Telegram Web Link
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
⚡️Acorns ቦትን በስልኮት በመጠቀም ብቻ በወር 100,000ሺ ብር በላይ ተከፋይ ይሁኑ 💸

🎁የ Acorns ቦት ጋር ልክ እንደገቡ የ 1000ብር ስጦታ ያገኛሉ በተጨማሪም 1 ሰዉ ወደ ቦቱ ሲጋብዙ በየቀኑ የ 50ብር ቋሚ ክፍያ ያገኛሉ

🔗ይህ የእርሶ የመጋበዣ link ነው ለወዳጅ ዘመድዎ ያጋሩ 👇👇
https://www.tg-me.com/FreeEearnMoneyPay_Bot?start=r03892356955
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
👵❀✿ያልወለደች እናት❀✿👵

ክፍል1
...ከብርድ ልብሴ ውስጥ አንገቴን አውጥቼ ለመከፈት የሚታገለውን አይኔን ከፈት ሳደርግ መኝታ ክፍሌ በብርሀን ተከቧል እንደነጋ ገባኝና ከአልጋዬ ለመውረድ መታከክ ጀመርኩ ገና ከጠዋቱ ከአልጋዬ ሳልነሳ ድብርቱ ተጫጭኖኛል እንደ ምንም እራሴን ለማነቃቃት አልጋዬ ላይ ተቀመጥኩኝ ትንሽ የእንቅልፉ ስሜቱ ሲለቀኝ የመኝታ ልብሴን እንደለበስኩ ከኔ ክፍል ቀጥሎ ወዳለው መታጠቢያ ክፍል አመራሁ መክፈቻውን ጫን ሳረገው አልከፈት አለኝ ውስጥ ሰው እንዳለ ስለገባኝ ማንነቱን ለማወቅ ኳኳኳ አረኩት ያው ከአንድ ሰው ሌላ ማንም ስለማይገባ እሱ እንዳለ ገመትኩ "ምንድነው ሻወር ላይ ነኝ እታች ውረጂ"አለ የ ፋይሰል ድምፅ ነበር ፋይሰል ማለት ታላቅ ወንድሜ ነው እየተነጫነጭኩ "አንተ ደሞ ሁሌ እኔ ልገባ ስል ነው መታጠብ ሚታይህ ብሽቅ"ብዬው መኝታ ቤት ገብቼ ጋወን እና ሂጃብ ደርቤ ወደ ምድር ቤት ወዳለው መፀዳጆ ቤት አመራው ሰው መኖርና አለመኖሩን ለማረጋገጥ ኳኳ ሳረግ ከውስጥ ድምፅ ሰማው ብዙም ሳይቆይ ከመፀዳጃ ቤቱ ሀሩን ወጣ ሀሩን ማለት የአባቴ የጓደኛው ልጅ ነው ያው ለቤታቸው ወንድ እሱ ብቻ ስለሆነ ቅዳሜና እሁድ እኛ ቤት ነው የሚሆነው በነዚ ቀናቶችም ፋይሰልም ስራ ስለሌለው ስናዝግ እንውላለን ሁለቱ እኩያሞች ኛቸው በዛላይ በጣም ሚዋደዱ ጓደኛሞች! ሁለቱ እኔን በ 5አመት ይበልጡኛል እንደው አንዳንዴማስ ቅዳሜ እስኪደርስ ሲጨንቀኝ! ያው ከሰኞ እስከ አርብ ብቻዬን ስለምውል ይጨኝቃል ከትምህርት ቤት ወደ ቤት ከቤት ወደ ትምህርት ቤት እቤት መቶ ደሞ ለብቻ መዋል ይደብራላ?ዛሬ ግን ገና ከጠዋቱ ቢደብረኝም ፋይሰል አንድ ቦታ አሳያቹኃለው ብሎ ስላጓጓን እሱን እያሰብኩ ፈታ ማለት ጀመርኩ ከመፀዳጃ ቤት ወጥቼ ወደ ክፍሌ ለመሄድ ደረጃውን ልወጣ ስል አንድ ነገር ትዝ አለኝና እየበረርኩ ወደ ኪችን ገባው መኪያ ስታየኝ እየደነገጠች "ምነው ዳኒ ምን ያሮጥሻል አሁን ብትሰበራስ"ብላኝ የያዘችውን ሰሀን ይዛ ወደ ሳሎን ወጣች ማታ ፋይሰል ጠዋት እበላዋለው ብሎ ፍሪጅ ውስጥ ያስቀመጠው እሩዝ በስጋ(ሀኒድ)ትዝ ብሎኝ ነው ፍሪጁን ከፍቼ አወጣሁና አሙቄ ወደ ክፍሌ ይዤው ወጣው ክፍሌ እንደገባው አባባ መጣራት ጀመረ ዳኒያ ዳኒያ ሲለኝ የክፍሌን በር እየከፈትኩኝ ወይ አባባ መጣው እያልኩት ወደ ሳሎኑ ሮጥኩ ሳሎን ስገባ ሁሉም ተሰብስበዋል እንደገባው ፋይሰልን ሳየው በምልክት ቆይ አለኝ ከንፈሩን ነክሶ አይኑን እያፈጨጨብኝ እንደማይለቀኝ ስለገባኝ "አባባ አየኀው አይደል ሲያስፈራራኝ"አልኩት እናቴና አባቴ መሀል ያለው ክፍተት ቦታ ላይ እየተቀመጥኩ አባቴም ነገሩ ስለገባው "የሆነ ተንኮል ኮልሰራሽው በቀር ከመሬት ተነስቶ አይነካሽም"ብሎኝ የቀረበውን ምግብ ለመመገብ ከመብላት በፊት የሚደረጉትን ፀልቶች ብለው ሁሉም መመገብ ጀመሩ እናቴ ሰሀኔ ባዶ መሆኑን ስታይ "አንቺ ልጅ አበይም እንዴ ምን ስርአት ታጣለቸሸ"ብላ ተቆጣች የሆነ ነገር እንደሚል ስለገመትኩ ፋይሰልን ተመለከትኩት "እሷ ነገር ትብላ እንጂ ምግብማ ከየት መቶ ነጎሮሮዋም ዝቅ አይል"አለና ከት ብሎ ሳቀ እናቴ በፋይሰል ንግግር እየፈገገች መኩ በልታለች እንዴ ወይስ እላይ የተለየ ምግብ አለ እስኪ መኝታ ቤቷ ጊቢና ካለ አምጭው ብላ ፍለፊቷ ብና ወደ ምቀዳው መኪያ ተመለከተች መኪያ ማለት ሀዲማችን(እኛ ቤት ስራ የምትሰራ)ልጅ ናት እኛ ቤት ለ 7 አመት ቆይታለች ለዛ ነው መሰል ማንም እንደ ሰራተኛ አይቆጥራትም ሁሉም ይወዶታል በተለይ እንግዳ ሲመጣ የምታደርገው እንክብካብ አያምጣው ነው ሳያመሰግናት ሚወጣ የለም መኩ ከተቀመጠችበት ልትነሳ ስትል "ቁጭ በይ እራሷ ትሂድና ታምጣ አለ አባባ እኔ እያለው እሶ ስትላክ አይወድም ደስ እያለኝ እየሮጥኩ ወደ ክፍሌ ሄድኩና ቁጭ ብዬ ምግቡን ካጋመስኩት ብኃላ 3 ጉርሻ የምትሆን ሲቀር ይዤው ወረድኩ ፋይሰል ስቆይበት ጨርሼው እንደምመጣ ስላወቀ "እእእ የተላክሽው ቅድም እስካሁን ምን አቆየሽ"አለ ሁሉም መላኬን ረስተዉት ነበር "ወይኔ ለዚች ምግብ ጎሮሮዬ ላይ ልትቆም ነው እንዴ ያው ብላው ብዬ እንደተከደነ አጠገቡ አስቀመጥኩለት የኔ ምስኪን ወንድም ያለው መስሎት ሰፍ እያለ እማማ ትበያለሽ አላት እናቴ ከ አባቴ ጋር ተመስጣ እያወራች ስለነበር አልሰማችውም ቀጠል አሮጎ "ሀሩኔ ትላንት እስኪያቅርሽ በልተሻል ዛሬ የኔና የ መኩ ተራ ነው ብሎ የተከደነውን ሰሀን ከፈት ሲያረገው በሱ አበላል 1 ጉርሻ ቢህን ነው ሁላችንም ተያይተን ሳቅን እነ እማማ ሳቃችንን ሲሰሙ ወሬያቸውን አቋርጠው ምን እዳሳቀን ለማየት ፋይሰል ላይ አፈጠጡ እማማ ስለገባት "አንቺ ልጅ ግን እረፊ አንድ ቀን በጥፊ ብሎሽ"ነገር እንዳታመጪ ብላ ከተቀመጠችበት ተነሳች አባባም ተከትሏት እየተነሳ ፋይሲ በል እኛ ባለፈው ያልኩህን ሰውዬ እንያቸው ብለን ነበር እና እዛ ነው ምንውለው አይሻልም?ብሎ ጠየቀው አባባ ሁሌ አንድ ነገር ሲኖር ለ ፋይሰል ሳያማክር አያረግም"አይ አራፍ ነው ስላስለመዳቿቸው ደሞ ስትቀሩ ይከፋቸዋል"ብሎ ፈገግ አለ ፈይሰል ነበር አባባ ቀጠል አርጎ "እናንተም ከወጣቹ በጊዜ ተመለሱ ብሎ ከሳሎን ወጥቶ ደረጃውን እንደወጣ "ዳኒ ነይ"ብሎኝ እንደጠራኝ ብድግ ብዬ አባባ ወዳለበት ሄድኩ "ስወጣ አስታውሺኝ የምትውሉበትን እሰጣቿለው" ብሎኝ ወደ መኝታ ቤቱ ገባ እኔም ወደ ሳሎን ገብቼ ከመኩ ጋር የተበላበትን ማነሳሳት ጀመርን የሚገርመው የፈለገ ስራ ቢበዛባት መኪያ ማንም እንዲያግዛት አትፈልግም እኔም አውቃለው ግን ሼም ነው በሚል ዝም ብዬ እነካካለው እነ ፈይሰል ቴሌቭዥን ከፍተው አስቂኝና ድንቃ ድንቅ እያዩ ይስቃሉ እነ አባባ ለባብሰው ጨርሰው እየወጡ ነበር በር ላይ ቆሜ "አባባ"ስለው የቅድሙ ትዝ ብሎት ወደኔ መጣና የጋወኔ ኪስ ውስጥ ስጉጥ አርጎልኝ መኪናውን አስነስቶ ወጡ እኛም ትንሽ እንደቆየን ለባብሰን ልንወጣ ስንል የመኩ ብቻዋን መሆን ትዝ አለኝና ለማፅናናት ያህል "ቶሎ እንመለሳለን በጣም ከደበረሽ ደሞ ደውይልኝ" ብያት ተያይዘን ወጣን መንገድ ላይ እያለን....


#ክፍል_➋ ይቀጥላል.....
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
👵❀✿ያልወለደች እናት❀✿👵
:በነኢማ ኸድር
ክፍል:2
ፋይሰል ድንገት "ግን እናንተ በቃ ዝም ብላቹ መነዳት ነው በቃ የት ነው ምትወስደን እንኳን አትሉም"አለና ፈገግ አለ እኔም ቀበል አርጌ "እእ ፋይሲ ወደየት ግድም ነን ወንድም አለም"ብዬው ከ ሀሩን ጋር ተያይተን ሳቅን በርግጥ ሀሩን ንግግሬ ነው ያሳቀው እኔ ግን ፋይሰልን ለማናደድ ብዬ ነው "አረ አሁን እኔ ስልሽ ነው ነይ ባክሽ አርፈሽ እንደ በግ ተነጂ"ብሎኝ አቀፈኝ እና የቦሌን ታክሲ ወደ ምናገኝበት አስፓልት ተሻግረን መጓዝ ጀመርን ሀሩን ብዙውን ጊዜ እኔ ስኖር ዝምታን ይመርጣል ከፋይሰልጋ ሲሆን ግን አያምጣው ነው እንደው ብዙ ጊዜ ፋይሰል ነገር ሲበላ "ምንድነው አንተ እሷ ስትመጣ ምትዘጋው ፓስወርድህ ናት እንዴ አረ በናትሽ ክፈችልኝ"እያለ ሙድ መያዝ ይቀናዋል እንዲ እንዲ እያለ አራፍ ውሎ ውለን 1፡00 ሰአት ሲል እኔና ፋይሰል ወደቤታችን ሀሩንም ወደቤቱ ተለያየን ነገ ሰኞ መሆኑን ሳስበው በጣም ጨነቀኝ እቤት ስንገባ እነ አባባ አልመጡም ነበር ቀድመናቸው ስለደረስን ደስ ብሎን የኡሻን(ማታ ላይ የሚሰገድ ስግደት) ሰግደን እነ እማማን መጠባበቅ ጀመርን በነገራችን ላይ እናትና አባታችንን እንዲ የምንላቸዎ ድሮ ልጅ እያለን በስማቸዎ ስንጠራቸው አያታችን ሰምታ ተቆጣችን "እማዬ/አባዬ በሉ ወይ ምንድነው ምትሉት ስትቀናጡ እማማ/አባባ"ብላ አስጀመረችን በሷ ቤት እኮ ማማ እና ባባ ማለቷ ነው አዪ አያቴ የኔ ተናፋቂ ክረምት መቶ እስክትመጣ ጨንቆኛል ከጓደኛም በላይ ነው ምቀርበኝ እንደው ብዙ ጊዜ አባባ እዚ ኑሪ ሲላት እንቢ ብላዋለች" የትውልድ ሀገራን የ ቤተሰቤን መሬት አልተውም ባይሆን ክረምት ክረምት እመጣለው"ይቺ የሁሌ የአያቴ መፈክር ነች እንደ ድንገት ክላክስ ተሰማን መኪያ ፈጠን ብላ ወጣችና እነ አባባ መሆናቸውን ስታይ በሩን ከፍታ መኪናው ሲገባ ዘጋችው እና እነ አባባ እስኪገቡ ከጠበቀች ብሀላ እማማን ተከትላ ገባች እነ እማማ ትንሽ ካረፉ ቡኃላ እራት በላልተን የዛሬው ምሽት በዚህ አለፈ፡፡ ጠዋት ላይ እንዴት እንደነጋ አላውቅም ብቻ የሞላሁት አላርም ድምፅ ማሰማቱን ጀመረ ስልኬን በዳበሳ ፈልጌ የሚጮኀውን አላርም አጥፍቼ እንደተኛው የክፍሌ በር በሀይለኛው ተንኳኳ የፋይሰል ስራ መሆኑ ስለገባኝ ዝም አልኩት ደግሞ እያንኳኳ "አንቺ አረ ተነሺ ዛሬ እኝኮን ቢያንስ ይለፍልሽ"ብሎ ቅድም ከሚያንኳኳበት ፍጥነትና ሀይል እየጨመረ "ዳኒ ተነሽሽ ወይኔ አረ ሴት ልጅ እስከዚ ሰአት አተኛም ቆይ ስታገቢ ምን ሊውጥሽ ነው"ብሎ የበሩን እጀታ ሲጫነው ተከፈተለት አንገቱን እያስገባ "አረ ዳኒ በአላህ ተነሽ ሰው ምን ይልሻል"አለ ይሄን ሁሉ ሲል ግን መልስ አልሰጠሁትም ነበር "ስታገቢ"ምትለዋ ቃል ግን ዶሮዬ ላይ አቃጨለች በቅፅበት ብርድልብሴን ከፊቴ እያነሳው "ስታገቢ"አልኩት ከት ብሎ እየሳቀ "እስቲ ምናለ ሌላውን ብትሰሚ በይ ተነሽ" ብሎን ትቶኝ ሄደ አይ ፋይሲ አልኩ በውስጤ የፈለገ ብንጨቃጨቅ አንድ ቀን ተሰዳድበን ወይ መቶኝ አያቅም እኔ ደሞ ነብሴ እስክትወጣ ነው ምወደው በቃ ገና ሳየው አንጀቴን ይበላኛል ለቤተሰቡ ያለው ፍቅር በተለይ ለ እማማ እሷም የልቡን ስለምታቅ ለሱ ነው ምታደላው አንድ ነገር ተፈጠረ "ፋይሲ" አንድ ነገር ከፈለገች "ፋይሲ"አይ እማማ አንዳንዴ እኔ ልጇ አልመስላትም መሰለኝ፡፡
እንደምንም ከአልጋዬ ተነስቼ ከክፍሌ አጠገብ ካለው መፀዳጃ ቤት ገብቼ ተጣጥቤ ከነ እማማ ጋር ቁርስ ለመብላት ስወርድ ማንም የለም የተበላበት ብርጭቆ እና የተበላበት የመመገቢያ ሰሀን ሱፍራው ላይ ተመለከትኩ 'እእ እነሱ ስለሌሉለት ነው እንዲ ሚቀውጠይ'አልኩ በውስጤ እነ እማማ ቁርስ እንደበሉ ገብቶኛል ግን የት ሄደው ነው? ብዬ እራሴን ጠየኩ ቁርሴን ለመብላት ወደቀረበው ሱፍራ(መመገቢያ ላስቴክ) ቀረብኩ ወዲያው ፋይሰል ከክፍሉ እየመጣ ሳሎን በር ላይ ቆሞ "ቶሎ ብይና እንሂድ"አለኝ የሸሚዙን ቁልፍ እየቆለፈ"በዚ ጠዋት የት ነው ምኔደው አንተ ልጅ ነቀልክ እንዴ"ብዬ የቀዳሁትን ሻይ ተጎነጨው "አረ ተነሺ ይበቃሻል እነ አባባ ሀናንን ሊጠይቁ ሊሄዱ ነዎ እማማ ሄዳለች አባባ ደሞ ሱቅ ሊከፍት ወቷል ቶሎ ኑልኝና እኔም በጊዜ እሄዳለው ብሏል በይ ተነሺ"ብሎኝ ጫማውን ወፈለግ ጀመረ ነገሩ ግራ ስለገባኝ "ፋይሲ ቆይ ሀናንን ወለደች?"አልኩት ድምፅን ከፍ አርጌ " አይ አንቺን እየጠበቀች ነው"አለኝ ሀናን ማለት የአባባ የእህቱ ልጅ ናት ካገባች 4 አመቷ ነው ግን ሳትወልድ ቆይታ አሁን እንደ አላህ ፍቃድ ተሳካላት ለዛ ነው ያካበዱላት ቁርሴን በላ በላ አረኩና ልብሴን ቀይሬ ከ ፋይሰልጋ አባባ ሱቅ ሄድን እንደደረስንም አባባ ወደ ሆስፒታል ሄደ እኔና ፋይሰል አምሽተን ሱቅ ዘግተን ወደቤት እየሄድን ሳለ ድምገት መኪናውን ሲጢጥጥ አርጎ አቆመው "ምነው ፋይሲ" አልኩት ደንግጬ
......

#ክፍል_➌ ይቀጥላል......
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
👵❀✿ያልወለደች እናት❀✿👵
:በነኢማ ኸድር
ክፍል:3
ፋይሰል ፋት ላይ ጥሩ ስሜት አይነበብም ደግሜ ጠየኩት"ፋይሲ እእ"አልኩት አይን አይኑን በስስት እያየው "ምንም ዳኒ ትንሽ ብዥ አለብኝ ልረጋጋ ብዬ ነው ያቆምኩት"ብሎኝ ወደ እኔ ዞረ ያየሁትን ግን ማመን ተሳነኝ እሱ ሳይታወቀው እየነሰረው ነበር "ፋይሲ አ.....ፍንጣህ እ....የደሞ ነው"አልኩት እየተንተባተብኩ አንድ ቀን መኪያ የፋይሰልን ክፍል ስታፀዳ ከ አልጋ ስር ሸሚዝ አግኝታ አሳይታኝ ነበር ሸሚዙ ደረቱ አካባቢ ቀይ ቀለም ይዟል ሁለታችንም ደነገጥን ፋይሰል ሲመጣም አግባብቼ ብጠይቀውም ጥርሴ ደምቶ ነው ብሎኝ ሊያሳምነኝ ሞከረ "ፋይሲ ወይ ሀኪም ቤት እንሂድ እየደሞ እኮ ነው ደሞ ሶፍትም ጨርሰሀል እቃው ባዶ ነው" የማረገው ግራ ገብቶኝ ከአይኔ የእንባ ጅረት ቁልቁል እየተምዘገዘገ "ዳኒ ደሞ አረ አታካብጂ አሁን ይቆማል እዙ አካባቢ ሱቅ ካለ ውሀ ብቻ እንግዛ ኪኒን አለኝ" ብሎ መኪናዋን ሊያስነሳ ከተደገፈበት ቀና ሲል ይብስ ከአፍጥጫው የሚወጣው ደም በሀይል ይወርድ ጀመረ ምን እንደማረግ ግራ ገባኝ ፋይሲ በእጁ የያዘው ደም ወደ ሹራቡ መንጠባጠብ ጀመረ አንደቴን በላኝ ያለኝ አማራጭ ሂጃቤን መቅደድ ነበር ያሰርኩትን ሂዳብ እየፈታው "ፋይሲ እኔን እሺ ወንድሜ ቆይ በዚ ትይዝበታለህ" ብዬ ከመኪናው ወርጄ ሂጃቡን የምቀድበት ድንጋይ መፈለግ ጀመርኩ ደግነቱ ብዙም ሳለፋ የእግረኛ ወንገድ ላይ አንድ ድንጋይ ተመለከትኩ በድንጋዩ የሂጃብን ጫፍ ከመታሁት ብሀላ በእጄ ቀደድኩት ይህ ሁሉ ሲሆን ግን ሊያስቆመኝ አልቻለም ስሜን ለመጥራት ራሲ አቅም አጣ ወደ መኪናው ተመልሼ የቀደድኩትን ሂጃብ ሰጠሁት እና እጁ ላይ ያለውን ደም በመስኮት በኩል ወደውጪ አፈሰሰው በሂወቴ ደም እፈራለው በዛላይ የነስር ደም በዛላይ እፍኝ እፍኝ በደቂቃ የሚነስረው ሰው ማየት ይባሱን ያስፈራኝ ደሞ ወንድሜ መሆኑ ነው ከመኪናው የጎን ኪስ አንዲት ትንሽ ብልቃጥ እያወጣ "ዳኒ ውሃ አለኝኝ"እንጀቴን በላው እኛ ከቆምንበት በትንሽ እርቀት ሱቅ ይታያል ከኪሱ ብር አውጥቼ በምን ቅፅፈት ደርሼ እንደመጣው እንጃ ውሀ እና ሶፍት ይዤለት ወጣው ለካ አንዳንዴ ድንጋጤ ፈጣን ያረጋል ምነው ሁሌ እንዲ ብንሆን ብዬ ተመኘው
መዳኒቱን ሲወስድ የሚወርደው ደም እየቀነሰ ወጣ ትንሽ እንደተረጋጋ ሳይ "ወንድሜ እእ አሁንስ እየተሻለህ ነው"አይኑ ውስጥ ምላሽ አገኝ ይመስል አይን አይኑን አየዋለው "ደና ነኝ ትንሿ ግን መንዳት ምችል አይመስለኝም ያለማመድኩሽ ለመቼ ነው ስለደረስን ቀይሪኝ"ብሎ በሩን ከፍቶ ወጣና ተቀያየርን የፈለገ ያለማምደኝ እንጂ ነድቼ አላቅም ግን ከፋይሲ ይበልጥ እያጣደፍኩት ከነፍን እቤት በር ላይ ቆመን ፋይሰል እጄን ይዞኝ "ዳኔ ፍቅር በአላህ እነ እማማ እንዳይሰሙ ይጨነቃሉ ደና ነኝ እኮ እሺ"ብሎ በአይኑ ተማፀነኝ ላስጨንቀው አልፈለኩም እና ተስማምተን ቤት ገባን እኔ ቀጥታ ወደሳሎን አመራው ፋይሰል ደሞ ልብስ ሊቀይር ወደ ክፍሉ ወጣ መኪያ ጊቢ ገብተን ፋይሰል ከመኪና ሲወርድ ስላየችው ደንግጣለች አይኗን እያፈጠጠች በድምፅ አልባ ቃላች በአይኗ ጠየቀችን እኔም ዝም እንድትልና የተፈጠረውን ብኃላ እኔ እንደምነግራት አስረድቻት ነው የገባነው ብዙም ሳይቆይ ፋይሰል ልብስ ቀይሮ መጣ እማማና አባባን ስሟቸው ከ እማማ አጠገብ ተቀመጠ "ስራ እንዴት ነበር"አለች እንደ ህፃን ፊቱን እያሻሸች "አልሀምዱ ሊላህ አሪፍ ነበር ያው አባባ እንዳለው ጊዜ ባይሆንም እናንተጋስ ውሎ?"አለ በስስት እያያት ሲያስቀኑ ቆይ አሁን እንዲ ሚሆኑት ማንን ለማስቀናት ነው "አራፍ ነበር የአክስታቹ ልጅ ልክ እንዳንተ ሸበላ ወንድ ዱብ አረገች ነገ ሄዳቹ ዘይሯት እሺ አበባዬ"ብላው ትክ ብላ ተመለከተችው የሌላ ጊዜ እኔ ብሆን አኩርፌ ክፍሌ ሄጄ ተኝቼ ነበር፡፡እህህ እቀናለዋ! ዛሬ ግን በሀሳብ ጭልጥ ብዬ ሄጃለው አካሌ ከአ እማማና ፋይሲ አጠገብም ቢሆን አይኔ ቢያያቸውም ልቤ ግን የቅድሙ ክስተት ላይ ነው 'ልብ ካላየ አይን ቢያይ ዋጋ የለውም' ትል ነበር አያቴ ለካ እውነቷን ነው እንደድንገት የአባባ ጥሪ ከገባሁበት የሀሳብ ሸለቆ ጎትቶ አወጣኝ ለካ አባባ ደጋግሞ ሲጠራኝ ነበር "አረ አንቺ ልጅ የት ሄድሽ"አለኝ ስስ ትራስ እየወረወረብኝ "አረ አባባ የትም እዚው ነኝ"ብዬው እማማና ፋይሰል ምን እንደሚያወሩ ማዳመጥይ ጀመርኪ እማማ ለረዥም ደቂቃ ስትመለከረው ግራ እየተጋባ "አረ እማማ ምንድነው እንዲ ምታይኝ" ብሎ ወደኔ ተመለከተ
እማማ ቀጠል አርጋ "ፀሀይ ላይ ነበር እንዴ የዋልከው"አለችው አረ አይደለም ምነው ውዷ"አላት ፋይሲና እማማ ሲያወሩ ፍቅረኛሞች እንጂ እናትና ልጅ አይመስሉም እንዳንዴማስ አባባ ሁሉ ሳይቀና አይቀርም ብዬ እጠራጠራለው ከአፉ ቀበል አርጋ "እሺ አሞሀል እንዴ? በአንድ ቀን ጠቆርክ እኮ"ብላ ትክ ብላ አየችውና "ደሞ ፂምህን ተቆረጥ"ብላ ወደኔ እያየች "ዳኒ እእ ውሎ?"አለች "አይደል አሁን ነው የታየሁሻ እማማ እንዴ ቆይ ልጅሽ እሱ ብቻ ነዋ"ብዬ አባባ አጠገብ ተቀመጥኩ ብዙም ሳንቆይ መኪያ እራት አቀራርባ ተመገብንና ወደ ክፍላችን ገባን ክፍሌ ገብቼ ስለቅድሙ ክስተት ወደኀላ ተመልሼ እያሰብኩ እንቅልፍ ቢጤ ሸለብ አረገኝ እንደ ድንገት ፋይሲ ፋይሲ ተነስ ዳኒ አባባ የሚል ድምፅ ሰማው መኩ ነበረች ሁላችንም እሮጠን ስንመጣ ፋይሰል መሬት ላይ ተዘርሯል ከአፍንጫው ደም እንደ ቧንቧ ይንቆረቆራል...

#ክፍል_➍ ይቀጥላል......

አንብበው ሲጨርሱ ሼር ያድርጉ
👵❀✿ያልወለደች እናት❀✿👵
:nimu khedivo
ክፍል:4
ያየሁትን ማመን ተሳነኝ ፋይሰል እንዲ ሲሆን አይቼው አላቅም እማማ ከአንገቱ ቀና አድርጋ የሲቃ ለቅሶ ታሰማለች ፋይሰል አይኑን ወደ ጣሪያው እያገላበጠ የጭንቀት እስትንፋስ ያሰማል ከአፍንጫው የሚወርደው ቀይ ቀለም አዘል ፈሳሽ ቀድሞ ይፈስ ከነበረበት ሀይል ጨምሮ ይጎርፋል ሁላችንም መላው ጠፋን ትንሽ እንደቆየን ፋይሰል ሰቅጣጭ ድምፅ አሰምቶ አይኑን ወደላይ እንደሰቀለ ፈዞ ቀረ "ፋይሲ ብዬ ከአልጋዬ ብድግ አልኩ ሰውነቴ ዛለ ፊቴ ውሀ እንደተቸለሰበት ሳፋ ውሀ በውሀ ውኖል እንደምንም ተፍጨርጭሬ ከአልጋዬ ወርጄ ወደ ፋይሰል ክፍል አመራው በሩን በዝግታ እያንኳኳው "ፋይሲ ፋይሲ" እያኩ ተጣሪው መልስ ሳጣ በሩን ከፍቼ ገባው ፋይል እልም ያለ እንቅልፍ ላይ ነው ትንሽ እንደመረጋጋት ብዬ ወደ ክፍሌ ተመለስኩ "ድንበርህን ጠብቅ "እንደተባለ ወታደር ለሊቱን ሙሉ እንቅልፍ በአይኔ አልዞር አለኝ ፈራሁ አንዱን ወንድሜን ማጣው መሰለኝ እንዳልናገር ቃል ባልገባ እናገር ነበር ግን ነገ ሀኪምጋ አብረን አንሄድም ካለኝ የግድ ለነ እማማ መናገር ግድ ሊሆንብኝ ነው እያልኩ ከራሴጋ አወጋሁ አይነጋ የለምና ነጋ ከሁሉም ቀድሜ ተነሳው መኪያ በጊዜ መነሳቴን ስታይ ተገርማ "ዳኒ ምነው ዛሬ በጠዋት? በሰላም ነው?"ብላ በጥያቄ አጣደፈችኝ እኔም ምንም ስለማልደብቃት ሁሉንም ነገርኳት ማታ ከፋይሰልም ጋር የተፈጠረውንም ጭምር ደነገጠች ለነ እማማ ካልነገርን አንገቴ ላይ ካራ ብላ ድርቅ አለች እንደምንም አስማምቼ የሀኪም ውጤቱን እንይና ከዛ እንደምንወስን ነገርኳት በዚ ተስማማን ያው መኩ ደስ ባይላትም ቁጭ ብዬ እንዳላያት ብዬ መሰራራት ጀመርኩ ከ አንድ ሰአት ቆይታ ብኃላ እነ እማማ ተነሱ እና ለባብሰው ወደ ሳሎን ገብ እማማ በጊዜ መነሳቴን ስታይ እየተገረመች "ምን ተገኘ ደሞ ዛሬ ያለመደብሽን"አለች እንደ ጨቅላ ህፃን ፊቴን እየዳበሰችኝ "ምንም እማማ ልለማመድ ብዬ ነው"ብዬ ፈገግ ለማለት ሞከርኩ እማማ ቁርስ ቀራርቦ እንዳለቀ ስታይ "መኩ ፋይሲ አልተነሳም?"አለቻት "እንጃ እማማ ልየው እንዴ"ብላ ስትነሳ "አይ ተይው ተነሺ እስኪ እይው ምን ሆኖ ነው ለወትሮ እንዲ አርፍዶ አያቅም"ብላ እንድነሳ በእጇ ገፋ አረገችኝ ደረጃውን እየወጣው እግሬ ቸብረከረከ ክፍሉ ገብቼ ምን እንደሆነ ለማየት አቅም ከዳኝ 'በባዶ ሜዳ ጭንቀት ሆሆ ምን ሆኜ ነው'ብዬ እራሴን አረጋጋሁና የፋይሰልን ክፍል አንኳኳው ደገምኩ ደጋገምኩ መልስ የለም በሩን ከፍቼ ስገባ ፋይሲ እልም ያለ እንቅልፍ ላይ ነው ለሊቱን እንዳልተኛ ገብቶኛል "ፋይሲ ተነስ ሰአት ረፍዷል እህህ" እያልኩት ብድርብሱን ከፊቱ እያነሳው "ውይ ትንሿ ነጋ እንዴ ቅይ እሺ አምስት ደቂቃ አይኔ እስኪከፈት"ብሎ ብርድልብሱን ለበሰው ትንሽ ላስቀው ብዬ "አረ ፋይሲ ተነስ ሰው ምን ይልሀል ወንድ ልጅ እስካሁን አይተኛም" ብዬ ብርድልብሱን ገፈፍኩት "አንቺ ሲንቢር እገልሻለው ውጪ"ብሎ እየፈገገ ትራስ ወረወረብኝ "እሺ ግን 5 ደቂቃ" ብዬ ወጣው ፋይሱ እንዲ ሲስቅ ልቤ ጮቤ ትረግጣለች እንጃ ደስስስ ይለኛል! እአእማማ ጋር ወርጄ እየለበሰ እንደሆነ ነግራያቸው ተቀመጥኩ እኛ ቤት አንድ ህግ አለ ሁሉም ሳይሰበሰብ እራትም ሆነ ምሳ ወይ ቁርስ አይበላም ትንሿ እኔ ሳልቀር ካልመጣው እጠበቃለው አሁንም የሆነው እሱ ነው ፋይሰል እስኪመጣ መጠበቅ ብዙም ሳይቆይ መጣ "አሰላሙ አለይኩም ደና አደራቹ"ብሎ አዘውትሮ ወደሚቀመጥበት ቦታ ሄዶ ቁጭ አለ እማማና አባባ ለሰላምታው መልስ ከሰጡት ብኃላ እማማ "ጓረምሳዬ ምነው ዛሬ በለሊት ተነሳህ"ብላ ፈገገች ፋይሲ ያ ሚያምረውን ሳቁን እየገለፈጠው "አይ እማማ ትንሽ እራሴን አሞኝ ነው"ብሎ መልሶ ያን ፈገግታውን ደገመው ቁርስ በልተን እንደጨረስን አባባ በር ላይ ሆኖ "ፋይሲ ናማስ" ብሎት የሆነ ነገር አወሩና አባባና እማማ ወደ ሱቅ ተያይዘው ሄዱ
ገና እነሱ እንደወጡ ፋይሰልን ላዋራው ወደ ቤት ገባው ክፍሉ ስለነበር ቀጥታ ወደዛው አመራው የክፍሉ በር ገርበብ ተደርጎ ተከፍቶል ቀስ ብዬ ክፋት አርጊ በሩ ላይ ቆምኩ ፋይሲ መስገጃ አንጥፎ በግንባሩ ተደፍቶ ይንሰቀሰቃል አሳዘነኝ የእህትነት አንደቴ አንሰፈሰፈኝ ከይኔ የእንባ ዘለላ የአይኔን መስመር ይዞ በጉንጮቹ ላይ ተረማምደው ወፊቴን አረጠቡት ስላላስቻለኝ ድምፅ አውጥቼ አለቀስኩ ፋይሰል ከተደፋበት መስገጃ ሲነሳ እሮጬ ወደክፍሌ ገብቼ በሬን ዘጋሁት በሩን እንደተደገፍኩ ቁልቁል ወርጄ መሬት ላይ ዘፍ አልኩ አቃተኝ ድምፅ አውጥቼ አለቀስኩ ፋይሰል ደንግጦ በሩን ያንኳኳል "ዳኒ ምን ሆነሽ ነው ማሬ በአላህ በሩን ክፈችው" እያለ ተማፀነኝ ስላላስቻለኝ ከፈትኩለት ከፋይሲ ጀርባ መኩ ነበረች ተያይዘው ገቡ"በወንድም እንዲ ድጨከናል ቆይ በጭንቀት ብሞትብሽስ"ብሎ ሲለኝ ተጠምጥሜበት ማልቀስ ጀመርኩ
ፋይሲ ግራ ተጋብቶ "ምን ሁነሽ ነው በአላህ አታስጨንቂኝ"ብሎ አይን አይኔን ያየኛል እንድነግረው ተማፀነኝ "አይሲ........

#_ክፍል➎ ይቀጥላል......

አንብበው ሲጨርሱ ሼር ማድረጎን አይርሱ🥰
🤴-- ዳግማዊ አፄ ምኒልክ ከተናገሯቸው ታሪካዊ ንግግሮች በጥቂቱ -- 🤴

🗣 ሰው ሁሉ እኩል ስለሆነ ማንም ሰው ሰውን ባሪያ አይበል ።

🗣 ድኻ እወደደበት ቦታ ይቀመጥ
በዘር ፣ በወገን ልዩነት አይከልከል ።

ለመንግሥት ተሿሚዎች የሰጡት መመሪያ፡-
‹‹… እንቅልፍ ሳትወዱ፣ መጠጥ ሳታበዙ፣ ገንዘብን ጠልታችሁ ተግታችሁ ሥራችሁን ፈጽሙ ። እኔ እናንተን ስለአመንኩ እናንተም የምታምኑትን ፣ ገንዘብ የማይወደውን፣ ድኻ የማይበድለውንና የሚረዳችሁን ሰው እያመለከታችሁኝ ከሥራው በመግባት መንግሥታችንን እርዱ ››

🗣በጣም ወደኋላ የቀረን ሕዝቦች ነን፤ ገና የሚሠራ ብዙ ሥራ ስላለ ወጣቶቻችን መማር አለባቸው ።

🗣 እኔ ቤት እንጀራ የለም ። እንጀራ ያለው ትምህርት ቤት ስለሆነ ፤ እሠራሁት
ትምህርት ቤት ልጆቻችሁም እያስገባችሁ አስተምሩ ።

🗣 የኔ ርስት ኢትዮጵያ ናት ፤ የግል ርስት አልፈልግም ። ደግሞስ የተሾምነው
እርስት ከተካፈልን ለሕዝቡ ማን ያካፍለዋል?

🗣 ሐገራችን አንድትለማ የሚቀርቡንን ሁሉ በታላቅ ደስታና በአክብሮት
እንቀበላቸዋለን። በሌላ ለሚመጡብን ግን ፤ ሁላችን ሳናልቅ ሀገራችንን
ለባዕድ አሳልፈን እንሰጥም ።

🗣 የሚጠሉህን ሰዎች ከማጥፋት፤ የሚጠላብህን ማጥፋት እንዲሉ፤
የሸፈቱባቸውን፣ የወጉአቸውንና ያሤሩባቸውን ሰዎች በጋብቻ ፣ በዝምድና
ወይም ወዳጅ አድርገው ያቀርባሉ እንጂ ክፉን በክፉ መመለስና መበቀልን
አይሹም ።

አንድ የፈረንሳይ ዜጋ የቦታ ግዥ ፈቃድ ሲጠይቃቸው ምኒልክ በሰጡት መልስ
🗣 ‹‹ ያገሬ መሬት የሁሉም
ኢትዮጵያዊ ስለሆነ ፤ መሬት መሸጥ መለወጥ የሚችለው ሕዝቡ ነው ።
ደግሞስ የውጭ ዜጎች መሬት እንዲገዙ ከፈቀድኩና ባለመሬት ከሆኑ ፤ ለኔ
ምን ቀርቶ እገዛለሁ ? ›› አሉ ።

📜Share ➱----@ethioleboled
⚡️Acorns ቦትን በስልኮት በመጠቀም ብቻ በወር 100,000ሺ ብር በላይ ተከፋይ ይሁኑ 💸

🎁የ Acorns ቦት ጋር ልክ እንደገቡ የ
1000ብር ስጦታ ያገኛሉ በተጨማሪም 1 ሰዉ ወደ ቦቱ ሲጋብዙ በየቀኑ የ 50ብር ቋሚ ክፍያ ያገኛሉ

🔗ይህ የእርሶ የመጋበዣ
link ነው ለወዳጅ ዘመድዎ ያጋሩ 👇👇
https://www.tg-me.com/FreeEearnMoneyPay_Bot?start=r03892356955
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
በህይወትህ ትልቁ ጠላትህ ውስጥህ ያለው መጥፎ ሃሳብ ነው መጀመርያ እሱን ታግለህ አሸንፍ ከዛ ሌላው ይደርሳል ኧ
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
?❀✿ያልወለደች እናት❀✿👵
:በነኢማ ኸድር
ክፍል:5
"ፋይሲ ምን ሆነህ ነበር ምታለቅሰው በቃ ክፍልህ ስመጣ እንደዛ ሆነህ ሳይህ አላስቻለኝም"ብዬ ከአይኔ የ እንባ ዘለላ አራገፍኩ ፋይሰል እንደመደንገጥ እያለ "አረ ዳኒ ምንም ሆኜ አይደለም ምን ታካብጃለሽ በይ ተነሺና ተጣጠቢ፣ለባብሺ ከዛ እንወጣለን"ብሎ ሊወጣ ሲል "ፋይሲ"አልኩት ፈራ ተባ እያልኩ "ወዬ ዳኒ ምነው?"ብሎ ቆመ "መጀመሪያ ግን ሀኪም ቤት ደርሰን እንምጣ"ብዬው በአይኔ እማፀነዋለው "እንዴ ለምን ዳኒ ምን እንሰራለን ሀናን እኮ ከሀኪም ቤት ወታለች" ባላወቀ ዳር ዳር እንደሚሄድ ስለገባኝ "ፈይሰል አትቀልድ እንሄድና በሽታህ ምን እንደሆነ እናጣራለን ቆይ መሞት ነው ምፈልገው"እያልኩ ጮህኩኝ "ፋይሰል ነው ያልሽው ዳኒ? እንዴት አስችሎሽ በሄወቴ እኮ እኔ እንደዚ ብለሽ የጠሪሽኝን ቀን አላስታውስም ዛሬ ምን ተገኘ.."እያለ ሲጮህ መኪያ እየሮጠች መጣች ከተጠርን እኔና ፋይሰል የመጀመራያ ጭቅጭቃችን ነበር መኩ ያጨቃጨቀን ነገር ሴለገባት"ፋይሲ እሺ በልና ሂድ እኛንም አታስጨንቀን"ብላ አስማምታ እንድንሄድ አሳመነችው ወዴያው ለባብሼ አንድ የግል ሆስፒታል እየሄድን ሳለ እንደ ድንገት እማማ ደወለች እና የት እንደሆንን ጠየቀችን ሀናን ጋር እየሄድን እንደሆነ ነግራያት ስልኩ ተዘጋ ከሰአታት ብሀላ ሆስፒታሉ ደርሰን ወደ ውስጥ ዘለቅን ልብ ፈራ እጆቼ መንቀጥቀጥ ጀመሩ ገና ሀኪም ቤቱ ለራሱ ሲገባ ሚከብድ ነገር አለው ደግነቱ ወረፋ አልነበረም ካርድ አውጥተን ስማችን እስኪጠራ መጠባበቅ ጀመርን ከኛ በፋች 3 ሰዎች እየገብ ወጡ በ አራተኛው "ፋይሰል ነቢል"ሲባን ብድግ አልኩ "የተጠሪሁት እኔ አንቺ ምን ቤት ነሽ" ብሎ ተነሳ አብሬው ልገባ አልፈለገም ገብቶኛል "አብረን ነው ምንገባው" ብዬው ወደ ዶክተሩ ጋር ገባን የ ዶክተሩ ክፍል እንደገባን ሁሉ ነገር ጨለመብኝ ፈሪው ፋይሲን እዚው የማጣው መሰለኝ 'ወይኔ ግን ሁሉም እህቶች እንደኔ ወንድምቸውን ይወዳሉ፤በዛላይ እንደፋይሲ አይነት ወንድም ያላቸውስ ምንኛ ታድዋል'እያልኩ ለራሴ አወራሁ ዶክተሩ አብረን ስንገባ ሲያይ እየተገረመ በተራ በተራ ያየናል
ዶክተሩ፡"እሺ ፋይሰል ምን ነበር ኬዝህ?"አለ ጠንከር ባለ ድምፅ
"ያው ይነስረኛል" አለ የኔው ጉድ እየተቅለሰለሰ
ዶክተሩ፡"በቀን በቀን ነው ወይስ..?
"አይ አልፎ አልፎ በ አስራ አምስት ቀን እንደዛ ነገር"አለ ፋይሰል የዶክተሩን ጥያቄ እየተሰላቸ
ዶክተሩ፡እሺ ሊነስርህ ሲል ሚሰማህ ስሜት አለ?"አሁንም ጠየቀ
"አረ የለም..."ብሎ ሳይጨርስ ከአፉ ቅብል አርጌ አረ "አረ ዶክተር ያዞረኛል ይላል"ብዬ ዶክተሩን አየሁት ከዛ አንድ 3 ጥያቄ ካከታተለ ብሀላ ደም እንዲመረመር ወደ ላቦራቶራ ላከን ደሙን ሰተን ውጤት መጠባበቅ ጀመርን እኔ ፈርቻለው አስሬ ቁና ቁና እተነፍሳለው 30 ደቂቃው እንደ 30አመት ረዘመብኝኝኝኝ እንደምንም የሞት ሞቴን 30 ደቂቃ ተቀመጥኩ ላብራቶራስቱ ውጤቱን ይዞ ወደ ዶክተሩጋ ገባ ከ ሁለት ሰዎች ብሀላ ተጠርቶ ገባን
ዶክተሩ፡ውጤቱን አብሩቹ ልሰሙ ፍቃደኛ ናቹ"አለ በአወንታ ጥንቅላቴን ከላይ ወደታች ነቀነኩለት
ዶክተሩ፡"አንተስ?" ብሎ ፋይሰልን አየው
"በቃ ይነገረን" አለ ውስጡ መፍራቱን ንግግሩ ያሳብቃል.....

#ክፍል_➏ ይቀጥላል......

ሼር
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
👵❀✿ያልወለደች እናት❀✿👵
:በነኢማ ኸድር
ክፍል:➏
ጎሮሮውን እንደመጠራረግ አለና"well እንግዲ ፋይሰል በሽታህ ትንሽ ቆይተህበት ቢሆን ኖሮ ለህይወትህ አስጊ ነበር አሁንም ቢሆን ግን ደና ነህ ማለት አይደለም በሽታው አደገኛ ስለሆነ በጥንቃቄ መዳኒትህን መውሰድ ግድ ይልሀል"አለና ወረቀት ቢጤ ላይ ጫር ጫር አረገ "እንካ ይሄን መዳኒት ግዛ መቼም አንተን ለሚያክል ጎረምሳ በአግባቡ ውሰድ አይባልም አይደል"ብሎ ፈገገ
ዶክተሩ ቀለል አርጎ ለመናገር ቢማክርም እኔ ግን የተራራ ያህል አግዝፎት ጭንቅላቴ ላይ እንደከመረብኝ ነገር ንግግሩ የጭንቅላቴን ሚዛን እያሳተ እንደሰካራምም ያንገዳግደኝ ጀመር እኔ ተረብሼ ፋይሰልን ልረብሸው ስላልፈለኩ እንደምንም እራሴን አረጋግቼ ወደነ ሀናን ቤት እንድንሄድ ጠየኩት እሱ ዶክተሩ ያለውን ከቁብም ሳይቆጥረው ጭራሽ የሌለ ደስ ብሎታል ሀናን ቤት እንደደረስ መኪናውን አጥሩ ጥግ አቁመን ወረድን ሀናን ስታየን ደስ አላት ያቺ ቀጫጫዋ ሀናን አሁን አምሮባት ሰውነቷ ሞላ ብሏል ቀልታለች በቃ እንቡጥ ፅጌሬዳ ነው ምመስለው ገና ሳያት ቀናው እናት መሆን አማረኝ ምነው አግብቼ ወልጄ በነበር አስባለኝ የታቀፈችውን ልጅ እመተኛው ላይ አስቀምጣ ሳመችኝ ከ ፋይሰል ጋር በቃል ሰላምታ ከተለዋወጡ ብሀላ እኔ አልጋው ጠርዝ ላይ ተቀመጥኩ ፋይሲ ደሞ መሬት ላይ የተፈረሸው ፍራሽ ላይ ተቀመጠ ብዙም ሳይቆይ የሀናን ባል መጣ ከፋይሰልም ከኔጋም ለመጨረሻ ጊዜ የተያየነው የዛሬ አመት ልጅ እንቢ ብሏቸው ሀይለኛ ሰደቃ አውጥተው ነበር የዛኔ ነው እኛም የተገናኘነው ከፋይሰል ጋር ተቃቅፈው ሰላምታ ተለዋወጡ እኔን መጣና በቃላት ሰላምታ አጣደፈኝ በነገራችን ላይ የ ሀኒ ባል ፈታ ያለ ሰው ነው እና እስፔሻል ዶክተር ነው እኔም ከሀናን ጋር የቆጥ የባጡን ሳወራ ፋይሲም ከ ነቢል ጋር እየተጨዋወትን በመሀል የግዴታ ሰላቶችን ለመስገድ እየተነሳኝ 1 ሰአት ሲል ተሰናብተናቸው ወጣኝ እንዲ እንዲ እያለ ቀናት ሳምንታትን ሳምንታት ወራቶችን አርግዘው እየወለዱ ሀናን ከወለደች 4 ወር ሆናት ፋይሰልም መዳኒቱን በአግባብ እየወሰደ ከበሽታው ድኗል እንደ ድንገት አንድ ቀን ከረፋዱ 5 ሰአት ላይ አንድ ስልክ ወደ እማማ ስልክ ተደወለ የማይታወቅ ቁጥር እማማ ስልኩን አነሳችው "ሄሎ"አለች ከውስጥ ያለው ሰው ድምፅ ባይሰማኝም የሆነ መርዶ እንዳረዳት ያሳብቃል "ምን ብላ ስልኩን ለቀቀችው እኔም አብሪያት ክው አልኩኝ ለካ በሂወታችን የኛ የምንላቸው ሰዎች ሲጎዱ ወይ አደጋ ውስጥ ሲገብ ብቻ አይደለም ለካ የሚያስደነግጠን ለካ ድንጋጤያቸውም ያስደነግጠናል እማማ ክው ብላ ሳያት የኔም አሞቴ ፈሰሰ እማማ በሂወቷ እንዲ ክው ስትል አይቻት አላቅም ለዛ ደነገጥኩ "እማማ ምን ተፈጥሮ ነው"አልኳት ለመስማት አቅሙ ባይኛረኝም እሷን ለማረጋጋት እማማ ዝም አለችኝ "እማማ እእ?"አልኳች የሞት ሞቷን "ያይኔ አበባ" ብላ እንባዋን አጉረፈረፈችም በጣም ስላስጨነቀችኝ "እማማ ማልቀስ መፍትሄ አይሆንም ምን ተፈጥሮ ነው" አልኮት እማማ ያይኔ አበባ ምትለው ፋይሰልን ነው "እማማ ፋይሲ ምን ሆነ ተናገሪሪ"አልኳት እየጮህኩ "ከሰው ተጣልቶ እስር ቤት ነው"አለችኝ እርፍ! "ምን"
ብዬ የቆምኩበት ቦታ ላይ ደርቄ ቀረው "ቶሎ በይ ለ አባባሽ ደውይ ብላ ስልኳን ሰጠችኝ እጄ ተንቀጠቀጠ ስልክ ለመክፈት እስክቸገር! እማማ ሞተ እንደተባለ ሰው ቤት ውስጥ እያለቀሰች ትዟዟራለች እማማ የ ፋይሰል ነገር አያምጣው ነው ልክ በስለት እንዳገኘችው ነገር ነብሷን ትሰጠዋለች አይ እማማ ሁሌ እንዲ የምለው ለፋይሰል ያላትን ስሜት ስለማቅ ነው አንዳንዴማ እኔ ከነመፈጠራ ምትረሳኝ ይመስለኝና እፈራለው አባባ ጋር ደመልኩለት ወዲያው ወደ ፋይል ጋር ሃድ....


#ክፍል_➐ ይቀጥላል......
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
የሎጥ መንገድ - ተክሉ ጥላሁን.pdf
24 MB
📓 ርዕስ፦ የሎጥ መንገድ
✍️ ደራሲ፦ ተክሉ ጥላሁን

  ማጋራት መተሳሰብ ነው!
📚 @ethioleboled
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
#በቀጣይ

2 ሰአት ላይ

📓 ሌሎች አለማት
✍️ ታፈሰ ሙሉነህ


📓 ምርኮኛ
✍️ ቆንጅት ብርሃን

#ይጠብቁን!

📚 @ethioleboled
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜 (🍁𝙼𝚎𝚔𝚒🍁)
ሌሎች አለማት @Bemnet_Library.pdf
12.6 MB
📓 ሌሎች አለማት
✍️ ታፈሰ ሙሉነህ

  ማጋራት መተሳሰብ ነው!
📚 @ethioleboled
ምርኮኛ.PDF
9.8 MB
📓 ምርኮኛ
✍️ ቆንጅት ብርሃን

  ማጋራት መተሳሰብ ነው!
📚 @ethioleboled
2024/09/21 13:42:10
Back to Top
HTML Embed Code: