Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜
ራስን መለወጥ @Bemnet_Library.pdf
36.5 MB
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜
ሾተላዩ ሰላይ @Bemnet_Library.pdf
59.4 MB
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜
የነፍስ መንገድ @Bemnet_Library.pdf
20.3 MB
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜
✨✨የዶርም ወግ....✨✨
ምነው በእኩለ ለሊት ለምትሉኝ አንባብያን ሰሙነ ማማረር ላይ እንደሆንኩ ልነግራችሁ እወዳለሁ።
"ከእዚህ ጊቢ በሰላም ከወጣሁ ወደፊት ማንኛውንም ከባድ ሁኔታ ማለፍ እችላለሁ....."
"እስማማለሁ"
"እዚህ ጊቢ ለሚመጡ ነው ማዝነው..."
"ፎቁን ሲያዩት እኮ ደህና ጊቢ ይመስላል..."
" በእኔ የደረሰ በእናንተም አይድረስ...እኔ እንደተሸወድኩት እንዳትሸወዱ ምናምን እያልኩ ነው ከበር የምመልሳቸው..."
"ምኑም የጤና ጊቢ አይመስልም...."
"ጤናችንን አጥተን መውጣታችን ነው..."
የ pharmacy ትምህርት 6 አመት ከተደረገባቸው ጓደኞቼ ጋር እያወራን ነው....
"የኮሮና ጊዜ የተበላሸው scedule እንዳለ ሆኖ አንድ አመት የሚያስጨምር የኮርስ መጨመር እንኳን በሌለበት ሁኔታ ለምን 1 አመት ተጨመረ...ማንም አያውቅም...."የትምህርት ሚኒስቴር ትዕዛዝ ነው"...ነው የሚለው ጥገራው..የትምህርት ሚኒስቴር ህግ የሚሰራው ለዚህ ጊቢ ብቻ ነው...."...ጦ ናት።
"እኔ እንኳን ተመራቂ ነኝ...ይብላኝ ለከራሚ...."....እኔ ነኝ።እኔ ከmedical labratory ትምህርት ክፍል ነኝ። እኔም የዚህ ኢ-ፍትሀዊነት ተጠቂ ነኝ...4 አመት የነበረው ኮርስ 5 አመት ሆኖብኛል...
እንዴት 5 አመት ሆነ...lag አርገሽ ነው ሌባ...የሚሉኝ ሰዎች አልጠፉም....እንዴት ማለት ጥሩ ብዬ የተነገረኝን ስነግራቸው የስላቅ ሳቃቸው ያመልጣቸዋል....የምር ያስቃል እኮ...
"ሰኔ 30 የተበጀተ በጀት በዛው አመት ማለትም ከአንድ ወር በኃላ ሀምሌ ላይ አልቆ 5 ወር እረፍት ተሰጠን..."...የሚል ሰበብ አያስቅም ነው የምትሉኝ...
አንድ material or reagent በሌለበት ጊቢ
"ለትምህርት ጥራት ሲባል 7 አመትስ ብትቆዩስ ምን አለበት ...."...የሚል ቀልድ አያስቅም ነው ምትሉኝ...
እናቴ መመላለስ ሳበዛ ምን ብትለኝ ጥሩ ነው....
"ለምን ምሳ እየቋጠርሽ አትሄጂም....ከዛ ጊቢ እኛ ሀብታም ነን...😂"
"ባለስልጣኖቹ የጀመሩት ፎቅ...ወይ ሆቴል ብቻ whatever ካላለቀ እኛ እዚው እድሜያችን ማለቁ ነው..."
"እኔ እኮ አጥር ለሌለበት ጊቢ በአጥር ዘሎ መግባት አይቻልም ሲሉ ነው በእነርሱ ተስፋ የቆረጥኩት..."
"በቃ በቃ ዝም በሉ...በቃ በቃ አናውራው...pc አቀብዪኝ ፊልሜን ልይበት....ተቃጠልኩ እኮ...."
"አንድ መንገድ ብቻ ባለው ጠባብ ጊቢ ውስጥ አሸን አዛዥ ምን ይሉታል...ባላየ ማለፍ ራሱ እኮ አይታሰብም በቀን ሰላሳ ጊዜ ሰላም እየተባባልን ካካካ..."
"የምንሳልበት የምንሞረድበት የህይወታችን ክፍል ነው ...ለበጎ ነው ብለን እናስብ...."
"እንደዛ ማሰቡ ባይከፋም ሮቦት መሆን ግን ሰልችቶኛል....በሆነ አካል መመራት...programmed እንደተደረገ አካል እላይ ባሉ አካላት መሽከርከር..."
"አሁን ተሳሳትሽ...."
"ምኑ ጋር ነው የተሳሳትኩት...."
"እላይ ባሉት አካላት ብቻ አይደለም...እታች ያለም ስልጣኑን ሊያሳይሽ የቻለውን ያደርጋል...የምር የዚህ ጊቢ በማንኛውም ዘርፍ የመቀጠሪያ መስፈርት 'ተማሪዎችን ማንገላታት...ማስመረር...ተማሪዎችን ውሻ ማድረግ.....ማመናጨቅ...መበደል...'...እና የመሳሰሉት ስርአት አልበኝነቶች ነው የሚመስሉኝ...."
"ደግሞ በሆነ አካል መሽከርከር ከጊቢም ከወጣን በኃላ አይቀርልንም...እሱ ደግሞ የህዝብነት መስፈርት ይመስለኛል...."
"ፖለቲካ ውስጥ ገባን ሳናስበው...."
"በቃችሁሁሁ እንዴ በቃ እንዳታሳብዱኝ...እንዴ ያማችኃል እንዴ በቃን በጌታ ባሰብኳቸው ቁጥር እየነደድኩ ነው...ሸ መስኮቱን ክፈቺው በጌታ ጋልኩ በንዴት....."
ከምናሳብዳት ብለን አቆምን....ግን የምር እውነቷን ነው ሮቦት መሆን ይሰለቻል።
✍ሸዊት ነኝ የሚዛን ቴፒ ቀበጥ የጤና ጊቢ ምርኮኛ😂....ብሶቴን ጨርሳችሁ ስላነበባችሁት አመሰግናለሁ....ይሄን ጊቢ ስቦጭቅ እንደተመረቅኩ ነው ሚሰማኝ😂 መልካም አዳር።
https://www.tg-me.com/ethioleboled

Telegram
📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜
📚📚እንኳን በደህና መጡ📖📗🧾
➥ እዚህ ቻናል ላይ የተለያዩ የ አማርኛ እና እንጊሊዘኛ ..... መፅሀፍትን በ 📙 Pdf እና ትረካዎችን እና ሌሎችም ጠቃሚ ነገሮችን ያገኛሉ።
📖 ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል‼️
B-) :-መረዳዳት ቢኖር ሁሉም ቢተባበር
100K ይደርስ ነበር ።
For any comment @Meki3
➥ እዚህ ቻናል ላይ የተለያዩ የ አማርኛ እና እንጊሊዘኛ ..... መፅሀፍትን በ 📙 Pdf እና ትረካዎችን እና ሌሎችም ጠቃሚ ነገሮችን ያገኛሉ።
📖 ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል‼️
B-) :-መረዳዳት ቢኖር ሁሉም ቢተባበር
100K ይደርስ ነበር ።
For any comment @Meki3
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜
በህይወቱ ለመጀመርያ ጊዜ ስላፈቀራት ሴት ታሪክ በውስጥ መስመር ካጋራኝ የቻናሉ ተከታይ ፅሁፍ
የቃላት ማሻሻያ ተደርጎበት የቀረበ
📜....📝
በእውነት ነው ምላቹሁ በህይወቴ የዛሬ 14 አመት ገደማ በጣም የምወዳት ቆንጅዬ ሴት ገጠመችኝ እሷን ለማገኘት ያልሆንኩት ያልደረሰብኝ ስቃይ የለም እኔ 18 ቀበሌ ልጅ ስሆን እሷ የ42 ቀበሌ ልጅ ናት በመሀላችን አስፓልት ነው የሚለየን ምንም የደሀ ልጅ ብትሆንም ለኔ ልዩ ሴት ነበረች። እስካሁንም ለኔ ልዩ ናት።
ትዝ ይለኛል የዛኔ በኢት..አቆጣጠር በ1986 አ.ም የ8 ተኛ ክፍል ተማሪ ነበርኩ እሷን ካየሁ በኋላ ሚኒስትሪ ሁለት ጊዜ ወድቅያለሁ ሀሳቤ ሁሉ እሷጋ ነበር። ቤቴ ውስጥ ሆኜ መሽቶ እስኪ ነጋ በጣምም ይጨንቀኝ ነበር። በሷ ጉዳይ ያልተጣላሁት ጎረምሳ የለም እሷን ለማግኘት በራሴ ላይ ትልቅ ችግር እየፈጠርኩ ሄድኩ። ከቤተሰብ ጋር አለመስማማት፣ ጸባዬ ሁሉ ተቀየረ።
ቤተሰቦቼ እኔን ይናፍቁኝ ጀመር ውሎዬ ከሷ ጋር... ጠዋት እነሳና ሰፈሯ እቤታቸው ፊትለፊት መገተር ሆነ ስራዬ ታሪኳን ስታጫውተኝ ልገልጽላት የማልችለው ፍቅር ያዘኝ እንቅልፍ ነሳችኝ ቤቴ ውስጥ ምንም ነገር አልጥም አለኝ የሚያሳስበኝ ምን ጊዜም የሷ ችግር ብቻ ነው። ስለቤተሰቦቿ ጠይቂያት እናቷ በህይወት አለመኖራቸውን እህት ወንድም እንደሌላት አባቷ በፖለቲካ ችግር እስር ቤት መሆኑን እና በእንጀራ እናት መቅረቷን ገለጸችልኝ።
እንጀራ እናቷም በጣም እንደምትበድላት ነገረችኝ እኔም አይዞሽ ከጎንሽ ነኝ እላት ነበር እንጀራ እናቷ እንጀራ በመጋገር ሲሆን ኑራቸውን ሚገፉት ልጅቷ ደግሞ የተጋገረውን እንጀራ አምጥታ እኛ ሰፈር ነበር ምትሸጠው አንድ ቀን ትዝ ይለኛል በጣም ስለምወዳት "ፎቶ በቀለ" ሄደን ፎቶ አብረን መነሳት አለብን ብያት ቀጠሮ ይዘን ሁለት የቁም ፎቶ ጭንቅላት ለጭንቅላት ተደጋግፈን ተነሳን::
የዛን ቀን የእንጀራ እናቷ ከባድ ቁጥጥር ይቆጣጠሯት ስለነበር ጉሊት ፈልገው አጧት መሰለኝ ለሶስት ቀን ያህል መምጣት ተወች ምን ይዋጠኝ የዛን ቀን የጀመረኝ በሽታ ልክ እንደ እርጉዝ ሴት ጠናብኝ በጣም ተረበሽኩ ምሽት ያበሳጨኝ ጀመር የዛን ጊዜ ከምሽት ይልቅ ንጋትን ብቻ እመርጥ ነበር ሲነጋ አድፍጬ በራቸው ላይ መጎለት ጀመርኩ በጠዋት እየተነሳው ብቻ ከሶስት ቀን በኋላ ወደመደበኛው ስራዋ ተመለሰች እኔም መንገድ ላይ እየጠበኳት የያዘችውን መሶብ በጭንቅላቴ እየተሸከምኩላት ወደ ገበያው ማድረሴን ተያያዝኩት የያዘችው እንጀራ እንዳያድር ብዙ እጥርላት ነበር😂😂😂
ብቻ ገበያተኛ ሲመጣ ሰርገኛ ነው ቀጭ ቀጭ አይልም አረ ጥሩ እንጀራ ነው ማለቱን ተያያዝኩት ተመስገን እንጀራውም ቶሎ ቶሎ ማለቅ ጀመረ በንደዚህ አይነት ሁኔታ በጣም እንዋደድ ጀመር ትምህርቴን ብዙም መከታተል ትቻለሁ በመሀል አንድ ቀን አባቴ የክፍለ ሀገር ሹፌር ስለነበር (ነብሱን ይማረው) መሶቧን ተሸክሜላት ያየኛል አይቶኝ እንዳላየ ሆኖ አለፈኝ ወደቤት ገባ እኔም በጣም ደነገጥኩ መኪናውን ሳየው ቶሎ እሷን አድርሼ ተመልሸ ቤቴ ገባሁ። ሰላም አልኩት እሱም ሰላም አለኝ በጣም ሀይለኛ ስለነበር ሁላችንም እንፈራዋለን።
አባቴም "ስማ ልጄ አልታይም ብለህ ከምትሰራው ስራ እታያለሁ ብለህ ብትተወው ይሻልሀል::" ብሎኝ ዝም አለኝ እኔም እሺ አልኩት እያሳሳቀ ነበር የተናገረኝ:: ፋዘርም አንድ ቀን አድሮ ወደስራው ሄደ እኔም በጣም ስለምወዳት በወቅቱ አንድ እንጀራ ዋጋው ስሙኒ ነበር(25 ሳንቲም) ስሯ እየተቀመጥኩ የአንድ ብር ከሰባ አምሳንቲም እንጀራ ቁጭ ብዬ እየገዛኋት እበላ ነበር። (አስቡት 7 እንጀራ😂)
እኔም እሷም ሆነን በቃ ምን ልበላቹሁ እኔ ግን በዛን ሰአት ለፍቅራችን መስዋት መክፈሌ ነው እንሸጥና እንጀራውን ካላለቀ ችግር እንደሚደርስባት ስለማውቅ በቃ እኔው እራሴ እየገዛሁ አብረን ሜዳው ላይ ደረቅ እንጀራ እንበላ ነበር ቁንጣን እስኪይዘን ድረስ 🙈
በእውነት ነው ምላቹሁ ከሷ ጋር እንደዚህ አይነት ኑሮ ስንገፋ ከርመን እንደተለመደው አባቴ ምን ያህል ሀይለኛ እንደሆነ ነግርያቹሀለሁ እኔ በሌለሁበት ወንድሜን የሱንም ያንተንም ደብተር አምጣ ይለዋል። የኔን ደብተር ሲከፍተው ውስጡ ሙሉ ሴሜስተር አንድ ገፅ አልተፃፈበትም ነገርግን ውስጡ የኔንና የሚሚን ፎቶ ያየዋል።
ልክ እንደፈረደብኝ ወደ ቤት ስገባ ቤቱ ጸጥ ጭር ብላል ማን የት ምኑጋ እንዳለ አይታየኝም ከውጪ ስለገባሁ የሰማሁት ያባቴን ድምጽ ብቻ ነው እሱም ና ና ወደዚህ የሚል እኔም አቤት ብዬ ገባሁ የቤቱ በር ተቆለፈ ጎረቤት መጥቶ እንዳይገላግለን 😭😭😭
ከዛው አምጣ ደብተሮቹን አለኝ አመጣሁለት ትምህርት ለምድነው ማትማረው የኔ ጎረምሳ ብሎ ተውኝ ዋጋዬን ሰጠኝ ቦታ ሳይመርጥ አገራችን ትዝ ካላቹሁ ብረት ምጣድ አለ በጣሳ ሻውር መውሰጃ እሱ ላይ ሳሙና አረፋ ተመታና እዛ ላይ ሆኜ የዱላ መአት ወረደብኝ ብድግ እያልኩ ቁጭ ብረምጣዱ ላይ ሆኜ በመጨረሻም ዱላውን ስላልቻልኩት በጣም ስለበዛብኝ ቤት ውስጥ በገመድ ታስሬ ነበር።
እንደበግ ቤት ውስጥ ታስሮ መቀመጥ ስላልቻልኩ የታሰርኩትን ገመድ በጥሼው እሷን ፍለጋ ወደ ሰፈሯ ሄድኩኝ በወቅቱ ስነግራት በጣም አዘነች አለቀሰች የት አባቴ ልውሰድህ አለችኝ በወቅቱ እሷም ሆነች እኔም ችግር ላይ ነን ያለነው ምንም ገንዘብ አልነበረኝም ከእንጀራው ሂሳብ ላይ አጉድላ 3ብር ሰጠችኝ በዛው ዘመድጋ ሄድኩ ለምን እሷን ማየት ነብሴ ይፈልጋል ግን ሊመጣ የሚችለውን ችግር እያሰብኩ ብዙ ጊዜ ሆነን ከሷም ከቤተሰብ ጋርም ሳንገናኝ እዚህ ያለሁበት አገር እህት ነበረችኝ ደብዳቤ ጽፌላት ሁሉንም ነገር ጨረስኩ።
ከአገር ለመውጣት ሁለት ቀን ሲቀረኝ ከአባቴ ጋር ይቅር ይቅር እንድንባባል ከቤተሰብ ጋር አስታረቁኝ እሷንም አግኝቻት በጣም አዘነች እና መቼም እዛ ቴሌፎን ችግር ታውቁታላቹሁ በስደት ላይ ሆነን ሶስት ጊዜ አቀረቡልኝ በአራተኛው እንዲህ አይነት ስም አናውቅም ይሉኛል።
እና የመጀመሪያ ፍቅር አያድርስ ነው የአንድ ብር ከሰባምሳንቲም እንጀራ በየጊዜው ያስበላል ብላቹሁ አታምኑኝ ይሆናል እና እናንተም የደረሰባቹሁን እስኪ ጻፉት ወደዚህ ለመራሽኝ እህቴ እድላዊት በጣም ነው ማመሰግንሽ አክባሪሽ ጣሴ ጣሱካካካ ☺️☺️😔
#ያጋሩ
➴
@ethioleboled ▬▭🌹▬▭▬🌹

📝አንዳንድ ታሪኮች ርዕስ የላቸውም--ተነግረው እንዳልተነገሩ ይረሳሉ።
📝አንዳንድ ሰዎች ስም የላቸውም--ኖረው እንዳልኖሩ ይቆጠራሉ።
📝አንዳንድ ገድሎች አልተዘከሩም--የባከኑ መስዋቶች ይባላሉ።
📝አንዳንድ ቅሌቶች ሰው ፊት አልታዩም--እንዳልተፈፀሙ ሁሉ በጨለማ ውስጥ ይቀራሉ።
📝አንዳንድ አወዳደቆች ከትዝብት ተጋርደዋል--ዙሪያውን ገላምጠን ልብሳችንን አራግፈን እንቀጥላለን።
📝አንዳንድ ህዝቦች በወል ተረስተዋል--ለመታሰቢያነት የቀረላቸው ምንም የለም።
📝አንዳንድ ኮቴዎች በመርሳት ተጠቅተዋል--አንዳንድ ወኔዎች ለሞት ዳርገዋል--ከሁሉም በላይ ግን አንዳንድ ልቦች በሶስት መሀላ ተክደዋል።
📓ሀገር ያጣ ሞት
✍️ ሄኖክ በቀለ ለማ
🔵 @ethioleboled

እንዲው በደፈና "ወደድኳት! አበድኩላት።" የሚያሰኝ ድፍን ፍቅር አልነበረም የያዘው።በርህራሄ እና በመተሳሰብ ላይ መሰረቱን የጣለ እውን የሚዳሰስ እና የሚጨበጥ፤ንፋስ የማይገፋውና ውርጭ የማያበርደው ፍቅር.....
📓ወገግታ
✍️ የሺጥላ ኮኮብ
📚 @ethioleboled
📓ወገግታ
✍️ የሺጥላ ኮኮብ
📚 @ethioleboled
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜
ወገግታ @Bemnet_Library.pdf
11 MB
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜
⚪️⌨#ልጅ ፡ አባቴ ባህሪዬ እንዴት ቢሆን ደስ ይልሃል ?
#አባት፡ እንደዚህ ሁን ልጄ
⚪️⌨#ልጅ ፡ እንዴት ?
#አባት ፡ እንደ ውሃ ሁን ባስቸገረ ግዜ እሳትን ቢያጠፋም በተፈለገ ጊዜ ግን እንዲገኝ ዛፍ ማሳደጉን አይተውምና ፤
እንደጨውም ሁን ለሁሉም ምግብ ቢፈለግም በቀላሉ ይገዛ ዘንድ ግን-ዋጋው ውድ አይደለምና ፤ ከሁሉ ከሁሉ-ግን እንደ ወተት ሁን በተውት ግዜ በሌላ-መልክ ተመልሶ ይመጣል እንጅ አይበላሽምና-በተገፋም ግዜ ከፍ ከፍ ይላልና።
⚪️⌨#ልጅ፡ እሽ አባቴ እንዳልሆንስ የምትፈልገው የለም ?
#አባት አለ ልጄ፤ እንደዚህ አትሁን
#⌨ልጅ ፡ እንዴት ?
⚪️#አባት፡ልጄ ሆይ እንደ መርፌ አትሁን የሌሎች ብዙ ቀዳዳ እየደፈነ የራሱን አንዷን መድፈን አይችልምና፤
እንደ መቋሚያም አትሁን ለሌሎች መደገፊያ እየሆነ ለራሱ ግን መቆም አይችልምና ፤
ከሁሉ ግን እንደ ደወል አትሁን ! ከሁሉ ቀድሞ ነቅቶ ሌሎችን ለቅዳሴ ቢቀሰቅስም እርሱ ግን አያስቀድስምና።
...............
**** መልካም ቀን

➡️አንዳንዴ useless እንደሆንን ሊሰማን ይችላል፤
አንዳንዴ ሰዎች እንዲረዱን ፈልገን አልተረዱን ይሆናል፤
✅አንዳንዴ ምክንያቱንም ሳናውቀው በምንወዳቸው ሰዎች ፊት ላይ ጥላቻ ተስሎ አይተን ይሆናል፤
አንዳንዴ ለሰዎች ከሰጠነው አክብሮት በተቃራኒ ንቀት ተቀብለን ይሆናል፤
⭐አንዳንዴ እድሜያችንን ሙሉ ስንመኘው የነበረና ትልቅ የመሠለን ነገር ስናገኘው ትንሽ ሆኖብን ይሆናል፤
👍አንዳንዴ ለሰዎች መድረስ ፈልገን ሁኔታ፣ ጊዜና አቅም አጥተን መድረስ አልቻልን ይሆናል፤
አንዳንዴ አንደመልአክ የምናያቸውን ሰዎች በህይወት አጥተን ይሆናል፤
⭐አንዳንዴ ለቤተሰቦቻችን ልንፈጥርላቸው እንፈልግ የነበረውን ዓለም ቀርቶ ትንሽ እንኳን ልንደግፋቸው አለመቻላችን አሳዝኖን ይሆናል፤
⭐አንዳንዴ ሁሉም ነገር ትርጉም አጥቶብን ይሆናል፤
አንዳንዴ ሁሉም ቀን አሰልቺ፣ በድብርት የተሞላ እና ተመሳሳይ ሆኖብን ይሆናል፤
አንዳንዴ ከዛሬ የበለጠ ነገ ጨለማ ሆኖ ታይቶንም ሊሆን ይችላል፤
አንዳንዴ ሁሉም ነገር መኖር ራሱ ሳይቀር ከብዶን ይሆናል፤
አንዳንዴ ...
አንዳንዴ...
አንዳንዴ...
✅ግን It's okay to feel bored, sad, useless, and hopeless at times..
live
Lough
Love
ከሁሉም በላይ የተሻለ ጊዜ ከፊት አለ። 💙
✅በውስጣችሁ ያለውን ክፋት በውስጣችሁ ባለው መልካምነት የምታሸንፉበት የተዋበ ቀን ይሁንላችሁ።

every friend you invite! 🎉
🌟 Share this link: https://www.tg-me.com/botifyai_bot?start=referral_6405623892
Best ai bot arif Nw mokrut
🌟 Share this link: https://www.tg-me.com/botifyai_bot?start=referral_6405623892
Best ai bot arif Nw mokrut
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜
እፎይታ @OLDBOOKSPDF.pdf
17.9 MB
📚ርዕስ:- እፎይታ The Count of mònte
📝ደራሲ:-Alexander Dumas
👤ትርጉም:-ተሾመ ዳምጠው
📜ዘውግ:- ልብወለድ
📅ዓ.ም:- 1982 እኤአ
📖የገፅ ብዛት:- 602
📌ማጋራት አይዘንጋ!
@ETHIOLEBOLED
📝ደራሲ:-Alexander Dumas
👤ትርጉም:-ተሾመ ዳምጠው
📜ዘውግ:- ልብወለድ
📅ዓ.ም:- 1982 እኤአ
📖የገፅ ብዛት:- 602
📌ማጋራት አይዘንጋ!
@ETHIOLEBOLED
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜
አልቦ ዘመድ - ብርሃኑ ድንቄ.pdf
3.5 MB
"አልቦ ዘመድ" እንደያዘው ጠቃሚ ሀሳብ ብዙም ያልተዋራለትና ያልተነገረለት ምርጥ መጽሐፍ ነው።አንብቡና አትርፉበት።
ማጋራት መተሳሰብ ነው!
📚 @ethioleboled
ማጋራት መተሳሰብ ነው!
📚 @ethioleboled
Forwarded from 📚📚ቤተ__መፅሀፍት📖📗🧾📜
💥📚ኢትዮ-ልቦለድ📚📖💥
Photo
ክፍል አንድ
ታስታውቃለች ብዙ ፍቅር አግኝታ ነው ያደገችው ፤ የለመደችውን እንክብካቤ አልሰጠኋትም መሰለኝ ወይ ደግሞ አንደበቴ እና ሁኔታዬ አልተገጣጠመላትም ።
ግራ ገብቶታል ።
በፈለገችው ሰዓት አታገኘኝም ፣ ባላሰበችው ጊዜ ከብዙ እወድሻለሁ ጋጋታ ጋ እጠራታለሁ...አታመነታም ትመጣለች ።
ካለ እቅዶ እንበላለን ፣ እንጠጣለን ፤ ሞቅ ይለናል ። አልጋ ቦታ ቀድሜ ባሰብኩት መሰረት እወስዳታለሁ ፤ ልብሷንም እሱንም ምንቅርቅር እያደረኩ አራቁታታለሁ።
እንደምወዳት እየነገርኩ አልጋው ላይ እየገለባበጥኩ ፣ እየተገለባበጠችልኝ እወስባታለሁ ።
ሁኔታዋ መቁነጥነጧ ደስ ይለኛል
እርቃኗን ለብዙ ሰው የታየች አይመስለኝም ከተወሰብን በኋላ ቶሎ ትከናነባለች ፤ ጡቷን ፣ ገላዋን ምናምን በአንሶላ ትከዳድናለች ።
ወሲብ ላይ እንደፈለገችው አትቃትትም ወይ ከቃተተች በኋላ አንገቴ ውስጥ ትወሸቃለች ፤ ታፍራለች ነፃ መሆን ይሳናታል
ሻወር ቤት ተጣጥቤ ስመለስ ቅር ያለው አይን አያለሁ ፤ ቀስ ብላ አይኗን ከእኔ አሽሻ ሻወር ቤት ትገባለች ፤ ሻወሩን ትከፍተዋለች ሻወሩን እንደከፈተችው የምታለቅስ ይመስለኛል።
Empty sex አለመደችም ።
ስሜቷ ተብትቧት መላመድ አጃጅሏት በፈለኳት ሰዓት እስሬ አለመጥፋቷ ይዶክካታል ።
ከመርኋ ጋ አኗኗሯ ተጣርሶባታል ፤ ሁኔታዬ እንደምትፈልገው ፣ እንደምትመኘው አይደለም መሰለኝ !
አብሬያት ያለሁት እኔ ልኳ እንዳልሆንኩ ገብቷታል ፤ ልቤ ላይ ቦታ እንዳላት እና እንደሌላት እርግጠኛ አይደለችም ፤ እልህ እና ግራ መጋባት ነው ከእኔ ጋ ያጣበቃት ።
ልምድ ስለምበልጣት ፣ በእሷ ልክ ስለማልወዳት ሁኔታዋን ከስሜት ውጪ ሆኜ ማጤን አልከበደኝም ።
እያንዳንዱን ነገሬን ትመራመራለች ፤ በዋዛ የማወራውን ነገር ሁሉ ትርጉም ትፈልግለታለች ።
ታሳዝነኛለች ።
ልጅነቷ ያሳሳል ። ስንዋሰብ ፊቷ ፣ አተነፋፈሷ መቅበጥበጦ ይማርከኛል
ስለምታፈቅረኝ እንድወስባት እንደፈቀደች
ለመናዘዝ ስትዳክር ። ምን ማለት እንደፈለገች ስለሚገባኝ እያብራራች ውስጤ ሲፈግግ ይታወቀኛል።
የዋህነቷን እየተነተንኩት ነው ። ይብላኝ ለቀጣዩ...፦
ስላሳዘነቺኝ መከርኳት ፣ ጥሩ ሰው ስለሆነች መብከንከኗ አሳዝኖኝ መከርኳት ፣
ይሄውልሽ ሃሴት
ሁኔታችን ላይ ከሚገባው በላይ እየተመሰጥሽ ነው !...አትመሰጪ ቀለል አድርጊው don't take everything seriously አንቺ በጣም አሪፍ ልጅ ነሽ ትበዥቢኛለሽ አንጂ አታንሺብኝም.... ምናምን .... ገለመሌ.... እያልኩ ቢራ እየተጎነጨው ተረጋግቼ መከርኳት።
ዝም ብላ በትዝብት ስትሰማኝ ቆይታ ሳቀች፤ እየጠጣነው የነበረው ቢራ አስክሯት መስሎኝ ነበር
<< አየህ አሸናፊ ሰዉ ሲያወራ ደስ ይላል፤ ፈታ ብሎ እየተመፃደቀ ነው ፣ መልሱ አያስጨንቀውም፣ አይፈራም ፣ ከተሸነፈው ሰው የሚሰነዘረው አፀፋ ማታ እቤቱ ገብቶ እንቅልፍ እንዳይነሳው አይጨነቅም ።
ስላሸነፍክ ነው የተመፃደከው ።እኔ ላይ የሆንከውን መንቀባረር እና መፈላሰፍ ሌላ ያፈቀርካት ጋር እንደማታንፀባርቀው አንተም እኔም እናውቃለን ።!
ጥሩ ሰው ማለት ለሆነ ሰው ብሎ ክፉ እንደሆነ አክት የሚያደርግ እንጂ በአሰብኩልሽ በኩል ቅዱስ ነኝ ፣ፈላስፋ ነኝ የሚል አይደለም ።
እንደ አንተ አይነት ወንዶች ሂዱ ስትባሉ እንደምትመጡ ተረድቻለሁ በRevers psychology ማኔጅ የምትደረግ ወንድ እንደሆንክ ይገባኛል ። ራሴን ስለማከብር በቁም ነገር መሃል game አልወድም ።
አንተ ሳትደክም ያገኘኸው ላይ ውበት ያለ አይመስልህም ። የነገሮችን ትልቅነት በሚያለፋ ልክ ነው የምትመዝነው ።!
እምባዬ የሚታገለኝ በገባኝ ጉዳይ እየተሸነፍኩ መሆኔ ሲገባኝ ነው !።
ሴት ልጅ ከወሲብ በኋላ የምትታቀፈው መታቀፍ፣ የምትሰማው እወድሻለሁ ትጣፍጫለሽ ትረካ፤ ወሲብ ስታደርግ ካለው ደስታ አያንስም ሊያውም ይበልጣል እንጂ ።
አንተ ማግኘት ላይ እንጂ ማቆየት ላይ Lazy ስለሆንክ ስሜትህን ካራገፍክ በኃላ ሮጠህ ሻወር ቤት ሄደክ ብቻህን እየዘፈንክ ትደሰታለህ ።
እስቲ ግዜ ወስደህ የምትልክልኝ ቴክስቶችን እያቸው፤ የምታወራኝ ነገሮችን እየው.... ግራ ይገባል እኮ ....ግራ እያጋባኸኝ ግራ ሲገባኝ ልትመክረኝ ለምን ቃላት ትሞርዳለህ
..እ ?
በጣም ካዘንክልኝ ለምን እርግፍ አድርገህ አተወኝም ...??!
አንጠልጥሎ ከመያዝ አክብሮ መተው እንደሚበልጥ አታውቅም ? !
የመጨረሻው ክፍል ይቀጥላል ግን React እና Like👍👍 ካረጋችሁ