኩ። ፈገግ አልኩ ኢክራምን በፈገግታዬ ፈገግ እንድትል አስገደድኳት።
እኔና ኢክሩ ከመቀመጫችን ስንነሳ ሪሀናና ብሩክም ወዲያዉ ብድግ አሉ። ለካ የዛሬዉ ቀጠሮ እኔን ለማርዳት ነበር።

ሪሀና እና ብሩክ አስቀድመዉ ሁሉንም ነገር ያዉቃሉ። ከአሁን አሁን ምን ይላል እያሉ እኔን በአይናቸዉ እየሰለሉ ነዉ። ባለፈዉ ኢክራም ቤተ መፅሀፍት መጥታ "ከኔ ሌላ ጥሩ ሴት አለ!!" ምናምን ያለችኝ ቅኔዉ አሁን ተፈታልኝ። በሰዓቱ ያልነገረችኝ ፈተና ስላልጨረስኩ እንዳልረበሽ ብላ ነበር። ለራሷ አፍናዉ ስትሰቃይ ነበር!! ኢክሩዬ የኔ ሚስኪን!
.
ኢክሩን ወደ ቤቷ ስሸኛት በቻልነዉ መጠን መንገዱን ለማስረዘም ዙሪያ ጥምጥም ተሽከረከርን። በመሽከርከር ብዛት ጋብቻዉ ይሰረዝ ይመስል። መንገዱ ላይ በጠጠር ኳስ እየተጫወትን ለጊዜዉም ቢሆን ጭንቀቷን እንድትረሳዉ ለማድረግ ሞከርኩ። እሷ ፊት ሀዘኔን አሳይቼ የባሰ እንድትጎዳ አልፈለግኩም።

ኢክሩዬን የዛን ቀን ወደ ሪሀና ቤት ነበር የሸኘኋት ፣ እስከመጨረሻዉ የቻልነዉን ያህል መንገዱን ለማስረዘም ብንሞክርም እነሪሀና ቤት ደረስን። ልቤ ዉስጥ የታመቀዉን ህመም እኔ ነኝ የማዉቀዉ። ጥርሴ ግን ይስቃል። ሰማዩ ያጉረመርማል።

"ኢክሩዬ በቃ ቻዉ!!" ድምፄ ዉስጥ ስቃይ አለ!!
"ፈዊዬ ቻዉ!!"እንባዋ ለመፍሰስ ከአይኗ ጋር ይታገላል።
ኢክሩን ድጋሚ ስታለቅስ ማየት አልፈለግኩም። ብሩክ ከርቀት ቆሞ እየጠበቀኝ ነዉ። ሪሀና ወደ ቤት ገብታለች።

ዞሬ ብሩክ ቆሞ ወደሚጠብቀኝ ቦታ ስሄድ ዝናቡ መዝነብ ጀመረ።ከብሩኬ ጋር ሮጥ ብለን ሱቅ ስር ተጠለልን። ሱቁ ስር ቆሜ ኢክራምን ከርቀት ተመለከትኳት አይኖቿን እየጠራረገች ወደነ ሪሀና ቤት ሄደች።

ኢክሩን ዛሬ ለመጨረሻ ጊዜ ይሆን የማያት? ግራ ተጋብቻለሁ። ብሩክ ዝናቡ ሀይሉ ሳይጨምር እንድንሮጥ ጠየቀኝ። እየሮጥን ከነ ሪሀና ሰፈር ወጣን። ወደነ ብሩኬ ሰፈር መግቢያ ጋር ስንደርስ ዝናቡ በሀይል መዝነብ ጀመረ። አንድ ፎቅ ስር ገብተን ተጠለልን። ፎቁ ስር ረዊና እና ሁዳን አገኘናቸዉ። ተያይዘን ፎቁ ላይ ወዳለዉ ካፌ ገባን።

ረዊና እየተሽኮረመመች "ፈዊዬ ቀሽቷ ሚስትህ እንዴት ናት?" አለችኝ።
ምን ልበላት? አሁን ነዉ ቁርጤን አዉቄ የመጣሁት። ፈገግ ብዬ "ደህና ናት" አልኳት። በደህና ናት ዉስጥ ስንት ስቃይ፣ ምን ያህል ህመም እንዳለ ማን ይረዳል? ማንም። ሰዉ የፈለገ ተሰቃይቶም እንዴት ነህ ብትለዉ "ደህና ነኝ" ነዉ የሚልህ። ቁጭ አድርገህ "ችግር አለ?" ስትለዉ ነዉ ስቃዩን የሚዘረግፈዉ።"ደህና ነህ?" እኮ ጥያቄ አይደለሁም ብሎ ራሱን ሰላምታ ካደረገ ቆየ። "ደህና ነህ?" ይሉት ሰላምታ በጣም ይቀፋል።
.
ከነረዊና ጋር ተጨዋዉተን ዝናቡ ሲያባራ ሁዳ ሂሳብ ከፍላ ወጣን።
ኢክሩን የእዉነት አጥቼያታለሁ የሚል ስሜት እየተሰማኝ አይደለም። ቅዠትም ቀልድም ይመስለኛል።ገና ከእዉነታዉ ጋር ለመጋፈጥ አልደፈርኩም።

እንዴ እኔና ኢክሩ እኮ የመጋባት እቅድ አለን። እኔና ኢክሩ እኮ የምንወልዳቸዉ የልጆች ብዛት ላይ ብዙ ተከራክረን ተስማምተን ወስነናል። ኢክራም እኮ ከኔ ጋር ስትጋባ ፊልም መከታተል ለማቆም ቃል ገብታልኛለች።

እኔ እኮ ለኢክሩ ስንጋባ ከስራ መልስ ሁሌ ቤት ከሷ ጋር ለመሆን ቃል ገብቼላታለሁ። ኢክሩ እና እኔ እኮ ጁምዓ(አርብ)ቀንን ቤታችን ዉስጥ እንደ ኢድ አድምቀነዉ ለማሳለፍ ተስማምተናል። እና ይሄ ሁላ ህልም ገደል ሊገባ ነዉ? የኢክሩን ውብ አይኖች ዳግመኛ ላላይ? ማነዉ ከዚህ በኋላ የኔን ህይወት እንደ ኢክሩ ተረድቶ የሚያማክረኝ? ኢክሩ እኮ ያልገባችበት የህይወቴ ጓዳ የለም!! ቤተሰቤ እኮ እሷ ነበረች።እሺ ኢክሩዬ 'ደ'ን እየተኮላተፈች ስትል ላልሰማ ነዉ? ቆይ ግን ማነዉ ትዳርን እንዲህ ከባድ ያደረገዉ? ለምን ኢክራምን እኔ አላገባትም? ለምን ኒካህ ታስሮልን ራሳችንን እስክንችል በየቤታችን አንኖርም? ሀብታም ካልሆነ ሰዉ አያግባ ያለዉ ማነዉ?


ቀጣዩን ክፍል አሁን 4 ሰአት ላይ ይጠብቁን
እስከ 👍👍👍 እያደረጋችሁ
👫 ይጋብዙ እና ገንዘብ ይስሩ !

🎁 አንድ ሰው ሲጋብዙ 3 ብር ይሰራሉ ።

እስካሁን የጋበዙት ሰው መጠን: 0 ሰው

🔰 መጋበዣ ሊንክ : https://www.tg-me.com/hulepay_official_bot?start=r03892356955

ዛሬውኑ ጀምሮ ገንዘብ ያካማቹ እና በቴሌብር ይቀበሉ ።
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
💥📚ኢትዮ-ልቦለድ📚📖💥
Photo
●●●ነጠብጣብ●●●♥️

           

                            #ክፍል_10



.              ቆይ ግን ማነዉ ትዳርን እንዲህ ከባድ ያደረገዉ? ለምን ኢክራምን እኔ አላገባትም? ለምን ኒካህ ታስሮልን ራሳችንን እስክንችል በየቤታችን አንኖርም? ሀብታም ካልሆነ ሰዉ አያግባ ያለዉ ማነዉ?


ማነዉ ጥፋተኛዉ? ቤተሰቦቿ? እነሱ ስለኔ መች ያዉቃሉ? እንደዉም እኔ ነኝ ተጠያቂዉ በዚህ ሰአት ሀብታም ሆኜ ኢክራምን የማትፈልገዉ ሰዉ ሚስት እንዳትሆን ማድረግ ያቃተኝ ቀሽም ሰዉ እኔነኝ። አዎ እኔ!!
በፍፁም ኢክራምን ማጣቴን ማመን አልፈልግም በፍፁም!!



...🖊ኢክራም ከህይወት መስመሬ ወጥታ ወደማትፈልገዉ ሰዉ የህይወት መስመር ዉስጥ ልትገባ እንደሆነ ያወቅኩበት ጨለማ ቀን መሸ።

ከብሩክ ጋር ተለያይተን ቤት ገባሁ። ኢክሩን መርሳት ይኖርብኛል። ትዳር ዉስጥ ልትገባ ነዉ። ልረብሻት አልፈልግም። የእዉነት ካሰብኩላት ዝም ከማለት ዉጪ ምንም ማድረግ የለብኝም። መዉደድ የወደዱትን የራስ ማድረግ ብቻ አይደለም።

እንደሻማ እየቀለጡ ሌሎች ለቤተሰባቸዉ ሲሉ እንዲያደርጉት የተገደዱትን ነገርም እንዲያደርጉ መፍቀድ ነዉ። የአይዞሽ ባይነት ፈገግታን መሳየት መቻል!! ማድረግ ያለብኝ እሱኑ ነዉ። በጊዜዉ የማስተዳደር አቅም ኖሮኝ የኔ ላደርጋት አልችልም። ያለኝ ምርጫ የሚሆነዉን እጄን አጣጥፌ መመልከት ብቻ ነዉ።
.
ስልኬን አዉጥቼ ፌስቡክ ላይ ስገባ ኢክሩ ፕሮፋይል ፒክቸሯን ደም በምታነባ ሴት ፎቶ ቀይራዋለች። ሰው በሰርጉ መዳረሻ የሰርጉን ቀን ናፍቆ የደስታ መግለጫ ይፖስታል እሷ ደም በምታነባ ሴት ምስል ስቃይዋን ትነግረኛለች።

ይሄ ሰርግ ለኢክራም አዲሱን ባሏን የምታገባበት ሳይሆን ባሏ እንዲሆን የምትፈልገዉንና ሚስቱ እንድትሆን የሚመኛትን ሰዉ ከህይወቷ የምትገነጥልበት ምዕራፍ ነዉ።

ሁሉ ነገሬን የቻለችኝ እኮ ኢክሩ ነበረች!! የእምነት ጥንካሬዬ ዝቅ ብሎ ሙዚቃ በግድ ሳስደምጣት ዞር በልልኝ አላለችኝም፣ አቋሜ እስኪስተካከል ቻለችኝ!! እንደድሮዉ እንድሆን አደረገችኝ!! እና እኔ እንዴት ይህቺን ልጅ ማጣቴን ልመን?

ብሎክ ላደርጋት አሰብኩ ግን ስለኔ ሁኔታ ለማወቅ አካዉንቴን መጎብኘት መፈለጓ ስለማይቀር አንፍሬንድ ብቻ አደረግኳት። ልብ ለልብ ስትግባቡ አጋራችሁ ምን እንደሚፈልግ ሳይነግራችሁ ታዉቃላችሁ። አዎ ኢክሩ አካዉንቴ ላይ እየገባች ሁኔታዬን ለመከታተል መፈለጓ አይቀርም። በልቤ የሆነ ሰዉ በቀሰቀሰኝ ፣ ምነዉ በህልሜ በሆነ እላለሁ።
.
እጄን ቆነጠጥኩት፣ አመመኝ፤ አዎ በእንቅልፍ ልቤ አይደለም። አልጋዬን አየሁት በጣም ሰፋኝ። ከዚህ በፊት ሳየዉ ኢክሩ ልጃችንን አልጋዉ ላይ ስታጫዉተዉ ነበር በእዝነህሊናዬ የማይበት። ዛሬ ጭር ያለ ሜዳ መሰለኝ።
ኢክሩን ከኔ ሌላ የሆነ ወንድ ሊያገባት ነዉ። እሺ ታግባ!! ግን እኮ የምትፈልገዉን ሰዉ አይደለም የምታገባዉ!! እኔን የሚያንገበግበኝ ኢክሩ የምትወደዉን ሰዉ አለማግባቷ ነዉ።

ከብቸኝነት ብርዷ ዉስጥ ሙቀት ለመፍጠር በወዳጅነት በቆየንባቸዉ ቀናት እና ፍቅረኛ ሆነን ባሳለፍናቸዉ ጊዜያት ዉስጥ ይሄ ባል ተብዬ መጥቶ እስኪበጠብጠን ብዙ የኢክራምን የህይወት ታሪኮች አዳምጫለሁ። ሁሉም የሀዘን ታሪክ ናቸዉ።

ዛሬ የማትፈልገዉን አታግባ የምለዉ ቢያንስ ቀሪ ህይወቷን ፊቷ በፈገግታ ተዉቦ ደስተኛ ሆና እንድታሳልፍ ስለማልም ነዉ። እሷ የምትወደዉ ሰዉ ደግሞ እኔ ነኝ። የኔ ህልም ደግሞ ኢክሩን ደስተኛ ማድረግ ነበር። ምን ያደርጋል ነበር ሊሆን ነዉ!! ከህይወቷ እንደጨረቃ ቤት ልፈርስ ነዉ። ለነገሩ ትዳር ያልመሰረቱ ጥንዶች ምሳሌ እንደጨረቃ ቤት ነዉ። ቤተሰብ ሴቷን ለልማት ሲፈልጋት ጥምረታቸዉን ያፈርሰዋል። ልማቱ ደግሞ ትዳር ነዉ። ምን ነበር የማልማት አቅሙ በኖረኝ!!
.
ጠዋት ከእንቅልፌ ስነሳ ቤት ዉስጥ ማንም የለም። ባዶ ቤት ዉስጥ ባዶነት የተሰማኝ እኔ ብቻ አለሁ። አሁን ከእዉነታዉ ጋር ፊት ለፊት ተጋፈጥኩ። ኢክራም ሌላ ሰዉ ልታገባ ነዉ። እንደዛ የምሳሳላት ቆንጆ ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ በፍቅር የከነፈችልኝ ሴት ልታገባ ነዉ። የማትፈልገዉን ሰዉ እንደምታገባ ሳስብ በጣም ከፋኝ። አልጋዬ ላይ እንዳለሁ እንባ ከአይኖቼ ፈሰሰ። ሰዉነቴ መንዘፍዘፍ ጀመረ። ተንሰቀሰቅኩ። ወንድነቴ ትጥቁን ፈቶ ተማረከ ፣ ለአምስት ሰዓታት ተነፋረቅኩ።

ኢክሩን እያሰብኩ አልቅሼ ሲበቃኝ አምስት ሰዓት ላይ ብሩክ ጋር ደዉዬ ቤት እንዲመጣ ነገርኩት።
ቤት መጥቶ አብረን ቁጭ እንዳልን ብሩኬ "ፈዉዛን በተፈጠረዉ ነገር በጣም አዝኛለሁ!!" አለኝ።
የብሩኬ ንግግር ስሜቴን አገነፈለዉ። ተንሰቅስቄ ማልቀስ ጀመርኩ።
"ብሩኬ እኔ እኮ የሚያሳዝነኝ መለያየታችን አይደለም። ግን ኢክሩ የማትፈልገዉ ሰዉ ላይ ልትወድቅ ነዉ።" እያልኩ እንሰቀሰቃለሁ።
ብሩክ አቅፎኝ ማልቀስ ጀመረ። ተላቅሰን ሲያባራልን ተነስተን ወደ ብሩክ ቤት ሄድን።

ብሩኬ መንገድ ላይ ሆነን "ፈዊ ግን የኢክራም ቤተሰቦች በጣም ደደብ ናቸዉ።" አለኝ እልህ እየተናነቀዉ።
"ያሉበት ሁኔታ ይሆናል ያስገደዳቸዉ።" አልኩት የኢክሩ ቤተሰቦች ሲሰደቡ ኢክሩ የተሰደበችብኝ ያህል ነበር የተሰማኝ።
አሁን ላይ ሳስበዉ የዛን ቀኑ የብሩኬ ሁኔታ ያስቀኛል። እኔን እንደማባበል እሱ ራሱ ተንሰቅስቆ ያለቅሳል።
.
እኔና ኢክሩ ከተለያየን ቀናት አልፈዉ ሳምንታት ተተኩ። ሰዉ አጠገቤ ሲኖር ህመሙን እረሳዋለሁ። ብቻዬን ስሆን ግን እሷን ብቻ ነዉ የማስበዉ። የኢክራም ጓደኛ ሪሀና አንዳንዴ እየደወለች ታፅናናኛለች።

ጌታዬን ለመንኩት!! ህይወቷን ያማረ እንዲያደርግላት ፣ ባሏንም ለሷ ጥሩ እንዲያደርግላት ተማፀንኩት። ምንም ብወነጅለዉ ጌታዬን ለምኜዉ ከልክሎኝ አያዉቅም። በሰዓቱ ፌስቡኬ የሀዘን ቤት መሰለ። የምፖስታቸዉ ነገሮች ሁሉ ብሶቶች ነበሩ። ከኢክራም ጋር አንገናኝም፣አንደዋወልም በቃ የግንኙነት መስመሮቻችን ሁላ ተቋርጠዋል።


አላለቀም
እንዴት ነው ትረካው እየተመቻችሁ ነው ደሞ ሀሳብ አስተያየት Like Share እያረጋችሁ
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
2024/09/21 03:18:15
Back to Top
HTML Embed Code: