Telegram Web Link
የኛ ሰፈር .....20



"ስንት ነው...?"...የማላውቀው ሰው ድምፅ ነው...የጠነበዘ ሰው ድምፅ...እጁ መቀመጫዬን ጨብጧል...እሱ ያለኝን ነገር እኔ የምጠቀመው እቃ ስገዛ ነው ...ስንት ነው...?የምለው ለሽንኩርት ወይም ለድንች መደብ ነው...ከዚህ ቀደም ወንድ ልጅ መቀመጫዬ አካባቢ እጁን ሲያርመሰምስ ትዝ አይለኝም...እስከማውቀው ድረስ ከንፈሬን ለቀላመደ ወንድ መልሴ ግልምጫ ነበር....


"አንቺን እኮ ነው የማናግረው ወይስ በነፃ ነው...?"....አሁንም ተለጉሜያለሁ....አይኔ በእንባ ጢም ብሏል...በውስጤ ብቻዬን አነበንባለሁ...ቆይ ምን ፈልጌ ወጣሁ...?...እንዲጣራልኝ የገላለጥኩት ገላ እንደፈለግኩትም ሲጣራ ምነው ሸከከኝ...?ልሸጥ ወጥቼ ዋጋ ማውጣት ከበደኝ...?....እንዲህ ከራሴ ጋር ስሟገት የጨበጠኝ እጅ ከበፊቱም ጠበቀ...


"ማማዬ ምነው...ዳቦሽ አይጣፍጥም እንዴ...?"...አጠገቤ ከቆሙት ሴተኛ አዳሪዎች አንዷ ናት ይሄን ባይዋ....

"ካካካካካካካካካ".....የተቀሩት በሳቅ አጀቧት....

አሁንም ትንፍሽ አላልኩም...በውስጤ ግን ብዙ ጩኧት ነበር...ካለሁበት ንቅንቅ አላልኩም...በልቤ ግን ከምድረ ገፅ እንኳን ብጠፋ ደስታውን አልችለውም ነበር....ዝምታዬን ስገፋበት የጨበጠኝ እጅ ከላዬ ተነሳ...ከዛም የዚህ ቀፋፊ እጅ ባለቤት ፊት ለፊቴ ተደነቀረ....ፊቴ ላይ እቃ እንደጣለ ነገር ፊቴ ላይ ያሉት ህዋሳቶቼን በየተራ አፈጠጠባቸው...መረመራቸው....


"አባቴ የእኔ አስተማማኝ ነው..."...የቅድሟ ሴት ናት...

"አስጠብቤዋለሁ ስልህ..."...ቀጠለች

"ካካካካካካካካካ...."...እኔና እነርሱ ፍፁም አንድ አይነት አለም ላይ ያለን አንመስልም...

"ታካብጃለሽ እንዴ ሸ*"...አለኝ የዛ እጅ ባለቤት...ማለቱ ብቻ አልበቃውም መሰል ፊቴ ላይ ተፍቶብኝ የቅድሟ ሴት ጋር ሄደ...የለጠፈብኝን ምራቅ ቅድም ባጠራቀምኩት እምባ አጥቤ ካንዱ ሸራ ስር ተሸጉጬ አደርኩ....


ብዙ ተሰምቶኝ...ብዙ ብዬም አውቃለሁ....ከዚህ ስሜት የሚስተካከል ስሜት ግን ከዚህ ቀደም አላስተናገድኩም....በቃ ዝም ያስባለኝ ያበደነኝ ስሜት ነበር...


*


"አዳር እንዴት ነበር"....አለችኝ ዊንታ ገና እግሬ የቤቷን ወለል እንደረገጠ...

"የመጀመሪያሽ ስለሆነ ሊከብድሽ ይችላል...ግን አይዞሽ ትለምጂዋለሽ...."

"ምኑን ነው የምለምደው...እ..ንገሪኝ እንዲህ ነው የማወጣው ማለትን ነው የምለምደው...እ...በያ ንገሪኝ ምን ይለጉምሻል...አልችልም...ትሰሚኛለሽ አልችልም...እንዲህ ነው የማወጣው ብዬ ማለትን መልመድ አልችልም...ትሰሚኛለሽ እኔ አንቺን አይደለውም...."

"እኔን መሆንም አትችይም...ብትፈልጊም...ብትሳዪም እኔን አትሆኚም"


"ኧረ አንቺን መሆን ያን ያሀል የሚከብድ ነው የሚመስልሽ..."

"ይከብድሻል...ፅኑ አንቺ ራስሽን አለማስቀደም አትችይም...አንቺ ከክብር ፍቅርን ማስቀደም አትችይም... አትችይም...ፅኑ ቃል ሌላው ቀርቶ   ሀዘን ያቆሰላት ማጣት ያደከማት ፍትህ የጠማትን የእናትሽን ነብስ አይቶ ከመቁሰል ውጪ ምንም ልታደርጊላት አልቻልሽም...እኔን መሆን ቀላል አይደለም ...."......


"መርከስ አይከብድም እሺ!!!"...ምን አስቤ ይሄን እንዳልኳት አላውቅም...መርከስ ከብዶኝ አፌን ሞልቼ ቀላል ነው ካልኳት በኃላ ሽምቅቅ አልኩ...የተናገርኩትን ብውጠው ብዬ ተመኘሁ...



"እኔን አትሆኚም...እኔ ክብረ ቢስ ነኝ አይደል ርካሽ...ሂጂ...ከክብረ ቢስ ቤት ምን ትሰሪያለሽ...ውጪ...የክብረ ቢሷ ልብስ ላይሽ ላይ ምን ይሰራል...አውልቂው እንጂ.....አይሆንሽም ይሄ ስራ..አንቺ ክብር አለሽ...ውጪልኝኝኝ!!!!".......አንዴ ስታንባርቅብኝ በሩ እስኪጠፋኝ ተደናበርኩ...

"ዊንታ...እንደዛ...እንደዛ ማለቴ እኮ አይደለም...ማለት...."....ተንተባተብኩ...

"ውጪልኝ ማለት አማርኛ ነው አይደል....ወደፈለግሽበት ሂጂ...ብቻ አይንሽን እንዳላይ..."

"በፈጠረሽ ዊንታ ይቅር በይኝ...በፈጠረሽ...ዊ..ን..ታ...በፈጠረሽ ከፍቶኝ እኮ ነው...ቢጨልምብኝ እኮ ነው....በፈጠረሽ".....እግሯ ስር ተደፍቼ መነፋረቄን ተያያዝኩት....


"በፈጠረሽ ለምን ትይኛለሽ...እ...እ...እሱን ተይው...እንደረሳኝ ልርሳው...የፈጠረኝን ተይው...እንደተወኝ ልተወው በቃ....እሱን ተይው ...ተይው"....ከተደፋሁበት አንስታ አቀፈችኝ....



**



"ትሰማኝ እንደሆነ ስማኝ...ብቻ አንተም እንደ ሌሎቹ ለበጎ ነው እንዳትለኝ...እኔ ምለው እንዲሁ ሾጥ ሲያረግህ ነው እንዴ የፈጠርከን...ወይስ አዲስ የፈጠርከውን አፈር ልትሞክርብን ነው ያድቦለቦልከን....ምንድን ነው ችግርህ....?እሺ የለህም....?ከሌለህ ቁርጤን አውቄ ልተውህ....እንዴት ነው አንጀትህ ሚችለው....እስከመቼ ነው ዝም የምትለው....አውጣን ወይ ውሰደን..."....የመጨረሻ ፀሎቴን ፀለይኩ።






እያለቀ ነው ወገን....





Shewit dorka

Https://www.tg-me.com/ethioleboled
የኛ ሰፈር......21




"ስድ...ባለጌ ያሳደገሽ...የኔ ሸራ ያንቺ መዳርያ ነው...."....የተወጠረው ሸራ ባለቤት ናት...ሁለተኛው አዳሬም እንደመጀመሪያው ነበር...ሊነጋጋ ሲል ነበር ከዚች ሴትዮ ሸራ ስር አረፍ ያልኩት...



ተናግራ አላባራ አለች...ከአፏ ስድብ ይዘንባል....እኔ ከብርድ ብዛት ያባበጠውን የተገላለጠ ገላዬን ታቅፌው ለማሞቅ እታገላለሁ...ብርዱ ላይ ድንጋጤ ተጨምሮ አደንዝዞኛል...ድምጿ የሞተን ለመቀስቀስ እንጂ እኔ ከስሯ ያለሁትን ለማናገር የሚወጣ አይመስልም...ቀና ብዬ አየኃት...አከሳሷ ከሰው ተራ አስወጥቶ ሳር አስመስሏታል..በእጇ እሷን በኪሎ የሚበልጣት ዘንቢል አንጠልጥላለች ...ውስጡ ፔርሙዝና ብርጭቆዎችን የያዘ...አንገቷ ላይ ከጠመጠመችው ስከርፕ ጋር ልትታነቅ ፈልጋ ገመዱ ተበጥሶ የጣላት እንስት መስላለች....




ሰውነቴን ማሟሟቅ ትቼ ተራራ የሚያክለው ጫማዬን ለማድረግ ስታገል ሰውነቴ በውሀ ሲረጥብ ታወቀኝ...የምን እጣቢ እንደሆነ እንጃ ግን ንፁህ ውሀ እንዳልነበር እርግጠኛ ነበርኩ...



"ሸ*...አሰዳቢ...ይብላኝ ለወለደሽ...."...ባሁኑ ባልታገስ የሚቀርብኝ ብታገስ ደግሞ የማገኘው ነገር አልታየኝም...አዎ ይቺን ክፍት አፍ ታግሼ ምንም አላገኝም...ያሁኑ ዝምታዬ ማንንም አያድንም...አዎ ማንም በዚህ ዝምታ አይጠቀምም...ጫማ ማድረጌን ገትቼ እንደ ሆነ ነገር ሰፈርኩባት...እሷም ስድቧን ገታ አድርጋ እሪታዋን አቀለጠችው.....እኔ ስሰደብ የተሰበሰቡ አፎችና እግሮች እርሷ ስትደበደብ ከመቅፅበት ተበለቀጡ...ቦታው በአንዴ በሰዎች ተወረረ።




እናንተ እኛ ኢትዮጵያውያን ግን እንዴት ያለን ነን...እንዴት አድርጎ የባረከን ነን...እንዴት ያለን መልካም ሰዎች ነን...እንዴት ያለን ፍፁማን ነን ....አንዳንዴ ብቻ ማለትም በአመት 310 ቀን የወደቀን ስናይ ምራቃችን ያመልጠናል እንጂ እንዴት ያለን መልካም ነን....ከስንት አንዴ ማለትም በአመት 312 ቀን የቆሸሸን ስናይ አርባ ክንድ እንርቀዋለን እንጂ ደግነታችን ወደር የለውም...የቆሸሸ ሁሉ ሌባ እና ቀማኛ ይመስለናል እንጂ እኮ መልካም ነበርን...አሁን አሁንማ እግር መንገድ ሚያበዛም እንደ እብድ ይታያል እንጂ አስተሳሰባችን ይለይ ነበር...



ምናል ቆሸሸ ብለን ተስፋ ባንቆሮጥበት...ምናል ክምር ቆሻሻ ላይ የራሳችንን ቅንጣት ቆሻሻ ባለመጣል ብንተባበረው...ምናል ሰው ብንሆን...ወይ ጉራውን ብንተው....እኛ ኢትዮጵያውያን እኮ ምናምን እያልን ባንፎትት....አሁን እኔ የስራዬ ስም ጠፋኝ...ምናል አፏን ብትሰበስብና የራሷን አንድ ቆሻሻ ከመወርወር ብትታቀብ...ምናል እኔን ከራሴ ጋር ብትተወኝ...ህሊናዬ የሚሰድበኝ መች አነሰኝ.....



ውስጤ ሲበላ ይታወቀኛል...ድር ሲያደራ....ተስፋዬ ሲመክን....


"በቃሽ"....ይለኛል..."እንደ ስምሽ አይደለሽም በቃ ከዚህ በላይ አትታገዪ".... ይለኛል....


ልሰማው ነው መሰል....



በማጠሩ ቅር እንዳትሰኙ ውድ አንባብያን...ከባዶ ይሻላል ብዬ ነው...ብዙ type ማደርግበት ሁኔታ ላይ ስላልሆንኩ ነው...ነገ እክሳለሁ🙏




Shewit dorka


Https://www.tg-me.com/ethioleboled
የኛ ሰፈር....22





"እስከ መቼ ነው እንደዚህ የምቀጥለው...."...ዊንታ ቤት ሄጄ የምተርከው የብልግና ታሪክ የለኝም...አሁንም ራስ ወዳድ ነሽ መባል አልፈለግኩም...መሄዴ ባይቀርም ከወይዘሮ አፀደ ጎጆ አቅንቼ ተስፋ መሰነቅ ፈለግኩ...እንደሚያውቁት ነገር የመከራውን ማብቂያ መጠየቅ ያዝኩ....

"በቃ እስኪል ነዋ....አመሻሹ ሊሰምር ነው ረፋዱ የከፋው አላልኩሽም...."

"መሸ እኮ...."

"መምሸቱን ፈጣሪ ብቻ ነው  ሚያውቀው...ጠንከር በይ...ደግሞ ምንድን ናት የለበሻት ቢጢሌ ጨርቅ...ምነው ምን ነካሽ...ልብሶችሽን ተሰርቀሽ ነው....?....ምንድን ነው ጉዱ...."

"አዎ ተሰርቄ...የቀረኝ ይሄ ብቻ ስለሆነ ነው...."....ከእሳቸው ቤት ጓዜን ጠቅልዬ ዊንታ ጋር ስለተጠቃለልኩ ውሸቴን እንደማያውቁብኝ
ርግጠኛ ነበርኩ....

"ውይ በሞትኩት..."....ብለው ከመቀመጫቸው ተነሱ...

"የት ሊሄዱ ነው....?"....ጠየቅኩ

"እዚ የሙሉ ልጅ ጋር...ልብሷ ቁምሳጥን አጣቧል ስትል ነበር እናቷ...."...



"ኧረ ይቅር አልፈልግም ....ከጓደኞቼ እበደራለሁ...."....

"ሂጂ ምን ትላለች እሷ....አሳልፊኝ እንጂ ...."....ድርቅናዬ ከእሳቸው ድርቅና እንደማይበልጥ ስረዳ መንገዱን ለቀቅኩላቸው...ትንሽ ቆይተው በኩርቱ ፌስታል ሙሉ ልብስ ይዘውልኝ መጡ....


****



"ተስፋ ልቆርጥ ነው...."

"እናትሽን ረስተሻት ነው...?ተስፋ መቁረጥን ምን አመጣው ልጄ...."

"ምን እንዳመጣውማ ያውቃሉ...እኔ አሁን ተስፋ ባልቆርጥ እኮ ነው መገረም ያለቦት...ለእናቴ ብዬ ነው እስካሁንም.... ለእርሷም አልሆንኩም...ሰው ኑሯት እንደሌላት ከምትኖር አንደኛዋን የላትም ቢባል ይሻላል...."

"ምን እያሰብሽ ነው ልጄ..."

"አይኔን ይዤ ልጠፋ...."

"በስመአብ ወወልድ ምን አይነቱ የሰይጣን ሀሳብ ነው...ተይ ልጄ እንደዚህ አይደለም...5 አመት ነገ ናት እኮ...ጊዜው እኮ በራሪ ነው ምነው ባትቸኩዪ....."

"አልቸኮልኩም....እንዲያውም ዘገየሁ...."

አስተያየታቸው ላይ ፍርሀት አለ....ትክ ብለው ያዩኝና መልሰው ያቀረቅራሉ....እንዲህም አይነት ኢትዮጵያዊ አለ...የእናት ሆድ ዥንጉርጉር አይደል...እሳቸውንም ባለሸራዋም የዚች የኢትዮጵያ ፍሬዎች ናቸው....?


"እስቲ ዛሬ እዚ እደሪ...እኔም አጫዋች አገኛለሁ...ሳሮኔ አክስቷ ጋር ሄዳለች..."....የልጅ ልጃቸውን አለመኖር ሰበብ አድርገው ሊያሳድሩኝ መሆኑ ነው...እየጠበቁኝ ነው በእሳቸው ቤት...ፍርሀታቸው በጉልህ ፊታቸው ላይ ተፅፏል...እርጅና አጣጥፎ በረድፍ የደረደረው ቀይ የፊታቸው ቆዳ በርበሬ መስሏል...


እንደማላድር እንቅጩን ነግሬያቸው ቀትር ላይ ወደ ዊንታ ቤት ሄድኩኝ.....



"ዛሬ ጎብዘሻል...."....አለቺኝ ቆይቼ መምጣቴን overtime work አርጋው።


"አይደል....."

"በርትተሻል...ስንት ሰራሽ...."...

"ዊንታ ከትናንትናው የተቀየረው ነገር ፊቴ ላይ የተፋብኝ ወንድ አለመኖሩ ነው...ምንም አልሰራሁም...."

"አንድ ቅባት አለ...አስመጪና ላኪ ነው...ከውጪ ሲመጣ አስተዋውቅሻለሁ....ደንበኛዬ ነው....አናግረውና ለእናትሽ የሚሆን ግማሽ ያሀል ሊሰጥሽ ይችላል ....ለአንድ አዳር አይደለም 250 ሺ ሚከፍልሽ...እርሱ እስከፈለገው ጊዜ...በቃ እስከሚልሽ...የሚመጡትን ወራት ከእርሱ ጋር ነሽ...ትንሽ ጊዜ ብቻ ታገሺ ."...በዚህ ጉዳይ መልስ መስጠት አልፈለግኩም...


"እናቴ ጋር መሄድ እፈልጋለሁ...."

"ሂጂአ ምነው..."....አለችኝ የሆነ ነገር የፈለገ ሰው አስተያየት ሳያት...

"ዛሬ ማታ ካልሰራሁ ትንሽ ብር ታበድሪኛለሽ...ነገ ጠዋት ምግብ ይዤ መሄድ አለብኝ...."

"ኧረ ችግር የለውም...ግን እስከአሁን የት ነበርሽ ቆየሽ በጣም...ደግሞ ምንድን ነው በፌስታል የያዝሽው.."....


"የድሮ ሰፈሬ ሄጄ ነው የቀረኝ ልብስ ነበር...."












Shewit dorka

Https://www.tg-me.com/ethioleboled
ለሬሳ ስንቅ ምኑ ነው....







"ምን አድርጊ ነው የምትዪኝ...መልሼ አልውጥሽ ነገር...ባክሽ ተይኝ...."

"አልተውሽም...አልተውሽም...አንቺን እና ያ አባት ተብዬውን ካልወቀስኩ ማንን ልውቀስ...የእናንተ ጥፋት ነው...መውለድ ስለቻላችሁ ብቻ መውለድ አልነበረባችሁም...ትልቅ ጥፋት..."


"ልጄ ርቦሽ ያውቃል...አንድ ቀን እንኳን ተጠምተሽ ታውቂያለሽ..."


"አዎ ያውቃል...እማ ርቦኝ ያውቃል...እናንተ እያላችሁ ሰው ርቦኝ ያውቃል...በአይዞሽ ባይ ጥም ተቃጥዬ አውቃለሁ....እናንተ ሰውነቴን ከማፋፋት ውጪ ምንም አታውቁም....ሲጀመር መች በቅጡ ታውቁኝና...እኔ ለእናንተ እንደተክል ነኝ...ከውሀ ውጪ ምንም የማትሰጡኝ...ሆዴን ከመሙላት ውጪ ምንም የማታውቁ..."


ማድያት የወረረው ፊቷ በቅፅበት ከሰል መሰለ...ከስራ ብዛት ሽቦ በሆነው እጇ እጄን ጨበጠች...ለመጀመሪያ ጊዜ...ከከረደደው እጇ በላይ እናትነቷ ለሰለሰኝ...አፍ አውጥቶ አለሁልሽ አለኝ...ምናል ላለፉት 28 አመታት ላንዴ እንኳን አድርጋው በነበር አልኩ...በእጇ ብቻ እንደዚህ የሆንኩ ብታቅፈኝማ  የ 28 አመት ሀጥያቴ ይታጠብ ነበር አልኩ ደግሜ...


"ተይ ልጄ..ተይ...ባክሽ ተይ...በምን አቅማችን እንይሽ...በየትኛው ልባችን ያንቺን የልብ ቁስል እናስታም...የኑሮ ከፈን ከጋረደን ሰነባበተ...ከፈኑ ለአመል እንኳን ዞር አልል አለ...ባለችው ትንሽ ሽንቁር ማየት የቻልነው አለመሞትሽን ብቻ ነው...."

"በምን አቅማችን እንይሽ ነው ያልሽው...?...ቆይ በምን አቅማችሁ ወለዳችሁኝ...ከፈኑ እኔን ስትወልዱ ገሸሽ አለ...?...ቢገባችሁ ያዳናችሁኝ ከትንሹ ሞት ነው...እኔ ትልቁን ሞት ሞቻለሁ...የጠበደለ ሰውነት ላይ ከከተመች የከሰመች ልብ በላይ ከስታ በጠወለገች ሰውነት ላይ ያለች ጠንካራ ልብ  መለኪያ የላትም...ልቤን ገላችሁ ገላዬን ማፋፋታችሁ ምን ጠቀመኝ...."


"ልጄ ባክሽ አትውቀሽን...ተይ ልጄ..."....ፊቷ ተንዘፈዘፈ...እምባዋም ጅረት ሆነ...ያፋፋችው ሰውነቴ ሊያቅፋት ዳዳው...እጄ ሊሰበስባት ትከሻዬም ሊያሳርፋት ዳር ዳር አለ....የገደለችው ልቤ ግን አሻፈረኝ አለ....


"በደንብ አልቅሺ...እርምሽን አውጪ...ልጅሽ ሞታለች...."........እነዚህ ቃላቶች ከአፌ ተወረወሩ....


ሲላፉ ፈጥረውኝ አንቺን ማየት ተሳነን ትለኛለች...ህይወት ትግል እንደሆነ እያወቁ አምጥተውኝ ብቻዬን እንድታገል ተዉኝ....በጦር ሜዳ ላይ ያለ ጦርና ጋሻ ትተውኝ ሄደው ስንቅ አቀበሉኝ....ቆይ ግን ለሬሳ ስንቅ ምኑ ነው......?





Shewit dorka




https://www.tg-me.com/ethioleboled
የኛ ሰፈር......የመጨረሻው ክፍል




ዛሬ እንደ ሰሞኑ አልሆንኩም....አንፃራዊ  መቀላጠፍ ይታይብኛል....ገላ ሸመታ ጎራ ላሉት ወንዶች በሙላ ጥርሴን እያሰጣሁ ነው......

እግረኞቹ እየዘለሉኝ ሲያልፉ አንድ V8 እኔ ከቆምኩበት ቆመ...ሸማች እንደሆነ በአይኑ ምልክት ሰጠኝ...እኔም ከመኪናው መስኮት ተጠጋሁለት....

"ስንት ነው...."....አለኝ ገና እንደተጠጋሁት...ስንት እንደምለው ግራ እየተጋባሁ "10,000 "....አልኩት...

"አይቀንስም...."...ይሄን ያለኝ የስላቅ ሳቁን አስቀድሞ ነው...

"እሺ 8000..."

"ምንድን ነው ይሄን ያሀል...ዳይመንድ ነው እንዴ ይዘሽ ምትዞሪው....3000 ይመችሻል"...አለኝ ባለመኪናው...

"አይ አይ ትንሽ ጨምር..."

"ትንሽ ስንት ነው....?"

"2000....."

"እሺ ጊቢ.....".....

የባለመኪናው እጅ ላይ ቀለበት አለ...እጁ ላይ እንዳፈጠጥኩ ካንዱ ጥግ መኪናውን አቆመው.....

"ስምሽ ማነው...."...

"ፅኑቃል..."

"ቆንጆ ነሽ...."

"አመሰግናለሁ..."....በአይኑ ሰውነቴን እየገረመመ ነው ሚያወራው....አስተያየቱ ላይ ሽፍደት አለ...ከገረመመኝ በኃላ እጁን ተነክቼ ከማላውቅበት ሰደደ...ወዲያው እጁን ከሰካበት ነቀልኩት....እስከ እግር ጥፍሬ ድረስ ነዘረኝ... በላብ ተጠመቅኩ....እርሱ ያማታል እንዴ አስተያየት ያየኛል....

"የመጀመሪያሽ ነው...?"....ጠየቀኝ...

"አዎ...."....ምንም ሳይለኝ መኪናውን መንዳት ጀመረ....በአንድ እጁ እየነዳ በአንድ እጁ በስልኩ ይፃፃፋል....


"ወዴት ነው ምንሄደው...."....አኳሀኑ አላማረኝም...ፍጥነቱ ከልክ አለፈ....

**"የትስ ብንሄድ....".....ከዚህ እብሪት ካጥለቀለቀው መልሱ በኃላ መልስ ልሰጠው ፈራሁት...*,

ስልኩ ጠራ...

"መጣሁ መጣሁ እዚያው ናችሁ..."....ይሄን እንደሰማሁ አእምሮዬ 'ከመኪናው መውረድ አለብሽ ደስ የማይል ነገር አለ'....ብሎ ደውሉን ደወለ.....

"አውርደኝ....ሰማህ አልፈልግም አውርደኝ...."

"ካካካካካካ ሌላስ ....አንቺ ብቻ እዘዢ የት አባቱ...ሌላስ እመቤቲቱ ምን ልታዘዝ..."....መኪናውን እያበረረው ነው...ሰአቱን ለመገመት ያዳግታል...ግን ሰው
አልፎ አልፎ ነው የሚታየው....የምንሄድበትን ለማወቅ ብዙም አልተቸገርኩም....ዊንጌት አካባቢ እንዳለሁ ሳውቅ ፍርሀቴ ጨመረ...ጨለማው፣ጭርታው ....አንዳች የማላውቀው ስሜት ውስጥ ከተተኝ....


"አውርደኝ በፈጠረህ...እናት የለህም...እህት የለህም....በእናትህ....".....ይሄን ብዬ ወደ በሩ እጄን ላኩት...እጁ ከእጄ ቀድሞ  በሩ ላይ ደረሰ...መጮህ ጀመርኩ....የት አንዳለሁ መለየት የማልችልበት ጨለማ ጋር ደረስን...ሰው ዝር ከማይልበት.....ያኔ መኪናውን አቆመው....የማደርገው ግራ ሲገባኝ ከበሩ ጋር ትግል ገባሁ......

"ደርሰናል....".......ከዚህ የስልክ ንግግሩ ትንሽ እንዳረፈ ፊታቸውን ለማየት የሚያዳግቱ ሰዎች ከመኪናው ትይዩ ሲመጡ ተመለከትኩ....ጩኸቴ ከቅድሙም ባሰ....እሪ በከንቱ የሆነ ጩኸት....ሰሚ የሌለበት ጩኸት....መኪናውን ተከፈተልኝ....ከመውረድ ተቆጥቤ ባለመኪናውን መለማመጤን ፀናሁበት....


" ምን ልታደርጉኝ ነው...በፈጠረህ እንድሄድ ፍቀድልኝ....እባክህ ስቃይ ይብቃኝ....ብዙ ፈተና ያ....".....ልለው ያሰብኩትን ሳልጨርሰው ከውጭ የሆነ እጅ ወደራሱ ሳበኝ....ከአምስት የማያንሱ ወንዶች እንደ ጅብራ ተገትረዋል....ባለመኪናውም ተቀላቀላቸው....አንዴ እሪታዬን ሳቀልጠው ሰፌድ የሚያስንቅ እጅ ከአፌ ጋር ተላተመ....ከነሱ ሁለቱ ተሸክመው ጫካ ውስጥ አስገቡኝ.....ሌሎቹም ተከተሏቸው....የሆነ ሽታውን የማላውቀውን ነገር ይቀባበላሉ....ከእነርሱ በአፍንጫ የሚወሰድ እፅ የሚወስድም አለ....መብራት የሚባል ነገር የለም....በጨረቃ ብርሀን ታግዤ በአይኔ ሁኔታቸውን እቃኛለሁ....

ሰፌድ እጁ ቀበቶውን መፍታት ሲጀምር ባለመኪናው አስቆመው....

"ምን ልትሆን ነው....አይደብርህም እንዴ...ማን ባመጣ ማን ይቀድማል....ብዙ ሼር የኔ ነው ዞር በል...."....ብሎ ገፈተረው....ጩኸቴን ከመጮህ እና በመሀል በመሀል እነርሱን ከመለመን አልቦዘንኩም.....



አይኔ እያየ ተፈራረቁብኝ...ጩኸቴ እየቀነሰ መጣ...አቅሜም እየከዳኝ....

የሚፈልጉትን አድርገው እንደጨረሱ ጥለውኝ ሄዱ....በሰለለ ድምፅ መጮሄን ቀጠልኩ....ደሜ እንደ ውሀ አጥለቅልቆኛል....ትንፋሼ 'ልከዳሽ ነው በይ በርቺ' ይለኛል...."እ....ማ.......".....ጠራኃት....ድምፄ እየጠፋ ነው.....ጭር ካለው ጫካ ውስጥ የምትሰማ ጭላንጭል ድምፄ ሰው ሳይሆን ሚበላው የጠረረበት ጅብ ነበር የጠራብኝ....ልቤም እንደ ድምፄ ሰለለ....ልክ እንደ ወንዶቹ ጅቦቹም በቋንቋቸው መጠራራት ጀመሩ....



ባለ በሌለ ሀይል መንተፋተፍ ያዝኩ....ጉሮሮዬ በቻለው ልክ ጮህኩ...አልሆነልኝም....ስንፏቀቅ ደሜን እየተከተሉ ይመጣሉ....እጄን እግሬን መነካካት ሲጀምሩ ከየት እንዳመጣሁት በማላውቀው ጩኸት ጮህኩ....ጩኸቴ ጠብ አልልሽ አለኝ....ከነ ነብሴ ይሞካክሩኝ ጀመር....

በዚህ ሁሉ መሀል የመጨረሻ የመሰለኝን ፀሎት ፀለይኩ....

"አድነኝ....እባክህን እየኝ...."...... ድንገት ጭላንጭል ብርሀን ጫካውን ሰንጥቆ ተጠጋኝ...


**

አንዳንድ ስሜቶች አሉ ለብእር የሚከብዱ....አሁን ዊልቸሬ ላይ ተቀምጬ የዛን ምሽት ስሜት በብእር ማስቀመጥ ስሜቴን ማሳነስ ነው...እኔ ደራሲ አይደለሁም...አልችልም....ያን ስሜት መግለፅ አልችልም.....

ለዛን ምሽት ስሜት እስከ አሁን ቃላት አልተፈጠረም...አሁን ሽባ ሆኛለሁ....ግን ሽባ ያደረጉኝ ጅቦቹ ብቻ አይደሉም...ሰውም ጭምር  ነው እንጂ ....


ፅኑ ቃል ነኝ.... አሁን አትድረስብኝ ካልኩት ከፈጣሪ ደጅ በልመና እተዳደራለሁ....እናቴ ከእስር ልትፈታ 6 ወር ቀርቷቷል...በወ/ሮ አፀደ በኩል ስንቅ እሰዳለሁ...ጅቦቹ ባስተረፉልኝ ግራ እጅ እና አንድ አይን እፅፋለሁ....ሲጨልምብኝ ፅፌ ይወጣልኛል...እናቴን ጥዬ መሄድ አቅቶኝ የግዴን እኖራለሁ....


"ይሄ ሁሉ በእኛ ላይ ለምን ..."...ብዬ ስጠይቅ መልስ አግኝቼ አላውቅም....እንደው ምን አልባት እናንተ ከተማራችሁበት ብዬ አሰፈርኩት....አሁን  እኔ ሰው የማጣት...ፍቅር የማጣት...ባስ ብሎም ሀገር የማጣት ውጤት ነኝ....


ዊልቸሬ ላይ ተቀምጬ ስጡኝ የምለው ገንዘብ ብቻ አይደለም....ሀገሬንም ጭምር እንጂ...


