Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜
💥📚ኢትዮ-ልቦለድ📚📖💥
Photo
አትሂጂብኝ…
ፀሀፊ የአብስራ
ሀዋሳ እንደሄደች ስሰማ ወደ ሀዋሳ መሄድ እንዳለብኝ ወሰንኩ
እንደ ሁል ጊዜው መሽቶ ነጋ
ሲነጋ ግን እኔ ወደ ሀዋሳ የሚሄድ አውቶቢስ ውስጥ ተቀምጫለሁ
12 ሰዓት ሲሆን አውቶቢሱ ጉዞውን ወደ ሀዋሳ ጀመረ ህመሙ አልተሻለኝም በጣም እያመመኝ ነው
ሰላምን እያሰብኩ መሄዴ ግን በትንሹም ቢሆን ህመሙንእያስረሳኝ ነው
በተቀመጥኩበት የ አውቶቢስ ወንበር አንገቴን ዘንበል አርጌ እንቅልፍ በትንሹ ወሰድ መለስ እያረገኝ ነው አሞኛል.. እያቃሰትኩ ነው.. ለኔ ግን አልታወቀኝም! እንደዚሁ ህመም እያሰቃየኝ ሀዋሳ ደረስኩ
የ አውቶቢሱ ረዳት ከእንቅልፌ ቀስቅሶ
"አባ ተነስ ደርሰሀል!'' ሲል ሰማሁት
ሰውነቴ ዝሏል መነሳት ከበደኝ
ከተቀመጥኩበት እንዲያነሳኝ ለረዳቱ እጄን ሰጠሁት እሱም ደግፎ ከመኪናው አወረደኝ
የተሸከምኩት ትንሽዬ ቦርሳ ኩንታል ሙሉ ማዳበሪያ የተሸከምኩ ያህል ከበደኝ
ቦርሳው ብቻ ሳይሆን የለበስኩት ልብስም ሳይቀር ሸክም ሆኖብኛል
ከመኪናው እንደወረድኩ አይኔን ጠበብ አድርጌ ያለሁበትን ማየት ጀመርኩ ተመሳሳይ አውቶቢሶች ተደርድረው
ቆመዋል ፀሀይ ለኔ ብቻ ያበራች ይመስል ሰውነቴን ማቃጠል
ጀምራለች የማላውቀው ከተማ ላይ ከማላውቃቸው ሰዎች ጋር መሆኔ
ትንሽ አስፈራኝ ትከሻዬ ላይ ያለውን ቦርሳ መሬት ላይ ጣል አረኩት ኡፍፍፍፍ ትንሽ ቀለል አለኝ
አሁን የት ነው ምሄደው? ጎኔን ማሳርፍበት ቦታ ማግኘት አለብኝ!
በአይኔ ታክሲ እየፈለኩ ነው
ብዙ የታክሲ ረዳቶች የሚሄዱበትን ቦታ ስም እየጠሩ ሰውእየጫኑ ነው
"ፒያሳ ፒያሳ" የላል አንዱ የታክሲ ረዳት ከሩቅ ሆኖ!
ፒያሳ ሀዋሳ ውስጥ ካሉት ፀዴ ሰፈሮች አንዱ ነው ለምሳሌ ቦሌ ለ አዲስ አበባ የሚሰጠውን ድምቀት ያክል ለ
ሀዋሳ ደሞ ፒያሳ አለችለት!
ወደ ፒየሳ መሄድ ብፈልግም ገና ከዚ ተነስቼ ታክሲው
ያለበት ድረስ እንደምሄድ ሳስብ ህመሜ እና ድካሜ ተደምረው እንዳልሄድ ከለከሉኝ..
"ፒያሳ ፒያሳ!'' እያለ ከሚጠራው ትንሽ ቀረብ ብሎ ደሞ "ሞቢል፣ ጥቁር ውሀ" ይላል ሌላ ታክሲ
ሁለቱም እሩኡኡኡ.....ቅ የሆኑ ያክል ተሰማኝ ራሴን በጣም እያዞረኝ ስለነበር የጣልኩትን ቦርሳዬን አንስቼ አጠገቤ ወዳለው ታክሲ ውስጥ ዘው ብዬ ገባሁ
እኔ የገባሁበት የታክሲ እረዳት ከውጪ ሆኖ .ዳቶ....... ዳቶ
ዳቶ የት እንደሆነ አላውቅም...ነገር ግን አማራጭ ዳቶ የት እንደሆነ አላውቅም...ነገር ግን አማራጭ
አልነበረኝም ደክሞኛል፣ አሞኛል፣ ሰውነቴ ዝሏል፣
እርቦኛል። የማላውቀው ከተማ ታምሜ መምጣቴ ሳያንስ፤የማላውቀው ሰፈር ሄጄ ልንከራተት ነው።ኤጭ ምን አይነት እዳ ነው!! ምርር አለኝ
ዳቶ የሚባለው ሰፈር ደረስኩ.. ገና ከታክሲው ወርጄ ቀና ስል "ፕላዛ የ እንግዳ ማረፊያ" የሚል ትልቅ ፅሁፍ ያለበት
ፎቅ አየሁ
እንዳሰብኩት ሳልደክም ማረፊያ ቦታ ማግኘቴ ደስ እያለኝ ገብቼ አንድ ከፍል ይዤ የዛለውን ሰውነቴን አሳረፍኩት
እዛው ጋደም ባልኩበት እንቅልፍ ወሰደኝ
ትንሽ ቆይቼ ከ እንቅልፌ ነቃሁ
እንደነቃሁ ስልኬን ከኪሴ አውጥቼ ኤፍራታ (የሰላም ጓደኛ) ጋር ደወልኩላት
አነሳችው
"ሄሎ ኤፍራታ እንዴት ዋልሽ?"
"ደና ነኝ እንዴት ነህ?"
"ደና ነኝ ሰላም ሀዋሳ አክስቷ ጋር ናት ብለሽኝ ነበር
አደል?"
"አው አው! እኔ እንደነገርኩህ ግን ማወቅ የለባትም חו!"
"ማንም አያውቅም አታስቢ፤ አሁን እሷን ፍለጋ ሀዋሳውስጥ ዳቶ ሚባል ሰፈር ነው ያለሁት።
"ምን..!" ደነገጠች
"አው ምነው!'' እኔንም አስደነገጠቺኝ
"እንዴት! ቆይ ባንተ ምክንያት ነው እንዴ ስልኳን አጥፍታ
አክስቷ ጋር የሄደችው?"
"እኔንም ግራ ያጋባኝ እሱ ነው?"
"ቆይ ምን ተፈጥሮ ነው?" ጠየቀቺኝ
መመለስ ማልፈልገውን ጥያቄ!
ምን ብዬ ነው ምነግራት?
ሰክሬ እገልሻለው አልኳት ነው ምላት?
ምን ብዬ? ምን ተብሎ ይነገራል?
"ምነው ዝም አልክ ነገረኛ! ምን ተፈጥሮ ነው!'' ለሁለተኛ
ጊዜ ጠየቀቺኝ
"ይኸውልሽ ኤፊ" ከ አንድ ሳምንት በፊት ከ ጓደኞቼጋር ተገናኝተን እየጠጣን ነበር... ከዛ ትንሽ ከጠጣን በኋላ እየሩስ እኔ ጋ ደወለች...ትንሽ ሞቅ ብሎኝ ስለነበር እየተቆጣሁ እና እየተሳደብኩ ስልኩን ዘጋሁባት እሷ ግን ደጋግማ መደወል ጀመረች እኔም በተደጋጋሚ ስልኩን
እያነሳሁ እየተሳደብኩ ዘጋሁት
በዚ መሀል ሰላም እኔ ጋር ደወለች እኔም እየሩስ የደወለች መስሎኝ ስልኩን አንስቼ
"አንቺ ከሀዲ ከዚ በኋላ ካንቺ ጋር ምንም የማወራው
ነገር የለም ተይኝ ከዚ በኋላ ድጋሚ ለመደወል ብትሞክሪ ያለሽበት ድረስ መጥቼ አንቄ እገልሻለሁ" ብዬ ስልኩን ለ አንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ዘጋሁባት
በነጋታው ከ እንቅልፌ ነቅቼ ስልኬን ስከፍተው ሰላም እኔጋር 46 ጊዜ ደውላ ነገበርመልሼ ስደውል ስልኳ እምቢ አለኝ
አንዱ ጓደኛዬ ጋር ደውዬ ስጠይቀው ማታ የተፈጠረውንነገር በሙሉ ነገረኝ እንጂ እኔ ምንም የማስታውሰው ነገር አልነበረም"
ይሄን ሁሉ ነገር ሳወራ ኤፍራታ ዝም ብላ እየሰማቺኘሰ ነበር
ትንሽ ዝም ብላ ከቆየች በኋላ
"እሺ ቆይ አድራሻዋን ልላክልህ" አለችና ስልኩን ዘጋችው
አሁን ትንሽ ህመሙ ቀለል ብሎልኛል
በጣም ስለራበኝ ምግብ አዘዝኩ...
ብዙም ሳይቆይ አንድ አስተናጋጅ ምግቡን ይዞ መጣ ያመጣውን ምግብ አስቀምጦ ሊወጣ ሲል "ሰው ብጠይቅህ ታውቃለህ?" አልኩት ደገምኩለት "እዚ ሀዋሳ ሰው ፈልጌ ነው የመጣሁት ቤት አስተናጋጅ ይሄን ጥያቄ መጠየቄ ለራሴምበ እጁ የያዘውን የለስላሳ መክፈቻ እያሽከረከረ "ምን አልከኝ ወንድሜ?" አለ
እባክህ ምታውቅ ከሆነ ብትረዳኝ?"
ከዛሬ ውጪ አይቼ የማላውቀውን አንድ የምግብ ገርሞኛል...ቢጨንቀኝ ኮ ነው!
የያዘውን የለስላሳ መክፈቻ ወደ ኪሱ ከተተና "የምትፈልገው ሰው የት ሰፈር ነው?" ሲል ጠየቀኝ
ስልኬ በትንሹ ጮኾ ዝም አለ
አንስቼ አየሁት ኤፍራታ የሰላምን አድራሻ በ message ላከችልኝ
"Ye akstua sm belay nesh nw yalechbet sefer demo 05" ...
ፈጠን ብዬ ለ አስተናጋጁ "ያለችበት ሰፈር 05 ነው በላይ ነሽ ምትባል ሴቲዮ" ታውቃታለህ?"
አስተናጋጁ ፈገግ እያለ "አላውቃትም! ነገር ግን ሀዋሳ ውስጥ ያለ ሰው ፈልገህ ልታጣ አትችልም! ነገ ስራ እረፍት ስለሆንኩ አብረን ሄደን እንጠይቃለን"
"የምርህን ነው!??"
"አው ችግር የለውም"
Https://www.tg-me.com/ethioleboled

እስከሚነጋ ጨንቆኛል..አንዴም እንቅልፍ አልወሰደኝም እንዲው አይኔን እንዳፈጠጥኩ ለሊቱ ነጋ
ያው ነጋ ባይባልም እየነጋ ነው
ከ ለሊቱ 11:47 ሆኗል ከዚ በላይ እንዴት ይንጋ! አስተናጋጁ ስልኩን ሰቶኝ ስለነበር ደወልኩለትበጎረነነ ድምፁ አንስቶ
"ሀሎ" አለ
"ሄሎ እንዴት አደርክ ይቅርታ ቀሰቀስኩህ አደል?"
አሁንም በጎረነነ ድምፁ "ማን ልበል?'' አለ "ትላንት ሆቴል ያወራሁህ ልጅ ነኝ ሰው ፈልጌ"
"እእእ. አወኩህ እንዴት አደርክ? በጠዋት ኮ ስልኬ ሲጠራ ማነው ብዬ ነው"
"ዛሬ እረፍት እንደሆንክ ነግረኸኛል..እመጣለሁ አብረን እንሄዳለን ብለኸኝ ነበር" አልኩት ለማስታወስ ያክል
"እሺ ሲነጋ እመጣለሁ አታስብ አብረን ሄደን የምትፈልገውን ሰው አገናኝሀለው እመነኝ ታገኛቸዋለህ ሀዋሳ ሰው ፈልገህ አታጣም" አለኝ
ደስ እያለኝ "እሺ" ብዬ ስልኩን ዘጋሁት
12 ሰዓት ከሞላ በኋላ ሰአቱ ወይ ፍንክች አለ አይነጋም እንዴ? ስልኬ ላይ ያለውን ሰአት አንስቼ አየሁት
12:13 ይላል ስልኩን አልጋ ላይ አሽቀንጥሬ ጣልኩት በድጋሚ ከብዙ ደቂቃዎች በኋላ ስልኬን ድጋሚ አየሁትع
እንዴዴ... !!! መንድነው ስልኬ አይሰራም እንዴ?
የሰላም ጉዳይማ ገና ጨርቄን ያስጥለኛል
እንደዚው ስበሰጫጭ ቆይቼ ነጋልኝ
ልጁ ደውሎ እንድዘጋጅ ከነገረኝ በኋላ ብዙም ሳይቆይ አብረን ወጣን
"ቁርስ በልተሀል?" ብሎ ጠየቀኝ
"አው በልቻለሁ" ብዬ ዋሸሁት ሰላምን ለማግኘት ካለኝ ትልቅ ጉጉት የተነሳ
ሌላ ጥያቄ ጨመረልኝ "ማታስ ሙቀቱ እንዴት ነው? ሀዋሳ
ትሞቃለች አደል?"
ምናልባት ተኝቼ ባድር እርግጠኛ ነኝ ይሄን መልስ እመልስለት ነበር
አው ምንም አይልም ቆንጆ ነው" ለ ሁለተኛ ጊዜ ዋሸሁት
"ሳይህ ግን የተኛህ አትመስልም አይንህ ቀልቷል ከንፈርህም ደርቋል እርግጠኛ ነህ ቁርስ በልተሀል?" ኦሆሆሆ.....! ይሄ ሰውዬ ምን ነካው ለምን ዝሞ ብሎ
ሰላምዬ ጋር አይወስደኝም!
"አዎ! ግን ስምህን አልነገርከኝም" አልኩት በዛውም
የጠየቀኝን ጥያቄ ለማረሳሳት እየሞከርኩ
"ስሜ ሱራፌል ይባላል እዚው ሀዋሳ ነው ተወልጄ ያደኩት
አንተስ?" አለ
"እኔ የአብስራ እባላለሁ የ አዲስ አበባ ልጅ ነኝ" አልኩት
"የት ነበር ያልከኝ የ ልጅቷን ሰፈር" አለ መራመዱን አቁሞ
"05 ሰፈር" አልኩት
"ና እሺ የ 05 ታክሲ እንያዝ" አለኝና አንድ ታክሲ ውስጥ ገብተን ተቀመጥን
ብዙም ሳይቆይ ታክሲው ጉዞውን ጀመረ
ገረመኝ! አንድ የማላውቀው ሰው በኔ ምክያት አንድን ሰው ፍለጋ እንደዚ ለመንከራተት ፍቃደኛ ሲሆን ሳይ ፈገግ አልኩኝ...እውነትም የ ሀዋሳ ሰው ፍቅር ነው! 05 ሚባለው ሰፈር ደርሰን ከታክሲው እንደወረድን
እንቅልፍ ሳልተኛ ማደሬ እና ቁርስ አለመብላቴ በጋራ ሆነውያስጨንቁኝ ጀመር
ነገር ግን ከምንም በላይ ሰላምን ማግኘት እንዳለብኝእያሰብኩ ፍለጋችንን ቀጠልን
"ማን ነበር ያልከኝ ስማቸውን" ድጋሚ ጠየቀኝ
"ወይዘሮ በላይ ነሽ" አልኩኝ ፈጠን ብዬ
በየመንገዱ ያገኘነውን ሰው "የነ በላይ ነሽ ቤት የቱ ጋርነው" እያልን ማስጨነቅ ጀመርን
እስካሁን የጠየቅነው ሰው ሁሉ ግማሹ ትንሽ አሰብ ያረግና
''በላይ ነሽ በላይ ነሽ? እኔንጃ" ይላል
ግማሹ ደሞ "አላውቅም" እያለን ፍለጋችንን ቀጠልንበመጨረሻም አንድ ባለሱቅ ጋር ደረስን
"ወንድሜ እዚ ሰፈር በላይ ነሽ የሚባሉ ስቲዮ ያውቃሉ ?"
"ያው ፊለፊት የሚታየው ቆርቆሮ በር የነ በላይ ነሽ" ብሎ ሳይጨርስ ወደ ቆርቆሮው ቤት መሮጥ ጀመርኩ
በሩ መለስ አለ እንጂ ክፍት ነበር
በሩን በርግጄ የሰው ጊቢ ዘው ብዬ ገባሁ
ሱራፌልም ተከትሎኝ ወደ ጊቢው ገባ
"ማነው!" እያሉ ቀጠን ያለ ምርኩዛቸውን ከመሬት ጋር እያጋጩ አንድ በ እድሜ ገፋ ያሉ ሴትዮ መጡ
"እኔ ነኝ እማማ" አልኩኝ ባለሁበት ቆሜ
"እኮ አንተ ማነህ?" ወደኔ እየቀረቡ መጡ
ወደኔ እየቀረቡ ሲመጡ አይናቸው ማየት እንደማይችልእና የያዙት ምርኩዝ አይን ለሌላቸው መምሪያ ምርኩዝ
እንደሆነ አስተዋልኩ
"የአብስራ እባላለሁ እማማ ሰላምን ፈልጌ ነው የመጣሁት"
"አብስራ? አብስራ ማለት አንተ ነህ" አሉ አጠገቤ መተው ፊቴን እየዳበሱ
ግራ ተጋባሁ! ለምን ፊቴን እንደሚነኩኝ አልገባኝም ለምንስ ነው የአብስራ ማለት አንተ ነህ ብለው የጠየቁኝ? ያውቁኛል ማለት ነው?
ጥያቄዬን ደገምኩት "ሰላምን ፈልጌ ነው የመጣሁት
"ቅንድቡ የሚያምር ጆሮው አነስ ያለ ትከሻው ሰፊ" ብላ ነግራኝ ነበር ሰላምዬ ከመሄዷ በፊት" አሉ ከ ቅንድቤ ጀምሮ አስከ ትከሻዬ ድረስ በእጃቸው እየዳበሱኝ
ደነገጥኩ! "ሰላም የት ሄደች?" የቀላው አይኔ ላይ እንባ ተጠራቀመ
በእጃቸው እየዳበሱኝ ያሉት ወይዘሮ በላይ ነሽ አይኔን መዳሰስ ጀመሩ
አይኔ ላይ የነበረው እንባ ወረደ
ደንገጥ ብለው እጃቸውን ከፊቴ ላይ አንስተው እያቀፉኝ "አታልቅስ የኔ ልጅ ና ቁጭ በል ማወራህ ነገር አለ" አሉኝ በምርኩዛቸው እየመሩኝ የጊቢው ጥግ ላይ ካለ ዛፍ ስር
ተቀመጥን
አቤኔዘር አዛው በቆመበት ነው ያለው
ቀጠሉ ወ/ሮ በላይ ነሽ "ሰላምን ትወዳታለህ ልጄ?"
ምን አይነት ጥያቄ ነው ይሄ? ባልወዳት ነው ከዛ እዚ ድረስ እሷን ፍለጋ የመጣሁት! እንዴት ትወዳታለህ ወይ ተብሎ ይጠየቃል?
መለስኩኝ "አው እማማ በጣም እወዳታለሁ"
"ታዲያ እንዴት የምትወደውን ሰው እንደዛ አልክ ልጄ? እሷ ምንም ብትበድልህ አገልሻለሁ ብለህ መዛትህ ተገቢ ነው חו?"
"እማማ እኔ እሷን አልነበረም እንደዛ ተቆጥቼ ስናገርየነበረው"
"ታዲያ ማንን ነው?"
"የድሮ ጓደኛዬን...ማለት የድሮ...የድሮ ፍቅረኛዬን ነበር"
እማማ ደነገጡ "እኮ እንዴት!?"
ቀጠልኩ ማስረዳቴን "እማማ ጥፋቱ የኔ እንደሆአውቃለሁ በርግጥ ትንሽ ጠጥቼ ነበር ነገር ግን በሰአቱ የድሮዋ ፍቅረኛዬ ደጋግማ እየደወለች ነበር ከሷ ጋር
እየተጨቃጨቅን ስልኩን ዘጋሁት በዚ መሀል ሰላም እኔ ጋ ደወለች ከዛ የድሮዋ ፍቅረኛዬ ደግማ የደለች ስለመሰለኝ ስልኩን አንስቼ ከዚ በኋላ ካንቺ ጋር ምንም የማወራው ነገር የለም ተይኝ ከዚ በኋላ ድጋሚ ለመደወል ብትሞክሪ ያለሽበት ድረስ መጥቼ አንቄ እገልሻለሁ ብዬ ስልኩን ዘጋሁት..እኔ ሰላም እንሆነች ባውቅ እንዴት እንደዚ አረጋለሁ በፍፁም አላረግም!'' አልኩና የሳቸውን መልስ መጠበቅ ጀመርኩ
"አሄሄ...ተሰብሮ ቢጠገን፤ እንደነበር አይሆን፤...ነው የናንተ ነገር ልጄ"
"ለማለት የፈለጉት አልገባኝም እማማ!?" አልኩኝ ግራ ስለገባኝ
"ልጄ! እሷ ኮ የነገረቺኝ "ወደ ውጪ ልትሄድ ሶስት ሳምንት እንደቀራት፣ ለማንም እንዳልተናገረች እና አሁን ግን አንተ እንደሰማህ እና ይሄን ስታውቅ ደሞ እንደዛትክባት ነው የነገረቺኝ ልጄ! ፍፁም ስህተት ነበር ማለት ነው?"
"ወደ ውጪ?" መተንፈስ አቃተኝ ነገሩ ሁሉ እንደተመሰቃቀለ ታወቀኝ
ይቀጥላል...

ነገሩ ሁሉ እንዳልጠበኩት ሆኖ ምስቅልቅሉ እንደወጣ ለካ...ሰላም ይሄን ያክል የሸሸቺኝ መጀመሪያውኑ ጥላኝ ለመሄድ ስላሰበች ነው።
ቆይ እኔ ላይ ይሄን ማረግ ለምን አስፈለገ? የበደልኳት ነገር አለ እንዴ?
ታዲያ እንዴት ትታኝ ሄደች? ለምንስ ትታኝ ሄደች? አትወደኝም ነበር ማለት ነው?'' ከራሴ ጋር እንደ እብድ እየለፈለፍኩ ነው
ወይዘሮ በላይነሽ አሁንም ከአጠገቤ ተቀምጠው "አይዞህ ልጄ አይዞህ" እያሉ እኔን ለማፅናናት እየሞከሩ ነው እኔ ግን ሰላምዬን እንጂ ሚያፅናናኝ ሰው አደለም ምፈልገው!
ድንገት ወይዘሮ በላይነሽ የተናገሩት ነገር ዝም አስባለኝ "ምናልባት አብስራ ከመጣ ይሄን ደብዳቤ ስጪው ብላኝ የሆነ ወረቀት እንዳስቀምጥ ሰታኝ ነው የሄደችው" አሉኝ ድንገት የሰማሁት ነገር ብቻዬን ከምለፈልፍበት ሀሳብ አወጣኝ
"የታለ ወረቀቱ እማማ! ስጡኝ" አልኩኝ መሬት ላይተንበርክኬ እጃቸውን በሁት እጄ ይዤ እየተማፀንኩ
"ሳሎን ቤት ጠረጴዛ ስር ነው መሰል ያስቀመጥኩት ልጄ...ቆይ ላምጣልህ" ብለው ከተቀመጡበት እስኪነሱ እኔ ሳሎን ቤት ገብቼ ጠረጴዛ ስር ወረቀት መፈለግ ጀመርኩ።
ጠረጴዛ ስር ምንም ወረቀት የለም
"እማማ..! ጠረጴዛ ስር ምንም ነገር የለም!'' ብዬ ጮህኩ እማማ በምርኩዛቸው ራሳቸውን እየመሩ ወደ ሳሎን ከገቡ በኋላ ከሳሎኑ ጥግ ላይ አነስ ካለች ጠረጴዛ ስር እጃቸውን ሰደድ አርገው መዳበስ ጀመሩ
ትንሽ ከቆዩ በኋላ "አአ...ው" አሉና በእጃቸው አንዲት ወረቀት አነሱ
"ይኸው ይህ ነው ወረቀቱ" ብለው ደብዳቤውን የያዘው
እጃቸውን ወደኔ ዘረጉት እኔም ተንገብግቤ ከ እጃቸው ላይ ነጠኳቸው
እማማ ከ አጠገባቸው ካለው ትንሽዬ ወንበር ላይ እየተቀመጡ
"ልጄ! የሷ መሄድ አንተን ብቻ ሳይሆን እኔንም ጎድቶኛል እንደው አትሂጂ ብዬ በዚህ በ እውሩ አይኔ አልቅሼ ብለምናትም እሺ አላለቺኝም....."
እማማ ማውራታቸውን ቀጥለዋል
እኔ ግን የሰጡኝን የሰላምዬን ደብዳቤ በእጄ ጨምድጄ ይዤ ወደ ውጪ መሮጥ ጀመርኩ
ሱራፌል የኔን መሮጥ ሲያይ እሱም ከኋላዬ እየሮጠ ይከተለኝ ጀመር
ከጊቢው ወጥቼ እግሬ ወዳመራኝ መሮጥ ጀመርኩ ወዴት እንደምሄድ አላውቅም ለምን እንደምሮጥም አላውቅም
ከብዙ ርቀት ሩጫ በኋላ ድንገት ፍሬን እንደያዘ መኪና ግትር ብዬ ቆምኩ
ግራና ቀኜን ፊት እና ኋላዬን ማየት ጀመርኩ ከፊቴ የ ሀዋሳ ሀይቅ በረጅሙ አንደተነጠፈ ትልቅ ምንጣፍ ተዘርግቶ ይታየኛል
እግሬ ወደ ሀይኩ መራመድ ጀመረ
ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ እኔና የሃዋሳ ሀይቅ ፊት ለፊት ተገናኘን
አይኔን ጨፍኜ ወደ ሰማይ ቀና አልኩኝ
ሀይለኛ ንፋስ ዛፎቹን እየገፋ ሲያስጮሀቸው ይሰማኛ እንደዛ ንፋስ ከሚያንገላታቸው ዛፎች ውስጥ የተለያዩ ወፎች ሰላም የሚሰጥ ድምፃቸውን ያሰማሉ
የሀይቁ ማእበል ከድንጋይ ጋር እየተጋጀ የሚያወጣው ድምፅ ውስጥን ያሳምማል
ወደ ሀይቁ ጠጋ ብዬ አንድ ትልቅ ድንጋይ ላይ ወጥቼ ተቀመጥኩ
ማእበል የሚያንገላታው ሀይቅ እኔ ከተቀመጥኩበት ድንጋይ ጋር እየተጋጨ ይመለሳል
እጄ ላይ ያለውን ደብዳቤ ከፈትኩት የሰላምዬ ፅሁፍ እንደሆነ ያስታውቃል የደብዳቤው መጀመሪያ ላይ ''ያብዬ" ይላል ቃሉን ሳነበው የሰላም ድምፅ ይሰማኛል
እጄ መንቀጥቀጥ ጀመረ
ሀይለኛው ንፋስ እጄ ላይ ያለውን ደብዳቤ ልክ እንደ ባንዲራ ወደዚ እና ወደዛ እያውለበለበው ነው አሁንም ማንበቤን ቀጥያለሁ
"ያብዬ እንዳትቀየመኝ እባክህ? ይሄንን ያረኩት ግዴታ ሆኖብኝ ነው
ትዝ ይልሀል ያኔ አብረን ቁጭ ብለን የጠየኩህ ጥያቄዎች? መቼ ታገባኛለህ ስልህ አሁን አገባሻለሁ ብለህ ከኪስህ
ቀለበት አውጥተህ ያረክልኝ? እ?ትዝ አለህ? እሱ ቀለበት ሁሌም እጄ ላይ አለ...ሁሌም!
ያብዬ!.... ይሄን ደብዳቤ መቼ እንደምታነበው አላውቅም...ግን አንድ ምነግርህ ነገር አለ......"
ድንገት ከሚንቀጠቀጠው እጄ ላይ ንፋስ ደብዳቤውንነጠቀኝ
ከተቀመጥኩበት ተነስቼ ንፋስ ከጄ የነጠቀኝን የሰላምዬን ደብዳቤ አየር ላይ በንፉስ ሲንገላታ ማየት ጀመርኩ..
ሀይለኛው ነፉስ ደብዳቤውን ከኔ አርቆ ሀይቅ ላይ ጣለው
የቆመኩበት ትልቅ ድንጋይ ላይ በጉልበቴ ተንበረከኩእየጮህኩ ማልቀስ ጀመርኩ
ሀይቁ የሰላምን ደብዳቤ እና የኔን እንባ አንድላይ ወሰደው።
"እዚ ጋ ይብቃ...''
ፀሀፊ <"የአብስራ">

የጣና ዳር አርሶ አደሮች ስሙን 'እንቦጭ' ሲሉ ሰይመውታል።
ስያሜውን ያመነጩት 'ውሀ ቢወቅጡት እንቦጭ' ከሚለው ብሂል ተነስተው ይሁን አልያም ከአረንጓዴው ጉድ አፈጣጠር ተነስተው እንደሆነ አልታወቀም።
📖ዮቶድ📖
ይስማዕከ ወርቁ
(የዴርቶጋዳ አምስተኛው ክፍል)
share⬇
@ethioleboled
ስያሜውን ያመነጩት 'ውሀ ቢወቅጡት እንቦጭ' ከሚለው ብሂል ተነስተው ይሁን አልያም ከአረንጓዴው ጉድ አፈጣጠር ተነስተው እንደሆነ አልታወቀም።
📖ዮቶድ📖
ይስማዕከ ወርቁ
(የዴርቶጋዳ አምስተኛው ክፍል)
share⬇
@ethioleboled
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜
ደግሞ ሌላ ቁም ነገር ልንገርህ?
The power of Naw
Eckhart Tolle
አሁንን የመኖር ጥበብ
ደግሞ ሌላ ቁም ነገር ልንገርህ፡፡ ትሰጋለህ እንዴ? «እንዲህ ቢሆንስ? » «እንዲያ ባይሆንስ? » የሚል ስጋት ተጠናውቶህ ይሆን? እንዲህ ያለ ስጋት ካለብህ ክፉ አሉታዊ ስሜት መሆኑን ተረዳ።
ምክንያቱም እንዲህ ያለው ስጋት " ወደፊት " እያለ ወደፊትን በመጥፎ ሁኔታ እንድትጠባበቅ እና አሁንህን እንዳትኖር የሚያደርግህ ነው፡፡ ይሄን ስጋት የሚከተለው ደግሞ ፍርሃት ነው፤ መጭውን ሁሉ መፍራት፡፡
ለመሆኑ ገና ስላላመጣው ‹‹ወደፊት›› ምን ስቅልጥ አደረገህ? አርፈህ አሁንህን አትኖርም እንዴ? እንዲህ ያለ ስጋት ተጠናውቶህ እንደሆነ አንድ ነገር ብቻ አድርግ፤ አሁንህ ላይ አተኩር፡፡ ያኔ ያ ስጋት ሳይወድ በግድ ይተናል፡፡

የአሁን ሃያልነት ((ሙሉዉ።)).pdf
16.2 MB
📖ርዕስ:- የአሁን ሀያልነት ወይም
አሁንን የመኖር ጥበብ
(The power of now)
📚ደራሲ:- ኤክሀርት ቶል
📚ዘውግ:- ሳይኮሎጂ
📖የገፅ ብዛት:- 230
✅ብዙ ሰዎች አሁንን ረስተው የሚያስቡት ገና ስላልደረሱበትና ወደፊት ስለሚመጣው ወይም ሊመጣ ስለሚችለው ነገር ነው
✅ አሁን የሚያደርጉት ነገር በሙሉ ወደፊቱ ለሚሰጠው ውጤት ብለው ሲሆን ፣ የአሁንን ጊዜ ለወደፊቱ መሸጋሪያ ብቻ አድርገው ይወስዱታል ፡፡
✅ ነገር ግን ያ ወደፊት የሚሉት ነገር ወይም ሁኔታ ላይመጣም ፣ ላይኖርም፣ ላይከሰትም ይችላል ፡፡ በዚያን ወቅት እነርሱም ያንን ነገር ለማየትም ሆነ ለመመልከት በዚያ ቦታ ላይገኙም ፣ ላይኖሩም ይችላሉ ፣ ነገር ግን ልክ በወደፊቱ ጊዜ እንደሚኖሩ እርግጠኛ በመሆን ላልደረሱበት ጊዜ አሁን የሚያደርጉትን የወደፊቱ እነርሱ ይመጣል ለሚሉት ነገር መሰረት እየጣሉ እንደሆነ አድርገው ያስባሉ ፡፡
በሆነ ወቅት ስኬታማ እሆናለሁ ብላችሁ አታስቡ እናም ወደፊት በአንድ ወቅት እንደዚህ እሆናለሁ ብላችሁ አትጠብቁ ፣ ከአሁኑ ወቅት ጋራ ስኬታማ የሆነና የሚመቻሁን ግንኙነት ውህደትና መስተጋብርን ፍጠሩ እንዲሁም አሁን በምትሰሩት ማንኛውም ነገር ምሉእነትና እርካታ ይሰማችሁ
ኤክሀርት ቶሌ የአሁንት ሀይል ‹‹The Power of Now››
ከመፅሀፉ የተወሰዱ ቁልፍ ነጥቦች:-
1️⃣. በዓለም ውስጥ በጣም ውድ ነገር የአሁኑ ጊዜ (the present moment) ነው።
2️⃣ ያለህበትን ሁኔታ ከቻልክ ቀይረው፣ ካልቻልክ ተቀበለው። ሌላው ሁሉ እብደት ነው።
3️⃣ለአሁኑ ጊዜ ምስጋና መስጠት እውነተኛ ብልጽግና ነው።
4️⃣. የትም ሂድ፣ በሄድክበት ቦታ ሙሉ በሙሉ እዚያ መሆንህን አረጋግጥ
5️⃣. ያሁኑንም ሆነ የወደፊትህን ጊዜ እንዳያበላሽብህ ከፈለክ ያለፈውን ጊዜህን ተወው
6️⃣. ላለው ነገር እጅ ስትሰጥ እና ሙሉ በሙሉ አሁን ላይ ስትሆን ያለፈው ጊዜ ምንም አይነት ሀይል ማግኘት ያቆማል።
7️⃣በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ብትሆን ስሜትህን ተቆጣጠር
በ😄ዚህ የክፍለ ዘመናችን ድንቅ መጽሐፍ የተላለፉትን የመንፈሳዊ መገለጥ ፍልስፍና፣ እሳቤዎች እና መርሆዎችን በመረዳትና በመተግበር ህይወትዎን ለመቀየር ከፈለጉ እንደ መጽሐፉ ስም
✅አሁን ላይ መኖር በጣም ትክክለኛው የደስታ እና የእውቀት መንገድ እንደሆነ መጸሃፉ ይናገራል። , ኤክሃርት ቶሌ አንባቢዎችን የራሳቸው ስቃይ ፈጣሪዎች እንደሆኑ በመግለጽ መጸሃፉን ይጀምራል፡፡ , እናም አኗኗራቸውን ወደ አሁን ላይ በማምጣት ከህመም እና ስቃይ ነጻ የሆነ ማንነት እንዴት እንደሚኖራቸው ያሳያቸዋል

🔵ወንድ ሆኖ መኖር ቀላል አይደለም ወንድነቴን ምወደው በፈተናው ነው። ገና ስትወለድ ወንድ ነው ሲባል ቤታችን ተከበረ ብለው ወላጆችህ ይደሰታሉ። ዳዴ እየሄድክ ብሎም በእግርህ ቆመህ ወድቀህ ስታለቅስ "አይዞን ወንድ አይደለህ አታልቅስ ወንድ ልጅ አያለቅስም" ትባላለህ።
✅ትንሽ ከፍ ትላለህ ታናናሾች ይኖሩሃል ትምህርት ቤትህ ውስጥ ደግሞ ጀማ አለህ በቃ ሁሌ ይደባደባሉ እብሪት ጉርምስና አፍላነት ጆሮህን ዘግቶታል። አየር በአየር ፣ የእንጨት ስራ ጋራዥ ጎማቸ መፍታት ብረት መቀጥቀጥ በጎን ካልሰራሁ ብለህ ትፈጋለህ። ትንሽዬ ገንዘብ ስታገኝ ምትወዳትን ሴት ትቀጥርና ሳምንት የሰራኸውን ቅዳሜ ታጠፋዋለህ።
✅ምሽት ላይ እንደ ቢሮ ተስተናጋጅ አመሰግናለሁ ብላህ እንዳይደብርህ ብላ ጉንጭህን ስማ በምትኩ ብርህ እና በብርድ ሰበብ ፊልም ላይ አይተህ የሰጠሃትን ጃኬት ይዛው ትገባለች። ጠዋት ስትነቃ እህትህን ሚያስቸግራት የሰፈር ጎረምሳ አስጨንቋት ዛሬ ትምህርት ቤት አልሄድም ብላ ስታለቅስ ትነሳለህ። ለእህትህ ስትል እንቅልፍህም አሳዝኖህ ተነስተህ ሄደህ ትደባደባለህ ትዝታለህ ታስፈራራለህ።
🟢እድሜህ ሃያዎቹን ይረግጣል ትንሽ ትረጋጋለህ አሁንም ግን ምርጫህን አታቀውም ከተሳካልህ ዩኒቨርሲቲ ካልሆነ ቀን ጋራዥ ማታ የርቀት ከወረቀት ጋር እየታገልክ ነው። ቀን ፍግት ብለህ የሰራኸውን ቅዳሜ አጠብቅም ማታውኑ ብርጭቆ ስር ትጥለዋለህ። ጠርሙስ ካላወረድኩ ብለህ በየምሽት ቤቱ ትደባደባለህ። ትንሽ ስትጠጣ ያየኸው ጭን ሁሉ ሚለሰልስ እና አንተን ሚጠብቅ ይመስልሃል የመቀመጫ እና የጡት ሜዳ ላይ መንከባለል ጠርሙስ ስር ማፏጨት ህይወትህ ይሆናል በዚ ግርግር ውስጥ ዲዳ ትሆናለህ አንዲት ሴት ሆዷን ታሳይሃለች።
🟢✅ድንገት አባት ትሆናለህ አስወርጂው አታስወርጂው በየቀኑ ትነዛነዛለህ ትዝታለህ ቀኑ እየጨመረ ይመጣል ቤተሰብ መሃል ላይ ስለስማቸው ብለው በአናትህ ላይ ይነጋገሩብሃል አባት ትሆናለህ ሳትጠብቀው አስረግዘህ አቅደህ ታገባለህ የሰርግ ቀን ፊትህን ትጥላለህ በማግስቱ እቁብ እድር ትጀምራለህ። ጠርሙስ አይበቃህም ጠርሙሶች ታስወርዳለህ እርጉዝ ሴት ቤትህ አስቀምጠህ ብርጭቆ ስር ትጮሃለህ።
🟢✅ያ ድንገተኛው ልጅ ይወለዳል ስሜቶችህ ስታየው ይቀያየራሉ ለሱ መኖር ትጨምራለህ ጠርሙስ ሰቅለህ ፔርሙዝ ታወርዳለህ ብርጭቆ አስቀምጠህ የወተት ቆርቆሮ ታነሳለህ በብስጭት ያቋረጥከውን ትምህርትህን ትቀጥላለህ ጋራዥህ በሰአት ትገኛለህ እሷ በተፈጥሮ ተሰጥቷት እናት እኮ ተብሎ የተዘፈነላትን አንተ በስራ እና በትጋት አባት ለመሆን ትጥራለህ። የሆነ ቀን ከልብህ ትስቃለህ ከስራ ተበሳጭተህ ደክሞህ ዝለህ የለበስከው አስጠልቶህ የቤትህን በርህን ከፍተህ እንደገባህ ሚስትህ እጅህን ስታይ የባሰ ስትበሳጭባት አባቢ እያለ እጁን ዘርግቶ ሚሮጥ ህፃን ሊያቅፍህ ይመጣል ስሜት ሳትሰጠው አቅፈህ ስትለቀው ስሜት ሳይሰጠው ወደ ጨዋታው ይመለሳል።
🟢✅ጀግና ነህ ወንድነት ቀላል አይደለም ቢያልፍልን ሃገር ስናስተዳድር ፎቅ ስናስገነባ ጎማ ሳይሆን መሪ ስንጠመዝዝ እንውላለን ነገ እሱን አስበን ዝቅ ብለን ብረት ቀጥቅጠን አፈር አቡክተን እንጨት ቆርጠን እንጨት ፈልጠን ቤት ጥቂት ሆዶች እንዳይጎድሉ እንሟሟታለን ሃገር ብትወረር ምንዘምት እኛ ሚዘምቱብንም የእኛው ወንዶች ናቸው። ወንድነት ቀላል አይደለም!

በየቀኑ 4 ድሎች!
1.) አካላዊ ድል (መራመድ፣ መሮጥ፣ ስፖርት፣ ጥሩ አመጋገብ....)
2.) የአእምሮ ድል (ማንበብ፣ መማር፣ መፍጠር፣ ማጥናት...)
3.) የመስተጋብር ድል (ማድነቅ፣ ጥልቅ ውይይት፣ መደጋገፍ...)
4.) መንፈሳዊ ድል (ማመስገን፣ ፀሎት፣ መልካም ተግባር፣ ቀና መሆን..
- ሣሙኤል ተክለየሱስ
(የሕይወት ክህሎት አሰልጣኝ)
📚 @ethioleboled

ወንጀልና ቅጣት @Bemnet_Library.pdf
18.1 MB
--
ርዕስ:-ወንጀልና ቅጣት
ደራሲ :- ፊዮዶር ዶስቶዮቭስኪ
ተርጓሚዎች :- አምባሳደር ካሳ ገ/ህይወት እና ፋንቱ ካሳ
ዘውግ :- ልብ ወለድ
ማጋራት መተሳሰብ ነው!
📚 @ethioleboled
ርዕስ:-ወንጀልና ቅጣት
ደራሲ :- ፊዮዶር ዶስቶዮቭስኪ
ተርጓሚዎች :- አምባሳደር ካሳ ገ/ህይወት እና ፋንቱ ካሳ
ዘውግ :- ልብ ወለድ
ማጋራት መተሳሰብ ነው!
📚 @ethioleboled
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜
ሰመመን @Bemnet_Library.pdf
88.4 MB
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜
የተቆለፈበት ቁልፍ @Bemnet_Library.pdf
12.4 MB
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜
ማነሽ አንቺ ከአለም ከተኳረፍኩ በኋላ የመጣሽው ፤ እምነት የማያልቅ ከነፍስ የተዋሀደ መሆን የምታበስሪኝ ማነሽ ?
ታውቆሻል ?
መወደድ የሚገባ ነህ እያልሺኝ ነው? እንደምናፈቅ እያሳየሺኝ ነው? መወደድን የሚያክል ምን በረከት አለ?
ገብቶሻል አይደል?
እንቅስቃሴሽ ይመለከተኛል እያልኩ ነው?
የሚቆረቁርልኝ ፣ ያገባኛል የሚለኝ ሰው ሊኖረኝ ነው ?
እየደረኩ ነበር
እንደናፈቅሺኝ አይኖችሽ ሲያቃጥሩ ነው የለመለምኩት ።
ስቀና ፣ ስብከነከን ፣ ስትናፍቂኝ ጊዜ ነው እስከዛሬ የተዜሙት ዜማዎች ትርጉም የሰጡኝ ።
እወድሻለሁ ❤
በእጦት ምክንያት የተወለዱ አቋሞቼን ናቸው ያመከንሽልኝ ። አልፈለጌነቴን ነው የናድሽው ።
መፋቀር ብቻ አልነበረም የሚናፍቀኝ መጣላትም እንጂ ፤ የሚሆን አልመስል ብሎኝ ነው ያላስተያየሁት ፤ ማደግ ውስጥ የማይገኝ ነገሮችን መተውን ይጨምር የለ ?
እወድሻለሁ ❤
ፖለቲካ ብቻ የማወራው የፍቅር ታሪክ ስላልነበረኝ ነው ፤ ስለፆታዊ ፍቅር ሲወራ ዝም የምል የነበረው ስለማላውቀው ነበር ።
✅ማነሽ አንቺ የፍቅር አማልክት ?
እወድሻለሁ❤