☯ብርታትና ድካም፣ ውድቀትና ጽናትን
ለሚያፈራርቀው የሰው ልጅ ሚዛናዊ የሆነ ቃል በእጅጉ አስፈላጊ ነው፡፡ በጎ ጎኑን የምናደንቅለት ሰው ደካማ ጎን፣ ስለ መጥፎ ጎኑ የምንነቅፈው ሰው መልካም ጎን እንዳለው መረዳትም ብሩክ
የሆነ አስተዋይነት ነው፡፡ሚዛናዊነት በጎደለው አቋም ምንምና ማንንም አንለውጥም፡፡
☯ዛሬ ለምድራችን መከራ፣ የማያቋርጥ ስቃይ ትልቁን ድርሻ የሚይዘው ሚዛናዊነት የጎደለው
አመለካከት፣ ንግግርና ተግባር ነው፡፡ ምክንያቱም ሚዛናዊ ሰው አጥርቶ የሚያይ እውነተኛ፣ ለፍርድ
የማይቸኩል ትዕግስተኛ፣ ሰውንም በሆነው የሚቀበል ጥበበኛ ነው፡፡አንድ ዙር እስኪቀርህ ድረስ ሩጫውን እየመራህ ሳለ ያጨበጭብልህ የነበረ ሕዝብ መመራት ስትጀምር ቦታውን እየተወ ቢወጣ ምን ይሰማሃል? በእርግጥ ዓለም ከዚህ የተለየ ምንም ለማድረግ ፍላጎትም ሆነ አቅም የላትም፡፡
☮ብዙ ሠርተው የነበሩ ምንም እንዳልሠሩ፣ ብዙ ነገር ታግለው ያቀኑ በቦታው እንዳልነበሩ
ሲቆጠሩ ልባችን ታዝቧል፡፡ ከሁሉ በላይ ግን እምነት አለን በሚሉ መካከል ሚዛናዊነት ሲጠፋ ማየት ያሳፍራል።በአብዛኛው ቢወራልንና ብናወራ የምንወደው በኑሮ የበረታንበን፣ ታግለን የጣልንበትን፣ ተናግረን የረታንበትን ነገር ብቻ ነው፡፡ ለዚህም ይመስላል ቆመው አይደለም ሞተው እንኳን ስለ
ድክመታቸው እንዲወራ በማይፈልጉ ሰዎች ምክንያት በየቀብር ሥነ ስርዓቱ ላይ የሚነበበው የሕይወት ታሪክ የጥቂት እውነትና የብዙ ውሸት ድምር ውጤት የሚሆነው፡
☯የፍቅር ሰው ግን የእውነትና የማመዛዘንን በረከት የተረዳ ነው፡፡ ሕይወት የደስታና ሐዘን፣ የመልካም ዜናና የክፉ ወሬ፣ የሚያረኩ አጋጣሚዎችና ነፍስ የሚያስቱ
መሰናክሎች አስደናቂ ቅይጥ ናት፡፡ በመሆኑም አስቀድመን ይህንን እውነታ በተቀበልነው መጠን በተሻለ መልኩ ሕይወትን በጥበብና በማስተዋል መጋጠም እንችላለን፡፡ በመጨነቅ፣ በማዘንና በቅሬታ ለማሳለፍ ሕይወት በጣም አጭር ናትና ጨክነን ከእውነት ጋር መስማማት ይኖርብናል፡፡
☯ዛሬ ሁሉም ነገር ለመደሰት ሳይሆን ለመማረር፣ ለመቆም ሳይሆን ለመውደቀ፣ ለማረፍ ሳይሆን ለመቅበዝበዝ ብቻ ምክንያት እስኪመስል፤ ኑሮም ከሞት እንጉርጉሮ የከፋ፣ከነፋስ ሽውታ የሳሳ፣ ከማዕበል ሞገድ የጠለቀ፣ ከሕይወት ምሥጢር የረቀቀ እንደሆነ በማሰብ ጥቂት የማይባሉ ወገኖች በውስጣቸው ያለው ደም ተንጠፍጥፎ ያለቀ ያህል ተስፋ በመቁረጥ ውስጥ ይመላለሳሉ፡፡ ነገር ግን ብዙ ሕመምን ያስከተሉ ነገሮች ያላቸው መልካም ጎን ቢታወቅ ኖሮ ሐሴትን ይፈጥሩ ነበር፡፡
☮ሁሉም ነገር መልካምና መጥፎ ጎን ሲኖረው ቁም ነገሩ ያለው ግን ነገሮችን በመልካም ጎናቸው መጠቀሙ ላይ ነው፡፡ የአንድ ነገር ገጽታ እንደ ተመለከትንበት አቅጣጫ ይወሰናል፡፡ ስለዚህ ነገሮችን በሚዛናዊነት እንመልከታቸው፡፡
ውብ አሁን ❤️
@EthioHumanity
@EthioHumanity
✍ @ETHIOHUMANITYBOT

በዚህ በኩል ሳልፍ;
[ ይህችን ሰንበት ለዚህ ሰው ብንሰጠውስ😍 ]
ምን አልባት በሙሉ አፌ በደንብ አዳምጨዋለሁ የምለው አልበም የዚህን ሰው ነው!
ያምራል ሀገሬ👍
በዲጂታል የሙዚቃ መሣሪያ የተንቆጠቆጠውን የሀገሪቱን ሙዚቃ በክራር መስበር እንዴት ይከብዳል መሰለህ! ስለሺ ደምሴ ነው ክራር ገርፎ ብቻ መዝፈን እንደሚቻል ያሳየን!
ሰውየው ያዝናናልም ያስተምራልም! ለዛ ቢስ የምትለው ሰው አደለም! ከማንም ያልተቀዳ የራሱ ለዛ አለው ሰውየው!
በአንቺአሮ❤
ኢትዮጵያ የምትባለውን ሀገር በጣም በተሻለ መንገድ በሚጣፍጥ ለዛ ባልተሄደበት መንገድ የሚያስተውላት ይህ ሰው ነው! ከድምፃውያን የኢትዮጵያን ሳሎን ፈትፍቶ ያውቃል ከምላቸው አንዱ ነው! ስለሺ👍
ለምሳሌ ያህል-
ራያ ነው ራያ ነው
ራያ ነው ጎበዝ እርሻው ማሽላ ነው
ከሰሜን ትግራይ ነው
እህ ዲ ዲ ዲ [ እኚህ ድምፆች ከባድ ማጣፈጫ ናቸው]
ከደቡብ ሸዋ ነው
አሃ ዲ እህ ዲ
ከምስራቅ ሐረር ነው
አሃ እህ ዲ
ከምዕራብ ላስታ ነው
አሃሃ ዲ
ዞብል አዋሳኙ አፋር ድንበሩ ነው🤔
አየኸልኝ የስለሺን መገለጥ! ኪነት ይህች ናት! የማህበረሰብ ስብጥርን እንዲህ ለማየት የቻለው ጋሽ አበራ ሞላ ነው!😍
[ የማንነት አስመላሾችን አይመለከትም🙄 ]
ከእጅጋየሁ ሽባባው ለጥቆ ' አባይ ' ን የገለፀው ይህ ሰው ነው! ባልተሄደበት መንገድ! ክችች ባላለ አማርኛ😍
ጎጃም❤
ስለሺ ባለ-ከባድ ሚዛን ከያኒ ከሚያደርጉት ምክንያቶች ውስጥ ገለፃው ነው! የስለሺ ቋንቋዎች ስዕሎች ናቸው! በሙዚቃው የሚተርካቸው ትረካዎች ራሳቸውን ችለው የሚቆሙ ታሪኮችም ናቸው😍
ምንትዋብ❤
አንዱን የሀበሻን ማህበራዊ ትስስር የሆነውን ትዳርም ስለሺ ቃኝቶታል! ' የሠርጌ ለታ ' ብሎ በተለየ ዕይታ😍
ያ መጋሌ❤
ፍቅርን ውበትን ከፊደል ገበታ ጋር አቆላልፎ የተራቀቀብን ማነው🤔 ጋሽ አበራ ሞላ ነው😍
አዚላ❤
ብቻ እንዲሁ ለመነካካት ያህል እንጂ ለመዘየር እንጂ ሰውየው ብዙ ነው ነፍ ነው...
በረዥሙ ቁመቱ እና በረዥሙ እሁድ እኔም ላለመርዘም እንጂ🙄
📝ኖሀ ዘ አድዋ
@Ethiohumanity

❤️በባህር ዳር ላይ የሚበቅሉ ዛፎች፤ አውሎ ንፋሱን የሚቋቋሙት፤ ጎንበስ በማለት ነው። እንዚህ ዛፎች ግትር ብለው ቢቆሙ እጣ ፋንታቸው በአውሎ ንፋሱ መሰበር ነው። ጎንበስ ማለታቸው የመኖራቸው ሚስጥር ነው።
📍 የሰው ልጅ ህይወትም ከዚህ አውሎ ነፋስ አያመልጥም፤ ጎንበስ ካላላን ሰብሮን የሚያልፍ ከባድ ነፋስ አለ:: ማጎንበስ የመሸነፍ ምልክት አይደለም፤ በአንጻሩ የብልህነትና ልዩ የሆነ የማሸነፍ ጥበብ ነው። ነገሮች እኛ ካሰብናቸው ውጪ ሲሆኑ፤ ጎንበስ ማለትን እንደመሸነፍ አንቁጥር።
ማጎንበስ መሰበር አደለም !
ውብ አዳር ❤️
@Ethiohumanity
@Ethiohumanity
✍️@Ethiohumanitybot

ለእሁዳችን!
💚
እስቲ ደሞ እንቦጭቅ;
ሐበሻ በጣም ሲወድህ ስምህን ያሳጥረዋል! አሳጥሮ መች ይተውና ' ዬ ' የምትል ጣፋጭ ተቀጽላ ይሰጥሀል።
ቁልምጫ የትም የሌለች የሀበሻ በረከት ነች! ስለዚህ እኛም እንላታለን- ብዙዬ❤
ቀጭን በጣም ቀጭን እንደ ክር ሊበጠስ የደረሰ የድምፅ ባለቤት! ከሆዷ ነው ከአንጀቷ ወይስ ከጉሮሮዋ ይህ አጃኢብ ድምፅ የወጣው🤔 ትላለህ ብዙዬን ልብ ብለህ ካደመጥካት!
' የሩቅ ሰው አፍቅሮ በስሜት መንከፉ
ላያዛልቅ ፍቅር ትዝብት ነው ትርፉ ' ትላለች ብዙዬ ስርቅርቅ በሚለው ድምጿ😍
ብዙዬ የሐረር በረከት ነች! በረከቷ ግን ሐረር ላይ ብቻ ተቀርቅሮ አልቀረም! መላው ሀገርን በድምጿ ወረዋለች! እኔ ድረስ የሚደርስ ወረራ!
የስመ-ጥሩ ደራሲ የበዓሉ ግርማ ፍቅር ነች ብዙዬ😍 ምን አልባትም የበዓሉ ትንታግ ብዕሮች የሚመዘዙት በብዙዬ ውብ ዜማ ነው! ብዙዬን ካላያት ይደብተዋል! ድምጿን ካልሰማ ይጨንቀዋል!
' ብዙዬ ' ይላታል!
' ወዬ በቃሉዬ ' ትለዋለች። በቀጭን ድምጿ!
' እባክሽ ውዴ አንጎራጉሪልኝ ' ይላታል።
ታንጎራጉራለች! አይኑን ጨፍኖ በሠመመን ያደምጣታል! ወደ ሆነ ቦታ ትወስደዋለች! የፁሑፍ ሐድራው ይወርድበታል!
የእግዜር መልካም ፍቃድ ቢሆን አስማታዊ መስታጋብር ነበር። ድምፅ እና ቃል😍
ጭንቅ ጥብብ😍 የእናት ውለታዋ😍 ደህና ሁን😍 የጎረቤት ልጅ😍
ብዙዬ በሁለት ቋንቋዎች አሳምራ ትዘፍናለች! በአማርኛም በኦሮምኛም!
የዘመን ጓዶቿ የእሷን ትዝታ ሲያወሩ ሁሉም በተመሳሳይ ነፃ ጨዋታ አዋቂ እና ደግ ናት ይላሉ! ድሮስ ሐረር አደለች😍
ብቻ ዛሬም ነገም የሚመጣው ትውልድ ሁሉ እንዲህ እንደሚጠራት አልጠራጠርም-
ብዙዬ❤ ብዙዬ❤ ብዙዬ❤
📝ኖሃ ዘ አድዋ

ለውብ ቀን!
💚
የኦሽዊትዙ ሰው..
በጦር ወንጀለኝነት፣ በሰው ልጅ ላይ አሰቃቂ ሳይንሳዊ ሙከራዎችን በማድረግ፣ ጤነኛ ሰዎችን ለምርምር ሲባል በበሽታ አምጪ ባክቴሪያዎች በመበከል፣ የሚገደሉና ለምርምር የሚውሉ ሰዎችን በመለየት ሂደት ውስጥ በመሣተፍ፣ ወዘተ የሚሉ መዓት ዓይነት አሳቃቂ ክሶች የቀረበባቸው 40 ሰዎች ነበሩ።
ሰዎቹ የሰው ግዞት፣ ጉልበት ሥራና የሰው ምርምር በተካሄደበት በአሰቃቂው የኦሽዊትዝ የሞት ካምፕ ያገለገሉ የናዚ አባላትና ቅጥረኞች ናቸው። ናዚ ሲገረሰስ በአሜሪካኖቹ እጅ ወደቁ።
አሜሪካኖቹ ደሞ የሚመርጡትን መርጠው፣ የሚፈልጉትን ምርመራ አድርገው፣ 40ዎቹን የኦሽዊትዝ የሞት ባልደረቦች ለፖላንዶች አሳልፈው ሰጧቸው።
የፖላንድ ቤተእስራኤሎች ደሞ ዋነኛዎቹ የናዚ አራዊት ተጨፍጫፊዎች ናቸው። ከጦርነቱ በፊት በፖላንድ ከ4 ሚሊየን በላይ ትውልደ-እስራኤል ዜጎች ነበሩ። ጦርነቱ ሲጠናቀቅ በህይወት የተረፉት 350 ሺህ አይሞሉም።
ከ3.5 ሚሊየን በላይ አይሁዶች በ5 የተለያዩ የመግደያ የግዞት ካምፖች እየተወሰዱ ነው የተጨፈጨፉት። ይህ ማለት ከመቶው 98 ፐርሰንቱ እስራኤላዊ ከምድረ-ገፅ እንዲጠፋ ተደርጓል። (በዘመናዊዋ ዓለም እንደ ናዚ ዘረኛ ምሁራን በንፁሃን ደም የተጨማለቀ አረመኔ ኡመክ ታይቶም ተሰምቶም አያውቅም።)
ለፖላንዶች ተላልፈው የተሰጡትና በዋና ከተማዋ (ከዋርሶ በፊት) በክራኮ ክሳቸው የተደመጠው እነዚያ 40ዎቹ ናዚዎች ዶክተሮች አሉባቸው። ሳይንቲስቶች። የተማሩ የተመራመሩ ኡመክ የሚለውጨቃል የማይገልፃቸው አረመኔ ምሁሮች ናቸው።
ሁሉም ሞት ተፈረደባቸው። ከአንዱ በስተቀር። በናዚ የፍርድ ሂደት ታሪክ ውስጥ፣ በሰው ዘር ማጥፋትና በሰው እንደ አይጥ በመጫወት ተከስሶ፣ በነፃ የተሰናበተ ብቸኛው ሰውም ሳይሆን አይቀርም ይሄ ሰው።
የህክምና ዶክተር ነው። ዶክተር መንች ይባላል። የወጣለት ባክቴሪዎሎጂስትም ነው። ገና በኮሌጅ ተማሪ እያለ ነው የናዚ አባል የሆነው። ጦርነቱ ሲጀመር ካላዘመታችሁኝ ሞቼ እገኛለሁ ብሎ፣ ግን ዕውቀትህ እጅግ ጠቃሚ ስለሆነ አትዘምትም ተብሎ ነው ወደ ኦሽዊትዝ፣ በሳይንቲስትነት ማዕረግ ተመደበ።
(የኦሽዊትዝ ምሥጢር የሚል መፅሐፍ ከፃፈውና በመንታ ህፃናት ላይ የላብራቶሪ ምርምር ያካሂድ ከነበረው ከዶክተር ሜንጌሌ ጋር በባልደረባነት አብሮ ሠርቷል)።
ብዙዎች የናዚ ወንጀለኞች ክስና ፍርድ ተራ በቀል ነው፣ አይሁዶች ተጨፈጨፈፉ የሚባለውም ውሸት ነው ሲሉ ይደመጣሉ። ...
ሌሎች ብዙዎች ግን የህግን ልፍስፍስነት ሲረግሙ ነው የሚገኙት። ያንን ሁሉ ግፍ ለፈፀሙ የሰው ሥጋ ለብሰው የዲያቢሎስን ሥራ በፍቅር ሲከውኑ ለነበሩ እነዚያ የናዚ አውሬዎች የሚገባቸው ቅጣት ሞት ብቻ ነው ወይ? ህግ የሚባለው ነገር ከቅፅበት ሞት የበለጠ (የከፋ) ቅጣት የለውም ወይ? ብለው። መፈክር ሁሉ ይዘው ወጥተው ህጉን ረግመዋል።
ሁሉም ናዚ የዲያብሎስ ደቀመዝሙር ነው ባይባልም፣ የኦሽዊትዞቹን የኤስ ኤስ የናዚ መኮንኖችና ቅጥረኞች ግን ዲያብሎስ ራሱ የሚቀናባቸው ከሠይጣንም የባሱ አረመኔ ኡመኮች ናቸው።
ይሄ ዶክተር ግን ከኡመኮቹ ተለይቶ ተገኘ። ትንሽ ሰብዓዊ ህሊና ተገኘበት። ከናዚ ፓርቲ ቃልኪዳኑ ይልቅ ቃል ለገባለት ለሂፖክራቲክ ቃለኪዳን አድልቶ ተገኘ።
በኦሽዊትዝ አዲስ ከሚራገፉ አይሁዶች መሐል ለጉልበት ሥራ የሚሆኑትን፣ ለህክምና ምርምር የሚሆኑትንና በእርጅናቸው ወይ በህፃን ዕድሜያቸው የተነሳ ወይ ደግሞ በአቅመ-ቢስነታቸው ተስፋ የሌላቸውንና ወዲያው ወደ መርዝ ጋዝ መገደያ የሚላኩትን እንዲለይ ተመደበ።
ይሄ ዶክተር ግን ትዕዛዝ ባለመቀበሉ የሚደርስበትን ለመቀበል ቆርጦ (ህይወቱን ሸጦ) የተሰጠውን ግዳጅ አልቀበልም ብሎ ፀና። እና ታሪኩና የናዚ ፍቅሩ ተጠንቶ ተረፈ።
እና ከኦሽዊትዝ አጠገብ የሚገኘው የበሽታ አምጪ ሚክሮብስን ለማጥናትና ለመጠቀም በሰው ልጆች ላይ ምርምር የሚያደርገው ኢንስቲትዩት ሀላፊ ተደርጎ ከኦሽዊትዝ ዘወር ተደረገ።
በዚያ ላብራቶሩ ውስጥ ሆኖ ብዙ ትውልደ-እስራኤሎችን ለምርምር ይላኩልኝ እያለ ከኦሽዊትዝ የሞት ካምፕ በብዛት እያስመጣ ከጋዝና ከምድጃ አፍ አትርፏቸዋል። የታመሙትን በምሥጢር እያከመ አድኗል። ብዙዎች እንዲያመልጡ ረድቷል።
ብዙዎች መሠከሩለት። ታሳሪዎች፣ ተጋዦች፣ ከሞት ያስመለጣቸው። እና እርሱም በፀፀት ያደረገውን አመነ፦
"ብዙዎችን ለማዳን፣ ሌሎች ጥቂቶችን
መግደል ነበረብኝ፣ ጥቂቶችን ለሞት
ዳርጌ ብዙዎችን አትርፌያለሁ፣ ማድረግ
የምችለው ያ ነበር፣ አለበለዚያ ሁላችንም
ያልቅልን ነበር።"
ታማኝነቱን ለማረጋገጥ ዓይኑ እያየ በሰዎች ላይ ዘግናኝ የአይጥና የዝንጀሮ ምርምር ሲካሄድ መተባበር ነበረበት። ግን ህሊና አለውና ብዙዎችን አዳነ። እና ብቸኛ ባለ ህሊናነቱ፣ ብቸኛው ነፃ ሰው አደረገው። ክሶቹ ውድቅ ተደርገውለት፣ በነፃ ተለቀቀ።
በነፃ መለቀቀ ብቻ አይደለም። የህክምና ፈቃዱም ተመለሰለት። መፅሐፎችና ፊልሞችም ተሠርተውለታል። "The Good Man of Auschwitz" (የኦሽዊትዙ መልካም ሰው) የሚል መጠሪያ ስምም ወጥቶለታል። በብዙ ችሎቶችና ሕዝብ አዳራሾች እየተገኘ "ያለፈው እንዳይደገም" ምስክርነቱን ሰጥቷል።
አንዳንዴ የፈለገው መጥፎ ሥራና መጥሰዎች ቢከብቡህ፣ ህሊና እስካለህ ድረስ፣ ከመጥፎዎች መሐል ሆነህ ጥሩ መሥራት እንደምትችል፣ ከዚህ ሰው ህይወት መማር ይቻላል።
ሰሞኑን ያየሁትና የመሰጠኝ አንድ አባባል ነበር፦ "መርከቡ የሚሰምጠው በውሃ በመከበቡ የተነሳ አይደለም፣ ውሃው ወደ መርከቡ ውስጥ ሲዘልቅ ነው የሚሰምጠው" የሚል አባባል።
ታዲያ ይህ እውነት ለሰውም የሚሠራ ይመስለኛል። የፈለገውን ያህል በመዓት እርጉሞች ተከብበህ የምትንቀሳቀስ ሰው ብትሆን፣ ክፋታቸውን ወደ ውስጥህ እስካላስገባኸው ድረስ በእርጉምነታቸው አትለከፍም። ውስጣቸው ሆነህ፣ ክፋታቸውን መታገል ትችላለህ። ክፋታቸው ንፁህ ህሊናህን እንዳያጨቀየው፣ ሌላውን ባትችል ራስህን ማዳን ትችላለህ። ለዛሬው ታሳሪህ ብትራራለት፣ የዛሬ ታሳሪህ የነገ አስፈቺህ ይሆናል።
በዘመነ ኢህአዴግ ባለፍንበት የልዩ አቃቤ ህግ የዘር ጭፍጨፋ ክስ አሳዛኝ ድራማ መሐል፣ አንድ እየተማረረ በልዩ አቃቤ ህግነት ይሠራ የነበረ አቃቤ ህግ ወዳጄ ያጫወተኝ አሁን ትዝ አለኝ።
ከተከሰሱት የደርግ (ወታደራዊው) መንግሥት ባለሥልጣናት የአንዱ ክስ ሂደት እየተደመጠ በነበረበት ወቅት፣ ወሬውን የሰማ አንድ ምስክር ማንም ሳይጠራው በራሱ ተነሳሽነት ከእንግሊዝ ሀገር ድረስ በርሮ አዲሳባ ልዩ አቃቤህግ ቢሮ መጣ። ምን ሊመሠክር?
ይሄ ባለሥልጣን በቀይሽብር ወቅት የእስርቤት ውሳኔ አስፈፃሚ ሆኖ በኃላፈፊነት ሲሠራ፣ እኔ ተወስኖብኝ ልረሸን በጭለማ ወደ እንጦጦ ተወሰድኩ። ነገር ግን ይህ ሰው ጥይቱን ወደ ድንጋዩ አከታትሎ ከተኮሰ በኋላ፣ ደርቄ በቀረሁበት ወደ ጆሮዬ ጠጋ ብሎ፣
"በል ሳትገላመጥ ሸምጥጠህ ሩጥ።
ለዛሬ አትርፌሀለሁ። ተመልሰህ ብትያዝ፣
እኔንም ጭምር ነው የምታስገድለኝ። አሁን
ጥፋ ከፊቴ!"
"ብሎ ከሞት አትርፎ አባረረኝ። አያውቀኝ። አላውቀው። ወጣትነቴ አሳዝኖት ብቻ ነው። በተሠጠው ትዕዛዝ አላመነበትም። በዚያው ካገር ኮበለልኩ። ሱዳን ስደተኛ ካምፕ ሆነን ከዚህ ካመለጡ ኢትዮጵያውያን ጋር ስናወራ፣ ይህ ሰው በዚህ መልክ ከሞት አፋፍ ያስመለጠን ሶስት ሰዎች ነበርን። ስሙን ያወቅኩትም እዚያ ነው።...

"ብዙ ዓመታት አለፉ። የአራት ልጆች አባት ነኝ። ይህን ሰው ሁሌ አስበዋለሁ። በቅርቡ መከሰሱን ሰማሁ። እና ለሀቅ መመስከር አለብኝ ብዬ፣ ልጆቼ ይቅርብህ እያሉኝ፣ ልመሠክርለት ነው የመጣሁት። ለልጆቼ ያልኳቸው አንድ ነገር ነው፣ ይህ ሰው ባይኖር፣ እናንተ አትኖሩም ነበር ብዬ። ይህን ሀቅ ለመመስከር መጥቼያለሁ። ከዚህ በኋላ የሚፀፅተኝ ነገር የለም። ከነፃ ህሊናዬ ጋር መኖር እችላለሁ።"
ብሎ ለአቃቤ ህጎቹ ተናዝዞ ወደመጣበት እንግሊዝ ውልቅ። ከዚያስ? ለኢህአዴጎቹ (ለአንቱዎቹ ባለሥልጣናት) ጉዳዩ በውስጥ መስመር ተላለፈ። ሰውየው ለጥቂት ጊዜያት እስኪበቃው ታሽቶ፣ ከሌሎች ተከሳሾች ቀድሞ ተለቀቀ።
ኧረ ቆይ ለመሆኑ ያ (የሩቅ) ወዳጄ የነበረ ልዩ-አቃቤ ህግስ? በሥርዓቱ ግፍ እየተማረረ የደርግ ባለሥልጣናቱን ማለቂያ የሌላቸውን ምሥክሮች እያሰማ በእስር ማሰቃየቱን ቀጠለ? እስከተወሰነ ጊዜ አዎ። ከዚያስ?
ከዚያማ የፈለገው ጥቅማጥቅምና ሥራ በአፍንጫዬ ይውጣ ብሎ አቃቤህግ መሥሪያቤትን ለቅቆ ጥብቅና አወጣ። እና ወንጀለኞችን የሚከላከል ዕውቅ ጠበቃ ሆነ። አንዴ ታግዶ፣ ሌላም ጊዜ በሰበብ አስባቡ እስከመታሠርም ደርሶ ነበር። ግን ለመጨረሻ ጊዜ ሳውቀው ስምና ብር ነበረው። ከጥሩ ህሊና ጋር። አሁን የዘር ነገር ስቦ ለጊዜው ሥርዓት ካላስገበረው ደግሞ ዕድለኛ ሰው እለዋለሁ።
የዚህ ሁሉ (ዳውላ ሙሉ) ታሪክ ጭብጡ ምንድነው? ከክፉዎች ተለይ። በክፉዎች መሐል ስትሆን ክፋት ወደ ውስጥህ እንዳይገባ ተጠንቀቅ። ከዘረኞች መሐል ሆነህ፣ ከበቀለኞች መሐል ሆነህም፣ ከአረመኔዎች፣ ከባለጊዜዎች መሐል ሆነህም - የራስህን አንዲት መልካም ነገር ዝራ። አንድን ሰው በመልካም ሁኔታ አስተናግድ።
አንዳንዴ አንድ ሰው በቂ ነው። አንድን ሰው ከግፍ አትርፍ። አንድን ሰው አድን። አንድን ትግል ታገል። ጥሩ ሥራ እንደ ውሃ ኩሬ ነው። በመጨረሻ ውሃው ወደቤትህ ይመጣል። ያላሰብከውን የዳክዬ ሲሣይ ይዞ።
"ጥሩነት ለራስ ነው"። ለራስ ጤንነት። ሰውነትን፣ ሰብዓዊ ህሊናን ለማንፃት እንደ ጥሩነት ያለ ፍቱን መድሃኒት የለም። የትም ሁን፣ የትም ተወለድ። በጥሩነት ክፋትን ድል መንሳት ትችላለህ። እንደ ኦሽዊትዙ መልካም ሰው። እንደ ዶክተር ዊልሄልም መንች።
ማሳረጊያ፦
በጣም የሚያሳዝነው፣ ይሄ ባለ ታሪኩ ዶክተር (ዶክተር መንች) በ89 ዓመት ዕድሜው ላይ (በ2001 ዓመተጠምህረት ላይ ከመሞቱ ከሶስት ዓመት በፊት) የAlzheimers (የመርሳትና የመምታታት) በሽታ ያዘው። የቤቱን ወንድና ሴት ድመቶች መለየት እንኳ እስኪሳነው።
በዚህ መሐል አንድ የተረገመ🙂 ጋዜጠኛ ቤቱ ድረስ ሄዶ የShindler's List የሚለውን ከእርሱ ታሪክ ጋር ተያያዥነት ያለውን ስለ አንድ የናዚ አባል ሆኖ ሳለ ሀብቱን አንጠፍጥፎ ብዙ ጂዊሾችን በማትረፍ መልካም ውለታ ስለሠራ ሰው የሚያወሳውን የ3 ሰዓት ፊልም አሳየውና ቃለመጠይቅ አደረገለት።
በዚያ ቃለመጠይቅ ዶክተር መንች በስተርጅና "በናዚ ይካሄድ የነበረው በሰው ልጅ ላይ የተደረገ ሙከራ አስፈላጊና ጠቃሚ ነበር፣ አሁንም ዕድሉ ቢሰጠኝ አደርገዋለሁ፣ በኦሽዊትዝ የተራገፉ ሰዎችን በመምረጥ ሂደት ውስጥም ነበርኩበት" በማለት ቃሉን ሰጠ። ቃለመጠይቁ በመፅሔት ሲሠራጭ በመላ ዓለም ያሉ ባተእስራኤላውያንን ቁጣ ቀሰቀሰ። በዚህ ብቻ አላበቃም።
ሌላ ቀደም ብሎ ለራዲዮ ፍራንሴ የሰጠው ቃለመጠይቅም ወጣ። ሮማዎችና ሲንቲዎች የተባሉትን አሁን ከናዚ እልቂት ተርፈው በጀርመን (በአውሮፓ) የሚኖሩ ቁጥራቸው በመቶ ሺህዎቹ የሚገመቱ ነገዶችን በተመለከተ አስተያየቱን ሲጠየቅ፦ "ለእነሱ በትክክልም የሚገባቸው ያ የኦሽዊትዝ የጋለ ምድጃ ነው፣ ያ ነው የመጨረሻውና ብቸኛው ፍትሃዊ መፍትሄያቸው" - ብሎ እርፍ።
አዪዪዪዪ...! የት ይደርሳል ያሉት...! ክንፍ የሌለው መልዓክ ያሉት.... ከሠሩ። ክሶች በያቅጣጫው ተወነጨፉበት። ፈረንሳዮቹ በሌለበት ጭምር ፈረዱበት። ግን በእርጅናው እና በመርሳት በሽታው ምክንያት ቅጣቱ ሳይፈፀምበት ቀረ።
ቃለመጠይቅ አድራጊዎቹን የሚወቅሱም አልታጡም። ቢተዉትስ ይሄን የደከመ ሽማግሌ?! በሚል። አመል አይለቅም። አልዛይመሩ ጎልጉሎ አወጣበት ያሉም አሉ።
ወንድ ልጁ በመጨረሻ በሚዲያ ፊት ቀርቦ፦ "አባቴ መልካም ሰው ነው። በህመሙ የተነሳ የሚናገረውን ይዛችሁ አንድን አዛውንት ለማዋረድ በመነሳታችሁ ከልብ ያሳዝነኛል።" በማለት የመረረ ብሶቱን አሰማ።
ሰሙት መሠለኝ። ሁሉም ተዉት። የናዚው ሳይንቲስት። የኦሽዊትዙ መልካም ሰው። አወዛጋቢው። በበኩሌ የመልካምነት ምሣሌ ላደርገው የወደድኩት ሰው። ያመሠገኑትን ሰዎች አወዛግቦ፣ በ92 ዓመቱ ሞተ። አረፈ። ተገላገለ።
ይህ ሰው። እንደ ማንኛውም ሰው። ታሪኩ በሞት ተቋጨ። ግን ሞት የሰው ታሪክ መጨረሻ ነው እንዴ? ሞት ሁሉን ግብራችንን ይዘጋዋል? - አይመስለኝም! ከሞት በላይ ምን አለ? ስም!!! ስም የሚባል ነገር!!!
ዶክተር ሃንስ ዊልሄልም ኧርነስት መንች። የሚገርም ስም!
ስም ከመቃብር በላይ ይኖራል።
አበቃሁ።
📝አሰፋ ሀይሉ

ለጁምኣችን!
💛
'ጦርነት' ማለት ምን ማለት ነው? (እውነተኛ ፍቺው?)
ጦርነት ማለት፦
"አሳምረው የሚተዋወቁ፣ የሚጠላሉና ቅራኔያቸውን በሠላም መፍታት ያልቻሉ፣ ዕድሜያቸውን ያመነዠኩ ሰዎች - የማይተዋወቀውን፣ የማይጠላላውንና ቅራኔውን በሠላም ለመፍታት የማይገደውን ወጣት፣ በሠላም ከተቀመጠበት ከሞቀ ቤቱ ጠርተው፣ እርስበርሱ የሚያጨፋጭፉበት የተረገመ መንገድ ነው"
"War is an abominable situation in which old people, who knew each other, hate each other, and failed to solve their problems peacefully, would drag the young people, who do not know each other, who do not hate each other, and who are willing to make peace with each other, to kill each other."

🕰Invest in yourself
" ለሰው ልጅ ሁሉ እኩልና ያለስስት የተሰጠ ሀብት ቢኖር ጊዜ ነው ። ጊዜህን መጠቀም ስትችል እራስህን ትለውጥበታለህ...ራሥህን መለወጥ ሥትችል ሌሎችንም ትለውጣለህ ። ራስህን ለመለወጥ ጊዜን ካልወሰድህ ሌላን መለወጥ አትችልም ። ( Invest in your self )ራስህ ላይ ፈሰስ አድርግ መጀመርያ ራስህን ለውጥ ።
አስተሳሰብህን ሞርድ ፣ እይታህን አጥራ ፣ ንግግርና እርምጃህን ገምግም ነገ የሚኖርህ ዛሬን ስትጠቀምበት ነው ። ከዛሬም ያለህ ጊዜ አሁን ነው...አሁን ደግሞ እያለፈ ነው! ጥያቄው እንዴት እያለፈ ነው የሚለው ነው ። ለዚህ ጥያቄ የምትመልሰው መልስ #ነገ በምትለው ምናባዊው ቀን ላይ ያለህን አንተነት ይወስነዋል ። "
ዛሬህን ተጠቀምበት...
ዉብ አዳር❤️

🔆እኔ ነኝ ተጠያቂው በል
ለምታገኘው ደስታም ሆነ ለሚደርስብህ ችግር ተጠያቂው አንተና አንተ ብቻ ነህ ማንም ላንተ ህይወት ሃላፊነቱን አይወስድም...
የራስህን ገነት የምትገነባውም ሆነ እራስህን በገሃነም እሳት የምትጥለው አንተ እና አንተ ብቻ ነህ ።
ውብ አሁን ❤️
@EthioHumanity
@EthioHumanity
✍️ @Ethiohumanitybot

ለቅዳሚታችን!
❤
ምርጥ 50 ፊልሞች ከዓለም ዙሪያ
============================
ከዚህ በታች ያስቀመጥኳቸው 50 ፊልሞች (movies) በተለያዩ ወቅቶች ተመልክቼያቸው እጅግ ግሩም ቁምነገር ያገኘሁባቸው፣ ያዝናኑኝና፣ ለየት ብለው ያስደመሙኝ ምርጥ ፊልሞች ናቸው።
ምርጥ የምላቸውን ፊልሞች ሳካፍል ይህ ለ3ኛ ጊዜ ነው። ፊልም የማየት ፍቅሩና የተመቻቸ አጋጣሚው ያላችሁ፣ እነዚህን ፊልሞች ጊዜ ሰጥታችሁ ተመልከቷቸው።
በበኩሌ ፊልሞች ከመፅሐፎች ባልተናነሰ ብዙ ግርምትንና ትምህርትን ይሰጡኛል። ከፊልሞች ተለይቼ አላውቅም። እና ዓለምን ካጥለቀለቁ ከሺህዎች መሐል አይተን ያደነቅናቸውን ምርጦቹን እየቀዳን እንካፈል።
አሉኝ የምትሏቸው ምርጥ ፊልሞች ካሉ በcomment ላይ አክሉልኝ። ቀጣዩ 4ኛ ዙር የምርጥ ፊልሞች ዝርዝር ደግሞ ከተወሰኑ ሳምንታት በኋላ ይቀጥላል።
በተለየ ለማስታወስ ያህል፦ እንደ ከዚህ በፊቶቹ የፊልም ዝርዝሮቼ ሁሉ፣ በዚህ በ3ኛው ዙር ዝርዝር ውስጥም ሶስት የአማርኛ ሙቪዎች ተካተዋል። ከሶስቱም ላይ የተለየ ግሩም ለዛ አግኝቼባቸዋለሁ።
Lucy የሚለው ድንቅ የmind evolution ፅንሰ ሀሳብ ይዞ የተነሳው ፊልምም መነሻውና መድረሻው የእኛዋ ሉሲ (ድንቅነሽ) ነች። የሀገርኛዎቹንም ሌሎቹንም ልክ እንደ እኔ ያያቸው ሰው ሁሉ አድናቆቱን ሳይቸራቸው እንደማያልፍ፣ የኳኮሜዲ ይዘት ባላቸውም ፈገግ ሳይል እንደማይጨርስ እርግጠኛ ነኝ።
እስቲ ለማንኛውም አረፍ እንበል። እና በፊልሞቻችን ዘና እያልን መንፈሳችንን እናዝናና። እንደነቅ። እና ራሳችንን በሌሎች ተሞክሮ እናበልፅግ።
መልካም የዕረፍት ቀናት ለሁላችን በያለንበት ይሆንልን ዘንድ ተመኘሁ። ፊልሞቹ እነዚሁና፦
1) A Beautiful Mind (2001)
2) A Fortunate Man (2018)
3) A Thin Red Line (2014)
4) Cold Mountain (2003)
5) Darkest Hour (2017)
6) Defiance (2008)
7) Emperor (2012)
8) First They Killed My Father (2017)
9) Free State of Jones (2016)
10) Glory (1989)
11) Green Book (2018)
12) In Love and War (1996)
13) In the Land of Blood and Honey (2011)
14) Léon: the Professional (1994)
15) La Borena (ላ ቦረና) (2013)
16) Lucy (2014)
17) Milada (2017)
18) Mission of Honor (2018)
19) Mosul (2020)
20) No Direction Home: Bob Dylan (2005)
21) Official Secrets (2019)
22) On the Basis of Sex (2018)
23) On the Road to Berlin (2015)
24) Rebuni (ረቡኒ) (2014)
25) Riphagen the Untouchable (2016)
26) Road Trip (2000)
27) Schindler's List (1993)
28) Second in Command (2006)
29) Selma (2015)
30) The Angel (2018)
31) The Aviator (2004)
32) The Butler (2013)
33) The Devil's Mistress (2016)
34) The Dig (2021)
35) The Exception (2016)
36) The Great Debaters (2007)
37) The Green Mile (1999)
38) The Guernsey Literary & Potato Peel Pie Society (2018)
39) The Notebook (2004)
40) The Photographer of Mauthausen (2018)
41) The Railway Man (2013)
42) The Theory of Everything (2014)
43) The Two Popes (2019)
44) The Wolf's Call (2019)
45) The Zookeeper's Wife (2017)
46) Wonder (2017)
47) Yearbegnaw Lij (የአርበኛው ልጅ) (2015)
48) You Don't Mess with the Zohan (2008)
49) 12 Years a Slave (2013)
50) 22 July (2018)
ሸጋ ቅዳሚት!💛

ሰብዓዊነት የገዘፈበት የፍትህ ኮከብ!💛
ምንም እንኳን የአርጀንቲናዊ ተወላጅ ቢሆንም እሱ ለኔ ሐገር አልባ የዓለም ነው። እሱ ብዙ ነው ፊዚስት፣ፀሀፊ፣አስተማሪ፣ዲፕሎማት፣
የጦርሀይል አዛዥ እና የመብት ተሟጋች ነው ። ይህ ሰው ማነው ስመ ገናናው ዓለማቀፋዊው የነጻነት ፋኖ ተዋጊ .....ኤርኔስቶ ቼ ጉቬራ
ያላደለው በቀበሌ ፤ በወረዳ ፤በብሄር ፤በሃይማኖት ተሰባጣጥሮ በጎጥ ተተብትቦ ይጣመዳል ይቧቀሳል የኔ ጀግና ኤርኔስቶ ቼ ጉቬራ ለዘመዶቹ ለሰው ልጆች ዘብ ይቆማል ይህ ሰው ቅዱስ ነው።ቅድስና ማለት ህይወትቱን ሙሉ ለሰው ልጆች ነፃነት መታገል ብሎም አንድያ ነፍሱን መገበር አይደለምን ?ካለምንም ስስት ማንነትን ዘርን ሳይቆጥር ሰው መሆን ክብር ነው ብሎ ለሰው ልጆች ነፃነትን ሊለግስ አቅም አልባዎችን አለሁላቹ እሚል ለኔ ይህ አለማቀፍ የነፃነት አርበኛ ቅዱሴ ነው።
ዓለም ህዝቦቿ ሁሉም ሰዎች በእኩልነት እና በሰላም ይኖሩ ዘንድ ለማየት ተመኘ
ህልሙንም እውን ለማድረግ ጣረ ይህ ክንፍ አልባ በምድር የተመላለሰ መልአክ ነው።
እውነተኛ ኮሚኒስት ነው ኮሚንዝም የአለም ማህበረሰብን ወደፊት እሚያስጉዝ እና አዲስ
ማህበረሰብን ለመፍጠር ያስችላል ብሎ ለሰው ልጆች እኩልነት ለማምጣት ከጨቋኞች ጋ ታገለ ማን ?....ዶክተር ኤርኔስቶ ቼ ጉቬራ የአለም ሰዎች በሰላም የመኖር እና ያለመኖር እጣ ፈንታ በልእለ ሃያል አገሮች መውደቅ ፍትሃዊነት የገደለው ነው ያለው ኤርኔስቶ ቼ ጉቬራ ወደ ሰሜን አፍሪካ አቀና በአልጄርያ እርእሰ ከተማ በአልጀርስ ንግግር አደረገ ቋንቋው ሁሉ ጭቆና ፤ ግፍ ፤በደል ይቁም ነው ።
ይህ ፍትሃዊ የፍትህ ተወርዋሪ ኮኮብ
በምድር እነሆ ላይፈዝ በሰው ልቦች ደሞቆ እና ህያው ሆኖ አልፏል።
# ስለአለማቀፍ ! ስለ ሰውነት ጥግ ሳስብ አእምሮዬን ላይ ድቅን የሚልበኝ አንድ ሰው
ነው. ....Che Guevara ገፁ ሰውነትን የሚያገዝፍልኝ አርማ ነው!!! አለማቀፋዊነት ዜማ የሚያቀነቅን ሰንደቄ አድራጓቱ ከመረዳት አቅም በላይ ጥልቅ የሰውነት ትርጉምን ተሸክሞል።
ህልመኛም ጭምር ነው 1956 ስምንት ሆነው ከሜክሲኮ ተነስተው የገዜው አንባገነኑን
የባቲስታ መንግሥት ለመገልበጥ ወደ ኩባ አቀኑ ለስምንት በኩባ ጫካዎችም የጉሬላ ውጊያ ጀመሩ አምባገነኑ የባቲስታ መንግሥት የመጣል ትግሉም ቼ ወሳኝ ሚና ተጫውቶ በድል
ተጠናቀቀ።
ይህ ጀግናዬ ማለም ብቻ ሳይሆን መተግበርም ይችልበታል።በተተኪው የካስትሮ አስተዳደርም የካስትሮ ቀኝ እጅ ሆኖ እስከ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴርነት ድረስ ላልወለደው የኩባ ህዝብ አገለገለ።ምከንያት እሱ ዘመዶቹ የሰው ልጆች ናቸውና ።ቼኮ ከጨቋኝ ሃያላን ጋ ሲታገል ከተጨቆኝ ጋ ሲያብር ኖሯል የእውነት!!እንደምን ሰው ከተሸናፊ ጋር በፍቅር ይወድቃል ??
ቼ!! መለክያው እኩልነት ነበር ተጨቆኝና ጨቆኝ የሌለበት ምድር ለመፍጠር ።
ዛሬ የERNESTO CHE GUEVERA መፅሀፍ በአሜሪካ ሳይቀር በአለም መፅሀፍት ቤቶች
ይገኛል የቼ ምስል ያረፈበት ሰአቶችን ቲሸርቶች በሺዎች ይቸበቸባሉ የላቲን አሜሪካ ተማሪዎች ጠዋት ጠዋት እንደ ብሄራዊ መዝሙር ቼ እንወድሀለን ቼ አንተን እንወርስሀለን
እያሉ ያዜማሉ።
ቼ የፍትህ ተወርዋሪ ኮኮብ ነው !!❤️
ልክ የዛሬ 55 አመት! በዛሬው ቀን የፍትህ ቀንዲል፤ የጭቁኖች አባት፤ የአርነት አርማ ቼ! ወደቀ።
ለገንዘብ በተገዙ ሴረኞች፤ ነፃነትን በጥቅም በሸጡ መደዴዎች፤ በደል በእጃቸው በተነባበረ ወለፈንዲዎች ቼ ከሞተ ድፍን 55 አመት።
ቼ ሰው ነበር! የሰውነት ውሀ ልክ ነበር። ከራስ ይልቅ ለሰው መኖርን፤ መስዋዕትነትን እና ፍቅርን አስተምሯል!
°°
Your eternal flame
Has shown us the light of dawn
[ማሪያ ማኬባ - አሉታ ኮንቲኒዋ]
°°
You can kill a revolutionary but you can't kill the revolution.
Aluta Continua ✊✊
°°
55th anvarsary day of the heroic Guerrilla.
Che ♡

💡ዛሬ ከእንቅልፋችን ስንነሳ ብዙም አልተደነቅንም ነገር ግን እንዳሸለቡ በዛው የቀሩም አሉ !
💎ዛሬ ከዋልንበት በሰላም ወደቤታችን ስንገባ ብዙም አልተደነቅንም ነገር ግን እንደወጡ በዛው የቀሩም አሉ ! ዛሬ ሳናዝን መዋላችን ምንም አልደነቅንም ነገር ግን ሌሎች የሚወዱትን አጥተው ያዘኑ አሉ
💡እንደው ህይወታችንን ለደቂቃ ብናስተውል ከምንማረርባቸው ነገሮች ይልቅ ልናመሰግንባቸውየሚገባን ብዙ መልካም ነገሮች አሉ። ፤
💎ከጎደለን ነገር ይልቅ ያለንን እንይ። በሰላም ውሎ በሰላም ማደር እጅግ ትልቅ ነገር ነው። ነግቶ ለአዲስ ቀን መታጨት ደግሞ ትልቅ እድል ምክንያቱም አዲስ ቀን አዲስ ህይወት ነውና። ፤በአለም ላይ በየሰአቱ ለአዲስ ቀን የማይታደሉ ሞልተዋል። :
💡እናም አዲስ ቀን እንድናይ ስለተፈቀደልን ብቻ ትልቅ ምስጋና ይገባል።አመስጋኝ ነፍስ በስጦታዎች ትሞላለችና ፣ ሁልም በፈጣሪህ ደስ ይበልህ!
ውብ አሁን!!🙏
@EthioHumanity
@EthioHumanity
✍ @EthioHumanityBot

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
💎በጣም አትጥበቅ በጣምም አትላላ
🔆" ማጥበቅም ሆነ ማላላት ትርጉም የለውም! አስተውል በእጅህ የያዝከው የክር መሳርያ አለ ክሩን ካላላህው ስትነቀንቀው ወይም ክሩን ስትፈትገው ብትውልም የምትፈልገውን ሙዚቃ ማድመጥ አትችልም ክሩን በጣም ካጠበከውም ስታነዝረው ይበጠሳል እንጂ የምትፈልገውን ዜማ ላይሰጥህ ይችላል ።
💡የሰውም ልጅ ልክ እንደዚህ ነው የራሱን ህይወት ራሱ በሚጫወተው መሳርያ እራሱ በሚመርጠው ዜማ ይቃኘዋል ። በኋላ ቀር አመለካከቶች ከረገብክም ሆነ የኔ ብቻ ነው ትክክል በሚል ብሂል ከረር ብለህ ከጠበቅህ ፍፃሜህ ትርጉም አልባ ነው ።
📍እራስህ የያዝከው መሳርያ በአግባቡብ ከተወጠረ የምትመሰጥበትን ዜማ እንደሚሰጥህ ሁሉ ራስህ አጨዋወቱን ያበላሸህው ዜማ ደግሞ መልሶ አንተኑ ያደነቁርሃል ። በጣም አትጥበቅ በጣምም አትላላ።
ውብ ምሽትን ተመኘን!❤️