ሀገሬን ስጡኛ።




ተፈፀመ።










Shewit dorka
ውድ አንባብያን...ሸዊት ነኝ..."..የኛ ሰፈር.." የመጀመሪያ ረዘም ያለ ድርሰቴ ነው...ራሴን ደራሲ ብዬ መጥራቴ ድፍረት ካልሆነብኝ....እንደ መጀመሪያ ስራዬ የሚጎሉት አንዳንድ ሙያዊ ነገሮች ሊኖሩት ይችላሉ...በ inbox እና በዚ የምትሰጡኝ ገንቢ አስተያየቶች ወደፊት ከዚህ በላይ የተዋጣለት ስራ እንድሰራ ያግዘኛል።በጣም አመሰግናለሁ...የኛ ሰፈር የመጀመሪያ ልጄ እንደመሆኑ እሱ ላይ ያያችሁበትን ድክመት ቆንጥጬ አልያም በርበሬ አጥኜ ቀሪዎቹ ልጆቼ ላይ እንዳይደገም እሰራለሁ...ከአስተያየታችሁ እንደተረዳውት ጠንካራ ጎኑ ያይላል....ያላየሁትን ላሳያችሁኝ...ላበረታታችሁኝ...ላነበባችሁልኝ ሁላ ምስጋናዬ ከልብ ነው።


ማስተላለፍ ስለፈለግኩት ነገር ደግሞ ትንሽ ልበላችሁ....


በእኔ ምናብ ውስጥ ፅኑ ቃል አንድ  ሰው አይደለችም....ፅኑ ቃል ኢትዮጵያ ናት....ኢትዮጵያ ...ፅኑ ቃል ፈተናዋ ከእለት እለት እያየለ...አንዱን ስትለው አንዱ እኔም አለሁ እያለ የመከራዋን ጊዜ እንዳስረዘመው ሁላ ኢትዮጵያም በዘር የተነሳው ፀብ ጋብ አለ ስንል የሀይማኖቱ ይከተላል....እሱ ደግሞ በረድ ሲል የኑሮ ውድነቱ አላስኖር ይላል...


አንዳንድ ታሪኮች አስተማሪ እንዲሆኑ የግድ happy ending መኖር የለበትም...የፅኑ ቃል መጨረሻ ያስደነገጣችሁን ያህል የኢትዮጵያ መጨረሻ ሊያሳስባችሁ ይገባል....

ኢትዮጵያ ላይ ማሟረት አይደለም...ግን ደግሞ እያየን እንዳላየን ማለፉ እና የእኛን በር እስኪያንኳኳ መጠበቁ መፍትሄ አንደለም...ሁላችንም ሀላፊነት አለብን...ሀገር ማለት ሰው ነው አይደል...በቀላሉ እንጀምር...የጎረቤታችንን እንባ እናብስ...ሁላችንም እንደ ወይዘሮ አፀደ ብንሆን...ሁላችንም እንደ ሄኖክ ብንሆን (የሄኖክ መኖር እንዲህም አይነት ሰው አለ የሚለውን ለማሳየት ታስቦ ነው ሲቀጥል ደግሞ በህይወት አጋጣሚ ላይ እንደዚህ አይነት መራራቅ ይፈጠራል...ማለትም ሄኒን ረስቼው አይደለም😁)

ሁላችንም የራሳችንን አሰተዋፅኦ ብናረግ ሀገራችን ሽባ አትሆንም....የሀገራችንን እጅ እና እግር ቀርጥፈን የበላነው እኛ ነን...እባካችሁ ወደ ኢትዮጵያዊነታችን እንመለስ....ሁሉም ጥሩ ይሆናል🙏



ሸዊት ነበርኩ....በቅርቡ በሌላ ድርሰት እመለሳለሁ...አደራ እንዳትረሱኝ😊



ደህና እደሩልኝ።


Https://www.tg-me.com/ethioleboled
የሀብት_መንገድ_በሮበርት_ኪዮላኪ_@shuktus_books.pdf
15.5 MB
የሀብት መንገድ(rich dad poor dad) በሮበርት ኪዮላኪ

📌ማጋራት አይዘንጋ!
@ETHIOLEBOLED
@ETHIOLEBOLED
4 any comment @meki3
ለፈገግታ😁



መቼስ እናንተ በእኔ ህይወት መሳቅ አይሰለቻችሁም😁



ትናንት አመሻሽ ላይ lifeboy ሳሙና ከአብዲ ሱቅ በ50 ብር መግዛት....ወይኔ lifeboy ነው የምትጠቀሚው ምናምን የምትሉ አንባብያን ካላችሁ lifeboym ተወዶብኝ ላማርር እንደመጣሁ ስነግራችሁ በታላቅ ደስታ ነው😁....ደግሞ አብዲ አብዲ ሳበዛ promotion እንዳይመስላችሁ....ጊቢ ስሆን የሚያስፈልጉኝ ነገራቶች ተገዝተው ስለሚላኩልኝ እምብዛም ሱቅ አልጠቀምም....


እያንገበገበኝ ገዛሁ....ካርድ,ሳሙና,ችብስ ልገዛባት ያሰብኳትን 50 ብር አንድ ሳሙና ገዝቼባት ተመለስኩ....


እስከ አሁን እኮ ደህና ነበርኩ....ሳሙናዬን ለሁለት ከፍዬ አንዱን መጠቀም ያዝኩ....በነጋታው ሁለቱም ቁራጮች ከቦታቸው የሉም...አሁን ነው ትንሽ ብቻዬን እንደመለፍለፍ ምናምን ያረገኝ....ቤቱን በአንድ እግሩ አቆሞኩት...ሳሙናዬን ውለዱ ደም መፋሰስ ሳይከተል ምናምን😂 ....


"ኧረ ተረጋጊ"...ቢሉኝም ወይ ፍንክች....ደግሞ እኮ አንዱ ልጣጩ አለ ስለዚህ ሆን ተብሎ እኔ ላይ ያጠነጠነ ሴራ ነው....እንደውም ብሄርን መሰረት ያደረገ....😂(እብደቱ ሲጀማምር እንዲህ ነው...በቃ የማይገናኝ ነገር ማገናኘት....እንደ ዘመኑ ፖለቲከኞች መሆን)

"ሸ ተረጋጊ በቃ አይጦቹ ወስደውት ነው ሚሆነው..."...ቢሉኝስ😳....

"የዚህ ቤት አይጦች ደግሞ አይደብራቸውም እንዴ...አርፈው ሰፌድ ምናምን አይበሉም...ሲያስጠሉ "...

"ኧረ ሰፌድ ይብሉ ...ሆሆሆሆ ሰፌዴን አደራ አቡነ አረጋዊ...ደግሞ ሲያስጠሉ ምናምን አይባልም...ይብሳሉ..."....እናቴ እኮ ናት😂

"ቆይ የልብስ ሳሙና ለምን አልተበላም...የእኔን ብቻ...አያችሁ እኔ ላይ ያነጣጠረ......"

"ባልሽ ስለሆነ ይሆናላ...የሚስቱን ሳሙና ቢወስድ ምንድን ነው ክፋቱ...(አይጥ እኛ ቤት የሸዊት ባል ነው ሚባለው ሁሌ😡)..."...ሁሉም አሽካኩ...


"ምን አገባኝ እኔ ሀገር ያወቀኝ ተማሪ ነኝ...ከየትም አላመጣም...ብር ስጪኝ ልግዛ..."

"ለምን ሳትታጠቢ ሰባት አመት አትቀሪም ምን አገባኝ...እንዴ አንቺ በተዝረከረክሺው እኔ ምን ቤት ነኝ..."

"ከቤቴ ውጪ የት ማስቀመጥ ነበረብኝ እንዴ"

"እዚ ሳጥንሽ ውስጥ ቁልፍ አታረጊበትም ነበር...(ሳጥኑ እኮ doucment ማስቀመጫ ነው)"

"እሺ ቆልፍበታለሁ አሁን ስጡኝ...."

"ታጥቦ ይመልስልሽ ይሆናል ትንሽ ጠብቂው..."

"ካካካካካ...."

"ባልሽ አይደል ግዛልኝ በይው...."

"ቀልድ መሆኑ ነው...ሁላችሁም አስመሳዮች ናችሁ...ከጎናችሁ ታገኙታላችሁ.....😒"



እሺ እኔ አሁን ባብድ ይፈረድብኛል😔




እኔው ነኝ





https://www.tg-me.com/ethioleboled
#መጥፎ_ልማዶችህን_አሸንፍ

🌐🌐ህይወትህ ከተማርከው ይልቅ የልምዶችህ ነጸብራቅ ነው። የሸዋዚንገርን ፊልም የሚያይ 'እንደ' ሸዋዚንገር ያለ ሰውነት እንዲኖረኝ እፈልጋለሁ'' ቢል አይገርምም። ልምዱ ሸዋዚንገርን ፊልሞች ማየት ስለሆነ።

🙂ይህ የሚያሳየው ልምዶች ባህሪያችንን እንደሚቆጣጠሩትና ፍላጎታችንን እንደሚወስኑልን ነው።

🚩ስለዚህ መጥፎ ልምዶች ካሉህ እነሱን ማሸነፍ እና በጥሩ ልምዶች መተካት ያስፈልግሃል።

☑️ ለዚህም ያሉህን ልምዶች በትክክል ማወቅ እና ጥቅም እና ጉዳታቸውን መገንዘብ ያሻል!

በ2016 መጥፎ ልማዶችን አስወግዶ አዳዲስ ልማዶችን ለመገንባት ደግሞ #የልማድ_ኃይል መጽሐፍ ይጠቅምሀል፡፡

#የልማድ_ኃይል_ATOMIC_HABITS መጽሐፍ

Https://www.tg-me.com/ethioleboled
አንድ ቀን አንድ ሽማግሌ ከልጁ ጋር በጫካ ውስጥ እየተንሸራሸሩ ሳሉ በድንገት አንድ ትንሽ ድመት በአንድ ጉድጓድ ውስጥ ወድቆ ያያሉ። ድመቱ ከጉድጓዱ ለመውጣት እየተፍጨረጭረ ነበር። እና ሽማግሌው ድመቱ ከጉድጓዱ እንዲወጣ እጁን ሰጠው። ድመቱ ግን በፍርሃት እጁን ቧጨረ።✅️

🧡☑️ሰውየውም በቡጭሪያው ህመም እየጮኸ እጁን ሰበሰበ ግን አላቆመም። ለድመቱ በድጋሚ እጁን ደጋግሞ ለመስጠት ሞከረ። አብሮት የነበረው ልጅ ትዕይንቱን እየተመለከተ በመገረም ጮኸ "በፈጣሪ ይሁንብህ አባዬ ይህንን ድመት መርዳት አቁም፤ ድመቱ እራሱን በራሱ ጊዜ ከዚያ ያወጣል" አለ። ልጅየው ስለድመቱ ደንታ አልነበረውም።

✍️ሽማግሌው ግን ድመቱን ማዳን ቀጠለ፤ "ልጄ፤ እሱ እንዲቧጨር እና እንዲጎዳኝ የሚያደርገው የድመት ባሕርዩ ነው፤ እኔ ደግሞ መውደድ እና መንከባከብ ሰብአዊ ግዴታዬ ነው"
ብሎ በድጋሚ እጁን ለእርዳታ ዘረጋለት ድመቱ ባጨረው። እንዲህ እያሉ ከአድካሚ ሙከራዎች በኋላ በመጨረሻ ከጉድጓዱ አወጣው። እና ድመቱን ወደቤቱ ወስዶ የራሱ አደረገው።🙂
***
✅️ሞራል- በዙሪያዎ ያሉትን ሁሉ በራሳችሁ መልካም አመል አስተናግዱ እንጂ የሰዉን መጥፎ ባህርይ አትከተሉ። ያኔ ልታዩት የምትፈልጉት መልካምነት ሁሉ በዙሪያችሁ ይሆናል።
***

☺️እናንብብ፣ እንወያይ ፣ነጻ እንውጣ
ንበብ ለንባብ

Https://www.tg-me.com/ethioleboled
#ስሜትህን_ቀይር!

አንድ ማወቅ ያለብህ ነገር ስሜትህን መቀየር እንደምትችል ነው።

ነገር ግን እንዴት የገባህበትን ከባድ ስሜት ወደተሻለ ስሜት መቀየር ትችላለህ? ከባድ ጥያቄ ይመስላል።

በትክክል ቀላል አይደለም። ልምምድ ያስፈልገዋል።

ህምምም... እንበልና የሆነ ሰው አበሳጨህ፣ ዝቅ አድርጎሃል! ጉዳት ተሰምቶሃል እና? በመጀመሪያ ስሜቱን አትካደው ነገር ግን ለምን እንደዛ ሊሰማህ እንደቻለ ራስህን ጠይቅ... ምናልባት ያ ሰው እንደዛ እንዲሰማህ አልፈለገም... ምናልባት ያ የራስህ የአረዳድ ችግር ይሆናል... ምናልባት ያለብህ የበታችነት ስሜት... ምናልባትም ለዛ ሰው ያለህ ድብቅ ጥላቻ... ወይም በትክክል ያበሳጨህ ሰው ሆን ብሎም ሊሆን ይችላል።
የፈለገ ይሁን የሚረብሽ ስሜት ለምን ውስጥህ ቀረ? ይሄን ጥያቄ ምትመልሰው አንተ ሁነህ ሳለ እኔም የምጠቁምህ ነገር ይኖራል።

እዚህ ጋር- ህይወት ሁሌም ደስታ፣ መፈለግ፣ ማግኘት፣ እኩል መሆን፣ ስኬት እንዳልሆነች ተገንዘብ። ብስጭት ወይም የስሜት መረበሽ ሲያጋጥምህ ዝም ያለ ቦታ ሂድ፤ ከራስህ ጋር በፍቅር ተነጋገር። የመጥፎ ገጠመኞችን ጥሩ ጎን ለማየት ራስህን በአዎንታዊነት እንዲመራ አስገድድ።

የበደለህን ይቅር በለው ጤና ይሰጥሃል። የተበላሸብህ ነገር ደግመህ ሞክረው- ጥንካሬን ስለምታገኝ። ደስተኛ ለመሆን ቻል መከፋት ሲረዝም በብዙ ስለሚያሳጣ። ፈጣሪህን አመስግን- የተሻለ ስለምታገኝ። ካንተ የባሰበትን ተመልከት መጽጽናናት ስለሚሆንልህ። ካንተ የተሻለውን አስተውል- ተስፋ ስለሚጎበኝህ። ስለገጠመኝህ ሰዎችን አማክር- መፍትሄ ስለሚሰጡህ። ጸልይ፣ ለብቻህ ተደብቀህ አልቅስ- ለእፎይታህ።

☑️ ከዚህ ሁሉ በኋላ ሁሉም ጥሩ ይሆናል። እመን ብቻ። ሁለቱን መጽሐፍት ደግሞ አንብባቸው፡-

#የሕይወት_መመሪያ 9ነኛ ዕትም
#የሕይወት_ኬሚስትሪ 2ተኛ ዕትም
#ሕይወትህን_የሚለውጡ_ምክሮች

#1️⃣100%_ሃላፊነት_ውሰድ

-ሰበቦችን እና ቅሬታዎችን ተው።
-ትክክለኛ ጊዜ እስኪመጣ አትጠብቅ።
-የምትፈልገውን ምቹ ሁኔታ ለራስህ ፍጠር።

2️⃣2_ከራስ_ጋር_በመሆን፣
      -በማንበብ እና
      -በመፃፍ ጊዜህን አሳልፍ።

#3️⃣መርዛማ_ግንኙነቶችን_ቋጭ

ወደ ኋላ እየገተተህ ያለን ማንኛውንም ግንኙነት አቋርጥ።

ከሱስ፣ ከሰዎች፣ ከቦታዎች እና ከመጥፎ ትዝታዎች ጋር ያለህን ማንኛውንም መጥፎ ግንኙነቶች አቋርጥ።

#4️⃣ካለፈው_ጋር_ሰላምን_ፍጠር

ለትላንት ጥፋትህ ትንሽ ምሕረትን እና ርሕራሄን ለራስህ አሳይ።

ትላንት አልፏል፤ በመጥፎ ትዝታው ዛሬን እንዳታጣ ከትላንት ጋር ስላምን ፍጠር።

#5️⃣_ግልጽ_ግቦችን_አውጣ፤
ለግቦቹ መሳካትም ቃል ግባ፤
ያለማቋረጥም ጠንክረህ ስራ።



📗#የሕይወት_መመሪያ መፅሐፍ


Https://www.tg-me.com/ethioleboled
😄#6ቱን_ብትሆን_ምን_ይልሀል?!

የሰው ልዩ ተሰጥኦ የሚገኘው በማስሎው አምስተኛ ደረጃ ላይ እንደሆነ አምናለሁ፡፡ እዚያ ደረጃ ላይ ለዛሬው ዓለም በጣም አስፈላጊ የሆኑ ሃያል እና ውብ ቃላት፣ እሴቶች፣ ችሎታዎችና ብቃቶች ይገኛሉ፡፡

እነዚህ ሃያል እና ውብ ቃላት የሚከተሉት ናቸው፡-

#1😄_ሞራል_ያለው_ሰው_መሆን፡- ሀብታም ለመሆን ሰዎችን ማጭበርበር አያስፈልግም፡፡

#2_😄ፈጣሪነት፡- ልዩ ተሰጥኦህን እና ችሎታህን ማውጣት፡፡

#3_😄ነጻነት፡- ስህተቶችን የመስራት ፍርሃት ሳይኖርብህ መኖር፡፡

#4_😄መፍትሔ_አመንጭነት፡- ችግሮችን የመፍታት ችሎታ- መፍትሔዎች ላይ ማተኮር፡፡

#5_😄ከአድልዎ_ነጻ_መሆን፡- ሰፊ የህይወት ሁናቴ መያዝ፡፡

#6_😄እውነታን_መቀበል፡- እውነታን ለመጋፈጥ አለመፍራት፡፡

#ሀብት_የመገንባት_ጥበብ መጽሐፍ

🔴🔴🔴🟢🟢🟢


Https://www.tg-me.com/ethioleboled
ማሃትማ ጋንዲ ሙሉቀን ታሪኩ.pdf
33.8 MB
😄😄 ማሃትማ ጋንዲ ✘ ⇲ ⇲
🔵⭐️

═══════════════════
▢ ትርጉም ➪ ሙሉቀን ታሪኩ
▢ ይዘት ➪ ግለ ታሪክ
═══════════════════

═══════════════🟦🟦🟥🟦🟥🟦🟦🟥🟦🟥

Https://www.tg-me.com/ethioleboled
ጠበኛ እውነቶች 1.pdf
41.2 MB
😄😄 ጠበኛ እውነቶች 😄😄


═══════════════════
ደራሲ ➪ ሜሮን ፈለቀ
ይዘት ➪ ልብወለድ
═══════════════════

➠➠➠ ሼር ያድርጉ!! ➠➠➠
ትልቅ ህልም አለኝ.pdf
78.6 MB
😄⚡️ትልቅ ህልም አለኝ.pdf👌
📚ርዕስ:- ትልቅ ሕልም አለኝ

➡️ድርሰት:- ዳዊት Dreams

ይዘት:-  ስለ ልቦና (psychology)

➡️የመጀመሪያ ዕትም:-
የገፅ ብዛት:- 376
🔖

**ትልቅ ህልም አለኝ ህልሜ
👉
አቅሜን ከመረዳቴ በፊት ፣ ህልሜ የማይቻል እና ከአቅም በላይ ይመስለኝ ነበር። **

😄🌟🌟🌟
ጆሴ ሞዪንካ ኡራጋይ.mp3
24.3 MB
ስለዚ ሰውየ ሰምታችሁ ታቃላችሀ ካልሰማችሁ ስሙት ብዙ ቁምነገር ታገኛላችሁ።

ጆሴ ሙየንካ የቀድሞ የኡራጋይ ፕሬዜዳንት

ሸገር መቆያ እሸቴ አሰፈ👍

የእሸቴ አሰፋን መቆያም ብታዳምጡ ብዙ ቁምነገር ትጨብጣላችሁ

@ethioleboled
2024/09/22 13:36:27
Back to Top
HTML Embed Code: