Telegram Web Link
እመጓ @Bemnet_Library.pdf
56.7 MB
ርዕስ=እመጓ
ደራሲ=አለማየሁ ዋሴ
 
  ማጋራት መተሳሰብ ነው!
📚 @ethioleboled
እውነታኛ ማንነቴ እሱ ነው የሚያውቀው ፤ ማንነቴን እንደ ገላዬ መለመሉን አይቶታል ፤ የድብርቴ እና የደስታ ጣሪያዬን ዳስሶታል ።

ቀልድ ይችልበታል ፤ እኔን የእሱ ለማድረግ
አልጣረም ፤ ወይ ደሞ የእሱ ለማድረግ በሌሎቹ መንገድ አልመጣም ፤ ከእሱ ጋ እንድሆን ክችች አይልም ፤ ሳያብራራ በማህበረሰቡ የተገነቡ ህጎችን ይገነብራቸዋል ፤ ሰው የማይጎዳ ነገርን ከምን ይሉኝ ወጥቶ ማድረግ የመሰለ ነፃነት የለም ።

ኤልዱ ሲለኝ ደስስ ይለኛል ። ጭንቀቴን ስነግረው ጣልቃ ሳይገባ ይሰማኛል ፤ አይዞን መፍትሄ አይጠፋም ይለኛል ወይ እቅፍ ያደርገኛል ፤ ጨንቆኝ አግኝቼው ቅልል ያላለኝ ግዜ አላስታውስም።

መብሰልሰል እና ማወሳሰብ ውስጥ ስለሌለ ይሆን እንደ እኩዮቹ ያልሸበተው አልያም ደግሞ ያልተመለጠው ስል አስባለሁ።

መንገድ ላይ አንገቴ ስር ገብቶ በስስት ይስመኛል ፤ ዙሪያ ገባውን ተሳቅቄ ስቃኝ ክባዳም እያለ የበለጠ አይን ውስጥ በሚያስገባ ሁኔታ እቅፍፍ አድርጎ ይስመኛል ።

ስንዋደድ ፣ አንሶላ ስንጋፈፍ ፣ ፍቅር አሰጣጡ ጣፈጠኝ ከሚሰጠኝ ደስታ እና ከማንነቱ ሱስ ያዘኝ


ከውጪ ለሚያዩን ቁንጅና እና ሃብቴ በግንኙነታችን የጌታ እና የሎሌ አሰተላለፍ ያለን ይመስላቸዋል ።

እውነታው ፦

ባውንደሪ አለው ፤ የማይወደውን ሳደርግ አይለማመጠኝም ፣ አይልመጠመጥም ፣ ይዘጋኛል ይርቀኛል ፤ ቆፍጠን ያለ ልበ ሙሉ ነው ።

የሰዎች በደል ይሰማዋል ፤ የወደቀ ላይ አይፈርድም ትክክል መስሎ ለመታየት የማይጋጋጥ ነፍስ ያለው ፍጡር ነው ።

ከሚታየው በላይ በሂደት እየገዘፈ የሚሄድ የማፈቅረው ልጅ እሱ ነው
💥📚ኢትዮ-ልቦለድ📚📖💥
Photo
🔵ከተወዳጀኋት በርካታ ቀን ሆነን ። ስራ ነው ያገናኘን ። መልከ-መልካምነቷ ቢስብም ፤ የግንባሯ መቋጠር አያቀርብም ።ቁጥብ ያለች elegant ነች።

አንድ ቀን መንገድ እየሄድን አንድ ጎረምሳ የአንዲትን ልጅ ቂጥ ቸብ አደረጋት ፤ ልጅቷ ተናደደች ፤ ልጁ ደግሞ አሽካካ ። በሰጨኝ ሰደብኩት ሰደበኝ ፤ ተገለገልን ፤ ቤተሳይዳ ደነገጠች ፤ ለማረጋጋት ሞከረች ፤ ተናደድኩ እንዴት እንደዚህ ይሆናል ።

ሰው ክቡር ነው። ሊያውም ያልደረሰብሽ ፤ ሊያውም የማታውቂው ፤ ሊያውም ሴት ልጅ
አልኩ ።

ንዴቴ ሲተን በግርምት ዝም ብላ ስታየኝ ፤ አየኋት ። በሌላ ቀን ስንገናኝ ከበፊቱ ትንሽ ቀረበችኝ ።

ደሞ በሌላ ቀን ፤ ከፊታችን የሚመጡ የተጎሳቆሉ እናትን ከኋላ ቀረት ብዬ ብር ሰጠኋቸው

ምርቃቴን ፣ በረከቴን ወስጄ ስመለስ ፤ ምን አድርገህላቸው ነው አንዲህ ተጎንብሰው
እጅ የሚነሱህ አለችኝ ።ምንም ብዬ አድበሰበስኩት ።

ፍጥጥ ፤ ፈርጠም ፤ ደረቅ ብላ ጠየቀችኝ ። መለመን አልጀመሩም እንጂ ኑሮ ከብዷቸዋል ፤ ቡና መግዣ ሳንቲም ነገር ሰጠኋቸው ይኸው ነው አልኳት ።

ሳይለምኑህ አለችኝ ?

አይናችንን ስንከፍት ፤ ከቃል በላይ ገፅታ ሁሉንም ይናገራል አልኳት ። ቃል አልተናገረችም ።

በሌላ ቀን ስንገናኝ ።
እጮኛ አለሽ አልኳት?? የለኝም ወንድ አላምንም አለችኝ !

በእርጋታ ለምን አልኳት ?

እ ዝም አለች

ዝም ብዬ ሳያት ቀጠለች

አባቴ ሃይለኛ ነው ። እናቴ ስታናደው በር ዘግቶ በቀበቶ ነበር የሚገርፋት ። እንፈራዋለን ። ይጮህብናል ። ዝም የሚል ነበር ፤ ሲስቅ እንኳን አይቼው አላውቅም ። እናቴ በጣም ታሳዝነኝ ነበር ። እኔን እንኳን እንደሚወደኝ ለማሳየት ቃል ሳያወጣ ፀጉሬን ነበር የሚያሻሸው ፤ በቃ እቺ የፍቅሩ ማሳያ አፅናፍ ነበረች።

ከቁጣ በስተቀር ገርፎኝ አያውቅም ግን እናቴ ሳበሳጫት ለአባትሽ ነው የምነገርው ስትለኝ ፤ ሽንቴ እንሲኪያመልጠኝ ነበር የምደነግጠው ፤ ብርገጋዬን ስለምታውቅ በቀላሉ በአባቴ አታስፈራራኝም ።

አንድ ቀን ለስራ ክፍለ-ሀገር በሄደ በአራተኛ ቀን መኪና ተገልብጦ የአባቴ በድን በሳጥን ተጀቡኖ መጣ ። ሃዘን ሆነ ። እናቴ በጣም ስታዝን ገረመኝ ፤ ይመታት ፤ ይቆጣት ፤ ትፈራው አልነበር እንዴ ለምንድን ነው እንዲህ የምታዝነው አልኩ ።

ጊዜ ሄደ ። እናቴ ኑሮ በጣም ከበዳት ። አበራ የሚባል ፤ ሴት ወሲብ ብቻ የምትመስለው ሸፋዳ አገባች ።

ኑሮ ቀለል አለን ፤ አበራ ቸር ነው ገንዘብ አይሰስትም ።ነገር ግን ባዳው መሆኔን እይታው ይነግረኛል ። እናቴ ከሌለች ይጎነትለኛል ፤ ይተሻሸኛል ፤ ወደ ራሱ ይስበኛል

እናቴ ተሳቀቀች ። እኔም ቤታችን እናቴ ከሌለች
ያለመደኝ ተናካሽ ውሻ ያለበት ግቢ ነው የሚመስለኝ ። ከአቅሜ በላይ ሲሆን ፤ የጭቅጭቃቸው ምክንያት ስሆን ፤ ትምህርቴን አቋርጬ ፤ መስተንግዶ ገባሁ ፤ ጥንጥ ቤትም ብቻዬን ተከራየሁ ።

ለካ ሁሉም አበራ ነው። ትንሽ ያወራኸው ፤ ፈገግ ያልክለት ወንድ ሁላ እራት ልጋብዝሽ ፤ ሌላ ቦታ እንገናኝ ፤ እንቀምቅም ፤ ልሳምሽ ፤ እንዋሰብ እንመቻች ፤ ወሬያቸው ቢቋጭ ፣ ቢገመድ ፣ ቢሰፋ ከዚህ አይዘልም ።

የወንዶች መስገብገብ ነው ወሲብን ወንድ ብቻውን የተለየ ደስታ የሚያገኝበት ያስመሰለው። ፍትወታችንን ያፈዘዘልን መንቀዥቀዣቹ ነው ።

ከከስተመሮቼ ቃለዓብ ደስ ይላል ። ረጋ ያለ ። ትንሽ ፈገግታ ፤ ከትንሽ ቲፕ ጋ የሚሰጥ ነው። በጣም ከብዙ ጊዜ በኋላ ተግባባን ።መደዋወል መገናኘት አበዛን ። በአባቴ ፍርሃት እና በአበራ ሴሰኝነት ፤በከስተመሮቼ ሴት አውልነት ተፅዕኖ የተበጃጀሁት ቤተሳይዳ በቃለዓብ ምክንያት አንድ አንድ ወንድ አለ ማለት ጀመርኩ ።

ትንሿ ቤቴ ይመጣል ። ተስፋ ፤ ገንዘብ ፤ክብር ፍቅር ፤ ትርጉም ሰጠኝ።

ወደድኩት ።ያቺ የወንድ ገላ የሚሸክካት ቤተሳይዳ

ገላዬ ከገላው ሲነካካ ፤ ሰውነቴ ይለዋወጣል ይቅበዘበዛል ፤ ይከፋፈታል ። እቅፍቅፍ አደርገዋለሁ ፤ ጉያው ውስጥ እገባለሁ ፤ አንገቴን ሲስመኝ ደስታ መላ አካሌ ላይ ሲርመሰመስ ይሰማኛል። ስንራከብ እና ውስጤ ሲጨርስ ሃሴት ሲያጥለቀልቀኝ ከፀጉሬ እስከ ጥፍሬ እርካታ ይመዘምዘኛል ።

ቃለአብን ወደድኩት ። እንደዚህ ከሆን አምስት ወር ከሰባት ቀን በኋላ ።
ቃለአብ ድንገት ጠፋብኝ ፤ ፈለኩት የለም።
በህልሜ አየሁት ፤ ቃዠው ለፈለፍኩ ፤ በአይነ ስጋ ዳግም ማግኘት ግን አልተቻለኝም ።

እጦት ፤ ናፍቆት ፤ ፍቅር ፤ ስጋት ተባብረው ከደቆሱኝ ከትንሽ እለት በኋላ አንድ ጓደኛው ሚስቱ እና ልጁ ጋ አሜሪካ መሄዱን በማያጠራጥር መልኩ ነገረኝ ።

ማርያም ደጅ ሄድኩኝ እና ለምን አልኳት ፤ እንዴት አንቺ እያለሽልኝ ከክፉ ነገር አልጋረድሺኝም ። እንዴት አላጋለጥሺውም ፤ ነገሩ እንደሆነብኝ ቢሆንበት ፤ የዘራውን ቢያጭድ ፤ እሱ ይጎዳል እንጂ እኔ ስብራቴ አይድን!!

ምነው ማርያም? ምነው? ምነው ብርሃኔ ? ከስንት አፈ ጮሌ ፤ ከሰንት መደለያ ቁስ አስመልጠሺኝ ፤ ምነው ዛሬ ተውሺኝ ምነው ማርያሜ ?!
እንዴት አንቺ እያለሽ ያመንኩት ፤ ራሴን የሰጠሁት ሲያጠፋኝ ዝም አልሺኝ እያልኩ አነባው ፤ አዘንኩ ተደበትኩ ። አሁን ጠባሳው ልቤ ውስጥ ተሰንዷል"

አለችኝ

በገጠመኝ ባየሁት ፤ በሆነብኝ ምክንያት ወንድ አላምንም አለችኝ ። ብዙ ባገኘኋት ቁጥር ፤
የልቧን እውነት ባጫወተቺኝ ብዛት ፤ ከአባቷ ፣ ከእንጀራ አባቷ ፣ ከቦይፍሬንዷ በኋላ ፤ ዛሬም ፊት ለፊት የልቧን የሚሰማትን ልጅ ለማመን ዋዜማ ላይ ነች ። አንዳንድ ወንድ አለ ልትል ነው።

ማስታወሻ፦
ሰው መሆን እንዲህ ነው


ይሄ ሁሉ አንብባችሁ እማ👍👍👍👍 ተጫኑ
ጥላቻዬ ግንባሬ ላይ ቢነበብ የሚቀርበኝ አልነበረም። ጥላቻዬ አቅም ሲያገኝ ከሚያዘንበው በቀል ማን ይተርፋል ? ጥላቻዬንስ ማን ችሎ ያለዝበዋል?

ምቹ ግዜ ነው የምጠብቀው ። በእናቴ ሞት ምክንያት የቀዠበው አባቴን ካለ እናት ያሳደገኝን አባቴን ኮቴ እየተከተሉ ናላውን የዞሩትን የሰፈሩ ነዋሪዎችን አቂሜባቸዋለሁ ።

በልጅነቴ አባቴ የሚደበቅበት ሲያጣ ተመልክቼዋለሁ። ሳድግ አንደማስጥለው እየተኳላተፍኩ ቃል ገብቼለታለሁ።

እብድ ስሜት አልባ የማያስተውል ይመስላቸዋል ። እብድ የሚከፋው አይመስላቸውም ። እብድ ሃያ አራት ሰዓት ሙሉ የሚቀዥብ ይመስላቸዋል ።

ምን በድሏቸው ነው እንዲ እግር በእግር አየተከተሉ የሚያበሽቁት እያልኩ በልጅነቴ መልሱን ፍለጋ አስሻለሁ ።

በዓይኔ አባቴን የሚቆጣለት ፈልጌ አጥቻለው። ውለታ ለማይከፍሉ ጥብቅና የሚቆሙ ፃዲቅ አላገኘሁም ።

ሲናደድ ፤ ሲሳደብ፤ ሲጮህ ካጠገቡ ራቅ ብለው በሁኔታው ይዝናናሉ ። በሰው እንባ የሚስቁት ጤነኛ ተብለው አባቴ እንዴት እብድ ተባለ??

ስምምነት ብቻ እንዴት ሚዛን ደፋ ?

ጓደኛ ስለሌለው ይሆን ፤ መንገድ ላይ ከሚተነኩሱት እንዳድነው ይሆን ፤ስለሚወደኝ ይሆን ብቻ ካጠገቡ አይለየኝም ።

ያወራኛል። ስለእናቴ ይነግረኛል ፤ እንዴት እንደጠበሳት ፤ እንደናፈቀችው፤ የገዛላትን ውድ ስጦታ አይነት ይተርክልኛል ።
የሚያወራኝን ለእናቴ ያለውን ፍቅር ፤ ህልሙን የሚያጫውተኝን ሁሉ ብናገር ማን ያምነኛል ??

ከጓደኞቼ ጋር ጨዋታ ላይ ስንጣላ የእብድ ልጅ ብለው ሰድበውኝ ሶስት ልጅ ከፈነከትኩ በኃላ ድሮስ የእብድ ልጅ ብለው ቤተሰቦቻቸው ከኔ ጋ እንዳይጫወቱ ከለከሏቸው ፤ ሁሉም ፊት- ነሱኝ ።

የበዳይን ምክንያት ሳንጠይቅ በደልን ከመንጩ ማድረቅ እንዴት ይቻላል??

ሂደቱን ሳንመረምር በውጤቱ ብቻ እንዴት እንዳኛለን ?!

በቃ አባቴን ጓደኛዬ አረኩት ። ህመሙን መገፋቱን እያየው አደኩ ። አባቴን ከለካፊዎች ልከላከልለት ትንሽ ዓመት ሲቀረኝ ሞተብኝ ።

ስልጣን ፤ ገንዘብ ለማግኘት የምጓጓው ያቄምኩባቸውን በግላጭ ለማግኘት ነው።

ክፉ ባለስልጣን ፤ ግፈኛ ሃብታም፤ የሆነ ክፉ ሰው ሲያጋጥመኝ አባቱን ወይ እናቱን አሳብደውበት እየተበቀላቸው ይመስለኛል ። ሊበቀላቸው ስለተቻለው እቀናበታለሁ ።

ሁሉም የሚያስቀናው ነገር የተድቦለቦለው
በልጅነቱ በተዋቀረው ህልሙ መነሻ ነው
በኢያሪኮ ከተማ @Bemnet_Library.pdf
53.1 MB
ርዕስ=በኢያሪኮ ከተማ
ደራሲ=አዝርግ
 
  ማጋራት መተሳሰብ ነው!
📚 @ethioleboled
ናፋቂ ዜማዎች @Bemnet_Library.pdf
2.8 MB
ርዕስ=ናፋቂ ዜማዎች
ደራሲ=ዮሐንስ ፍስሀ
 
  ማጋራት መተሳሰብ ነው!
📚 @ethioleboled
የሸገር ወጎች @Bemnet_Library.pdf
25.6 MB
ርዕስ=የሸገር ወጎች(2005 ላይ የታተመ)
ደራሲ=ሰለሞን ታደሰ
 
  ማጋራት መተሳሰብ ነው!
📚 @ethioleboled
ወንዶች_ከማርስ_ሴቶች_ከቬነስ_ናቸው.pdf
25.5 MB
📚ርዕስ:- ወንዶች ከማርስ ሴቶች ከቬነስ ናቸው
👤ትርጉም:- አበባየሁ ወርቁ

📜ዘውግ:- የፍቅር ሳይኮሎጂ

📖የገፅ ብዛት:-  220

📆ዓ.ም

📚እንማር 📚📚☑️
እንደመደበርም እንደመሰልቸትም አድርጎኝ ነበረ።  ለመኖር ምክንያት አጣሁ ማለት ጀምሬ ነበረ።

እነዚህ ትናንሽ ሀሳቦች ቀኔን መረበሽ ጀመሩ ። ጠዋት መነሳትና ድጋሜ ሌላ ተመሳሳይ አድካሚ ቀን መዋል ትርጉሙ አልታይሽ ብሎኝ ነበረ።

ከዛ ግን ቀልቤን ገዛሁ የእናቴን እጅ አየሁት። ቆዳዋ ተሸብሽቦ ደምስሮቿ በጉልህ ይታዩ ነበረ። ደነገጥኩ ያ እንደዛ የሚያሳሱ ቀያይ እጆቿ አሁን መዳፎቿ ሳይቀሩ ጠቋቁረዋል።

ውሎዋን አየሁት እንደነገሩ ነው የምትለብሰው ያ ሁሉ መሸቀርቀር የት እንደ ሄደ ግራ ገባኝ። ፈጥና ያረጀችም መሰለኝ።

ከዛ ድግስ ተጠርተን ዘመድ ቤት ስንሄድ በእያንዳንዱ ነገር ላይ የምትሰጠውን የሰላ ሂስ ሰማሁ።

እቤት ስንገባ ጠየኳት ለምን ስራሽን ተውሽው እስካሁን በጣም ምርጥ ጭንቅላት አለሽ እኮ አልኳት በቁጭት

"ኤድያ ተይው ባክሽ ሁሉም ነገር ከቤተሰቤ አይበልጥብኝም" አለች

"እስኪ ተመልከቺ እንዴት ትናንሽ እንደነበራችሁ "በእጇ ህፃን ሆነን እኔና እህቴ የተነሳነውን ፎቶ ይዛ

"አሁን ያላችሁበት ደረጃ ለኔ ከምንም ነገር በላይ ነው" አለቺኝ በፈገግታ።

እንዴት እንደሆነ ባላውቅም መሰልቸቱ መደበሩ ቀርቶ ጭራሽ አዲስ ጉልበት ይሰማኝ ጀመረ።

ስለእሷ ማሰብ ከአልጋዬ ተስፈንጥሮ ለመነሳት በቂ ነበረ። እሷ መኖር ያቆመችው ለኔ ስትል አልነበር ስለዚህ እኔም የምልፈሰፈስበት ምክንያት አልነበረኝም።
ለኔ ማማር የሷ መጎሳቆል ይበልጥ አጠነከረኝ። በደንብ በኔ እስክትኮራ ድረስ...
🔵በአንድ ወቅት ባል ጠዋት ተነስቶ ወደ ስራው ሊሄድ እየተሰናዳ ሳለ ሚስት ትመጣና “ውዴ ሆይ ምነው ፊትህ ላይ ጥሩ ስሜት አይታየኝም ምን ሆነህብኝ ነው” ብላ ትጠይቀዋለች??

ባልም “እንጃልኝ ማሬ ዛሬ ለሊቱን ሙሉ ሲያቃዠኝ ፡ እንቅልፍ ባይኔ ሳይዞር ነው ያደርኩት። ድሮ ልጅ እያለው እናቴ በመኪና አደጋ ከመሞቷ አንድ ቀን በፊት ልክ እንደዛሬው ለሊት ሲያደርገኝ ስለነበር አሳስቦኝ ነውና ዛሬም ጥሩ ነገር ስለማይሸተኝ እባክሽ አንችም አንድ ነገር እንዳትሆኚብኝ ከስራ ቀርቼ አብሬሽ ልዋል?” ይላታል።

ሚስትም “ውዴ ሆይ አታስብ አትጨነቅ አንተ አብረሀኝ ዋልክም አልዋልክም ዛሬ ቀኔ ከሆነ ምንም የሚለወጥ ነገር አይኖርም ስለዚህ በቃ ወደስራህ ሂድ” ትለዋለች።

ባልም እየከበደውም ቢሆን በሚስቱ ሀሳብ ተስማምቶ ወደስራው ሄደ። እኩለ ቀን ላይም ምሳ ለመብላት ወደ ክበብ ሄደ ምሳውንም ለመብላት ሲሰናዳ ክበብ ውስጥ ካለው ቴሌቪዥን ውስጥ አንድ ሰበር ዜና ዓይኑን ሳበው

ዜናው እሱ የሚኖርበት የጋራ መኖሪያ ሰፈር በከፍተኛ የመሬት መንቀጥቀጥ መመታቱን ያትታል። በዚ ጊዜ ባል በከፍተኛ መሸበር እና መደናገጥ በፍጥነት ወደ ሰፈሩ በሩጫ አቀና።

አከባቢው ላይም ሲደርስ መንደሩ በፖሊሶች እና በነብስ አድን ሰራተኞች ተከቦ ያገኘዋል። ወደ ውስጥም ዘልቆ ሊገባ ሲል ባከባቢው የነበሩ ፖሊሶች እንዳይገባ ይከለክሉታል።
“እባካቹ አሳልፉኝ የልጅነት ፍቅሬ(ሚስቴ) ከውስጥ ነው ያለችው” እያለ መማፀን ጀመረ::
ፖሊሶቹም “አፓርታማው በጣም ስለተጎዳና ሙሉ ለሙሉ ሊፈርስ ስለሚችል ለህይወትህ አደጋ ነው ስለዚህ ማለፍ አትችልም” ይሉታል።

በዚ ጊዜ ባል “ከፈለጋቹ ተኩሳቹ ግደለኝ!” ይልና ፖሊሶቹን ጥሶ በከፊል ወደፈራረሰው አፓርታማ ዘልቆ ይገባል። ከብዙ ፍለጋና ልፋት በኋላም ሚስቱ በፍርስራሽ ተሸፍና ለመሞት እያጣጣረች ያገኛታል። ሊያወጣት ቢሞክርም በላያ ላይ ያለው የብሎኬት እና የሲሚንቶ ፍርስራሽ ብዙ ስለነበር ሊያወጣት አልቻለም።

ሚስትም እያቃሰተች የመጨረሻ ቃሏን እንዲህ ስትል ነገረችው “ውዴ አንተ የመኖሬ ምክንያት ነህ ። ዛሬ አንተ እውነተኛ አፍቃሪ እንደሆንክ በቃላት ድርደራ ሳይሆን በተጨባጭ በተግባር አሳይተኸኛል። ዛሬ አንተ ባትመጣ ኖሮ ሁለት ሞት እሞት ነበር። አንድም በአካል አንድም በመንፈስ። ነገር ግን አሁን አንተ ስለኔ ስትል ህይወትህን አደጋ ላይ ጥለህ ስለመጣህልኝ በመንፈስ ከመሞት ተርፌ በአካል ብቻ እሞታለው።” ቀጠለችና “ውዴ ጠዋት እንደነገርኩህ የፈጣሪ ትእዛዝ እስከሆነ ድረስ የመጣውን ሁሉ በፀጋ አለመቀበል ፈጣሪን መፈታተን ነው። ስለዚህ የእውነት የምትወደኝ ከሆነ ቀጥሎ የምልህን ነገር እህህህ ብለህ ስማኝ … “

ትንፋሽዋን ሰብሰብ አድርጋ “…እኔ ቀኔ ስለሆነ ለዘላለሙ ልሄድ ነው። አንተ ግን ሌላ ሚስት አግባ ልጆችም ውለድ።
ነገር ግን ይሄን ቃሌን ጥሰህ በኔ ሀዘን ተቆራምተህና እኔን እያሰብክ ቀሪ ህይወትህን የምታበላሽ ከሆነ ዛሬ እኔን የገደለኝ የመሬት መንቀጥቀጡ አደጋ ሳይሆን አንተ ነህ” ብላ የዘላለም እንቅልፍ አሸለበች

***
የሰሙትን የባሰ የሚሉትን ነገር ለመንገር ይሟሟታሉ።

ያያቸው ያያቸውና ይኸውላችሁ እኔ እኮ ነገሮች የሚያስገርሙኝና የሚያስደግጡኝን ደረጃ አልፌያለሁ ይላቸዋል።

ይገርማቸዋል ታድሎ ይላሉ። እንደ ጥንካሬ አድርገው ነው ያዩት ፤ እኔ ግን እንኳን ሊገርመኝ ደነገጥኩ በዛ ላይ አሳዘነኝ።

ቆይ ግን ሰው ምን ሲሆን ነው መደንገጥና መገረም የሚያቆመው ። ስንት ሰቆቃስ የደረሰበት ሰው ነው ልኩ የሚደርስበት? እንዴት ነው ስሜት አልባ መሆን ጥሩ ነገር የሆነው?
ተሰብስበን እያወራን ስለለከፋ ተነሳና ሁሉም በየተራ እንዴት እንደመረራቸው ማውራት ጀመሩ።

"በተለይ ማማዬ የሚል ወንድ በፈጣሪ"አለች ራሄል በምሬት ትከሻዋን እያርገፈገፈች።

"እሙዬ ፤ ቆንጅዬ ምናምን ሲሉ በቃ ድንጋይ አንስተሽ ግንባራቸውን በያቸው በያቸው ነው የሚለኝ" አለች ቆንጆ መሆኗን ያሳመነችን ጎደኛችን።

እኔ ግን ዝም አልኩ ተለክፌ አላቅማ። ያን ያህል መልከ ጥፉ እንኳን ሆኜ አደለም እኮ ብቻ ግን እንደነሱ እስኪመረኝ ቀርቶ አንዴ እንኳን አለመለከፌ ሀሳብ ውስጥ ይከተኛል።

በቀደም እለት እኮ ነው የሆኑ ሴቶች ተሰብስበው ቴሌቭዥን ላይ ቀርበው እየተቀባበሉ ያማርራሉ። አንዷ ምን ትላለች "ኢትዮጵያ ውስጥ ስለሆነ እኮ ነው እንጂ ሌላ ሀገር ለለከፋ ራሱ ማመልከት ማሳሰር ይቻላል በቃ ማንማ በየመንገዱ አያስቸገረንም አለች"

ሌላኛዋ ቀበል ብላ "አዪ ፖሊስ ያስጥለኛል እንኳን ብሎ ማሰብ ሞኝነት ነው። መቼ ለታ መንገድ ላይ አንዷን አንዱ ፖሊስ ይዟት ስልክሽን ካልሰጠሺኝ ብሎ ሲያስጨንቃት ነበረ።"አለች ሁሉም በግርምት ራሳቸውን ነቀነቁ።

ታድለው ከመቸገራቸው የተነሳ እኮ የፖሊስ እርዳታ እያስፈለጋቸው ነው።
ለመለከፍ
" ግን መስፈርቱ ምን ይመስላችኋል" አለች አወያይዋ "ምንም መስፈርት የለውም" አለች ከሁሉም ቀጫጫዋ "ቆንጆ ሆነች አልሆነች፤ ወፍራም ሆነች ቀጭን፤ ረጅም ሆነች አጭር ጉዳያቸው አደለም ብቻ ሴት ትሁን እንጂ ከነሱ አፀያፊ ቃል አታመልጥም። "አለች እየተውረገረገች።

እሺ ታዲያ እኔ ምን ሆኜ ነው? እንደው ለወሬም የማይመች ሰው አማክሩኝም የማይባል ነገር ሆሆ ቆይ እንድለከፍ ምን ላርግ ነው ምለው?
ውስልትና-ዘ-አዲስ_አበባ @Bemnet_Library.pdf
10.1 MB
ርዕስ=ውስልትና-ዘ-አዲስ_አበባ
ደራሲ=ሚልዮን ሹሩቤ
 
  ማጋራት መተሳሰብ ነው!
📚 @ethioleboled
#በቀጣይ

አለማችን ላይ ካሉ የራስ-አገዝ(Self-help) መጽሐፎች ውስጥ ተወዳጅ የሆነውን "The Principles and Benefits of change" የተሰኘውን የማይልስ ሙንሮ መጽሐፍ በአማርኛ እናቀርባለን።

መልካም ቆይታ!
📚 @ethioleboled
2024/11/14 12:26:35
Back to Top
HTML Embed Code: