Telegram Web Link
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
💥📚ኢትዮ-ልቦለድ📚📖💥
Photo
●●●ነጠብጣብ●♥️

           
 
#ክፍል_11


ከኢክሩ ጋር ከተለያየን ወደ አንድ ወር ገደማ ሆነ።ሰአቱ የረመዳን ፆም የተጀመረበት ጊዜ ነበር። ሪሀና ደዉላ ልታገኘኝ እንደምትፈልግ ነገረችኝ። ረመዳን ላይ ከሴት ጋር መቀጣጠር አልወድም!ትኩረቴን ሙሉ ለሙሉ አምልኮ ላይ ማድረግ ያስደስተኝ ነበር። ግን ሪሀና ስለሆነች ለጥቂት ደቂቃ ላገኛት ተቀጣጠርን።ሪሀና ልትነግረኝ የፈለገችዉ ነገር እንዳለ ገብቶኛል።ምን እንደሆነ ግን አላወቅኩም። ምናልባት ከብሩኬ ጋር ተጋጭተዉ ይሆን?ብቻ ግራ ገብቶኛል።
ሪቾ ለምንድነዉ በአካል ልታገኘኝ የፈ ለገችዉ? ለነገሩ ምን አስቸኮለኝ ራሷ ትነግረኝ የለ።

ሪሀና ስትደዉልልኝ መስጂድ ዉስጥ ነበርኩ። ረመዳን ላይ መስጂድ ድርሽ ብሎ የማያዉቅ ሰዉ ሳይቀር በረመዳን መስጂዱን ቤቱ ነዉ የሚያደርገዉ። ወንጀለኛ ልቦች ሁሉ ወደ ጌታቸዉ ይዋደቃሉ።ቀን ላይ መስጂዱ ቁርዓን በሚቀሩ ሰዎች ተዉቦ ይዉላል።ምሽቱን በዉብ ድምፃቸዉ ቁርአንን በምሽቱ የተራዉሂ ሰላት ላይ በሚያሰግዱ ኡስታዞች ይደምቃል።የሁሉም እጅ ይፈታል። ያለዉ ለተቸገረዉ በጣሙን እጁን የሚዘረጋበት ወር ነዉ። እኔ እንኳ ረመዳን ባይሆንም ከመስጂድ አልጠፋም።ዞሬ ዞሬ መመለሻዬ መስጂድ ነዉ

ከመስጂድ ወጥቼ ሪሀና ወደ ቀጠረችኝ ቦታ ሄድኩ።በሪሀና ተወስዉሼ ፆሜ እንዳይበላሽ አይኔን ሰብሬ ነዉ የማናግራት። መወስወስ ስል ሴት ናትና የሚያምር ነገር ይኖራታል።ደግሞም ቆንጆ ናት እና ዉበቷን አይቼ ልቤ እንዳይንሻፈፍ እየተጠነቀቅኩ መሆኑ ነዉ።

ሴት ሲፈጥራትም ሁሉ ነገሯ ዉብ ነዉ።እኛ ደግሞ የሴት ልጅን እንኳ መልኳን አይተን በድምጿ ብቻም ልባችን ይዋልላል።እኛ ወንዶች
ሪቾ የተቆጣሁ መስሏት ግራ እየተጋባች "ፈዊ የሆነ ነገር ልነግርህ ነበር።"አለች
"ሪቾ ፈታ ብለሽ ንገሪኝ ምንድነዉ?
"ፈዊ እየቀለድንብህ ምናምን ሊመስልህ ይችላል! እኔ ራሱ ይቅር ብዬ ነበር ግን እሷ ሁሌ አንተን እያሰበች ስታለቅስ አልቻልኩም።
"ምንድነዉ ለምን ግልፅ አታደርጊዉም?አልኳት ግራ እየተጋባሁ
"ፈዊዬ ኢክሩ ልታገባዉ ከነበረዉ ሰዉ ጋር ስላልተስማሙ ጋብቻዉ ከተሰረዘ ቆይቷል።እና እስከአሁንም ልንነግርህ ነበር ግን ፈራንህ።ከኢክሩ ጋር እንደድሮዉ ብትመለሱ ምን ይመስልሀል? እሷ እያለቀሰች አስቸገረችኝ።"አለች

ገረመኝ ኢክሩን ድጋሚ ላገኛት ነዉ? ድጋሚ እነዛን ዉብ አይኖቿን ላያቸዉ ነዉ? ጆሮዬ የናፈቀዉ ቁምነገር የተሞላ ንግግሯን ሊያደምጥ?ስለኔ የሚጨነቅ ሌላ ሰዉ ላገኝ ነዉ?በጣም ነዉ የሚገርመዉ በጣም
ከኢክሩ ጋር የፍቅር ግንኙነት ዉስጥ ስንገባ እኔ ጋር ለኢክሩ የወንድምነት እንጂ የፍቅር ስሜት አልነበረም።

ኢክሩን ስለያት ግን መላመድ ምን ያህል መለያየትን እንደሚያከብድ ተረዳሁ።
ሪቾ ልልሽ የምችለዉ አንድ ነገር ነዉ። ኢክራምን እወዳታለሁ።አሁን ብቻ ሳይሆን ከዚህ በኋላም ከህይወቴ ወጥታ ብትመለስ እቀበላታለሁ።"አልኳት።
ሪቾ ይሁንታዬን በማግኘቷ ፊቷ ፈካ።

ሪሀና ለኢክራም ምርጥ ጓደኛ ናት።እኔን ለሷ ስትጠይቀኝ ራሱ ለጓደኛዋ በጣም ታደላ ነበር።
ሪቾ ለኢክራም ደዉዬ እንድንቀጥል መፍቀዴን እንድነግራት ጠየቀችኝ። ሪቾ ትቸኩላለች።አሁን ነዉ እንድደዉል የፈለገችዉ።እኔ ወደ ማታ እንደምደዉልላት ነግሬያት ተለያየን
ከሪቾ ጋር እንደተለያየን ወደ መስጂድ ሮጥኩ።ጌታዬን በግንባሬ ተደፍቼ አመሰገንኩት።ጌታዬ ምስጋናዬን ይቀበለዉ አይቀበለዉ አላዉቅም። ሲጀመር በእስልምና ሀይማኖት ፍቅረኛ የሚባል ነገር በጣም የተወገዘ ነዉ። እስልምና ወደ ዝሙት የሚወስዱ መንገዶችን ገና ከሩቁ ነዉ የሚዘጋቸዉ ግን እኔ ስሜቴ አሸንፎኝ ተነክሬበታለሁ አላማዬ ግን ኢክራምን ማግባት ነዉ። እስከአሁን ዝሙት ዉስጥ አልገባሁም። ከዚህ በኋላ ላለዉም ዋስትና የለኝም። ዝሙት ዉስጥ መግባት ይቅርና ኢክራምን ነክቼያት እንኳ አላዉቅም። በእምነቴ ሌሎች ጎኖች ላይ ጠንካራ ነኝ አንዱና ዋነኛዉ ክፍተቴ ከኢክራም ጋር የፍቅር ግንኙነት መጀመሬ ነዉ።
.
ሲመሽ ኢክሩ ጋር ደወልኩላት።ኢክሩዬን አናገርኳት።ከአንድ ወር በኋላ ድምጿን ሰማሁ።ጊዜዉ ረመዳን ስለሆነ ፆሙ እስከሚጠናቀቅ በአካል እንደማንገናኝ እና እስከዛዉ በስልክ እንደምንገናኝ ተነጋገርን

ረመዳን ሊያልቅ አስር ቀናት ቀሩት። እነዚህ የመጨረሻ አስር ቀናት ከረመዳን ሌሎች ቀናት በጣም ከፍ ያለ ክብር አላቸዉ።ከነዚህ አስር ቀናት በአንደኛዉ "ለይለተል ቀድር"የምትባል ለሊት አለች። በነዚህ አስር ቀናት ዉስጥ እንደሆነች እንጂ የትኛዉ ለሊት ላይ እንደምታልፍ አይታወቅም።ስለዚህ ሰው በዚህች ለሊት የሚገኘዉን ታላቅ ምንዳ ለማግኘት የመጨረሻዎቹን አስር ቀናት ከሌሎች የረመዳን ቀናት በተለየ በአምልኮ ተወጥሮ ያሳልፋቸዋል።
በነዚህ የመጨረሻ አስር ቀናት ከኢክሩ ጋር ላለመደዋወል ተስማምተን ከኢድ በኋላ ለመገናኘት ከወዲሁ ተቀጣጠርን።

እነዛ ዉብ የረመዳን ለሊቶች አልቀዉ የኢድ ዕለት ደረሰ። ከኢክራም ጋር ተደዋዉለን በነጋታዉ ለመገናኘት ተቀጣጠርን
ከተጣጣን በኋላ ድጋሚ በአካል ተገናኘን።ኢክሩ እንደድሮዉም እንዳማረባት ናት።ቤቴ ዉስጥ ሚስቴ ሆና ላያት የምመኝላት ኢኩዬ ደህና ናት።
የሀፍረት ፈገግታ ፈገግ እያለች "ፈዊዬ እራስወዳድ ሆኜ ትቼህ ስለሄድኩ በጣም ይቅርታ"አለችኝ።
አይኗን እየተመለከትኩ"ኢክሩ ከዚህ በፊት ያጠፋሽዉን እና ከዚህ በኋላም የምታጠፊዉን ጭምር ይቅር ብዬሻለሁ"አልኳት።ይሄ ንግግር ከፈጣሪ የተኮረጀ ነበር። አላህ ለነብዩ ሙሀመድ (ሰ ዐ ወ)ያላቸዉ ነዉ።አላህ ነብዩን ስለወደዳቸዉ እንዲህ አላቸዉ። እኔ ኢክራምን ስለወደድኳት የፈጣሪን ንግግር ኮረጅኩላት።ወደፊት የሚፈጠረዉን ሳላዉቅ ይቅር ብዬሻለሁ ማለቴ አግባብ ይሁን አይሁን አላዉቅም።
.
ከኢክሩ ጋር የፍቅር ግንኙነታችን አዲስ ምዕራፍ ከፈተ።ብሩክን በድጋሚ ስለመመለሳችን ነግሬዉ ደስ አላለዉም። "ድጋሚ ማልቀስ ፈለግክ?"ነበር ያለኝ። እሱ ለኔዉ አስቦ ይመስለኛል። እኔ ደግሞ ለኢክራም የማሰብ በሽታ አለብኝ።
ብሩክ እና ሪሀና በየመሀሉ ቢጋጩም አሁንም እንደከነፉ ናቸዉ።
.
ኢክሩ ቾኮሌት በጣም ዝንደምትወድ ነግሬያችኋለሁ።ሰሞኑን ስንገናኝ ቸኮሌት ይዤላት መሄድ አዘዉትሬያለሁ።
በዚህ መሀል የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ዉጤት ወጣ።አሪፍ ዉጤት ነበር ያመጣሁት።ረዊና እና ሁዳም ሰቅለዉታል።ብሩኬም አልፏል።ሄኖክ ግን ዉጤቱ ወርዷል።
አሁን የዩኒቨርሲቲ ዉጤት ተለቅቋል። የምንመደብበትን ዩኒቨርሲቲ በጉጉት እየጠበቅን ነዉ።እኔ አዲስአበባ እንዲደርሰኝ ነዉ የምፈልገዉ።ስነ አእምሮ ማጥናት እፈልጋለሁ።የሰዉን አስተሳሰብ እና ማንነት መረዳት ወትሮዉንም እወዳለሁ።ይሄን ፍላጎቴን ዩኒቨርሲቲ ገብቼ በትምህርት ማዳበር ይኖርብኛል። ስነ አእምሮ(Psychology)መማር ህልሜ ነዉ።

ኢክሩ ገና ከአሁኑ ስጋት ይዟታል። አንዳንዴ ክፍለሀገር ደርሶኝ እንዳንለያይ ትሰጋለች።ድጋሚ እንዳታጣኝ ነዉ ስጋቷ! አንዳንዴ ደግሞ ዩኒቨርሲቲ ስገባ ከሌላ ሴት ጋር የፍቅር ግንኙነት የምጀምር እየመሰላት ትፈራለች። እኔ ቆንጆ ሴት በጣም እወዳለሁ።አልዋሽም!! የኢክራምም ስጋት ዩኒቨርሲቲ ስገባ ሌላ ሴት አይቼ እንዳልከዳት ነበር።ለኔ ግን ጭንቀቷ መሰረት የለሽ ነዉ።ኢክራምን በጣም እወዳታለሁ።እኔ ሴት ቀድማ ካላናገረችኝ እንኳ የማላናግር ልጅ ነኝ። ኢክሩ ስትጠረጥረኝ ደስ አይለኝም።
ከጥቂት ቀናት በኋላ የዩኒቨርሲቲ ምደባ መዉጣቱ ተነገረ።ምሽቱን እኔና ብሩኬ ለማየት ብንሞክርም ኔትዎርኩ ተይዞ ስለነበር አልቻልንም።ክፍለሀገር እንዳይደርሰኝ በጣም ፈርቼያለሁ በጣም!!

                
#ይቀጥላል
ታሪኩ ቶሎ እንዲቀጥል ላይክ አርጉ
፡፡
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
ባሌን ያገባሁት ብርሃነን ስለሚመስል ነው ። ጥንካሬው እና ታማኝነቱ የአባቴ የብርሃነን አይነት ነው ።

መውደዳችን ውስጥ አስተዳደጋችን ተፅፏል።

አባቴ በጊዜ ነው የሚገባው ፣ እናቴን የሚወዳት መጠን ፣ የሚያከብራት አከባበር የተለየ ነው ፤ አለሙን ያገባሁት ቁርጥ ብርሃነን ስለሆነ ይመስለኛል ።

የሆነ ቀን...የሆነ ገፊ እና ቀፋፊ ቀን....አለሙ መሸርሞጡን ደረስኩበት ።

እንዴት እንደጠላሁት ። ጥላቻዬ የጀመረው መልከስከሱን ስደርስበት ነው ። ፍቅሬ እሱ ላይ ካለኝ እምነት ጋር የተዋሃደ ነበር። እምነቴ ሲተን ፣ ፍቅሬ ብቻውን መፅናት ሳይችል ቀረ ፤ አለሙን ጠላሁት ።

"ተፋተናል" የሚል ቁራጭ ወረቀት ትቼለት እናቴ ቤት ሄድኩ ። እናቴ ከአለሙ ጋር ተጣልቼ እንደሆነ አወቀች ።

እንደእናት ብዙ መከረችኝ: እንደጎደኛም አደመጠቺኝ ። "እኔ የብርሃነ ልጅ ነኝ ልክስክስነትን አልታገስም" አልኳት ።

"ያደግኩት አንቺን እና ብርሃነን እያየሁ ነው" አልኳት ። "ያደግኩት ሚስቱን እንደንግስት ከሚቆጥራት አባት ጋር ነው። ያደኩት ባሏን እንደንጉስ ከምታከብረው እናት ጋር ነው" አልኳት ።

ሳወራ ...ስፎክር.... ስቅለሰለስ፣ ሆድ ሲብሰኝ ... በማዘን ቃል ሳታወጣ ነበር የምትሰማኝ ።

እናት አይደለች ባሸንፍ እንኳን "ደከመሽ አይደል፣ ባተልሽ አይደል?" ብላ ደስታዋ ውስጥ ሳይቀር ማዘን ይኖረዋል!!

በሰባተኛው ቀን እንደዋዛ ... "ኤልሱ የኔ ኤልሳ" አለች
"አቤት ማሚ "
" ብርሃነ ከተጋባን በኋላ ከሌላ የወለደው ልጅ ነበረው ፤ ገመና ሆኖ የቀረው የወለደው ልጅ በለጋ እድሜው ስለተቀጠፈ እና ስለማይጠቅም ብለን ነው በፊትሽ አውርተን የማናውቀው " ብላ በሃዘኔታ አየችኝ ።

የሆነ ነገር ሲናድብኝ ፣ የሆነ ፍርሃት ሲያላውሰኝ እየታወቀኝ ነው ። የምናውቀው በሚመስለን
ጎጆ ውስጥ እንኳን ብዙ የማናውቀው እውነት ተቀብሯል



@Meki3
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
💥📚ኢትዮ-ልቦለድ📚📖💥
Photo
.              ♥️●●●ነጠብጣብ●●●♥️

           
     
#ክፍል_12

...🖊ለሊት ተኝቼ ስልክ ተደወለልኝ። ስልኬን በእንቅልፍ ልቤ ለማንሳት ስታገል ወደ ታች ጣልኩት። እንደምንም ስልኬን ከአልጋ ስር አውጥቼ አነሳሁት። አዩብ ነበር። የሪም ፍቅረኛ!! እንደዉም የኢክሩን ስልክ እንዳገኝ የረዳችኝ ልጅ!! አስታወሳችኋት?

"ፈዉዛኔ እንኳን ደስ አለህ!" አለኝ።
"ምንድነዉ?" አልኩት ከእንቅልፌ ለመላቀቅ እየታገልኩ።
"አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ደርሶሀል!" አለኝ።
በጣም ደስ አለኝ "አንተስ የት ደረሰህ?"

"ባክህ አብረን ነን እኔም እዚሁ ነኝ።" አለኝ። ስለደወለልኝ አመስግኜዉ ስልኩን ዘጋሁት።
ያዉ አዩብ የሪጅስትሬሽን ቁጥራችንን ያዉቀዉ ስለነበር ነዉ ያየልን።
.
ኢንተርኔቴን አብርቼ የጓደኞቼን ምድብ ማየት ጀመርኩ።
ብሩኬ አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ደርሶታል። ስለተለያየን በጣም አዘንኩ። እኔ አዲስ አበባ ስለደረሰኝ ደግሞ በጣም ደስ አለኝ።

ረዊና ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፣ ሁዳ ደግሞ ጅማ ደርሷቸዋል። ሁለቱም የመጀመሪያ ምርጫቸዉን ነበር ያገኙት።
ወዲያዉ ፌስቡክ ላይ ገብቼ "አልሀምዱሊላህ" የምትል ምስል ለጥፌ ወጣሁ። አልሀምዱሊላህ ማለት ለአላህ ምስጋና ይገባዉ ማለት ነዉ።

ደስታዬን ለመግለፅ ነዉ የለጠፍኩት። ነግቶልኝ ለኢክሩ ደስታዬን እስክነግራት ጨንቆኛል። ግን ትንሽ ላስጨንቃትም ፈልጌያለሁ።

ኢክሩ ግን ገና ከፌስቡክ ፖስቴ አዲስ አበባ እንደደረሰኝ ተረድታለች። ወደማታ ስንገናኝ ፈገግ ብላ "የት ደረሰህ?" አለችኝ በነዛ ዉብ አይኖቿ ፊቴን እየሰለለች። ፊቴን አጨፍግጌ ክፍለሀገር እንደደረሰኝ ነገርኳት። ሳቋን ለቀቀችዉ። ኢክሩ እኮ ትሳቅ! የእዉነት ትሳቅ! ስትስቅ በጣም ነዉ የምታምረዉ።

"ምን ያስገለፍጥሻል!" አልኳት ሳቋ እየተጋባብኝ
"ፎግረህ ሞተሀል!! ባክህ እዚሁ አዲስ ነዉ የደረሰህ!!" አለች በከሸፈዉ የፉገራ ሙከራዬ እየሳቀች።
.
ሰዓቱ ትንሽ ሀይማኖቴ ላይ የነበረኝ ጠንካራ አቋም እየላላ ያለበት ነዉ። እስከዚህች ቅፅበት ድረስ እኔና ኢክራም ተጨባብጠን እንኳ አናዉቅም ብላችሁ ታምናላችሁ? በቃ በእስልምና ሀይማኖት እንድትጨብጣቸዉ የተፈቀዱልህ የተቆጠሩ ዘመዶችህ አሉ ከነሱ ዉጪ ማንንም መጨበጥ አይፈቀድልህም። ምክንያቱ ደግሞ የዝሙትን መንገዶች ሁሉ ከሩቁ ለመጠንቀቅ ነዉ። የእኔና የኢክሩ ግንኙነት ማለትም ፍቅረኛ መሆን የሚባለዉን ግንኙነት ደግሞ ሀይማኖታችን አበክሮ ያወግዘዋል። አንዳንድ ሰዎች "ቆይ ፍቅረኛ መሆናችሁም ሀራም(የተከለከለ) ነዉ ፣ አንጨባበጥም ማለቱ ምን የሚሉት ነዉ?" ብለዉ ይፎግሩናል።

ግዴታ አንደኛዉን ወንጀል ከሰራህ ሁለተኛዉንም ወንጀል መስራት አለብህ ብዬ አላምንም። እኔና ኢክሩ የፍቅር ግንኙነት ዉስጥ ገባን ጥፋት ነዉ አዉቃለሁ!! ግን አለመጨባበጣችን ወደ ዝሙት የምትወስደዋን መንገድ ይዘጋል ብዬ አስባለሁ። ሁሉም ነገር ደረጃ በደረጃ ነዉ እያደገ የሚሄደዉ። ሳልጨብጣት ልስማት አልችልም።
.
ግን ጊዜዉ እየተራዘመ ሲመጣ ከኢክሩ ጋር መላፋቱ እያማረኝ ስሜቴ ምክንያታዊነቴን እየተጫነዉ መጣ። የኢክሩን ዉብ ከንፈሮች መቅሰም አማረኝ። የማንጨባበጥ ሰዎች በአንዴ ለመሳሳም ለመድረስ ከባድ ስለሆነ ትንሽ የማላመድ ስራዎችን መስራት ነበረብኝ። እኔ ግን የሚገርመኝ ጭንቅላቴ በአንድ ጊዜ ዉስጥ ስንት እቅድ እንደሚያቀነባብር!!

በእቅዱ መሰረት የመጀመሪያዉ ስራ መጎሻሸም መጀመር ነበር። በተለምዶ ሴቶችን ስንነካቸዉ ከጮሁ ድንግል ናቸዉ ምናምን እያልን የምናረጋግጥበት ቦታ አለ አይደል? በዳሌያቸዉ እና በወገባቸዉ መካከል ስምንት ቁጥር የሚፈጥረዉ ቦታ ማለት ነዉ።

ኢክሩዬ እሱ ጋር ስትነካ ትጮሀለች!! ትጮሀለች አይገልፀውም በቃ ትሰቃያለች። ደስታም ለቅሶም አይደለም ግን ለየት ያለ ጩኸት!! እንድትነኳት አትፈልግም። አብረን የምንቀመጥበት ቦታ ላይ ስንሆን እሱጋር እየነካኋት ምናምን መላፋት ጀመርን። መላፋቱ ሲያድግ ወደ መኮራኮር አደገ።
ደረጃዉን ወደ ላይ ከፍ አደረግነዉ ማለት ነዉ እንግዲህ!!

ኢክሩዬን እንባዋ እስኪፈስ ነበር የምኮረኩራት። ሳቅ ፣ እንባ እና ትንፋሿ አሁንም ድረስ ትዝ ይለኛል። በጣም ከምወዳቸዉ ሽታዎች መካከል የኢክሩን የላብ ጠረን የሚደርስ የለም። ምናልባት በፀሀይ ዎክ አድርገን አሊያም ከትምህርት ቤት ደክሟት እኔ ጋር ስትመጣ የሚሸተዉ የሰዉነት ጠረኗ ወደር የለዉም። ሽቶ አይደለም!! ትክክለኛ የተፈጥሮ የላብ ጠረኗ በጣም ደስ ይለኝ ነበር!! በጣም ነበር የምወደዉ። ስወድ እወዳለሁ! የኢኩዬ ሲሆን ምንም እወዳለሁ!! እስከአሁንም ሳስባት ጠረኑ ያዉደኛል። ሁሌም ጠረኗ ሚስቴ ሆና በእቅፌ ተኝታ ሳሸተዉ በኖርኩ እል ነበር። ደስታ ይሰጠኝ ነበር።

እናም ወገቧን ከመንካት ወደመኮራኮር ዙሩ ከሯል። ኢኩዬን መኮርኮር!! ሰዉ እንዴት አንድን ሰዉ ኮርኩሮ እንደዚህ ደስ ይለዋል? ከጀርባችን እያረካነዉ ያለዉ ፆታዊ ፍላጎታችን ስላለ ነዉ እንዲህ ደስ የሚለን። ይህን ድርጊት ለጥቂት ጊዜ ደጋገምነዉ። ጉልበቴ ላይ አድርጌ ስኮረኩራት ቀልቧ እስከሚጠፋ ድረስ እየሳቀች እንባዋ ሲፈስ አስታዉሳለሁ።

የኔ ቆንጆ!! ለቅሶሽም ሳቅሽም የተዋበ!!
አሁን መጎሻሸሙም መኮራኮሩም መንገዱን ይዟል። አሁን ቀጣዩ እቅድ መሳሳም የሚለዉ ነዉ!! ኢክሩዬን መሳም የታፈነዉን ስሜቷን ማዳመጥ!! የታፈነዉን ሰዋዊ ስሜቴን ማስተናገድ!! የፈጣሪን ህግ መናድ!!
.
ሴት ልጅ አይነአፋር ናት ብትፈልግም አትናገርም ምናምን ሲባል ስለሰማሁ ፈልጋ በፍርሀት ታፍና ከምትሞት እኔ ራሴ ልስማት ወሰንኩ። ግን በጣም ይከብድ ነበር ሊያዉም ከኔ ኩራት ጋር ተደምሮ አስቡት!! ግን መሆን እንዳለበት ስለወሰንኩ እኔንም እሷንም ጀማሪ በማያስብል መልኩ የምንሳሳምበትን እቅድ አወጣሁ።

አሁን ሰዉ ለመሳሳም እቅድ ያወጣል? ፎርማል ነገር ነኝ አላልኳችሁም ነበር? አሁን እቅዱ ተነድፎ ወደ ትግበራ ለመግባት በቀጣይ የምንገናኝበትን ጊዜ እየጠበቅኩ ነዉ። እምቢ ብትለኝስ? መዋረድ አልፈልግም። ለዛ ነዉ እቅዱን እኔን ጀማሪ በማያስመስል መልኩ የነደፍኩት። አሁን የትግበራ ሰአት ደርሷል።
.
ሁሌም ባይሆንም በአብዛኛዉ ኢክሩ ጋር ስሄድ ቸኮሌት ይዤ ነዉ የምሄደዉ። ኢክሩ ቸኮሌት ነብሷ ነዉ። እና የእኔም እቅድ እንደ ነብሷ በምትወደዉ ቸኮሌት ነብሷን መዉሰድ ነዉ። ሌላ ጊዜ ቾኮሌት ስወስድላት በእጇ ነበር የምሰጣት አሁን ግን በእጄ እየሰበርኩ ላጎርሳት እና መጨረሻ ላይ በአፌ ይዤ እንድትጎርስ መጠየቅ ነዉ።

ቸኮሌቱን ለመጉረስ ከንፈሬ ጋር ስትደርስ ቾኮሌቱን ወደ አፌ እከተዋለሁ። ከንፈሯ ቸኮሌቱን ስቶ ከንፈሬ ላይ ያርፋል። እንግዲህ እቅዱ ይሄ ነዉ። ሚሽኑን Chocolet kiss ብየዋለሁ።(በቤትም ሆነ በስራ ቦታ እንዳይሞክሩት) ኢኩዬን ለመሳም እቅድ ተነድፏል አሁን ለትግበራ የምንገናኝበትን ሰዓት በጉጉት እየጠበቅኩ ነዉ።...

          
#ይቀጥላል
ታሪኩ ቶሎ እንዲቀጥል ላይክ አርጉ
፡፡
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
እየተዘጋጀ ነው
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
💥📚ኢትዮ-ልቦለድ📚📖💥
እየተዘጋጀ ነው
.              ♥️●●●ነጠብጣብ●●●♥️

           
  
#ክፍል_13

...🖊ከኢክሩ ጋር ተገናኝተን ሰሞኑን ወደምንሄድበት ጭር ያለ ቦታ ሄድን። ቦታዉ ደስ ይላል። ሰዉ አይበዛበትም ነፃነት ነገር ይሰጣል። ቾኮሌት ይዣለሁ። ሊያዉም ሁለት ቾኮሌት ነዋ!! በአንዱ ቢከሽፍ በአንዱ እቅዱን ላሳካ ታጥቄያለሁ።

ከኢክሩ ጋር ትንሽ ካወራን በኋላ ሰሞኑን የጀመርነዉን መጎሻሸም ጀመርን። ወገቧን ስነካት ስትለምነኝ ምናምን!! ስነካት ፣ ስትጮህ ፤ ስኮረኩራት "ፈዊዬ በአላህ!!" እያለች እየሳቀች ስታለቅስ፤ በቃ ምንልበላችሁ ሙዱ ውስጥ ገባን።
አሁን ቾኮሌቱን ከኪሴ ዉስጥ አወጣሁና በእቅዴ መሰረት በእጄ እየሰበርኩ አጎረስኳት።

ቾኮሌቱ አልቆ ትንሽ ሲቀር በጥርሴ ይዤ እንድትጎርስ ጠየቅኳት። ኢኩ አየችኝ እና ፈገግ አለች። አላማዉ በደንብ ገብቷታል። "ቸኮሌቱን ልበላ ስል ነዉ የሳመኝ" የምትልበትን ምክንያት ስላመቻቸሁላት ደስ ሳይላት አይቀርም።

አንዳንዴ ነገሮችን ማድረግ እየፈለግን ይሉኝታን ስንፈራ ነገሮችን ለማድረግ የሚገፋን ምክንያት እንፈልጋለን። ከራሳችን ላይ ሀላፊነቱን ለመግፋት እንሞክራለን።

እኔም ኢኩዬ በቸኮሌቱ ምክንያት ስትስመኝ አጋጣሚ እንጂ እኔ አስቤዉ አይደለም ለማለት ነዉ እቅድ ያዘጋጀሁት። እሷም ሳምኩት ላለማለት ቆንጆ ምክንያት ታገኛለች ማለት ነዉ። ግን ይሄ ከሰዉ ይሉኝታ እንጂ ከፈጣሪ አያስጥልም።
.
ወደ አፌ ቀረብ ስትል ቾኮሌቱን ትንሽ ወደ ዉስጥ ሳብ አደረግኩት። ትንሽ ቀረብ ብላ ከከንፈሬ የራቀዉን በላችዉ። እየበላች ወደ ከንፈሬ ስትደርስ አቆመች።
ፈገግ ብላ "እሱን በእጄ ስጠኝ!!" አለችኝ። እቅዱ ተሳካ ስል ልታበላሸዉ ነዉ ብዬ ተናደድኩ።

ግን አሁንም ጭንቅላቴን አሰራሁት። ቸኮሌቱን ትንሽ ወደ ዉጪ ገፍቼ እንድትበላ ነገርኳት። መብላት ጀመረች አሁን ቸኮሌቱን እየበላች በከፊል ከንፈሮቻችን እየተነካኩ ነዉ።

አሁንም ትንሽ በልታ አቆመች እና አየችኝ "ብዪ እንጂ!!" አልኳት። "ኧረ ልትስመኝ ነዉ አይደል?" አለችኝ። መግደርደር መጀመሩ ነዉ እንግዲህ!
"እስከአሁንስ ከንፈሮቻችን አልተነካኩም እንዴ? ባክሽ ብዪ!" አልኳት እየሳቅኩ ሀፍረቴን ለመደበቅ እየሞከርኩ።
ወደ ከንፈሬ ተጠግታ ቾኮሌቱን መብላት ጀመረች።

ቸኮሌቱ ሲያልቅ ከከንፈሯ ጋር ተገናኘን። ነዘረኝ!!! ከንፈር ስስም ለመጀመሪያ ጊዜዬ ነዉ። እሷም የመጀመሪያዋ ይመስለኛል። ኢክሩ አይኖቿ ተዘጉ ሰዉነቷን ክንዶቼ ላይ ጣለችዉ። ኢክሩን አንገቷን ደግፌ ከንፈሯ ዉስጥ ጠፋሁ። እየሳምኳት አያታለሁ። ደስ ትላለች። እምነቷን እኔ ላይ ጥላ፣ አይኖቿን ጨፍና ፣ሰዉነቷን ክንዶቼ ላይ አደላድላ ሌላ አለም ዉስጥ ገብታለች።

"ከንፈር መሳም የረጠበ ስፖንጅ እንደመምጠጥ ነዉ።" ብሎ ኡስማን የነገረኝ ትዝ አለኝ። እዉነቱን ነዉ።
.
ስሜታችን ሲግል መሳሳሙ መላላስ ሆነ። ከንፈሮቻችንን ዘለን ምላሳችንን መመጣጠጥ ጀመርን። በስሜት አበድን!
ለረዥም ሰዓት ከተሳሳምን በኋላ ሁለታችንም በቃን እና አቆምን።

ካለንበት ስሜት ለመዉጣት ትንሽ ቁጭ ብለን ራሳችንን አረጋጋን።
ተነስተን ከነበርንበት ቦታ መዉጣት እንደጀመርን ኢክሩ እየሳቀች "አሁን አንተ አሚራቸዉ ነህ?"አለችኝ። በሰዓቱ አንድ አቋቁመነዉ የነበረ ሀይማኖታዊ ህብረት አሚር(ሰብሳቢ) ነበርኩ።

ይሄን የሚያክል ህብረት ላይ እየተሳተፍኩ ከንፈሯ ስር ስሜት ትንፋሼን ሲቆራርጠዉ ስታይ ቀለልኩባት። እንኳን እኛ ንጉሶቹም ለሚስቶቻቸዉ ቀልለዋል ብዬ አለፍኩት።
ኢክሩን ቀረብ ብዬ ሳያት ከንፈሯ አብጧል። ይህቺ ልጅ እዉነትም የመጀመሪያዋ ነዉ። እንዴት የእኔ ከንፈር አላበጠም? ጉንጭ መሳም አበዛ ስለነበር ይሆናል።(ሀሀሀ)

በጣም የሚገርማችሁ ነገር አሁን ከተሳሳምን በኋላ እንኳ ሸኝቼያት ስንለያይ አልተጨባበጥንም ፣ አልተቃቀፍንም። በቃ ለምዶብናል መጨባበጡ ግዙፍ ወንጀል ሆኗል። መሳሳሙ ያን ያህል አላስጨነቀንም። አሁን ላይ ሳስበዉ ያስቀኛል።

አንዳንድ ሰዎችን ካስተዋላችሁ ዉዱዕ አለኝ አልጨብጥሽም ባይሆን ጉንጬን ሳሚኝ ይላሉ እጃቸዉን ወደ ኋላ አጣምረዉ። ፊቴን አልታጠብም ባይሆን ዋና ልዋኝ እንደማለት ነዉ።
.
ለማንም ከኢክሩ ጋር ያደረግኩትን ነገር አልተናገርኩም። ኢክሩዬን አከብራታለሁ። ማንም ስለሷ አንስቶ እንደሌላዉ ሴት እንዲዘበዝብ አልፈቅድም።

እኔ ስለማከብራት ጓደኞቼ ዘንድም የተከበረች ነበረች።ሁለተኛዉ ምክንያቴ ደግሞ መሳሳማችን ሃጢያት ከመሆኑ ጋር አላህን ከወንጀሉ በላይ ወንጀሉ መወራቱ ስለሚያስቆጣዉ ነዉ።
በነጋታዉ ደዉዬ ስጠይቃት አሁንም የከንፈሯ እብጠት እንዳልጠፋ ነገረችኝ።ገርሞኛል።

በነጋታዉ ተገናኘን ከትምህርት ቤት በቀጥታ ነበር ወደምንገናኝበት ቦታ የመጣችዉ። ምናልባት የትናንቱን ትዕይንት እንደምንደግመዉ ሳታስብ አትቀርም። እኔ ግን ኢክሩዬን ለስሜቴ እንደምፈልጋት ብቻ እንድታስብ ስላልፈለግኩ እንኳን መሳሳም መጎሻሸሙንም ተዉኩት። ያመጣሁላትን ቾኮሌት በእጇ ሰጠኋት። እስኪበቃን አዉርተን ተለያየን።
.
በሶስተኛዉ ቀን ስንገናኝ ልስማት ሞከርኩ። ኢክሩ እንዲቀርብን ጠየቀችኝ። በጣም ተሰማኝ። ኢክሩን የማትፈልገዉ ነገር ዉስጥ እንደዘፈቅኳት አሰብኩ። ኢክሩን ስለምትወደኝ ከሀይማኖቷ ህግጋት ጋር እያጋጨኋት እንደሆነ ነበር የማስበዉ። ፊቴ ሲቀያየር ኢክሩ ፀፀቴ አመማት።ለማለት የፈለገችዉ እንደዛ እንዳልሆነ እንድረዳት "ሁሌ ጥፉቶችን ወደራስህ ማስጠጋት ትወዳለህ።" አለችና አንገቴን ስባ ከንፈሬ ላይ ተለጠፈች። ቀለጥን። ሳናስበዉ በጣም ለረዥም ሰዓት ተሳሳምን።
.
ረሂማ ልታሞቀዉ ወስዳዉ የነበረዉን ወተት ይዛልኝ መጣች።
"በጣም ቆየሁ ይቅርታ ሳፊዉ!!" አለችኝ።
ከሀሳቤ ለመዉጣት እየታገልኩ "ችግር የለዉም ኮካዬ!" አልኳት። ወተቱን ረስቼዉ ነበር።አሁን ቅድም ካፌዉ ዉስጥ ከፊት ለፊቴ ተቀምጠዉ የነበሩት ጥንዶች የሉም። ሌሎች ጥንዶች ቦታዉ ላይ ተተክተዋል። አዲሶቹን ጥንዶች እያየሁ ወደ ሀሳቤ ባህር ተመለስኩ።
.
ከኢክሩ ጋር ግንኙነታችን በዚህ መልኩ እየቀጠለ ባለበት ሰዓት ዩኒቨርሲቲ ተጠራሁ።

እዚሁ አዲስ አበባ ስለደረሰኝ ብዙም ከኢክሩ ጋር ክፍተት አልፈጠርንም። እንደሁሌዉ እንገናኛለን።
ብሩኬ ወደ ካምፓስ ሄደ።በነገራችን ላይ ሄኖክ የግል ኮሌጅ አካዉንቲንግ ተመዝግቧል። ብሩክ አርባምንጭ ከሄደ በኋላ ቢያንስ በሳምንት አንድ ጊዜ እደዉልለታለሁ። እሱ ግን ሳይረሳኝ አይቀርም። ሁለ ነገሩ ተቀያይሯል። ከጥሩ ልጆች ጋር አልገጠመም።

የካምፓስ ላይፍ የሚባሉት እንደ ክለብ መዉጣት መቃም ምናምን አታለዉታል። ብሩክ እምቢ የማለት አቅም የለዉም። ከሰዉ ጋር ተመሳስሎ ነዉ የሚኖረዉ።
እኔ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አብረን ከተመደብን የሸገር ልጆች ጋር ጊዜዬን አሳልፋለሁ።

ከክፍለሀገር ልጆች ጋር ግን በፍፁም መግባባት አልቻልኩም። ብዙዎቹ እንደጠላት ነዉ የሚያዩኝ። ግን ብዙም ግድ አልሰጠኝም። ኢክሩ አሁን የመሰናዶ ተማሪ ሆናለች። ኢክራምን በትምህርት ደረጃ ልብለጣት እንጂ እድሜያችን እኩል ነዉ ማለት ይቻላል።በወራት ነዉ የምበልጣት!!

ዩኒቨርሲቲን ተላምደነዉ እኔም ስነ አእምሮ(Psycology) ደርሶኝ በፍቅር እየተማርኩት ትንሽ እንደቆየሁ ብሩኬ ወደ ሸገር ተመለሰ።ሀገሩ አልተስማማኝም አልቀጥልም አለ። እኔ የእዉነት ደስ አለኝ። በጣም ናፍቆኝ ነበር። እዚሁ ቆይቶ ቀጣይ ዓመት የግል ኮሌጅ ለመማር ነዉ ያሰበዉ። ከሪም ጋርም በአካል ለመገናኘት በቁ!! ግን ...

                 ይቀጥላል...

ይሀው እኔም ቶሎ ለቀቁኝ አይደል እናተ ደሞ ላይክ 
#SHARE አርጉ፡፡
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
#ከምርጥ_መጽሐፍቶች

“ማንም ሰው በመስጠት ደሀ አይሆንም፡፡”
"ያም ሆነ ይህ ሰዎች ከስር መሰረታቸው መልካሞች ናቸው፡፡ "
     
#ከአና_ፍራንክ መጽሐፍ የተወሰደ

“አንዳንድ ሰዎች የሰዎችን ከባድ ችግር መቅረፍ ቢችሉም በእነሱ ጥቂት ችግር ይወድቃሉ፡፡”
"በህይወትህ ትልቁ ጠላትህ ውስጥህ ያለው መጥፎ ሀሳብ ነው ስለዚህ መጀመሪያ እሱን ታግለህ አሸንፍ ከዛ ሌላው ቀላል ነው!"
''ለሰዉ የከበደዉ የወደቀን ማንሳት እንጅ የቆመን በርታ ማለት አይደለም፡፡''
            
#ከውብ መጽሐፍ የተወሰደ

“ሞት ሆይ ....ና እስቲ እቀፈኝ ፤ ድብን አድርገህ እቀፈኝ ወደ ሰማየ ሰማያት እንምጠቅ።”
           
#ከየጭን_ቁስል መጽሐፍ የተወሰደ

“ቀን ጎድሎብህ ሁሉንም ብታጣ፣ሁሉም ቢከዳህ፣ ሁሉን ነገር እንደ ነበረ መመለስ የሚያስችልህ አንድ ነገር ብቻ አለ፣ በራስ ልቦና ዉስጥ የምትፈጥረዉ የአይበገሬነት እልህ።”
           
#ከያልታበሱ_እንባዎች" መጽሐፍ የተወሰደ
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
የአና ማስታወሻ - በአዶኒስ.pdf
13.9 MB
የጭንቁስል
:
ለካ ሁለት ቃላት የሠውንልጅ ህይወት የመከራ ቋት ውስጥ መክተት ይችላሉና።ለካ ሁለት ቃላት ብቻ ማንነትን እልም ያለ ውልአልባ ቀውስውስጥ ለመጨመር ብቃቱ አላቸውና።
ሠማይናምድሩ ዞረብኝ ያለችኝን ሁለት ቃላት ደግሜ ሣስታውሳቸው ውስጤ መቃጠል ይጀምራል።እና በምድር ላይ እንደ ሣር የበቀልኩ ብቸኛ የሠውፍጡር የሆንኩ ያህል ይሠማኛል። " እናትሽ አይደለሁም " ነበር ያለችኝ።

"የጭን ቁስል"መፃሐፍ ገፅ 55
በጉጉት ጀምሮ በጉጉት የሚያልቅ መፅሐፍ  ነው።

👇   የአና  ማስታወሻ   👇
.............    በስጋ ከሞትኩ ቦኃላ እንኳን በመንፈስ መኖር እፈልጋለሁ ስሜ አብሮኝ እንዲቀበር አልፈልግም ሥለዚህም ለዚህ ተስጥኦ ያደለኝን እግዚሀብሄርን አመሰግናለሁ
ራሴን በራሴ ማሳደግ እንድችል ስለማንኛውም ነገር ጥሩ አድርጌ መፃፍ እንድችል በውስጤ ያለውን ሁሉ ያለምንም ችግር መግለፅ እንድችል አድርጎ የፈጠረኝ አምላኬን ከልብ አመሰግነዋለሁ
---=--- ገጽ 199 ቀረበ በቢኒ ቡክ


ውድ አንባቢያን"ያልታበሱ ዕንባዎች"መፅሀፍ ሳነብ ደስ ያለችኝን ሀሳብ ላካፍላችሁ።
     "በአንድ ሀገር ውስጥ ያሉ ህዝቦችና መንግስት ከተኮራረፍ ምድርና ሰማይዋም ይቀያየማሉ።ያኔ ከዜጎቿ ልብ ውስጥ ተስፋ ይጠፋል።ተስፋ የሌለው ህዝብ ጭካኔ ይወልዳል።በተለይ ድሀ ሲጨክን ጠላት የሚያደርገው የገዛ ሀገሩን ነው።አምባገነኖች የቱንም ያህል ጡንቻቸው ቢፈረጥም ድሀን ማስተዳደርና መቆጣጠር አይችሉም።እንዲያውም በቁጣው እነሱንም ያጠፋቸዋል።ያኔ ገዢና ተገዥ አይኖርምና ጥፍት ይነግሳል።"ገፅ 203
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
#የጭን_ቁስል


ሕጻናት ዐምባ ውስጥ ያደገችው እንስት ማን እንደሆነችና ከየት እንደተገኘች አታውቅም፡፡ ዐምባው ወደ ሌላ ተቋም ሲቀየር ህይወቷ አደጋ ላይ ወደቀ…

እናም በገጠማት እጅግ መራርና አንገሽጋሽ የሕይወት ትግል እግዚአብሔርን የምታስፈራራ፣ ሞት ታግሎ ታግሎ ሊጥላት ያልቻለች ነፍስ ሆና የሁላችንንም ጓዳ እያስፈተሸች ማንም ትንፍሽ ሊል የማይደፍረውን ገመና ገላልጣ ታሳየናለች…

                              ***
#ለደራሲው_ሥራ_ከተሰጡ_አስተያየቶች

ታሪኩ አጓጊ ነው፡፡ በእያንዳንዱ ምእራፍ ወይም ክፍል የሚተረኩት ታሪኮች ስሜት ይዘው የሚነጉዱ ናቸው፡፡ ልብ ያንጠለጥላሉ፡፡ ቀጥሎስ? ከዚያ በኋላስ? መጨረሻውስ እያልን ነው የምናነበው፡፡                                   
#አዲስ_አድማስ_ጋዜጣ

በመጽሐፉ የተካተቱት… ታሪኩን ለማንበብ ይረዳሉ፤ የጸሐፊውንም ብቃት ይመሰክራሉ                                         
#ኔሽን_ጋዜጣ

አገላለጹ ነገር ታኮ፣ ጨዋታን ተመርኩዞ ነው፡፡ አዋዝቶ ያወጋል፡፡ ከገጽ ገጽ ልብ እያንጠለጠለ ይህች ሴት ምን ልትሆን ነው? እያስባለ ያስጉዛል፡፡                                     
#ምኒሊክ_ጋዜጣ

መጽሐፉ በሚመስጥ መልኩ ተጀምሮ፣ በሚመስጥ መልኩ የሚያልቅ ነው፡፡                                         
#ኤፍ_ኤም_97.1
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
8ቱ የሉቅማን ምርጥ አባባሎች
* ሁለት ነገሮችን አስታውስ ሁለት ነገሮችን እርሳ፦
1, ፈጣሪህን እና ሞትን አስታውስ
2, ለሰዎች ያደረግከውን በጎ ነገር እና ሰዎች ባንተ ላይ ያደረሱትን መጥፎ ነገር እርሳ
* ሰዎች በንግግራቸው ሲኮሩ አንተ በዝምታህ ኩራ።
* በፀሎትህ ውስጥ ልብህን ጠብቅ።
* ሰው ቤት ውስጥ አይንህን ጠብቅ።
* ምግብ ስትበላ ጉሮሮህን ጠብቅ።
* ከሰዎች መሀከል ምላስህን ጠብቅ።
* አራት ነገሮች የእውቀት ተማሪዎችን ያሳፍራሉ:- ሰዎችን መተቸት፣ እራሳቸውን ማሞገስ፣ እውቀትን አለማስተማር እና የሚያውቁትን አለመተግበር።
* ነገ ምን እንደምታገኝ አታውቅም።

ማጋራት መተሳሰብ ነው!
@ethioleboled
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
💥📚ኢትዮ-ልቦለድ📚📖💥
Photo
.              ♥️●●●ነጠብጣብ●●●♥️

           
  
#ክፍል_14
.
ዩኒቨርሲቲን ተላምደነዉ እኔም ስነ አእምሮ(Psycology) ደርሶኝ በፍቅር እየተማርኩት ትንሽ እንደቆየሁ ብሩኬ ወደ ሸገር ተመለሰ።

ሀገሩ አልተስማማኝም አልቀጥልም አለ። እኔ የእዉነት ደስ አለኝ። በጣም ናፍቆኝ ነበር። እዚሁ ቆይቶ ቀጣይ ዓመት የግል ኮሌጅ ለመማር ነዉ ያሰበዉ። ከሪም ጋርም በአካል ለመገናኘት በቁ!! ግን በመካከላቸዉ ትንሽ ክፍተት ተፈጥሯል።
ከአርባምንጭ ከተመለሰ በኋላ ብሩክ በፍፁም የማዉቀዉ ብሩክ ሊሆንልኝ አልቻለም። ፀባዩ ተቀያይሯ ል።

ለሱ እርድና ማለት ክለብ መዉጣት እና ሴት ማዉጣት ሆኗል። በተግባር አያደርገዉም በምላሱ ግን ሁሌም የሚያወራዉ እሱኑ ነዉ።
እኔ የኢክራምን እና የእኔን ግንኙነት በተመለከተ ትልቅ ዉሳኔ ለመወሰን እያዉጠነጠንኩ ነዉ።...

🖊ካምፓስ ገብቼ ሁለተኛዉ የትምህርት ዘመን አጋማሽ ተጀምሯል። ብሩኬ ጊዜዉን ፊልም በማየት ያሳልፋል። እኔ የላላዉን ሀይማኖቴ ላይ የነበረኝን አቋም ለማስተካከል እየሞከርኩ ነዉ። ከኢክሩ ጋር ከሁለቱ ቀናት በኋላ ድጋሚ ተሳስመን አናዉቅም። አንነካካም!! እናወራለን!! ስለ ጋብቻ እናልምና እንለያያለን!! አለቀ።
ቀኑ ሀሙስ ነበር። ከ6ኪሎ ካምፓስ ታክሲ ይዤ ወደ ፒያሳ ሄድኩ።

ወደ መስጂደ ኑር!! ይሄ መስጂድ በተለምዶ በኒ መስጂድ ይባላል። መስጂዱ ዉስጥ ገብቼ ከመድረኩ የሚሰጠዉን ትምህርት መከታተል ጀመርኩ። የመስጂዱ ግርማ ሞገስ የሆኑት ሸህ ኡመር ኢድሪስ የቁርዓንን ትርጉም ይተነትናሉ። ከቁርዓኑ እየተተነተነ የነበረዉ አንቀፅ የዩሱፍ(ዮሴፍ) ምዕራፍ ነበር። ይህ ምዕራፍ የዩሱፍን ታሪክ በሰፊዉ ይተርካል።

ዩሱፍ በወንድሞቹ የዉሀ ጉድጓድ ዉስጥ ከተጣለ በኋላ ነጋዴዎች አግኝተዉት ለአንድ የምስር(ግብፅ) ባለስልጣን ይሸጡታል። ይህ የገዛዉም ሰዉ ዩሱፍን ለሚስቱ በስጦታ መልክ ያበረክትላታል። ዩሱፍ በጣም ቆንጆ ከመሆኑ የተነሳ የባለስልጣኑ ሚስት ለነፍሷ ትመኘዋለች። ከዚህ ዉብ ፍጥረት ጋር አለሟን መቅጨት ያምራታል። ዩሱፍንም በሮቿን ሁሉ ዘጋግታ ለሱ እንደተዘጋጀችለት እና አብሯት የስጋ ጥሙን እንዲያረካ ትጋብዘዋለች። ዩሱፍ ግን ጥሪዉን ገፍቶ አልቀበልም ይላል። የባለስልጣኑ ሚስት እልህ ግን ዩሱፍን ከእርሷ ጋር ከመተኛት አሊያም ከመታሰር የሚያስመርጥበት ደረጃ ላይ ይደርሳል።
.
ሸይኹም(መምህሩም) ትኩረት ሰጥተዉ እየተነተኑት ያለዉ ቦታ ይሄ ነዉ። ዩሱፍ ከመታሰር እና ጌታዉን ከማመፅ ምርጫ ሲቀርብለት የተናገረዉን ንግግር ሸይኹ እንዲህ ሲሉ ተናገሩ

"ዩሱፍ ሴቲቱ የዚህ አይነት አጣብቂኝ ዉስጥ ስትከታቸዉ እንዲህ ብለዉ ጌታቸዉን ለመኑ 'ጌታዬ ሆይ በርሱ ከሚጠሩኝ ነገር (ከዝሙት) ይልቅ መታሰር ለኔ የተወደደ ነዉ። ተንኮላቸዉንም ከኔ ላይ ባትመልስልኝ ወደነሱ እዘነበላለሁ ፣ ከስህተተኞችም እሆናለሁ።' አለ። አላህም ፀሎቱን ተቀበለዉና ታሰረ።"
ከዚህ በላይ ማዳመጡ ከበደኝ

ከኢክራም ጋር ያሳለፍኳቸዉ ሁለቱ ቀናት ትዝ አሉኝ።በጋብቻ ያልተሳሰርኳትን ኢክራምን ከንፈር የሳምኩባቸዉ ፣ የተከለከልኩትን የአካሏን ክፍሎች የነካሁባቸዉ ሁለት ቀናት!!
እኔ ጌታዬን ለማመፅ እቅድ አዉጥቼ ተገበርኩ። ዩሱፍ ግን ማንም ሰዉ በሌለበት ሊያዉም ከባለስልጣን ሚስት የደረሰዉን የእንተኛ ጥያቄ ገፋዉ ፤ ጌታዉንም ላለማመፅ ሲል ታሰረ።
ዛሬ ሁሉም ነገር ግልፅ ሆኖ ይታየኝ ጀመር።

እኔ አሁን ገና የካምፓስ ተማሪ ነኝ። ኢክራምን ለማግባት የቁስም ሆነ የስነ ልቦና ዝግጅቱ የለኝም። የኢክራምን ዉድ የወጣትነት እድሜ እያባከንኩባት ነዉ፤ ጌታዬንም እያስቆጣሁት ነዉ። መጃጃሉ ይበቃል! ከኢክሩ ጋር እዉነቷን ተነጋግሮ መለያየት ይሻላል!! ግን የዛን ቀን ለራሴ አንድ ቃል ገባሁ። እኔ የስነ ልቦናም ሆነ የቁስ ዝግጅቴ ለጋብቻ ብቁ ሲሆን የፈለጉ አመታት ቢነጉዱ እንኳ ኢክራምን ፈልጌ ካላገባች እሷኑ ላገባ። አዎ በፍቅር የሰከርኩላትን ፣ ከማንም በላይ የማዝንላትን ኢኩዬን ለማግባት!!
.
ከስድስት ኪሎ ወደ ፒያሳ ተሳፍሬ ሄጄ የሰማሁት ነገር አቋሜን ለዉጦት ወደ ስድስት ኪሎ ተመለስኩ።
አሁን ለኢክራም እንዴት ማስረዳት እንደምችል አሰብኩ።

መጀመሪያ እኔ ከሷ ጋር ግንኙነቴን ለማቆም ምክንያት የሆኑኙን ሁለት ነገሮችን አሰብኩ። ጌታዬን እያስቆጣሁ መሆኑና ኢክሩ ከእኔ ጋር በመሆኗ ምክንያት አለማግባቷ ናቸዉ።

ከኔ ጋር ፍቅር የሚሉትን እቃቃ ባትጀምር ኖሮ የማግባት እድሏ ሰፊ ነበር። የሷ ማግባት ደግሞ ለቤተሰቦቿም ጥቅም አለዉ።
ኢክራምን በምክንያት ለማስረዳት ከሞከርኩ እኔዉ ራሴ ከዚህ በፊት ባስጠናኋት የቃላት ድርደራዎች ልትረታኝ ትችላለች። ስለዚህ አዲስ ስልት መጠቀም ነበረብኝ። ኢክራምን እንድትጠላኝ ቢያደርጋትም እንኳ ግንኙነታችንን ለማቋረጥ እንደሚረዳ አሰብኩ። አዎን ዉጤታማ መንገድ አቀድኩ!! ለበጎዉም ለመጥፎዉም የማቀድ በሽታ አለብኝ።
.
ኢክሩ ፌስቡክ ላይ ስትፅፍልኝም እንደድሮዉ ትኩረት ሰጥቼ አላወራት አልኩ። የሳምንቱ የትምህርት የመጨረሻ ቀን ጁምዓ (አርብ) ሲደርስ ከስድስት ኪሎ ዶርም ወደ ሰፈር ተመለስኩ። በነገራችን ላይ ከዶርም ወደ ቤት የምመለስበት ዋነኛዉ ምክንያት ቤተሰቦቼ ናፍቀዉኝ ሳይሆን ኢክራምን ለማግኘት ነበር።

እሷ ሰሞኑን ብዙም በስልክም ስላልተገናኘን ናፍቄያት ነበር። ደዉላ የምንገናኝበትን ሰዓት ጠየቀችኝ ፤ነገርኳት።

አሁን ልቤ ለአንድ አመት ያክል አብሬያት የነበረችዉን ልጅ ይብቃን ለማለት ያለዉን ጥንካሬ ሁሉ እየሰበሰበ ነዉ። በቃ ከእዉነታዉ ጋር መጋፈጥ አለብኝ!!
.
ሰዓቱ ሲደርስ ከኢክሩ ጋር ወደኛ ሰፈር የሚያስገባዉ መንገድ ጋር ተገናኘን። ኢክሩ ዛሬ ጅልባብ ለብሳ ነዉ የመጣችዉ። ጅልባብ ማለት ሙስሊም ሴቶች የሚለብሱት ፊትንና እጅን ብቻ የሚያሳይ ልብስ ነዉ።

የሰዉነታቸዉን ቅርፅ በፍፁም አያሳይም። ሰፊ ነዉ። ኢክሩን በጅልባብ ሳያት ደስ አለኝ። በጅልባብ ደግሞ በጣም ነዉ የምታምረዉ። ይሄ ፈገግታ ፣ ይሄ ዉበት ላይ ነዉ ጨክኜ ፣ ከፈገግታዋናዉበቷ ዘላቂ ደስታዋን እና የጌታዬን ክብር መርጬ በቃን ልላት የወሰንኩት።
ልክ አጠገቤ እንደደረሰች እንደተለመደዉ ከአጠገቤ ቆማ "አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላህ" አለችኝ። የአላህ ሰላምና እዝነት ባንተ ላይ ይሁን ማለት ነዉ።
"ወአለይኩሙሰላም ወራህመቱላህ" አልኳት።

ባንቺም ላይ የአላህ ሰላም እና እዝነት ይሁን ማለት ነዉ።
.
ሰላም ተባብለን ከጨረስን በኋላ ወዲያዉ እዛዉ እንደቆምን ወደገደለዉ ለመግባት ፈለግኩ።
ፊቴን አጨፈገግኩ እና ትንፋሼን ዉጬ "ኢክሩዬ ለረዥም ጊዜ አብረን ቆይተናል ግን ግንኙነታችን ወዳልሆነ መስመር እየወሰደን ነዉ። ባለፈዉ ያደረግነዉን ታስታዉሻለሽ አይደል?(መሳሳሙን ማለቴ ነበር) በዚህ ከቀጠልን ሌሎች ነገሮች ላይም ልንወድቅ እንችላለን። ስለዚህ ከዚህ በኋላ ለዝሙት ካልሆነ በቀር ወደ እኔ አትምጪ!!" አልኳት።
ኢክሩ ፊቷ ተቀያየረ ፣ አይኗ በእንባ ተሞላ ፣ ወዲያዉ በዉሸት ፈገግታዋ እንባዋን ለማጨንገፍ ሞከረች።

"ኢክሩ መናገር የምትፈልጊዉ ነገር አለ?" አልኳት። ልቤ በጣም ይመታል።
ትንሽ አየችኝና በአሉታ አንገቷን ነቀነቀችልኝ። በቆመችበት ትቻት ሄድኩ!!
ንግግሬ በራሴ ጆሮ ላይ እየደጋገመ ያስተጋባል። "ለዝሙት ካልሆነ በቀር ወደ እኔ አትምጪ" የኢክራምን እኔን ለመመለስ የሚያስችሉ ሙከራዎች ሁሉ ለመክሸፍ የተጠቀምኳት ቃል ነበረች።
.

ነጠብጣብ ትረካ ሊያልቅ ጥቂት ክፍል ብቻ ይቀራል ከወደዱት Like share
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
💥📚ኢትዮ-ልቦለድ📚📖💥
Photo
♥️●●●ነጠብጣብ●●●♥️

   
#ክፍል_15


"ኢክሩ መናገር የምትፈልጊዉ ነገር አለ?" አልኳት። ልቤ በጣም ይመታል።
ትንሽ አየችኝና በአሉታ አንገቷን ነቀነቀችልኝ።

በቆመችበት ትቻት ሄድኩ!!
ንግግሬ በራሴ ጆሮ ላይ እየደጋገመ ያስተጋባል።"ለዝሙት ካልሆነ በቀር ወደ እኔ አትምጪ" የኢክራምን እኔን ለመመለስ የሚያስችሉ ሙከራዎች ሁሉ ለመክሸፍ የተጠቀምኳት ቃል ነበረች።

እኔ ከኢክራም ጋር ስለያይ ምንም እንኳ ከዚህ በፊት አብረን የነበርን እንደመሆናችን መልካም የሆነ ወንድማዊ ግንኙነት እንዲኖረን እናድርግ ማለቴ እንጂ በደረስኩበት አትድረሺ ማለቴ አልነበረም።

ኢክሩ ዉሳኔዬን ማክበሯን ፌስቡክ ላይ አንፍሬንድ ከማድረግ ጀመረችዉ።
መንገድ ላይ ስታገኘኝ ባላየ ማለፍ ወይም ለሰላምታ ከብሩክ ጋር ስሆን ብሩክን ብቻ ጠርታ ሰላም ማለት ጀመረች።
ነገሩ ምንም አልጥምህ ስላለኝ አግኝቼ ላናግራት ወሰንኩ።ኢክሩ በጣም ልቧ ተሰብሯል ፤አዝናብኛለች።

ልትረዳዉ ያልቻለችዉ ትልቅ ሀቅ አለ።እኔ ዛሬ ማንንም አይቼ አይደለም ይብቃን ያልኳት።ግን እዉነቱን መቀበል ነበረብን። እዉነቱ ደግሞ ድርጊታችን ጌታችንን የሚያስቆጣ ከመሆኑም ጋር የኢክሩን እምቡጥ እድሜ የሚያባክን ነበር።ግን ከማንም በላይ የምወዳት ሴት እሷ ነበረች።

ኢክራምን አግኝቼ በመካከላችን ያለዉ ግንኙነት የጠላት እየመሰለ እንደሆነ እና እንድናስ ተካክለዉ ነገርኳት።
ኢክሩ በሂደት በመካከላችን ያለዉ ግንኙነት ሰላማዊ እንዲሆን የበኩሏን አደረገች።

ሀሙስ ቀን ላይ ኢክሩ ስልክ ደወለችልኝ።
"ወዬ ኢክሩ" አልኳት መደወሏ ገርሞኝ
"ፈዊ ላገኝህ እፈልጋለሁ የማማክርህ ጉዳይ አለኝ።"አለችኝ።
በሰዓቱ ስድስት ኪሎ ካምፓስ ነበርኩ። ከፈለግኩ መምጣት እንደምትችል ነገረችኝ።
በጣም ግራ ስለተጋባሁ ወደ ሰፈር ስመለስ ለመገናኘት ተቀጣጠርን።

ከራሴ ጋር ከባድ ትግል ዉስጥ ነኝ። ኢክሩ ለምን ፈለገችኝ?ግራ ያጋባል።...

🖊ወደ ሰፈር ከመመለሴ በፊት አንድ የማላዉቀዉ ስልክ ተደወለልኝ።
"አቤት!!"አልኩ ስልኩን አንስቼ!!አንዲት ሴት እንደ ሙዚቃ በሚሰረቀረቅ ዉብ ድምፅ"ፈዉዛን ነህ አይደል?"አለችኝ።
ድምፁ አዲስ ስለሆነብኝ ግራ እየተጋባሁ "አዎ ነኝ ምን ልታዘዝ?"አልኩ።
ልጅቷ ኢክራም የምትመራዉ ሀይማኖታዊ ማህበር ዉስጥ የስነ ፅሁፍ ዘርፍ ላይ እንደምትሰራ እና መፅሔት ለማዘጋጀት እየሞከሩ ስለሆነ እንዳግዛቸዉ ዘፈነችልኝ።(የልጅቷ ድምፅ ከመስረቅረቁ የተነሳ ተናገረች ማለት ስለሚከብደኝ ነዉ ዘፈነችልኝ ያልኩት)
እኔም ወደ ሰፈር ስመለስ ላገኛቸዉ ለጁምዓ(አርብ) ተቀጣጠርን።

ጁምዓ(አርብ) ዕለት ከደወለችልኝ ልጅ ጋር ሰፈር መስጂድ ዉስጥ በመካከላችን መጋረጃ ተጋርዶ በአካል አወራን። አልተያየንም!! አብረዋት ሁለት ልጆች ነበሩ። ወንድና ሴት ዉይይት ሲያስፈልግ ሁሌም እንዲህ ነዉ የሚደረገዉ መጋረጃ ተጋርዶ እንወያያለን።

ይሄ የሚደረገዉ ሀራም(ክልክል) ፆታዊ መፈላለጎችን ለመታደግ ነዉ።
ልጅቷ ስሟ ሱመያ ነዉ።ድምጿ በጣም ያምራል። በምችለዉ ሁሉ ላግዛት እና ስለስራዉ በስልክ እየተደዋወልን ለመነጋገር ተስማምተን ተለያየን።
ሱመያ ገና ከዛዉ ቀን ጀምሮ ፌስቡክ ላይ ስለብዙ ነገሮች ታማክረኝ ጀመር።ምናለ ታይፕ ተደርገዉ የተላኩ ሚሴጆችን በፀሀፊዉ ድምፅ የሚያነብ ማሽን በኖረ!

የሱመያን መልዕክቶች በሷ ድምፅ እሰማበት ነበር።የፈጣሪ ያለህ የሰዉ ድምፅ እንዲህ ይስረቀረቃል?የሷ በጣም ይለያል።
.
በነጋታዉ ቅዳሜ ኢክሩ ደዉላ የምንገናኝበትን ሰዓት ተነጋገርን።ሰዓቱ ሲደርስ መንገድ ላይ ተገናኝተን ወደዚህ ካፌ መጣን። ኢክሩ ጥቁር ሰማያዊ ጅልባብ ለብሳለች።ረሂማ መጥታ ከታዘዘችን በኋላ ኢክሩ አይኔን ትኩር ብላ እያየችኝ "ፈዉዛኔ ግን ምንም የአቋም ፅናት የለህም።"አለችኝ።

እዉነቷን ነዉ አንድ ነገር ላይ ለረዥም ጊዜ በፅናት መቆም ይከብደኛል። አሁንም ከሷ ጋር በፍቅር ግንኙነት ዉስጥ ለመቆየት ከጌታዬ ጋር የምጋፋበት ፅናት አጥቻለሁ።
እየሳቅኩ "ኢክሩ ልክ ነሽ" አልኳት።
አሁን ከኢክራም እየተረዳሁ ያለሁት ግን ከዚህ ቀደም በመካከላችን ያለዉን ግንኙነት የጠላት አናስመስለዉ ማለቴን እንደገና ወደፍቅር ህይወት እንመለስ ለማለት እንዳሰብኩ አድርጋ ነዉ የተረጎመችዉ።

በፍቅር አብረዉት ከነበሩት ልጅ ጋር ወንድም ሆኖ መቀጠል ይከብዳል። ሱመያ እኔን ወንድም ብሎ መቀበል ከብዷታል። እንዴት አይክበዳት? ስንቱን አብረን አሳልፈናል እኮ!! ትዳር ተወድዶ ጉድ አደረገን። ማህበረሰባችን የትዳርን ዋጋ አስወድዶ የዝሙትን ዋጋ አርክሶንብን ተቸገርን!!

ወሬ ለመቀየር ያህል"ሱመያ የምትባል ልጅ ከናንተ ጀመዓ(ህብረት) አናግራኝ ነበር።"አልኳት።
እየሳቀች "እኔ ነኝ እንዲያናግሩህ የጠቆምኳቸዉ!!" አለችኝ።
እኔም ሳቋ ተጋባብኝ!!ከዛ ደግሞ አሳዘነችኝ።
ኢክሩ ነገረ ስራዋ ሁሉ ግራ ያጋባል።
.
ኢኩ ለሷ ጥላቻ እንዳለኝ መጠርጠር ሳትጀምር አትቀርም።በስልክ ስናወራ እየጮህክብኝ ነዉ ፣ተቆጣኸኝ ምናምን የሚሉ ሰበቦችን እየፈለገች ታኮርፋለች። የሚንቃትን ፈዉዛንን እና ኩርፊያዉን እራሷ በጠርጣሪዉ ጭንቅላቷ ትፈበርካለች። እኔ እንዴት ኢክሩን እጠላታለሁ?የማይመስል ነዉ።
የዛን ቀን ጉዳያችንን እንደጨረስን ወደ ቤቷ ሸኝቼያት ተመለስኩ። ከዚህ ቀን በኋላ ከኢክራም ጋር በስልክም በአካልም ያለን ግንኙነት እየቀዘቀዘ መጣ።

እኔ ፍቅረኛ የሚባለዉን ታፔላ ብታነሳልኝ ከጎኗ ሆኜ እንደወንድም ላማክራት ፈቃደኛ ነበርኩ። እሷ ግን የፈለገች አይመስለኝም።

ከነሱመያ ጋር በቀጣይ ልንገናኝ ስንቀጣጠር ከመስጂድ ዉጪ ስለነበር ከብሩክ ጋር አብረን ሄድን። አንድ ሙሉ የቆንጆ ቡድን ከተቀጣጠርንበት ህንፃ ስር ቆሞ ጠበቀን። አራት ነበሩ።ሱመያ የትኛዋ እንደሆነች አላዉቅም። ወደኔ ቀረብ ሲሉ አንደኛዋ ቀደም እያለች ስትመራቸዉ እሷ መሆኗን ገመትኩ። ከአራቱ ዉስጥ አንደኛዋ በጣም ነበር የምታምረዉ!!በጣም!! ሲጀመር ሁሉም ቆንጆ ነበሩ።

ሱመያ እንደሆነች የገመትኳት ልጅ ፈገግ
ብላ አንድ ደብተር እየሰጠችኝ "ሁሉንም እዚህ ላይ ፅፈነዋል እየዉና አስተያየትህን ትሰጠናለህ!!" ብላ ሞዘቀች!! ሱመያ ነበረች። ድምጿ ሲስረቀረቅ ነበር የለየኋት።

ብሩኬ እኔ ከሱመያ ጋር ሳወራ እሱ አብራት ያለችዉን ቆንጅዬ ልጅ እየተመለከተ ተቁነጠነጠ። ደብተሩን ተቀብያቸዉ ገና ዞር እንዳሉ ብሩኬ ደብተሩን ቀምቶኝ ሮጠ።
ነገረ ስራዉ ሁሉ ስለገባኝ "ብሩኬ አይሆንም!!" እያልኩ ተከተልኩት። ደብተሩ ላይ ስልክ ቁጥሮችን ስላየ ነበር ነጥቆኝ የሮጠዉ።
ብሩኬ ስልክ ቁጥሩን ስልኩ ላይ ለመመዝገብ አስፓልት ተሻግሮ ሮጠ። ተከተልኩት። ረዥም መንገድ ተሯሯጥን። እኔ በሀይማኖት ጉዳይ ምክንያት ሴቶች የሰጡኝን የግል መረጃ አሳልፌ መስጠት አልፈልግም።

በሀይማኖት ጉዳይ ተገናኝቶ ፈጣሪን የሚያምፅ ነገር መፈብረክ ያስጠላል። አንዳንዶች ሀይማኖታዊ ህብረቶችን ሲቀላቀሉ ቁጥብ እና ቆንጆ የሆኑ ልጆችን ለማጥመድ ነዉ።ለነገሩ ሁሉም የሀሳቡን ያገኛል። ቆንጆ የፈለገዉ ቆንጆ ፣ የቆንጆዎች ካዝና ባለቤት የሆነዉን ፈጣሪዉን የፈለገ ደግሞ ፈጣሪዉን!! ለዛ ነዉ ከብሩኬ ጋር እንዲህ የተሯሯጥነዉ። አለማዊ ሽኩቻዉ ሰልችቷቸዉ መስጂድ የመጡትን ልጆች ወደማይፈልጉት ጉዳይ ዉስጥ እንዲገቡ መሳሪያ ላለመሆን!! ግን ብሩኬ ስልክ ቁጥሩ ያለበትን ገፅ ቀድዶ ወሰደዉ።

በኋላ ላይ ሳጣራ ብሩክ የሻፈደባት ልጅ ስም ኢማን ነበር። በኋላ ላይ ከኔ የወሰደዉ ስልክ ትክክለኛ አለመሆኑን ሲያዉቅ ኢክራምን እንድትሰጠዉ ለመናት።

ነጠብጣብ እኮ ሊያልቅ ነው አንብበው ከወደዱት Like Share
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
እቺ ሳምንት ደስ ትላለች ። የሆነ ድል በድል የመሆን ስሜት የታከከኝ ሳምንት ነች ። ስነቃ የማስበው ነገር ደስ ይላል ።

የማገኛቸው ሰዎች ደስ ይላሉ ። አበዳሪዎቼ ያበደሩኝን ገንዘብ ሳይረሱልኝ አይቀሩም ።ብድር ከፈለክ ጠይቀኝ እያሉ ነው ። አከራዬ እንዳትሰጋ የቤት ኪራይ አልጨምርብህም ሁሌ አብራቹ ከማያችሁ ቆንጆ ልጅ ጋ አብራቹ ኑሩ እያሉኝ ነው ።

ቆንጆ ክላሲክ መፅሃፎች ስጦታ ተሰጦቶኛል ። ሎተሪ እየቆረጥኩ ነዉ ። እምወዳቸውን ሰዎች እየደወልኩ እወዳችኃለሁ እያልኩ ነው ። ፈግግ ስል ነው የምዉለው ።
ሃዬ
መኖር ደስ ይላል
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
💥📚ኢትዮ-ልቦለድ📚📖💥
Photo
♥️●●●ነጠብጣብ●●●♥️

            💞እውነተኛ እና አስተማሪ ታሪክ💞

                         
#ክፍል_16

ኢክሩ እኔ ጋር አትደዉልም ግን ብሩኬ ጋር ትደዉላለች። እሱም ይደዉልላታል።
አንድ ቀን እነ ብሩኬ ቤት ሆነን ብሩኬ ኢኩን ችላ ሳይል እንዲያማክራት አደራ አልኩት። እሱም አደራዉን ተቀበለ። ኢክራም ወደ ትዳር ህይወት እንድትገባ ብዬ እንደተዉኳት ያዉቃል። ስለዚህ ከማንም ጋር እንዳትንዘላዘል መምከር አያቅተዉም ብዬ አስባለሁ።
.
በቀጣዩ ሳምንት ልጆቹን ለመተዋወቅ ወደ ተቀጣጠርንበት ከስድስት ኪሎ ዩኒቨርሲቲ ዋናዉ በር ፊት ለፊት ወዳለዉ መናፈሻ ሄድኩ።ከአንድ ዛፍ ስር ያለ ወንበር ላይ የተቀመጠች ቀይ ሴት እጇን አዉለበለበችልኝ። እኔ ሁለት ሴቶች እንደሚጠብቁኝ ነበር የተነገረኝ።
"ፈዉዛን ዌልካም!!" አለችኝ ከመቀመጫዋ ተነስታ እንድቀመጥ እየጋበዘችኝ።

"ሁለት ሰዉ እንደሚጠብቀኝ ነበር የተነገረኝ!!" አልኳት።
"አዎ ነዉ ግን ዛሬ ለምናወራዉ ነገር የሜሮን መኖር አስፈላጊ ስላልሆነ ነዉ ብቻዬን የመጣሁት!!" አለችኝ።
"ባይዘዌይ ፊርደዉስ እባላለሁ!!" አለች የአክብሮት ፈገግታ እያሳየችኝ።
አየኋት በጣም ቆንጆ ናት! በጣም!! ከኢክሩ ሌላ ቆንጆ ነበር እንዴ? የእዉነት በጣም ዉብ ናት። የለበሰችዉ ቀሚስ ሰፋ ያለ ነዉ። አይጨንቅም!! በጣም ልብሱን አሳምራዋለች።

"እና እንደዚህ ዉብ ሆነሽ ፊርደዉስ ካላሉ ምን ብለዉ ስም ሊያወጡልሽ ነበር?" አልኳት እየሳቅኩ
ፊርደዉስ ሳቋን ለቀቀችዉ!! ጉንጯ ላይ ስርጉድ አለ። ወይኔ በቃ ይህቺ ልጅ ልቤን ልታሰረጉደዉ ነዉ።
ፊርደዉስ ከጀነት በጣም ያማረዉ ጀነት ነዉ።

ጀነት እንደሆቴል ባለ4 ባለ5 ኮከብ እንደምንለዉ ይለያያል። ሰው እንደስራዉ ምርጡ ላይ ይገባል። ስሟ እና ዉበቷ በጣም የተስማማ ነዉ።

ፊርደዉስ ስቃ ስትጨርስ"ፈዉዛን መንገድ ላይ ነበር ያየሁህ! ከዛም ከሰዎች ስላንተ አንዳንድ መረጃዎችን አገኘሁ!!" አለችኝ።
ፈገግ አለችና እጇን እየዘረጋችልኝ ያዘዉ አለችኝ። ይሄ ነገር ወዴት ወዴት እየሄደ እንደሆነ ግራ ገባኝ።

"ይቅርታ ሴት አልጨብጥም!!" አልኳት
"ለምን?" አለችኝ
የእዉነት የእስልምና እምነት ተከታይ አልመስልህ አለችኝ። ሙስሊም ሆና ይህን አለማወቋ አሳዘነኝ።
"ቁርዓን ላይ ማን ማንን መንካት እንደተፈቀደልሽ ተፅፏል አንብቢዉ!!" አልኳት።

"እሺ ለዛሬ ብቻ ጨብጠኝ!!"አለችኝ በአይኖቿ እየተለማመጠችኝ። አለንጋ ጣቶቿን ፊቴ ድረስ አስጠጋቻቸዉ።
የአይኗን እንቅስቃሴ በሚገባ አጤንኩት ይዞር ይዞርና ወደ ግራ እየሰረቀ ያያል። የስነ አእምሮ ተማሪ እንደመሆኔ በግራ በኩል የሚያየን ሰዉ እንዳለ ገመትኩ። ዞር ስል አንዲት ሴት የስልኳን ካሜራ አነጣጥራ እየቀረፀችን ነዉ።
.
ያላየሁ መስዬ
"ፊርደዉስ ሪያሊቲ ሾዉ ለመስራት አስበሽ ነዉ እንዴ የጠራሽኝ?" አልኳት
ወዲያዉ እንደባነንኩ ስለገባት ጓደኛዋ መቅረፅ እንድታቆም በእጇ ምልክት ሰጠቻት።
.
"ፈዉዛን በጣም ይቅርታ!! በቃ እዉነቱን እነግርሀለሁ!"አለችኝ የመሸነፍ ስሜት እየታየባት
እኔ የሰዉነቷን እንቅስቃሴ እና የምትመርጣቸዉን ቃላት በማዳመጥ የምታወራዉ እዉነት መሆን እና አለመሆኑን ለማጤን ተዘጋጀሁ።

"ፈዉዛን እኔ የሶፍትዌር ኢንጅነሪንግ ተማሪ ነኝ። እኛ ባች ዉስጥ "አይ ዊል ዱ ኢት" የሚባል ሙድ አለ።አንድ ቀን ጓደኛሞች አንድ ላይ ሆነን የኛ ጓደኛ ልትጨብጥህ ስትል ሴት አልጨብጥም ስትላት አየሁ። እና እኔ "አይ ዊል ዱ ኢት" አልኩ። እኔ አንተን በግድ እንድትጨብጠኝ ላደርግህ ከነሱ ጋር ተወራረድኩ።"አለችኝ።
"ዉርርዱን ባትፈፅሚ ምን ይከተልሻል?" አልኳት በጣም አሳዘነችኝ!

"ለኔ ዉርደት ነዉማንንም የሚያንበረክክ ዉበት አለኝ!! ጓደኞቼ መቀለጃ ነዉ የሚያደርጉኝ የምፈራቸዉ እነዚህን ነዉ ሲቀጥል ሁሉንም ሸራተን እራት ለመጋበዝ እገደዳለሁ።" አለችኝ።
ሁለት ነገሮች አስገረሙኝ በዉበቷ እርግጠኛ መሆኗ እና ሀንዳዉት ኮፒ ማድረጊያ ያጡ በሞሉባት ሀገር ለቀልድ ሸራተን ራት የሚገባበዙ ተማሪዎች መኖራቸዉ። ደግሞ እኮ እራት መጋበዙ ለሷ ቀላል ነዉ። ያስፈራት ሙድ መያዣ መሆኑ ነዉ።

"ልትጨብጪኝ ብቻ ነዉ የፈለግሽዉ?" አልኳት ድርድሩ ለመጨባበጥ ብቻ የተደረገ አለመሆኑን ከመቀጮዉ ስለተረዳሁ።
እንደማፈር እያለች"አይደለም ከንፈርህን መሳም ነዉ ዉርርዱ አለችኝ።"
ከወንበሬ እየተነሳሁ "እንዳታስቢዉ!!" አልኳት።
ፊቷ በእልህ እየቀላ "ፈዉዛን ታደርገዋለህ!!"አለችኝ። በተቀመጠችበት ትቻት ሄድኩ።.

ሰዓታት ምንም የሰዉ ልጅ ለዉጥ ቢፈጥርም ባይፈጥርም ከመቁጠር አይወገዱም። ተኝተንም እንዋል በስራ ተጠመድን ቀን ይነጉዳል።እንደቀልድ አመት አለቀ ይባላል።

ከኢክራም ጋር የፍቅር ግንኙነታችንን ካቋረጥን ከሶስት ወራት በላይ ተቆጠሩ። በወንድምነት የነበረንንም ትስስር ኢክሩ ካቆረፈደችዉ ሁለት ወር ሆነ።
የዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ አመት ትምህርቴን አጠናቅቄ ክረምቱን እየቦዘንኩ ነበር

አንዳንዴ እዚህ ካፌ እየመጣሁ ከረሂማ ጋር እጫወታለሁ።አንዳንዴ ብሩኬ ጋር እየሄድኩ እደበራለሁ።በዛ ሰሞን ግን ለተለያዩ ተቋሞች የስነ ፅሁፍ ስራዎችን ድህረ ገፃቸዉ ላይ በመስራት ተጠምጄ ስለነበር ኢንተርኔት ላይ ተጥጄ እዉል ነበር።

አንድ ቀን እንደተለመደዉ ኢንተርኔት ላይ ተጥጄ ከማላዉቀዉ ሰዉ መልዕክት ደረሰኝ።

ልጁ ሰላምታ እንደተለዋወጥን
"ፈዉዛኔ እኔ ሰፈር አካባቢ አዉቅሀለሁ። ከኢክሩ ጋርም ግንኙነት እንደነበራችሁ አዉቃለሁ። አሁን የፍቅር ግንኙነት ዉስጥ ናችሁ እንዴ?"የሚል መልዕክት ላከልኝ።
ወዲያዉ "እኔና እሷ መገናኘት ካቆምን በጣም ቆይቷል።

በመካከላችን ምንም አይነት ግንኙነት የለም።"አልኩት።
ልጁ አመስግኖ ተሰናበተኝ።ትንሽ ቆይቼ አሰብኩና በመልሴ ተፀፀትኩ። ፍቅረኛዬ ናት ነበር ማለት የነበረብኝ።ኢክሩን ከዚህ በኋላ አግብታ እንጂ ከማንም ወንድ ጋር ስትንዘላዘል ማየት አልፈልግም። ልጁ ጥያቄ ደግሞ ከተዉካት ልዉሰዳት አይነት ነዉ። ማንም የጣለዉን ሲያነሱበት አይወድም።

ሊያዉም እንድታገባ የምመኝላትን ሴት አብራዉ ስትንዘላዘል ማየት ያመኛል። ዉስጤ ሰላም አጣ።የኢክሩን የፌስቡክ ገፅ ለመጎብኘት ገባሁ አንፍሬንድ እንደተደረግኩ ነዉ።ላወራትና ከልጁ ላስጥላት ፈለግኩ።
.
ከኢክሩ ጋር ከሶስት ወራት በኋላ ድጋሚ ፌስቡክ ላይ አወራን።ስላለችበት ሁኔታ አንዳንድ ነገሮችን ጠየቅኳት።እንደድሮዉ በመካከላችን ሰላም አዉርደን በወንድምነት እንድንቀጥል ጠየቅኳት። መልዕክቱን የላኩላት በእንግሊዘኛ ስለነበር የፍቅር ግንኙነታችንን ድጋሚ መልሰን እንቀጥል ያልኳት መስሏት እንዲህ አለችኝ

፦"እኔ ስትፈልግ የምትጥለኝ ስትፈልግ የምታነሳኝ እቃ አይደለሁም።አሁን ከሌላ ሰዉ ጋር የፍቅር ግንኙነት ጀምሬያለሁ።"
ደነገጥኩ!እሞትልሀለሁ ስትለኝ የነበረችዉ ኢክሩ ናት በሁለት ወር ዉስጥ ከህይወቷ ማህደር ፍቃኝ ከሌላ ወንድ ጋር ፍቅቅሮሽ የጀመረችዉ?ወይስ ሲጀመርም አፈቀርን ሲሉ ሰምታ እንጂ ፍቅር ምን እንደሆነ እንኳ አታዉቅም? እንዴ እኔ እኮ ኢክሩ ግጥም ስለማትወድ ብዬ ግጥም መፃፍ ያቆምኩኝ ይኸዉ እስከአሁን ግጥም አልፃፍኩም።ቆሻሻ ላይ የተወለደ ፍቅር ንፅህና ሊኖረዉ እንደማይችል ግልፅ ነበር።ትዳር ላይ ያልተመሰረተ ግንኙነት ፍሬ ሊያፈራ አይችልም። ኢክሩ እንዴት እኔን ረስታ ሌላ ወንድ ጋር ለመሄድ ደፈረች?እኔ እኮ እንኳን ልረሳት በጣም ስትስቅ የሚሸበሸበዉ አፍንጫዋ አሁንም አይኔ ላይ አለ።ኢክሩ እኮ እየተኮላተፈች 'ደ' ስትል አሁንም ጆሮዬ ላይ ይደጋገማል


ነጠብጣብ ዛሬ ማታ 3 ሰአት ላይ ፍፃሜው ያገኛል
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
●●●ነጠብጣብ●●●♥️

            💞ሊጠናቀቅ አንድ ክፍል ቀርቶታል

                          
#ክፍል_17


ራሴን አረጋጋሁ እና ኢክሩ ልታናደኝ ፈልጋ እንጂ እንደዚህ የምታደርግ ልጅ እንዳልሆነች ብዙ ምክንያቶችን እየሰጠሁ ራሴን አሳመንኩት።
እንደዉም እኔ እወድሻለሁ ስላት አይኗን ወደ ሰማይ እየሰቀለች "ፈዉዛኔ የኔ ድመት አንተ ትወደኛለህ። እኔ ላንተ ያለኝ ፍቅር ግን ካንተ በጣኣኣኣም ይልቃል።" ያለችዉን አስታወስኩ።
ኢክሩ በሁለት ወር ዉስጥ ይሄን ፍቅሯን ከልቧ አስወጥታ ከነገስኩበት የልቧ ዙፋን ላይ ሌላ ሰዉ እንደማታስቀምጥ ለራሴ ነገርኩት።
"ምንም ችግር የለዉም። መብትሽ ነዉ!" ብዬ መለስኩላት። አልተናደድኩልሽም እንደማለት ነበር ያሰብኩት።
እኔ ፍቅረኛ ይዤ ከሆነ ጠየቀችኝ እንዳልያዝኩ ነገርኳት።
.
ወደ ማታ ላይ ብሩኬን አግኝቼ የተፈጠረዉን ነገር ነገርኩት። ኢክሩ ፍቅረኛ ይዛ ከሆነም ሁለቱን ለመነጣጠል ስል የፍቅር ግንኙነት ከሷ ጋር ልጀምር እንደምችል ነገርኩት። ማንም እንደኔ ሊያስብላት አይችልም ብዬ አምናለሁ። ቢያንስ ከኔ ጋር ከሆነች ዝሙት ላይ አትወድቅም። ሌላ ወንድ ኢኩ ላይ ስሜቱን ሲያስታግስ መመልከት አልፈልግም። ኢኩ ንግስት ሆና ባል ስታነግስ ነዉ መመልከት የምሻዉ።
አንገቴን አቀርቅሬ "ብሩኬ ኢኩ የእዉነት የፍቅር ግንኙነት ጀምራ ከሆነ እኔ ኢኩን እና ልጁን ለማጣላት ከሷ ጋር የፍቅር ግንኙነት እስከመቀጠል ድረስ ለመጋፈጥ ወስኛለሁ።" አልኩት
ብሩኬ እንደመቆጣት እያለ "በቃ ተዋት የራሷን ህይወት ትኑርበት!!" አለኝ
ሳግ እየተናነቀኝ "ብሩኬ እኔ እኮ እንድታገባ እንጂ ከማንም ጋር እንድትንዘላዘል አይደለም የተዉኳት!!" አልኩት።
"በቃ ተዋት አይመለከትህም!!" አለኝ አሁንም ቆጣ እንዳለ ነዉ።
ብሩኬ ይሄን አቋሜን ስላልደገፈልኝ ተበሳጨሁ። ከዚህ በኋላ የምወስዳቸዉን እርምጃዎች እሱን ሳላማክር ለመዉሰድ ወሰንኩ።
.
ፊርደዉስ ክረምቱን በተደጋጋሚ እየደወለች እንድንገናኝ ትጠይቀኛለች። እኔ ግን ዉርርዷን ልትፈፅምብኝ እንደሆነ ስለማስብ ላገኛት ፈቃደኛ አልሆን አልኳት። እዉነት ለመናገር በኔና በሷ መካከል ሀይማኖት እና ማህበራዊ ስርዓታችን ልቅ መሳሳምን ባያወግዝ ኖሮ እኔ ነበርኩ ከንፈሯ እንደ ኢክሩ እስኪያብጥ የምስማት!! ግን ሰዉ እንደመሆኔ እንደ እንስሳ ማሰብ የለብኝም። ስጋዬ ይፈልጋል አልዋሽም!! ግን ፈጣሪዬን ማስቆጣት አልፈልግም። እሱን ካስቆጣሁ አንዷን ፊርደዉስን አግኝቼ ጌታዬን ላጣ እችላለሁ። እሱን ባስደስት ግን ጌታዬ የፊርደዉስ አይነት ሴቶች ካዝና በእጁ ነዉ።
አንድ ቀን ሀሙስ እለት ፊርደዉስ ደዉላ የጓደኛቸዉን ልደት ስለሚያከብሩ እንድገኝ ጠየቀችኝ። ሙስሊም ስለሆንኩ ልደት እንደማላከብር ነገርኳት።
"ኧረ ፈዉዛኔ ይሄን ያህልማ አታካብደዉ!!" አለችኝ።
በሷ ቤት አክርሬባት ሞታለች።
"ፊርደዉስ እኔ ሙዴ እንደዚህ ነዉ!! እንደየሙዳችን ብንሆን ይሻላል ከምንከራከር!" አልኳት
"እሺ በጣም ጥሩ!! በርዝደይ ፓርቲዉ ላይ እኔም አልገኝም። ካንተ ጋር መገናኘት እፈልጋለሁ።" አለችኝ።
ተስማምተን ቀጠሮ ያዝን።
.
ፊርደዉስ ስትስቅ ጉንጮቿ በጣም ይሰረጉዳሉ። በጣም ታምራለች። ሳር ቤት አካባቢ ተገናኘን። መኪና ይዛ ነበር የመጣችዉ። ገቢና ገብቼ ከዚህ በፊት ገብቼበት ወደማላዉቀዉ መናፈሻ ይዛኝ ሄደች። ቦታዉ በጣም ቆንጆ ነዉ። መኪናዋን ቦታ አስይዛ ካቆመችዉ በኋላ ከመኪናዉ ወርደን ዉቡ የሳር መናፈሻ ላይ የተቀመጡት ወንበሮች ላይ ተቀመጥን።
"ፈዉዛኔ እኔ ማንንም ወንድ እንዳንተ ተለማምጬ አላዉቅም። ይህን ሁሉ የማደርገዉ እንድስምህ ስለተወራረድኩ ብቻ መስሎህ ከሆነ ተሳስተሀል! አንተ የራስህ አቋም አለህ። እንቢ ማለት መቻልን አስተምረኸኛል። እኔ ደግሞ አላማ አለኝ። ይሄን አላማዬን ለማሳካት ካንተ የተሻለ አማካሪ የማገኝ አይመስለኝም።" አለችና በረዥሙ ተነፈሰች
ፊርደዉስ የኮምፒዩተር እዉቀቷ በጣም ከፍተኛ መሆኑን ከነገረችኝ እቅዶቿ ተረዳሁ። ያለማቋረጥ ለአንድ ሰዓት እቅዷን ነገረችኝ። አሁን ፊርደዉስን በጣም አከበርኳት። በምችለዉ ሁሉ ላግዛትም ቃል ገባሁላት።

.
የኢድ አል አድሀ ማለትም የሀጅ ስነ ስርዓት እንዳለቀ ያለዉ የኢድ በዓል ደረሰ። ሁልጊዜም እንደማደርገዉ በስም ቅደም ተከተል ሰዎች ጋር እየደወልኩ እንኳን አደረሳችሁ እያልኩ በኢ ተርታ ያሉት ጋር ደርሼ ኢክራም ጋር ደወልኩ።
የዛሬን አያድርገዉና ሌላ ጊዜ መጀመሪያ እሷ ጋር ደዉዬ ነበር ቀሪዎቹ ጋር በስም ቅደም ተከተላቸዉ የምደዉለዉ።
አነሳችዉ "ኢኩዬ እንኳን አደረሰሽ!!" አልኳት።
"እ ንኳን አብሮ አደረሰን!" አለችኝ እየተንጠባረረች
"በዓል እንዴት ነዉ?" አልኳት
"ጥሩ ነዉ አለችኝ" በአጭሩ።
በመልሷ በጣም ተበሳጨሁ በስርዓቱ ተሰናበትኳትና ስልኩን ዘጋሁት። እኔ የስነ አእምሮ ተማሪ ነኝ ኢክራምን እንዲህ ያንጠባረራት ጉዳይ እንዳለ ተገለፀልኝ። አዎ ኢክራም ፍቅረኛ ይዛለች። ካንተ ሌላ ላፈር ስትለኝ የነበረችዉ ኢኩ በሁለት ወር ዉስጥ ሌላ ሰዉ ለምዳለች። ሰዉዬዉ ማን እንደሆነ ማወቅ ፈለግኩ። ኢክራምን በቅርብ ርቀት መሰለል ይኖርብኛል።
ትኩረቴን ሙሉ ኢክራም ላይ አደረግኩ። አሁን ስላለችበት ሁኔታ በአምስት ቀናት ዉስጥ ሙሉ መረጃ ሰበሰብኩ። አዎን የኢክራም ህይወት ባልገመትኳቸዉ መንገዶች ሁላ ሳይቀር ተለዉጧል። ማመን የማልችላቸዉን መረጃዎች አገኘሁ።...

  
ብዙ ሰዎች ኢክሩ በፍፁም ጥፋተኛ እንዳልሆነች ነዉ የሚያስቡት። "ሳይቸግርህ ጭረሀት" "አንተ ነህ የተዉካት!!" ምናምን ይሉኛል። መተዉ ምን ማለት ነዉ? እኔ እኮ ኢክሩን በጊዜዉ ለማግባት ስለማልችል እንድታገባ ብዬ ነበር የተለየኋት። አደራ ያልኩት እኮ ፈጣሪዬን ነበር። እኔ እሷን የመናፈቅ እሳቴን አፍኜ ይብቃን ስላት ለሷ የወደፊት ህይወት ማማር እየተሰዋሁ እንደነበር ለምን አይገባቸዉም? ተዋት ይላሉ እንዴ? አቅሜን አዉቄ ለፈጣሪ አሳልፌ በሰጠሁ ገፋት ይላሉ እንዴ? አስመሳይ ሁላ!! ለነገሩ የነሱ ወሬ ለኔ ምንም ነዉ። ያመንኩበትን ነገር እንጂ አላደርግም! ስሜት ያወረዉ ትዉልድ የሚታይ ድርጊት እንጂ የታፈነ ስሜት አይገባዉም። ኢክራም እንደተሰዋሁላት እንዲገባት ከፎቅ ላይ ራሴን መፈጥፈጥ አይጠበቅብኝም። ማንም ሳያዉቅ በልቤ እንደታፈንኩ እኖራለሁ። በኔ ዝምታ ዉስጥ ብዙ ትርጉም ነበር። እሷን በመተዌ ያሳለፍኩትን ስቃይ እኔ ነኝ የማዉቀዉ። እስከዛሬ ጠረኗ የማይረሳኝ ሰዉ እኮ ነኝ!! ከሷ በኋላ ማንንም ያላየሁ!! አዎ የሱመያን የድምፅ መስረቅረቅ አድንቄያለሁ ፣ የፊርደዉስን ዉበት አሞግሻለሁ ግን አንዳቸዉንም ከምላሴ አሳልፌ ልቤ ዉስጥ አላስገባሁም። በሁሉም ሴቶች ዉስጥ የምትታየኝ ኢኩዬ ነበረች። ሁሌም ቃሌን አስታዉሳለሁ። ስንለያይ ለራሴ የገባሁትን ቃል!! የማግባት የስነ ልቦና እና የገንዘብ አቅም ሲኖረኝ መጀመሪያ ኢኩዬን ፈልጌ ካላገባች ላገባት ለራሴ የገባሁትን ቃል!! ተዋት ይላሉ እንዴ? ለሷ አልጋዉን አደላድዬ እኔ መሬት ላይ በተኛሁ ገፋት ይላሉ እንዴ? ወረኛ ሁላ!! ሲጀመር እነሱ የመዉደድን ልክ የወደዱትን የራስ ከማድረግ አሻግረዉ መመልከት አልቻሉም። እኔ ዉዴታዬ በዝቶ ለኢክሩ ባል ተመኘሁላት!! ኢክሩ ንግስት እንድትሆን ከነክብሯ እንድትለየኝ አደረግኩ። ጌታዬን አስደስቻለሁ እሷ የፈለገችዉን ትበል ግድ የለም። እንደኔ ያሰበላት፣ ወደፊትም የሚያስብላት ሰዉ ግን የሚኖር አይመስለኝም።

እንዳተኙ 4 ሰአት ላይ ቀጣዩን ክፍል ይጠብቁን ነጠብጣብ ዛሬ ፍፃሜውን ያገኛል

እስከዛ Like share
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
2024/09/21 05:39:23
Back to Top
HTML Embed Code: