Telegram Web Link
አለም በእሱ ዛቢያ የምትሸከረከር ይመስለዋል ፤ በዙሪያው ያለነውን ሰዎች የፊት ገፅታ እንደዋዛ አይመለከትም ፤ ይተነትነዋል ፤ እይታው ደግሞ ያስደምማል ፤ በዙሪያው ያለነው እራሳችን   አስተውለነው የማናውቀውን እንቅስቃሴ ሳይቀር ያስተውለዋል ።

በጊዜ ብዛት ተወዳጀን ፤ ጥንቅቅ ያለ ልጅ ነው ፤
በህይወት ቀልድ አላውቅም ይላል ፤ ጠንካራ ሰራተኛም ነው ።

ምንም እንደዋዛ የሚቆጥረው ነገር የለም ፤ ጥንቁቅ ነው ፤ አመንኩበት የሚለውን ለማንም በቀላሉ አያጋራም ፤ አስር ግዜ የግራ ቅንድቡን በሌባ ጣቱ ልብስ ማድረግ ለምዶበታል  ።

የበለጠ በቀረብኩት ቁጥር የበለጠ ስጉነቱ ታዋቀኝ ፤ በዙሪያችን ያሉትን ሰዎች እንከን ያሳየኛል እኔ ደግሞ አይ አይመስለኝም እለዋለሁ ፤ በሌላ ቀን በዙሪያዬ ያሉትን ሰዎች እንከን በነገረኝ መሰረት ማስተዋል ስጀምር ትክክለኝነቱ አስደመመኝ ።

እራሴን ጠይቄው የማላውቀውን ጥያቄ ይጠይቀኝ እና ካልመለስኩለት የደበቅኩት ይመስለዋል ፤ ለራሴ ደግሜ የማልነግረውን  ቅሬታዎችን መንገር ጀመርኩ ፤ የህይወት ስጋቶቹን ባጋራኝ ቁጥር ስጋት ነው እያለ ሲጠቁመኝ ሳስተያየው በህይወቱ ውስጥ የሚፈራቸውን ነገሮች እኔም የምፈራቸው ነገሮች ሆኑ ።

ፍርሃቱን አጋባብኝ ፤ ስላለው ነገር ስለማያሰላስል ስላለኝ ነገር ማገናዘብ አልቻል አለኝ ፤ ከበጎ ነገር መጥፎ ነገር በፍጥነት ይገባል መሰለኝ እሮሮ ላይ አስከተመኝ ።

ስነቃ

ቀስ እያልኩ ስጉ ፤ ቀስ እያልኩ ሁሉን ነገር በቁም ነገር የምወስድ ፤ ቀስ እያልኩ በዙሪያዬ ባሉ ሰዎች እንከን ላይ እየተመሰጥኩ ፤ ቀስ እያልኩ እንከኔ ላይ ብቻ የከተምኩ ልጅ እየሆንኩ ጠንካራ መስዬ የምታየው ስነልቦናው የቆሳሰለ ልጅ መሆኔ ትንሽ ዘግይቶ ተገለፀልኝ ።

እራሴን መጥላት ሊጀማምረኝ ሲል ነው የነቃሁት ስልኬን ዘጋሁ ለአስር ቀን ፀሎት ላይ ፣ ፀበል ላይ ፣ ተፈጥሮ ጋር ከተምኩ

የችግሬ  ወላጅ አባት ወዳጄ መሆኑን ለማወቅ ስነቃ ፋታ አልወሰደብኝም ። 

ወዳጄን ካለ ርህራሄ ዘጋሁት ፤ መቀየር ከማንችለው ሃይል ጋ መታገል ብክነት አይደለምን? !

ለራሳችን በበቂ ያሳመነንን እውነት የማናብራራበት  ወቅት ጥቂት አይደለም።

ሸሸሁት...!

ጨለማውን መግፈፍ  እስካልተቻለው  ድረስ ብርሃን ከጨለማ ጋር ምን ህብረት አለው ??
ምንም  እራሱን ከማጨለም በቀር !!

          
<<እንደሚወደኝ አልነገረኝም አለች አሉ >>

ውሸቷን ነው እንደምወዳት ነገርያታለሁ ።

<አልነገርካትም >

ነግሬያታለሁ !

መቼ ? የት ነው የነገርካት ? አለቺኝ ጓደኛዋ ናት

በርግጥ እወድሻለሁ አላልኳትም ። ከእወድሻለሁ ቃል እንደምወዳት ማሳየት አይበልጥም ??

ከቃል ተግባር አይረቅም? ?

ምኔን ሰስቼባት አውቃለሁ ፣ላግኝህ ብላኝ ሳይመቸኝ ቀርቶ ያውቃል ? አይበሉባዋን እንደንግስት አይደል የምስማት ። እሷ ጋ ስሆን ደስ እንደሚለኝ አታውቅም ? ሳወራት እንምወዳት ድምፄ አያስታውቅም ? አብርያት ስሄድ አካሄዴ አልነገራትም ?

ሴት ነች ይሄን ማየት አያቅታትም !!

መውደዴ አይኔ ላይ አስተቃቀፌ ላይ መፈለጌ ላይ አላየችውም ?

የውነት ነው የወደድኳት ። አወዳደዴ ሁሉ ነገሬ ላይ ይታያል ተግባር ደሞ ከቃል ይበልጣል ተግባር ያልታየው ቃል አያሳምነውም ።

I think መውደዴ ግድ አልሰጣትም
!!
Mndnaw share react yalam enda


@Meki3
✅️✅️ስሜታችንን የሚወስነው ምንድነው?
======================
አንድ ፈረሰኛ እየጋለበ ሲሄድ መንገድ ላይ ጓደኛው ያገኘውና "ወዴት እየሄድክ ነው?" ይለዋል። ፈረሰኛውም "እኔ አላውቅም። እሱን ጠይቀው" ብሎ ወደ ፈረሱ ጠቆመው። ፈረሱ ስሜቶቻችንን ይወክላል። ፍርሀታችን፣ ጭንቀታችን፣ ሀዘናችን፣ ደስታችን...ወዘተ። በህይወት ወዴት እየሄድን እንደሆነ ለመረዳት የፈረሳችንን ፀባይና እንዴት እንደምንቆጣጠረው ማወቅ አስፈላጊ ነው።

ጊዜያዊ ስሜታችንን ሁኔታዎች ሊለዋውጡት ይችላሉ። በዘለቄታ የሚኖረን ስሜት በዋናነት የሚወሰነው ግን በህይወታችን ወሳኝ ከሆኑ ሰዎች ጋር በሚኖረን ግንኙነት ነው። እነዚህ ወሳኝ ግንኙነቶች፦ በህፃንነት ከወላጆቻችን፣ ከፍ ስንል ከጓደኞች፣ ከዛ ከፍቅረኛ/የትዳር አጋር በስተመጨረሻም ከልጆች ጋር የሚኖሩ ግንኙነቶች ናቸው።

እነዚህ ግንኙነቶች ጥሩ ሲሆኑ ደስታ ይሰማናል። ግንኙነቶቹ ሲሻክሩ ጭንቀት ይፈጠራል። የሻከሩት በራሳችን ጥፋት እንደሆነ ካሰብን ፀፀት፣ ሌላኛው ሰው ጥፋተኛ እንደሆነ ካሰብን ንዴት ይሰማናል። በመጨረሻም ግንኙነቱ ከመሻከር አልፎ ሙሉ ለሙሉ ከተቋረጠ ሀዘን ይሰማናል።

የስነ ልቦናችን ጥልፍልፍ የሚከሰተው ከወላጆቻችን ጋር የነበረንና ያለን ግንኙነት አሁን ከፍቅር/ከትዳር ጓደኛ ጋር ባለን ግንኙነት ሲንፀባረቅና ሲደባለቅ ነው። ልጆች ሲጨመሩበት ደግሞ የበለጠ ይወሳሰባል።

"በዚህ ምድር ቋሚ ነገር የለም። መከራዎቻችንን ጨምሮ።" ቻርሊ ቻፕሊን



ዶ/ር ዮናስ ላቀው
አልኬሚስቱ @Bemnet_Library.pdf
27.8 MB
ርዕስ:- አልኬሚስቱ
ደራሲ:- ፓውሎ ኮዮልሆ
የገፅ ብዛት:- 172
ዘውግ፦አስተማሪ

ማጋራት መተሳሰብ ነው!
📚 @ethioleboled 📚
ያልወጣለት ፍቅር - ሲድኒ ሼልደን.pdf
23.3 MB
📖ርዕስ (ያልወጣለት ፍቅር)

✍️ደራሲ (ሲድኒ ሽልደን)

📝ተርጓሚ (ዐሊይ መህዲ)

🔍ዘውግ (ልብወለድ)

📚የገፅ ብዛት (278)

✈️ @ethioleboled
🔵ጉስቁል ያለች እናት የተቀደደ ነጭ ነጠላ ፣ ኮንጎ ጫማ ያደረገች ፣ በእጇ ማዳበርያ ነገር ያንጠለጠለች ፣ ስልል ያለን ልጅ እጁን ይዛ ከእሷ የተሻለ ጫማ አስደርጋው ፤ የሆዷን እየነገረችው እንደ ዘበት እየሰማት ሲሄዱ እንባዬ መጣ ፤ ድህነታቸው ፣ አካሄዳቸው ፣ አወራራቸው አሳዘነኝ

ዝም ብዬ በዓይኔ ሸኘኋቸው ።

የምናየው ትርጉም ባሳለፈነው መንገድ ይመረኮዛል መሰለኝ ። ሁለ ነገራቸው ሳይነግሩኝ ገባኝ። ወይ እንዲህ ናቸው ብዬ በየንኳቸው ።

ልጅነቴ ጋ ወሰዱኝ ።

እናቴ የቤት ሰራተኛ ነበረች ። አሰሪዋ አስረገዛት ፤ እኔን ከወለደቺኝ በኋላ እስከ ልጇ የሚቀጥራት ስላጣች በየቤቱ እየጠሩ እና እየዞረች ያዘዟትን መስራት ጀመረች ። እኔም ትንሽ ሳድግ በየቤቱ ፣ በየድግስ ቤቱ ፣ በየሆቴሉ ትርፍራፊ እየበላሁ ጭምር አደግኩኝ ።

እናቴ የሆነች ምስኪን ናት ። "እከሌ ጥሩ ሰው ነው" ትለኛለች ፤ ምን አደረገልሽ ስላት "ሰላምተኛዬ ነው" ትላለች። እናቴ ጥሩ ነው የምትለው ያልናቃትን ነው ። እንደው ሚዛኗ ይገርመኛል ።
ካልተናቀች ነው የምትገረም !!

ከልጆች ስጣላ አግዛልኝ አታውቅም ። እኔን ነው ተው የምትለኝ ። እናደድ ነበር
ስለማታግዝልኝ ። ለካ የምጣለው የለበሱትን ልብስ እና የተረፋቸውን ምግብ ከሚሰጡኝ ወላጅ ልጆች ጋር ነበር ።

እኛ ሰፈር በጣም ደሃ እኛ ነበርን። ማንም ምን አሉ የማይለን ፣ ለቅሶ ለነፍስ ተብሎ የምንደረስ ፤ ምንም እንደማናመጣ የምንታወቅ ። ስሜታችን እና ኩርፊያችን ከቁብ የማይቆጠርልን ነበርን ።

ትምህርትም ከዘጠኝ አቋረጥኩ ። ጋራዥ መዋል ጀመርኩ ። በሰው አይን የማንሞላ በዓለም መመዘኛ ነጋችን የጨለመ ነበርን።

ስነቃ ሳላስበው ቀስስ አድርጎ እኔን ኡ በቃ አበቃለት የተባለ መኪና ስነካው የሚሰራ አድርጎ አበጃጀኝ ። እናቴን በአንድ ልጅ አራት የልጅ ልጅ እንድታይ ፣ የልጅ ልጆቿ አያቴ ትገዛልኛለች እያሉ የሚፎክሩባት ፤ አዛኝ እንደነበረች ሲኖራት ማሳየት ተቻላት ።

ሰው አክባሪነቷ ፣ ሰላምተኛነቷ ፣ ትህትናዋን እግዜር ያውቃል ማለቷ ድህነቷ የወለደው ማንነት የሚመስለው ብዙ ነበር ። እውነተኛ ማንነቷ መሆኑን ማግኘት መሰከረላት ።

ደግነትን ለካ ሁኔታ ይሰውረዋል !

እኔንም ትላንት እንዳልታበይ እንዳልጨክን ፣ እንዳልጠግብ ሁሉን አሳይቶ አበጃጅቶኛል ።

ነገ ውስጥ ያለው ሚስጥር ከጌታችን በቀር ማንም አያውቅም ።
ADHANOM METEKU
እሺ እናንተስ እንዴት ነው የተገናኛችሁት
#2

"የእነሱን እኔ ነኝ የማወራው" አለች እሌኒ እየተቅለበለበች

"ጀመራት ደግሞ artistic ልትሆንብን" ናቲ እየተበሳጨ።

"እነሆ ሁለት ነብሶች ተያዩ፥ ጊዜ አላባከኑም አያት፤ ተመለከታት፤ ተመቸችው እናውራ አላት።

ለመግባባት ቀለሎ አገኘችው ...ተዋወቁ የሆድ የሆዳቸውን ተዘረጋገፉ።

በሰው እንዴት እንደተገፋ ነገራት ፤እሷም ስንቴ እንደተገፋች አወጋችው።

ከዛም ሁለቱም አፋቸውን ያዙ "ምናልባት ይሄኛው ቢሰራስ?" ራሳቸውን ጠየቁ።

ተቆጥበው ኖረው ነበራ፥ እንደውም ተስፋ አንደመቁረጥም ብለው ነበረ፤ ምናልባት ግጣም ሳይፈጠርልኝ ተዘልዬ ቢሆንስ?...(ትንሽም ጭንቀት....)


"ብንሞክረውስ" ወንዱ ደፍሮ ጠየቀ "ይሁና" አለች ሴቷም።
ሞከሩ ሙከራው በተሳካ ሁኔታ አለፈ.... ቀጠሉ፤ ዘለቁ።

እርስ በርስ ተካከሙ። ያውቃሉዋ የመገፋትን አስቀያሚነት፤ የባዶነትን ጥልቀት።

ከዛስ? ከዛማ ተሞላሉ ድክመታቸውን ያጡትን ብርቅ የሆነባቸውን ፍቅር ተሰጣጡ።

በቃ አታፍጡ ይኸው ነው" አለች እሌኒ አወራሯ ጥሟቸው ወደ አፏ አስግገው አይን አይኗን ሲያዩ።

"ቺርስ አባቴ እንዲ ነው እንጂ ነፍስ ስትግባባ ማለት" ሲል ሶፊ

ሁሉም "ቺርስ" አሉ በስሜት


©nani

https://www.tg-me.com/ethioleboled
ከምገልፅህ በላይ😍

💞 ያማሩ ቃላቶች የሉኝም ግን ምን ያህል እንደምወድሽ እነግርሻለሁ😘
Geography ባልችልም በልቤ ውስጥ ስላለሽ ስፍራ ልነግርሽ እችላለሁ…
history አልችልም ለመጀመሪያ ጊዜ አንቺን ያየሁባትን ቀን ግን አስታውሳለሁ…
chemistry ባይገባኝም ነገርግን ፈገግ ስትይ የሚሰማኝን reaction ልነግርሽ እችላለሁ…
በትምህርት ዘርፎች ላይ ደካማ ብሆንም የሁሉም ርዕስ አንቺን ብትሆኝ ኖሮ ሁሉንም ትምርቶች አልፍ ነበር 😘 የኔ ንግስት
💞አፈቅርሻለሁ
💞💞💞መልካም ቀን ምርጦቼ💞💞💞
Join @fetaenbeel
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
🌾🍁🍄🌿🍂🍄🌸🥀🍃🌺💐🌹
እጅግ ደጋግሜ አንብቤው ሁሌም የምወደው ፅሁፍ ነው! አንብቡትማ.......


በአንድ ወቅት ባልና ሚስት አብረው ሲኖሩ በመሀላቸው ልዩ የሆነ ፍቅር ነበራቸው።
ሁለት ልጆችም ወልደው ነበር ነገር ግን ችግር ላይ በመውደቃቸው ባል ሊሰራ ተሰማምተው ራቅ ወዳለ ከተማ ሄዶ መስራት ጀመረ

በተከታታይ ለ16 ዓመታት ሰራ ከዚያ ወደናፈቁት ቤተሰቦቹ ለመሄድ ሲነሳ ያልገመተው ነገር
ከቀጣሪዎቹ ሰማ፤ደሞዙ በተለያየ ምክንያት ተቆራርጦ ከሚጠብቀው ከግማሽ በታች የሆነው
3000 ብር ተሰጠው። የተሰጠውን ተቀብሎ እግረ መንገዱ ስራ ካገኘ እየሰራ ጠርቀም ያለ ብር ይዞ ቤተሰቦቹ ጋ ለመሄድ ተነሳ።

በመንገዱ አንድ ሸምገል ያሉ አባት አገኘ...
"ወዴት ትሄዳለህ ልጄ ከየት ነውስ ምትመጣው?" አሉት
እሱም ከመጀመርያው እስከ መጨረሻው ነገራቸው ።እሳቸውም
እንዲህ አሉት:---"እንግዲያውስ የምትፈልገውን ነገር ማግኘት ቀላል ነው እሱም እንዴት አባቴ?" ሲል ጠየቃቸው

እሳቸውም "በል አንድ ሺህ ብሩን አምጣና እነግርሀለሁ" አሉት
የቸገረው ነውና አንስቶ አንድ ሺህ ብሩን ይሰጣቸዋል።

እኒህ አባትም "አቆራጭ ነው ብለህ በማታውቀው መንገድ አትሂድ

" ይህ ምክር አንድ ነው ይሉታል።
ሁለተኛውን ሺህ አምጣና ሁለተኛውን መንገድ ልንገርህ ይሉታል። እሱም
በየዋህነት ሁለተኛውን ሺህ ይሰጣል "በማያገባህ አትግባ፤ ይሄ ደግሞ ሁለተኛው ምክሬ ነው" ይሉታል ።

"በቃ ይሄ ነው?" ቢላቸው "አዎን ልጄ ሶስተኛውን አምጣና በጣም አሰፈላጊውና
የመጨረሻውን ስጦታዬን ልስጥህ" አሉት ሰጠ።
እሳቸውም "ክፉ ለማድረግ አትቸኩል"
ብለውት በባዶ ኪሱ ከሶስቱ ምክሮች ጋር አሰናበቱት። እሱም ጉዞውን ወደ ቤቱ አደረገ ።
በመንገድ ነጋዴዎች አግኝቶ እያወጋ ሲጓዝ መሸ ነጋዴዎቹም ለምን ባቋራጭ አንሄድም
በማለት ጉዞ ጀመሩ እሱም አብሮዋቸው ጉዞ እንደጀመረ የሽማግሌው አባት ምክር አንድ ትዝ
አለው።
"አቋራጭ ነው ብለህ በማታውቀው መንገድ አትሂድ" የሚለው።
ሰለዚህ ተመልሶ በሚያወቀው መንገድ ተጉዞ ብቻውን ከጨለመ ከተማ ገባ ። "የመሸበት
እንግዳ ነኝ አሳድሩኝ" በማለት ሰው ጠየቀ።
አንድ የዛ ከተማ ሰውም "የውልህ ወንድሜ እዛ
ቤት ሂድ ያሳድርሀል፤ ነግር ግን እዛ ሰው ቤት የገባ አይወጣም ለማንኛውም እድልህን
ሞክር።" እሱም የተባለበት ቤት አንኳኩቶ ቤት የእንግዳ ነው ተብሎ ገባ ።
ታድያ ከቤቱ ባለቤት ጋር ሲያወጉ ከየት እንደመጣ ቢነግረው ባለቤቱ ተገርሞ "እንዴት ሆነክ
ተረፍክ ፧ባልከው መስመር ይመጡ የነበሩ ነጋዴች ተዘርፈው ነጋዴዎቹም ተገለው ከተማው
ለቅሶ ብቻ እኮ ነው የሆነው" አለው።
ያቺ በአንድ ሺህ ብር የገዛት ምክር በብር የማትገዛ
ህይወቱን አተረፈችለት ማለት ነው።
ሰለ መሸ የቤቱ እመቤት ምግብ ለእንግዳው ልታቀርብአመሰግናለሁ
ከጓዳ ብቅ አለች " እንግዳው አይኑን ማመን አልቻለም የተወሰነ አካሉዋ ብቻ ነው ሰው
የሚመስለው በዛ ላይ ማስፈራቷ ወደ ጓዳ እስክትገባ ናፈቀ።
"ከዚህች ጋር እንዴት ትኖራለህ?" ብሎ ሊጠይቅ ሲል አንድ ነገር ትዝ አለው

"በማያገባህ አትግባ" የሚለው
ሆዱ መጠየቅ እየፈለገ ፍላጎቱን ተቋቁሞ አደረ ።
ደግሞ ሌላ ፈተና የቤቱ ባለቤት ከመሄድህ በፊት የማሳይህ ነገር አለኝ ብሎ ወደ ጓሮ ወሰደውና የሰው አጽም የሞላበት ሜዳ አሳየው እንግዳውም "ይሄ ምንድ ነው?" ማለት ፈልጎ ነበር ግን በማያገባህ አትግባ ብሎ ራሱን እየነቀነቀ ዝም አለ ።

የቤቱ ባለቤትም ተገርሞ "በእውነት አንተ የምትገርም ሰው ነህ ይህ። የምታየው ሰው ሁሉ ሰለ ሚስቴ የማያገባቸውን አሰተያየት
ስለሰጡ የተገደሉ ናቸው፤ እንዳንተ እዚህ ቤት በእንግድነት የመጡ ነበሩ።
አንተ ግን ታላቅ ሰው ስለሆንክ የሀብቴን 1/4 ኛ ሰጥቼሀለሁና ይዘህ ትሄዳለህ" ተብሎ ባለ ብዙ ሀብት ሆኖ ወደ ቤቱ ሄደ።
እዛች ደሳሳ ጎጆ የደረሰው ከለሊቱ ስድስት ሰዓት ነበር።
ሁሉም ነገር ቢለወጥም ቤቱን ግን አላጣውም በትልቅ እንጨት የምትዘጋ በሩን ገፋ
ሲያደርጋት ተከፈተች አይኑ ግን ከማያምነው ነገር ላይ አረፈ ሚስቱ ሁለት ጎረምሶች መሀል ተኝታለች በንዴት ጦፎ ትልቅ ድንጋይ አንስቶ ወደ ውስጥ ሊገባ ሲል 3ተኛው ምክር ትዝ አለው።
"ክፉ ለማድረግ አትቸኩል" የሚለው። ከቤቱ ውጭ በተጋደመው ዛፍ ላይ ቁጭ
ብሎ አደረ።

ሚስት በጠዋት ተነስታ ደፋ ቀና ስትል ድንገት ባሏን ስታየው እልልታዋን
አቀለጠችው ዘላ ተጠመጠመችበት።
ከእንቅልፉ የነቃው ባል በመደናገጥ ሳለ እጆቹን ይዛ ወደ ቤት ገብታ ሁለቱን ጎሮምሶች አሰተዋወቀችው "ይህ የመጀመርያ ልጅህ ይህ ደግሞ ሁለተኛው" ብላ እንግዲህ
የመጨረሻው ምክር የልጆቹን ነፍስ ከማጥፋት እረዳው ማለት ነው። ሰውዬው ሶስቱ
የሽማግሌው አባት ምክሮች በደስታ ከቤተሰቡ ጋር እንዲቀላቀል አደረጉት።

1. አቋራጭ ነው ብለህ በማታውቀው መንገድ አትሂድ
2. በማያገባህ አትግባ
3. ክፉ ለማድረግ አትቸኩል

👇👇👇👇👇👇join
@ethioleboled

ለማንኛውም ጥያቄ እና አስተያየት
@Meki3
🌾🌸🍁🍄🌺🍀🌹🥀💐🌸🌼🌱🌺
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
-----------💞------------
🎁ለፍቅር ፊዳ🎁
-----------💞-------------

ክፍል አንድ

«በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ»

…ቀኑ ጁመዓ ነው ወቅቱ ደሞ ክረምቱ ሊገባደድ የደረሰበት ነው በጠዋቱ ቀኑ ጨልሟል ለመዝነብ እየዳዳው ነበር ሁሉም ጃኬት ደርቦ መጓዝን መርጧል ሚፍታህም ቡኒው ጀለቢያው ላይ እርሳሳማ ከለሩን ጃኬት ደርቦ አምሮበታል ከኮሌጅ በጥሩ ነጥብ ሲመረቅ አባቱ እንደ ስጦታ የገዙለትን መኪናውን  አስነስቶ እናቱን እና እህቶቹን ጀሞ ያለችው አክስቱ ስለወለደች አቂቃ ጠርታቸው ለመጠየቅ ስለሚሄዱ እሷ ቤት አድርሷቸው  ጁመዓን ለመስገድ ወደ በኒ መስጂድ አቀና ሚፍታህ ቀይ የፊት መልክ ያለው በአለባበሱ በአረማመዱና በፈርጣማ ሰውነቱ ወንዳወንድነቱን የሚያስመሰክር በዲኑ በትንሹም ቢሆን ጠንከር ያለ ልጅ ነው ቤተሰቦቹ ሀብታም የሚባል አይነት ኑሮ ነው ሚኖሩት እሱም ቢሆን በፋርመሲስትነት ተመርቆ የራሱን ፋርማሲ ከፍቶ እየሰራ ይገኛል ከቤተሰቦቹ እሱ የመጀመሪያ ልጅ ነው  ወንድ ልጅም እሱ ብቻ ነው እናቱ ወ/ሮ ካሚላ አባቱ ደሞ አቶ ያሲን ይባላሉ 3 እህቶች አሉት ሀፍሳ፣ሶፊያ እና ኢልሀም ይባላሉ ሀፍሳ ሁለተኛ ልጅ ስትሆን የ11 ክፍል ተማሪ ናት ሶፊያ ደሞ የ7 ክፍል ተማሪ ናት ኢልሀም ግን ገና 4 አመቷ ነው በተፈጥሮ እግሮቿ ተጠላልፎ ነው የተወለደችው ቁማ መራመድ አትችልም በዚም ሰበብ ትምርት አልገባችም ነገር ግን ውበት አላብሷታል በዚ ምድር እንደሷ ቆንጆ ያለ አይመስል የፊቷ ቅላት የቅንድቦቿ መብዛት የከንፈሯ መቅላት የአይኗ መተለቅ የፀጉራ ሉጫት ብቻ ሁሉንም ሰቷታል ቁሞ መራመድን ከለከላት እንጂ… ሚፍታህ ጁመዓን ሰግዶ ወደ አክስቱ ቤት ሄዶ እስኪወጡ ዳር ይዞ መኪና ውስጥ ተቀምጦ እየጠበቃቸው ነው በመሀል ግን  ድንገት ግን አንድ ነገር ላይ አይኑ አረፈ ፈዞ ቀረ ጥልቅ የሀሳብ በሀር ውስጥ ገባ እንዲ ያለ ውበት አይቶ ሚያቅ አልመሰለውም አንዲት ልጅ ጥቁር አባያ ለብሳ ወፍራም ጃኬት ደርባ ሸምገል ያሉ አባት አቅፈዋት እያሳቋት ከአክስቱ ቤት ሲወጡ ነበር ይሄን ውበቷን የተመለከተው ለነገሩ የሷ ውበት እሱን ብቻ አልነበረም ሚያፈዘው ያያት ሁሉ ይመሰጥባታል ከውበትም ውበት ተላብሳለች ችምችም ያለው ቅንድቧን ወጣ ወጣ ያሉት አይኖቿ ብቻ ሁሉ ነገሯ በቃላት ሊገለፅ የማይችል ውብ ነበረች እሷ ላይ እንደተመሰጠ አንዲት እናት በመስኮቱ በኩል መተው
"ልጄ እባክህ ልጄ ታማብኛለች ማሳከሚያ የለኝም እንደው ትንሽ ብር ስጠኝ"አሉት እሱም ልጅቷ ላይ ተመስጦ ስለነበር ጁመዓ ሰግዶ ሲወጣ ከባንክ ያወጣውን አስር ሺህ ብር ሳያስበው ሰጣቸው እናትየውም አመስግነው መርቀውት ሄዱ አሚን እንኳን አላላቸው ስትራመድ ዝም ብሎ እየተመለከታት ነበር ምናልባት የወደፊት ሀላሌ ትሆን አላህ ከወደደኝ እሷን አይሰጠኝም  ይሆን እያለ ያስባል ልክ አንድ መኪናውስጥ ገብተው ሲሄዱ ነበር ከሀሳቡ የነቃው አኡዙቢላሂሚነሸይጧኒረጂም ብሎ ባነነ በሰራው ስራ ኢስቲግፋር ማድረግ ጀመረ በመሀል የሰጠውን ብር አሁን ገና ልብ አለው ከመኪናው ወርዶ ቢፈልጋቸውም የሉም አላህ ሰደቃ ያርገው ብሎ ትቶ ወደ መኪናው ገብቶ ኢስቲግፋር ማድረጉን ቀጠለ ነገር ግን ከሀሳቡ ልትወጣ አልቻለችም ደጋግሞ ኢስቲግፋር ቢያረግም አሁን ፈገግታዋ መቶበት ፈገግ ያስብለዋል እናቱናእህቱ በሀሳብ ከሄደበት አባነኑት
<<ወዴት ነው ባክህ ወይስ አዲሷ ፋሪማሲ መድሀኒት የገዛችህ ናት እንዲ ወንድሜን ብውው አርጋ የወሰደችህ>>ሀፍሳ የተለመደውን ነቆራዋን ጀመረች
<<ኡፍ አንቺ ደሞ ምታወሪው አታጪም ወረኛ ነይ ግቢ አሁን አስጠበቃቹኝ እኮ>>
ሀፍሳ እናቷ ልታወራ ስትል ቶሎ ቀምታ
<<አስጠበቀችኝ አትልም ምን አለፋህ እረዳሀለው  እኮ አፍረህ ነው አሁን ምን አለበት ዳሩኝ ብትል ከሩቅ ከምትናፍቃት…>>
<<ሀፍሳ…>>እናቷ ተቆጧት
<<ዝም በይ መሪ ይዞ ያለው ምን ያሳብድሻል>>እናቷ ተቆጥተው ዝም አስባሏት ሚፍታህ ግን"ምን አለበት ዳሩኝ ብትል ከሩቅ ከምትናፍቃት" ያለችው ፈገግ አስብሎታል መሪ መያዙን ረስቶ ሀሳቡን እሷ ጋር ጥሎ በደመነፍስ ይነዳል በመሀል አንድ ሆስፒታል አከባቢ ሲደርሱ አንዲትን እናት ሊገጫት ሲል ፍሬኑን በሀይል ይዞ አስቆመው ሁሉም ደንግጠዋል እሱም አንድ ነገር የሆኑ መስሎት ወረደ እሳቸው ደንግጠው ክርናቸውን ፊታቸው ላይ አድርገው ቆመዋል
<<ደና ኖት እማማ ጎዳዎት እንዴ>>
<<ቀስ ብለህ አትነዳም ልጄ ጥሩ አይደለም እኮ ፍጥነት>>ብለው ካጎነበሱበት ቀና ሲሉ ያዩት ነገር አስደሰታቸው
<<ውይ…ውይ…ውይ ልጄ አንተነህ እንዴ ውይ እንደው ብገጨኝ ራሱ ይቅር እልህ ነበር ልጄን እኮ ነው ከሞት ያተረፍክልኝ እግዜር ወዶኝ አንተን ላከልኝ ተመስገን>>አገላብጠው ይስሙታል ቅድም አስርሺ ብር የሰጣቸው እናት ነበሩ እናቱ እና እህቱ ምን እየተፈጠረ እንደሆነ አልገባቸውም እንዳይወርዱ መሀል መንገድ ነው ያቆመው ሰው የገጫት መስሏቸው ክላክስ ሳያረጉ ያልፋሉ ሚፍታህ ግን ሀሳቡ ልጅቷ ጋር ስለነበር እናቲቱን ብዙም አላስታወሳቸውም ግራ ተጋብቷል
<<እንዴ እማማ ምን አርጌሎት ነው ይሄን ያህል>>ግራ በመጋባት ጠየቃቸው
<<እንዴ ልጄ አንተኮ ነህ ቅድም አስር ሺ ብር ሰጠሀኝ ልጄን ያዳንክልኝ ረሳሀኝ እንዴ?>>
<<አሀ አሁን አስታወስኮት ልጆ ዳነችሎት>>
<<አዎ ልጄ እግዜር ያሰብከውን ያሳክልህ እድሜ ይስጥህ…>>የምርቃት መአት አዥጎደጎዱበት እሱም በሷ ሰበብ ሰደቃ ስለሰጠና የሰው ደስታ ማየት ምን ያህል እንደሚያስደስት አስቦ ይበልጥ ሳያውቃት ወደዳት ሊያደርሳቸው ሲጠይቃቸው ቤታቸው እዚው እንደሆነ ነግረውት ተሰናብቷቸው ወደ መኪናው ተመልሶ ሲገባ እናቱ ና እህቱ በጥያቄ ያፋጥጡት ጀመር እሱም ስላሰባት ልጅ ሳይነግራቸው ስለ እናትየው ብቻ ነግሮ ዝም አስባላቸው እናቱም የሴትየዋን መደሰት ከልክ በላይ ስላዩ ልጃቸው በሰራወረ ስራ ተደሰቱ ሚፍታህም ቀልቡ ወደ ተሰረቀበት አውላላ ሜዳ ጉዞውን ቀጠለ……

ከወደዳችሁት ሼር



#ክፍል_2 ይቀጥላል★★
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
የአንዳንድ ሰው እንክብካቤ ደካማ አድርጎ ያስቀረናል የአንዳንድ ሰው ቸልተኝነት ደግሞ ይበልጥ ያበረታናል።ምናልባት ድርጊቱ ሳይሆን ልዩነቱን የሚያመጣው እኛ የመለስንበት መንገድ ነው።
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
------------💞-------------
🎁ለፍቅር ፊዳ🎁
------------💞-------------

ክፍል ሁለት

«በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ»

…የክረምቱ ወር አልፎ የበጋው ወቅት የገባበት ተማሪው የናፈቀውን ት/ቤቱን የሚያገኝበት ባስራው ከእረፍቱ የሚኳረፍበት ጊዜ ነው የሚፍታህ እህት ሀፍሳም ዛሬ የአጎቷ ልጅ በአሁኑ አመት ት/ቤት ቀይራ እነሱ ሚማሩበት ት/ቤት ገብታለች ዘመዷም ጓደኛዋም ስለሆነች ደስ ብሏታል ልጅቷ ስሟ ማያ ያባላል ውበት ከማንም ሴት በላይ በጣም ቆንጆ ናት ሚያምር መካከለኛ አቋም ነው ያላት  አባቷ አቶ ኢያድ  ከቤተሰቦቹ የወረሰውን ድርጅት ስለሚያስተዳድር ለስራ ወደ አሜሪካ በሄደበት ወቅት ሊንሳ ምትባል አሜሪካዊ አስልሞ ካገባት ቡሀላ ነው ማያን የወለዱት ማያ የአሜሪካ ተወላጅ ናት ማያ ያለቻት እናቷ ናት ያለችበት ምክኒያትም 1 አመት ሳይወልዱ ቆይተው ከ1አመት ቡሀላ ስትወለድ አላህ ለኔ ብሎሻል ብላ ከኢንጊሊዘኛው mine  ከሚለው ወስዳ ማያ አለቻት እናቷ በመኪና አደጋ ነው በሞት የተለየቻት  ማያ  እናቷ ከሞተች አሜሪካ ለ2 አመታት ኖራለች ማለትም ባጠቃላይ ለአምስት አመታት ኖራለች ከዛ ቡሀላ ግን አባቷ የሚያፈቅራትን ሚስቱን ካጣ ቡሀላ እዛ ሀገር መኖር ስላልፈለገ ሀገሩ ኢትዮጲያ መኖር ጀምሯል የማያ አባት ያደጉት ማደጎ ነው አንድ ሀብታም ሙስሊም ሰዎች ወስደው አስተምረው አስመርቀውት ነው ከዱኒያ የተለዩት ሌላ ልጅ ስለሌላቸው ቤተመንግስት የሚመስለው ትልቁና የሚያምረውን ፎቅ ቤት የወረሰው እሱ ስለሆነ ከማያ ጋር እዛ ነው ከሁለት ሰራተኛ ጋር የሚኖሩት ድረጅታቸውንም እሱ ነው ሚያስተዳድረው ማያንም ብቻውን አቀባሮ ነው ያሳደጋት በኢማኗም ጠንካራ እድቶን አድርጎ ነው ያሳደጋት በዚም ሰበብ እንደ ሀብታም መቅበጥ አይመቻትም ሁሌም ሰፋፊ ጥቁር እና ረዣዥም አባያ ነው ምትለብሰው ሁሌም ብቸኝነት ያስደስታታል ጩሀት ነገር አይመቻትም ወዳው ራስምታት ይይዛታል ፀጥታ የበዛበት ቦታ በጣም ያስደስታታል ሰው መቅረብ አትፈልግም በተለይ ወንድ የተባለ ፍጡር ከአባቷ ውጪ የውድቀቷ ምክኒያት የሚሆኑ  ስለሚመስላት ትፈራለች አትቀርባቸውም በውበቷ ምክኒያት ጓደኛዋ መሆን የሚፈልጉ ብዙ ወንዶች አሉ እሷ ግን የድሮው ጠባሳዋ ስላልሻራ ወንድ ሲባል ያንቀጠቅጣታል ሰውን መቅረብ ባትፈልግም ሀፍሳን ግን አባቷ ስላላት ነው ጓደኛ የሆነቻት ከቀረበቻት ቡሀላ ግን ወዳታለች ሁሉንም ሚስጥሯን ነግራታለች ሰውን መቅረብ ከፈራችበት ምክኒያት ውጪ እሱንም በደንብ ስትግባባት ነው ልትነግራት የፈለገችው…አምስቱን ፔሬድ ተምረው ምሳ ሰአት ሲደርስ ሀፍሳ ማያ ጋር ወደ መስጂድ ሊሄዱ ወጡ ሰግደው ከመስጂድ እንደወጡ ሀፍሳ ወደቤት ሄደን ምሳ ካልበላን ብላ ያዘቻት የነሀፍሳ ቤትና ት/ቤቱ ብዙ አይራራቅም አንደምንም ተከራክራ ይዛት ሄደች… ምሳ ሰአት ላይ ሚፍታህ ላፍቶፑን ጠረጴዛ ላይ አስቀምጦ የውጪው ኮሊደር ላይ እየተንጎራደደ አዲስ ስለገቡ መድሀኒቶች እያወራ ነው በመሀል በር ተንኳኳ ሰራተኛቸው ሄዳ ከፈተች ሀፍሳ ነበረች ከማያ ጋር የመጣችው ከዛም ማያን ማማ ሰርፕራይዝ ላርጋት አንዴ ቁሚ አለቻት ና ኩሽና ፊትለፊት ያለችዋን እናቷን እያፈጠጠችባት  ትስቃለች
<<ወይ ጉድ ደሞ ምን መጣ ልትበይኝ ነው አሰላሙ አለይኩም የለም እንዳይረፍድብሽ ቶሎ በልተሽ ውጪ ምን ይገትርሻል>>በሳቅ እያዋዙ ነገሯት
<<ሃሃሃ ኡሚዬ ዛሬ ሰርፕራይዝ አለሽ እንግዳ ይዤ ነው የመጣውት  ገምቺ ማንን ነው>>
<<ልዕልቴን ይዣት መጣው እንዳትይኚ ዞር በይ እንጂ ትግባበት>>አሏት ቆንጆ ስለሆነች ልዕልቴ ብለው ነው ሚጠሯት ግን በአካል አንድ ጊዜ ብቻ ነው ቤታቸው ሄደው ያዩዋት ሌሎቹ ጋር አትተዋወቅም
<<ጎበዝ ገማች እኮ ነሽ ኡሚ ሰርፕራይዝ… ነይ ግቢ ውዴ>>ሄዳ እናትየውን ሰላም ብላ ስትዞር
<<አው እነሱን መዳኒቶች በሱ……በ……በ……በ…>>ለመጨረስ ከበደው አይኑ ፊት ለፊት የሚመለከተው ነገር ቅዠት መስሎታል ሀፍሳም የሱን ምፍጠጥ አይታ
<<ሚፍቱ ማያ ትባላለች ተዋወቃት የአጎታችን ልጅ ናት>>አለችው ሳቅ እያለች ማያ ግን ቀና ብላ አላየችውም አንገቷን እንደደፋች ነው ሚፍታህ ከያዘው ስልክ በተደጋጋሚ ሄለው የሚል ድምፅ ይመላለሳል የሚመለከተው ነገር ላይ አይኑ እንደፈጠጠ እጁ ከዳው የያዘውን ስልክ በቁሙ ለቀቀው…

ሼር

#ክፍል_3
★★ይቀጥላል★★
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
✅️እንቁራሪቱን መጀመርያ መብላት

👇🏾

አንዳንዴ አስገዳጅ ሁኔታ ውስጥ ገብተን ትልቅ እንቁራሪት: ትንሽ እንቁራሪት እና የበሬ ስጋ ቢቀርብልን እና መብላት ግዴታ ቢሆን የትኛውን ነው የምንመርጠው?

"Eat the frog first” ወይም "እንቁራሪቱን መጀመርያ መብላት" በሚለው መርህ መሰረት በመጀመርያ ትልቁን እንቁራሪት መብላት: ከዚያም ትንሹን መብላት: በስተመጭረሻ የበሬውን ስጋ መብላት

ምን ማለት ነው?

👇🏾

ቀናችንን ስንጀምር አስቸጋሪ የሚባሉ ስራዎቻችንን የቀኑ መጀመርያ ላይ መስራት: ከዚያም ቀጣዩን አስቸጋሪ ስራ መከወን: በስተመጨረሻ ደግሞ ቀናችን እየገፋ ሲሄድ እምብዛም አስቸጋሪ ያልሆኑ ስራዎቻችንን መጨረስ

የሚመከረው መንገድ - አስቸጋሪ እና ፈታኝ ስራዎቻችንን የቀኑ መጀመርያ ላይ መከወን

ብዙዎቻችን የምደርገው - ቀላሉን ስራ ሰርተን ስኬታማ የሆንን እንዲመስለን ማድረግ ነው

🙌🏼❤️
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
‍ ----------💞--------------
🎁ለፍቅር ፊዳ🎁
----------💞---------------

ክፍል ሶስት

«በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ»




…ሚፍታህ ከያዘው ስልክ በተደጋጋሚ ሄለወ ሄለው የሚል ድምፅ ይመላለሳል የሚመለከተው ነገር ላይ አይኑ እንደፈጠጠ እጁ ከዳው የያዘውን ስልክ በቁሙ ለቀቀው ሀፍሳ እና እናቷ ደንግጠው ተያዩ ማያ ላይ  እያፈጠጠ ፈገግ ማለቱና የስልኩን መውደቅ አለማስተዋል ግራ አጋብቷቸዋል እናቱ በሁኔታው ደንግጠው ፊቱ ላይ ውሀ ረጩበት ከእንቅልፍ እንደነቃ ሰው ባነነ በስራው ፈርቶ እያፈጠጠባቸው መንተባተብ ጀመረ
"አ……ም…ም…ን…ድ ነ…ው ም…ን ተ…"ሀፍሳ አቋረጠችው
"ቆይ ቆይ ወንድሜ እኔ አፈር ልብላልህ እንዲ ከንፈህልኛል እስቲ ጎንበስ ብለህ እግርህ ስር ተመልከትልኝ ስልክህ ዘርገፍ ብሎ ተኝቶልሀል"ብላ ማብሸቋን ጀመረች እሱም እየተናደደባት ወደ ታች ሲመለከት ስልኩ መሬት ላይ ወድቋል ደንግጦ ሲያነሳው በጣም ተከስክሷል ስልኩን ሲመረቅ አጎቱ ከአሜሪካ እንደ ስጦታ የላከለት iphone13 ነበር የአጎቱን ማስታወሻ በመስበሩ  ተበሳጨ ሀፍሳም መበሳጨቱን አይታ
ᐸᐸድሮስ ሰው ብሎ ላንተ ስጦታ መሰጠት አልነበረበትም ምንም ቢሆን የሰው ስጦታ መጠበቅ ያቅተዋል" ስትል በሁኔታዋ እናቷ ተናደው
"ሀፍሳ እንግዲ አንቺ መንገድ ካገኘሽ ትጨማለቂያለሽ በይ ግቢ ልጅቷን አታስቁሚያት ሂጂ ግቢ ልጄ" ብለው ሀፍሳን ተቆጧት እየተነጫነጨች ይዛት ገባች ማያ አንዴም ቀና ብላ አልተመለከተችውም ስልኩ ሲወድቅ ብቻ አንዴ ቀና ብላ ተመልክታው ቶሎ ነው ያጎነበሰችው በዚም ሚፍታህ ተናዷል በሴት ሳይደነቅለት ማያልፈው ውበቱ በሷ መናቁ አበሳጭቶታል በብዙ ሀሳቦች ተወጥሮ ተቀምጧል እናቱም
"ሚፍታሄ በል ተነስ ሚሰራ ከሆነ አይተህ ና"ብለው ነገሩት እሱ ግን በብዙ ሀሳቦች ተጠምዶ ስለነበር እሺ ብሏቸው ማያ እስክትወጣ መጠበቅ ጀመረ ውስጥ መግባት ፈርቷል እነ ሀፍሳ ምሳቸውን በልተው ወደ ት/ቤት ለመመለስ ሲወጡ ሚፍታህ ሊወጣ እንደሆነ አስመስሎ
"ላድርሳቹሀ በዛው ስለሚሄድ"አላቸው ሀፍሳም ነገሩ ገብቷት
"አረ እንሄዳለ ለምን አንሄዳለን እንጂ"አለች ማያ ደንግጣ አፈጠጠችባት
" አረ እንዲ አትይኝ ወንድምሽ እኮ ነው" አለቻት ሚፍታህም ግራ ተጋብቶ
"ምነው ሌላስ ቢሆን ምን ያስፈራታል"
"አይ ወንድ ስለምትፈራ ነው" ስትል ማያ ረገጠቻት
" ማ…ለቴ ከወንድ ጋር ለብቻ መሄድ ሀራም ስለሆነ ነው" ብላ አስቀየሰችላት…
*
*
ሚፍታህ ስልኩ ስለማይሰራ ሌላ ስል ገዝቶ ሁሉንም ካረገ ቡሀላ ኢሻን ሰግዶ አልጋው ላይ በጀርባው ተኝቶ ያስባል ቆይ ወደድኳት ማለት አይ አይሆንም መሸነፍማ የለብኝ ግን መሸነፍ አለብኝ እሰከ መቼ ልቀመጥ ነው ሀላሌ አድርጊያት ከሷ ጋር ልኑር እያለ ስለሷው ደጋግሞ ያስባለረ ስልኳን ሀፍሳ ለመጠየቅ አስቦ ግን ወንድነቱ ከድቶት ፈርቷል ውበቷን እየሳለ ከሷ ጋር ሚያሳልፉትን ህይወት እያሰበ የሞት ታናሽ ወንድም ይዞት በረረ…

#ክፍል_4

★★ይቀጥላል★★
2024/09/21 11:01:28
Back to Top
HTML Embed Code: