Telegram Web Link
💥📚ኢትዮ-ልቦለድ📚📖💥
Photo
ክፍል ሁለት ፦

ይሄውልሽ ሃሴት.... አንድም እንኳን
ካልሽው ስህተት አለው ማለት አልችልም ።

ነገር ግን ፦

በስሜት ውስጥ ሆነሽ እየታገልሽ ነው ። 
ምንም ብርቱ ቢሆን ስሜቱን ብቻ  የሚከተል ሰው የሚያሸንፍ አይመስለኝም ።

ራስ ወዳድ ስለሆንሽ ይመስለኛል ራስሽን ለጥቂት ቀን ማስደበር ከብዶሽ ዘለቄታዊ ደስታሽን ጠላት የሆንሽው

በርግጥ ፦

ድብርትሽን  ያበዛው 'ego' ሽ  ይመስለኛል። ራሴ ነኝ  ከምትይው እና በዙሪያሽ ናት ከሚሏት ጋ የምቶኚው ተጣርሶብሽ ነው  ኣ?

እንግዲህ ይመስለኛል ነው ፦

ሰው ራሱን ሲቀበል እና ሲወቅስ ነው ራሱን መግዛት እና ማሸነፍ የሚችለው ። የኔ ድክመት እና ማንነት ላይ ስፔሻላይዝ ያደረግሺውን ያህል ራስሽ ላይ ተመሰጪ  እስኪ ።

ሰው መጀመርያ ራሱን ሲያሸንፍ ነው በሌላው የማይሸነፈው.... በርግጥ ፍቅር የመሸናነፍ ጉዳይ አይደለም የሁኔታ እንጂ .....

በነገራችን ላይ ብሪሊያንት ነሽ ፣
ከጠበኩት በላይ ሁኔታዬን መረዳትሽ ደስ ይላል ነገር ግን  ማወቅ እና ያወቁትን መኖር ይለያያል።

ይልቁንስን ሃሱ   ፦

መሳቅ እየቀነሽ ነው  እንደውም እየተውሽ ነው ። አብረሺኝ ሆነሺም፣ ተለይተሽኝም ሁሉንም  እንቅስቃስዬን እያማሽው ነው

ጉድለትን ብቻ ማየት የሰነፍ ሰው በሃሪ ነው ።!

ትንሽ ፈታ እያልሽ ፦

ፈታ እያልኩ አለመታገሌ ፣ በወደኩ ቁጥር በእልህ ለመነሳት መጣሬ ደጋግሞ ጥሎኛል ደጋግሜ ልደምቅበት በተገባ ስፍራ አንሻለሁ።

ባይሆን  ፦

ሁሉም ነገር ቁምነገር አይደለም ሁሉም ነገር ጨዋታ አይደለም ።  አንድ ነገር ላይ ብቻ ሙጭጭ ማለት ድሉም እጦቱም ዋጋ ያስከፍላል።

እንከን በመተንተን ሰንፍናዬን በማጉላት ቅያሜ እንጂ ፍቅር አይገኝም ።በዚህ ውድድር አለም የሚያስወድደው  የሰዎችን ድክመት  እየነገርን አይደለም የሚወደድ ነገራቸውን እያሳየናቸው  ጭምር እንጂ

በነገራችን ላይ፦

ነገረኛ ሰዎች ውስጥ ያለው ሎጂክ ለክስ እንጂ ለደስታ የሚረዳቸው አይመስለኝም ። 

ሃሴት ....ቅንድቧን ከፍ አድርጋ አይኗን ፈጠጥ  አድርጋ እ ... ነገረኛ ነሽ እያልከኝ ነው ?

አላልኩም... ትልቅ ሰው ወሬን ሰፋ አድርጎ ሃሳብ አሳክሎ ማውራት አለበት የሚል ፈሊጥ ስላለኝ ጨዋታውን ማስፋፋቴ ነው  ........ ... ሃሳቡ ላይ እናተኩር ካልወከለሽ እሚወክለን ላይ እያተኮርን እንቃደድ ፦

ይልቁንስ ፦

ይገባኛል ህይወት ማለት ያላገኘነው እና ያጣነው ነው ። የሰው ልጅ ቀልቡ የበለጠ የሚገዛው በሁለት ሁነት ነው  ። 

ምድር ደም ካጣነው ነገር ውጪ መኖር የምንለማመድበት የምንፈልገውን የምናሳድድበት  ያለንን ለማቆየት የምንታገልበት ሜዳ ናት ።

በርግጥ ምድር  የምንፈልገውን ሁሉ መስጠት አትችልም ንፉግ ናት ...... !

የሆነው ሆኖ

ሂድ ስባል የምመጣ ባተሌ መሆኔን ማወቅሽ አስገርሞኛል ።
      


አይ እዮብ .... እንደ ወንድ ልጅ ጅል ፍጡር እንደሌለ ምስክር ትሆናለ አይደል ?

እንከኔ ያልከውን ሁሉ በምክር ስም ወርውረሃል ።

ሴት  እኮ አስራ አምስት አመት የሚበልጣት አዳም ሲሰጣት በአስራምስት  አመት ካልበለጣት 'Match' እንደማታደረገው ፈጣሪ ቀመሩን ሰርቶ ነው ።

ለወንድ ጡንቻ የጨመረለት እርቀታችን እሩቅ ስለሆነ ካሳ ነው

'anyways' እስካሁን  እየተሰናበትኩ እንደሆነ አልገባህም ።

የሄደን ሰው ሂጂ ማለት ጥላኝ ሄዳ አይደለም ልኬያት ነው ለማለት እንዲመችህ ነው ።

አያያዝህን አልወደድኩትም አልኩህ እኮ ፦
አታፈቅረኝም አልኩህ እኮ፦
ሁኔታህ ገብቶኛል አልኩህ እኮ ፦

አንተ ራስህ የስሜትህ ባሪያ ባትሆን የማትወዳትን ልጅ ተስገብግበህ አትወስባትም ነበር ። ሰው በወደቀበት ጉዳይ ላይ አዋቂ ሆኖ ሲመጣ ሳቄን መቆጣጠር ነው የሚያቅተኝ ።

ቅድም የደሰኳርከው ዲስኩር አብዛኛው ስላንተ ነው።
እኔን  አይወክለኝም !!

የሚያናድድ ነገር እያየሁ የምስቀው ስለምንድን ነው? ትክክል ማለት አንተ የምትፈልገው ሲደረግ ነው ? ?

ሰው አይደለሁም ወይ?
ስሜት የለኝም ወይ?

እያስከፋኝ ባለ ሰው ፊት ሳልደሰት ደስ ሳይለኝ የምስቀው ስለምንድ ነው?

ይልቁንስ ፦

Choose of paradox እያሰቃየህ ነው ።  ከእኔ ጋ የማትሆነው ስላልወደድከኝ አይደለም ሌሎች የሚፈልጉህ የመሰሉህ ሰዎች  ፍላጎትህ ላይ እንዳታተኩር አድርገውህ ነው ።

'improve your focus!'

አንበሳ ሲያድን አደኑ ስኬታማ የሚያደርገው ሊበላት ካሰባት ውጪ ሌላ ነገር ላይ ትኩረቱን ስለማያደርግ ነው ።  በልጅነት እንክብካቤ አላገኘህም መሰለኝ ተወዳጅ መሆንህን ለራስ ለማስመስከር እየባዘንክ ትመስለኛለህ ።

ከዛ ያሸነፍክ የመሰልካቸው ሰዎች ላይ እየመከርክ ትልቅ ነኝ ፣ አዋቂ ነኝ ዲስኩር ትደሰኩራለህ ። አስር ጊዜ ስለማሸነፍ እና ስለመሸነፍ ትተነትናለህ ።

የአሸናፊ 'Mentality' የሌለው ሰው ነው ሁሌ ስለመሸናነፍ የሚተነትነው  !!

ካንተ ጋ የነበርኩበት ጊዜን አልወደውም ።  ከትውስታዬ መሃደር ከትዝታዬ 'Deliberately ' እፍቅሃለሁ ።

ደስስ እያለኝ  ነው ስለይህ !! ሰነፍ ሰው ከሂወት ሲሄድ እጦት አይደለም ድል  ነው !!


ይሄ ሁሉ አንብባችሁማ👍👍 ተጭናችሁ እለፉ
ከአንድ ሳምንት በፊት ደውላ እንደደበራትና ከቻልኩ እንዳገኛት ጠይቃኝ ነበር!....እኔም በሰዓቱ “ውይ አንቺና ድብርት ግን ስትዋደዱ!... ወይ ለምን ተጋብታችሁ አብራችሁ አትኖሩም እ'? ብዬ ቀለድሁባት

...እሷም “ ሰርግ ደግሰን እወቁልን አላልንም እንጂ ከተጋባንማ ቆየን እኮ"አለችኝ...ያው ሁሌ ስለምንቀላለድ ንግግሯን ከ ቁም ነገር ሳልቆጥረው ሰሙኑን እንደማገኛት ነግሪያት ስልኩን ዘጋሁት!

ከሁለት ቀን በኋላ ደግማ ደወለችልኝ...ጫጫታ ቦታ ነበርኩ!...ስልኬ ሶስት ግዜ እንደ ጠራ አነሳሁትና “ቤቲዬ ጫጫታ ቦታ ላይ ነኝ ያለሁት አይሰማኝም መልሼ ልደውልልሽ!?...አልኳት!

"እዮብ በጣም ከፍቶኛል ምትችል ከሆነ አሁን ቤት ና በናትህ..አለችኝ

ያለሁበት ቦታ ጫጫታ ብዙም እያሰማኝ ስላልነበር “ቆይ ቤቲዬ ከ 5 ደቂቃ በኋላ ደውልልሻለሁ እሺ' ብዬ ስልኩን ዘጋሁት!....ቀኔ አድካሚ ስለነበር መደወሉን ረስቼ ቤቴ እንደገባሁ እራቴን እንኳ ሳልበላ ተኛሁ!...ጠዋት ተነስቼ ስልኬን ሳየው ቴክስት ገብቶልኛል... ቤቲ ነበር የላከችው!..ሰዓቱን አየሁት!... ትናንት ምሽት ሁለት ሰዓት

ነው የተላከው….. “ቻው እሺ እዮብዬ የማልደበርበት ቦታ ሄጃለሁ" ይላል!...ምን ለማለት ፈልጋ ነው? ግራ ገባኝ...ስልኳ ላይ ደወልኩ አይነሳም!...ደጋግሜ ሞከርኩ መልስ የለም!...ጫማዬን አደረኩና የቤቴን በር እንኳ ሳልቆልፍ በፍጥነት ወጣሁ!

የነ ቤቲ በር ላይ ስደርስ ድንኳን ተጥሏል! ልቤ ለሁለት ሲሰነጠቅ ተሰማኝ!...እግሬ እየተንቀጠቀጠ ወደ ውስጥ ገባሁ!...እናትየው የቤቲን ፎቶና የሆነ ወረቀት በእጃቸው ይዘው ግራና ቀኝ በሁለት ሰዎች ተይዘው እያቃሰቱ ቁጭ ብለዋል! ...ሰማይ ምድሩ ተደበላለቀብኝ!...የግዴን “ም… ምንድነው ማዘር'' ብየ ጠየኳቸው!...ምንም መልስ አልሰጡኝም!...ከ ጎን ያለችው ልጅ እምባ በተናነቀው ድምፅ! ልጃቸው አርፋለች አለችኝ!....''ማ ..ቤቲ?'' አልኳት...''አዎ'' አለችኝ!....''እራሷን ከ ማጥፋቷ በፊት ይሄን ወረቀት ፅፋ ነበር'' ብላ ከ እናትየው እጅ ላይ ወረቀቱን ወስዳ ሰጠችኝ!...እጄ እየተንቀጠቀጠ ተቀበልኳትና አየሁት ....''አይዞሽ የሚለኝ ሰው ብቻ ነበር የፈለኩት ....'' ይላል! ምንም አላልኩም.... ወረቀቱን እንደያዝኩ እግሬን እየጎተትኩ ከድንኳኑ ወጣሁ!...በእርግጥ ወዴት እንደምሄድ አላውቅም!

! ይሄ ፅሁፍ የሚያስተምረን በሂወታችን ችላ የምንለው ነገር እስከ ሂወት ማጣት ድረስ ዋጋ እንደሚያስከፍለን ነው


::አንበበው ከወደደት👍👍 ተጭናችሁ እለፉ
🔴ምን እንደሚቆጨኝ ታውቃለህ ?

ካንተ ጋር ያሳለፍነው ሳይሆን

ተስፋ ያደረግኩት ነው
💙🔚
አልቦ ዘመድ - ብርሃኑ ድንቄ.pdf
3.5 MB
"አልቦ ዘመድ" እንደያዘው ጠቃሚ ሀሳብ ብዙም ያልተዋራለትና ያልተነገረለት ምርጥ መጽሐፍ ነው።አንብቡና አትርፉበት።

ማጋራት መተሳሰብ ነው!
📚 @ethioleboled
💫ለፈገግታ 😁



ህፃን ማጫወት አለ አይደለ "አቡቱቱ ምንድ ነው እሹ...እምሽቅንን"...ምናምን ማለት ብፈልግም አልችልበትም ነበር።እንደምችል ያወቅኩት ከትናንት ወዲያ ነው....😁


ነገሩ እንዲህ ነው...ከዶርሜ የወጣሁት ምሳ ልበላ ነው...በልቼ በዛው class ልገባ...ታዲያ እጄን ታጥቤ መመገቢያ ካርዴን ላወጣ እጄን ኪሴ ስከት ነገርየው የለም...ወደ ቦርሳዬ ተሻገርኩ...አሁንም የተቀየረ ነገር የለም...I was like "ቤብ prank መሆኑ ነው...አትቀልድ በናትህ..."...(ቤብ ያልኩት መመገቢያ ካርዴን ነው...😁)...መብላቷን ሳታውቅ እጇን ታጠበች ያሉት ለእኔ መሆን አለበት አልኩ በሆዴ...


ወደ ቲከሯ አይኔን ስሰድ ተስፋ ቆረጥኩ...ይቺ ሴትዮ መመገቢያ ካርድ ይዤ እንኳን ባታስገባኝ ደስ እንደሚላት ሁሌ ፊቷን በማገለባበጥ ትነግረኛለች....አልሰማትም እንጂ....ሰአቴን አየሁ...ዶርም ሄዶ መምጣት አይታሰብም...ካፌው ሊዘጋ 2 ደቂቃ ነው የቀረው..."እና ውጪ አትበዪም ወይ" ካላችሁኝ ደግሞ እፈነክታችኃለሁ😏


ይቺ ሴትዮ ያለ ካርድ እንድታስገባኝ ሁለት መስፈርት ማሟላት አለብኝ....


አንደኛው ወንድ መሆን ነው።...እሱን አልችልም...በዚህ አጋጣሚ ለእኛ ጊቢ ወንዶች ያለኝ አድናቆት ላቅ ያለ ነው...በቃ አንድ ቃል ወርወር...ከዛ ጥርስ በጥርስ ማድረግ...ከቲከር እስከ ወጥ ጨላፊ...ከኩባያ አጣቢ እስከ ሳህን አጣቢ..ከዳቦ አከፋፋይ እስከ ላይብረሪስት(ዳቦ ስል ሌላ ነገር እንዳታስቡ🙄)....ወይ ጥበሷቸው ከአመት አመት ከምታቁለጨልጯቸው😂

ሁለተኛው ደግሞ ልጇን ማጫወት😓...
ከራሴ ጋር እየተሟገትኩ ተጠጋሁ...


"አቡቱቱቱ እምንድነው እሹ የእኔ ሚጢጢ....እምሽቅንንን..."...ጀመርኩ...የሆነ ሰአት ለአፍታ ዝም እያልኩ እሄ ድምፅ ከእኔ መውጣቱን መፈተሽ ገባሁ....ድዱን እያሰጣ ተጠጋኝ...ከዛ ሊፋታኝ ነው...

"ኧረ በናትህ አትጃጃል እርቦኛል ለራሴ...".....በሆዴ ነው።ሴትየዋ ደስታ ሊገላት ደረሰ...እንኳን ካርዴን እንደረሳሁ ላብራራ ቀርቶ ታምኑኛላችሁ  ሳልጠየቅ እንደገባሁ..(ወዲያው የወለዱት ሲሳም....የሚባለው ተረት ነው የመጣልኝ) ....


እስከዚህ እኮ ደህና ነበርኩ....ዛሬ ካርዴን ይዤ በኩራት ላጥ ላጥ ብዬ ልገባ ስል ህፃኑ ገና ሲያየኝ እየተፍነከነከ ሲወጣብኝ ነው በቃ እንደ ማበድ ያደረገኝ.... ከሁለት ቀን በፊት ያደረግኩትን ረገምኩት..


"አንተ እኩያህ መሰልኩህ እንዴ...ኧረ በፈጠረህ እኔ ሰላማዊ ሰው ነኝ...ምኔ ነው ኢቶጲስን የሚመስለው...."....አሁንም በሆዴ ነው🤨



እኔ ብቻ ነኝ ግን....?



ሸዊት


👉
https://www.tg-me.com/ethioleboled
Based on true story❤️

   

       ግን የኔ አይደለም😊...አደራ ቤተሰብ "የእኔ አይደለምን ምን አመጣው"....ምናምን ብላችሁ ነገር ባለመብላት ተባበሩኝ...ከተስማማን ፅሁፌን እነሆ.......



ለመጀመሪያ ጊዜ መታቀፍ ፈለግኩ...ልብ በል...ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ያልኩት...


ከዛ አንተ ምን አደረግክ???


የመታቀፍ ፍላጎቴን...በሰው ጉያ የመደበቅ ፍላጎቴን...ለአፍታ የመሰወር ፍላጎቴን...እነዚህን ከመታቀፍ ጋር የሚደመሩ የመጀመሪያ  ስሜቶቼን የመጨረሻ አደረግካቸው...

እግዚአብሄር ይስጥህ ሳልወድ በግዴ ይቺን መከረኛ አለም ተጋፈጥኳት.. መራራ ፅዋዋን ጠጣሁ...እድሜ ላንተ ሞቴ የቀረበ በመሰለኝ ማግስት  ከአምላኬ ጋር ተጣበቅኩ...አላስጠጋ ስትለኝ እርሱ ሰበሰበኝ...ለአፍታ ነክተህ ለመመለስ የተጠየፍካት እኔን እርሱ ሳያቅማማ እቅፍቅፍፍፍ አረገኝ....


ያኔ እኮ ካንተ ጋር መጥፋት ፈልጌ ነበር...እጅህን መያዝ ፈልጌ ነበር...አንተ ጋር የምመጣው እኮ እንደምለው ልወቅስህ አልነበረም...ይዘኧኝ ጥፋ ልልህ ነበር እኮ አመጣጤ...ያኔ ምኞቴ አንድ ብቻ ነበር...እንድትፈቅድልኝ ብቻ ነበር የምፈልገው...


ህይወቴ ብልህ መልስህ ምን ነበር...?
ብስምህስ መልስህ ምን ነበር....?
ውስጤ ያለውን ጠራርጌ እንዳልነግርህ ፊትህ ገፋኝ...


ከዚህ መከረኛ ስሜት መላቀቂያ ባጣ ባልንጀሮችህን የሙጥኝ አልኩ...ቢያንስ ስላንተ ለመስማት...በሰአቱ ደህንነትህን ማወቅ በጥቂቱም ቢሆን ያሳርፈኝ ነበር....


አሁንም እምብዛም አላረፍኩም...ባንደኛው ቀን ያበጠ ይፈንዳ ከዚህ በላይ ምን ይመጣል ብዬ ስሜቴን አንድም ሳላስቀር ነገርኩህ....


ከዛ መልስህ ምን ሆነ....?


"ለወንድ ብለሽ እንደዚህ አትሁኚ...."...የዛን እለት ስብራቴን በምንም አትጠግነውም...በዘመነ ኮሮና  አንተ ጋር ለመምጣት ተከናንቤ የወጣሁት ነጠላ በእንባ ረጠበ...እሱ ጋር ነኝ ብዬ ረግጬው ያለፍኩትን የሰፈሬን ታቦት ስመለስ በደንብ አስተዋልኩት...


አውጣኝ ከዚህ ስሜት...እኔስ ልጅህ አይደለሁም ወይ አልኩት...ምነው የሞቴን ደብዳቤ እንትለውጠው የግድ ባህራንን መሆን አለብኝ ወይ አልኩት...እየሞትኩ እኮ ነው እንዴት አይታይህም ...ከፈጣሪዬ አማልደኝ ብዬ አለቀስኩበት....ምን እንደገረመኝ ታውቃለህ ረግጣኝ ሄደች ብሎ ጥያቄዬን አለመናቁ....


ረሳሁህ...ልክ እንዳልተፈጠርክ...በቃሽ ሲለኝ ብዙ የምኖርበት አላማ እንዳለኝ ገለጠልኝ....ሲገባኝ ለካ አንተ የሞቴ ደብዳቤ ነበርክ...አንተን ከአእምሮዬ ነጠቀህና የምኖርባቸውን ምክንያቶች ሰገሰገ...ደብዳቤዬን ቀየረው...አየህ እኔም ባህራን ሆንኩ..

ለመጨረሻ ጊዜ ላንተ የምፅፈው ይሄንን ነው..ስላላቀፍከኝ አመሰግናለሁ ....ስለገፋከኝ እግዚአብሄር ይስጥህ...ርቀህ ከፈጣሪዬ ስላቀረብከኝ እድሜ ይስጥህ......


እስቲ የተዉንን ሰዎች እናመስግናቸው....በነርሱ ድልድይነት ከፍ ያለ ቦታችንን ለገለፁልን ሰዎች አንዴ ከመቀመጫችን ተነስተን🙏





Shewit dorka





https://www.tg-me.com/ethioleboled
💥📚ኢትዮ-ልቦለድ📚📖💥
Photo
አትሂጂብኝ…

ገና በጠዋጡ ስልኬ እየጮኸ ከተኛሁበት ቀሰቀሰኝ ማን እንደሆነ እንኳን ሳላይ ስልኩን አንስቼ "እእእ..." አልኩኝ ሄሎ ማለቱ ትንሽ ከብዶኛል "ያቡ የት ነህ? ቤት ነህ? ማታ በጊዜ ገባህ? ራስህን አመመህ እንዴ? አሁን ቤት ነህ አደል?" የመአት ጥያቄ ይዘንብ ጀመር

ግራ ገባኝ "ማነው" ብዬ ስልኩን ከጆሮዬ ላይ አንስቼ አይኔን የምችለውን ያህል ጠበብ አርጌ ማን እንደሆነ ለማየት ሞከርኩ ግን ማየት አልቻልኩም አይኔን ደጋግሜ እየጨፈንኩ እና እየገለጥኩ ስልኩን ለማየት ሞከርኩ ጨፍኜ በገለጥኩ ቁጥር እንደ አዲስ እየደበዘዘ ይታየኛል... ደነገጥኩ "እንዴ! አይኔ ምን ሆኖ ነው" ከተኛሁበት ተስፈንጥሬ አልጋው ላይ ቁጭ ለማለት ስሞክር የሆነ ነገር ጭንቅላቴን የመታኝ ይመስል ራሴን ወጥሮ ያዘኝ በትንሹ ራሴን ነቅነቅ እያረኩ ከቆየሁ በኋላ አይኔን አሸት ከቅድሙ የበለጠ አሁን ብዥ አለብኝ ፈራሁ አይኔ ማየት ሊያቆም ትንሽ ደቂቃ የቀረው መሰለኝ በዚ መሀል በእጄ ከያዝኩት ስልክ "ሄሎ ያቡ አይሰማም ሄሎ ሄሎ" ይላል

የወንድ ድምፅ ነው...ማን እንደሆነ በድምፁ ለመለየት እንኳን አልቻልኩም ጆሮዬም ልክ እንደ አይኔ ብዥብሎበታል

ምን ሆኜ ነው ዛሬ!? ጭራሽ እውን አልመስል ብሎ "በህልሜ ነው" እያልኩኝ ራሴን ማሳመን ጀመርኩ ከስልኩ ሚወጣው ድምፅ አሁንም ይሰማኛል

"ሄሎ..ሄሎ..ሄሎ ያቡ"

ከጓደኞቼ ውስጥ አንዱ እንደሆነ አውቄያለሁ ነገር ግን ማንእንደሆነ ማወቅ አልቻልኩም

ባለማወቄ እያፈርኩ "ሄሎ ማን ልበል" አልኩኝ

"ያቡ ቀሰቀስኩህ እንዴ ዳግም ነኝ"

ዳግም ማነው? ዳግም ሚባል ጓደኛ አለኝ?

በድጋሚ ሼም እየያዘኝ

"ይቅርታ ዳግም አላወኩህም" አልኩት

እየሳቀ ''ኸረ ያቡ ስካሩ አሁንም አለቀቀህም ወይስ እየቀለድክ ነው ይልቅ አሁን እንዴት ነህ? ማታ ኮ ጠጥተህ" እስኪጨርስ አልጠበኩትም

"ጠጥተህ ምን!? ማ እኔ ጠጥቼ?" ስልኩ ተቋረጠ

ራሴን በጥያቄ ማስጨነቅ ጀመርኩ "ማታ የት ነበርኩ? አሁንስ የት ነኝ?" ያለሁበትን ቦታ በ አይኔ እየዞርኩ ማየትጀመርኩ

ቤት አደለሁም! አሁን የበለጠ ደነገጥኩ ዙሪያዬን ሳይ አንድ ጠበብ ያለ ቤርጎ ውስጥ ግድግዳ ላይ ከተሰቀለ ቴሌቪዥን እና ጥግ ላይ ብቻውን ከተቀመጠ ወንበር ጋር ራሴን አገኘሁት

ካለሁበት ተነስቼ ለመውጣት ብሞክርም ሚዛኔን መጠበቅስላልቻልኩ እየተንገዳገድኩ የክፍሉ ውስጥ ወዳለው አንድ ወንበር ላይ ሄጄ ተቀመጥኩ ራሴን መጠየቅ ጀመርኩ "ምን ጠጥቼ ነው? ለማስታወስ በጣም እየሞከርኩ ነው "ማታ የት ነበርኩ? ከማን ጋር ነበርኩ? ማነው እዚ ያመጣኝ? አሁንስ ለምንድነው ሚያዞረኝ?" ራሴ በጥያቄ ብዛት ሊፈነዳ ደረሰ

በዚ መሀል እጄ ላይ ያለው ስልኬ ድጋሚ ጠራ

አይታየኝም ብዬ ስላሰብኩ ማን እንደሆነ ለማየት አልሞከርኩም ዝም ብዬ አነሳሁት "ሄሎ" አለኝ...አሁን የማን ድምፅ እንደሆነ ለየሁ "ሄሎ ዳጊ ኸረ ምንድነው የት ነኝ በጣም እያመመኝ ነው' ብዬ የ እርዳታ ጥሪ በሚመስል ጥያቄ ተማፀንኩት "ተነስና ፊትህን ታጠብ ትንሽ ቀለል ይልልሀል" አለኝየጓደኝነቱን

እኔ ግን ፊቴን ከመታጠቤ የበለጠ ያስጨነቀኝ ብዙ ነገር አለ

መጠየቅ ጀመርኩ "ማታ ምን ተፈጠረ" ብዬ የመጀመሪያ

ጥያቄዬን አቀረብኩለት

''ኸረ ያቡ ማታ ኮ በጣም ጠጥተህ ማይሆን ነገር ስትናገር ነበር

"በደንብ ማስታውሰው ሰላም ጋር ደውለህ ብዙ ነገርእንዳልካት ነው"

ይሄን ስሰማ የልብ ምቴ ጨመረ ሰሊ የኔ ፍቅረኛ ናት ምናልባት እሷ ጋ ደውዬ እወድሻለሁ ያላንቺ መኖር አልችልም ምናምን ብዬ ነው ሚሆነው ብዬ እያሰብኩ.. "እሷ ጋር ደውዬ ምን አልኩ?" መልሱን ቶሎ እንዲመልስልኝ እኔም ቶሎ ነው የጠየኩት ከመጀመሪያው ጀምሮ ይነግረኝ ጀመር "እየሰደብካት ነበር "ከዛሬ በኋላ ላይሽ አልፈልግም ባንቺ ምክንያት ብዙ ነገር አጥቻለሁ ከሂወቴ ውጪልኝ ምናምን። ብቻ ብዙ ነገር ብለሀል ያቡ" ብሎ ዝም አለ ልቤ ሲመታ ጆሮዬ ድረስ ይሰማኛል

"ማ..! እኔ ነኝ ሰሊ ጋር ደውዬ ይሄን ያልኩት?'' ለራሴ ማመን እያቃተኝ ጠየኩት

"ለሊቱን ሙሉ ስትደውልልህ ነበር አላነሳኸውም?''

"ቆይ አንዴ" አልኩና ስልኩን ዘግቼ ማን እንደደወለ መየትጀመርኩ

ድነጋጤው ነው መሰለኝ አሁን ጥርት ብሎ ነው ሚታየኝ

46 missed call .. ይላል እሷ ነችእጄ መንቀጥቀጥ ጀመረ...


ፀሀፊ የአብስራ

ከወደዱት ይቀጥላል ግን 👍👍ላይክ እያረጋችሁ
መህምሩ ለተማሪዎች ወደፊት ማሳካት የምትፈልጉትን ነገር በሙሉ ጽፋችሁ በነገው ዕለት እንድትመጡ ብሎ አዘዘ..

☑️“በዚያ ምሽት ተማሪው ሕልሙን እና ማሳካት የሚፈልገውን ሁሉ ጻፈ እናም እንዲህ ይል ነበር በመጪው 10 ዓመታት የፈረስ እርሻ ባለቤት እንደሚሆን፣ አራት ሕንጻዎች እንደሚኖሩት፣ 200 ሄክታር የእርሻ መሬት እና 4,000 ካሬ ቤት እንደሚኖረው ጻፈ ለዚህም ዝርዝር የወለል ፕላን አዘጋጀ። እና በሚቀጥለው ቀን ለአስተማሪው አስረከበው።

ከሁለት ቀናት በኋላ ወረቀቱን መልሶ ተቀበለ።
አስተማሪው ወረቀቱ ላይ ጉልህ "ኤፍ"አድርጎበታል። ልጁም ተበሳጭና መምህሩን ሄዶ አናገረ።

⚫️አስተማሪውም ይህ እንደ አንተ ላለው ወጣት ልጅ ከእውነታው የራቀ ሕልም ነው። ገንዘብ የለህም፣ የድሃ ቤተሰብ ልጅ ነህ፣ ምንም ሀብት የለህም። የፈረስ እርሻ ባለቤት መሆን ብዙ ገንዘብ ይጠይቃል። 4ሺህ ካሬ እና ትልቅ እርሻ ላንተ "ላም አለኝ በሰማይ ነው" ብሎ ተዛባበተበት። እናም እንዲህ አለ "ማታ እንዳዲስ ሊሳካ የሚችል እቅድ ጻፍና ውጤትህን አስተካክልልሃለው"

➡️"ልጁ ወደ ቤቱ ሄዶ ብዙ አሰበበት። አባቱንም ምን ማድረግ እንዳለበት ጠየቀ። አባቱም "ተመልከት ፣ ልጄ፤ እዚህ ጋር የራስህን ሐሳብ መወሰን አለብህ። እኔ ግን በጣም አምንብሃለውና ልብህን ስማ" አለው።
በነገታው እቅዱን ምንም ሳይቀይር መልሶ ሰጠ አስተማሪውም በ"ኤፍ ግሬዱ" ጸና።

ከዓመታት በኋላ ያ መምህር አርጅቶም እያስተማረ ሳለ አንድ ቀን ማለዳ ላይ በቴሌቭዥን የአንድ ወጣት ቃለመጠይቅ ይቀርብ ነበር... ወጣቱ ልጅ እያለ አሳካዋለሁ ካለው አንድም ያልቀረው የናጠጠ ሀብታም ሆኖ ነበር። እንዲህ አለ "ሕልሜን አስተማሪዬ ሊሰርቀኝ ሲታገል እንደምንም ነበር የተረፍሁት... እኔም ህልሜን እሱም ኤፉን ወሰደ"

➡️የዛኑ ቀን መምህሩ ለተማሪዎቹ ወደፊት ማሳካት የምትፈልጉትን ጻፉልኝ ብሎ አዘዘ በነገታው መለሱለት ለሁሉም የሰጠው ውጤት "ኤ"ነበር።
***
➡️ሞራል፡ መምህራን የጠቀሙ መስሏቸው የስንቱን ሕልም ሰረቁ። በሕልማችሁ አትደራደሩ ለማሳካት የምታስቡት ሁሉ የሚደረስበት እና የተደረሰበት
ነው።
***
💫ዝም ብላችሁ ሳቁ😂😂


እኔ ሲጀመር እነዚህ ጓደኛ ተብዬዎች እያሉ ጤነኛ አልሆንም😁...በሳቅ ቢሞት ኖሮ ይሄኔ ሞቼ ተረስቼ ነበር.....

ከአራት ወር በፊት የሆነ ታሪክ ነው።

አንድ ጓደኛዬ ናት....ላይብረሪ ስትገባ ያየኃት ግፋ ቢል ከ 5 ደቂቃ በፊት ነበር....እየተክለፈለፈች ስትወጣ ጤንነቷ አጠራጥሮኝ መጠየቅ....

"ደህና ነሽ ሴትዮ...አሁን አ እንዴ የገባባሽው...."

"ባክሽ ፋራው መጥቶ ነው...."(የፋራውን ማንነት ለማወቅ ማንበባችሁን መቀጠል ነው)....ማውራቷን ቀጥላለች...."ግራ ግብት የሚለኝ ከየት ነው ሚመጣው...በቀን ሰላሳ ጊዜ ቆይ ሌላ ጓደኛ የለውም እንዴ..."


"ካካካካካ....."....።

"ቆይ ግን እዚ ቅርብ አለ አ እንዴ  እዛ አትሄጂም..."

"ባክሽ ተዘግቷል..."...ከዚህ ንግግሯ በኃላ እንደመሮጥ እያለች ከአይኔ ተሰወረች።

ማታ ላይ ሀዘን የወረራት ሴት መስላ ዶርም ተቀምጣ አገኘዋት...ቆሌዬን አረጋግቼ ምን እንደሆነች መጠየቅ....መልሷን ስሰማ እኔም ነጠላ ዘቅዝቄ ከእሷ ጋር "አይ ሰው ከንቱ" ማለት ጀመርኩ....

"ቅድም ፋራውን ላባርር ሽንት ቤት በገባሁበት ስልኬ ከእጄ አምልጦኝ ገባ....".....ነበር መልሷ(ፋራው ማን እንደሆነ የገባው...😉)

"ማለት ያንቺ ስልክ... ማለት አዲሱ ስልክሽ...."....መቀጠል አልቻልኩም....



አሁን ከአራት ወር ቤተሰብ ጅንጀና በኃላ ባለ ስልክ ሆናለች....(የኔዎቹ አስራ አራት አመት ቢጀነጀኑም ኮሽ አይልባቸውም😕).....ከዛላችሁ እኔ እህታችሁ አዲሱን ስልክ አስታኮ እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ምክር ቢጤ መወርወር አሰኘኝ...

"አደራ ከዚህ በኃላ ስልክሽን ይዘሽ መፀዳጃ ቤት አትግቢ...አንዳንዴ ፋራውን ፊት ለመንሳት ሞክሪ...ማስተዋል አለብሽ...ገብቶሻል አ አለማስተዋል ይታይብሻል..ነገ ምን ይመጣብኛል...."....ምናምን እያልኩ ከእርስ እየወጣሁም እየገባሁም ስቀበጣጥር አስቁማኝ ....


"ኧረ ጀለስ አረጋጊው...በዚህ አራት ወር የሆንኩትን እኔ ነኝ የማውቀው..."...ብላ ዝም አለች..

"so ከዚህ በኃላ ስልክሽን ይዘሽ ሽንት ቤት አለመግባት ነው አየሽ ለምሳሌ..."....ያልኩትን ሳልጨርስ ምን ብትለኝ ጥሩ ነው😂😂

"ሴትዮ አፍሽን ዝጊ...አይገርምሽም እንደውም ከዚህ በኃላ አላ*ም...."

"ካካካካካካካካካ እውነትም መሮሻል...."


😂😂😂😂


እና አንዳንዴ የገባበት ሁኔታ በደንብ አድርጎ የመከረውን ሰው መምከር ትርፉ አፍ ማድከም ነው።


መልካም ውሎ።



ሸዊት።



https://www.tg-me.com/ethioleboled
ለፈገግታ😂




"ማንን ነበር ያስገባሽው"....

"ማለት ማሚ..."(የዶርም ተቆጣጣሪ ፕሮክተሮችን ማሚ ነው ምንለው)

"ጥለኃኝ አትሂድ እያልሽ የነበረው ማንን ነው...."

"ኧረ ማሚ ትረካ እየሰራሁ  ነው....ከፈለግሽ ላሰማሽ"


"ኧረ...ትረካ...ሌላስ...እኔ መጫወቻሽ ነኝ....አታታልዪኝም....አሁን ስታዋሪው የነበረው ልጅ ማነው...".....ብላ ባልዲ ውስጥ ሳይቀራት ፈተሸች😂....የሆነ ሰአት የፒሲ ቦርሳ ስትከፍት ሳቄ አመለጠኝ....እግረ መንገዷን ስቶቭ ካላቸው ብላ ይሆናል ብዬ ራሴን አረጋጋውና ሳቄን አባርኩት....

"ይኧውልሽ ሸዊት ትሰሚኛለሽ አንቺም ጎረምሳሽም ችግር ውስጥ ከምትገቡ በጨዋ ደንብ እንነጋር...ቆይ በመስኮት አዘልለሽው ነው...."....አልረዳ ስትለኝ ሪከርድ እያደረግኩ የነበረውን የትረካ ክፍል ከፈትኩላት....

"አዎ እንደዛ ነበር ለጎረምሳሽ ስትይው የነበረው...ከተያዝኩ እንደዚህ አታልላታለሁ ብለሽ ቀድመሽ ተዘጋጅተሽልኛል አንቺ....እከከከከከ ባለጌ...አይጣል አንቺን የወለደች ቱቱ....."....ውሀ በሚያነሳ ነጥብ ላይ ፕሮክተር ይረዳኛል ብሎ ከማስረዳት አንድ አህያ ጋር ሄዳችሁ

"እኔ ህይወት መሮኛል...ቺኬ ጥላኝ ፈርጥጣ ይኧው ምግብ የመጨረሻ ዘግቶኛል"....ብትሉት የወንድምነቱን ይመክራችኃል😂 አፍ አውጥቶ "በቃ ብሮ ተዋት...እኔ ጋር አንድ አራት አሉ...ያው አህያ ስለሆኑ እንዳይደብርሽ እንጂ...እና አንድ አንዴ እኔ ጋር እየመጣሽ ጋጪ... ያጋጥማል...."....ሊላችሁ ሁላ ይችላል😂


ብቻ ከብዙ ንትርክ በኃላ ጓደኛዬ መጣች....

"ማሚ አንዴ ነይ ላናግርሽ..."...ብላ ይዛት ስትወጣ ምን ብላ እንደምታሳምናት ግራ እየገባኝ መምጣታቸውን በጉጉት መጠበቅ ያዝኩ።


ከጥቂት ደቂቃዎች በኃላ ተያይዘው መጡ...ለያዥ ለገናዥ ያስቸገረችው ሴትዮ አሁን እንደ ተነፈሰ አፉፋ ሙሽሽ ብላለች...ጓደኛዬ ፊት ላይ የታፈነ ሳቅ አለ...ሴትየዋ ፊት ላይ ደግሞ የሆነ አይነት አዘኔታ....

"ምፅ...ዘንድሮ ነው አይደል የምትመረቂው...."

"አዎ ምነው...."...ይሄኔ ጓደኛዬ ከነ ሳቀ ፊቷ ከጎኔ ቆመችና በእጇ ቀስ አድርጋ ጎነተለችኝ....

"አይዞሽ...እኔም ሴት ልጅ አለኝ...አይዞሽ እማ...የኪዳነ ምህረትን ፀበል ተጠመቂ...አይዞሽ ምንም አያመጣም...አይነጥላ እኮ ነው....ውይ የእኔ እናት....."......ጓደኛዬ የሚተናነቃት ሳቋን በውሸት ሳል እየደበቀች ክንዴን በስሱ ትቆነጥጠኛለች።

ጀለስ ለካ መንፈስ ያማታል ብላት ነው ያረጋጋቻት....


"አንድ አንዴ በሀይለኛው ያስጮሀታል ስላልኳት የሚጮሁ ፓርቶች ላይ መስኮት መዝጋትና በር መጠቅጠቅ አይጠበቅብሽም...እኔ ጓደኛሽ ልኑርልሽ ካካካካካ".....


አሁን ይቺን ልጅ ብገላት ይፈረድብኛል🤨



እናላችሁ አሁን እንደ እንቁላል ነው treat የምደረገው😂



የትረካውን ሊንክ ቻናሌ ላይ ታገኙታላችሁ😊መልካም አዳር።




https://www.tg-me.com/ethioleboled
💥📚ኢትዮ-ልቦለድ📚📖💥
Photo
አትሂጂብኝ…

ፀሀፊ የአብስራ

እስካሁን የዘነበብኝ እያንቀጠቀጠኝ ነው

የነ ሰላምን በር በሀይል ማንኳኳት ስጀምር

እናቷ ከ ጊቢው ውስጥ ሆነው "ኸረ ማነው!'' እያሉ በሩንለመክፈት እየመጡ ነው

ድጋሚ በሩን በሀይል ደበደብኩት

"ኸረ ቀስ ማነው!'' እናትየው እየተቆጡ በሩን ከፈቱት
የሰላምን እናት ለመጀመሪያ ግዜ በአካል አየኋቸው እስከዛሬ የማውቃቸው ሰላም ስለ እሳቸው ስትነግረኝ ነው

ዛሬ ግን አይን ለ አይን ተያየን

ከሰላም ጋር በጣም ነው ሚመሳሰሉት

በተለይ አይናቸው እና አፍንጫቸው አከባቢ እራሷ ሰላምን!ሰላም ቁጭ በእናቷ ነው የወጣችው!

በሩን ከከፈቱ በኋላ የልብሴ መጨቅየት እና የሰውነቴን መንቀጥቀጥ ሲያዩ ደነገጡ

እብድ መስያቸው ነው መሰለኝ ግራ ተጋብተው "ምነው ልጄ ምን ሆንክ" ብለው ጠየቁኝ ገረመኝ! ድምፃቸውም ከሰላም ጋር አንድ አይነት!

ብርዱ እያንቀጠቀጠኝ ''ሰሰሰ....ሰ..ሰላምን ፈልጌ ነው"
ቆጣ ብለው "ሰላም የለችም!'' አሉ "የ.የ.የ.የ የት ሄ.ሄደች?"

አልኩኝ በ እናትየው ትከሻ በኩል ወደ ጊቢው እያየሁ "እኔ ምን አውቄ" አሉና በሩን ገፈተሩት እዛው በቆምኩበት በሩ "ጓ..." ብሎ ተዘጋ

ጠረጠርኩ...እናትየው የሆነ ሚያውቁት ነገር ሳይኖር አይቀርም ምናልባ ሰላም ስለኔ ነግራቸው ይሆን? አይ አይ አይሆንም! ልትነግራቸው አትችልም!

ሰላም ትመጣለች ብዬ ስላሰብኩ እዛው በር ላይ እየተንቀጠቀጥኩ ተቀምጫለሁ እጄን ወደ አፌ አስጠግቼ በ አፌ ትንፋሽ እጄን ለማሞቅ እየሞከርኩ ነው

"ትትትትት..ት ት ትመጣለች"

አዛው በሩን ተደግፌ እንደተቀመጥኩ ግራና ቀኙን እያየሁ ቀኑ መሸ ምንም ሰው ሚባል ነገር ሰፈር ውስጥ የለም ብርዱ ከቅድሙ አሁን እየባሰ ሲመጣ እንደምንም ተነስቼ ወደ ቤት ሄድኩ

ቤት እንደገባሁ የረጠበውን ልብሴን ቀይሬ አልጋዬ ላይ ጋደም ብዬ እየተንቀጠቀጥኩ እንቅልፍ ወሰደኝ
ጠዋት ከ እንቅልፌ ስነሳ ግን በጣም ታመምኩ ያስለኛል፣ ያስመልሰኛል፣ ራሴ ግሏል፣ ያዞረኛል...በትላንቱ ዝናብ እና ብርድ ምክንያት እንደሆነ ገብቶኛል

እንደዚሁ በህመም ለ አራት ቀን ስሰቃይ ከቤት ሳልወጣ

ታምሜ ያሳለፍኩት አራት ቀን ሰላምን እንዳላገኝ አርጎኛል ገና ያመመኝ ቀን ነበር የሰላም ነገር ያስጨንቀኝ መደወሌን አላቋረጥኩም ሁሌ እደውላለሁ ግን ስልኳ ሁሌ ዝግ ነው ዛሬ ተሽሎኝ ቤቷ እሄዳለሁ! ወይም ደሞ ነገ ይሻለኝና እሄዳለሁ እያልኩ አራት ቀን በስቃይ ካሳለፍኩ በኋላ በ አምስተኛው ቀን ባይሻለኝም ተሽሎኛል ብዬ ራሴን አሳምኜ ከቤት ወጣሁ

እነ ሰላም ቤት ስደርስ እንደበቀደሙ በሩን በሀይል አላንኳኳሁም

ረጋ ብዬ በሩን "ኳ.ኳ.ኳ.ኳ.ኳ.ኳ" አረኩት "ማነው" አሁንም የበቀደሙ ድምፅ

በሩ እስከሚከፈት መጠበቅ ጀመርኩ

በድጋሚ "ማነው!"

አሁንም መልስ አልሰጠሁም ዝምታን መረጥኩ

በሩ ተከፈተ
የሰላም እናት ለ ሁለተኛ ጊዜ አዩኝ

"እንዴት ኖት እማማ..ባለፈው መጥቼ ሰላም የለችም

ዝም ብዬ መቆየት ስላልቻልኩ

ብለውኝ ነበር ዛሬ ትኖራለች ብዬ ነው የመጣሁት" ፊታቸውን አኮሳትረው በዝምታ ያዩኝ ጀመር "ዛሬም የለችም?'' አልኩኝ ዝም ብለው የቆዩት የሰላም እናት "ሰላም ከዚ በኋላ እዚ የለችም" ብለው በሩን ዛሬም ወርውረው ዘጉብኝ

ደነገጥኩ...ቆይ ምንድነው የተፈጠረው? ለምድነው ሰላም ቤቷ የሌለችው? ለምንስ ነው እናትየው ሲያዩኝ እንደዚ የተበሳጩት? ብዙ ጥያቄ በውስጤ እየተመላለስ ያስጨንቀኝ ጀመረ

ጭንቀቱን መቋቋም ሲያቅተኝ ስልኬን አንስቼ ለሁሉምየሰላም ጓደኞች መደወል ጀመርኩ

አስካሁን ስድስት ጓደኞቿ ጋር ደውዬ አናውቅም ብለውኛል በ ሰባተኛው መቅደስ ጋር ደወልኩ..

"ሄሎ መቅዲ! ከሰላም ጋር ተገናኝታቹ ታውቃላቹ እንዴ?!

"ያቡ ሰላምታ አይቀድምም?"

ለሰላምታ ጊዜ አልነበረኝም ስልኩት ዘግቼ ሌላኛዋ ጓደኛዋጋር ደወልኩ

"ሄሎ ኤፍራታ ሰሞኑን ሰላምን አግኝተሻት ታውቂያለሽ?!

"እእእእእ...አው ምነው?"

ስፈልገው የነበረውን መልስ ሰማሁ! በውስጤ ኡፍፍፍፍፍስል ይሰማኛል

"የት ናት?" ሰሞኑን ትንሽ ተጣልተን ላገኛት አልቻልኩምበናትሽ ላወራት ፈልጋለው የት ናት?"

"እሱን ልነግርህ አልችልም"

"ለምን!?" ግራ ገብቶኝ ጠየኳት

"እሺ እኔ እንደነገርኩህ እሷ እንዳትሰማ!"

"አትሰማም እውነት አልነግራትም ንገሪኝ"

"አክስቷ ጋር ሀዋሳ ሄዳለች"

"ሀዋሳ !?"

አላለቀም
ከወደዳችሁት ይቀጥላል
Https://www.tg-me.com/ethioleboled
እንባና ሳቅ @Bemnet_Library.pdf
17 MB
--

ርዕስ=ዕንባና ሳቅ(ልቦለድ)

ደራሲ=ገበየሁ አየለ

የገፅ ብዛት= 223

📚 @Bemnet_Library
አስበህ ሀብታም ሁን! @Bemnet_Library.pdf
18.5 MB
ሚኪ "Think and Grow Rich" ወይም በአማርኛው "አስብህ ሀብታም ሁን" የሚለውን "የናፖሊዮን ሂል" መጽሐፍ ጠይቋል፤ይህው ሚኪ መልካም ንባብ😘

ማጋራት መተሳሰብ ነው!
📚 @ethioleboled
የፍቅር ኬሚስትሪ @Bemnet_Library.pdf
23.5 MB
ሮዝ "የፍቅር ኬሚስትሪ" የተሰኘውን
የብርሀኑ ንጉሴ ምርጥ መጽሐፍ ጠይቃለች፤ ይህው ሮዝዬ መልካም ንባብ😘

📚 @ethioleboled
የጭን ቁስል @Bemnet_Library.pdf
15.6 MB
ዳምጦ "የጭን ቁስል" የተሰኘውን የተክሉ ጥላሁንን መጽሐፍ ጠይቋል፤ይህው ዳምጦዬ መልካም ንባብ😁

📚 @ethioleboled
የብርሃን ፈለጎች @Bemnet_Library.pdf
7.3 MB
ዳንኤል "የብርሃን ፈለጎች " የተሰኘውን የአለማየሁ ገላጋይ መጽሐፍ ጠይቋል፤ይህው ዳኒ መልካም ንባብ😘

ማጋራት መተሳሰብ ነው!
📚 @ethioleboled
የአና ማስታወሻ @Bemnet_Library.pdf
13.9 MB
ሄለን "በአና ፍራንክ" የተፃፈውን "የአና ማስታወሻን" ጠይቃለች።ይሄ መጽሐፍ አለማችን ላይ በጣም ከተወደዱና ዝናን ካተረፉ መጽሐፎች ውስጥ አንዱ ነው።ይህው ሄሉዬ መልካም ንባብ😘

ማጋራት መተሳሰብ ነው!
📚 @ethioleboled
2024/11/14 12:11:25
Back to Top
HTML Embed Code: