Telegram Web Link
የዛሬ 4 አመት አካባቢ ከምማርበት ኮሌጅ entrepreneurship( ስራ ፈጣሪነት) የሚባል ኮርስ እንወስድ  ነበር እና መምህራችን  "Final Exam የሚሆነው   የስራ ፈጠራ ሃሳባችሁን በደንብ በተደራጀ መልኩ project ሰርታችሁ አቅርቡ"> ብሎን ሁላችንም የተሻለ ሃሳብ ለመፍጠር ተሯሯጥን

መጨረሻ ላይ እኔም ለረጅም ጊዜ ሳስበው የነበረው ሃሳቤን ካለምንም ስስት በፕሮጀክቱ ላይ አስፍሬ እንዴት እንደሚሰራም ጭምር የያዘ ፕላን ጨምሬበት  ለመምህሩ አቀረብኩ

መምህሩም በጣም በመገረም Class ውስጥ በደንብ Present እንዳደርግ አድርጎኝ 50+ ሰጠኝ😊

መጨረሻ ላይ ግን  ራሴ የሰራሁትን ፕሮጀክት 5 ሰዎች አክስዮን መስርተው  የፕሮጀክቱን ስም እንኳን ሳይቀይሩ ስራ ጀመሩበት! ከባለ አክስዮኖቹ መሃል  አንዱ ደግሞ መምህሩ ራሱ ነበር 😊

|| እና ሃሳባችሁንና ህልማችሁን ለማንም አታጋሩ
🙏
ድንገት ጭር ያለ ቦታ ሳለሁ ብዙ ምልክት ሳያሳይ ወይ እኔ ሳላስተውለው አላቅም ብቻ ዶፍ ዝናቡን ለቀቀው ። የቱም ቦታ የታየኝ መጠለያ አልነበረም ።

በቅርቡ ወለም ያለኝ እግሬ መሮጥ ስላላስቻለኝ በተቻለኝ መጠን ለመራመድ ሞከርኩ

በቲሸርት መሆኔን ፣ መራመድ አለመቻሌን ከምንም ሳይቆጥር ዝናቡ ያለርህራዬ ቀጠቀጠኝ

አለቀስኩ ......።

ደብሮኝ ነበራ!!!

አጥንትን የሚፍቅ ድብርት ውስጥ ነበርኳ ፣ ማንም ሊያድነኝ ከማይችል ዱካክ ውስጥ ነበርኳ

በችግር ውስጥ ማለፍ ፣ በችግር ማደግ የሚያስተምረው ችግር ሲመጣ አለመቸገርን አይደለም ችግሩ እንደሚያልፍ መረዳትን እንጂ !

የጠዋት ፀሃይ ውስጥ ተስፋ ማየት እያቆምኩ ነበር ፣ የምሰማው ነገር ሁሉ አልጥም ስላለኝ ማንንም ላለመስማት ከብቻዬ ጋ ብቻ ለመሆን እየታገልኩ ነበር ...

በዚህ ሁኔታዬ ዝናቡ ሲቀጠቅጠኝ ሆድ ባሰኝ ፤ አለም ላይ ሁሉም ሊያጠቃኝ የተዘጋጀሁ የመስዋዕት በግ የሆንኩ መሰለኝ ።

ዝናቡ እያባራ መጣ ፣ እምባዬም እየደረቀ ሄደ

ከዛ ዶፍ ዝናብ በኋላ
መጠለያ ከማጣት በኋላ
ሁኔታዬን ሳያገናዝብ ከቀጠቀጠኝ በኋላ
ከአለ'ማንም አይዞህ ባይ ከተደበደብኩኝ በኋላ

ዝናቡ ቀጥ አለ!!!

በማያሳምን ፍጥነት ፀሃይ ወጣች ። የፀሀይ አወጣጧ የተደበደበው ልብሴን እንደሚያደርቀው ፣ የበረደው አካሌን እንደሚያሞቀው ተስፋ ሰጠኝ ።

ከዶፎ ዝናብ ቀጥሎ የወጣችው ፀሃይ ሳያት የሆነ ሚስጥር እንደነገረቺኝ አይነት ፈገግ አልኩ ።

ፀሃዬ
እሱ እረስቶት ይሆናል...ለእኔ ግን እንደ ትናንት ትዝ ይለኛል....ያ መልኩን አስታውሰዋለሁ...ምን መልኩን ብቻ እየያንዳድዋን sily moment አእምሮዬ ውስጥ ቆልፌባታለሁ..ለዛ ነበር አይኑን ባየሁበት ቅፅበት ሁሉ ከእምባዬ ጋር ትንቅንቅ ምገጥመው....

እጄን ይዞ ከትምህርት ቤት ሲያመጣኝ...በዛ እድሜዬ ለእኔ የማይገባኝን የፍቅር ዘፈን ሲያንጎራጉር ድምፁ ውስጤ ቀርቷል...ልቡን አውቀዋለሁ...ከአፉ መጥፎ ቃል ሲወጣ ሰምቼው አላውቅም..."አባትሽ ነኝ...እኔ እስካለሁ ድረስ ላንቺ የሚገባሽን ሁሉ አደርግልሻለሁ..."...ይለኝ ነበር አባት የለኝም ብዬ ሳማርር...ሲያመኝ አይተኛም ነበር...በባነንኩ ቁጥር ቁጭ ብሎ ሲጠብቀኝ አገኘዋለሁ...በጤናዬስ መች አስተኛው መሰላችሁ ...የባጥ የቆጡን እየቀበጣጠርኩበት ቀባጥሬም ሳበቃ መብራት ከጠፋ ፈራለሁ አይጥ ይመጣብኛል ብዬ እበጠብጥ ነበር...እኔን አስተኝቶ መብራት ካላጠፋ አይተኛም ነበር...ደሞ በመሀል ከባነነንኩ ጩኸቴ መከራ....


በመንገድ እየሄድን የኔ ቢጤ ረግጦ አያልፍም..."የሮጠ አይቅደምህ..."...የሚለው ምርቃት አሁንም ድረስ ውስጤ አለ...አውቃለሁ ሁሉንም እረስቶታል...እኔ ግን ሁሉንም አስታውሳለሁ....


የተበጣጠሰ ጫማ ከመጫማቱ በፊት ትንሽ አቧራ እንዴት ይጠየፍ እንደነበር አውቃለሁ...ያቺ የሁላችንም እድሜ...እኮ ያቺ አለምን መቀየር የምንችል የሚመስለን እድሜያችን አለች አይደል...እሱ ያቺ እድሜው ላይ እኔ ደግሞ ልጅነቴ ላይ ነበርኩ...

አንድ ያለኝ ቤተሰብ እርሱ ነው...እናቴን ልምሰል አባቴን አላውቅም...ሰፊው አፍንጫዬ እና እብድ የሚያህል ከንፈሬ ተደምረው ከግንባሬ ፊት  አውራሪነት ጨምሮ ጥቀርሻ የሚያስንቀው ጥቁረቴን ከማን እንደወረስኩ አላውቅም....ወንዝ ዳር ተጥዬ ነው ያገኘኝ.....

"...ቆሻሻ ሁልጊዜ መጥፎ አይደለም..እንደ እኔ ከታደልክ ቆሻሻ ልትጥል ወጥተህ ወርቅ ይዘህ ትመለሳለህ..."...ይል ነበር እኔን ያገኘበትን አጋጣሚ ሲተርክ...

ለዛ ነው መሰለኝ "ወርቅነሽ" ብሎ ስም ያወጣልኝ...ደግሞ እኮ አመሌ..."ይሄን ስም እንደው ምነው ምን አርጌህ ነው...ካልጠፋ ስም...ቲቲ...ሜላት...ሰላም...ኧረ ስንት አለ አንተ ድሮም ስለማትወደኝ ነው"...እለው ነበር በእንጭጭ ጭንቅላቴ..ተማሪዎች በስሜ ሲቀልዱ እኔ ደግሞ ወቀሳውን አዥጎደጉደው ነበር።

አሁን ላይ ለሚያወራው ነገር ከእኔ በቀር ቦታ የሚሰጥ ሰው የለም...ይግባኝም አይግባኝም አንገቴን እያወዛወዝኩ እሰማዋለሁ...ባያስቀኝም ቀልድ ብሎ ለነገረኝ ነገር ጥርሴ ሰንፎ አያውቅም...በሳቅኩለት ቁጥር  "ወርቅ ነሽ የምልሽ እኮ ለዚያ ነው "...እያለ እንደ ልጅነቴ ያቅፈኛል...

ወዳጆቹ መሸሻቸውን ከሱ አብልጬ አማርራለሁ...

"እነርሱም እንደ ዘንድሮ ሽንኩርት ሆኑብን እኮ....ብር ሲጠፋ ጠፉ..."...እላለሁ ክፍት ሲለኝ...በስሱ ፈግጎ እንዲህ ይመልስልኛል.....

"ሰው ሲንቅሽ አትጥዪ...እግዚአብሄር የሚያከብርሽ የመናቅ ፅዋሽ ሲሞላ ነው...".....ተገርሜ አፈጥበታለሁ...

"ኧረ ሽንኩርት የሌላት ሽሮአችን አትብረድ አምጫት...."...ብሎ ከግርምቴ ይመልሰኛል...

ይሄ ነው አንድ ግን ብቻውን ሺህ የሆነ ቤተሰቤ................


አሁን ላይ ሁሉም ታልፎ "ዶክተር ወርቅ ነሽ ተካልኝ" ተብዬ ስጠራ እንደ ድሮ በስሜ አልናደድም...የምናደደው በእኔ ፈንታ እርሱ "ዶክተር ተካልኝ" ባለመባሉ ነው...

የምርቃት ጋውኔን ለብሼ ፊቱ ስቆም "አስከበርሽኝ ልጄ ..."...ብሎ ግንባሬን ሳመኝ...ቀጥሎም አቀፈኝ...መልሶ ለቀቀኝና ፀጉሬን ሳመኝ...የእንባው እርጥበት ቆዳዬ ጋር ደረሰ...ተመልሶ ደግሞ አቀፈኝ...የሚያረገኝ ግራ ገባው...ፊቱ ፀዳል መሰለ...

"የመናቅ ፅዋዬ ሞላ ልጄ...አስከበርሽኝ ክበሪ...የሮጠ አይቅደምሽ...አግኝተሽ አትጪ...."....መረቀኝ....እኔ ግን "የሮጠ አይቅደምሽ".... ጋር ነኝ....አልረሳውም ነበር ማለት ነው




Shewit dorka




Join for more👉https://www.tg-me.com/ethioleboled
የዛሬው ደግሞ ይለያል......😂


ፈተና ተፈትነን በዛው class ገብተን ነው...ጀዝበናል...ፈተናው የጦለበው ሙዳችን እንቅልፍ ከነሳነው አይናችን ጋር ተማክሮ ነው መሰለኝ ጥፉ ጥፉ አሰኝቶናል.....

አስተማሪው በሞራል ያስተምራል...ኖት የሚይዝ ተማሪ የለም....እንደውም ግማሽ ያሀሉ ተማሪ ከፈተናው በኃላ ወደሚሄድበት ሄዷል...እዚ ያለነውም "ምን ሲያቀብጠን ነው የገባነው"...እያልን ነው....

አጠገቤ ያለችው ልጅ ስእል አይሉት ነገር ትቸከችካለች...እኔ ደግሞ አእምሮዬ ላይ የመጣልኝን ነገር እሞነጫጭራለሁ...

THE END.....የሚለው  የትምህርቱ ማብቂያ የሚበሰርበት slide ላይ ስንደርስ እኩል ነው "ኡፍፍፍፍ"....ያልነው።

ግን መምህሩ እስከአሁን ፒሲውን አልዘጋም...ግራ ገባን...."ሊቀጥል እንዳይሆን..."...."አያረገውም.."..."እኔ አመመኝ ብዬ ልወጣ ነው...."....እንሾካሾካለን።

"quez(ፈተና) አላችሁ ወረቀት አውጡ ሲል...."....ሰውነታችን ውሀ ሆነ...

"ወይኔ ኖት አልፃፍኩም ምንም አላዳመጥኩም.... "....ትለኛለች አጠገቤ የተቀመጠችው....

ድንገት "ስትፅፊ ነበራ...."...ብላ ወረቀቴን ከጠረጴዛው ላይ አፈፍ አደረገችው...

ወዲያው "እመብርሀን ድረሺ...."....አለችና ወረቀቴን አሽቀነጠረችው....የውርደት ቀን አይመሽም አይደለ ሚባለው ተዋረድኩ....

"ባሌን አስራ ሁለት ቦታ ቆራርጬዋለሁ...12 ቦታ....."....እያለ የሚቀጥል ፅሁፍ እየፃፍኩ ነበር....😒


ባስረዳት ባስረዳት አልገባት አለ....ብዬ ብዬ ሲደክመኝ

"እንኳን ደግ አደረግኩ...አንቺንም እንዳልገልሽ...ስንት ቦታ ይሻልሻል...."...ስላት


Run💃💃💃




Shewit dorka



😁https://www.tg-me.com/ethioleboled
የኤፍራጥስ ወንዝ @Eotc_Books_By_Pdf.pdf
56.9 MB
📚⛪️የኤፍራጥስ ወንዝ⛪️📚

ጸሐፊ ፦ ዲያቆን ሀይሌ

 

➡️ከወደዱት ያጋሩ
share & join
   🔻
➡️ርዕስ: የኤፍራጥስ ወንዝ
📝ደራሲ: ዲያቆን ሔኖክ
📜ዘውግ: ሃይማኖታዊ
📅ዓ.ም: 2013
✈️አዘጋጅ: ምንተስኖት
ስለ ቱርኩ ሐገር መሪ ኤርዶጋን ሕይወት የሚተርከው መጽሐፍ ::

መጽሐፉ በ ሙሐመድ ሰዒድ ተጠናክሮ ለንባብ ቀርቧል ::  
airdogan.pdf
11.8 MB
📖ርዕስ:- ኤርዶጋን
📝ደራሲ:- መሀመድ ሰኢድ
📅ዓ.ም:-...
የገፅ ብዛት:- 180

ኤርዶጋን

😄ስለ ቱርኩ ሐገር መሪ ኤርዶጋን ሕይወት የሚተርከው መጽሐፍ ::

መጽሐፉ በ ሙሐመድ ሰዒድ ተጠናክሮ ለንባብ ቀርቧል ::  
ኑ ሀገሬን እናዋልዳት... @Bemnet_Library
18.4 MB
ርዕስ=ኑ ሀገሬን እናዋልዳትና ሌሎችም
ደራሲ=ዳንኤል ክብረት
 
  ማጋራት መተሳሰብ ነው!
📚 @ethioleboled
Selam endat nacehu tariku yetjemerew be tg nbr yetwaweknew be tg nw ena selamta telewaweten ena yemjemeriya geza yemelsekulet meles tekekl alenbrem meknyatum befkr betam yetgodalhu ena gena eyagegemku nbr yemjemeriya kn bemleskulet melse dengeto bezaw yekeral bye saseb degami liyawarag mokere yegeremg gn esu adelm afkrekush nbr yalew ena bemgerem west hoja bezu teyake teyekute gn esum endemayakg ena liyakeg endemifelg nbr yenegreg bezu aweran ena beza mahale guadte west yalhu sew endehonku ena mnm endemalfelg ngrkute gn aberen lehun ene lekasesh nbr melsu keza eyaweran koyen bezum sankoye aberen honen ena bemhakel betam enetala nbr ena ene demo feraca west ng degami lalemgodat so tolo bye eneleyaye malet nbr mikenage gn endzam hono cgrocun eyefetan aberen koyen beakale hula teganagen selrasu bedenb ngreg gn afen moleca akewalhu yakegale malet bemalecelbet huneta west ende lelaocu fekregamoch sex gedeta nw selzi mefetre alebet kalhone gn aberen mehonacen mndew alg ene demo yeha tenama asetesaseb adelm gedeta sex wesage ngr adelm alkute esu gn wedesu hasab endemta sifelg 1 samnt sidelg 3 kn eyekoye hasabshen alkeyereshem ene ewedshalhu ebaksh wedene ney yelale mndenw madereg yalebg esti amakrug yene hasab tekekel adelm weyes tekekelgaw ngr mndew fkregamoch yeged sex madereg alebacew?????


https://www.tg-me.com/ethioleboled
ውልኝ ያለችውን ሁሉ ትውኩኝ ። አትወደውም የምለውን ነገር ሁሉ ተውኩ ። እወዳታለሁ

እኔ ስለፍቅር ምንም አላውቅም ። መተንተን አይቻለኝም

ስለምወዳት ቅር እንዳትሰኝ እጠነቀቃለሁ እማትፈልገውን ላለማድረግ የቻልኩትን አደርጋለሁ። ጨዋታ እመርጣለሁ ። ስትናደድ ንዴቷን እውቅና እሰጠዋለሁ

ይሄ ሁኔታ ማክበር ነው ስሙ አሉኝ ።

ስለምወዳት ለኔ የሰጠችውን ለሌላ የሰጠች ሲመስለኝ ሌላ ወንድ እንደኔ ካንዣበበ እና ፊት ካልነሳችው ይደብረኛል ።

ይሄ ደሞ ስሙ ቅናት ይባላል አሉኝ

ጥውልግ ያለች ከመሰለኝ ፣ ካዘነች ከተከዘች ፣ካመማት ከተከፋች ያሳስበኛል ይሄ ስሙ ስስት ነው አሉኝ

ካላገኘኃት ይደብረኛል አግኛት አግኛት ይለኛል ፤ ፊቴ ጭር ሲል ፣ ሁኔታውን ሁሉ ከሷ ጋ ሳያይዘው ያለችበት ለመሄድ እሞክራለሁ ፦

ይሄ ሁኔታ ናፍቆት ነው አሉኝ

እወዳታለሁ ። መኖሯን አለምደውም ህልሜ ከሷ ጋ አጣብቄዋለሁ ። ነብሴ ተቀብላታለች ። ተሸንፌያለሁ እሷ ጋ ጀብድ አልችለም ቁማር አልችለም ሁሉ ነገሬ ትመስለኛለች። ችላ የምለው የሷ የሆነ ነገር የለም ። ይሄ ስሙ ማፍቀር ነው አሉኝ ።

I think አፈቅራታለሁ
#አታስመስል_የሆንከውን_ሁን!

በትክክል የሆንከውን ሆነህ መታየት ስትጀምር ሕይወትህን በከፍተኛ ደረጃ መለወጥ ትጀምራለህ።

የሆንከውን ሆነህ መታየት ስትጀምር፣ አላስፈላጊ መረጃዎችን እንዲቆሙ ታደርጋለህ።

በዚህም ራስህን እንደምትወድ ብቻ ሳይሆን፣ ዋጋ ያለህ መሆንህንም ለዓለም ታውጃለህ።

ከዚያ እሴቶች ብቻ ሳይሆን ሊያስፈልግህ የሚችል ሁሉም ነገር ይኖርሃል።

የምትፈልገው ቦታ ስትደርስም ባለመርህ ብቻ አትሆንም።

የሆነ ሰው ሲያፈቅርህም ደስተኛ ብቻ አትሆንም። እንደሆንከው ሆነህ ስትመጣ ይህንን አካሄድ ታፋልሳለህ።

ከዚህ በኋላ የሕይወት መልካምነት ምናልባት ላትሆን ለምትችለው ለተሻለው አንተነትህ የተያዘ አይደለም።

እንዴት መታየትና ስሜትህን ማሳየት መፍቀድ መጀመር እንዳለብህ ከማወቅህ በፊት፣ በተፈጥሮ ጥሩ ስሜት የማይሰማህ ለምን እንደሆነ ለራስህ ማብራራት ለአንተ ሁልጊዜ ጨዋታ ነበር። አሁንም በጨለማ ውስጥ የምትኖር ከሆነ፣ ያንን ማፈንና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ማሳየት ነበረብህ።

ዛሬ የሆንከውን ሆነህ እየታየህ፣ ለምናባዊው አንተነትህ የሚገባውን ሳይሆን፣ የአንተ የሆነውን ትወስዳለህ። ዓለም የሚሰጥህ ያስብልኛል ብለህ የምታስበውን ሳይሆን፣ አንተ፣ እዚህ፣ አሁን የምታስበውን ነው።

#እውነተኛ_ፈውስ_ያ_ነው

ልክ ልክህን እየነገረ ምርጥ ጓደኛ የሚሆንህን
#ተራራው_አንተ_ነህ_መጽሐፍ ደግሞ እንድታነበው ትጋበዛለህ
💥📚ኢትዮ-ልቦለድ📚📖💥
Photo
🔵#ስትሞት በጣም ደስ አለኝ።

እልልታዬን አቀለጥኩት ያንተ መሞት እረፍት ሰጠኝ።አጠገቤ ነበርክ አንገትህን ጭኔ ላይ  አስደግፌ በእጆቼ ፀጉርህን እያሻሸው እያያውህ አይንህ እኔን እያያ ደርቆ ቀረ።አልጮኩም ጎረቤትም አልሰማኝም አይንህን በእጆቼ ከደንኩት ።እንደምትሞት ሲገባኝ የገዛሁት አዲስ ነጠላ ሸፈንኩህ.....

የተዘበራረቀ ቤቴን አፀዳው. ..ማውራት አላቆምኩም እያወራሁህ ነው...
እየዘፈንኩልህ ነው. .............

ቤቴን አፅድቼ ስጨርስ ወደ አባትህ ስልክ አጮሁኩኝ። ታላቅ እህትህ አነሳችው. ...

በጣም እንደምጠላኝ አውቃለው!
ቤተሰቦችህ እንደሚጠሉኝ አውቃለው !
ነገሩ እንዴት ይወዱኛል።....

ታላቅ እህትህ ሄሎ. ...
አረ ሄሎ.....................

እ.....ትዕግስት ነሽ. ...

"አዎ ምን ፈለግሽ?"

እንኳን ደስ አላቹ....

"ምን ተገኘ ደሞ." ..

ልጃቹ አርፏል...

ምን? ስልኩ ኳ ኳ  ብሎ ሲወድቅ ተሰማኝ...
ጆሮዬን ከስልኩ አንስቼ ወደ ሶፋው ወረወርኩት....

ሻወር ቤት ገባው ሻወሬን ወሰድኩኝ
ቆንጆና አዲስ ቀሚስ ለበስኩኝ ውድ የሚባለውን ሽቶዬን ተቀባው ፀጉሬን አድርቄ በማለስለሻ አለሰለስኩና በተንኩት ቀይ ሊፒስቲኬን ተቀባው።

ከሰአታት ቡሀላ ቤቴ ሲደበደብ  ሰማው ማነው? ልጥጥ ባለ ድምፅ....
 
ከፈትኩላቸው ሁሉም  ወዳንተ ነጠላ ወዳለበስኩህ ልጃቸው ሄዱ. ..
ሞቷል ኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡ

እናትህ ወይኔ ልጄ ኡኡኡኡኡኡኡ

እህትህ ወይኔ ወንድሜ ኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡ

አባትህ ግን ወደኔ በአለቃቀሳቸው እየተዝናናው ወዳለሁት አይናቸውን ፍጥጥጥጥጥጥ አርገው  መጡብኝ።ግዙፍ ናቸው ያስፈራሉ....

"እጃቸውን ወደ አንገቴ ልከው...
አንቺ ነሽ አንቺ ነሽ ልጄን የገደልሽው አንቺ ነሽ አንቺ".....
ለማላቀቅ አልሞከርኩም...
ሰው እንዳለ ወደሳቸው ሞቶ አላቀቃቸው።

ምነው ጋሼ ደስ ሊሎት ነው ሚገባው እኔ እኮ ደስ ብሎኛል ስላቸው...
አንቺ አውሬ አንቺ የሴጣን ቁራጭ ልጄን በላሽው......

ወጣሁና የቀብር ማስፈፀሚያ ኮሚቴ ደወልኩኝ. ...
በጣም ረጅም ደቂቃ ዘና ብዬ  እያወራዋቸው ነው።
እህትህ ወደኔ ጠጋ አለችና እንዳንቺ ግን አውሬ ሰው አለ?ባልዋ ሞቶ ስቃ የምታወራ ሽቶ የምትቀባ. ....

ቆይ አንዴ ስልክ ልጨርስ ስላት ጭራሽ አበደች።

እና ሳጥን ዋጋው ስንት ነው?

ኦኦኦ አረ አልተወደደም?

አስር ሰአት ሞላ  የቀብር ሰአትህ ደረሰ....

ጉድጓድ ከጊዮርጊስ ጓሮ ተቆፍሮ አለቋል።ሬሳህ እንዲያድር ሆነ ዘመድ እንዲጠበቅ አልፈለኩም።

ስርአተ ቀብርህ ላይ ብዙ ሰው ተገኘ. ..ከሁሉም 1 ሰው ብቻ ነው ያሳዘነኝ እሷም እናትህ ሌሎቹ ግን አስመሳዮች ነበሩ።

ልጄ.....ምን አገኘው ኡኡኡኡኡኡኡኡኡኡ
አፈር ካልገባው.....
የምር ሳቄ መጣ ፊልም ማይ መሠለኝ

እኔ ትንሽዬ ጥቁር ሻርኘ ፍትሀት የሚያረጉትን አክብሬ ጣል አድርጊያለው።

አለማልቀስ መብቴ ነው በቃ ደስ ነው ያለኝ ስለሞትክ. ...
ሰው ሁሉ ከቀብር መልስ እኔን እያየ ያወራል  አለም ላይ ያለች ትልቋ ጭራቅ ይሉኛል😂😂

ሰው ሁሉ ከቀብር መልስ ወደ አባትህ ቤት ሄዱ። እኔ ወደቤቴ....
እርቦኝ ስለነበር ቆንጆ ምስር ወጥ ሰርቼ በላሁ። ኡፍፍፍፍ እርቦኝ ነበረ።

ቤተሰቦችህ እኔን በማግባትህ ልጃችን አይደለም ካሉክ ቡሀላ ገና ለገና ሀብታችንን ትካፈለናለች ብለው  ልጃችን አይደለህም ብለው ከካዱህ  ቡሀላ  እነሱን ትተህ እኔን መርጠህ ከመጣህ ቡሀላ.....

ብዙ ተሰቃይተናል። ታመህብኝ እነሱ እግር ስር ወድቄ ስለምናቸው አያገባንም ያሉኝ ቤተሰቦችህ ብድር ለመጠየቅ የሄድኩባቸው ጉዋደኞችህ ዛሬ ቀብር ላይ ሲያስመስሉ የነበሩ ሰዎች በሙሉ ያንተ ሞት ተባባሪዎች ነበሩ።

አንተ ከተሰቃየሀው ስቃይ ከታመምከው ህመም ይልቅ ሞትህ እረፍት ነው።እንኳን ሞትክልኝ።.......

ከመሳብያው ውስጥ ባለፈው ለልብስ ማስጫ የገዛሁት ትልቅ ገመድ አወጣው......

ትልቅ ወንበር ላይ ወጥቼ ከጣሪያችን ማገር ላይ አጥብቄ አሰርኩት። የመኪና ድምፅ ሰማው ቅድም ረጅም ሰአት ሳዋራቸው የነበሩት ቀብር አስፈፃሚያን ናቸው።

2 ሳጥን ነበረ ስጠይቃቸው የነበረው።12 ሰአት ላይ መተው ሬሳዬን ወስደው ካንተ ጎን እንዲቀብሩኝ........

ሰማዩን አላምነውም ያለኔ ምን ትችልና.... የዘነጥኩት አንተ ጋር ስለምመጣ  ነው....

11 ሰአታት ስላስጠበኩህ ይቅርታ
!

ይሄ ሁሉ አንበብባችሁማ👍👍👍 ተጫኑ
ንድ ቀን እንዲህ ብለሽ ትጠይቂኛለሽ...ከኔ ሕይወትና ካንተ ሕይወት ይበልጥ
አስፈላጊው የቱ ነው? ስትይ...እኔ ደግሞ የኔ ሕይወት! እልሻለሁ አንቺም ደንግጠሽ ከኔ
ታፈገፍጊያለሽ ምክንያቱም የኔ ሕይወት አንቺ መሆንሽን አታውቂምና ። "

ካህሊል ጂብራን
እያወራን ነው ከባሌ ጋር ። እሱ አልጋው ላይ ጋደም ብሏል አልጋው ጠርዝ ላይ ቢጃማዬን ለብሼ ቀሚሴን እስከጉልበቴ ገልቤ በእጄ የቆነጠርኩትን ግሪሲሊን ጉልበቴን፣ ጭኔን ፣ ቁርጭምጭሚቴን ... እየቀባባሁ ነው።

ከላይ ነጭ ፓካውንት፣ ከስር ቱታ ለብሶ አንዴ ስልኩን አንዴ TVውን ያያል። Televisionኑ የትዝታ ዘፈን ያስመለክታል። ዘፈኑ የድሮ ቢሆንም በአዲስ ክሊፕ አዲስ ቆንጆ ድምፅ ያለው ልጅ እየዘፈነው ነው ።

🎼🎼🎼🎼

ሞት አደላድሎኝ አፈር ካልተጫነኝ
ቃሌን አላጥፈውም ካንቺ ጋር ነዋሪ ነኝ
ውበትሽ ኩራዜ ይበራል ከቤቴ
ጠረንሽ ፈውሴ ነው የፍቅር እመቤቴ
ሞት አደላድሎኝ አፈር ካልተጫነኝ ቃሌን አላጥፈውም 🎶🎶

"ክሊፑ ላይ ያለችው ልጅ የድሮ እጮኛዬን ትመስላለች።" አለ ፈገግ እያለ አፈጋገጉ እንደናፈቀችው አይነት ነው ።

ስቀብጥ ይሁን ስጃጃል፣ ወይም የጎጆ እና የትዳር ቀመር ስላልገባኝ የድሮ ፍቅረኛው ስላላት ልጅ ጠየኩት ።

ትክዝ እንደማለት አለና ሲያፈጥበት ከነበረው የሙዚቃ ክሊፕ አይኑን ነቅሎ ሲነካካው የነበረውን ስልክ አስቀመጠው ።

"እወዳት ነበር በጣም ። ስትናፍቀኝ ብንጣላም እኔ ካላሁበት ብትርቅ ፣ አላገኝህም ብትልም የትም ሄጄ አያት ነበር ...ስታኮርፈኝ የበለጠ ማግኘት እፈልግ ነበር...።" ሳቅ ነገር አለ ።

"እሷ ላይ ከቻቻ ነበርኩ ! ቀልድ ትችላለች ፣ ኩርፊያዋም፣ አሳሳሟም፣ አደናነሷ ፣ አስተቃቀፏ፣ ግልፅነቷን እወደው ነበር .... ደስስ ትላለች" ደማቅ ፈገግታ ፈገግ አለና "ናይል እኮ እብድ ነገር ነች " አለ ።

"አለ ኣ ደስ የምትል እብድ : ብዙ ደስ የሚሉ ነገሮች አሳልፈናል... " እያለ እየተመሳሰጠ ያለ ይሉኝታ አብራራልኝ ።

የእሷን እሩብ ያህል እንደማይወደኝ አይነት ነው ሁኔታው ። ላየሁት.. ላሳየኝ ማረጋገጫ ይሰጠኛል፣

ከትላንት ዛሬ አይበልጥም?

ለምኖ ላገባት ለልጆቹ እናት ይሄ ይነገራል ? ፣ የልጆች እናትስ እኔ የጠየኩትን ትጠይቃለች? ፣

የተጠየቀ ነው በሃላፊነት መመለስ ያለበት ? ወይስ ጠያቂው ነው ተጠያቂ ??

ስንት ጥልፍልፍ መንገድ አብረን መጣን አይደል? ፣ስንት የሃሳብ ዳገት ተጓዝን አይደል ?፣ የተሸከምነው የወጣነው የወረድነው የግዜ መዓት ትንሽ ይሉኝታ እንኳን እንዴት አልወለደበትም ?፣

ለጎጇችን ብዙ ገንዘብ ስለሚያመጣ ነው?፣ ዘመዶቿ አቅም የላቸውም ቢከፋት አትሄድም ብሎ ነው?፣ ወልዳለች ፈላጊ የላትም ብሎ ነው ?፣ ስለማይወደኝ ስለሚሰማኝ ስሜት ግድ ስለሌለው ነው ?፣

አይውደደኝ እንዴት አያከብረኝም ?፣

እውነት የሆነ ሁሉ ይነገራል ?፣ ሳይሰክር ሳንጣላ ሳላናድደው እንደዚህ ግዴለሽ እንዴት ይሆናል ?!፣
ይሉኝታና ብስለት ካልከለለን ልባችን ያባውን፣ ያደረግነውን ሁሉ ፣ የተሰማንን ሁሉ ቢወራ መች ኑሮ ፡ጎጆ ይመሰረታል?

ብቻ አመመኝ ...አለመወደድ በመላ አካሌ ተርመሰመሰ ማምለጫ የሌለው ህመም ተላወሰኝ ... እንደዋዛ የማይተው ሰው ሲወጋ ህመሙ ይለያል !!

የተሰማኝ ህመም እንዳልታመን ፣ እንዳልወደው፣ እንዳልጠነነቅለት ሊያደርገኝ የገፋኝ መሰለኝ ።

የቱ ጋ ነው የወጋኝ ?!

ቁስሉ ያልታየ ህመም ለመታከም ምቹ አይደለም !!

የመርሄ ወላጅ አባት ፍቅሬ እንደሆነ አላወቀልኝም
!!
©Adhanom meteku
2024/09/21 13:54:41
Back to Top
HTML Embed Code: