❤️ህይወትን የምናፈቅር መኖርን ስለተለማመድን ሳይሆን ማፍቀርን ስለተለማመድን ነው።
⚜በፍቅር ውስጥ ሁል ጊዜ ዕብደት አለ። በዕብደት ውስጥ ደግሞ ሁልጊዜ ምክንያት አለ።አንቺ ታላቅ ኮከብ! ፍንትው ብለሽ የምታበሪላቸው ባይኖሩ ደስታሽ ምኑ ላይ ነበር?
⚜መብረርን የሚማር ሰው መጀመሪያ መቆምን፣ ከዚያም መራመድን፣ ብሎም መሮጥንና ዛፍ መውጣትን እንዲሁም መደነስን መማር አለበት፣ አንድ ሰው ከ መብረር መብረር አይችልም!
🔆እውነትን መናገር - በጣም ጥቂት ሰወች ይችላሉ! ከነዚህ ከሚችሉት ግን የሚፈፅሙት የሉም`!
ደፋር፣ ደንታ የሌለው፣ ተሳዳቢ፣ ጸበኛ-- ጥበብ ከኛ እኒህን ትፈልጋለች፡ ሴት ናትና የምትወደውም ጦረኛን ብቻ ነው።
✨እራሱን የማያዝ መታዘዝ አለበት። ብዙወች እራሳቸውን ማዘዝ ይችላሉ፣ ነገር ግን ለራሳቸው ከመታዘዛቸው በፊት ብዙ ይጎላቸዋል!ማህበረሰብ ተኩላውን አላምዶ ውሻ አደረገ። የሰው ልጅ ከሁሉም በላይ ለማዳ እንስሳ ነው!
💎አንድ ትውፊት አጀማመሩ በሩቅ የዘመን ጭጋግ እየተሸፈነ ከሄደ፣ አመሰራረቱም እየተምታታ ከመጣ - በክብር እያደገ ይሄዳል። ክብሩ ከትውልድ ወደ ትውልድ እየጨመረ ይሄዳል። በመጨረሻ ትውፊት ቅዱስ ይሆንና በሰወች ዘንድ ድንቅ ይሆናል።
ሰው በንዴት አይገልም፣ በሳቅ እንጂ።
✨በቁመና ለማደግ፣ ወደብርሃንም ለመጠጋት በተፈለገ ጊዜ፣ ስርን ወደ መሬት መላክ ያስፈልጋል፣ ወደ ድቅድቅ ጨለማው፣ ወደ ጥልቁ - ወደ መጥፎው።
💡"የታላላቆቹ ተራሮች አመጣት ከየት ይሆን?" ብየ ጠይቄ። ከባህር እንደመጡ ደረስኩበት፣ ማስረጃውም በአለቶቻቸውና በከፍተኛ ገጽታቸው ተጽፎ ይገኛል። ታላላቅ ከፍታወች የሚመጡት
ከታላላቅ ጥልቀቶች ነው።
💎ነጻ ከምን? ለዞራስተር ደንታ ይሰጠው ይመስል! ይልቁኑ ብሩህ አይኖችህ እንዲህ ይበሉ፡ ነጻ ምን ለማድረግ፣ሳንደንስበት ያለፈን ቀን እንደጠፋ ቀን መቁጥር ይገባል። እንዲሁ በሳቅ ያልታጀበን እውነት ውሸት ማለት ይገባል።
መተኛት ቀላል ጥበብ አይደለም፡ ለዚህ ሲባል ቀኑን ሙሉ መንቃት ግድ ይላል።
✍ዛራቱስራ
ውብ ምሽትን ተመኘን!❤️
@Ethiohumanity

💎አንድ ቤተሰብ ውስጥ አባት ከሞተ በኋላ የሚመገቡት እስኪያሳስባቸው ድረስ ይቸገራሉ።
💡አንድ ጌጣጌጥ መሸጫ ሱቅ ያለው ዘመድ አላቸው እና እናትየው ለልጇ ያላትን ለረጅም ጊዜ የተቀመጠ የአንገት እና የጣት ዳይመንድ ጌጥ ሰጥታው እዛ ሱቅ ሄዶ እንዲሸጠው ትሰጠዋለች፡፡
💎ልጁ የተባለው የዘመድ ጌጣ ጌጥ ሱቅ ሄዶ እናቱ እንደላከችው አስረድቶ እንዲገዛው ይጠይቃል፡፡ሰውየውም ከመረመረው በኋላ
"አሁን ገበያው ወድቋል ትንሽ ግዜ ጠብቀን በጥሩ ዋጋ እንሸጠዋለን፡፡"
💎ብሎ ይመልስለትና የተወሰነ ገንዘብ ከሰጠው በኋላ ለልጁም እስከዛው በየጊዜው እየመጣ እዛው ሱቅ ስራ እንዲሰራ ያደርጋል።
ልጁ በየግዜው እየሄደ የጌጣጌጥአሰራር ጥበብ ተካነ፡፡ የገበያም እውቀት አካበተ በስራውም ታዋቂም ለመሆን ቻለ፡፡
ይሄኔ ባለሱቁ
💡 "የሆነ ግዜ ልትሸጠው አምጠተኸው የነበረውን ጌጥ አሁን አምጣው አሁን ገበያው ጣራ ነክቷል እና ታተርፋላችሁ ፡፡"
ብሎ ይልከዋል፡፡ልጁ እንደተባለው እቤት ሄዶ ጌጣጌጡን በአይኑ በማየት ብቻ አርቴፊሻል ሆኖ ያገኘዋል፡፡
ወደ ሱቅ ይመለሳል፡፡ባለቤቱ ይጠይቃል
💎 "ዳይመንዱስ ?" ልጁም "አርቴፊሻል ነው ግን እያወክ ያን ጊዜ ለምን አልገርከኝም? አሁንስ ለምን ላከኝ?ሲል ጠየቀው፡፡ዘመዱም "ያን ጊዜ ለረጅም ዘመን ዳይመንድ ነው ብላችሁ ያመናችሁትን ነበር ይዘህ የመጣኸው፡፡ያለምንም እውቀት፤ ባዶህን እና በሙሉ እምነት ብቻ ! በሰዓቱ ባለህበት ሁኔታ ልክ ያልሆነ ነገር ለማስረዳት ይከብዳል፡፡ ምናልባት ላታምኑኝ ትችሉ ነበር ፡፡ምናልባትም ባለመግባባት የሚፈጠሩ የቃላት ልውውጥ አሁን ላይ መጥፎ ስሜት ሊያሳድርብን በቻለ ነበር ።" ብሎ በትህትና መለሰለት፡፡
እንዲህ ያለ የላቀ ስብዕና ባለቤትና ነገሮችን በብዙ አቅጣጫ የምናይበት ህሊና ይስጠን፡፡

❤️In the present time of darkness and disarray, we need communities that will be a guiding force of light.
💛In a landscape of war, climate change, and social atrocities, we need to see values that support our shared humanity. we need to hold onto the threads that connect us and walk together back into the light of love. We need communities to share experience from different part of the world.
💜As our members requested we have created a world wide group on IRL, the fastest platform to build communities online.
❤️We would be delighted to have you become part of our revolutionary movement . We look forward to welcoming you as a new member. Click on the group link below to join humanity Awakening on IRL.👇
https://go.irl.com/0KSM?g=zWLOSXFy&k=rLOhWS3j-zWLOSXFy

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
💡ሁሌም ቢሆን ጥቁር ብቻ መስሎ ከሚታይህ ቀን ጀርባ የታዘለ ደማቅ ብርሃን አለ፣ ሊገፈትሩህ ከበረቱ እልፍ ክንዶች ኋላ ሊያቀኑህ የቆሙ ልስልስ መዳፎች አሉ፣ አንሸራትተው ከሚደፉህ ሃሳቦች ባሻገር በተስፋ ሞልተው የሚያቆሙህ ቅን ሀሳቦች ተሰልፈዋል።
💎 ያላየኸው ነገ ብዙ አዲስ የህይወት ገፆችን ይዞ ይጠብቅሃል ካጎነበስክበት ቀና ትላለህ ሀዘንህ በሳቅ ይተካል፣ ጉስቁልናህን ወዝ ይሽረዋል፣ ይህ እንዲሆን ግን ነገን ጠብቀው ፦ ተስፋ አትቁረጥ ነገ ያንተ ሲሆን ብቻ አሸናፊ ነህ::
ውብ አሁንን ተመኘን!❤️

🛑ጎማ መቀየር እየቻልክ መኪናህን አትጣል!!
💎የመኪናህ ጎማ ተንፍሶ አላስኬድ ቢልህ ጎማውን ትቀይራለህ እንጂ መኪና አትጥለውም፡፡ ወዳጄ ይህቺ አለም ትልቅ ዳመራ ናት አንተ በዳመራው ስር ያለህ አንድ ችቦ ነህ አንተ ስትጠፋ የዳመራው ብርሀን ይቀንሳል፡፡ የቻልከውን ያህል ብራ አንተ ከነገሮች በላይ ነህ፡፡ በነገሮች አትረበሽ፡፡ አየህ አንፖል ተቃጠለ ተብሎ ቤት አይቀየርም፡፡ አንፖል ተቃጥሏል ብሎ ቤት የሚቀይር ሞኝ ነው፡፡ አንተም አንዱ የህይወቴ ጉዳይ አልተሳካም ብለህ ራስህን አታጥፋ፡፡ ይልቅስ አምፖልህን ቀይር ችግርህን ተጋፈጠው፡፡
💡 ያሰብከው ካልተሳካ ሀሳብህን ቀይር እንጂ ህይወትህን አታጥፋ፡፡ ፍቅርህ መሀል ችግር ቢፈጠር ፍቅርህን ጠግን እንጂ ቤትህን ትተህ አትሒድ፡፡ ህይወት ሁሌም ሙሉ አትሆንም፡፡ የጎደለህን እየሞላህ ቀጥል፡፡ በፍፁም አትሸነፍ አለምን እልህ የተጋባ ነው የሚጥላት ህይወት የስኬት ገበያ ናት በብልጠት ተገበያይ፡፡
💎ካህሊል ጅብራል እንዲህ ይላል ህይወት ልክ እንደ ክራር ጨዋታ ነው፡፡ አጨዋወቱን ያወቀ ጥሩ ሙዚቃ ይሰማል ያላወቀ ደግሞ ዝብርቅርቅ ጩኸቷን ለመስማት ይገደዳል፡፡ አሁንም እልሀለው ህይወት በደመነፍስ አትሄድም ስልቷን እወቀው፡፡ በህይወትህ ትላንት ያለፈውን መጥፎ ታሪክህን መቀየር ማስተካከል መሰረዝ አትችልም፡፡ የምትችለው አምኖ መቀበልና ለተሻለ ነገ መስራት ብቻ ነው፡፡
💡 "መቀየር የማንችለውን ነገር መቀበል ማለት ተስፋ መቁረጥ ማለት ሳይሆን አቅማችንን የምንችለው ነገር ላይ ማዋል ማለት ነው:: በፍፁም ተስፋ አትቁረጥ ግን አቅምህን የምትችለው ነገር ላይ አውለው።
✍ አቤል ብርሀኑ
ውብ አሁን ❤️
@ETHIOHUMANITY @ETHIOHUMANITY
✍ የተሰማችሁን አድርሱን @ETHIOHUMANITYBOT

ሰውመሆን ይስማው እና ስዩም ተፈራ
******
አጋጣሚ ሆኖ ሁለቱም ዳይሬክተሮች ናቸው ። ሶሚክ የፊልም እና ቴሌቪዥን ድራማ ፣ ስዩሜ ደግሞ የመድረክ ትያትሮች ። ስዩሜ የዛሬ 25 ዓመት ገደማ ለጥቂት የወቅቱ ወጣት ጥበብ ፈላጊዎች የነገረንና ሶሚክ ከደቂቃዎች በፊት ( ተደግሞ ) አርሂቡ ላይ ሲናገር የሰማሁት መሰረተ ሀሳባቸው አንድ አይነት ቃላት ገረሙኝ ። የስዩሜ ንግግር ቆይቷል ፤ ሶሚክ ደግሞ ስዩምን የመስማት እድል የለውም ። የሁለቱ ዳይሬክተሮች በሰው አይተኬነት ጉዳይ ላይ የተናገሩት ማስገረም ብቻ ሳይሆን መሰረታዊ ሆነው አገኘኋቸው ።
ስዩም ተፈራ
*****
" ተዋናይ ስትሆኑ በቀላሉ የምትተኩ አትሁኑ ። እናንተ ስትቀሩ ' እሱ ከቀረማ እንበተን እንጂ ማን ተክቶት ይሰራል ? ' ማስባል አለባችሁ ። ስትቁ በቀላሉ ' ና እገሌ ውጣና ተጫወተው ' ከተባለባችሁ ያን ያህል አስፈላጊ አልነበራችሁም ማለት ነው ። "
ሰውመሆን ይስማው
****
" በቀላሉ የምትተኩ አትሁኑ ። ስትሄዱ ሌላ ሰው የሚመጣባችሁ ከሆነ ዋጋ የላችሁም ። የማታጎድል ሰው አትሁን ። ስትሄድ ' ይሄ ሰው ሄደ ። በማን እንተካው ? ' ተብሎ ራስምታት መፈጠር አለበት ። ' ምን እናድርግ ? ' ተብሎ ሰው መወያየት አለበት ። "
🔥ባላችሁበት የስራ ዘርፍ ላይ ውጤታማ ሁኑ!

📍ቱንቢ
🟢ፈጣሪ ከተማን በቱንቢ ይለካል ፤ ቤቶችንና ቤተመቅደሶችን ሲመሰርትም ቱንቢን ይጠቀማል።ይህ አገላለጥ ግን ዘይቤአዊ/ሜታፎሪካል/ ነው። ቤት ማለት የሰው ህይወት ማለት ነው ፤ የምናፈራው ንብረት በቀጥታ ከስብዕናችን ጋር የተያያዘ ነው ።
🟡በመሆኑም የምንሰራው ቤት በእውነት የደከምንበትና በላባችን የተገኘን ሃብት ነው ወይስ በዝርፊያ? ፤ በህጋዊ መንገድ የሰበሰብነውው ወይስ በቅሚያ ያፈራነው ነው? በቅንነት እና በጽድቅ ወይስ በመርገምና በክፋት? የምንገነባው ከተማስ በደም የተገነባ ነው ወይስ በፍትህ? ሁሉም በቱንቢው ይመዘናል ፤ ይለካል። የገነባነው ከተማም ሆነ የምንኖርበት ቤት የሰዎች ደምና እንባ የተቀላቀለበት ከሆነ ባለ ዕዳዎች ነንና ከፊት ለፊት የምንከፍለው ዋጋ አለ ማለት ነው።
🔴ከዚህ እውነት ስንነሳ የእያንዳንዳችን ማንነትስ የተገነባው እንዴት ነው? ከቤተሰብ ፣ ከማህበረሰብ ፣ ከትምህርት ቤትና ከህይወት ልምዳችን ምን ወሰድን? በምን ተሞላን? ከወሰድናቸው ስንቆች ምን ተጠቀምን? ማህበረሰቡንስ ምን ጠቀምንበት? ይህንን ስራችንኑ ስራችንን የሚገመግም ፤ እጅግ የረቀቀ እና ለስጋ ዓይን የማይታይ መለኮታዊ ቱንቢ በእያንዳንዳችን አናት ላይ እንደተንጠለጠለ ልናስተውል ይገባል።
📖ምንጭ፦ በነጋ አባተ የተፃፈው
የቶጳዝዮን አሮኖች
ውብ ቅዳሜ ❤️

❤️ጥላቻን ለማወጅ አደባባይ መውጣት እንዴት ይቀፋል?... በቆሸሽኩበት ጭቃ ቆሽሹ ለማለት ይፋ መውጣት እንደምን ያስቀይማል? ማጠልሸትን ስራ አድርጎ ሰርክ ለክፋት መትጋት እንደምን እረፍት ይሰጣል?
💙ጥላቻ የነፍስ ዕድፍ ነው... በጊዜ ካልታጠቡት ያከረፋል... ጠይው በጥላቻው ሰበብ መቆሸሹን ፈጥኖ ስለማይረዳ ያንኑ ቆሻሻውን እንደ ደህና ነገር እዩልኝ ብሎ አደባባይ ይወጣል... የጥላቻህ ቁሸት ባስፎከተህ ቁጥር አውጫጭኝ መጥራት ደግሞ የጠላኸው ነገር የነሳህን ምቾት ሌሎችም ይጡት ያስመስላል... ወይም ሌላው በመውደድ አጽድቆ የተቀበለውን ጣሉልኝ ብሎ የመጫን ክፋት.
💚ጥላቻህን እራስህ ዘንድ አቆየው ወዳጄ... ፍቅርህን ለመጋራት ካልሆነ በቀር አንደበትህን አታላቅ... ብዙ የምታጋራው ፍቅር ከእልፍኝህ አለ... ሳትጎድል የምትሞላበትን በረከት መስጠት እየቻልክ ቆሽሸህ የምታጠለሽበትን ጥላት ይዘህ ለምን ትዞራለህ?... ፍቅርን ዝራ ፍቅር ታጭዳለህ. ጥላቻ ብትዘራ መልሰህ ትነዳለህ.
💛ራስህን ወክለህ ቁም..በዙሪያህ ያሉ 'መስማት ይፈልጉ ይሆናል' የምትለውን ከንቱነት ሳይሆን ልብህ የምትፈቅደውን ውበት ንገረኝ... ነፃ ውጣ ጎበዝ... ራስህን identify ባደረግህበት ከንቱ ስብስብ መንጋ እሳቤ ታጥረህ የፍቅር ጸሐይህ ሳትዋብባት እንዳትጠልቅብህ ንቃ... ከፍቅር በላይ የምትቆምለት አንዳችም እውነት የለምና.
❤️ቋንቋህን አለመስማቴ ሳያግደኝ.. ቋንቋዬን አለማወቅህ ሳያነቅፍህ ከአንድ ገበታ የተቀመጥነው በፍቅር ቃል አውርተን ነው. የአለማችን ቋንቋ ፍቅር ነውና!
✍ ደምስ ሰይፉ
ውብ ጊዜ ❤️
@EthioHumanity
@EthioHumanity
✍ለማንኛውም ሀሳብ ወይም
አስተያየት በዚህ አግኙን @ETHIOHUMANITYBOT

Sex tape
.
ትርጉም😁
[ራስን እየቀረጹ ወሲብ ማድረግ]
.
.
📽 ካሜሮን ዲአዝ የምትሰራበት 2007 e.c የወጣ የomedy ዘውግ ያለው ፊልም ነው።
.
.
🎞 ፍቅረኛማቾቹ ባገኙት ቦታ ሁሉ መለጣለጥ ይወዳሉ። ለሻይ እረፍት ሲወጡ ሽንት ቤት... መናፈሻ ውስጥ እላዩ ላይ አረፍ ያለች መስላ...በር ሳይዘጉ በኮሪደር ላይ የሚያልፍ ላጤ ሳያሰጋቸው በፍቅር ይለጣለጣሉ!
" ስለምደክልሽ ወድሻለሁ" ሲላት
" ስለምወድህ እደከልልሀለሁ" ትለዋለች።
ፊልሙን የሚተረከው በሷ("cameron) በኩል ነው። ሒወቷን የራሷ ብሎግ ላይ ስታሰፍረው ለኛ ድምጽ እና ምስል ሆኖ ይደርሳል። የወሲብ ሒወቷን እንደ ወረደ ስለምትጽፈው ብዙ ሰው ይወድላታል። የፍቅረኛዬ ብልት ከሱ በላይ ያውቀኛል ትላለች። ላይብረሪ ውስጥ እያነበበ ሲቆምበት ዞር ዞር ብሎ ሲያጣት ስሟን ይጠራል። "andy" ሲል ከሼልፉ ጀርባ ትወጣለች። ከጀርባ ይናፋሉ። በንቅናቄአቸው ከሼልፉ ላይ መጸሀፍት ይዘንባል። ይሔ የደስታ ካፊያ ሳያባራ ቀድመው ዝናብ ሆኖ እንዲወርድ ለመጋባት ይወስናሉ።
ውሳኔውን ለሷ ቤተሰቦች ሲያማክሩ...
እናት:- "ምምምምምን ምን! ምን! ማለት? አአአ ማለቴ? እእእ? ምነው ማለቴ ቸኮላቹ! ወጣት ናቹ! ትንሽ አዘግይታችሁት ነገ ምን እንደያዘ ማወቅ አትፈልጉም?"
ሁለቱም እንደሚዋደዱ እና በውሳኔአቸው እርግጠኛ እንደሆኑ ሲናገሩ አባትየው ጽዋውን ከፍ አድርጎ
" ብድ ደህና ሰንብት"
ይላል። እናት በፊቷ "ከወሰኑ በሗላ አይነገርም! በራሳቸው ይድረሱበት" አይነት ምልክት ታሳየዋለች።
.
.
💧
researchers say their findings are clear, that “the longer a couple waited to become sexually involved, the better that sexual quality15%, relationship communication, relationship satisfaction20% and perceived relationship stability22% was in marriage ...”
by...
Bill Hendrick
.
ከላይ እንደተገለጸው ወሲብ በዘገየ ቁጥር ጤናማ የብድ ምጣኔአችን በ15 በመቶ ያድጋል። የመግባባት ምጣኔ 20 በመቶ ይመነደጋል። እርስ በእርስ የመተማመን መጠን 20 በመቶ ይጨምራል።
💧 በግሌ አንድ ነገር በጣም ካስገበገበኝ ወይም እንዳደርገው በብዙ ሰዎች ከተጀነጀንኩ ከማድረግ በመዘግየት ፈትነዋለሁ። ስፖርት ለመስራት ሰውነቴ አይስገበገብማ! ስራም የሚለኝ ሰው ጥቂት ነው! እንቃም የሚልስ ጨቅ! ሜዲቴት ለማድረግ፣ ለመጸለይ፣ ለማንበብ የሚያነሳሳኝ ማንም የለም። ስለዚህ የአንድን ጉዳይ ጤናማ መልእክት ለመለየት ጦም ጥሩ መፍትሔ ይመስለኛል። ድርጊቱን መጦም/ማዘግየት/ ሁለት ጥቅም ይኖረዋል።
🌒 1ኛ ስናደርገው የምናገኘው እርካታ በቆይታችን መጠን እየጨመረ ይመጣል!
🌘 2ኛ የድርጊቱ ትክክለኛ መልክ እየተገለጠ ይመጣና ባህሪያችን ለመወሰን የሚችልበት የጠራ መረጃ ያገኛል።
.
.
📽 ተጋቡ
የተፈራው ሆነ።
ወላጆቻቸው ስህተት እንደነበሩና ወሲብ ከትዳር በሗላም ተጧጡፎ እንደሚቀጥል ለማመን ጥረት አደረጉ። ከዛ ደከማቸው! ከዛ ረሱት! በተለይ ባልየው ጅል መሆን አመጣ። ወሲብ ያጣ ወንድ ይጀዝባል ነው? በዚያ ላይ ልጅ ተወለደ። የወንድየው የቀዘቀዘ የወሲብ ወስፋቱ ላይ የወለደ የማህጸኗን በር ማየት ተጨመረ። ዘጋው ዘጋው ዘጋው። ከእለታት አንድ ቀን ባለቤቱ ብሎጓን በውድ ልትሸጥ ተስማምታ በደስታ ወደ ቤት ትመጣለች። ልጆቿን ወደ ቤተሰቦቿ ልካ ስሜት ቀስቃሽ ልብስ ለብሳ ትጠብቀዋለች። ደስ ብሎት የለበሰችውን ጫማ ለማውለቅ ሲሞክር እዛው ይደክመዋል። እሱን ትቶት ላዩአ ላይ ይዘልና እየሳማት አይኑን ይገልጣል። እሷም ስትገልጥ እኩል ይሆናል። በጀርባቸው ተኝተው "እንዴት እንዲህ ይሆናል" ብለው ይወያያሉ። ብዙ ቦታ ሞከሩት...ሶፋ ላይ..ኪችን ፍሎር ላይ አልሆነም። ጭራሽ አልቆምልህ አለው።
.
💧 ክሽፈተ ወሲብ ይባላል ይሔ። በብዛት በወንዶች ላይ የሚከሰት ነው። አልቆምም ሲል😩 ክሽፈተ ይባልና ቶሎ ካስታወከ ደሞ ስንፈተ😩 ይባላል። ምንጭ የአሌክስ አብርሀም ዙቤይዳ መጸሀፍ "ቀስ ብሎ ይቆማል" ንኡስ ርዕስ። ከክሽፈተ ይልቅ ብዙ ወንድ ላይ የሚስተዋለው ስንፈተ ነው። የአዳም ረታ የትኛው መጸሀፍ እንደሆነ እንጃ "የዚህን ዘመን ወጣት አንገቱን ይዘን ብናወዛውዘው የዋጣቸው ቪያግራዎች እየተጋጩ እንደ ጽናጽል ይጮሀል" ይላል። ቶሎ የመተኛቱ አንዱ ምክንያት ብልት እና አይምሮ ተቃራኒ መስራታቸውን ካለመገንዘብ የመጣ ይመስለኛል። ጋሼ የሚቆመው በደም ነው ናላም የሚሰራው በደም። ስለዚህ አንዱን መምረጥ ብልሀት ነው። የሚበዳ አያስብ የማያስብም እንደዛው። ወሲብ እራሱ ግብ መሆኑን አውቆ መረጋጋትና ልክ እንደ ዳንስ ራስን መርሳት ያረጋጋል። ይሔም ቢሆን ከንቱ ነው።
ወሲብ የዚህች አለም የእርካታ ጥግ ነው። ቢሆንም ከመጨረስ በሗላ የሚከተለው ባዶነት ጎዶሎ ያደርገዋል። አምላክ ብቻ ነው ጣሪያ የሌለው እርካታና የዘላለም የሒወት ምንጭ!
.
.
📽 እሱ ሶፋ ላይ እሷ ጭኑ ላይ ቁጭ ብላ በትዕግስት ጠበቁ። ላጃው በጸሀይ እንደ በሰለ ቃሪያ መዘናፈሉን አልተወም። በቮድካ ሞከሩት! ማጥመቅ ሳይሆን እንደ ነዳጅ። (በነገሬ ላይ አፕሬቲቭ አሪፍ ነው ይላሉ ለክሽፈተም ለስንፈተም) ከሞቅታ አንድ ነገር ወሰኑ "በካሜራ ራሳችንን እየቀረጽን ብንባዳስ"። ተሳክቶላቸው ለሶስት ሰአት እያረፉ ተናፉ። Sex guide መጸሀፍ ላይ ያለውን ፖዚሽኖች በሙሉ ተገበሩ። ሴቷ ፋካንድ ተከልብጣ ስክት የምትልበት ፖዚሽን ሳይቀር ተሞከረ። ለሊት ላይ Andy በሰመመን ሆና "ቤብ ቪዲዮውን ከታብሌቱ መሰረዝ እንዳትረሳ" ትለዋለች። በነጋታው party ነበር። ባል አንዴ ካየ በሗላ ማጥፋት እምቢ ብሎት ቪዲዮዋን የሆነ ፍልደር ውስጥ ይሸውካታል። ጭፈራው አልቆ ማታ እቃ እያነሳሱ የእጅ ስልኩ ላይ መሴጅ ይገባል
" አሪፍ ቪዲዮ ነበር! ስላጋራኧን አመሰግናለሁ" የሚል
"ይቅርታ ተሳስተሀል! you tube የለኝም" ይመልሳል።
"አልተሳሳትኩም! አስታውስ"
"ምን ማነህ? የምን ቫዲዮ"
ቶሎ አልመልስ ይለዋል። ሚስቱ ትጠራዋለች። ልቡ ትመታለች።
" አንተ ደደብ! Ur sex tape"
ለካ ለሁሉም ታብሌታቸውን ሲመልስ ሙዚቃ ያለበትን ፎልደር ልኮላቸው ነበር። ፎልደሩ ውስጥ ነበር ያስቀመጠዉ።
.
.
💧 ከዚህ በሗላ ያለው የፊልሙ ክፍል ታብሌቶቹን ለመሰብሰብ የሚያደርጉት ሀሰሳ ነው። ያነፍራል። እግረ መንገዱን ወደ ልባችን የሚላክ መልእክት ግን አለ።
1. የporn ኢንዱስትሪው እድገት እና ከባህል እስርቤት እየወጣን እንደሆነ። porn መከለም Normal ነው የማለት አዝማሚያ። አንዱ የፖርን ኢንዱስሪ ባለቤት በቀን 1,000 amateur ጀማሪ sex tape እንደሚደርሳቸው ይናገራል። የፖርን ካምፓኒ በስነምግባሩ የተመሰገነ ግዙፍ ሰው ነው በገጸ-በሀሪነት ሆኖ ተስሏል። በሩን በመኪናቸው ገንጥለውበትንኳ በነጻ የሚልክ። ባለትዳር የሆነ! ባለቤቱም Sex tape የሰሩትን ባለትዳሮች ልጆች በፍቅር የምትንከባከብ ናት። ካልተጠነቀቅን የምታጠምደን ውክልና ይቺ ናት። መጥፎ የሚባሉ ድርጊቶችን በባለቤትነት የሚያስተዳድሩ ሰዎችን በምናከብራቸው አልባሳት ስነምግባሮች በማስጌጥ የሚሰማንን ስሜት የግላችን ብቻ የማድረግ አዝማሚያ በብዙ የሆሊውድ ፊልሞች ይስተዋላል። ቡሽቲዎችን አዛኝ እና noble ማስመሰል። ይሔን የሚቃወሙ ሰዎች Dogmatic እና ሀሜተኛ ማስመሰል

Hollywood ገብቷል። ገለልተኛ ተመልካች በመሆን መዳን ይቻላል?።
.
2. የ porn site ጥቆማ። ይሔን በኛ ፊልም ላይም ተስተውሎ አይቼ አቃለሁ። የኢትዮጵያን ፊልም እንደ አውሬ ከሚሸሹት ብሆንም አንድ ቀን ጓረቤት በጨረፍታ አየሁ። አለምዘውድ ቢሮው ውስጥ በዴስክቶፕ ፖርን ሲያይ አለቃው ይደርስበትና ይደነባበራል። አለቃው አረጋግቶት መልሶ እንዲከፍት ያዘዋል! አይቶት ይቆጣዋል ብለን ስንጠብቅ ቢሮ ወስዶ ሊንኩን ጻፍልኝ ሲለው Brot...ብሎ እስከ መጨረሻው ሲጽፍለት ይታያል። በጣም በሸቅኩ Ebs cinema ላይ ነው ማተላለፈው። ሪሞት የሚይዝ የ9 አመት ጩጬ ወንድም አለኝ በዚህ ሰአት ቤት ሰው ባይኖር አለቃው ፊት ላይ ያየውን ደስታ ፈልጎ ታብሌቱ ላይ ቢጽፈውሰ። Wifi እንደ ሳተላይት ዲሽ በየቤቱ መግባት ጀምሯል።
Premium membership ካልጠየቅን ፖርን ነጻ ነው።
But "If u don't pay the product you are ghe product" ይባላል። "ለገዛኧው ቁስ ካላስከፈሉህ የተሸጠው ቁስ አንተ ነህ ማለት ነው" ነገር ነው።
በዚህ ውስጥ ለአመታት ሲንቧች እንደከረመ መውጣትም አቅቶት እንደነበረ Addicted ሰው ነው የማወራው። ይሔን ስፖንሰር የሚያደርጉ የአገር ውስጥ ተቋማትም ገጥመውኛል። ቤቲንግ ድርጅቶች። ስሙን አልጠቅሰውም እንጂ የአንዱ ቤቲንግ ቅርንጫፍ ደጄ አካባቢ ነው። ከረጨን በሗላ ተስፋ መቁረጥ ስለሚቀበለን ተስፋ የሚሰጠን እንሻለን። እዛውጋ ተስፋ የሚቸረችር ድርጅት እነሆኝ ይላል። እንደገና የመኖር ሞራላችን ይታደሳል! አረፍ ብለን እንመለሳለን።
.
ለማንኛውም ፈታ በሉበት። በሌላ መጣለሁ!
📝በሀይሉ ሙሉጌታ
@Ethiohumanity
@Ethiohumanity
@Nagayta

⏱Take time!!
“Give me six hours to chop down a tree and I will spend the first four sharpening the axe.” ― Abraham Lincoln
🔷እየሄዱ መቆም የመሄድን አቅም መጨመር ነው… መዘግየት አይደለም… እያረፉ መጓዝ የብልህነት ከፍታ ነው … ስንፍና አይደለም… ‘በየመሃሉ’ ማለት መታደስ ነው… ኋላ መቅረት አይደለም… ለረጅም ሰዓት ያሽከረከረ ሹፌር ጥጉን ይዞ ‘እረፍት’ የሚወስደው የበለጠ መጓዝ እንዲችል ነው… የጋለው ሞተር ቀዝቅዞ አቅም መግዛት አለበት… የዛለ ክንዱም በርትቶ መሪ ማዞር አለበት… በየሰከንዱ በምንስበው አየር የመታደስ ያህል ነው – ‘በየመሃሉ’ ማለት… አንዴ በሳቡት አየር ዕድሜ ልክ ልኑር አይባልምና…
ሰውየው በአንድ ድርጅት ውስጥ በእንጨት ቆራጭነት ስራ አምስት ዓመት ያህል ቢያገለግልም ሁሌም የደመወዝ እድገት እንደናፈቀው ነው… ከእርሱ በኋላ የተቀጠሩ ሰራተኞች ዓመት ሳይደፍናቸው የክፍያ መሻሻል አይተዋል… እናም ሰውየው ዘወትር ‘ለምን?’ ይላል… የድርጅቱ ኃላፊ ‘እንደምታውቀው ድርጅታችን ውጤት ተኮር ነው… ብዙ የሰራ ብዙ ያገኛል… አንተን እንደማይህ የዛሬ አምስት ዓመት ትቆርጥ የነበረውን እንጨት ነው ዛሬም የምትቆርጠው… ይሄ ደግሞ ላንተ ለውጥም ሆነ ለድርጅቱ እድገት አንዳች አይፈይድም’ ብሎታል… እናም ይለፋል… ይጥራል… ይግራል… ጠብ የሚል ነገር የለም…
🔶በድጋሚ አለቃውን አግኝቶ ጠየቀ… ‘እስኪ ካንተ በኋላ የተቀጠሩትን ቆራጮች ተመልከታቸው… በየጊዜው መሻሻል እያሳዩ ነው… ለምን እነርሱን አታማክራቸውም… ለምሳሌ እከሌን ማናገር ትችላለህ… ምናልባት እኔና አንተ የማናውቀውን ምስጢር ይጠቁምህ ይሆናል’… ሲል መለሰለት…
🔹ሰውየው የተጠቆመው ሰው ዘንድ ሄዶ ችግሩን አስረዳው… ባለሙያውም ሁኔታውን በደንብ ካጤነ በኋላ ‘ለመሆኑ መጥረቢያህን ከሳልከው ስንት ጊዜ ሆነህ?’ ሲል ጠየቀው… እንጨት ቆራጩ እንደ ማሰላሰል አለ… በጣም ቆይቶ ነበር… በጣም… ባለሙያው አከለለት… ‘ይኸውልህ.. እኔ በየጊዜው የተወሰኑ የእንጨት ክምሮችን ከቆረጥኩ በኋላ መጥረቢያዬን እሞርዳለሁ… በዚህም ምክንያት ብዙ እንጨት መቁረጥ ችያለሁ’ አለው… ሰውየው ለረጅም ጊዜ የተደበቀበት የስኬት ምስጢር ለካ ‘በየመሃሉ’ ማለት ነው…
🔸ብዙዎቹ መጥረቢያዎቻችን ደንዘዋል… ችግሩ ዛሬም በትናንት አቅማቸው እንዲያገለግሉን እየጠበቅን ነው… ነጋ ጠባ በሚቆርጡት እንጨት ጥርሶቻቸው ተሸራርፎ አልቋል… ችርችፍ ብሏል… ዶልዱሟል…
🔺ላሞችህ ወተት እንዲሰጡህ የምትጠብቀው መመገብ እንዳለብህ ዘንግተህ ከሆነ ችግር አለ… የገባው ነው የሚወጣው .. መልኩን ከመቀየሩ ውጪ… የአገልግሎት ማሻሻያ ሳያደርግ ከፍተኛ ገቢ የሚጠብቅ ድርጅት… ሳያነብ ልጨኛ ጽሑፍ መፃፍ የሚፈልግ ‘ደራሲ’… በአግባቡ ሳያስተምር ጎበዝ ተማሪዎችን ማየት የሚናፍቅ መምህር… የድርሻውን ሳይወጣ ያደገች ሃገር ማየት የሚሻ ሕዝብ… የሚጠበቅበትን ሳያደርግ የሚጠበቅብህን የሚጠይቅ መንግስት… ለአርዓያነት ሳይበቃ ‘የተመረቀ ልጅ’ የሚጠብቅ ቤተሰብ… ሁሉም የደነዘ መጥረቢያቸውን አስተውለውት አያውቁም… የአንዳንዶቹ እንዲያውም ዝገት ጀምሮታል…
ከድግሪህ በኋላ ማንበብ ካቆምክ ድግሪህ እርባን የለውም… ዶክትሬትም ቢሆን… ከሽልማት በኋላ መስራት ካቆምክ መሸለምህ ከንቱ ነው… ቅዱስም ብትሆን… ዜኖች እንዲህ ይላሉ… “Before enlightenment, chop wood, carry water. After enlightenment, chop wood, carry water.”
🔸መጥረቢያህን ሳል… በመቁረጥ ላይ ብቻ እንደተመሰጥክ ያስታውቃል… ስትሞርድ ስለት ብቻ አይደለም የምትጨምረው… የሆነ የምታራግፈው ቆሻሻም አለ… ውጋጅ ነገር… አሮጌ አስተሳሰብ… ጠማማ ገጽታ… የተንሸዋረረ እይታ… ግድግዳ ኩራት…
ለመሞረድ የምታጠፋው ጊዜ የባከነ አይደለም… ነዳጅ እንደመጨመር ነው… የሆነ ጊዜ ድንገት ቀጥ ትላለህ… ምናልባት ያኔ ለመሞረድ ሁነኛ ጊዜህ አይሆን ይሆናል… እናም መቆሚያህ እንዳያጥር መቋቋሚያህን አጽና…
A woodsman once asked “what would you do if you had just five minutes to chop down a tree?’… He answered, ‘I would spend the first two & a half minutes sharpening my axe.”…
MORAL OF THE STORY
📍 Let us take a few minutes to sharpen our perspective.
✍ ደምስ ሰይፉ
ባላችሁበት ሰላም!!🙏

🌻ጌዜ በነፃ የምናገኘው ነገር ቢሆንም ጥቅሙ ግን በዋጋ አይተመንም ። ልንጠቀምበት እንጂ የግላችን ልናደርገው አንችልም ።
🌼ስራ ላይ ልናውለው እንጂ ይዘን ልናቆየው አንችልም አንዴ ካጠፋነው መልሰን አናገኘውም ። አዲሱ አመት ጊዜያችንን በአግባቡ በመጠቀም ያሰብነውን የምናሳካበት ይሁንልን፣
📍ዓለም ጸንታ የቆመችው ለሌሎች በሚደረግ መልካም ነገር ነው። የእኛ ሰብዓዊነት የሚወሠነው የሌሎችን ሰብዓዊነት ስንገነዘብ ነው፡፡ ሌሎችም እንደእኛ ሰው መሆናቸውን ከተረዳን እንረዳዳለን እንጂ አንገፋፋም፤ እንተቃቀፋለን እንጂ አንገፈታተርም፤ የሚያፈናቅሉ እጆች ተሠብሥበው የሚያቅፉ ይሆናሉ፡፡
🌻ጥላቻና ልዩነትን አስወግደን በአንድነትና በፍቅር ወደ ተሻለ እድገት የምንሸጋገርበት የተባረከ ዘመን ይሁንልን !
አሜን😇
"መልካም አዲስ አመት"💛
ከጎናችን በመሆን አጋርነታቹን እደምሰሶ ላፀናቹልን ቤተሰቦቻችን ልባዊ ምስጋናችን ይድረሳችሁ . !!🙏
📍የተሰማቹን አጋሩን!! ሃሳባችሁን እዚሁ ላይ ፃፍፍ አድርጉልን
👇👇
@Ethiohumanitybot @Ethiohumanitybot

☯መጠነኛ ችግር የምቾች ጨው ናት!
.
እምነት ያለ ፈተና፤ ጤንነት ያለ በሽታ፤ ሀብት ያለ ድህነት፤ ሠላም ያለ ጦርነት፤ ደስታ ያለ ሀዘን፤ ጥጋብ ያለ ርሃብ፤ ፍቅር ያለ ቅናት፤ እረፍት ያለ ድካም፤ ብርሀን ያለ ፅልመት ጣዕም የለውም። ችግርና ፈተና ያልገጠመው ህይወት ጨው አልባ የአልጫ ምግብ እንደ ማለት ነው። ሠው ሆነህ ችግር አትጥላ መከራም አትፍራ፤ የስጋ ምቾትህን ግን አጥብቀህ አትውደዳት ዘልአለማዊ ደስታህን በመቀማት ለውድቀት ትዳርግሃለች።
.
☮አስተውል! ህይወትህ መጠነኛ ተግዳሮት ካልገጠመው ሙሉ ደስተኛ አትሆንም። የችግርን መራራነት በተግባር ካልቀመስከው የምቾትን ጣዕም በፍፁም ልትረ'ዳው አትችልም። ችግርን በፍፁም አትፍራ ግን ደግሞ ችግርን በቀጠሮ ብዛት እንዳትላመዳት አብዝተህ ተጠንቀቅ፤ ችግር እንደ ጨው ለህይወትህ ማጣፈጫነት ተጠቀምባት እንጂ ለደም ግፊትህ ምክንያት ሆና እስክትገድልህ ድረስ አብዝተህ አትዘፈቅባት። ችግርና ማጣት ካልቀመስክ ባለህ ነገር ስለማትረካ ከልብ አታመሰግንም፤ ካላመሰገንክ ደግሞ የደስታ ፀጋ ይርቅሃል። እናም አመስጋኝ ሁን!
ውብ አሁን❤️
@Ethiohumanity
@Ethiohumanity
✍ የተሰማቹን አጋሩን @Ethiohumanitybot