Telegram Web Link
ሰበዝ አለማየሁ ዋሴ.pdf
21.7 MB
አለማየሁ ዋሴ እሸቴ 6መፅሐፍትን የደረሰ ሲሆን: 4ቱ ተያያዥነት ያላቸዉ ሲሆኑ እነሱም
እመጕ
ዝጎራ
መርበብት
ሜተራልዮን የተቀሩር ግን ለየት ያሉ ናቸው.... እናም 5ቱም በ pdf አቅርበና #ችቦን ከ ዓመት በኃላ post ይደረጋል🙏
እመጓ (0).pdf
56.7 MB
ተያያዥነት ካላቸው መፅሐፍት
#የመጀመርያው.
💥📚ኢትዮ-ልቦለድ📚📖💥
Photo
❤️ሰላምታ ሰጥታኝ ከተቀመጠች በኋላ ለደቂቃዎች በዝምታ ስትብሰለሰል ዝምታዋ ስለጨነቀኝ
"ምን አይነት ሙዚቃ🎵🎵 ልክፈትልሽ?" አልኳት
" ፍሽኽታ አመለይ የሚለውን" አለችኝ።
"ሁሌ የምትሰሚው እሱን ሙዚቃ ነው።አይሰለችሽም?"
"ዋአ የምትወደው ነገር ፡፡ እንዴት ይሰለቻል?" ጥያቄዬን በጥያቄ መለሰችልኝ
"ሲደጋገም የማይሰለች ነገር አለ?" ጥያቄውን ያቀረብኩት ለእሷም ለራሴም ነበር።

⚽️መስራት፣ መማር፣ መውደድ፣ አምልኮ፣ ባስ ሲልም  መኖር ራሱ ይሰለቻል። እንዲያውም ለመሰልቸት በጣም ቅርብ ነን ብዬ አስባለሁ።
ሁሉም ነገር 'እንዳማረ አይዘልቅም' የሚለው አባባል ራሱ ለስልቹነታችን ማረጋገጫ አይሆንም? ተመሳሳይ በሆነ መልኩ የነበረንን ነገር ትተን አዲስ ፍቅር፣ አዲስ ጓደኝነት፣ አዲስ አመት፣ አዲስ ስራ፣ ለመጀመር በደስታ የምንዘጋጀው በመሰልቸት ቀለም የተፃፍን ስለሆንን ቢሆን አይደል?

የእህቴ ጓደኛ ናት። የጎረቤታችንን ቤት ተከራይተው ይኖሩ ስለነበር ብዙ ጊዜ እህቴ ባትኖርም ቤት መጥታ ከእኔ እና ከነእናቴ ጋር ተጫውታ ትሄዳለች። ብዙ አታወራም አንዳንዴ ሙዚቃ እየሰማች ታንጎራጉራለች ሌላ ጊዜ ደግሞ የምሰራቸውን ስዕሎች የምፅፋቸውን ፁህፍች በጥልቀት ትመረምራለች አልፎ አልፎ ደግሞ የመጣልንን እናወራለን። 

⭐️"መውደድህ የወረት እና የውሸት ከሆነ ነው የሚሰለችህ። መውደድህ ሀቅ ከሆነ እኮ በየቀኑ የበለጠ ይጥምሀል እንጂ አይሰለችህም። አንድ ቀን በጨመረ ቁጥር መውደድህ ላይ ሌላ የአንድ ቀን ትዝታ ይጣበቅበታል። ሲደጋገምና ቀን ሲጨምር መውደድ ይገዝፋል እንጂ አይሰለችም" አለችኝ አይኖቼን እየተመለከተች።

⭐️"ሁሉም ነገር ትዝታ እንዴት ይሆናል? ትዝታ ሁሉስ እንዴት የሚወደድ ይሆናል?" አልኳት ወሬዋን እንድትቀጥልልኝ ፈልጌያለሁ።

"የምትወዳቸው ሰዎች ጋር የምታደርገው ነገር ሁሉ ትዝታ ይሆናል። ተራ የሚመስሉ ነገሮች ነገ ዋጋ ያላቸው ነገሮች ሊሆኑ ይችላሉ። ዛሬ ትርጉም የሌላቸው ነገሮች ነገ ግዙፍ ትዝታዎቻችን ሊሆኑ ይችላሉ። ትናንት ከእህትህ ጋር ይህንን ዘፈን እየሰማሁት ነበር ያጫወተችኝን ነገሮች ሁሉ በዚህ ጣዕም እያጀብኩት ነበር ዛሬም ካንተ ጋር ያወራነውን ነገር ነገ ሳስታውሰው እና የቀን ማስታወሻዬም ላይ ስለማሰፍረው ማስታወሻዬና አእምሮዬ ውስጥ ትዝታ ተጨምሮበት ዘፈኑ ይኖራል ስለዚህ መልካም ትዝታ ፈጥሯል። ትዝታን በጥሩም ሆነ በመጥፎ የምትስለው ደግሞ አንተ ነህ።"

⭐️ከንግግሯ ውስጥ አእምሮዬ ላይ የቀረው 'የምትወዳቸው ሰዎች ጋ የምታደርገው ነገር ትዝታ ይሆናል።' የሚለው ስለነበር

"ትወጅኛለሽ?" ብዬ ውብ አይኖቿን እየተመለከትኩ ጠየቅኳት።

መልስ ሳትሰጠኝ የተቀመጠችበትን ወንበር በእጇ በመምታት ምናባዊ ኢንስትሩመንት እየተጫወተች አብራ ማንጎራጎር ጀመረች

ናብራ ከቢዱኒ እናማረርኩ
ጥዕና ዘይበሉ ምስ ረኣኹ
አፀናኒዐያ ንነብሰይ
አረጋጊኤዮ ንመንፈሰይ

ለካ ወሃቢ ምበር አይኮንኩን ሓታቲ
ተፀባዩ አይኮንኩን ተመፅዋቲ
ጥዕና አይትኽላአኒ ምስ ተስፋ
ትምረር ምበር ሂወት ከሰንፋ

የድምጿ ቅላፄ ለጆሮ ይጣፍጣል። የሆነ አእምሮ ላይ የሚቀር አዚም አለው።

ጥያቄዬን መመለስ እንዳልፈለገች ሲገባኝ እኔም ደግሜ ላለመጠየቅ ከራሴ ጋር እየታገልኩ ሳላስበው አብሬ ማንጎራጎር ጀመርኩ

ፍሽክታ አመለይ
ኩሉ ጼረ ፍሽክታ አመለይ

በእንጉርጉሮዬ ሳቀች

ረዥም ሳቅ ...

አብሬያት እንድስቅ ካደረገኝ ሳቋ  ቀጥሎ "ዋይ ሌላ ዘፈን የምትዘፍን ነው የምትመስለው። ደግሞ ፍሽክታ ሳይሆን ፍሽኽታ ነው የሚለው"  ብላ ወረቀት ላይ የተወሰኑ የዘፈኑን ስንኞች ፃፈችልኝ።

ናብራ ከቢዱኒ እናማረርኩ
ጥዕና ዘይበሉ ምስ ረኣኹ
አፀናኒዐያ ንነብሰይ
አረጋጊኤዮ ንመንፈሰይ

ለካ ወሃቢ
ተፀባዩ አይኮንኩን ተመፅዋቲ
ጥዕና አይትኽላአኒ ምስ ተስፋ
ትምረር ምበር ሂወት ከሰንፋ

ምዃነይ እነኹ አሚነ
ዝሃስኩዎ ሂዘስ አመስጊነ

ፍሽኽታ አመለይ
ኩሉ ጼረ ፍሽኽታ አመለይ
ፍሽኽታ አመለይ
ይጥዓም ይሕሰም ፍሽኽታ አመለይ
ፍሽኽታ አመለይ
አይሕለልን ክሳብ ዝሰምረለይ
ፍሽኽታ አመለይ
ይስዕሮ'ምበር አይስዕረንን ፀገመይ

ለመጨረሻ ጊዜ ብቻችንን ያወራነው ያኔ ነው...

አሁንም ራሴን እጠይቃለሁ
ያኔ በወረቀት ላይ የዘፈኑን ግጥሞች ነበር የፃፈችው? ወይስ ራሷን የአእምሮዬ ግድግዳ ላይ በትዝታ ቀለም አድምቃ ነበር የፃፈችው?

ሙዚቃውን እንዳለችው በሰማሁት ቁጥር የበለጠ እየወደድኩት ነው። እናም ጥያቄዋ ተራ ቢመስልም ትክክል ነበር። ዛሬ ላይ በምንም ነገር የመሰልቸት ስሜት ሲሰማኝ  'በእውነት የምንወደው ነገር እንዴት ይሰለቻል?' ብዬ ራሴን እጠይቅና 'የሰለቸኝ መውደዴ የእውነት ባይሆን ነው' ብዬ እመልሳለሁ።


✔️ይሄ ሁሉ አንብባችሁማ 👍 ተጫኑ
ቀልጣፋና የዋህ ስለነበር አክስቱን ወደ ቤቷ እንድትወስደው አጓጓት። የልጁ እናትና አባትም በደስታ እሺ አሉ። በአክስቱ ቤትም ከብት ጠባቂ የነበረው ብላቴና በስህተት የእህል ክምር ያቃጥላል፤ ቁጣውንና ግርፊያውን ፈርቶ ወደ አባቱ ጋር ወደ ትልቅ ከተማ ሸሸ።

የብላቴናው አባት የቤተክህነት ሰው ስለነበሩ ከአባቱ ጋር ኑሮው በመቃብር ቤት ሆነ። አባት አምላካቸውን በማመስገን እና ህዝቡን ወደ ፈጣሪው በመመለስ ሲባዝኑ ብላቴናው ደሞ ዘመናዊ ትምህርትን የሙጥኝ አለ። አባት መንፈሳዊ ዕውቀትን ለልጃቸው ከማስተማር ቦዝነው አያውቁም። ብላቴናው በመንፈሳዊም በዘመናዊም ትምህርት እያደገ ሄደ።

ድምጹ ለዝማሬ ስለማይኾን፤ መጽሐፍ ንባብ ላይ በረታ፡፡
ግዕዝን በኢትዮጵያ÷ አረብኛን በግብጽ ተምሯል፡፡ በግብፅም ከአቡነ ሺኖዳ ጋር ጓደኛ ነበር፡፡
አማርኛ÷ ግዕዝ እና አረብኛ ያላቸውን ዝምድና እና ኅብረትንም ተረዳ፡፡ በጀርመንም ሀገርም ግሪክ እና ላንቲን ቋንቋዎችንም ተማረ...

በዘመነ ደርግ፤ ለኢሰፓ ከባድ ተቃውሞ ነበረው፡፡ የኢሰፓንም ጥይት ቀመሠ፡፡ ተጎዳም፡፡ ንብረቱም ወደመ፡፡
ህይወቱን ለማትረፍ ለህክምና ወደ ለንደን ተጋዙ፡፡

ከህክምና ማግስት ከለንደን ወደ ሚኖሶታ አዲስ የህይወት እና የሙያ ደጅን ሠራ፡፡
በአሜሪካም በኢትዮጵያ ላይ ወጥ ጥናቶችን ሠራ፡፡

ሊቀ ሊቃውንቱ ጌታቸው ኃይሌ በኢትዮጵያ የግዕዝ መንፈሥ÷ በኮፕቲክ የእውቀት ድባብ÷ በጀርመን ዘመናዊ ፍልስፍና÷ በአሜሪካ የኢትዮጵያ የሴም የእውቀት ሠገነት ሲናገር ኖሯል፤ ተርጉሟል፡፡
ፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ ነፍስ ይማር!!!
***
ግን እኛ ሊቁ ስራዎች ውስጥ ምን ያህል አንብበናል??
እናንብብ እንወያይ ነጻ እንውጣ
ንበብ ለንባብ
💥📚ኢትዮ-ልቦለድ📚📖💥
Photo
🔵⭐️ደባሌ ነች። የስራ ባልደረባዬም ነች። አብረን ነው የምንውለው። አብረን ነው የምናመሸው። የምንለያዬው....ለመኝታ ብቻ ነው። "አትሰለችህም ወይ?" ይለኛል ጓደኛዬ። ስንተኛም የማንለያይበትን መንገድ ለማግኘት እየጣርኩ እንደሆነ አያውቅም።

እንደምወዳት❤️ እኮ ልነግራት ነበር። ግን ድንገት ስለምትፈልገው የወንድ አይነት ስታብራራ ሰምቼ ጉሮሮዬ ተዘጋብኝ። ፀጥ አልኩ። ውሸት ምን🥰 ያደርጋል? መስፈርቷ ውስጥ በከፊል እንኳን የለሁም። ድሮ ድሮ ኮራጅ ተማሪዎች ጎበዝ ተማሪ ሲያጡ ከሰነፉ ላይ ይኮርጁ ነበር...እሱ "True" ሲል እነሱ "False" እያሉ...እሷም መስፈርቷን ያወጣችው እንዲህ እያደረገች ሳይሆን አይቀርም....እኔ ስስ ስሆንባት "ደንዳና"...እኔ ፀይም ስሆንባት "ደማቅ ቀይ" እያለች!

🟢አንዳንዴ እንደዚህ ነው...የማይፈልጉት ነገር መሆንህን የሚሳውቁህ ስለሚፈልጉት ነገር እያወሩ ነው።

ስለዚህ በዝምታ መውደዴን ቀጠልኩ። መውደዴን ያልተውኩት ሞኝ ስለሆንኩ አይደለም። መውደዴን ያልተውኩት እሷ ያስቀመጠችውን መስፈርት የሚያሟላ አንድም ወንድ እንደማታገኝ ስለማውቅ ነው።
አውቃለሁ አለም እንደኔ ባሉ መካከለኛ ሰወች የተሞላች እንደሆነች። አውቃለሁ ህይወት ኮርኩማ ኮርኩማ ስታንዳርዷን እንደምታወርድባት። ከኔ የሚጠበቀው ያ ቀን እስኪመጣ ድረስ ከስሯ ሳልጠፋ መቆዬት ብቻ ነው።

የሴት ጓደኛም የላትም። ረጅም ስለሆነች ከነሱ ጋ ስትቆም ቀውላላ ያስመስሏታል። ስለዚህ እኔ እኩያዋ ጋ መሔድን ትመርጣለች። "እንደዚህ ረጅም ሴት ወይ ከአማልክቱ ወገን ነች...ወይ በስህተት ሴት ሁና የተፈጠረች ወንድ ነች!" ይላል ጓደኛዬ። እስማማለሁ በአባባሉ። በስህተት ሴት ሁና የተፈጠረች ወንድ እንዳልሆነችም አውቃለሁ።

ማታ ማታ የሆነ ቲቪ ሸው እናያለን። ትንሽ እንዳዬን እናቋርጠውና "Grey Anatomy" የሚለውን ተከታታይ ድራማ ለአስረኛ ጊዜ እንጀምረዋለን። ወይ "Friends" እናያለን። ጓደኛማቾቹ ሲሳሳሙ ዞር ብዬ አያታለሁ። እሷ ግን አታዬኝም። መልሼ እዞራለሁ።

ታዲያ ሁኔታችንን ሁሉ የሚገርመው የስራ ባልደረባችን "እንደኛ ባለትዳር ለመባል እኮ በሶስት ወር አንዴ ሴክስ ማድረግ ነው የቀራችሁ" እያለ ሙድ ይይዛል። ቀልዱ ቀልድ ነው እኔ ግን.... "ሜሪ" ብዬ ለሌላ ነገር በጠራኋት ቁጥር...በዛው "ሜሪ ሚ?" ብዬ ልንበረከክላት የሚያምረኝ ቀን ጥቂት አይደለም።

እሱም ነው ትልቁ ፍርሀቴ። የሆነ ቀን ኩሽና ውስጥ፣ ወይ ፊልም ስናይ፣ ወይ የሆነ ሒሳብ ሳስረዳት፣ ወይ ስለምናዬው ድራማ ስታብራራልኝ...ድንገት ደፍሬ እስማታለሁ። ከዛ ትክ ብላ ታዬኝና ተነስታ ወደ ከፍሏ ትገባለች። ዘግታኝ ልትውል ነው ብዬ ስጨናነቅ ተመልሶ በሯ ይከፈታል። ከዛ እንደገና ልትስመኝ ነው ብዬ መጓጓት ስጀምር በአንደኛው እጇ ሻንጣዋንም ይዛ እየወጣች ነው። በስማም!!.....ላብ በላብ ሁኜ ከእንቅልፌ እነሳለሁ። "ህልም እልም" "ህልም እልም" ብዬ አማትቤ እተኛለሁ።

ተይዣለሁ። ተይዣለሁ በጣም። በርግጥ እስከ ምን ድረስ እንደተያዝኩ ያወቅኩት አንድ ቀን አሟት ቀርታ ቢሮ ብቻዬን የሔድኩ ዕለት ነው።  "አንቺ ስትሔጅ ስንቶች ተጋለጡ" የሚለው የአብርሽ ግጥም እንዳዲስ ትርጉም ሲሰጠኝ ዋለ!
ከቤት እስከ ቢሮው ያለው መንገድ ለካስ እንደዚህ ሩቅ ነበር?! ምን ብርታት ሰጥቶን ነው በ'ግራችን ስንመላለስበት የከረምነው?
ለካስ ስራዬን እጠላዋለሁ!! አለቃዬስ ምንድን ነው እንዲህ የሚያስጮኸው? ቢሯችን ለምንድን ነው ሆስፒታል ሆስፒታል የሚሸተው? ሰራተኛው ሁሉ ለምንድን ነው የማያስቅ ቀልድ የሚቀልደው?
ከተማው ላይስ መቼ ነው ሰው እንደዚህ የበዛው? ሮፍናንን ማነው ዘፋኝ ያደረገው? ፀሀዩዋ እንዴት እንዴት ነው የሚሰራራት?

የምወደው ነገር ሁሉ አስጠላኝ። የምጠላውን ሁሉ ማጥፋት አማረኝ። ይሔን ሁሉ ሁኘ ምርር ብሎኝ ሰዓቱን ሳዬው ደግሞ ገና አራት ተኩል እያለ ነው። በርግጥ ሀያ ደቃቃ ይቀረዋል ለተኩልም። ራሴን አመመኝ። ስራውን ትቼው ወደቤት ተመለስኩ።

በሩን ከፍቼ ስገባ...!

ሜሮን በድንጋጤ ከላዩዋ ላይ ያለውን ወንድ ገፍትራው ተነስታ ቆመች። አይኔን ማዬት ከብዷት ተሸማቅቃ አንገቷን ሰበረች። እኔም የሰማኒያ ሚስቴ ስትማግጥብኝ የያዝኳት ያህል ግርጥት ብዬ ዝም አልኩ። ከተወሰነ መፋጠጥ ቡኃላ ነበር ሚስቴ አለመሆኗ ትዝ ያለኝ። ብንን ብዬ ይቅርታ ጠይቄያቸው ተመልሼ ልወጣ ስል ሩጣ እጄን ያዘችው።  "ምነው?" አልኩ ድምፄ እንዳይንቀጠቀጥ እየተጠነቀቅኩ።

"ጊዜ ማሳለፊያ መስሎህ😓😓 እንዳትቀዬመኝ" ብላ ጀመረች!...እጆቿን እያፍተለተለች...."ያው ነገሩ ትንሽ❤️ ሲሪዬስ እስኪሆን ደብቄህ ነው እንጂ...ስመኘው የኖርኩትን ልጅ'ኮ  አግኝቸዋለሁ!" አለችና በፈገግታ አዬችኝ። ከልቧ ❤️ደስ እንዳላት ታስታውቃለች። ሁኔታዋም ለሚወዳት ልጅ ሳይሆን ለታላቅ ወንድሟ እንደምትነግር...ሀፍረት እና ኩራት የተቀላቀለበት ነው። አይኖቿ የደስታ እንባ አቅርረዋል። እርግጠኛ ሆናለች። የኔም አይኖች ረጠቡ።
አንዳንዴ ደግሞ እንደዚህ ይሆናል....የምስራቻቸው ውስጥ መርዶህን ትሰማለህ
!😓🥹🥹

✔️ይሄ ሁሉ አንብባችሁማ 👍 ተጫኑ
➻ አምሳለ ኃሩይ (የብላቴን ጌታ ኃሩይ ወ/ስላሴ ልጅ)

➻ ልዕልት ፀሀይ ኃይለስላሴ

(ከግራ ወደ ቀኝ)

⩩ የመጀመሪያዎቹ የኢትዮጵያ ሴቶች ለትምህርት ወደ አውሮፓ በተላኩ ወቅት (ከመሀል ያለችው የት/ቤት ጓደኛቸው ናት)

#ታሪክን_ወደኋላ
የመንበረ ፀባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን

በግንባታ ወቅት ፤

መስከረም 28 ቀን 1928 ዓ.ም

#ታሪክን_ወደኋላ
ሀዲስ - በአሉ ግርማ.pdf
27.5 MB
📚ርዕስ:- ሀዲስ
📝ደራሲ:- ከበአሉ ግርማ

SHARE and JOIN🙏
@ETHIOLEBOLED
ኦሮማይ በአሉ ግርማ.pdf
4.6 MB
📚ርዕስ:- ኦሮማይ
📝ደራሲ:- በዓሉ ግርማ
📜ዘውግ :- ልብ ወለደ
📅ዓ. ም :- 1972
📖የገፅ ብዛት:- 372

SHARE and JOIN🙏
@ETHIOLEBOLED
የህሊና_ደወል_በዐሉ_ግርማ_@Only_Amharic_books_On_Telegram.pdf
4.3 MB
📚ርዕስ፦ የህሊና ደወል
📝ደራሲ ፦ በዐሉ ግርማ
📖የገፅ ብዛትፅ፦ 248


ማጋራት አይዘንጋ!
@ETHIOLEBOLED
😎እንዳንቺ አይነት ሴት ብዙ አገኛለሁ ሲላት....
.
.
.
👩‍🦰ልክ ነህ brand ስለሆንኩ  copy አይጠፋም አለችውም እሷም ኮራ ብላ!

😂😆🤣

join us➜ @ethioleboled
     
#የእስረኞቹ_እንቆቅልሽ

🔠አንተ እና ጓደኛህ በአንድ ወንጀል ተጠርጥራችሁ ታሰራችሁ፡፡ ሆኖም መርማሪ ፖሊሶቹ ምንም አይነት ማስረጃ ሊያገኙ አልቻሉም፡፡ እናም ሁለታችሁም በተለያየ ክፍል እንድትሆኑ ተደረገ። መርማሪዎቹም ለየብቻችሁ ያሉትን አማራጮች አቀረቡላችሁ።

🚩
#አማራጭ_አንድ - አንተ ከተባበርክ እና ወንጀላችሁን ከተናዘዝክ ነገር ግን ጓደኛህ ዝም ካለ አንተን በነጻ እንለቅሃለን እርሱ ግን አስራ አምስት አመታት ይታሰራል፡፡

🚩
#አማራጭ_ሁለት - ጓደኛህ ወንጀላችሁን ከተናዘዘ ነገር ግን አንተ ዝም ካልክ፣ እርሱ በነጻ ይለቀቃል... አንተ አስራ አምስት አመታትን ትታሰራለህ።

🚩
#አማራጭ ሶስት- ጓደኛህም አንተም ከተባበራችሁን ሁለታችሁም አምስት አመታትን ትታሰራላችሁ፡፡

🚩
#አማራጭ_አራት- አንተም ጓደኛህም ካልተናዘዛችሁ፤ ሁለታችሁም ቀላል የሆነ የአንድ አመት እስራት ትታሰራላችሁ።

🚩በዚህ አጣብቂኝ ውስጥ ብትሆን ምን ታደርጋለህ?

🔠መናዘዝህ የተሻለ ውጤትን የሚያስገኝ ይመስላል፤ ጓደኛህን ብትከዳውና ብትናዘዝ  የሚገጥምህ በነጻ የመለቀቅ ዕድል ነው። በተቃራኒው ዝም ብትልና ባትናዘዝ፣ የአንድ አመት ወይም የአስራ አምስት አመት እስራት ይጠብቅሃል።

🔠ሆኖም አንተ ነጻ ሁነህ ጓደኛህ አስራ አምስት አመታትን በእስር ቤት ሲማቅቅ ማየት ምን አይነት ስሜት ይፈጥርብሃል?

🔠እናም ይህ እንቆቅልሽ የሚያስነሳው መሰረታዊ ጥያቄ “እንደ ማህበረሰብ ማሰብ” ወይስ “እንደ ግለሰብ ማሰብ” የሚል ይሆናል። ለሁላችንም የተሻለ አማራጭ የሚሆነው እንደ ማህበረሰብ ማሰብ ነው፤ ሆኖም ሌላኛው ሰው ምን እንደሚያስብ አናውቅምና ለራሳችን መልካም የሚሆነውን ለማድረግ ስንል ራስ ወዳድ እንሆናለን፡፡ እኔ እንኳ ባልስርቅ ሌላው ይሰርቃል የሚል ሃሳብ ይፈጠራል። ይህ አስተሳሰብም በድሃ አገራት ላለው የሙስና እና ስርዓት አልበኝነት አንዱ ምክንያት ነው፡፡

⚡️ለምሳሌ ያህል፣ አንድ አሳ የሚሰገርበት ሃይቅ አለ ብለን እናስብ። አሳ አስጋሪዎች በዚህ ሃይቅ ውስጥ ያሉት አሳዎች በራስ ወዳድነት ያለ ልክ የሚያጠምዱ ከሆነ፣ የአሳዎቹ ቁጥር ተመናምኖ በአንድ አመት ውስጥ ሃይቁ አሳ አልባ ይሆናል። ሆኖም ግን አግባብ ባለው ሁኔታ በልክ እና በመጠን የሚያሰግሩ ከሆነ፣ የአሳዎቹ ቁጥር አይመናመንም፤ እንዲያውም ከአመት ወደ አመት የሚያገኙት የአሳ ቁጥር እየጨመረ ይመጣል።

እዚህ ላይ ዋነኛ ጥያቄው መተማመን የሚለው ነው፡፡ አሳ አስጋሪዎቹ በመጠን ሊያሰግሩ ቢስማሙም አንዳቸው ሌላኛውን እስካላመኑ ድረስ ስምምነታቸው ዋጋ አይኖረውም፡፡ ልክ በሁለት ክፍሎች ውስጥ ለብቻቸው ተቀምጠው እንዳሉ እስረኞችም ይሆናሉ፡፡

#ፍልስፍና_ከዘርዓ_እስከ_ሶቅራጥስ

📗📙📕
​​#10\_መረዳት\_ያለብህ\_እውነቶች

#አንድ- ደሞዝ ማለት ህልምህን እንዳትኖረው ቀጣሪዎችህ የሚሰጡህ አደንዛዥ እጽ ማለት ነው።

#ሁለት- ነገሮችን ለመጀመር ጥሩ ጊዜ የምትጠብቅ ከሆነ፣ ሙሉ ህይወትህን ታባክናለህ እንጂ ምንም የሚፈጠር አዲስ ነገር አይኖርም። ምክንያቱም ትክክለኛው ጊዜ አሁን ስለሆነ።

#ሶስት- ምንም ያህል ቅርብ የምትላቸው ጓደኞችህን እና ቤተሰቦችህን ብታምናቸው እንኳ፣ ስላንተ ሁሉን ነገር እንዲያውቁ አታድርግ።

#አራት- ሙሉ ለሙሉ የቅርብ ጓደኞችህን የምታጣው ያኔ ነው... ራስህን መለወጥ ስትጀምር!

#አምስት- አስር እጥፍ ደስተኛ መሆን ከፈለግክ ይቅር ባይ ሁን እና ለችግርህ ማንንም ተወቃሽ ማድረግ አቁም።

#ስድስት- በሳል ሰው የምትሆነው ራስህን መምራት ስትጀምር ነው።

#ሰባት- ራስህን እንዴት እንደምትቀይር የሚያስተምሩ መቶ መጽሐፎች አያስፈልጉህም። የሚያስፈልግህ ተግባራዊ መሆን እና በራስህ የምትከተለው ስነ-ስርአት ነው።

#ስምንት- በአለም ላይ ያለህ ከባዱ ተልእኮ ቢኖር ትኩረትህን አላማህ ላይ ማድረግ ነው። ቀላሉ ደግሞ እያማረሩ መኖር ነው። የቱን ትመርጣለህ?

#ዘጠኝ- ሰዎች አስፈላጊ ያልሆነ ጓደኝነት ላይ የሚቆዩት ብቸኝነትን ስለሚፈሩ ብቻ ነው።  አንተስ?

#አስር- ከላይ ያነበብካቸው አንተን እንደሚጠቅሙህ ካሰብክ ሼር በማድረግ ወዳጆችህን እንድትጋብዛቸው በትህትና እጠይቅሀለሁ🙏
🅱️🔠🔠 🚩🚩🚩🚩🚩🚩

Biography/Autobiography (የሕይወት ታሪክ) ማንበብ ለምን?

መፅሀፍ ለማንበብ ስንመርጥ የብዙዎቻችን የመጀመሪያ ምርጫ ልብወለድ እንደሆነ እጠረጥራለሁ። ነገር ግን ልብወለድ እንደስሙ ልብ ወለድ(ልብ የወለደው) ነው። ደራሲው ምናቡን በመጠቀም በፈጠራቸው ገፀባህሪያት እና ታሪክ አማካኝነት የሚፈልገውን መልእክት ያስተላልፋል። ልብወለድ በመሰረቱ አዝናኝ ነው ― ቅርፁ ይፈቅድለታል።

የግለሰቦችን የሕይወት ታሪክ ማንበብ ግን አንድ ጉልህ የማይተካ ጥቅም አለው። የምናነበው ተጨባጭ እና የሆነ እና መሬት የወረደ ነገርን ነው። ስለዚህ በቀላሉ ከራሳችን ህይወት ጋር ልናቆራኘውና ልንማርበት እንችላለን። የሕይወት ታሪክ የሚፃፍላቸው ግለሰቦች ብዙውን ግዜ ለማህበረሰቡ የሚጠቅም ነገር ያደረጉ፣በተሰማሩበት መስክ የስኬት ጫፍ ላይ የደረሱ ናቸው። የኑሮ ልምዳቸው ለሚሊዮኖች ይጠቅማል ተብሎ ሲታመንበት የሕይወት ታሪካቸው ይጻፋል። በዚህም ብዙዎች ይማሩበታል።

ከዚህ ባሻገር አንዳንድ የሕይወት ታሪክ መፅሀፍት እንደ ታሪክ ሰነድ ያገለግላሉ። የተክለሐዋርያት ተክለማርያም "የሕይወቴ ታሪክ" ጠብሰቅ ያለ የታሪክ ዶሴ ነው። የማንዴላ እና የአን ፍራንክ ሕይወት ታሪካዊ ዳራ አለው። አንዳንዴ የግለሰቦችን ታሪክ ስናነብ በዚያው የሕዝቦችን ታሪክ እያነበብን ነው። ግለሰቡ የሕዝብ ወኪል ሆኖ የሚያገለግልበት ግዜ ጥቂት አይደለም። የመንግሥቱ ለማ "ደማሙ ብዕረኛ" እና የስብሐት ገብረእግዚአብሔር "ማስታወሻ" የማይጠገብ ለዛ አላቸው። ሁለቱም ስብዕናዎች በውስጣችን ስር ሰደው ይገዝፉብናል።

ሁላችንም ብናነባቸው የምናተርፍባቸውን የሕይወት ታሪኮች ላስታውሳችሁ ፦

1️⃣ የሕይወቴ ታሪክ ― ተክለሐዋርያት ተክለማርያም

2️⃣ ማስታወሻ ― ዘነበ ወላ

3️⃣ ደማሙ ብዕረኛ ― መንግስቱ ለማ

4️⃣A Long Walk to Freedom ― Nelson Mandela

5️⃣The Diary of a Young Girl ― Anne Frank

6️⃣The Autobiography of Malcolm X

7️⃣ The Story of My Experiments with Truth ― Gandhi

8️⃣I Know Why the Caged Bird Sings ― Maya Angelou

9️⃣ The Story of My Life ― Helen Keller

1️⃣🚩 Life of Samuel Johnson ― James Boswell

1️⃣1️⃣ Autobiography of Benjamin Franklin

1️⃣2️⃣በአሉ ግርማ ህይወቱና ስራዎቹ―እንዳለጌታ ከበደ

🔵ስለዚህ አንዳንዴ ከልብወለድ ወጣ ብሎ ኢልብወለዶችንም መጎብኘት ያስፈልጋል። ብዙ ግዜ እንደሚባለው "ልብወለድ ለነፍስ፣ ኢልብወለድ ለስጋ ነው" በዚህ መሰረት የልብወለድ አንባቢ የሐሳብ ሐብታም ሲሆን የኢልብወለዱ ደግሞ የገንዘብ ሐብታም ይሆናል። ልብወለድ ማንበብ ሕልመኛ ያደርጋል ፤ ኢልብወለድ ደግሞ የተግባር ሰው። ስለዚህ ሁለቱንም አመጣጥኖ ማንበብ ፤ ሁለቱንም መንከባከብ ይገባል።
"ዝም ስትል የማታውቅ የሚመስላቸው ብዙዎች ናቸው ምክንያቱም እነሱ በማውራት ያምናሉና ፡፡ ነገር ግን ያወሩትን አይኖሩትም :: አንተ ግን በማውራት አትመን ዝም ብለህ ልታወራው የፈለከውን ኑረው ። ከዛም በአንተ ዝምታ ውስጥ የኖርከው ህይወት ጥሶ ይወጣና አንተ ዝም እንዳልክ ሳታወራ ሰዎች ያወሩልሀል ።''

📖አና ፍራንክ📖
ተርጓሚ አዶኒስ

@ethioleboled
🙏ማጋራት እንዳይዘነጋ🙏
2024/09/22 13:29:26
Back to Top
HTML Embed Code: