Telegram Web Link
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
👵❀✿ያልወለደች እናት❀✿👵
:በነኢማ ኸድር
ክፍል:➐
ከትንሽ ደቂቃ ብሀላ አባባ ደውሎ ከ ፋይሰልጋ እየመጡ እንደሆነ ነግሮኝ ስልኩን ዘጋው እኔም እማማን ለማረጋጋት መጣጣር ጀመሬኩ እማማ ግን አይኑን ሳላየው ወሬት አይነካኝም ብላ በር ላይ ቆማ ትጠባበቅ ጀመር
ከግማሽ ሰአት ቅይታ ብሀላ እነ አባባ ቤት ደረሱ ፋይሰል ከንፈሩ ቆስሏል እንጂ ምንም አልተጎዳም እማማ ስታየው ከደስታዋ ብዛት እንደ ህፃን ልጅ ቦረቀች አመሻሽ ላይ ሁሉም ከተረጋጋ ብሀላ እማማ በምን ምክንያት ይህ እንደተፈጠረ ጠየቀችው መልስ ሳይሰጣት ተነስቶ ሊወጣ ሲል እማማ "ፋይሰል"ብላ ጮኀች ሁላችንም ደነገጥን ምክንያቱም አንድ ሰው ወትሮ ያለመደበትን ሲያረግ ያስደነግጥም አይደል አሁንም የሆነው እሱ ነው እማማ "የአይኔ አበባ" የምትለው ወንድሜ አሁን በመታወቂያ ስሙ "ፋይሰል"ቢላው እርፍ ደንግጦ ቆመ በር ላይ እንደቆመ ወደ እማማ ዞሮ "ምን ፋይሰል ነው ያልሽኝ እማማ"አለ ሁሉምም ግራ ተጋብቷል "አዎ ፈይሰል የኔ የአይኔ አበባ እንደዚ ጋጠወጥ ሆነ ብዬ ማለት ይከብደኛል ጭራሽ እያዋራሁክ ጤለኀኝ ትነሳለህ "አለች በቁጣ እማማ መናደዷ ስለገባኝ ለማረጋጋት "በቃ እማማ ደሞ እስር ቤት ቀይረውት ይሆናል"አልኳት ለማሳቅ እየጣርኩ በዚ ሆኔታ ጠዋት ደረሰ እማማና ፋድሲ በማታው ነገር ተቀያይመዋል ቁርስ ራሱ ሳይበላ ነው የወጣው የት ሄዶ ነው ጨነቀኝ እማማ እንደተነሳች ወዲያው ጠየቀችኝ እንደወጣ ነገርኳት ስልኩ ላይ ስትደውል ስልኩ ዝግ ነው ይብስ የማታው ንዴቷ ጨመረ ቁርስ በላልተው ከ አባባ ጋር ሱቅ ወጡ የነሱን እግር ጠብቄ ስልኬም አነሳውና ፋይሰል ጋር ደወልኩ ስልኩ ይጠራል ግን አይመልስልኝም ደግሜ ስደውል "ሄሎ ዳኒ ሲቅ ህኜ ነው ሰው እያስተናገድኩ ነው ብሀላ እደውላለው"ብሎ ዘጋው አሁን ትንሽ እንደመረጋጋት አልኩ ምክንያቱም ሱቅ ከፍቶ ስታየው ትንሽ ትረጋጋለች ብዬ አሰብኩ ከአንድ ሰአት ብሀላ እማማ ደወለችና ፋይሰል ሱቅ መሆኑን ነግራኝ ዘጋችው አዪ የኔ ምስኪን እናት ቀድሜ ማወቄን አላወቀችም!አራት ሰአት ሲሞላ እኔም ለባብሼ ወደ ትምህርት ቤት ሄድኩ ትምህርት ቤት ስደርስ ጨነቀኝ የልቤ ምት ከወትሮ ተለየብኝ 'ምን ሊፈጠር ነው'አልኩ ለራሴ እንደምንም እራሴን አረጋግቼ ትምህቱንም ሳልማር ወደ ቤት ተመለስኩ መኪያ ወዲያው ስመለስ ግራ ገቦትና "ምን ረሳሽ ?ዲኒ መቼም አንቺ ቀልብ የለሽ"ብላ ጠየቀችኝ "ባክሽ መኩ ልቤን ጭንቅ ሲለኝ ነው የተመለስኩት ጥሩ ሙድ ላይ አይደለሁም በቃ ልብሴን ልቀይርና አግዝሻለው" ብያት ወደ ክፍሌ ወጣው ልብስ ቀይሬ ከክፍል ልወጣ ስል ስልኬ ትዝ አለኝና ከቦርሳዬ አወጣሁት 5 ሚስኮል አለው አባባ ነው ክው ብዬ ቀረው ልቤም ያለወትሮ እንደዚ አልተረበሸም ስልኬ ብር ስለሌለው መኪያ እንድታስደውለኝ ወደ መአድ ቤት ስገባ መኪይ "ዳና አባባ.."ብላ ሳጨርስ "ምን ሆነ" አልኳች መኪያ ግራ ገብቷት "አረ ዳና ተረጋጊ ስልክ አታነሺም ዛሬ ትንሽ እቃ ቤት ስለሚወጣ መጋዜኑን አስለካክሉት ብሏል"አለችኝ ኡፍፍፍፍ ተረጋጋው አባባ መጋዘን የሚለው ከቤታችን ጀርባ እቃ ማስቀመጫ ይሆናል ተብሎ የተሰራው 5በ 5 ክፍሏን ነው የዋዛ እንዳትመስላቸለ ብዙ ኮተት ትይዛለች አልፍ አልፎ ስለምትከፈት አቧራዋ የጉድ ነው መኩ ስራ እየሰራች ስለነበር ከአባባ ክፍል ውስጥ ቁልፉን አውጥቼ መጋዜኑን ከፈትኩት ከቧራ ብቻ ሆኗል ይንፈስጠትና ይጠረጋል ብያ ከፈት አርጊ ተውኩት ትንሽ እንደቆየ መኩ መታ ማፀዳዳት ጀመርን እንደድንገት መኩ የሆነ የተጠቀለለ ልብስ ስታይ ከተወሸቀበት ጎትታ እያወጣችው "ዳኒ ይሄ የፋይሲ አይደል"ብላ አሳየችኝ "አው በቅርብ የገዛው ቲሸርት እኮ ነው አይ እሱ አሁን ምን ሆነ እዛጋር ወርውሪው ይታጠባል"ብያት ለመኩ ጀርባዬን ሰጠው ወዱያው መኪ በጩኀት ቀወጠችው በቅፅበት ዞር ብያ አይኗ ያለበት ቦታ ሳይ ክው ብዬ ቀረ

#ክፍል_➑ ይቀጥላል......
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
❀✿ያልወለደች እናት❀✿
:በነኢማ ኸድር
ክፍል:➑
የፋይሰል ቲሸርት በደም ተጨማልቋል ማመን አቃተኝ ትላንትና ጨይቄው መድሀኒቱ ካለቀ ብሀላ እንዳልነሰረው ነግሮኛል እየዋሸኝ መሆኑ ገብቶኛል መኩ ወደኔ እያየች "ዳኒ ፋይሲ አሁንም ያመዋል ማለት ነው"አለች እንባ ያቀረረውን አይኗ አይኔ ላይ ጥላ መልስ ሳልሰጣት የፋይሰል ክፍል ሄድኩ በሩን ለመክፈት እጀታውን ስስበው እንቢ አለኝ ተቆልፎል! ወትሮ ያለወደበት ለምን? የሆነ ነገርማ አለ ብዬ አሰብኩ ቀኑን ሙሉ በጭንቀት ስብሰለሰል አመሻሽ ላይ ሦስቱም አንድላይ መጡ ጊቢ መኪና አቆሙና ወዱ እማማና ፋይሲ ለመታረቃቸው እቺን ታክል አልተጠራጠርኩም ጭራሽ ተቃቅፈው ነው ወደ ቤት የዘለቁት አባባ ደሞ ዛሬ ፊቱ ደና አይደለም ጥቁርቁር ብሏል ገና ከመግባቱ ክፍሉ ገባና ተኛ እራት ቀርቧ ከአሁን አሁን ይመጣል ቢባል ዘር አልል አለ እማማ"ዳኒ አባባ እራት እየተጠበቅክ ነው ምን መሆንህ ነው በይው"አለች የእማማን ትዛዝ ተቀብዬ ወደ ክፍሉ አቀናው አባባ ያቃስታል "ምን ሆነህ ነው አባባ አመመህ እንዴ"አልኩት አተነፋፈሱ ያስፈራል "ደና ነኝ ዳኒ ድካሙም የጨማምሮ ነው ያደከመኝ እናንተ ብሉ እኔ ዛሬ ይቅርብኝ ይልቁንስ ወተት ካለ አምጪልኝ " ብሎ ላከኝ መኩን ስጠይቃት እንደሌለ ነገረችኝ ፋይሰል ከሱቅ እንዲያወጣ ስነግረው "መሽቷል" ብሎ ግግም ሲል እኔና መኩ ልንገዛ በር ላይ ስንደርስ መጣና "አቦ ነይ ተመለሺ በዚ ማታ የት ልትሄዱ ነው" ብሎ ወጣ ብዙም ሳይቅቆይ ይዞለት መጣ እንደ ዴንገት እማማ እራት እየበላን የትላንቱን ጥያቄ አነሳችቀት ፋይሰል እንደትናንትናው ጥሏት አልወጣም "ባንቺ ለመጣብኝ አይደለም መታሰር እገደላለው አንቺን እኮ ነው የሰደበብ"እያለ ለምን እንደታሰረ ተናገረ እማማ ነገሩን ለማጣራት "እኔን እንዴት?" አለች "በቃ እማማ አለፈ እኮ ሆሆሆሆ"አለና ለማስቀየስ ሌላ ነገር መቀባጠር ጀመረ አይነገ የለምና ነጋ ጨዋት ላይ አባባን ሳየው ፊቱ ልክ አይደለም "አባባ ደና ነህ አልኩት" ፊቱ ላይ የሚያስጨንቅ ገፅ ይታያል "ምንም አልሆንኩም ውዴ አትጨነቂ"ብሎኝ ሊወጣ ሲል "አባባ"አልኩት አንዳች ነገር እንደምለው ገብቶታል "ወዬ ዳኔ" አለኝና የሳሎን በር ላይ ቆመ "አባባ ካመመህ ሀኪም ቤት እንሂድ እእ"አልኩት አይንን እያቅለሰለስኩ "ቆይ ትንሽ ልየውና ከባሰብን እሄዳለው "ብሎ ከቤት ወጣ 'ምንድነው ጉድ በዚ ፋይሰል በዚህ አባባ ምን ጉድ ነው እየተፈተንን ነው እንዴ" አልኩ ለራሴ ዛሬ እማማ እቤት ናት ፋይሰል በጠዋት ሱቅ ሊከፍት ወቷል ከእማማ ጋር ገበያ ሄደን አንዳንድ የቤት እቃ ገዛዝተን ተመለስን እቤት ስንገባ መኪያ ቡና አፈላልታ ምሳ አቅርባ ጠበቀችን እማማ ደስ አላት ለነገሩ መኩ እማማን ሁሌ እንዳስደሰተች ነው እንደው እማማ ለ አጎቷ ልጅ ልትዳራት እንዳሰበች ቅድም ነግራኝ ነበር
ድክም ስላለን ተጣጠብንና የዙሁርን(ከ 6 ሰአት ብሀላ የሚደረገውን ስግደት) ሰግደን አንድላይ መመገብ ጀመርን እንደ ድንገት እማማ "መኩ"አለቻት "ወዬ እማማዬ"አለች መኩ እማማ ሁሌ ስትጠራት መልሶ ይሆ ነው ደሞኮ ሲያምርባት እማማ ምን ብላ እንደ ምትጀምር ግራ ገብቷቶል "እንደው የቅርብ ዘመድ ምትይው ሰው አዲስ አበባ የለም ማለቴም አጎት አክስ ምናምን" አለቻት እማማ ዳር ዳር እየሄደች ነው "መኪያ እንደማቀርቀር ብላ "እማማ ታሪኬን ሁሉ ታቄ የለ እኔ ማንም እንደሌለኝ ብላ ከአይኗ የእንዳዋን ዣረት ማፏፏት ጀመረች እማማ ደንግጣ "መኩ እዚ ቤት ስትኖራ አንድም ቀን እንደባዳ ቆጥረንሽም አይተንሽም አናቅም እና ምንም እንዳይከፋሽ ደሞ ምትፈልጊውን ነገር በግልፅ ተናገራ እሺ እኔም ውለታሽን እንዴት እንደምከፍል እንጃ አላህ ውለታሽን ይመልስልሽ አላህ ምርጡን ትዳር ይስጥሽ"ብላ ጀርባዋን ደባበሰቻት መኪያ ግራ ተጋብታ "ትዳር እማማ?"አለች በመገረም ድምፅ "ምነው መኩ ገና እኮ ልጅ ነሽ ታገቢያለሽ ትወልጃለሽ "አለች ዳር ዳር እያለች መሆኑ ገብቶኛል መኩ በግርምት "አረ እማማ ዛሬ ደሞ ጨዋታሽ ሁላ ተቀይሯል ሆሆሆ" ብላ ልትነሳ ስትል እማማ "መኩ"አለቻት መኪያ ልትነሳ የነበረችው እየተቀመጠች "ወዬ እማማዬ"አለቻት እማማ ሳንባዋ ውስጥ የተቃጠለውን አየር ኡፍፍ ብላ ካወጣች ብኃላ "ምን መሰለሽ የነጎቴ ልጅ መሀመድ ሊያገባሽ ይፈልጋል"አፈነዳችም! መኪያ ከተቀመጠችበት በቅፅበት ብድግ አለች ቆሌ የሚገፍ አነሳስ!..

#ክፍል_➒ ይቀጥላል......


ቶሎ ቶሎ እንዲለቀቅ

Share ይደረግ
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
ኮብልስቶን ውስጥ ለውስጥ እየሄድኩ ነበር ። እርቦኝ ነበር ። ጫማዬ ቆሽሿል ሱሪዬ የመንተብ መንገድ ጀምሯል፣ ፂሜ አድጓል ።

ሳይ ትክ ብዬ ነው። ትክ በዬ ሳይ ፊቴ ክስክስ ይላል ።

የሆኑ ሴትዮ እንቅስቃስዬን ይከታተላሉ ፀጉረ ልውጥ ሆኜባቸው ነው ። በራቸውን አጥሩን ትክ ብዬ ሳይ ሌባ መስያቸው እንደሆነ ገብቶኛል ።

እንደማመንታት ብለው ሰባት እርምጃ ያህል ይመስለኛል እንዳለፍኳቸው "ልጄ" ብለው ተጣሩ አጠራራቸው ፍፁም እናታዊ ነው ።

"አቤት እማማ "
"ደና ውልሃል ልጄ"
"ደና እማማ "
"ለእህቴ ሰባተኛ የሙት አመት ትንሽ ነገር አዘጋጅቻለሁ ። ቤት ያፈራውን ቅመስልኝ" አሉኝ

ያኖረን አንዳችን ስላንዳችን ምን እንዳሰብን ስለማይታይብን
ነው መሰለኝ ።
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
እንዲወዱህ ወይም እንዲፈልጉህ ማስገደድ አትችልም

✅️"ነገር ግን አንድ ቀን ያጡትን ነገር እንዲገነዘቡ ታደረጋችዋለህ"
❗️
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
#Breaking_News

📌መብራት በመላው ሀገሪቱ እንደተቋረጠ እየተነገረ ነው።ችግሩም እስካሁን አልታወቀም🤔

መብራት ያላችሁ✋🏽


                   🦋#Share🦋
👩‍💻 @ethioleboled @ethioleboled
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
#ኢማን
#በእውነተኛ_ታሪክ_ላይ_የተመሰረተ


#ክፍል8

ቤት ሁሉም ለ ሰርጉ ሽር ጉድ ማለቱን ተያይዘውታል የቀረ ሰው ያለ አይመስለኝም ከ ክፍለ ሀገር የ እማም የአባም ቤተሰቦች መተዋል። አንድ የ እማዬ ወንድም አለ በጣም ነው ምወደው ሚወደኝ ምንም ብነግረው ይረዳኛል እሱ የመሰለው ፍቃደኛ ሆኜ እንደማገባ ነው ነገሩን ሲሰማ ግን የተገላቢጦሽ ነው
"ያልገባኝ ነገር ለምንድነው ይሄን ያህል ጀማልን የምትጠይው?"
ምን ብዬ የምወደው ሰው ስላለ ልበለው የቱንም ያህል ብቀርበው ይሄንን ማውራት ግን አልቻልኩም
በቃ ቀልቤም አይወደውም በዛ ላይ ተማሪ ነኝ.....
"እህ እሱ ታዲያ መች ልውሰድሽ አለ ኢሙ ትምህርትሽን ጨርሰሽ ነውኮ ምትገቢው"
አብዱ እንዴት ነው በአላህ የምጠላውን ሰው አግብቼ ምኖረው?
" እሱ ከሆነ ቀላል ነው የምትጠይውን ሰው መውደድ ትችያለሽ ዋናው ነገር ጊዜ ነው በጊዜ ሂደት ማይለወጥ ነገር የለም ም/ቱም ኒካህ ነው ሚታሰርልሽ በጊዜ ሂደት ስትገናኙ ትወጂዋለሽ"
አይ አልወደውም አይ አልወደውም እያልኩ እንባ ተናነቀኝ
" እሺ ኢሙ እንደሱ ከሆነ አብረን መፍትሄ እንፈልጋለን እቃ ስትገዛዢ አታብዢ ትንሽ ትንሽ ግዢ በጊዜ ሂደት ካልወደድሽው ኒካሽ ይወርድልሻል የገዛውንም እቃ ታስቦ እኔ አመልስለታለው"


አልሀምዱሊላህ የሆነ ነገር ቅልል አለኝ።አብዱ እንዳለኝም ወርቅ የእጅ እና የጆሮ ብቻ ገዛው ልብስም ሁለት ቅያሬ ሂጃብም እንደዛው ገዝተን ተመለስን እነ ማሚ ሲያዩት በጣም ነበር የተናደዱብኝ " ምንድነው ቁንጥር ቁንጥር ያለ እቃ ምትገዢው" እያሉ ተራ በተራ ጮሁብኝ ያሰብኩትን ማውቀው እኔ ነኝና ያሉትን ከምንም አልቆጠርኩትም

የኒካው ቀን ደረሰ የሰው ጫጫታ ሽር ጉዱ ሲታይ ግን ኒካ አይመስልም ነበር መቆሚያ ቦታ ራሱ የለም።የሰፈር ሰው ሁሉ ተጠርቷል ማንም አልቀረም።የመጀመሪያ ሚዜ ሰሚራ ናት ሁለቸኛ የ አክስቴ ልጅ ሀያት ሶስተኛም ዘመዴ ናት ሰአዳ። ከ ሚዜዎቹ ጋር አንድ ሀሳብ መጣልን " ሲታይ ገንዘብ ሚያወጣ አይመስልም ለምን ተናዶ እንዲተው ወጪ አናበዛበትም?"ሀያት ነበረች "እውነቷን ነው ቬሎ ተከራይ እንበለው" አለች ሰአዳ ደወልንለትና መከራየት እንደምንፈልግ ነገርነው አሺ ወደ ማታ ላግኝሽ ብሎኝ ጨረስን ማታ አካባቢ ከ ሀዩ ጋር ሄደን ተቀብለን በማግስቱ ሄደን ተከራየን መልካም ጋብቻ የሚል ፅሁፍ አፅፈን መጣን። በኛ ቤትኮ። እቃ እቃ መጫወታችን ነው አይ ልጅነት ሌላ ነገር አናስብምኮ በቃ የኒካው ቀን ደረሰና ለብሼ ተቀምጫለው ቤቱ ፏ ብሏል ሰው መምጣት ጀምሯል አጎት ተብዬው መጣ ሲያይ ቬሎ ለብሻለው ሲያይ መልካም ጋብቻ ይላል ጠራኝና
"አንቺ ግን እብድ ነሽ ወላሂ ብልጥ ትመስይኝ ነበርኮ ከመች ጀምሮ ነው ለ ኒካህ ቬሎ ሚለበሰው ምንድነውስ ጋብቻ ማናምን ያላቹት"!!!!
አረ አብዱ እኛኮ ምንም አስበን አይደለም አልኩት
"ምን ለነገሩ ቬሎ ስለለበስሽ ይወስድሻል ማለት አይደለም ፏ በይበት እንደውም" ብሎኝ ነገሩን ቀለል አደረገው።

#ክፍል9....ይቀጥላል......

ታሪኩ ሊያልቅ 2 ክፍሎች ብቻ ቀርተውታል


#Share #Share



ቻናላችንን ለውዳጅ ዘመድዎ ሼር በማድረግ ስራዎቻችንን ያበረታቱ። ስለምትከታተሉን ከልብ እናመሰግናለን
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
#ኢማን

#በእውነተኛ_ታሪክ_ላይ_የተመሠረተ


#ክፍል9

ወደ 7 ሰአት ገደማ ሰርገኛ መጣ በእልልታም ተቀበሉት። ምሳ ተበላ ተጨፈረ ኒካም ታሰረ ብናይ አይወጡም ብናይ አይወጡም። የሆነ የሰፈር ህፃን ልጅ መጣና በጆሮዬ " ልክ ቀለበቱን እጅሽ ላይ ሲያጠልቅ እኔን ከልብሽ አውጥተሽ አትጣይኝ ሁሌም አኑሪኝ" የሚል ከ ሀምዛ የተላከ መልእክት ነበር ውስጤ ተረበሸ ግራ ገባኝ እያለቀስኩ ሳለ የ አባ ወንድም አጎቴ መጣ
"እ ኢሙ ተበላ ተጠጣ መዝናኛ እንሂድ እየተባለ ነው ፎቶ ተነስታቹ አመሻሽ ላይ ትመለሳላቹ" ምን ትዝ አለኝ አንዷን ጓደኛችን እንዲህ ብለው ማይሆን ነገር ሰርተዋታል ማለት ወሰዷት እቤታቸው የሷ በቤተሰብ ቢሆንም ወዳዋለች ግን እኔስ?? ሃሃሃሃ በጣም ትሸውዱ የለም እንዴ በል ንገራቸው እንዳልተስማማው
"አረ እንደሱ አያደርጉም ካደረጉማ 20,000 አስይዘናል ይቀጣሉ" ታድያ ለኔ ምን ያደርግልኛል ከሄድኩ በኋላ እናንተ ትበሉበታላቹ ትጠጡበታላቹ በቃ🤷‍♀ ሲያቅተው አብዱን ጠራው ያው ቀረቤታዬም ከሱ ጋር ስለሆነ ምንም ቢለኝም አምነዋለዋ።
እ አብዱ የሚለው እውነቱን ነው?
"አዎ እውነቱን ነው" አለኝ አይ እንደሱ ከሆነማ እሺ ብዬ ስነሳ ዘወር ብሎ በምልክት እንቢ በይ አለኝ አረ አልፈልግም አልሄድም አልኩ ድጋሜ አጎት ተብዬው ተናዶብኛል ከፈለጋቹ እነሱ ከሄዱ በኋላ እኛ ሄደን እንዝናናለን አልኩት።

እንደዚህ እየተከራከርን 12 ሰአት ሆነ እነ ሀምዛ ቤት ተረብሸዋል ይሄ ነገር የምር እዚህ የሚደርስ አልመሰላቸውም ነበር ማዘርየው አልመጡም መረጃ የሚያመላልስ አለ ከኔ ወደነሱ ከነሱ ወደ እኔ መጨረሻ ላይ ጀማልን ጥሩልኝ ብዬ መጣ።
ቆይ ግን ያምሀል ምን ብላቹ ነበር መጀመሪያ እእእእ
"አንቺ ራሱ ምንድነው የምትይው እኔ ትምህርትሽን ስትጨርሺ እና የማስተካክላቸው ነገሮች አሉ ስጨርስ ብዬሽ አልነበር በአንዴው ምን ተለውጦ ነው ካልወሰድከኝ የምትይው"??
በጣም ደነገጥኩ ምን እንደሚያወራ ራሱ ግራ ገብቶኛል በሰአቱ ለካ ይሄን ሁሉ የሚጠነስሱት የኔ አጎት እና የሱ አባት ነበሩ። አባ እና እማ ምንም የሚያውቁት ነገር የለም የሱ አባት ልጅቷን ይዘን ካልሄድን ከዚህ ንቅንቅ አንልም አሉ አማም አባም ግራ ተጋብተዋል እኔን ተነሽ ሂጂ እንዳይሉ እጎዳባቸዋለው የመጣውንስ ሽማግሌ እንግዳውን ምን ብለው ተነስታቹ ውጡ ይላሉ? ተያይዘው ወጥተው መስጊድ ሄደው ማልቀስ ጀመሩ። ህዝብም ደሞ መጨረሻውን ሳናይ ንቅንቅ አንልም ብለዋል መሰለኝ የሚወጣም የለም በቆሙበት እርስ በእርሳቸው ይንሾካሸካሉ ትወጣለች አትወጣም የሚለውን በመሀል አባን ጥሩልኝ ስል ነው እንደሌሉ ያስተዋልኩት
ቆይ በአላህ ከኔ ከልጃቸው ሽማግሌ በልጦባቸው ነው የሸሹት? እ ለምንድነው መተው ማያባርሩልኝ ሁሉም እኔን እያየ የሚያለቅስ እንጂ ምንም የሚለኝ ጠፋ።

ማንም ከጎኔ ሊቆም አልቻለም ነበር መጨረሻ ላይ ተሸነፍኩ የተሸነፍኩትም አብዱ መጣና ይዞኝ ባዶ ክፍል ገብተን እንዲህ አለኝ
"በቃ ኢሙ አልቻልኩም ወላሂ ብዙ ጣርኩ አቃተኝ ከዚህ በላይ ምን ላርግልሽ እእ "ስቅስቅ እያለ ነበር የሚያለቅሰው
በቃ አብዱ አንተም ተሸነፍክ ምንም ተስፋ የለኝም ማለት ነው ከጎቴ በሩን እየቀጠቀጠ አንተ ነህ ልጅቷን የምትመክራት ተዋት ትሂድበት ይለዋል
"ኢሙ ሰማሽ አይደል ሁሉም እኔን እየወቀሱኝ ነው ኢሙዬ ከዚህ በላይ መታገል አልችልም ይቅርታ"እያለ እግሬ ስር ወደቀ
የኔ የ ኢማን ህይወት እዚህ ጋር አበቃ ማለት ነው እንጫወታለን ብለን ተጫወቱብን አይደል? አቅፌው መንሰቅሰቅ ጀመርን።


#የመጨረሻው_ክፍል10_............
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
#ኢማን
#በእውነተኛ_ታሪክ_ላይ_የተመሠረተ


#ክፍል10_የመጨረሻው_ክፍል


አብዱ ከክፍሉ ይዞኝ ወጣና ቦታዬ አስቀምጦኝ ቤቱን ለቆ ወጣ ጀማል መጣና ይዞኝ ወጣ ሰርግ ቤት ሳይሆን ለቅሶ ቤት ነበር የሚመስለው አባም እማም መጡ አይኔን ግን አላዩም ነበር በስራቸው ተፀፅተው ይመስለኛል እያለቀሱ ከቤት ወጣን።

እነሱ ቤት ስንደርስም ሰው በሽ ነው ምንም የቀረ ነገር የለም የታሰበበት ነው የሚመስለው።እኔ ግን ምንም ፊቴ አልተፈታም ተበላ ተጨፈረ ይዞኝ ወደራሱ ቤት አቀናን የኔ ሚዜዎች የለበስከለትን ቬሎ ቀያይረዉልኝ ሄዱ። ሽማግሌ ከተላከበት ቀን አንስቶ እስአ አሁን እንቅልፍ የሚባል አልተኛሁም አልጋው ላይ በተቀመጥኩበት እንቅልፍ ሸለብ አደረገኝ ትንሽ እንደተኛው ነቃ ስል አጠገቤ ጀማል ተቀምጧል ወደኔ ጠጋ ሲል አበድኩ ምን ያላልኩትት ነገር አለ ክፍሉን ለቆ እንዲወጣ ነገርኩት ምንም አላለኝም ወጣ በሩን ከዉስጥ ቆልፌ የሆንኩትን እያስታወስኩ አነባው ከማልቀሴ የተነሳ ፊቴ ፍም መስሏል ራስ ምታት ሊለቀኝ አልቻለም በዛው እንቅልፍ ወሰደኝ.......በማግስቱም ተመሳሳይ ነገር ነበር የተፈጠረው።

በ ሶስተኛው ቀን መልስ ተጠራን በጣም ነበር ደስ ያለኝ እንደዛ ቀን የተደሰትኩበትን ቀን ሁላ አላስታውስም ወላሂ...መልስ ሲባል ያሰብኩት መመለሴን እቤት የምቀር ነገር ነበር ግን አይደለም ሄድን አሪፍ ዝግጅት አድርገው ነበር። 5 ሰአት አካባቢ የተሰጠኝን ስጦታ ጭነን መጣን ትዳር ሲባል የራስን ስሜት ማዳመጥ ብቻ አይደለም የባል ሀቅ የሚባለውም ነገር አለ ምንም ማድረግ አልችልም ላያስችል አይሰጥም አይደል የሚባለው..ወላሂ በዛን ሰአት ጀማልን ቀና ብዬ ሳየው ራሱ ይቀፈኛል ራሴን ጠላዋለው ቢሆንም ግን ምንም አማራጭ አልነበረኝም ቢጃማዬን ቀይሬ አልጋው ጫፍ ላይ ቁጭ እንዳልኩ ጀማል መጣ ሰውነቴን እንደ እሾህ ይወጋኝ ጀመር ከዛን ሰአት በኋላ ምን ይፈጠር ምን ልሁን የማውቀው ታሪክ የለም ብቻ ስነቃ ያስተዋልኩት ማማ ግርግዳውን ተደግፋ ታለቅሳለች ሳሎን ላይ ተዘርሬ ብርድ ልብስ አልብሰውኛል ሁለት ሼኽዎች በግራና በቀኝ ቁርአን ይቀሩብኛል ዙሪያዬ በቤተሰቦቼ ተከብቤያለሁ።.....ከዛን ጊዜ በኋላ ተለከፍኩ ጊዜ እየጠበቀ ህመሜ ይነሳብኛል ቁርአንም ቤት እመላለሳለው።

አንድ ቀን እንደ ወትሮ ቁርአን ሲቀራብኝ እለፈልፍ ጀመር ለካስ የዚ ሁሉ መንስኤ ሀምዛ እና እናቱ ነበሩ ሱብሀንአላህ😔 እኔ በህይወቴ በትዳሬ ደስተኛ እንዳልሆን አስደግመውብኛል ወላሂ ይሄንን ሳውቅ ሀምዛን ከልቤ እርግፍ አድርጌ አወጥቼ ጣልኩት ሀምዛንኮ ሌላ ባገባ ብወልድ ራሱ አልረሳውም ነበር...ፍቅር እንዲህ ነው እንዴ በህይወቴ ምንም ደስታ አልነበረኝም 2 ልጆች አሉኝ ደስታዬ ግን አልነበረም አልሀምዱሊላህ ይሄን ስራቸውን ካወኩኝ በኋላ ቁርአንም መከታተል ስቀጥል ደስታ ወደ ቤቴ ገባ። ጀማል ይሄን ሁሉ ታገሰኝ ሁሌ ያዘነች ሚስት ቤት ውስጥ እያየ ሁሌ ያኮረፈች ሴት እያየ ኖሯል ሆኖም ግን አንድ ቀን እንዲህ ሆኜ ብሎኝ አያውቅም ታገሰኝ ይህንን ሳስብ እሱን ይበልጥ እንድወደውና እንዳከብረው አደረገኝ።

አልሀምዱሊላህ ከዛን ጊዜ በኋላ ደስተኛ ነኝ አሁን ላይ ትምህርቴን ጨርሼ ተመርቄ በተመረኩበት ሞያ ላይ እየሠራው ነው ሶስተኛ ልጄን ወልጃለው ለሁሉም ግን አልሀምዱሊላህ...........


#ተፈፀመ....
ታሪኩ እንዴት ነበር አስተያየተቻሁን ከስር አስቀምጡልን 👇👇👇

@Meki3
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
ነጠብጣብ የሚል ተከታታይ እጅግ በጣም አስተማሪ ታሪክ ልንጀምር አስበናል እስኪ አበረታቱን?

እንጀምር??
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
💥📚ኢትዮ-ልቦለድ📚📖💥
Photo
.              ●●●ነጠብጣብ●●●♥️

           በ ፋአድ ሙና

                
#ክፍል_1

...🖊ይገርማል ወደዚህች ምድር ከመጣሁ አስራዘጠኝ ዓመታቶች ነጎዱ ማለት ነዉ? እዚህች ምድር ከመጣሁ በልጅነት እንደ ልጅ ከልጆች ጋር የተጫወትኩበት ፣ የእሳቱ እድሜ ደርሶ ልቤ አብጦ ቤት ማንንም አልታዘዝም ያልኩበት እና ህይወትን ለመረዳት የሚያስፈልጉ ወሳኝ ነጥቦችን የተረዳሁበት እድሜ ነጎደ። አሁን ወደ ሀያኛ አመት ሩጫዉን ተያይዤዋለሁ።

በነዚህ ዓመታት ዉስጥ በህይወቴ ዉስጥ ብዙ ሰዎች አልፈዋል። ብዙ የማይረሱ ተወዳጅ እና አናዳጅ ሰዎችን አዉቄያለሁ። አስራ አምስት ዓመታትን መጨረሻዬን በመናፈቅ በትምህርት አሳልፌያለሁ።
.
◼️አሁን የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ነኝ።

ስሜ ፈዉዛን ይባላል። ጠይም እና ተጫዋች ነኝ። ቁምነገር ላይ ቁምነገረኛ ፣ ቀልድ ላይ ደግሞ ምርጥ ቀልደኛ ነኝ። በራሴ በጣም እተማመናለሁ። ብዙ ሰዎች ጢባራም ነህ ይሉኛል። ከሩቅ ሲያዩኝ የሚጠሉኝ ቀርበዉ የሚያዉቁኝ ደግሞ የሚወዱኝ አይነት ሰዉ ነኝ።

ስለራሴ እንደዚህ በድፍረት የማወራዉ ብዙዎች ከቀረቡኝ በኋላ ምን ያህል ከሩቅ ሲያዉቁኝ ይጠሉኝ እንደነበር እና ሲቀርቡኝ እና ሲያዉቁኝ በጣም እንደወደዱኝ በተደጋጋሚ ስለሚነግሩኝ ነዉ። ለራሳችን ያለን አመለካከት ከሚገነቡበት መንገዶች አንዱ ሰዎች ስለኛ በሚነግሩን ነገር ላይ የተመሰረተ መሆኑ እሙን ነዉ። ለዛ እኮ ነዉ ቤተሰብ እምነት የሚጥልባቸዉ ልጆች ፣ ሁሌም ጀግንነታቸዉን የሚነግራቸዉ ታዳጊዎች ከከፍታ መሰላል ላይ ቆመዉ የምናየዉ።

በአንፃሩ ደግሞ አታዉቅም እየተባሉና ትንሽነታቸዉ እየተነገራቸዉ ያደጉ ልጆች ትንሽ እንደሆኑ ይቀራሉ። በእርግጥ እየተሞገሱ የሚቀሽሙ እንደሚኖሩት ሁላ ከዚህ የትንሽነት ቀንበር አምልጠዉ ታላቅ የሚሆኑ ጥቂቶችም አይጠፉም።
.
እኔ ፈዉዛን ካመንኩበት ነገር ላይ ወደኋላ ዝንፍ አላዉቅም። እንደወራጅ ዉሀ በተቀደደላቸዉ እንደሚፈሱ ከንቱ ሰዎች አሊያም ወደነፈሰበት እንደሚነፍሱ ገለባዎች አይነት አይደለሁም።

ሰዉ ነኝ!! እንቢ የማለት አቅም አለኝ። ከአስተሳሰቤ እና ከማንነቴ ጋር የሚጣረስን ነገር እምቢ ከማለት ወደኋላ አልልም። ሁሌም ቃሙ ሲሏቸዉ ገረባ ሳይቀር የሚያኝኩ ፣ ጠጡ ሲሏቸዉ ፋራ ላለመባል አተላ የሚጋቱ ፣ አጭሱ ሲሏቸዉ ከማን አንሼ ብለዉ ኦ በጭስ ለመስራት አይናቸዉ ተጎልጉሎ እስከሚወጣ የሚያጨሱ ምስኪን፣ እንቢ የማለት ወኔያቸዉ የተሰለበ ፣ የመጣዉ ጎርፍ ሁሉ እያላጋ የሚወስዳቸዉ፣

የማንነታቸዉን ልዕልና ያላከበሩ ሰዎች ያሳዝኑኛል። በእንደዚህ አይነት ሰዎች መካከልም ተከብቤ እነሱ የመጣዉ ጎርፍ ሁላ ሲያላጋቸዉ እኔ በፅናት ቆሜ አዉቃለሁ። ለዛ ነዉ በድፍረት እንቢ የማለት አቅም አለኝ የምለዉ።
.
በተማርኩባቸዉ ትምህርት ቤቶች ዉስጥ ሁሉ ዝነኛ ነበርኩ። የትምህርት ቤት ክበባት ውስጥ መሳተፍ አዘወትር ነበር።

ስነፅሁፍ እወዳለሁ። አንዳንዴ እሞነጫጭራለሁ ብዙ ጊዜ ግን የሌሎችን የስነ ፅሁፍ ስራዎች መድረክ ላይ ማቅረብ ይዋጣልኝ ነበር። እናም ከዚህ ስብዕናዬ ጋር ብዙ ጓደኞችን አፍርቻለሁ።

ብሩክ እና ሄኖክ የልጅነት ጓደኞቼ ናቸዉ። ከብሩክ እና ሄኖክ ጋር የተዋወቅነዉ የአምስተኛ ክፍል ተማሪዎች ሆነን ነዉ። አንድ ትምህርት ቤት ከመማራችን በዘለለ ሰፈራችንም አንድ ነበር። ብሩክ በአቋራጭ የሚከብርበትን መንገድ ዘወትር የሚያስብ አይነት ሰዉ ነዉ። የሰዉ ታሪክ ማዳመጥ ይወዳል በተለይ የፍቅር ታሪክ። አንድ ሰዉ የፍቅር ግንኙነት ዉስጥ ገብቶ ካገኘዉ ልምድ ሊያወራ ከሚችለዉ በላይ ብሩክ የፍቅር ግንኙነት ዉስጥ ለመግባት ከመፈለጉ የተነሳ ብዙ ይቀባጥራል።

እኔ ከብሩክ ጋር የምካፈለዉ የህይወቴ ጎን የፍቅር ህይወቴን ነዉ። ማዳመጥ ስለሚፈልግ እነግረዋለሁ።

ሄኖክ ደግሞ ቀላ ያለ አጭር ቁመት ያለዉ ሚስኪን ልጅ ነዉ። መልካም ልብ አለዉ። ወደ መልካም ነገር የሚጠራዉ ሰዉ ካለ ሁሌም መልካም ለማድረግ ዝግጁ ነዉ። ነገር ግን የኔ የሚለዉ አቋም የለዉም። እኔ ጋር ሲመጣ ከኔ ጋር ያነባል ፣ ከብሩክ ጋር ሲሆን ደግሞ ከሱ ጋር ለመመሳሰል ይሞክራል። ከጊዜያት በኋላ ሄኖክ ሰፈር ቀይሮ ከኛ ሰፈር ትንሽ ራቅ ወዳለ ቦታ ስለሄደ ግንኙነታችን እየቀዘቀዘ መጣ። በአንፃሩ ደግሞ ከብሩክ ጋር በጣም እየተቀራረብን ሄድን። ቀናት ቀናትን እየወለዱ ወራት ከወራት ጋር እየተጋቡ ይኸዉ አስራ ዘጠኝ አመት አልፎኝ ወደ ሀያ ሩጫዉን ተያያዝኩት።
.
ዛሬ ዉስጤ ላይ የመሰበር ስሜት ይሰማኛል። ሁሌም ጠንካራ ነበርኩ ፣ ዛሬ ግን በህይወቴ ዉስጥ በፍፁም ሊከሰት ይችላል ብዬ የማልጠብቀዉ ነገር ተከስቷል። ዉስጤ የመሰበር ስሜት ይሰማኛል። ለካ የኛ ያልናቸዉ ሰዎች የእምነት ባንዲራችንን ቀድደዉ በተቃራኒ ወገን በኩል ሲሰለፉ ፣ ያመናቸዉን ልባችንን ፊት ሲነሱ ፣ ያጎረሷቸዉን እጆቻችንን ሲነክሱ በጣም ያማል።

ህመሙ የልብ ምታችንን ከወትሮዉ በተለየ እንዲመታ ሲያስገድደዉ ፣ አይናችንን ከእንቅልፍ ጋር ሲያጣላዉ ፣ ስሜቱን መግለፅ ሲከብደን ፣ በደፈናዉ ስብራት እንለዋለን። አዎን ሁሉም ቀጥ ብሎ የቆመዉ የህይወት መዘዉራችን ሲናጋ ፣ ምንም ባይገልፀዉም እንኳ መሰበር እንለዋለን።

አዎ ዛሬ እኔም ተሰብሬያለሁ። የስብራቴ ሁሉ ምንጭ ደግሞ ከክብር ዙፋኔ ወርጄ አብሬያት የተጫወትኩት ፣ ለማንም ያላረከስኩትን እኔነቴን ያረከስኩላት የህይወቴ ትልቋ ደስታ፣ ስህተት እና ስብራት ኢክራም ናት።
ኢክራም ቆንጆዋ!! ኢክራም ሀዘንተኛዋ!! ኢክራም አፍቃሪዋ!!

                 አላለቀም
...

ቶሎ ይቀጥላል ግን ከወደዱት Like ይጫኑ
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
⚫️አኩርፋ ሲያያት
ምን ሆነሽ ነው ብሎ ጠየቃት
እቀፈኝና እነግርሀለው አለችው

አቀፋት..🫂

እሷ ህመሟን ረሳችው
እሱም ሳይጠይቃት ረሳው ..♡
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
የሽቶን እቃ መስበር ሽቶውን በደንብ እንድታሸቱት ያርጋቹሀል

ነገር ግን ለመጨረሻ ጊዜ ነው ሚሆነው 🙅‍♀️


የማወራው ስለ ሽቶ አይደለም
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
💥📚ኢትዮ-ልቦለድ📚📖💥
Photo
.              ●●●ነጠብጣብ●●●♥️

            💞እውነተኛ እና አስተማሪ ታሪክ💞

ይሄን ታሪክ በጣም አስተማሪ ምርጥ ታሪክ ነው ያልጀመራችሁት አሁን ጀምሩት

                          
#ክፍል_2

...🖊ዉስጤ ላይ የሚሰማኝን የመሰበር ስሜት ለማስታመም ሰፈራችን ዉስጥ ወደሚገኘዉ ጭር ያለ ካፌ ሄድኩ።

ካፌዉ ሰዉ ስለማይበዛበት ጥንዶች ይመርጡታል። እኔ ካለሁበት ጠረጴዛ ፊት ለፊት ጥንዶች ተቀምጠዉ ያወጋሉ። እሱ ይቀልዳል እሷ ትስቃለች ፣ ፀጉሯ አይኗን ሲሸፍናት እሱ ወዲያዉ በጣቱ ፀጉሯን ወደኋላ ይመልስላታል።

አይን ለአይን እየተያዩ ይስቃሉ። ስናፈቅር አለም ሁሉ እጃችን ላይ ያለች ትመስለናለች። የኛ አለም ባፈቀርነዉ ሰዉ ህይወት ዉስጥ ይገደባል። ሀዘናችን ያፈቀርነዉ ሰዉ ሀዘን ይሆናል። ደስታችን ያፈቀርነዉ ሰዉ ደስታ ይሆናል። መለማመዳችን የህይወት መዘዉራችን የአንዳችን በአንዳችን ላይ የተደጋገፈ እንዲሆን ስለሚያደርግ አንዳችን ያለ አንዳችን ጎዶሎ እንደሆንን ይሰማናል። አንዳንዴ ደግሞ ከእዉነት ጋር እንከዳዳለን።

ከወደድናት ልጅ የሚበልጡ ቆንጆ ሴቶች ሞልተዉ እኛ ግን አፋችንን ሞልተን ከሷ ሌላ ዉብ ከየት መጥቶ እንላለን። ይህ ከፍቅራችን የሚመነጨዉ ስሜት ላፈቀርነዉ ሰዉ የመልአክነት ዘዉድ ይጭንለታል። ሲሳሳት ስህተቱ አይታየንም። ፍቅር የአእምሮን ምክንያታዊ አስተሳሰብ የሚያደነዝዝ እፅ ሳይሆን አይቀርም።
.
ከፊት ለፊቴ የተቀመጡት ጥንዶች አሁንም ይሳሳቃሉ። 'ምን እየተባባሉ ይሆን?' ብዬ አስባለሁ። ምናልባት እሱ "ካንቺ ዉጪ ሴት ምድር ላይ አለ እንዴ?" ይላታል ለሱ ከሷ ሌላ ማንም እንደማይጥመዉ ለመግለፅ።

እሷ ደግሞ ኩራተኛ ናት እንዳትባልም እሱንም እግረመንገዷን ለማሞገስ "ኧረ ያንተም እናት አሉ።" ትለዋለች ከዛ ሁለቱም በአንዴ ካካካካካ ብለዉ ይስቃሉ።
አሊያም እሷ "ፈጣሪ ግን አንተን መጥላት የሚችል አንጀት ፈጥሯል?" ስትለዉ እሱ ደግሞ "የአንቺን ዉበት የሚክድ አንደበት ፈጥሮ እንደሆን ምናልባት እኔንም የሚጠላ አንጀት ፈጥሮ ይሆናል።" እያላትም ሊሆን ይችላል የሚሳሳቁት። በጤነኛ አእምሮ ካሰብነዉ እኮ ምንም አያስቅም። በፍቅር የሚሉት ጉድ ዉስጥ ስንሰምጥ ግን የማያስቀዉ ያስቀናል።

ስናፈቅር እኮ የቃላት አደራደራችን እራሱ እንዴት እንደሚያምር። ስነ ፅሁፍ በዞረበት ዞሮ የማያዉቀዉ ራሱ እልም ያለ የስነ ፅሁፍ ሰዉ ይሆናል። ከሌሎች የስነ ፅሁፍ ባለሙያዎች የሚለየዉ እሱ ያፈቀራትን ሴት ለማሞገስ ቃላትን ሲያስዉብ ፣ ሌሎቹ ደግሞ የማትታወቅ ዉብ እንስትን ለመፍጠር አእምሯቸዉን ማስጨነቃቸዉ ነዉ።

አሁንም ከፊት ለፊቴ የሚሳሳቁትን ጥንዶች እየተመለከትኩ "ምን እየተባባሉ ይሆን የሚሳሳቁት?" እላለሁ። ምናልባት የሚያስቅ ነገርም ላይሆን ይችላል የሚያወሩት ግን አብረዉ መሆናቸዉ የፈጠረባቸዉ ስሜት በራሱ እንደጅል እያሳቃቸዉ ይሆናል። አዉቀዋለሁ ስሜቱን!!
.
የእነሱን የዛሬ ደስታ እያየሁ የራሴን ስብራት አስባለሁ። ዛሬ የተገኘሁበት ካፌ ዉስጥ የዛሬን አያድርገዉና እኔም እንደነዚሁ ጥንዶች ግጣሜ ትመስለኝ ከነበረች ሴት ጋር እመላለስ ነበር።

አዎን ሊያዉም መቼም የምለያት ከማትመስለኝ ቆንጆ ሴት ጋር ነበር ምመላለሰዉ። ስሟ ኢክራም ይባላል። ረዘም ያለች ናት። ፊቷ ቀላ ያለ ነዉ። አይኖቿ ጠበብ ብለዉ በጣም ያምራሉ።

ከንፈሯ ቆንጆ እንደሆነ ያወቅኩት ጓደኛዬ ብሩክ ከነገረኝ በኋላ ነበር። ምናልባት እኔ ያላየሁት የከንፈሯ ዉበት ለጓደኛዬ ለብሩክ እንዴት እንደታየዉ ፈጣሪ ነዉ የሚያዉቀዉ። እኔ ለሷ ከነበረኝ ፍቅር ይልቅ እዝነቴ ይገዝፍ እንደነበር ያወቅኩት አሁን ከተለያየን በኋላ ነዉ።

የህይወቷን እያንዳንዷን ገመና አዉቅ ስለነበር በጣም አዝንላታለሁ። አብረን መንገድ ላይ ስንራመድ እንኳ እንቅፋት ነካ ሲያደርጋት ልቤ ተገንጥሎ እስከሚወድቅ ድረስ ነበር የምደነግጠዉ። በጣም ታሳሳኝ ነበር። ሰዉ ግን ለሰዉ ይሄን ያህል ይሳሳል? የኔ የተለየ ነበር። እወዳት ነበር። ዉዴታዬ ሙሉ ለሙሉ የተገነባዉ ደግሞ ለሷ ከነበረኝ እዝነት ነበር።
.
እንደምታፈቅረኝ ሁሌም ትነግረኝ ነበር። እኔ ለሷ ካለኝ ፍቅር ፣ እሷ ለኔ ያላት ፍቅር እንደሚበልጥ ታወራልኛለች።

አዎን እነዛን ውብ አይኖቿን እያስለመለመች "ፈዊዬ አንተ ታፈቅረኛለህ ግን የኔ ድመት እኔ ላንተ ያለኝ ፍቅር ካንተ በጣኣኣኣም ይልቃል።" ትለኛለች። የፍቅሯን ደረጃ ሰማይ ይገልፀዉ ይመስል ወደሰማይ አይኖቿን እየሰቀለች። እኔም "አንቺ ከኔ በላይ እንደምታፈቅሪኝ አዉቃለሁ።" እላት ነበር።

ይሄ ግን ለሷ ያለኝን ታላቅ የእምነት ደረጃ የሚያሳይ ነበር። ይህ እምነቴ የመነጨዉ ደግሞ ለሷ ካለኝ ጥልቅ ፍቅር ነበር። በሰዓቱ እሷ ይሄን ስሜቴን ተረድታዉ ይሁን አይሁን አላዉቅም። እንደምታፈቅሪኝ አምናለሁ ከማለት በላይ የእምነት ደረጃ ፣ ከእምነት ጥግ በላይ ደግሞ የመዉደድ ልኬት እንደሌለ ይግባት አይግባት አላዉቅም።

በነገራችን ላይ የኔ ድመት የምትለኝ ወተት በጣም ስለምወድ ነዉ። እሷ ደግሞ ቸኮሌት ነብሷ ነዉ።
.
ትዝታዎቼ እጅጉን አዲስ ናቸዉ፤አላረጁም። የኢክሩ ጅልባብ መሬት እየጠረገ ፣ የጅልባቡን እጄታ በእጇ ይዛ ፣ በጥርሷ ጅልባቡን ነክሳ እያየችኝ የሳቀችበት ቀን አሁን እንደተከወነ ድርጊት ጥርት ብሎ ትዝ ይለኛል።

ኢክሩ ግጥም አትወድም ፣ እንደዉም የሆነ ጥፋት ካጠፋች መቀጮዉ ግጥም እኔ ሳነብ ማዳመጥ ነበር። ኢክሩን አጥፍታ አንበርክኬያት አዉቃለሁ። ኢክሩን ተንበርክካ ማየት በራሱ ሀሴት ይሰጣል። ከኢክሩ ሌላዉ የሚጣፍጠኝ ነገር 'ደ' የሚለዉን ፊደል በስርዓት ማለት አትችልም። 'ደ' ስትል ስሰማት ጉረሳት ጉረሳት ነበር የሚለኝ። ግን ማን ይሄ ሁሉ ነገር ነበር ይሆናል ብሎ አሰበ? ማንም!!
.
ዛሬም ከዚህ ሁሉ ስብራቴ ጋር ለኔ የነበራትን እንክብካቤ እና አክብሮት አልክድም። ሰዉ የራሱ መልካም ጎን እንዳለዉ ሁሉ ደካማ ጎንም ይኖረዋል። ገና ለገና ዛሬ ተለያየን ተብሎ የሰዉን ስም አተላ መቀባት አግባብ ነዉ ብዬ አላምንም። ኢክሩ አብረን እያለን ለኔ መልካም ነበረች።

                 ይቀጥላል
...

እኔ ሺ ፊደል ተጫንኩ እናተስ 👍👍

✅️@ethioleboled
✅️✅️
@ethioleboled
        
━━━━━━━✦🌹🌹✦━━━━━━━
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
(😢አሳዛኝ ታሪክ)

አንዲት ሴት ለፍቅረኛዋ ያለእሷ አንድ ቀን እንዲኖር challenge ትጠይቀዋለች፣ ምንም ሳያወሩ ሳይገናኙ ቀኑን ካሳለፈ ለዘላለም እንደምታፈቅረው ትነግረዋለች እሱም ይስማማል።

በቀጣዩ ቀን ፍቅረኛዋ ቀኑን ሙሉ መልእክት ሳይልክ ሳይደውል ዋለ ግን ያላወቀው ነገር ቢኖር ፍቅረኛው በካንሰር በሽታ ምክንያት ለመሞት 24 ሰአታት ብቻ ነበር የቀራት
በቀጣዩ ቀን ልጁ ወደፍቅረኛው ቤት ሄደ
"አደረኩት የኔ ፍቅር🥰" አለ ግን ከመቀፅበት ከአይኖቹ የእንባ ዘለላዎች ወረዱ ምክንያቱም ፍቅረኛው በሬሳ ሳጥን ውስጥ ነበረች😔 ለመጨረሻ ጊዜ የፃፈችለት ደብዳቤ ይህ ነበር....." አደረከው ፍቅሬ በል አሁን ሁልቀን አድርገው   እወድሀለውእሺ የሚል ነበር"❤️
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
. ♥️●●●#ነጠብጣብ●●

#ክፍል_3
...🖊ሰዉ የራሱ መልካም ጎን እንዳለዉ ሁሉ ደካማ ጎንም ይኖረዋል። ገና ለገና ዛሬ ተለያየን ተብሎ የሰዉን ስም አተላ መቀባት አግባብ ነዉ ብዬ አላምንም። ኢክሩ አብረን እያለን ለኔ መልካም ነበረች።
.
አስተናጋጇ ፊቴ መጥታ ቆመች ፈገግ ብላ "ፈዉዛን ሳፊዉ!!" አለችኝ። ስሟ ረሂማ ነዉ። ከኢክራም ጋር እዚህ ቤት ስንመላለስ ሁሌም የምታስተናግደን እሷ ነበረች። "ፈዉዛን ሳፊዉ!!" ያለችኝ ወተት በሳፊ ስለምጠጣ መሆኑ አንዱ ምክንያቱ ነዉ። ሰሞኑን ግን ይሄን ቃል የምትጠቀመዉ ብቻዬን ስለምመጣ ነዉ። ያዉ ወተት ሳፊ ሲሆን ያለቡና ብቻዉን አይደል የሚቀርበዉ።
ጨዋታዋ ደስ ስለሚለኝ ምንም ጥሩ ስሜት ላይ ባልሆንም ፈገግ ብዬ "ወዬ ረሂማ ኮካ" አልኳት።ሳቋ ወዲያዉ ወዲያዉ ቡፍ ስለሚል ነዉ ኮካ የምላት።

"ከወተት ሌላ ምትፈልገዉ ነገር አለ?" አለችኝ። ምን እንደምጠጣ በደንብ ታዉቃለች።

"ወተት ብቻ አምጭልኝ ኮካዬ"አልኳት እየሳቅኩ። ምላሷን አዉጥታብኝ ወተቱን ልታመጣ ሄደች። በነገራችን ላይ ከአስተናጋጆች ጋር እንደዚህ ያለ ወዳጃዊ ግንኙነት መመስረት ደስ ይለኛል።ካፌ ብቻ ሳይሆን የትም ስሄድ ፊቴን ከመከስከስ ይልቅ ፈታ ብዬ እየተጫወትኩ ከሰዎቹ ጋር መግባባት ያስደስተኛል። ተጫዋችማ ነበርኩ ኢክሩ ያደረገችኝ ነገር የሆነ አዚማም አደረገኝ እንጂ
ከኢክሩ ጋር የተዋወቅንበት መንገድ ትንሽ ለየት ይላል። ፈጣሪ እራሱ ተዋወቁ ብሎ ሜዳዉንም ፈረሱንም እንካችሁ እንደማለት ነበር ያመቻቸልን

ከኢክሩ ጋር እንዴት እንደተዋወቅን በደንብ አስታዉሳለሁ!አዎ በደንብ!!
ቀኑ ጁምዓ(አርብ) ቀን ነበር!ከኢክራም ጋር የተገናኘነዉ የዛሬ ሁለት ዓመት እኔ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተናዬን ለመዉሰድ ስዘጋጅ እሷ ደግሞ የመሰናዶ ትምህርት ቤት መግቢያ ፈተና ለመዉሰድ ስትዘጋጅ ነበር።

ይህቺን ዉብ ፈጣሪ ሲያንቀለቅል ታክሲ ዉስጥ ይዞልኝ መጣ። ታክሲዉ ዉስጥ ብቻም አይደለም! ከታክሲዉምእኔ የተቀመጥኩበት የመጨረሻዉ ወንበር ላይ በመካከላችን አንድ ሰዉ ብቻ እስከሚኖር ድረስ አቀራርቦ አስቀመጠልኝ።

በመካከላችን አንድ ሰዉ መኖሩ ፈጣሪ "አንተም የድርሻህን ያህል ጣር እንጂ" ሊለኝ ያደረገዉ ነበር የመሰለኝ።እኔም እሷም ከትምህርት ቤት እየተመለስን ነበር።እሷ የምትማርበት ትምህርት ቤት እኔ ከአራተኛ ክፍል እስከ አስረኛ ክፍል የተማርኩበት ትምህርት ቤት ነዉ። የለበሰችዉን ዩኒፎርም ስመለከት በትምህርት ቤቱ ያሳለፍኩት ትዝታ ወለል ብሎ ይታየኝ ጀመር።

ታክሲዉ ዉስጥ የሷን አይነት ዩኒፎርም የለበሱ ተማሪዎች ነበሩ። ከነሱ ጋር የመምህራንን ስም እና ባህሪ እየነገርኳቸዉ ስንሳሳቅ እሷም እየሰረቀች ስታየኝ ተመለከትኩ።

ጥሎብኝ ሴት ቀድማ ሳታናግረኝ አላዋራም።ለራሴ ዋጋ ስለምሰጥ ነዉ መሰለኝ ለማንም መርከስ አልፈልግም። የዛን ቀን ግን እየተሽኮረመመች ስትመለከተኝ ሳይ ወዲያዉ ፊቴን ወደሷ አዙሬ እርግጠኛነት በተሞላበት ስሜት "አንቺ የሆነ ቦታ ታዉቂኛለሽ።" አልኳት።እሷም አሁንም ከሳቋ ጋር እየታገለች በአዎንታ ጭንቅላቷን ነቀነቀችልኝ።በሁለታችን መካከል የነበረችዉ ልጅ "በሉ ልውጣላችሁ" ብላ ከታክሲዉ ወረደች።

የመዉረጃ ቦታዋ ደርሶ ይሁን የወረደችዉ አሊያም የኛን የማዉራት ፍላጎት ተረድታ አላወቅኩምብቻ ለትዉዉቃችን አስተዋፅዖ አበርክታለች። ግን ምናለ ልጅቷ ከመካከላችን ባልወጣች እና እኔና ኢክሩ ሳንተዋወቅ በቀረን ከነዉበቷም ከነፈገግታዋም ስብራቴ መሆኗ ላይቀር ምናለ ባላወቅኳት።
ልጅቷ ከመካከላችን እንደወጣች ኢክራምን የት እንደምታዉቀኝ ጠየቅኳት። መስጂድ የሚዘጋጁ ዝግጅቶች ላይ መድረክ ስመራ እንደምታዉቀኝ ነገረችኝ።
.
በትርፍ ሰዓቴ መስጂድ ዉስጥ የስነ ፅሁፍ ስራዎችን እሰራለሁ። በእስልምና ሀይማኖት መሰረት የወንዶች መስገጃ ቦታ እና የሴቶች መስገጃ ቦታ የተለያየ ቦታ ላይ ነዉ የሚሆነዉ።እኔ ኢክራምን ከዛ ቀን በፊት አላዉቃትም ነበር። መስጂድ ነዉ የማዉቅህ ስትለኝ ወዲያዉ አደብ ያዝኩ!! የተከበረ ቦታ ላይ ታዉቄማ እዚህ አልረክስም አልኩ በልቤ።

ግን ወዲያዉ የጓደኛዬ የአዩብ ፍቅረኛ ሪም ትዝ አለችኝ እና ታዉቃት ከሆነ ብዬ ጠየቅኳት። በጣም የቅርብ ጓደኛዋ እንደሆነች ነገረችኝ። ለማንኛዉም ከሷ ጋር የሚተዋወቁ ከሆነ የእኔ እና የእሷ ነገር እንዳለቀለት አሰብኩ።አዩብ እና ሪም ሲኮራረፉ ሁሌም እኔ ነበርኩ የማስታርቃቸዉ። ሪም ቀርባ ሳታዉቀኝ በጣም ትጠላኝ ነበር። ስንቀራረብ ግን በጣም ወደደችኝ።አዩቤ ደግሞ ቁጡ ስለሆነ ሲጣሉ ለማረጋጋት ግዴታ እኔ መግባት አለብኝ።ስለፍቅር ህይወት እኮ ምንም አላዉቅም ግን እንደ ቀበሌ ሹም በባዶ ገብቼ እለምድባቸዉ ነበር።
ኢክራም ስሜን እንደምታዉቀዉ ብገምትም ለወጉ ያክል ፈገግ ብዬ "እንተዋወቅ ፈዉዛን እባላለሁ" አልኳት። አይኖቿን በሀፍረት ሰበር እያደረገች "ኢክራም እባላለሁ" አለችኝ።

የመዉረጃ ቦታዋ ከኔ ትንሽ ይቀድም ስለነበር ቀድማኝ ወረደች።የዛን ቀን ከለበሰችዉ ዩኒፎርም ላይ ጥቁር ሰማያዊ ጅልባብ ለብሳ ነበር። ጅልባብ ማለት በአብዛኛዉ ሙስሊም ሴቶች የሚያዘወትሩት እጅንና ፊትን ብቻ የሚያሳይ ሰፊ ልብስ ነዉ።
ከወረደች በኋላ ስልኳን እንዳልተቀበልኳት አስታወስኩ።

ኩራቴ ተናንቆኝ ነዉ? ለምን ስልኳን አልተቀበልኳትም? አዎን ገባኝ የሪም ጓደኛ ነኝ ስላለችኝ ነዉ ስልኳን ያልተቀበልኳት።የሪም ጓደኛ ከሆነች እኔና ሪም በጣም ስለምንግባባ ስልኳን በቀላሉ ማግኘት እንደምችል ስላሰብኩ ነዉ ዝም ያልኳት
.
የዛን ቀን ታክሲ ዉስጥ ኢክራምን ሳወራት የነበራት አይነአፋርነት አሁን ላሉት አይንአዉጣ ሴቶች እና ለአሁን እሷነቷም ጭምር ቢታደል ይበቃ ነበር። የሆነ ከአይናፋርነትም ቀልብ የሚገዛ አይናፋርነት አለ እኮ የእዉነት!! የተመጠነ በዉስጡ ትህትናን እና አክብሮትን ያዘለ አይናፋርነት
ከተለያየን በኋላ ቤት ገብቼ አረፍ አልኩ።

ግን አሁንም የማስበዉ ዛሬ ታክሲ ዉስጥ ስለተዋወቅኳት ቆንጆ ልጅ ነበር። አይናፋርነቷ ፣ፈገግታዋ ሁሉ ትዝ እያለኝ ብቻዬን ፈገግ አልኩ። ወዲያዉ ራሴን አረጋጋሁት ምንድነዉ ስለማላዉቃት ሴት ማሰብ?በሰዓቱ እኔ የአስራሁለተኛ ክፍል ተማሪ ነኝ። ሀይማኖታዊ መድረኮችን መርቼ ከወረድኩ በኋላ በራሱ የሴቶቹ የፌስቡክ እና የስልክ መልዕክቶች ፈተና ነበር የሚሆኑብኝ።አንዳንዴ ፍላጎታችን ተመሳሳይ ሆኖ ግን የፍላጎታችንን ለማግኘት የተለያየ ቦታ እንሄዳለን።

አንዳንድ ሴቶች ሀይማኖታዊ መድረኮች ላይ የሚታዩ ወንዶችን ለመጥበስ በየዝግጅቶቹ ላይ ይገኛሉ። አሁን ላይ እኮ ሁላችንም የመጥበስ መልዕክተኞች ሆነናል።በየትምህርት ቤቱ በየሄድንበት ሁሉ!!ሀይማኖት ቦታ ላይ ያለዉ አጠገቡ ያለችዉን ይጠብሳል ወይ ትጠብሰዋለች።ይሄ ደግሞ ሁሉም ሀይማኖት ላይ ያስተዋልኩት ሀቅ ነዉ።እኔም ብዙ ጊዜ እንደዚህ ያሉ ነገሮች ገጥመዉኛል ግን ፊት አልሰጠኋቸዉም።

በየጊዜዉ የማላዉቃቸዉ ሴቶች ልብ የሚያቀልጡ መልዕክቶችን ፌስቡክ ላይ ይልኩልኛል።እኔ ግን ብዙም ግድ አይሰጠኝም ነበር።ታዲያ ቆይ ዛሬ ምን ተገኝቶ ነዉ ስለማላዉቃት ሴት የማስበዉ? ገርሞኛል።ቀልቤን ስርዓት ማስያዝ አለብኝ።
.
ሁሌም ከትምህርት ስመለስ እንደማደርገዉ አልጋ ላይ ተዘርሬ ፌስቡክ ላይ የምከታተላቸዉን ተከታታይ ፅሁፎች ማንበብ ጀመርኩ። ሲመሻሽ የማላዉቀዉ ስልክ ተደወለልኝ።አነሳሁት


ሳነሳዉ ሪም እየተፍለቀለቀች"ፈዊ ግን ኢክሩን ምን አስነክተሀት ነዉ? ቅድም ካገኘኋት ጀምሮ ስላንተ ነዉ የምታወራልኝ።" አለችኝ። ከሪም ድምፅ ጀርባ ኢክራም እንድትዘጋዉ ስትማፀናት ይሰማኛል።
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
ልክ ነበርኩ የሪም ጓደኛ ከሆነች የኔና የሷ ነገር አልቆለታል አላልኳችሁም ነበር? እየሳቅኩኝ "እስኪ እድል ስጫት ታናግረኝ" አልኳት። "ኧረ ፈዋ ልትገለኝ ምንም አልቀራትም፣ አሁን በመካከላችን መኪና ገብቶ ነዉ የማወራህ" አለችኝ። የሪም ስራ እያሳቀኝ "ይሄ የሷ ስልክ ነዉ?" አልኳት። "አዎ ፈዋዬ ቆጥበህ ተጠቀመዉ።" ብላኝ እየተፍለቀለች ስልኩን ዘጋችዉ።

ይቀጥላል
...

ቶሎ ይቀጥላል ግን ከወደዱት Like ይጫኑ
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
2024/09/21 05:30:42
Back to Top
HTML Embed Code: