Telegram Web Link
ከመኪተሉት የደራሲ ይስማዕከ ወርቁ ልብ-ወለድ መካከል ያልሆነው የቱ ነው?
Anonymous Quiz
26%
ሀ. የወንድ ምጥ
15%
ለ. ዮቶድ
14%
ሐ. ተከርቸም
20%
መ. ዛምራ
24%
ሠ. መልሱ አልተሰጠም
"ከቀስት ፊት ያመልጡ ዘንድ ለሚፈሩህ ምልክትን ሰጠሃቸው።" መዝ. 49÷4

እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በደህና አደረሳችሁ !


   #Share
              ➘
          
@ethioleboled
📜❦ ═══ •⊰❂⊱• ═══ ❦📜
ምልክአም_ሰይፈ_ነበልባል_አቤ_ጉበኛ.pdf
8.3 MB
ምልክአም ሰይፈ ነበልባል

አቤ ጉበኛ
መሬት የማን ነው-ከአቤ ጉበኛ.pdf
968.3 KB
መሬት የማን ነው

አቤ ጉበኛ
አልወለድም አቤ ጉበኛ.pdf
4.5 MB
ደራሲ አቤ ጉበኛ
መፅሀፉ አምባገነኖች እና ጉልበታሞች እንደፈለጉ በሚያሽከረክሯት ዐለም ላይ አልወለድም ይለናል ።
💟"ልረሳት እየጣርኩ ነው" ። ❤️

አልወዳትም እያልኩ እያጣጣልኳት ውስጤ ምን ጎቦ ቢበላ ነው የሚያብሰለስላት ። የትኛው አካሌ ከሷ ጋ አብሮ ነው ህልሜ ላይ ሳይቀር በፍቅር የማያት። ይሄ እንዲ እንዳለ ልረሳት እየጣርኩ ነው

እሷ አትወደኝም ! 🌹❤️

ለመታረቅ ለማግኘት የምሄዳቸውን ዙርያ ጥምጥም መንገዶች እየዘጋጋችው አይደል ? ጥንጥዬ የመታረቅያ መንገድ ለምን ገርበብ አላደረገችልኝም ? 🌹🥀

ውስጦ ከኔ ጋ ቢያብርልኝ ይሞኝልኝ ይታልልኝ አልነበር? ሰው ለሚወደው ጥንጥም ቢሆን ካልታለለ መውደዱ መኑ ጋ ነው? እውቀታችኝ ከስሜታችን እጅግ ከበለጠ ምኑን ፍቅር ሆነ ።

ሳንከሳ ሳንጠቁር ሳንብሰለሰል እርግፍ አድርገን ከተውን መጀመርያ ፍቅር ይሉት እሳቤ ውስጣችን አልረሰረሰም ማለት አይደል?!

ስለማትወደኝ እንድረሳት ውስጤን ላሳምፅባት እየጣርኩ ነው ።

ብትወደኝ ከኔ ጋ ለመሆን መስፈርት አትደረድርም!
❤️ማነው ስልጣኑን ገንዘቡን ፍላጎቱን በእውነተኛ ፍቅር ፊት መዝኗ መስፈርቱ ሚዛን የሚደፋበት

እሷ አትወደኝም !

የፊቴ መለዋወጥ አያስበረግጋትም እሷ ላይ የምይዘው አቆም አያብከነክናትም ፤ ዙርያዋ ላሉ ሰዎች ስለኔ አትነግራቸውም (አሁን ፍቅር ጅል እንደሚያደርግ ማሳያ ካልሆነ በቀር ስለኔ አትነግራቸውም ተብሎ ክስ አለ? )

ዘውትር ካስቀመጠችኝ ስፍራ መገኘት ለኔም ለሷም ኪሳራ ነው። መዋደድ ምን እንደሚመስል ፈቀቅ ብዬ ማየት አለብኝ ። ከመወደድ ወደ መዋደድ እንድትሸጋገር ፈቀቅ ልልላት ይገባል።

ስሄድላት እኮ እንደንፍጣም ትንሽ ልጅ እናቱ ጋ እንደሚታከከው ስንቴ ታካ መልሳኛለች ። ሰው ሁሉ እኮ እንደትንሽ ልጅ ነው❤️⭐️

ልጅነቱን በብልጣብልጥነት ጀቡኖት እንጂ። ህፃን ልጅ ሌላ ህፃን ልጅ ስናጫውት መሰስ እያለ ይመጣ የለ ለምነ ነው እኮ አሻፈረኝ ብሎ ቀርቶ ነበር።

🔵በጥበብ በማስተዋል ካልተጓዝን እለታችን እንደዋዛ ይበላብናል ። ስሜታችን እና ፍላጎታችን ከነባራዊ እውነት ጋ ካላጣጣምነው እንከስራለን❤️💟

አንብበው ከወደዱት 👍 👍👍 እየተጫናችሁ
❤️ከአልጋ መውረድ ተስኖኝ ፤ በአጀባ ተመርኩዤ ተደግፌ ወረድኩ ። መኪና ወደቆመበት መቶ ሜትር ያክል ለመድረስ ሽምጥ -ሸለቆን የማቋረጥ ያክል መከራ ሆነብኝ ። መራመድ የመብረር ያክል ክቡድ ሆነ ። ተደግፌ ታዝዬ ደረስኩ ።😣😰

ያ ምላሴ ከመቼው ተለጎመ ?
ያ መንጠራራቴ ከመቼው ከሰመ ??

❤️መፍረዴ ፣ መቅለብለቤ ፤ ድንፋታዬ ፤
መስገብገቤ እንዴት በአንዴ ተገታ ?!

በቃ እቺው ነኝ ፤ በቃ እቺው ነን ?!

ግን ነገ ስድን ማለቴ......ከዳንኩ

ዳግም ጀግና ነኝ ፤ አልደፈርም ፤ አካኪ ዘራፍ በበነነ በተነነ ቁጥር እል ይሆን ??

እንዴት በአንዴ ከመኖር ውጭ
እንዴት በአንዴ ከጤና ውጪ ሁሉ ትርፍ ሆነብኝ?!

ያ ማሽካካት !

ያ ማን ይደፍረኛል !

የት ሰመጠ ?!✈️

በዚህ ፍጥነት ሁሉ ትርፍ ሁሉ ከንቱ ሆነብኝ እንዴት ይሄን ቀድሜ ማወቅ ተሳነኝ?!

ልጄን አደራ አልኩ ተስፋ በመቁረጥ። እንዴት አንድ ቀን እንደዚህ እሆናለሁ ብዬ ማሰብ ከበደኝ ?!

በዙሪያዬ ያሉ ሰዎች ሲታመሙ ፤ ሲያጣጥሩ ሲደክሙ እና ሲሞቱ ነገ በእኔ ብዬ ለምን አልሰከንኩም ??

ለገንዘብ ፤ ለስልጣን ብዬ ለዚች ትንሽ ግዜ መክፋት ነበረብኝ ?! 💠

ወይኔ መሞቴ ነው🟢🟢 !!!

የተስገበገብኩበት ገንዘብ አይከተለኝም። በድንበር ተጣልቼ በዛ መጠን የከፋሁበት፤ ያሴርኩበት ይዞታዬ አብሮኝ አይመጣም

ተስገብግቤ ወጥቼ ፤ ወርጄ የሰበሰብኩት ንዋይ የምድር ቆይታዬን የአንዲት ቀን ፀሃይ ወጥታ ስትገባ እንዳይ አይረዳኝም።😮‍💨😣

ማስታወሻ 🙏
😔😣በመኖር ጅረት ላይ ተመስጠን መሞታችንን እረስተነዋል ። ብንረሳውም ሁላችንም እንሞታለን !!

አንብበው ከወደዱት 👍 👍👍 እየተጫናችሁ
🟢የሐሽማል መጽሐፍ ደራሲ ማዕበል ፈጠነ መጽሐፍ ። "ከርታታ ኮከቦች" ይሰኛል።

🔵ሐሽማል ከመሆናቸው በፊት የተዋነይን ውኃ መጠጣት ነበረባቸው። ሁለቱ ተማሪዎች ከውኃዋ ከተጎነጩ በኋላ ሊቁ ፋሬስ አንድ ታሪክ መዘዙ።
"እኔና ቀለሙ ተፈሪ ይችን ውኃ የጠጣን ቀን ደስታው ሊያሳብደን ደርሶ ነበር። ቀለሙ ከወሎ ሲመጣ ገና ብላቴና ነበር። ኪነ ጥበብ ከሚባል ብስል ተማሪ ጋር መጥቶ የተዋነይን የቅኔ መንገድ ቀጸለ። ከዚያ በፊት የዋድላውን የቅኔ መንገድ በደንብ ያውቀዋል። የኢትዮጵያ ዐውደ ዓመት መባቻ ቅዳሜ ቀን በባተበት የዓመቱ መጨረሻ ቅዳሜ ቀን ከውኃዋ አብረን ጠጣን። ክስተቷ በዚያ ቀን ነበር። ከዚያ በፊት ያችን የምሥጢር ቀን ስንጠብቅ ዓመታትን አሳልፈናል። ደጅ ጥናታችን የወግ አልነበረም። ሕይወትን ፍለጋ እንደእኛ የተንከራተተ የለም። ከርታታ ኮከቦች ነበርን።"

*ከመጽሐፉ* የተወሰደ**

***
መጽሐፉን ይሀው
***
እናንብብ እንወያይ ነጻ እንውጣ
ንበብ ለንባብ
ከርታታ ኮከቦች-፩ @ETHIO_PDF_BOOKS.pdf
10.2 MB
📚😊📖ርዕስ: ከርታታ ኮከቦች



📝ደራሲ: ማዕበል ፈጠነ

ይዘት፦ ልቦለድ


😄*አቅራቢ*: ብሔረ መፃሕፍት ዘ-ኢትዮጵያ**

🕓"ከርታታ ኮከቦች"
የሐሽማል መጽሐፍ ቁጥር 2

🚢🚢🚢
ማዕበሉ የሰማይ ኮከቦችን ማነዋወጥ ጀምሯል!!የምሥጢረ ሰማይ እና የሐሽማል ትልቅ ወንድማቸው።ከርታታ ኮከቦች። እነሆ ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ ከአባቱ ከማዕበል ፈጠነ ተወለደ።
ሁሉም ሰው እኒህን ከርታታ ኮከቦች እየቆጠረ።የእውቀት እጣ ፋንታውን እንዲያውቅ ፈቅደናል።ወበልደቱ ይትፌስሁ ብዙኃን አንባብያን።(መጋቤ ብሉይ አእምሮ ዘውዴ)

ሐሽማል ከመሆናቸው በፊት የተዋነይን ውኃ መጠጣት ነበረባቸው። ሁለቱ ተማሪዎች ከውኃዋ ከተጎነጩ በኋላ ሊቁ ፋሬስ አንድ ታሪክ መዘዙ።
🚢🚢🚢
"እኔና ቀለሙ ተፈሪ ይችን ውኃ የጠጣን ቀን ደስታው ሊያሳብደን ደርሶ ነበር። ቀለሙ ከወሎ ሲመጣ ገና ብላቴና ነበር። ኪነ ጥበብ ከሚባል ብስል ተማሪ ጋር መጥቶ የተዋነይን የቅኔ መንገድ ቀጸለ። ከዚያ በፊት የዋድላውን የቅኔ መንገድ በደንብ ያውቀዋል።

☑️የኢትዮጵያ*ዐውደ ዓመት መባቻ ቅዳሜ ቀን በባተበት የዓመቱ መጨረሻ ቅዳሜ ቀን ከውኃዋ አብረን ጠጣን። ክስተቷ በዚያ ቀን ነበር። ከዚያ በፊት ያችን የምሥጢር ቀን ስንጠብቅ ዓመታትን አሳልፈናል። ደጅ ጥናታችን የወግ አልነበረም። ሕይወትን ፍለጋ እንደእኛ የተንከራተተ የለም። ከርታታ ኮከቦች ነበርን። ከመጽሐፉ የተወሰደ።
🚢🚢🚢
ይለያል







ታቅፌ አቃለው....የሱ ግን ይለያል ....ስጋዬን ብቻ ሳይሆን ነብሴንም የሚነካ ይመስለኛል... እቅፉ አለም ነው.... ጫጫታ...ሁካታ ሁሉን አስቀርቶ ሰላም ፍቅር ብቻ የሚሰጥ ልስልስ ብሎ ጠንከር ያለ ምቾትም ደንነትም ያለው.....

ማንም አይገባውም....እኔ ግን አውቀዋለሁ እና ይለያል...ትንፋሹ ሌላ ነው .....አዎ ትንፋሽ ያሞቃል...ሰውነት ቀስ በቀስ እንዲግል ያደርጋል አውቃለሁ.... የሱ ግን ከዚህም ይልቃል... እያንዳንዱን ሰውነቴን ሲያነዝረው ይሰማኛል... ልቤም ምቷን እየቀነሰች መታ ዝም ያለች ይመስለኛል.... ከትንፋሹ ውጪ ምንም ሙቀት ምንም አየር ወደ ውስጤ አይገባም...የሱ ብቻ እሱ ብቻ።

ለሌላው አይገባም አውቃለሁ...ብቻ ግን ይለያል.. ዓይኖቹን ሳያቸው ሀጥያቴ በሙሉ የሚሰረይልኝ ይመስለኛል..ፈጣሪ ሀጥያትሽን ሰርዤልሻለሁ ሽልማትሽን ሰጥቼሻለሁ ብሎ የሰጠኝ ይመስለኛል እሱን። የኔን እሱ። ለዛ ነው መሰለኝ በአይኑ ሀፅያቴን ሲሰርልኝል በራሴ አፍሬ አይኔን ከአይኑ ስነቅል ቀና አርጎኝ "እገባሻለው" የሚለኝ...ከዛ ደስ ይለኛል እንዲህ ማን ይገኛል በእይታ ነብስንም ስጋንም ሚያስደስት።

ለሌላው አይገባም አውቃለሁ... ብቻ ግን ይለያል ። ሰውነቴን ሲነካኝ አለም መሽከርከዋን ድንገት ታቆማለች... ከኔ ሰውነት ጋር የሷም የተነካ ይመስል አብራኝ ታፍራለች።  ህመሜ በሙሉ ይፈወሳል ። ፀጥ...ልስልስ...ሞቅ.. ይለያል ።የእውነት 😊 ብዙ እንዲነካኝ ብዙ በታመምኩኝ እሱ እንዲያክመኝ ብዙ በቆሰልኩኝ እስክል ያደርሰኛል ።

አውቃለሁ ለሌላው አይገባም...ብቻ ግን ይለያል። ልክ ሲስመኝማ ውይይይይ የልቤ የሀሴት ምት ኒዩክለርን ያስንቃል... የሰውነቴ አካሎች በሙሉ ከንፈር እስኪመስሉ ድረስ ሲያጣጥሙት ይታወቀኛል.... እየሳመኝ እጁን ሰውነቴ ላይ ሲያንሸራሽር በቃ ያን ጊዜ የመፈጠሬን አላማ ያገኘው ይመስለኛል ። በሱ ለመሳም በሱ ለመነካት የሱን ጠረን ለማሽተት የሱ ለመሆን የሱ ብቻ ። የኔ እሱ 😚።ለሌላው አይገባም አውቃለሁ.... ብቻ ግን ይለያል።



የእውነት.......




Kalkidan






https://www.tg-me.com/ethioleboled
የታንጉት ምስጢር @OLDBOOKSPDF.pdf
1.2 MB
📚ርዕስ - የታንጉት ምስጢር
📝ደራሲ - ብርሀኑ ዘሪሁን
📜ዘውግ - ልብወለድ ( ታሪካዊ )
📅የህትመት ዘመን - 1958
📖የገፅ ብዛት - 228
በሀገራችን ከተፃፉ ታሪካዊ ልብወለዶች መሀከል እጅግ ተወዳጅ ከመሆኑም በላይ አንዳንዶች የአማርኛ ስነፅሁፍ ማስተርፒስ ይሉታል። በሀገራችን በአፄ ቴዎድሮስ ህይወት ዙሪያ ከተፃፉት 2 ታሪካዊ ልብወለዶች ( አንድ ለናቱ & የታንጉት ምስጢር ) የተሻለ ቦታ የሚሰጠውም ይህ መፅሀፍ ነው::

📌ማጋራት አይዘንጋ!
@ETHIOLEBOLED
ራስን ማወቅ ሌላውንም ማወቅ ይሆናል ካወክ ዘንድ ለራስህ የምትሻውን ለሌላውም ትመኛለህ ለራስህ እና ለሰው ልጅ ሁሉ በጎ ፈቃድና ፍቅር ይኖርሃል።ከዚህ እውቀት ደረጃ ላይ ስትደርስ ለምታደርገው ነገር ሁሉ ምስጋናም ሆነ ጥቅም ከሰው ዘንድ አትሻም።ልብህ ጥቅም ላይ ካተኮረ የተፈጥሮን በጎ ምግባር ትስታለህ።

ወዳጄ ልቤ የሰው አካል እና ነፍስ አንድ ስለሆኑ የሚፀድቀው የሚኮነነው በራሱ ልብ ውስጥ ነው እንጂ በሌላ ቦታ አይደለም።የማንኛውም ነገር መለኪያና ሚዛን ራሱ ሰው ነው ከሰው በላይ ምንም ነገር የለም.......

📖ደራሲው📖
በዐሉ ግርማ

share 🔗 @ethioleboled

🙏ማጋራት እንዳይዘነጋ🙏
አርቲስት ደበበ እሸቱ

ከያኒ ወጋየሁ ንጋቱ

#ታሪክን_ወደኋላ

Https://www.tg-me.com/ethioleboled
🔵የታያችሁን ያህል ተንቀሳቀሱ!

አንድ ምሽት ላይ አባት ልጁን ወደ ሲኒማ ቤት ሊወስደው ውጪ መንገድ ላይ መኪና ውስጥ እየጠበቀው ነው፡፡ ልጅ ከቤት እንደወጣ በጣም ስለጨለመበት ስልኩን አውጥቶ አባቱ ጋር ደወለ፡፡

ልጅ፡- “አባዬ እንዴት ልምጣ? ጨለማ ስለሆነ አይታይም”፡፡

አባት፡- “ምን ያህል ይታይሃል?”

ልጅ፡- “አምስት እርምጃ ያህል ብቻ ነው የሚታየኝ”

አባት፡- “አምስት እርምጃ ተራመድ”

ልጅ፡- “እሺ” (አምስት እርምጃ ተራመደ)

አባት፡- “አሁንስ ምን ያህል ይታይሃል?”

ልጅ፡- “አሁንም ሌላ አምስት እርምጃ ያህል ርቀት ይታየኛል”

አባት፡- “በፊትህ የሚታይህን አምስት አምስት እርምጃ እያልክ ከመጣህ እኔ ጋ ትደርሳለህና የታየህን ያህል ተንቀሳቀስ”

ልጅ ብዙም ሳይቆይ አባቱ ጋር ደረሰ፡፡

🟢ሁሉም ነገር ጥጉ ድረስ እስኪታያችሁ አትጠብቁ፡፡ በሚታያችሁ መጠን ተራመዱ፡፡ የሚታያችሁን ያህል ስትራመዱ፣ ከመራመዳችሁ በፊት ያልታያችሁን ማየት ትጀምራላችሁ፡፡

ሁሉንም ነገር እስከምታውቁ አትጠብቁ፡፡ በምታውቁት ልክ ስራን ጀምሩ፡፡ በምታውቁት እውቀት መጠን ስራን ስትጀምሩ፣ ያንን ከመጀመራችሁ በፊት ያልነበራችሁ ልምድና እውቀት ወደ እናንተ ይመጣሉ፡፡

ሁሉም ሰው እስኪቀበላችሁ አትጠብቁ፡፡ የሚቀበሏችሁ ላይ በማተኮር ተሰማሩ፡፡ በሚቀበሏችሁ ላይ ስታተኩሩና ደስተኛ ስትሆኑ፣ ቀድሞ የማይቀበሏችሁ ሁሉ እናንተን ከመቀበል ውጪ ምርጫ አይኖራቸውም፡፡

የጠየቃችሁት ነገር ሙሉ በሙሉ እስኪሰጣችሁ አትጠብቁ፡፡ የተሰጣችሁን ተቀበሉና በዚያ በመጀመር የምትችሉትን አድርጉ፡፡ በተሰጣችሁ በጥቂቱ የምታደርጉት ጥረትና የምታከናውኑት ነገር የቀረው እንዲለቀቅላችሁ መንገድ መክፈቱ አይቀርም፡፡

አትቀመጡ! የታያችሁን ያህል ተንቀሳቀሱ!

ዶክተር እዮብ ማሞ
🔵አንድ ቀን ሁሉም ሰራተኞች ወደ ቢሮ ሲደርሱ አንድ ጎላ ተደርጎ የተፃፈ ማስታወቂያ ተለጥፎ አዩ ፡፡ “በዚህ ኩባንያ ውስጥ እድገትዎን የሚያደናቅፈው ሰው በትላንትናው ዕለት ከዚህ አለም በሞት ስለተለየ በመሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ የሽኝት ሥነ ሥርዓት ተዘጋጅቷልና መጥተው ይሰናበቱት ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን" የሚል

🟢መጀመሪያ ላይ ሁሉም በሞተው የሥራ ባልደረባ ሐዘን ገብቷቸው ነበር ፣ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ግን የባልደረቦቹን እና የድርጅቱን እድገት የሚያደናቅፍ ያ ሰው ማን እንደሆነ ለማወቅ መጓጓት ጀመሩ፡፡

በአዳራሹ ውስጥ በርካታ ሰው ስለነበር ደንብ አስከባሪ ጥበቃ በክፍሉ ውስጥ ያለውን ሕዝብ እንዲቆጣጠሩ ትእዛዝ ተሰጣቸው። አዳራሽ ውስጥ ያለው ሰው እየጨመረ በመጣ ቁጥር የሟቹን ነገር ተረስቶ እድገታቸውን ያስተጓጎለው ሰው በሞሞቱ ደስታ ይሰማቸው ነበር፡፡ ብዙዎቹም እያጉረመሩሙ መደሰታቸውን ይገልጻሉ፡፡ ሰዎች ወደ ሬሳ ሳጥኑ በቀረቡ ቁጥር ደስታቸው እየጨመረ መጣ፡፡ በዛው መጠን ማን እንደሆነ የማወቅ ጉጉታቸው አየለ፡፡ “እድገቴን የሚያደናቅፈው ይህ ሰው ማነው? እንኳንም ሞተ! አሁን ቶሎ አድጋለው” ብለው የሚያስቡ በርካቶች ነበሩ፡፡ አስተናባሪዎች፤ ሰራተኞች አንድ በአንድ ወደ የሬሳ ሳጥኑ እንዲጠጉ እና ወደ ውስጥ እንዲያዩ አደረጉ፡፡ ሳጥኑ ውስ ያለውን ነገር ሲመለከቱ ግን በሙሉ ድንገት ዝም አሉ። በሬሳ ሳጥኑ ውስጥ የጠበቁት ሬሳ አልነበረም።

በምትኩ የራሳቸውን ምስል መልሶ የሚያሳያቸው መስታዎት ነበር የተቀመጠው።
ከመስተዋቱ አጠገብ “በእድገትዎ ላይ ገደብ የማድረግ ችሎታ ያለው አንድ ሰው ብቻ ነው ፡፡ እርሱም ራስዎ ነዎት” የሚል መልእክትም በጉልህ ይታያል። ያኔ ሁሉም ሰው ወደ ልቡ ተመልሶ ስራውን በአግባቡ ይሰራል ጀመር...
***
በህይወታችን ውስጥ ለውጥ ሊያመጡ የምንችለው ራሳችን ብቻ ነን፡፡ በደስታ እና በስኬታችንም ላይ ተጽዕኖ ልናሳርፍ የምንችለው እኛው ነን። ለእኛ ከእኛ በቀር ረዳት ከየት ሊመጣል ይችላል።

አለቃችን ስለተቀየረ ፣ ጓደኞች ስለለወጥን፣ መስሪያ ቤት ስለቀየርን፣ ሕይወታችን ላይ ለውጥ አይመጣም። ራሳችንን በለወጥን ጊዜ ግን ሁሉም ለውጥ ያሳያል፡፡ ለራሳችን ላይ ምቀኛ አንሁን።


እናንብብ፣ እንወያይ ነጻ እንውጣ
#ንበብ_ለንባብ
ከረፈደ...........




የማይመጣን ሰው መጠበቅ ወና ቤት እንደማንኳኳት ነው....


ትናንት ሰማዩን ትክ ብዬ እያየውት የሆነ ነገር አስተዋልኩ...እንደሌላ ግዜው ጨረቃ አልነበረችም።...በተንጣለለው ሰማይ ላይ በርከት ያሉ ኮከቦችን ተመለከትኩ...ከታጀቡት ከዋክብት ውጪ በርቀት ተነጥላ የምትታይ አንድ ኮከብ ነበረች...የታጀቡት ከዋክብት ሊቀርቧት የፈሩ ይመስላሉ.....ወይም ደግሞ በመሀላቸው ያለው ሙቀት ብቸኛይቱን ኮከብ እንዲያዩ እድል አልሰጣቸው ይሆን...?


ራሴን በራሴ እየጠየኩ ለተወሰኑ ደቂቃዎች አይኔን ተክዬ ቀረሁ....ከደይቃዎች በኃላ ብቸኛይቱ ኮከብ ከአይኔ ተሰወረች...በአይኔ ፍለጋዬን ብቀጥልም ላገኛት አልቻልኩም።


ላትመለስ ጠልቃ ኖሮ ዳግመኛ ላያት አልተቻለኝም...ብቸኛይቱ ኮከብ ከጠለቀች በኃላ የታጀቡት ከዋክብት እሷ ወደነበረችበት ተበተኑ....የሚፈልጓት ይመስላሉ...ግን እርሷ የለችም...ላትመለስ ጠልቃለች....


ይሄ ሁነት እኛና አንቺን አስታወሰኝ...ያንቺስ ትናንት ማታ እንዴት ነበር...?ሶስት አመት ብዙ ነው አይደል....ወደኃላ ልውሰድሽና ከሶስት አመት በፊት ማታ ላይ...ሲመሻሽ...መኖር በቃሽ ሊልሽ ሲዳዳው ምን እየተሰማሽ ነበር...?
አመመሽ...?
ከፋሽ....?
አለቀስሽ....?
ከጎንሽ ስታጭን ታዘብሽን አይደል....
ሶስት አመት ብዙ ነው አይደል...እያየሽን ይሆን...አንቺን ትተን መሳቅ ጀመርን አይደል....አለመኖርሽን ለመድነው አይደል....ከፋንብሽ አይደል...ከረፈደ በኃላ አንቺን ፍለጋ ዋተትን አይደል....ምን ነበር ካንቺ ያራቀን...? ብቸኝነቱ ይሆን ያጠለቀሽ.......?


ወደፊት ብዙ ልደቶችን እናከብር ነበር...ሚዜዎችሽ እንሆን ነበር...የልጆችሽ አክስት እንሆን ነበር...እጅሽን አንለቅሽም ነበር...."ነበር" ብቻ...ቁጭት ብቻ...

የፅሁፌ ማድመቂያ እያረኩሽ አይደለም እህቴ...



ግን እያየሽኝ ከሆነ ሶስት ቃል ብቻ እንድልሽ ፍቀጅልኝ...



ይቅርታ🙏
ናፍቀሽኛል😭
እወድሻለሁ....💙

መምጣቷን ስጠብቅ ለተሰወረችው እህቴ😔


......ከተሟሟቅንበት ለአፍታ ወጥተን ወንድማችንን፣ ጓደኛችንን፣ጎረቤታችንን.......እንይ....ቁጭት የሚቀፍ ስሜት ነው....ደግሞም ካለፈ በኃላ እምቧ ከረዩ ማለት ለማንም አይበጅም....ብልህ ከሞኝ ይማራል...ሞኝ ግን እራሱ መማርያ እስኪሆን ድረስ ይጠብቃል.....





Https://www.tg-me.com/ethioleboled
በነገራችን ላይ.....



በነገራችን ላይ 'እኛ ኢትዮጵያውያን' ምናምን ብለን ከምንፎክረው ማንነታችን ጀርባ ትልቅ ደም መጣጭ አውሬ አለ....በስም ተከልሎ ያለ....እኮ እኛ ...ማንንም አትይ አንተን ነው ማወራው...


.....አዎ እኛ ኢትዮጵያውያን በሰይፍ አንገት አንቀላም....በምላሳችን ግን ስንገዘግዝ እንውላለን...አንደኛውን በተሳለ ሰይፍ አንገት መቁረጥ እኮ ገላግሌ ነው....እኛ እኮ ባልተሳለ ሰይፍ በዚህ በምላሳችን ስንከረክም እንከርማለን...ከአንገቱ በፊት ሰውነቱን እንቦጫጭራለን.....


በነገራችን ላይ እኛ ኢትዮጵያውያን እንለያለን....
እንለያለን...በምላሳችን በቁም አፈር እናለብሳለን...ቀን ሲከዳ እኛም ተደርበን እንከዳለን...



ከቤተሰብ አቅም ልጆች እናበላልጣለን...ቀን የጣለው ልጃችን ላይ ፊታችንን ባናዞር እንኳን ቅንድባችን እሺ ብሎ አይፈታልንም...አንዳንዶቻችን የሰው አፍ ፈርተን ነው ሁላ አንቅረን የማንተፋቸው... .ጊዜ ያስጎነበሰው አንሶ እኛ የእኔ የሚለን ሰዎች እጥፍ እናስጎነብሰዋለን....ሰው ከቤተሰቡ በላይ ማን ያውቀዋል...ገንዘብ ሲኖረው እኮ እናውቀዋለን እንዴት እንደነበር...ብሶት ሳያይልበት እኮ እናውቀዋለን እንዴት ተጫዋች እንደነበር...ሰላም ሲኖረው እኮ እናውቀዋለን ዲዳ ጠርቶ እንደሚያናግር.....ኩርምትምት ከማለቱ በፊት እናውቀዋለን....በሰበብ በአስባቡ የሚያነጫንጨው መሰበርን ከመሰበሩ በፊት በፊት...ከስብርባሪው በፊት ያለውን እርሱ እናውቀዋለን....


ቀን ሲስቅ የዋለ ቤተሰባችን ማታ ጎኑን ሊያሳርፍ የመጣበት ቤቱ ውስጥ ጠብ ጠብ ሲለው አንድ ነገር እንጠርጥር...እኛ ጋር ማስመሰል እንዳልቻለ እንወቅለት....እናም እናመስግን...ትክክለኛ ስሜቱን ስላሳየን...ከዛም እንቀፈው...ልክ እንደ ልጅነቱ...ከዛም


"...ምንድን ነው የሆንከው...?" እንበለው...የምር በጣም ቀላል እኮ ነው....

ብዙ ጊዜ ስላጋጠመኝ ነው..."ሰላም እኮ ነው የዋለው...ቤት ሲመጣ ነው ሴጣኑ ሚነሳው...ለውጭ አልጋ ለቤት ቀጋ...."....የሚሉ ወጊ ምላሶች....በእኛ ምላስ ቤተሰብነት ትርጉም ያጣል....ተራ ስም ብቻ ይሆናል....እና ከልብ የልብ ሰው እንሁን...ከሰዎች ንጭንጭ ጀርባ ያለውን መከፋት እና ያልተሰማ ብሶት እንመርምር....


ህይወት ከውስጥ ወደ ውጪ ነው ይባል የለ...ውስጣችን ሰላም ሲሆን እኮ ያለ ምክንያት ጥርሳችን ይፈግጋል...የማያስቅ ቀልድ ያስቀናል.....በቃ አለም ዘጠኝ ላትሞላ አስር እያልን መዝፈን ሁላ ያምረናል...የእኔማ ይለያል... የሆነ የአበባ ማሳ ውስጥ ኩቹ ኩቹ ሆታሄ እያልኩ በዝናብ ስጨፍር ከዛ ሻሩክ መጥቶ "ሸዊትዬ እኔኮ በጣም ነው የምወድሽ...ለምንድን ነው የምትኮሪብኝ...ቆይ ምን ያንሰኛል...ይኸው ባንቺ ምክንያት አረቄ ከጀመርኩ ድፍን አንድ አመት ሆነኝ."...ብሎ ሲለማመጠኝ ሁላ ይታየኛል😂(ይሄማ እብደት ነው እንዳትሉኝ ብቻ)....ደግሞ እኮ በአማርኛ ነው የሚያወራው...ከዛ ድንገት ኩዚ ከየት መጣ ሳይባል "አንዴ ላናግራት...ዞር በልልን...."...(ይሄም በአማርኛ ነው😂)...ሲለው ሻሩክ ተናዶ እዛው ሲደባደቡ በቃ ከራሴ ምናብ ጋር ስዝናና መሽቶ ይነጋል...ውስጣችን ሰላም ሲሆን ቀልድ አንፈጅም....እና ምን ለማለት ፈልጌ ነው የሰውን ስሜት ለመረዳት እንሞክር...ሰው እስከሆንን ድረስ ውድቀት አያስገርመን...


አንድ አባት ምን አሉ "ወልዶ ያልጨረሰ በልጅ እንደማይስቀው...እኛም ኖረን አልጨረስንምና መውደቅ አያስገርመን....ክፋት አይሙቀን...መልካም ነገርም ብርድ ብርድ አይበለን...ያ ሰው መከራውን ተስሎ አላመጣውምና በሰው ውድቀት ጮቤ አንርገጥ...የሰውን ድክመት ስንሰማ በጆሮአችን እየሰማን በልባችን እንፀልይ...ፈተናው ፈተናችን እንዳይሆን....."



ሰላም ዋሉልኝ😊




Shewit dorka






https://www.tg-me.com/ethioleboled
አይቤን ማን ወሰደው.pdf
16.2 MB
📚ርዕስ: አይቤን ማን ወሰደው (who moved my cheese?)
📝ድርሰት:- ዶክትር ስፔንሰር ጆንሰን
ትርጉም:- በላይ ደስታ
📜ይዘት:- one of the most successful business books ever
📆የመጀመሪያ ዕትም:- 2009
📖የገፅ ብዛት:- በአማረኛ 70ገፅ : በ English 67
📌አዘጋጅ:- kassa belay

ማጋራት አይዘንጋ!
@ETHIOLEBOLED
ቢሆንም (ባይሆንም)

እጣ ይሁን ወይ ስንፍና ባልሆንኩበት ተረፍቄ
የማላፍሰው ላብ አፍስሼ የማይወጣ እድል ፍቄ
..
አለሁ እላለሁ እንጂ የመኖር እፍኟን ቅንጣት
መሆንስ እንዲ አልነበረም አቅም ይበላል ማጣት
           
     (ለዚህ ነው)

አባቴ ድምፀ መረዋው
አንዴ እንኳን ሞዝቆ አያውቅም
ሆድ ይሉት ዜማ እያለበት
ከጁ ላይ መዶሻ አይለቅም፣
.
እንጀራ ይሉት ተፈጥሮ የግዱን ከህልም ያግዳል
ልትፈስ ካሰብከው ቦይ ለቆ በራሱ መንገድ ይነዳል

(ለዚህ ነው)

እናቴ በልጅነቷ ሀኪም መሆን ብትፈልግም
ታማሚ አረጋትና እጣዋ በህልሟ ሲለግም
.
     ከተማሪ ቤት አስቀራት
  ችግሯ   እውቀት አሳጣት
መሆንስ እንዲ አልነበረም
አቅም ይበላል ማጣት
  
   ስንት ሀኪም - ስንት ሺ አየር አብራሪ
         ኢንጂነር - እልፍ አእላፍ ተመራማሪ
.
ስንት ህልም  ስንት ድንቅ ሀሳብ
ሲመክን ገደል ሲገባ በኑሮ ሰንሰለት ሲሳብ
.
እያየው በየገመናው እያየን በየጎዳናው
*እንደዚህ* ብትሆን አትበሉኝ
እንዲህ ነው ሰው ይሉት ዳናው

ቢሆንም አለን እንደዚሁ
ባይሆንም (ኾነን እንደዛው)



አስቱ 👏



https://www.tg-me.com/ethioleboled
2024/09/22 11:42:10
Back to Top
HTML Embed Code: